Telegram Web Link
ግምታችሁን አስቀምጡ

እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
25.
ሲዳማ 0 -0 ፋሲል
ጎል ሲዳማ ቡና
ጎልልልልልልልልልል ፍሲል ከነማ

ቃልኪዳን ዘላለም
ጨዋታው ተጠናቀቀ🇦🇹🇦🇹🇦🇹

የሙሉ ሰአት ውጤት ፋሲል ከነማ 2-1ሲዳማ ቡና

ቃልኪዳን ዘላለም
አምሳሉ ጥላሁን



@FASILSC
በዛሬው ጨዋታ ቃልኪዳን ዘላለም የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተመርጧል


@FASILSC
ዛሬ 7 ሰዓት ወላይታ ዲቻ ከፋሲል ከነማ

ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም

እናሸንፍለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹



@FASILSC
አፄዎቹ ከ ጦና ንቦች

ዛሬ 7:00

ሀዋሳ ዮኒቨርስቲ ስታዲየም


@FASILSC
ተጫዋቾቻችን ወደ ሜዳ እየገቡ ነው
መልካም እድል እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
ጨዋታው ጀምሯል

ፋሲል ከነማ 0-0 ወላይታ ዲቻ
ጎል ተቆጥሮብናል 😕

እናሸንፋለን በፋሲል ሙሉ እምነት አለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
ወላይታ 2-1 ፋሲል
#ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ከበዛብህ መለዮ ጋር ተለያይቷል!

ክለባችን ፋሲል ከነማ ከመሐል አማካዩ በዛብህ መለዮ ጋር ውል ለማቋረጥ ስምምነት ላይ ደርሰዋል::

በ2010 ክረምት ላይ ከወላይታ ዲቻ አፄዎቹን የተቀላቀለዉ አማካዩ ላለፉት 6 ዓመታት ፋሲል ከነማን በብቃት ያገለገለ ሲሆን በተለይ አፄዎቹ በ2013 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ሲያነሱ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ካደረጉ ተጫዋቾች መካከል ይገኝበታል።

በዛብህ መለዮ ከክለባችን ፋሲል ከነማ ጋር እስከ ዓመቱ መጨረሻ የሚያቆየዉ የኮንትራት ዉል ቢኖረዉም ሁለቱ አካላት ባደረጉት ስምምነት ተጫዋቹ ዉሉን በማቋረጥ ሌላኛዉን የሊግ ክለብ ሲዳማ ቡናን ተቀላቅሏል::

በዛብህ ከክለባችን ጋር ለነበረህ ቆይታ በፋሲል ከነማ እና በደጋፊዎቻችን ስም ምስጋናችንን እያቀረብን መልካሙን ሁሉ እንመኝልሃለን::
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ።
በዛብህ መለዮ (በዜ )እናመሰግናለን
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
#ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ከታፈሰ ሰለሞን ጋር ተለያይቷል!

ክለባችን ፋሲል ከነማ ከመሐል ሜዳ ተጫዋቹ ታፈሰ ሰለሞን ጋር ውል ለማቋረጥ ስምምነት ላይ ደርሰዋል::

ባሳለፍነዉ ዓመት መጀመሪያ አፄዎቹን የተቀላቀለዉ አማካዩ የ2015 የዉድድር ዓመትን በአፄዎቹ ቤት ያሳለፈ ሲሆን በቆይታዉም ፋሲል ከነማን በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እና በ CAF የኮንፌደረሽን ጨዋታዎች ከመወከልም ባለፈ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከመሐል ሜዳ እየተነሳ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ታፈሰ ከክለባችን ፋሲል ከነማ ጋር እስከ ዓመቱ መጨረሻ የሚያቆየዉ የኮንትራት ዉል ቢኖረዉም ሁለቱ አካላት ባደረጉት ስምምነት የተጫዋቹ ዉል ሊቋረጥ ችሏል::

ታፈሰ ሰለሞን ከክለባችን ጋር ለነበረህ ቆይታ በፋሲል ከነማ እና በደጋፊዎቻችን ስም ምስጋናችንን እያቀረብን መልካሙን ሁሉ እንመኝልሃለን::
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ።

ታፈሰ ሰለሞን (ታፌ) ስለነበረን ጊዜያዊ እናመሰግናለን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
#ከድር ኩሊባሊ (ኩሊ ጎንደሬዉ) እናመሰግናለን !

ክለባችን ፋሲል ከነማን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በመሐል ተከላካይ እና በተከላካይ አማካይ ቦታ በቋሚነት ለረጅም ዓመታት ያገለገለዉ ኮትዲቯራዊዉ ተከላከይ ከድር ኩሊባሊ ከፋሲል ከነማ ጋር ያለዉ ዉል መጠናቀቁን ተከትሎ ከክለባችን ጋር ተለያይቷል።

በቅፅል ስሙ ኩሊ ጎንደሬዉ እየተባለ የሚጠራዉ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ፤ ሜዳ ላይ ያለዉን አቅም አሟጦ በመጫዎት እና በአልሸነፍ ባይነቱ በአፄዎቹ ደጋፊዎች በእጅጉ ይወደዳል። ከዚህም ባለፈ ተጫዋቹ ከክለባችን ጋር ባሳለፋቸዉ 5 የዉድድር አመታት በጣት ከሚቆጠሩት ዉጭ በበርካታ ጨዋታዎች ላይ በቋሚነት ማገልገል ችሏል።

ኩሊባሊ ፋሲል ከነማ ወደ ሊጉ ካደገ በኋላ የፕሪሚየር ሊግ፣ የጥሎ ማለፍ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን ሲያሳኩ ከፍተኛ ግልጋሎትን የሰጠ ሲሆን አፄዎቹ ኢትዮጵያን ወክለዉ በአፍሪካ መድረክ የCAF ቻምፒየንስ ሊግና ኮንፌደረሽን ጨዋታዎች ላይ በቋሚነት በመሰለፍ ድንቅ 5 ዓመታትን ማሳለፍ ችሏል።

ከድር ኩሊባሊ ከክለባችን ጋር ለነበረህ ቆይታ በፋሲል ከነማ እና በደጋፊዎቻችን ስም ምስጋናችንን እያቀረብን መልካሙን ሁሉ እንመኝልሃለን::
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ።

ከድር ኩሊቤሊ(ኩሊ ጎንደሬው) ስለነበሩን ጊዚያት እናመሰግናለን 🙏🙏🙏🙏
# አስቻለው ታመነ (አስቼ አማቻችን እናመሰግናለን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏
በሄድክበት ሁሉ የተሻለውን እንመኛለን
2024/09/30 01:32:05
Back to Top
HTML Embed Code: