Telegram Web Link
#እንኳን_ደስ_ያላችሁ_ቅርንጫፋ_ማስተባሪያ_በአሜሪካ_ተከፍቶ_በይፋ_ወደ_ስራ_ገብቷል🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
ለመላዉ የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች በመሉ ለዓመታት ስንመኘዉ የነበረዉ ዕለት እነሆ ዛሬ ሆነ።ደጋፊ ማህበራችን ቅርንጫፍ ማስተባበሪያ በሀገረ አሜሪካ በይፋ የከፈተ ሲሆን በዛሬዉ ዕለትም የኢትዮጵያ ቀን በሚከበርበት በዳላስ ታላላቅ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት ደማቅ ዝግጅት እያከናወነ ይገኛል።

@FASILSC
ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ
Photo
የአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ደረጃውን በጠበቃ መንገድ ለማደስ ኮሜቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ተገለፀ ።

በጎንደር ከተማ የአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ደረጃውን በጠበቃ መንገድ ለማደስ ኮሜቴ ተቋቁሞ ከህብርተሰቡ ሀብት የማሰባሰብ ስራ መግባቱ ተገልጿል ።

የጎንደር ከተማ ተቀደሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ እንደገለፁት ለ2016 ዓ.ም ለፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ውጤተማ ሆኖ እንዲቀጥል በፋይናንስ ፣ በእውቀትና በአደረጃጀት ለማሻሻል በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ።

የእግር ኳስ ወደ ከተማችን ለማምጣት ተፈላጊ መስፈርቱን በሚያሟላ መንገድ የአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ለማሳደስ ኮሜቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መግባቱን ከንቲባው ገልጸዋል ።

ጎንደር ስፖርት አፍቃሪያን ያሉባት ከተማ ናት ያሉት ተቀደሚ ምክትል ከንቲባው ስታዲየሙ መታደስ ለከተማው ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል ።
ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ለማደስ አካውንት ተከፍቶ ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ ቴክኒክ ኮሜቴው በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ባዩህ ተናግረዋል ።

መላው የከተማችን ነዋሪዎች ፣የስፖርት አፍቃሪያን ፣ በሀገር ውስጥ ሆነ በውጭ ያሉ ባለሀብቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ጥሪ አስተላልፈዋል ።

የአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም የእድሳት ቴክኒክ ኮሜቴ አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል አማረ ደግሞ ኮሜቴው ከሁለት ወራት በፊት ተቋቁሞ እየሰራ ይገኛል ብለዋል ።
ኮሜቴው ከመንግሥት ፣ ከፋሲል ከነማ ደጋፊ ማህበር እና ከህብረተሰቡ የተውጣጣ መሆኑን አቶ ሳሙኤል ገልጸዋል ።

የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ ፣ሀብት አፈላላጊ ፣ የኦዲት ፣ የሚዲያና ዶክሜንቴሽን ኮሚቴዎች መዋቅራቸውን አቶ ሳሙኤል ተናግረዋል ።

ህብረተሰቡ ኮሚቴውን አግዞት ስታዲየሙ ታድሶ ለ2016 ዓ.ም ጨዋታ ጎንደር ላይ እንዲሆን ልንሰራ ይገባል ብለዋል ።

የአፄ ፋሲል ስታዲየም የእድሳት የቴክኒክ ክፋል ኃላፊ አቶ ደመላሽ አበበ በበኩላቸው ፋሲል ከነማ የስፖርት ክለብ ባለፉት አራት ዓመታት የሚጫወተው ከከተማው ውጭ ስለሆነ ክለቡ በከተማው እንዲጫወት ስታዲየሙን ማደስ አስፈላጊ ነው ብለዋል ።

ስታዲየሙን በሁለት ወራት ውስጥ መስፈርቱን በሚያሟላ መንገድ አጠናቆ ክለቡን ወደ ከተማው ለመመለስ በእቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ደመላሽ የእግር ኳስ መጫወቻው ሜዳ ተነስቶ እንደ አዲስ እንደሚሰራ ገልፀዋል ።

ለሜዳው አስፈላጊ የሆነ የግራውንድ የዉሃ ማሰባሰቢያ፣ የማልበሻ ክፋሎች ስታንዳርዱን በጠበቀ መንገድ እንደሚሰራ አቶ ደመላሽ ተናግረዋል ።

የአፄ ፋሲል ስታዲየም ግንባታ ሀብት አፈላላጊ ኮሜቴ ወይዘሪት ትግስት ሲሳይ ደግሞ ስታዲየሙን ለመገንባት ሲታስብ ትልቁ ሀብት ማህበረሰቡ መሆኑን ገልጸዋል ።

@FASILSC
የ ዘመናችን ቴወድሮስ በ ቀኑ የቴወድሮስ ደረጃ ያዘ
ያልሸነፍ ባይነታችን ማሳያ ;የኩሩነታችን ምሳሌ ኮረኔል ደመቀ ዘውዱ 💪💪
"ሰው ማለት ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋለት !!!!!"


ፋሲል ከክለብም በላይ ነው
🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
@FASILSC
@FASILSC
ኑ ጎንደርን ወደ ትልቁ ክብሯ እንመልሳት ; ንግስናችን ነው ቦታችን ; ማንም የሚቀናበትን የማሸነፍ ስነልቦናችን ከፍ እናድርግ ዘመቻ ሀምሌ 13 ተቀላቀሉ ፋሲል በአፍሪካ መድረክ የሚደምቅበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም ያሉብንን ክፍተቶች በ ትህትና እየተነጋገርን ክለባችን ከፍ እናድርግ የክለቡ ሀላፊነት የኔም ያንተም ያንችም ነው ። ወቀሳውን ወደጎን ትተን በሙሉ እምነት እንሳተፍ እንገዝ እናስተካክል ።

አብረን ስለሆንን እናመሰግናለን ።



We are Emperor's
ፋሲል ከክለብም በላይ ነው ።
@FASILSC
@FASILSC
የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ታወቀ!!

የ2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሐምሌ 01/2015 መጠናቀቁ ይታወቃል። በቀጣይ የሚካሄደው የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር መስከረም 20/2016 የሚጀምር መሆኑን አክሲዮን ማኅበሩ ይፋ አድርጓል።
🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
ትኩረት ፋሲል ስለተከለከለበት ዝውውር ጊዜ ሳይሄድ ቶሎ መፍትሔ ይፈለግ
@FASILSC
የ2016 የኢትዮጽያ ፕሪሚየር ሊግ የሚጀምርበት ቀን ታወቀ!!

የ2015 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዉድድር ሀምሌ 1/2015 መጠናቀቁ ይታወቃል ።

በቀጣይ የሚካሄደው የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዉድድር መስከረም 20/2016 የሚጀምር መሆኑን አክሲዮን ማህበሩ ይፋ አድርጓል ።


@FASILESC

🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ፈንታውን ኪዴ እና ካህሌ ታደሰ በ2011 ዓ.ም ፋሲል ከነማ ከባህርዳር ከነማ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ክለባቸውን ደግፈው ከባህርዳር ወደ ጎንደር በሚጓዙበት ጊዜ አውቶብስ የመገልበት አደጋ ሲደርስበት በርካቶች የመቁሰል አደጋ ሲያጋጥማቸው እነዚህ ሁለት ደጋፊዎቻችን ይወታቸውን አጠዋል ሆኖም ''የሐምሌ 13'' ዘመቻን የህይወት ዘመን ደጋፊዎች በማለት የምናስታውሳቸውን ፈንታሁን እና ካህሌን የፕላቲኒየም ደረጃ መታወቂያ በማውጣት በክብር እንድናስባቸው ያደረጉልን የክለባችን ደጋፊዎች እነሱም የፕላቲኒዩም አባሎች የሆኑት ሰናይት አማረ እና ማህሌት የኋላ ይሄን በጎ ተግባር በማሰብ ወደ ተግባር ቀይረው ላደረጉት ከፍተኛ ድጋፍ ክብር እንሰጣለን በፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ስም ምስጋናችን ይድረስ።

''ሐምሌ 13'' የመታወቂያ ማውጣት ዘመቻውን ይቀላቀሉ ክለብዎትን በተግባር ይደግፉ!!

በፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ቢሮ ቀርባችሁ መታወቂያ ማውጣት ያልቻላችሁ በሀገር እና ከሀገር ውጭ የምትኖሩ ደጋፊዎች በመረጣችሁት የደጋፊዎች መታወቂያ ደረጃ ብር በማስገባት ሪሲቱን ቢልኩልን አውጥተን እንልካለን።

የቴሌግራም እና ዋትሳፕ ቁጥሮች፦
0912745674
0918770424
0912614139
0911507744

@FASILSC
ፋሲል ከነማ የመጀመሪያ ፈራሚ ላለፉት ሁለት አመታትን በወላይታ ዲቻ ያሳለፈውን የመስመር አጥቂ ቃልኪዳን ዘላለምን አስፈርሟል።

ተጫዋቹም ለ3አመት ፊርማውን አስቀምጧል

እንኳን ወደ ታላቁ ፋሲል ከነማ ቤት በሰላም መጣህ

መልካም የስራ ጊዜ ከፍ ብለክ እምትነግስበት እንዲሆን እንመኛለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
ምስል ሶከር ኢትዮጵያ 👏

@FASILSC
2024/09/30 11:31:51
Back to Top
HTML Embed Code: