Telegram Web Link
አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከሲዳማ ቡና ጋር ስለነበረን ጨዋታ

ስለ ጨዋታው…

“ገና በአንድ ደቂቃ ነው ግብ የተቆጠረብን ፤ ይህ ደግሞ በተጫዋቾቹ ላይ የፈጠረው ተፅዕኖ አለ። ከዛ ውጪ በጣም ጥሩ ነበር። ያገኘናቸውን የግብ ዕድሎች አልተጠቀምንም እንጂ ጨዋታውን በምንፈልገው መንገድ ነው ያስኬድነው።”

በሁለተኛው አጋማሽ ስለ ታየባቸው የአጨራረስ ድክመት…

“እንግዲህ ባሉህ ተጫዋቾች ነው የምትሄደው። ካሉን ልጆች ውጪ ምንም ማድረግ አልችልም። በርካታ ግብ የሚሆኑ ዕድሎችን አግኝተናል ፤ ግን ወሳኝ አጥቂዎች ከሌሉ ምንም ማድረግ አይቻልም። የተቻለኝን ለማስተካከል እሞክራለሁ። መጀመሪያ ምልመላ ላይ ነው ሥራዎች የተበላሹት ስለዚህ ባለን ነገር ለማስተካከል እንሄዳለን።”



በቡድናቸው ላይ ስላላቸው ስሜት…

“እኛ ቤት የተለመደው ቻምፒዮን መሆን ነው። ደጋፊም የሚፈልገው ያንን ነው። ለውጡን ተመልካቹም ፣ ደጋፊውም ፣ አመራሩም ይረዳዋል ብዬ አስባለሁ። ግን የሚፈለገውን ያህል ባለመሄዱ ከውጤት አንጻር የሚሰማህ ነገር አለ ፤ የቡድኑ ለውጥ ግን ጥሩ ነው ባይ ነኝ።”

@FASILSC
ኢትዮጵያ ፒርሜርሊግ ደረጃ ሰንጠረዠ ከ 25ኛ ጨዋታ በኋላ
@FASILSC
@FASILSC
የፋሲል ከነማ እስፖርት ክለብ በደጋፊያችን አለማየው ሞላ ሞት የተሰማነን ሀዘን እየገለፅን ለመላው ቤተሰቦቹ ወዳጆቹ እና ለእስፖርት ቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን

@FASILE
የባህርዳር ደጋፊዎች ክለባቸው ነገ ላለባቸው ጨዋታ ዛሬ ከባህርዳር ወደ ሀዋሳ በመጓዝ ላይ እያሉ በደጋፊው ላይ የቦንብ ፍንዳታ ደርሶባቸዋል እጅጉን አዝነናል 😭

ለተጎዱት ፈጣሪ በቶሎ እንዲያሽላቸውና በመንገድ ላይ ያላችሁም ፈጣሪ በሰላም ይመልሳችሁ 🙏🙏🙏


@FASILE
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፋሲል ከነማ ከሲዳማ ቡና የነበረው ጨዋታ

እልህ ፣ ቁጭት፣ አልሸነፍ ባይነት የቻሉትን አድርገዋል ለዚህም ማሳያ ሳማኪን ማንሳት ይቻላል ፡፡

እርግጥ ጎሉ የተቆጠረ ከቅጣት ምት ሆኖ ሳለ በተከላካይና በበረኛ ስህተት ነበር ግን ከዛም በኋላ ላለውው ጨዋታ ተጫዋቾቹ ያቅማቸውን ጥረዋል ቀጣዩን ጨዋታ እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹




@FASILE
ፋሲል ከነማ ከ ድሬዳዋ ከተማ

እሁድ ግንቦት 20/2015

9:00 ሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም

ድል ለአፄዎቹ🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹




@FASILE
የጨዋታ መረጃዎች

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 26ኛ ሳምንት ጨዋታ እንደሚከተለው ነው

ድሬዳዋ ከተማ ከፋሲል ከነማ፦፦ በእለቱ ቀዳሚ መርሀ ግብር በ33 ነጥቦች 10ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡትን ድሬዳዋ ከተማዎች በ37 ነጥቦች በ4ኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጡት ፋሲል ከነማዎች ሲያገናኝ ለተመልካች ማራኪ የሆነ ፉክክር እንደሚኖርበት የሚጠበቀው ጨዋታ ቀን 9 ሰአት ሲል ይጀመራል፡፡

፦ከአራትጨዋታ በኋላ በሲዳማ ቡና ሽንፈት የገጠማቸው ፋሲሎች በኳስ ቁጥጥሩ ብልጫ ቢወስዱም የግብ እድሎችን በመጠቀም በኩል የነበራቸው ደካማ እንቅስቃሴ ድል ላለማሳካታቸው ምክንያት ነበር ፡፡ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከጨዋታ በኋላ በሰጡት አስተያየት በተለይ ከፊት መስመር ላይ ያለው የተጫዋቾች ስብስብ ከመጀመሪያ ምልመላ ጀምሮ ስኬታማ እንዳልነበር በመጠቆም በዛ ምክንያት ተከታታይ ድሎችን አለማሳካታቸውን መግለፃቸው ሲታወስ ቡድኑ ካለፉት 12 ጨዋታዎች 10 የሚሆኑትን ግብ አስቆጥረው መጠነኛ መሻሻል ላይ የነበረ ቢሆንም በቂ ባለመሆኑ ለተከታታይ ድሎች ከመቸገሩ በላይ አምስተኛውን ዝቅተኛ የግብ መጠን (26) ብቻ ማስቆጠራቸው ግን የአሰልጣኙን ሀሳብ የሚደግፉ ቁጥራዊ መረጃዎች ናቸው

ሆኖም አፄዎቹ በተከታታይ የሚገጥሟቸው ድሬዳዋ ከተማ እና ወልቂጤ የመውረድ ስጋት ያለባቸው ቡድኖች በመሆናቸው ድል ለማሳካት ጠንካራ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በፋሲል በኩል በዛብህ መለዮ በጉዳት ምክንያት ከጨዋታ ውጭ ሲሆን ፍቃዱ አለሙ ግን መሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ነው፡፡

በድሬዳዋ በኩል ያሲን ጀማል፣ ያሬድ ታደሰ፣ብሩክ ቃልቦሬ እና እንየው ካሳሁን በጉዳት ምክንያት ሲሆን ቢኒያም ጌታቸው እና ዩሴፍ ዮሀንስ ደግሞ በቅጣት ጨዋታ ያመልጣቸዋል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም ለ 11 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን እኩል አራት አራት ጊዜ ሲያሸንፉ በሶስቱ አቻ ተለያይተዋል በጨዋታው ፋሲል 14 ድሬዳዋ ደግሞ 10 ግቦች አስቆጥረዋል


እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILE
ፋሲል ከነማ የመጀመሪያ አሰላለፍ


እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹



@FASILE
ድሬ አደገኛ ቅጣት መተው አስቆጠሩ
ድሬ1 -0 ፋሲል
ፔናሊቲ ለፋሲል
ጎልልልልልል ሽሜ ፔናሊቲውን አስቆጠረ
ጎልልልልልልል ፋሲል ከነማ
29' ፋሲል 1-1 ድሬ ዳዋ
ሽመክት አብድለጢፍ
ፋሲል አሪፍ ቅጣት ምት አግኝተው ነበር አልተሳካም
ጎል አስቆጥረን ነበር ከጨዋታ ውጭ ተባለ
36' ፋሲል 1-1 ድሬዳዋ ከተማ
40'ከቅድሙ ቦታ ላይ ቅጣት ምት አግኝተው ነበር አልተጠቀሙበትም ድሬወች
2024/11/05 23:21:31
Back to Top
HTML Embed Code: