Telegram Web Link
ዋልያዎቹ ከአፍሪካ ዋንጫ ውጪ መሆናቸው ተረጋገጠ!

በ2023 በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ሲያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድቡ ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች እየቀሩት ወደ ውድድሩ የሚያልፍበት ዕድል ሙሉ ለሙሉ መምከኑ ተረጋግጧል።

በምድቡ ግብፅ ቀድማ ማለፏን ስታረጋግጥ ከቀጣይ ጨዋታ አንድ ነጥብ ብቻ ወይም የማላዊን መሸነፍ የምትፈልገው እና 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ጊኒ ከኢትዮጵያ ጋር ያላት የእርስ በርስ የበላይነት ዋልያዎቹ ከቀሪ 2 ጨዋታዎች ሙሉ ነጥብ ቢያገኙም እንዲያልፉ አያደርጋቸውም።

ዋልያዎቹ ምንም እንኳን ወደ አፍሪካ ዋንጫው ባያልፉም የፊታችን ማክሰኞ ሞዛምቢክ ላይ ከማላዊ አቻቸው ጋር ጨዋታ ያደርጋሉ።

@FASILSC
*ፋሲል ከነማ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ከስምምነት ደርሷል
የ2013 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ፋሲል ከነማ ለቀጣይ የውድድር አመት አሰልጣኝ ሊሾም ነው፡፡

* ከከፍተኛ ሊግ አድጎ በ2009 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መሳተፍ የጀመረው እና ከአምስት አመት በኋላ የሊጉን ዋንጫ በማንሳት ጠንካራ ክለብ እየገነባ መሆኑን ያስመሰከረው ፋሲል ከነማ በዘንድሮው የውድድር አመት ግን ተቀዛቅዞ መቅረቡ እየታየ ይገኛል ፡፡

* ወደ ቀድሞ ጥንካሬያቸው የሚመልሳቸው አሰልጣኝ ለወራት ሲያጤኑ የቆዩት ፋሲል ከነማዎች ባሳለፍነው አርብ ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ስምምነት መድረሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡

*አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዚህ ቀደም በፋሲል ከነማ ቤት ውጤታማ የማሰልጠን ቆይታ እንደነበራቸውም ይታወቃል ፡፡

*በስምምነቱ አጠቃላይ ዝርዝር ሁኔታውን በቅርቡ ይፋ እናደርጋለን

መልካም እድል አሰልጣኝ ውበቱ አባተ🇦🇹

Soccer Ethiopia

@FASILSC🇦🇹🇦🇹🇦🇹
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ አምስተኛ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከቀኑ 11፡00 በማፑቶ ዚምፔቶ ናሽናል ስታዲየም ከማላዊ ጋር ያደርጋል።

ድል ለኢትዮጵያ!
11:00

🇪🇹 ኢትዮጵያማላዊ 🇲🇼

ጨዋታ የሚካሄድበት ስታዲየም

ዚምፔቶ ስታድየም
ፋሲል ከነማና ውስጥ አዋቂው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ዳግም ተጣመሩ

👉ኢትዮጵያ ቡና ያቀረበው 350 ሺህ ብር ደመወዝ ተቀባይነት አጥቷል አጼዎቹ የንግስና ቦታቸውን ለማስመለስና በአፍሪካ መድረክ ጠንካራ ተፎካካሪ ክለብ ለመሆን በማለም አሰልጣኝ ውበቱ አባተን አሰልጣኝ ለማድረግ ተስማሙ።
ዋሊያዎቹን ለአፍሪካና ለቻን ሻምፒዮና የማብቃት ታሪክ የሰሩት አሰልጣኝ ውበቱ በጠንካራ ሁኔታ ሲፈልጓቸው ከነበሩትና ሙያዊ ግልጋሎታቸውን ካገኙት ከፋሲል ከነማና ከኢትዮጵያ ቡና ተወካዮች ጋር ድርድር ሲያደርጉ ቆይተው ከፋሲል ከነማ ጋር ተስማምተዋል።
አሰልጣኙ በ2003 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ካደረጉት የኢትዮጵያ ቡና ጋር ለሁለት ጊዜ የተደራደሩ ሲሆን ከክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ከአንድ የቦርድና ከደጋፊ ማህበሩ አመራሮች ጋር የተደረገው ውይይት ያለ ስምምነት ተቋጭቷል።
ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ አሰልጣኙ 400 ሺህ ብር የወር ደመወዝ በሶስት አመት የሚከፈለው 14,400,000 ለሁለት ተካፍሎ 7,200,000 ሺህ ብር በቅድሚያ ክፍያ ተከፍሎት ግማሹ በ36 ወር ተካፍሎ በደመወዝ 200 ሺህ ብር እንዲከፈላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም ምላሽ ሳያገኙ ቀርቷል። በተለይ የቦርድ አባሉ አቶ ዳንኤል ገንዘቡ መብዛቱን በመግለፅ አቅሙ የለንም ለቦርድም አይቀርብም በማለታቸው ያለ ስምምነት ተለያይተዋል።

ክለቡን የወከሉት ወገኖች ለሁለተኛ ጊዜ ድርድር ከመቀመጣቸው በፊት በአሰልጣኞቹ ወገን ሌላ የመደራደሪያ ሀሳብ ቀርቧል። በመጀመሪያ አመት የሚከፈለው የአንድ አመት ደመወዝ 4,733,000 በቅድሚያ ተከፍሎ ቀሪው ለሁለት አመት ለ24 ወር በደመወዝ እንዲከፈለው ቢጠይቅም የደጋፊ ማህበሩ አመራሮችና ቦርዱ ሳይስማሙ ቀርተዋል።
ከሳምንታት ቆይታ በኋላ ቦርዱና የደጋፊ ማህበሩ አመራሮች ተወያይተው ክለቡ 300 ሺህ ብር ደጋፊ ማህበሩ 50 ሺህ ብሩን ሸፍነው 350 ሺህ ብር ለመክፈል ቢጠይቁም ለውሳኔ በመዘግየታቸውና አሰልጣኙን ማሳመን ሳይችሉ በመቅረታቸው ፊታቸውን ወደ ሌላ የውጪ ሀገር አሰልጣኝ ማዞራቸው ታውቋል።
ጠንካራ ድርድር ያደረጉትና አሰልጣኙን ለማሳመን ሽንጣቸውን ገትረው የተደራደሩት አጼዎቹ ፋሲል ከነማዎች በኢትዮጵያ ቡና በአርባ ምንጭና በድሬዳዋ ከተሞች ከንቲባዎች ሳይቀር የተፈለገውን አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ለቀጣዮቹ ሶስት አመታት አሰልጣኛቸው አድርገው መርጠዋል።
የ2013ና የ2014 ጠንካራ ተፎካካሪነቱን ያጣው ፋሲል ከነማ የጎንደር ከተማ ከንቲባና የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢን አቶ ባዩ አቦሀይ ድርድሩን እንዲመሩ ያደርገው ጥረት በስምምነት መቋጨቱ ታውቋል። ከንቲባው ከዚህ ሀላፊነታቸው አስቀድሞ የፋሲል ከነማ ደጋፊ በመሆን ስታዲየም ተገኝተው ቡድኑን ያበረታቱ እንደነበር ያገኘነው መረጃ ያስረዳል ከንቲባው ለፋሲል ቅርብ መሆናቸው ለለውጥ ትልቅ ድጋፍ እንደሚሆን ይታመናል።
የክለቡ የውስጥ አዋቂ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አሰልጣኝ ውበቱ አስቀድሞ የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ የመሆን እድል የነበራቸው ሲሆን በወቅቱ ሀላፊነት ላይ የነበሩትን አሰልጣኝ ሃይሉ ነጋሽ /ቲጋናን/ ለመጀመሪያ ጊዜ ምክትል አድርገው እንደሾሙ በመጥቀስ ምክትሌ አድርጌ አሁን ደግሞ በመንገዱ ላይ አልቆምም በማለት ጥያቄውን አለመቀበላቸው ይታወሳል።
ፋሲል ከነማዎች እስከ ሰኔ 30/2015 ድረስ ያለው የአሁኑ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ውል እስኪያልቅ ድረስ ውሉን ይፋ ባያደርጉትም በኢትዮጵያ ቡና የቀረበላቸውን 350 ሺህ ብር ያልተቀበሉትን አሰልጣኝ ውበቱ ከቀጣዮቹ ሶስት አመታት አጼዎቹን እንዲያሰለጥኑ ኢትዮጵያ ቡናዎች ካቀረቡት የተሻለ እስከ 400 ሺህ ብር አካባቢ እንዲከፈላቸው ሳይስማሙ እንዳልቀረም እየተነገረ ነው። በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ሹመትና ዝርዝር ስምምነት ዙሪያ ከሁለቱም ወገኖች ይፋ የተደረገ መረጃ ባይኖርም የውል ስምምነታቸውን የሚገልጸው ሰነድ ባለፈው አርብ ፌዴሬሽን መግባቱን ከፌዴሬሽኑና ከክለቡ ታማኝ ምንጮች የተገኘ መረጃ ያስረዳል።
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በ250 ሺህ ብር ወርሃዊ ደመወዝ እየሰሩበት ከነበረው የዋሊያዎቹ ሀላፊነታቸው ለፌዴሬሽኑ ባስገቡት በስምምነት እንለያይ ጥያቄ በስምምነት ከተለያዩ በሳምንታት ውስጥ ከተሻለ የደመወዝ ክፍያ ጋር ጠንካራ ድጋፍ የሚያገኙበትን ሀላፊነት ለመረከብ መስማማታቸው ታውቋል።

አሰልጣኙ ቡድኑን በደንብ እንዲያጠናክሩ የፈለጓቸውን ተጨዋቾች የማስቀረት ሌሎች ቡድኑን የሚያጠናክሩ ተጨዋቾችን እንዲያስፈርሙ ሞቅ ያለ የዝውውር በጀት እንደተመደበላቸው የታወቀ ሲሆን በዲሲፕሊን ላይ ድርድር የማያውቁት አሰልጣኝ ውበቱ መልበሻ ቤቱን የመቆጣጠርና የመምራት ሙሉ ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ አሰልጣኙ ፋሲል ከነማን በአንደኛው አመት ጠንካራ ተፎካካሪ እንደሚያደርጉ በሁለኛው አመት ወደ ሻምፒዮንነት እንዲመልሱ በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ጥሩ ተፎካካሪ እንደሚያደርጉ በእቅድ ደረጃ ማሳወቃቸው የወጣው መረጃ ያስረዳል።


ፋሲል ከነማዎች በ2013 በፕሪሚየር ሊጉ ላይ የነገሱ ሲሆን በ2014 ሁለተኛ ሆነው ጨርሰዋል ክለቡ በ2015 አሰልጣኝ ሃይሉ ነጋሽና አሰልጣኘ አሸናፊ በቀለን ቢሾምም በእስካሁኑ 28ኛ ሳምንት መርሀግብር በ39 ነጥብና 4 ግብ 6ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የፊታችን ዓርብ ሳምንት ሰኔ 23/2015 ደግሞ ከወረደው ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር 29ኛ ሳምንት መርሀግብሩን ያካሂዳል።

ፋሲል ከነማ ቀጣዮቹን ሁለት ጨዋታዎችን ቢያሸንፍ እንኳ የሚደርሰው 45 ነጥብ ላይ በመሆኑ ከአራተኛነት የዘለለ ደረጃ እንደማይኖረው በመረጋገጡ የዝውውርና የሹመት ስራው ከአሁኑ ለቀጣዮቹ አመታት እየተዘጋጀ መሆኑን እንደሚያሳይ ከክለቡ ታማኝ ምንጭ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።

Hatrick Sport

@FASILSC
ተጠናቀቀ

🇪🇹 ኢትዮጵያ 0-0 ማላዊ 🇲🇼

@FASILSC
ቀጣይ ጨዋታ

ፋሲል ከነማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

አርብ ሰኔ 23

12 ሰአት አዳማ ዩኒበርስቲ


@FASILE🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ እህት/ወንድሞቻችን እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አል‐አድሀ በዓል አደረሳችሁ!

መልካም በአል!

@FASILSC
ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለ2016 የውድድር አመት ተጠናክሮ ለመቅረብ ከወዲሁ ስራ የጀመረ ሲሆን የክለባችን ደጋፊዎች ደግሞ የአባልነት መታወቂያ በማውጣት ደጋፊነታቸውን በተግባር እያስመሰከሩ ይገኛሉ!!
ውድ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች የአባልነት መታወቂያ የማውጣት ንቅናቄውን ሁሉም የክለባችን ቤተሰቦች የተመዘገቡ ደጋፊዎች እንዲሆኑ መታወቂያ የማውጣት ስራው በታቀደለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በውጭ ሀገር ያላችሁ ደጋፊዎች ይሄን በጎ ተግባር እንድትቀላቀሉ ጥሪው ተላልፏል::

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
ፋሲል ከነማ ከ ኢቶዮ ኤሌክትሪክ

አርብ ምሽት 12 ሰአት አዳማ ዩኒበርስቲ

ሽመክት ጉግሳ እና በዛብህ መለዮ በጉዳት የማይሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው


እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹



FASILESC
ፋሲል ከነማ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

የዛሬው አሰላለፍ ይሄን ይመስላል በዛብህ መለዮ፣ሱራፌል ዳኛቸው፣ ሀብታሙ ገዛኸኝ እና አስቻለው ታመነ በጉዳት ሲሆን ሽመክት ጉግሳ እና አምሳሉ ጥላሁን በግል ጉዳይ የዛሬው ጨዋታ እሚያልፋቸው ይሆናል

እናሸንፋለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹



@FASILESC
ሁለተኛ አጋማሽ ተጀምሯል

ፋሲል ከነማ 1- ኢትዮ ኤሌክትሪክ 0
ጎሎልልል ፋሲል
ፋሲል ከነማ 2-ኤሌክትሪክ 0
ጎል ኢትዮ ኤሌክትሪክ 1 -2 ፋሲል ከነማ
ጨዋታው ተጠናቀቀ

ፋሲል 2-1 ኢትዮ ኤሌክትሪክ
አብዱረህማን
ኦሴ ማውሊ
አለምብርሀን ይግዛው
ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ 🇦🇹🇦🇹🇦🇹

የ2015 የኢትዮጵያ የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ አሸናፊና ኢትዮጵያን በመወከል የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ለሆነው ለቅዱስ ጊዎርጊስ ክለብ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን

እንኳን ደስ ያላችሁ ከፋሲል ከነማ🇦🇹



@FASILESC
2024/09/30 19:30:27
Back to Top
HTML Embed Code: