Telegram Web Link
❗️ሊባኖሳውያን ​​በሞተር ሳይክሎች፣ መኪናዎች እና በተለያዩ መሳሪያዎች ላይ ፍንዳታ እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል
«ትራንስፖርት ፍጹም ይበላሻል በየትኛውም አለም መኪና ፣ ባቡር፣ አውሮፕላን፣ መርከብ ሁሉም ለመገልገል ያስቸግራል አደጋቸውም የበዛ ይሆናል፡፡ ለምህረት ያልታደሉትን ለማጥፋት ሞት ሁሉንም መገልገያዎች ወደ መግደያነት ይለውጣቸዋል፡፡ »

► ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 3 ተፃፈ 19/07/2001 ዓ፡ም
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
❗️ሊባኖሳውያን ​​በሞተር ሳይክሎች፣ መኪናዎች እና በተለያዩ መሳሪያዎች ላይ ፍንዳታ እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል።
❗️ባለፉት 2 ቀናት በሊባኖስ ውስጥ በደረሰው የመገናኛ መሳሪያዎች ፍንዳታ የ37 ሰዎች ህይወት እንዳለፈ እና በመጀመሪያው ማዕበል 12 ሰዎች እንዲሁም በሁለተኛው ማእበል ተጨማሪ 25 ሰዎች መገደላቸውን የሊባኖስ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታውቀዋል

በጉዳዩ ዙርያ ባለስልጣኑ የሰጡት ተጨማሪ መግለጫዎች፦

🟠 በመጀመሪያው ቀን ወደ ሆስፒታል የተወሰዱት ተጎጂዎች ቁጥር 2,323 ደርሷል።
🟠 608 ሰዎች እሮብ እለት ቆስለዋል።
🟠 1,343 የሚሆኑት ተጎጂዎች በመካከለኛ ወይም ከባድ ሁኔታ ላይ ናቸው።
🟠 በሁለተኛው የጥቃት ማዕበል የገመድ አልባ መሳሪያዎች ፍንዳታ ሃይል ጠንከር ያለ በመሆኑ የከፋ ጉዳት ተመዝግቧል።
🟢🟡🔴
መስከረም 10 |
#ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር ተገለጠ

ዳግመኛም በዚህ ቀን፦

🌼 የቅዱሳት ሥዕላት ሁሉ በዓል ነው።

🌼 #ተቀጸል_ጽጌ #ዓፄ_መስቀል ይከበራል። የጌታችን ቅዱስ መስቀል አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የገባበት ቀን ነው፡፡

● ከከሃዲው ከሆሎፎርኒስ እጅ በጥበቧ እስራኤልን ያዳነቻቸው የሜራሪ ልጅ #ጥበበኛዋ_ዮዲት (የጳጒሜን ጾም ላይ የምናስባት ቅድስት) ዐረፈች

🌼 #ንግሥተ_ሳባ (ንግሥት ማክዳ) ዕረፍቷ ነው።

🌼 ቅድስት መጥሮንያ ሰማዕት፦ በእምነት ከማትመስላት አይሁዳዊት ቤት አገልጋይ ሆና ብትኖር እምነቷን ልታስቀይራት ብዙ ሞክራ አልሳካ ሲላት የገደለቻት፣ በሃይማኖቷ ጸንታ እምነቷን ጠብቃ ሰማዕትነትን የተቀበለች ቀን ነው።

ከእመቤታችን፣ ከቅዱስ መስቀሉ፣ ከቅዱሳኑ ሁሉ ረድኤት በረከትን አይንሣን።

🍀🌼🍀
T.me/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (♝ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን♝ 🇨🇬🇨🇬)
"ይሁ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስራ ማደናቀፍ ያለ ዋጋ ክፍያ ይታለፋል ማለት ስህተት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ስራ ማንም በስጋ ጥበብና ጉልበት ሊያደናቅፈው የሚቻል አይደለም፡፡ ሲሞክርም ቅጣቱ ይሰነዘራል፡፡"

📎 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ቁጥር 5 ፡ ገፅ 38 * ተጻፈ መስከረም 21/2004 ዓ.ም
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
ሊባኖስ ዉስጥ ፔጀርስ በተባለዉ ሞባይል መሠል የመገናኛ መሣሪያዎች ዉስጥ የተጠመዱ በእንግሊዝኛ ምህጻሩ PETN የተባለ ከፍተኛ ፈንጂ መስሪያ የተሰሩ መሆናቸውን አንድ ለሙያው ቅርበት ያለው ሰው ለሮይተርስ ተናገረ። ይህ አደገኛ ፈንጂ ከባትሪው ጋር እንዲዋሃድ የማድረጉ ተግባር በቀላሉ እንዳይታወቁ በሚያስችል መልኩ እንደተሰራም ባለሙያው አክሏል።
ሊባኖስ ዉስጥ ፔጀርስ በተባለዉ ሞባይል መሠል የመገናኛ መሣሪያዎች ዉስጥ የተጠመዱ ቦምቦች ባለፈዉ ማክሰኞና ሮብ ፈንድተዉ በትንሹ 32 ሰዎች ተገድለዋል።ከ3000 በላይ ቆስለዋል።አብዛኞቹ ሟችና ቁስለኞች የሊባኖሱ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን የሒዝቡላሕ ተዋጊዎች፣ አባላትና ደጋፊዎች ናቸዉ።በፍንዳታዉ ከተገደሉት አንዱ የሊባኖስ የምክር ቤት እንደራሴ ልጅ ሲሆን፣ ከቆሰሉት ደግሞ በሊባኖስ የኢራን አምባሳደር ይገኙበታል።
ሒዝቡላሕ፣ የሊባኖስ መንግሥትና ኢራን ለፍንዳታዉ እስራኤልን ተጠያቂ አድርገዋል።አንድ የሊባኖስ የሥለላ ከፍተኛ ባለሥልጣን ዛሬ እንዳሉት ሒዝቦላሕ ከወጪ በገዛቸዉ 5000 ፔጄሮች ዉስጥ የእስራኤል የሥለላ ድርጅት ሞሳድ ከአንድ ወር በፊት ፈንጂ አጭቆባቸዋል።ፔጀሮቹ ከታይዋን በቡልጋሪያ በኩል ሊባኖስ መግባታቸዉ ተዘግቧል።ፔጀሮቹን ሠርቷል የተባለዉ ጎልድ አፖሎ የተባለዉ የታይዋን ኩባንያ ግን ፔጀሮቹ «የኛ ምርቶች ዓይደሉም» ይላል።
ዘግየት ብለው የወጡ መረጃዎች ደግሞ ባትሪዎቹ ICOM በተባለው የጃፓን ኩባንያ እንደተሰሩ ያመላክታሉ። ይሁንና የኩባንያው ሥራ አስኪያጅ ድርጅታቸው እነዚህ ለሬድዮ መገናኛ የሚውሉ ባትሪዎች መስራት ካቆመ አስርት ዓመታት እንዳለፉት ተናግሯል ስል ሮይተርስ ዘግቧል።
በዩክሬን ጦርነት ከ70 ሺ በላይ የሩሲያ ወታደሮችና ወዶ ገብ ተዋጊዎች መገደላቸው ተሰማ

በቢቢሲ የተተነተነ መረጃ እንደሚያሳየው ከ 70,000 በላይ ሰዎች በሩሲያ ጦር ውስጥ እየተዋጉ በዩክሬን መገደላቸውን አመላክቷል።

VoA Amharic
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
🟢🟡🔴
መስከረም 11 |
ለአንጾኪያ ነገሥታት አባታቸውና የሰማዕታት መካሪያቸው የሆነ
#ቅዱስ_ፋሲለደስ በሰማዕትነት ዐረፈ።

እርሱም ለሮም ንጉሥ የሠራዊት አለቃ ነው መንግሥቱም ሁለመናዋ በእርሱ ምክር የጸናች ናት። ብዙዎችም ወንዶችና ሴቶች የቤት ውልዶች አገልጋዮች አሉት።

ዝምድናውም እንዲህ ነው ስሙ ኑማርያኖስ የተባለ የሮም ንጉሥ ለቴዎድሮስ በናድሌዎስ እናቱ የሆነች የቅዱስ ፋሲለደስን እኅት አግብቶ ዮስጦስን፣ ገላውዴዎስን፣ አባዲርን ወለደችለት እሊህም ለቅዱስ ፋሲለደስ የእኅቱ ልጆች ናቸው።

የቅዱስ ፋሲለደስም ሚስት ለቅዱስ ፊቅጦር እናት እኅት ናት ከእርሷም ስማቸው አውሳብዮስና መቃርስ የተባሉ ሁለት ልጆችን ወለደ።

በዲዮቅልጥያኖስም አገዛዝ በቅዱስ ፊቅጦር አባት ኅርማኖስ ደጋፊነት ለጣዖት እንዲሰግዱ ከሞት ጋር ታወጀ።

ቅዱስ ፋሲለደስ ዘመዶቹን፣ ሠራዊቱን፣ አገልጋዮቹንም ሁሉ ሰበሰባቸውና በክብር ባለቤት በክርስቶስ ስም ደሙን ሊያፈስ እንደፈለገ አስረዳቸው።

ሁሉም በዚህ ምክር በአንድነት ተሰማሙ።

ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስም መልአኩን ልኮ፣ በመንፈስ ወደ ሰማይ አውጥቶ፣ በብርሃን ያጌጠ መንፈሳዊ ማደሪያን አሳየው። ነፍሱም እጅግ ደስ አላት።
ከዚህም በኋላ በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ፊት ቁመው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ከእርሳቸውም ግርማ የተነሣ ታላቅ ፍርሃትን ፈራ እነርሱ የመንግሥት ልጆች ናቸውና።

የቅዱስ ፊቅጦር አባት ኀርማኖስም ወደ ግብጽ አገር ይልካቸው ዘንድ በዚያም እንዲያሠቃዩዋቸው መከረው ሁሉንም እየአንዳንዳቸውን ለብቻቸው አድርጎ ላካቸው አባዲርንና እኀቱ ኢራኒን ወደ አንዲት አገር፣ አውሳብዮስንና ወንድሙ መቃርስን ወደሌላ ቦታ፣ ገላውዴዎስንም እንዲሁ አደረጉ። በናድሌዎስ ቴዎድሮስም እሼ በሚባል ዕንጨት ላይ በመቶ ሃምሳ ሦስት ችንካር ተቸንክሮ ገድሉን ፈጸመ።

ቅዱስ ፋሲለደስን ግን አምስት ከተማዎች ወዳሉበት ወደ አፍሪካ ምድር ወደ መኰንኑ ወደ መጽሩስ ላከው መጽሩስም በአየው ጊዜ መንግሥቱን ክብሩን ስለ ተወ እጅግ አደነቀ።

በዚያም ለቁጥር የበዙ፣ ለአእምሮ የከበዱ ስቃዮችን ተቀበለ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት ከዚያ ስቃይም ውስጥ አንስቶ ያለ ጉዳት ጤነኛ አደረገው። እንዲህም ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፦

"ፋሲለደስ ሆይ ዕውቅ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ ወይም ለድኆች በስምህ ምጽዋትን ለሚሰጥ ወይም ለተራቈተ ልብስን ወይም በመታሰቢያህ ቀን ለቤተ ክርስቲያን መባ ለሚሰጥ በብዙም ቢሆን በጥቂት መታሰቢያህን ለሚያደርጉ ሁሉ እኔ በደላቸውን ሁሉ እተውላቸዋለሁ መኖሪያቸውንም በመንግሥተ ሰማያት ከአንተ ጋራ አደርጋለሁ።"

ከዚህም በኋላ መጽሩስ መኰንን ከአማካሪዎቹ ጋር ተማከረ። እንዲህም አላቸው "ስሙ ፋሲለደስ ስለሚባል ስለዚህ ሰው ምን ላድርግ? እርሱን ያላሠቃየሁበት የሥቃይ መሣሪያ ምንም የቀረ የለም። ከሐሳቡም አልተመለሰም።" እነርሱም እንዲህ ብለው መከሩት፦ ራሱን በሰይፍ ቆርጠህ ከእርሱ ተገላገል። እነሆ የዚች አገር ሰዎች በእርሱ ምክንያት አልቀዋልና።

በዚያንም ጊዜ የቅዱስ ፋሲለደስን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘና ቆረጡት። የድል አክሊልንም ተቀበለ።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
የሂዝቦላ ከፍተኛ አዛዥ የሆነው ኢብራሂም አቂል ተገደለ 
  
በሊባኖስ ቤሩት ውስጥ እስራኤል በሰነዘረችው የአየር ጥቃት የሂዝቦላ ከፍተኛ አዛዥ የሆነው ኢብራሂም አቂል መገደሉ ተነገረ። 
 
እስራኤል የሂዝቦላ ቡድን ከፍተኛ አዛዥ የሆነውን ኢብራሂም አቂልን ዒላማ አድርጋ የአየር ጥቃቱን መፈጸሟን የሊባኖስ የደህንነት ምንጮች እና የእስራኤል ጦር ራዲዮ ገልጸዋል። 
 
በዚህም ከአዛዡ በተጨማሪ ስምንት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ሌሎች 59 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር መግለጹን ጠቅሶ ሬውተርስ ዘግቧል።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
📌 ይህች ጥቅጥቅ ግሩምና ድንቅ ታምራዊት ወንፊት የማታበጥረው (የማትመረምረው) ፍጥረት የላትም !!!

ሁሉንም ታበጥራለች !!
የቀለሉትን ለእሳት ትጥላለች !!
ምርቱን ከግርዱ ትለያለች !!

ስሟም የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ፍርድ አስፈጻሚ የእሳት ወንፊት ነው ።
እስራኤል በቤሩት ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት ከፍተኛ የሂዝቦላህ መሪዎችን ጨምሮ 31 ሰዎች ተገደሉ።

በደቡባዊ ቤይሩት በሚገኝ ህንጻ ላይ በትላንትናው ዕለት እስራኤል ባደረሰችው ሄዝቦላን ኢላማ ያደረገ የሚሳኤል ጥቃት ቢያንስ 31 ሰዎች መሞታቸውን የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፍራስ አቢያድ ተናግረዋል።

ከሟቾቹ መካከል የሂዝቦላህ አዛዥ ኢብራሂም አቂልን ጨምሮ ሌሎችም በስም ያልተጠቀሱ አዛዦች ይገኙበታል ተብሏል።

ከጥቃቱ በኋላ በአቅራቢያው ያሉ ሕንፃዎች ለግማሽ ሰዓት ያህል መናወጣቸውን የዓይን እማኞች መናገራቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል።

በቤይሩት የሚገኘው የሲኤንኤን ቡድን ከፍርስራሹ ስር ያሉትን ሰዎች ለመታደግ እና የቆሰሉትን በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ለመውሰድ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ተመልክቷል።
🟢🟡🔴
መስከረም 12 | እግዚአብሔር #ቅዱስ_ሚካኤልን ወደ ነቢይ ኢሳይያስ ዘንድ ላከው።

በዚህች ቀን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ወደ አሞጽ ልጅ ወደ #ነቢይ_ኢሳይያስ ላከው።

ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስ ሒዶ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለውና ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜውም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደ ጨመረለት ይነግረው ዘንድ አዘዘው።

ከጻድቁ ንጉሥ ከቅዱስ ዳዊት በኋላ በእስራኤል እንደ ሕዝቅያስ ያለ ሌላ ጻድቅ ንጉሥ አልተነሣም፡፡ ከሕዝቅያስ በኋላ የተነሡት ሁሉም ጣዖትን አምልከዋል፣ ለጣዖታቱም የሚሆን መሠዊያ ሠርተዋል፡፡ ንጉሡ ሕዝቅያስ በነገሠ ጊዜ ግን ጣዖታትን ሰባብሯቸዋል፣ የእስራኤል ልጆች ያመልኩት የነበረውን የነሐስ እባብ ቆራርጦታል፡፡ እግዚአብሔርንም በማመኑ መንግሥቱ እጅግ ሰምሮለታል፡፡ እግዚአብሔርም ያሳጣው በጎ ነገርም የለም፡፡

ንጉሥ ሕዝቅያስም #በቅዱስ_ሚካኤል በኩል ከሰናክሬም እጅ ያዳነውን እግዚአብሔርን ሲያመሰግን ኖረ፡፡

ከዚህም በኋላ ሕዝቅያስ ታሞ ለሞት በደረሰ ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ ‹‹እግዚአብሔር ‹ትሞታለህ እንጂ አትድንም› ብሎሃል›› አለው፡፡ ነገር ግን ሕዝቅያስ አሁንም ልብሱንም ቀዶ ማቅ በመልበስ ጸሎቱን ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፡፡

በዚህ ጊዜ #ቅዱስ_ሚካኤል በእግዚአብሔር ተልኮ መጥቶ ነቢዩ ኢሳይያስን ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ ሄዶ በዕድሜው ላይ 15 ዓመት እንደተጨመረለት እንዲነግረው ታዘዘ፡፡

መልአኩ እንዳዘዘው ነቢዩ ኢሳይያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን "እግዚአብሔር የአባትህ የዳዊት አምላክ ጸሎትህን ሰማሁ፤ ዕንባህንም አየሁ። እነሆ እኔ አድንሃለሁ፡፡ በዘመኖችህም 15 ዓመት ጨምሬልሃለሁ፡፡ ከፋርስ ንጉሥ እጅም አድንሃለሁ፡፡ ይህችን አገር ስለ እኔና ስለ ባለሟሌ ዳዊት አጽንቼ እጠብቃታለሁ›› ብሎሃል ብሎ የተላከውን ነገረው፡፡

T.me/Ewnet1Nat
🇱🇧 🇮🇱 እስራኤል በቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻዎች ባደረሰችው ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 37 መድረሱን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

💬 "በቤይሩት ደቡባዊ ዳርቻዎች በተፈጸመው የአየር ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 37 ደርሷል" ሲል ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ቀደም ሲል እንዳስታወቀው በጥቃቱ ሶስት ህጻናትን ጨምሮ 31 ሰዎች ሞተዋል። ሌሎች 68 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።

መስከረም 7 እና 8 ፔጀሮች እና ዎኪ ቶኪዎች በሊባኖስ የተለያዩ ክፍሎች ፈንድተዋል። እንደ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ገለጻ 37 ሰዎች ሲሞቱ ከ3,000 በላይ የሚሆኑት ቆስለዋል። ሄዝቦላ እና የሊባኖስ ባለስልጣናት ለጥቃቱ እስራኤልን ተጠያቂ አድርገዋል። እስራኤል በጥቃቱ እንደተሳተፈች ከማረጋገጥ ወይም ከመካድ ተቆጥባለች።
2024/09/22 01:06:20
Back to Top
HTML Embed Code: