Telegram Web Link
🇨🇲 በካሜሩን ከ230,000 በላይ ሰዎች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ የጎርፍ አደጋ መጎዳታቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል

💦 የሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ታይቶ የማይታወቅ ከባድ ጎርፍ ለበርካታ ሳምንታት ተመቷል።

🌊 ከቻድ ድንበር አቅራቢያ የምትገኘው የያጉዋ ከተማ የከፋ ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች አንዷ ስትሆን ሰፈሮቹ በውሃ ተውጠው ወደ 200 የሚጠጉ ትምህርት ቤቶች ተጎድተዋል፤ የ12 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል፣እንዲሁም ከአንድ ሺህ በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸው ታውቋል።

ከ18,000 በላይ ቤቶች ወድመዋል። ተጎጂዎቹ በከተማ ዳርቻው በሚገኝ ካምፕ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጓል።

➡️ መንግስት ለተጎዱ ወገኖች የሚውል 350 ሚሊዮን ሲኤፍኤ ፍራንክ (በግምት 590,000 ዶላር) መድቧል።

ምስሎች ከማህበራዊ አውታረመረቦች የተገኙ ናቸው
🇳🇬በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ በደረሰ አሰቃቂ የጀልባ አደጋ ከ40 በላይ ሰዎች ሞቱ

በዛምፋራ ግዛት ገበሬዎች ወደ እርሻ መሬታቸውን ለመድረስ ሲሞክሩ ነው ይህ አሳዛኝ ክስተት የተከሰተው። ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒዩ በሰጡት መግለጫ ለተጎዱ ቤተሰቦች ድጋፍ እንደሚደርግላቸው ገልጸው፤ የአደጋ ጊዜ ኤጀንሲዎች ጉዳዩን በጥልቀት እንዲመረምሩ ትእዛዝ ሰጥተዋል።

የዛምፋራ ፖሊስ ቃል አቀባይ ያዚድ አቡበከር ለምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን እንደገለፁት አምስት ግለሰቦችን ከሞት ሲታደጉ 40 ሰዎች ግን የደረሱበት አለመታወቁን አክለዋል። በአደጋው ​​ወቅት በጀልባው ላይ የነበሩት ተሳፋሪዎች አጠቃላይ ቁጥር እስካሁን አልታወቀም።

ጀልባው በዋነኝነት የሚያጓጉዘው ገበሬዎችን ሲሆን ገበሬዎቹ ምርቶቻቸው ለገበያ የሚያቀርቡበት መስመር ነው ። የአካባቢው ነዋሪዎች ጀልባዎቹ ብዙ ጊዜ ከአቅማቸው በላይ እንደሚጫኑ ይገልጻሉ።
❗️ ዩክሬን ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ  1,960 የሚጠጉ ወታደሮቿን ማጣቷን  የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዩክሬን እየተካሄደ ያለውን ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ አስመልክቶ በሚኒስቴሩ ዕለታዊ መግለጫ የተነሱ ሌሎች ቁልፍ ነጥቦች፡-

   የሩስያ አየር መከላከያ ሥርዓት አንድ ሂማርስ ሚሳኤል እና 36 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትተው ጥለዋል።

   የሩሲያ ጦር የዩክሬን መከላከያ ኢንተርፕራይዞች መሆናቸውን ካረጋገጠ በኋላ የሃይል ተቋማትን መትቷል።
🔔ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግስት ደብዳቤ ገጽ 8   ፦ ጥር 7 / 2012 ዓ፡ም የተጻፈ፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️Over 1,000 wounded in Lebanon explosions — Reuters
Audio
መልክአ ቅድስት ሐና የቅድስት ድንግል ማርያም እናት.
Audio
መልክአ ቅድስት ሥላሴ
Audio
በእንተ ሥላሴከ
Audio
መልክአ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ .
📌 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክን የሊቃውንት ጉባኤ ተቀዳሚ ዋና ሰብሳቢ የነበሩት ሊቁ አባታችን አለቃ አያሌው ታምሩ (ሰማዕት ዘእንበለደም) ላይ የተለያየ ያልተገባ ነቀፌታና በተሳሳተ ወሬ "ክህነት አልነበራቸውም፤ አይነስውር ስለነበሩ ክህነት የላቸውም ፤ በምን ስልጣናቸው ነው አጥፊውን የሚያወግዙ.... ወዘተ" እያሉ ያለምንም መረጃና ማስረጃ ሕዝቡን ለሚያደነቁሩ ደናቁርት ይህችን ደብዳቤ ደጋግመው እንዲያነቡ ይመከራሉ !!
Audio
የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫ
08-01-2017ዓ.ም

ክፍል ሀ
Audio
የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫ
08-01-2017 ዓ.ም

ክፍል ለ
🟢 🟡 🔴
መስከረም 9 | #ቅዱስ_ሚካኤል ሊቀ መላእክት የተአምር በዓሉ ነው።

ይህም እንዲህ ነው፦

የሰማይ ሠራዊት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚታዩ ድንቆችና ተአምራቶች ምክንያት ዮናናውያን ሰዎች ሰይጣናዊ ቅናትን ቀኑ።

ከመቅናታቸውም ብዛት የተነሣ በዚያ አካባቢ የሚወርደውን የወንዝ ውኃ በዚያች ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊመልሱትና ከሚጠብቃት መጋቢዋ ጋር በውኃ ስጥመት ሊአጠፏት ፈልገው መለሱት።

የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለቤተ ክርስቲያኑ መጋቢ ለናርጢኖስ ተገለጠለት። ወደርሱም ቀርቦ "ጽና አትፍራ" አለው።

ይህንን ብሎ በእጁ ውስጥ ባለ በትር ዐለቱን መታው። ዐለቱም ተሰንጥቆ እንደ በር ሆነ። የዚያ ወንዝ ውኃም በውስጡ አልፎ ሔደ።

ይህንንም ያዩ ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልንም አከበሩት።

ከዚያች ቀን እስከ ዛሬ የወንዙን ውኃ በዚያች በተሠነጠቀች ዐለት ውስጥ አልፎ ሲሔድ ያዩታል። ወደ መላእክት አለቃ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቶ አይቀርብም።

አምላከ ቅዱስ ሚካኤል የሀገራችንን እና የቤ/ክን ጠላቶችን ፈጥኖ ያርቅልን። ከመዓቱም ይሰውረን።

                   ◦🍀🌼🍀
T.me/Ewnet1Nat
ቱርክ የሶማሊያን የባህር ክልል ለመጠበቅ በቀጣዩ ወር የጦር መርከቦቿን ልትልክ ነው‼️

ቱርክ በመዲናዋ አንካራ በ6 ሚሊየን ዶላር ለሶማሊያ ኤምባሲ ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗ ተገልጿል

ቱርክ የሶማሊያን የባህር ክልል ከውጭ ከሚሰነዘር ስጋት ለመከላከል በመጪው ወር የጦር መርከቦቿን በአካባቢው ልታሰማራ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ 

በተያዘው የፈረንጆቹ አመት መጀመርያ የመከላከያ ስምምነትን የተፈራረሙት ሞቃዲሾ እና አንካራ በሁለትዮሽ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡

 ቱርክ በቀጣዩ ወር በሶማሊያ የባህር ክልል ታሰማረዋለች የተባለው የባህር ሀይልም የዚህ የመከላከያ ስምምነት አንድ አካል ነው፡፡

ወደ ቀጠናው የሚመጡት ሁለት አይነት መርከቦች ሲሆኑ አንድኛው አንካራ በአካባቢው ለምታደርገው የነዳጅ ማውጣት እንቅስቃሴ የሚያግዝ ሲሆን ሌሎቹ ድግሞ የሶማሊያን የባህር ክልል እና የነዳጅ አውጭ ቡድኑን የሚጠብቁ ናቸው ተብሏል፡፡

ቱርክ በሶማሊያ የሚሳኤል እና የጠፈር ሮኬት መሞከርያ ጣቢያ ልትገነባ ነው

የቱርክ የኢነርጂ ሚንስትር አልፓረሰላን ቤራክታር ባሳለፍነው ሳምንት ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን እንደተናገሩት ተርኪሽ ፔትሮሊየም የተባለው ኩባንያ እያንዳንዳቸው 5 ሺህ ኪሎሜተር ስኩየር በሚሸፍኑ ሶስት አካባቢዎች ላይ የነዳጅ ፍለጋ እንዲያደርግ ከሶማሊያ ፈቃድ ተሰጥቶታል፡፡
 
ሀገራቱ በገቡት ስምምነት መሰረትም እንደሚገኘው የነዳጅ መጠን ለመከፋፈል እና ላስፈለጋቸው አካል መሸጥ እንደሚችሉ ተጠቅሷል፡፡

 ይህን ተከትሎም ሁለት መካከለኛ የውግያ መርከቦች እና ሌሎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ አጋዥ መርከቦች አካባቢውን ለመቃኘት ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ ሚድልኢስት አይ ዘግቧል፡፡

ከጥቅምት ወር ጀምሮ እንደሚሰማሩ የተነገረላቸው እነዚህ መርከቦች ከባህር ላይ ሽፍቶች እንዲሁም ከምድር ሊሰነዘር የሚችል የትኛውንም ጥቃት የመመከት እና የቅኝት አገልግሎት በበቂ ሁኔታ መፈጸም የሚያስችል አቅም ያላቸው ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡

ከሶማሊያ ጋር ትብብሯን እያጠናከረች የምትገኘው ቱርክ በመዲናዋ አንካራ በ6 ሚሊየን ዶላር ለሶማሊያ ኤምባሲ ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗም ተዘግቧል።

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በወደብ ጉዳይ የተፈራረመችውን የመግባብያ ስምምነት ተከትሎ ሞቃዲሾ እና አንካራ የመከላከያ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ስምምነት ፈጽመዋል፡፡
  
አንካራ በሶማሊላንዱ ወደብ ምክንያት ቅራኔ ውስጥ የሚገኙትን አዲስአበባ እና ሞቃዲሾ ለማሸማገል ሁለት ያልተሳኩ ጥረቶችን ማድረጓ የሚታወስ ነው።
በሶማሌ ክልል ዋርዴር መስጂድ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ስድስት ሰዎች መደላቸው ተነገረ

በምሥራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን ዋርዴር ከተማ በአንድ መስጂድ ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው የአገር ሽማግሌ እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ሶማሊ ተናገሩ።

ማክሰኞ መስከረም 7/2017 ዓ.ም. በምሥራቃዊ የክልሉ ክፍል ውስጥ በሚገኘው ዶሎ ዞን ውስጥ የተፈጸመው ጥቃት ምክንያቱ፤ በአካባቢው ባሉ ጎሳዎች መካከል ከዚህ ቀደም ተከስቶ ከነበረ ግጭት ጋር ሳይያያዝ እንደማይቀር ተነግሯል።
አቂል ሞሐመድ ሞሐሙድ የተባሉት የአካባቢው የአገር ሽማግሌ ጥቃቱ መፈጸሙን እና ወጣቶቹ መገደላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

የተገደሉት ወጣቶች የሃይማኖት ተማሪዎች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የአገር ሽማግሌው “በስድስቱ ወጣቶች ላይ የተፈጸመው ድርጊት እጅግ ዘግናኝ ነው” በማለት ሐዘናቸውን ገልጸዋል።

ወጣቶቹ የተገደሉት ኩጂር በተባለው መስጂድ ውስጥ ለሶላት እየተዘጋጁ ሳለ መሆኑን የገለጹት የአገር ሽማግሌው፤ “ታጣቂዎቹ በአነስ ባለ መኪና ወደ መስጂዱ መጥተው በልጆቹ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል” ብለዋል።

በጥቃቱ መስጂድ ውስጥ የተገደሉት ስድስቱ ወጣቶች ወንዶች የቀብር ሥነ ሥርዓት ረቡዕ ዕለት እዚያው ዋርዴር ከተማ ውስጥ መፈጸሙን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
2024/09/22 20:23:39
Back to Top
HTML Embed Code: