Telegram Web Link
👆👆👆👆👆👆
"- 5 - በታላቁ የቁጣ ፍሰት በመላው ዓለም ያለ ማናቸውም የትራንስፖርት / አውሮፕላን ፣ መርከብ ፣ መኪና የእንስሳም ማጓጓዣ ሁሉ / አገልግሎት በሙሉ ይቆማል ፡፡
#ቢንቀሳቀስም_ወዲያው_ይጠረጋል ፡፡ ማናቸውም ማምረቻዎች ፣ ፋብሪካዎች አገልግሎት ሰጪዎች የጤና ተቋሞች የግልም የመንግስትም ድርጅቶች መሥሪያ ቤቶች አለም አቀፍ ተቋሞች ድርጅቶች በሙሉ ይከረቸማሉ ፡፡ የሚጠፉትም ይጠፋሉ ፡፡ ለመንቀሳቀስም ለመስራትም ለሁሉም በመላው ዓለም የፀናው ያለመንቀሳቀስ ትእዛዝ ሲነሳ ብቻ ነው ለመንቀሳቀስ የሚቻለው ፡፡ ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት በሚሰጥ ጊዜያዊም ሆነ ቋሚ የፈቃድ ትእዛዝ ብቻ ነው ለመንቀሳቀስ የሚቻለው ፡፡"

🔐 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት 9ኛ መልዕክት (የአስቸኳይ አዋጁ ክፍል) ገጽ 61 - ተጻፈ ታሕሳስ 21/2013ዓ.ም
🟢🟡🔴
ታኅሣሥ 14 | #ዕለተ_ብርሃን

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስንና የቅዱስ ያሬድን አስተምህሮ መሠረት አድርጋ ይህንን ዕለት (ታኅሣሥ 14ን) "ዕለተ-ብርሃን"  ሳምንቱን (ከታኅሣሥ 14-20 ያለውን) ደግሞ "ሰሙነ-ብርሃን" ስትል ታስባለች።

"ብርሃን" በቁሙ የእግዚአብሔር ስሙ አንድም የባሕርይ ገንዘቡ ነው። "እግዚአብሔር ብርሃን ነውና። ጨለማም በእርሱ ዘንድ የለችምና።" (ዮሐ. 1፥4)

● በዚህ ዕለት "ብርሃን" በሚል መነሻ ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ታስተምራለች፦

፩. እግዚአብሔር ብርሃን መሆኑን (ዮሐ. 1፥5)

፪. አምላካችን በመጀመሪያው የፍጥረት ቀን (በዕለተ እሑድ) ዲያብሎስ ቅዱሳን መላእክትን ሲረብሽ "ለይኩን ብርሃን" ብሎ ብርሃንን መፍጠሩን፣ (ዘፍ. 1:2, አክሲማሮስ)

፫. ነቢያት አበው በጨለማው ዓለም ሆነው መከራ ሲበዛባቸው "ፈኑ ብርሃነከ - ብርሃንህን ላክልን" እያሉ መጮሃቸውን፣ (መዝ. 42፥3)

፬. ጩኸታቸውን የሰማ ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ (እውነተኛው ብርሃን) ወደዚህ ዓለም መምጣቱን፣ (ሉቃ. 1፥26)

፭. "እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ" ሲል የባሕርይ ብርሃንነቱን እንደ ነገረን፣ (ዮሐ. 9፥5)

፮. ብርሃነ መለኮቱን በገሃድ መግለጡን፣ (ማቴ. 17፥1)

፯. ብርሃን የሆነችውን ሕግ ወንጌልን እንደ ሠራልን፣ (1ዮሐ. 2፥9)

፰. ድንግል እመቤታችን ብርሃን፣ የብርሃንም እናቱ መሆኗን፣ (ሉቃ. 1፥26፣ ራዕ. 12፥1)

፱. ቅዱሳኑ ብርሃን መባላቸውን፣ (ማቴ. 5:14)

፲. እኛ በሰው ፊት ሁሉ እንድናበራ መታዘዛችን (ማቴ. 5፥16) ሁሉ ይታሰባል


ክርስቶስ ብርሃን ዘአሰሰልከ ጽልመተ፥
ላዕለ ኪሩቤል ነቢረከ ዘትሬኢ ቀላያተ፥
ስቡሕኒ ወልዑል አንተ

(መልክአ ኢየሱስ)
              ◦

www.tg-me.com/T.me/Ewnet1Nat
🟢 🟡 🔴

ታኅሣሥ 15
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በዚች ቀን ያለ ደም መፍሰስ ሰማዕት የሆነ የአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዐረፈ።

ይህ ቅዱስ ንጉሡ ድርዳጥስ ስለሃይማኖቱ በጉድጓድ ጥሎት፣ በጉድጓዱ ውስጥም ቀሩንና ሐሩሩን ታግሦ ለ15 ዓመታት ቆይቷል። ምግቡንም አንዲት ቅድስት አሮጊት በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ሁል ጊዜ ታመጣለት ነበር።

ኋላም ንጉሡ ከሠራዊቱ ጋር አብዶ ወደ አውሬነት ስለተቀየረ ቅዱሱን ከጉድጓድ አውጥተዉት ሁሉንም ፈውሷቸዋል። ኋላም ሊቀ ጳጳሳት ሆኖ የአርማንያን ሰዎች የክርስትና ጥምቀትን አጥምቋቸዋል።

ወደ ዕብራውያን 12:1-2
"እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምሥክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፣ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፣ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፣ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ። እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።"

አምላከ ቅዱሳን የቅዱሳኑን ልብና ቆራጥነት ያድለን!
" የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ ተራራው የመሰንጠቅ እና የመደርመስ ምልክት አሳይቷል " - አታላይ አየለ (ፕ/ር)

🚨" የመሬት መንቀጥቀጡ የፍንዳታ ድምጽ ያስከተለ እና ጭስ የታየበት ነው " - አቶ አብዶ አሊ
ቄሱ በአክራሪ ሙስሊሞች አንገታቸውን ተቀልተው ተገደሉ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መሬት መንቀጥቀጡ በፈንታሌ ተራራ ፍንዳታ አስከትሏል

በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
በሞዛቢክ ዝናብ በቀላቀለው የአውሎ ነፋስ አደጋ የሟቾች ቁጥር 120 ደረሰ።

በሞዛቢክ ዝናብ በቀላቀለ የአውሎ ነፋስ አደጋ የሟቾች ቁጥር 120 መድረሱን የሀገሪቱ የመንግስት ባለስልጣነት አስታውቀዋል፡፡

በሃገሪቱ ሰሜናዊ ከፍል የተከሰተው እና ሳይክሎን ችዶ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የተፈጥሮ አደጋ፤ 900 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱም ተጠቅሷል፡፡

በሰሜናዊ ሞዛምቢክ ካቦ ዴልጋዶ፣ ናምፑላ እና ኒያሳ በተባሉ ግዛቶች የሚኖሩ ከ700 ሺህ በላይ ሰዎች አደጋው ተፅዕኖ አንዳደረሰባቸውም ተነግሯል፡፡

የሀገሪቱ አደጋ መከላከል ብሔራዊ ተቋም፤ በአደጋው 110 ሺህ መኖሪያ ቤቶች፣ 48 ሆስፒታሎች፣ 186 የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች፣ 9 የውሃ ማስተላለፊያ ቱቦዎች እና 171 ጀልባዎች መውደማቸውን ገልጿል፡፡

ሳይክሎን ችዶ የተሰኘው ይህ የተፈጥሮ አደጋ በሰዓት 200 ኪሎ ሜትር እንደሚያካልል ኤፍፒ የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

በደቡብ ምስራቅ አፍሪካ ከተከሰቱና ብዙ ውድመት ካስከተሉ ውሽንፈሮች በ4 ደረጃ ላይ የተቀመጠው ይህ አደጋ፤ በቀን ብቻ እስከ 250 ሚሊ ሜትር ልኬት ያለውን ዝናብ ቀላቅሎ እንደሚዘንብም ነው የተለፀው፡፡
ቡግና‼️
ቡግና ወረዳ ከ79 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ይሻሉ‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ አገዛዙ ሆን ብሎ ባባሰው ድርቅና የምግብ እጥረት ምክንያት 79, 418 ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለ።

በወረዳው ከ10 ሺህ በላይ እናቶችና ሕፃናት በከፋተኛ የምግብ እጥረት ምክንያት ጉዳት እንደደረሰባቸዉ የወረዳዉ ጤና ጽሕፈት ቤት አሳውቋል።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ኢትዮጵያዊ የተክለሃይማኖት ወዳጅ🇨🇬🇨🇬🇨🇬)
Audio
ማሳሰቢያ ከራዕይ ዮሐንስ 20
15/04/2017 ዓ.ም
🟢🟡🔴
ታኅሣሥ 16 | #_ቅድስት_ሉሲያ ሰማዕት ሆነች።

🌿 ቅድስት ሉሲያ ወይም ሉሲ (283-304) በሲራከስ (Syracuse) የተወለደችና በዲዮቅልጢያኖስ ዘመነ ሰማዕታት ወቅት የሰማዕትነት አክሊልን የተቀበለች ቅድስት ድንግል ሰማዕት ነች፡፡

🌿 ከሀብታም ቤተሰብ የተገኘች ልጅ ስትሆን አባቷ በ5 ዓመቷ ሞቷል። ከግሪካዊት እናቷ ጋር በሲራከስ (ሲሲሊ፥ ጣልያን) ኖራለች።

🌿 ሉሲያ የሚለው ቃል ከላቲኑ "ሉሲያስ" ወይም "ለክስ" ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ "ብርሃን" ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በትውፊት ቅድስት ሉሲያ ሰማዕትነት ከመቀበሏ በፊት ዓይኖቿን እንደወጡ ካለው ትውፊት ጋር ይገናዘባል፡፡

🌿 አንዳንዶች በሲራከስ ገዢ እንደወጣ ቢናገሩም በትውፊት ግን ራሷ በራሷ ዓይኗን እንዳወጣች እንረዳለን። ይህን በዓይኗ ውበት አድናቆት ሲበዛባት ለሌሎች መሰናክል ከሚሆኑ ብላ በገዛ እጆቿ አውጥታቸዋለች።

🌿 ታሪኳ ጠፍቶ ከዘመናት በኋላ ቅዱስ መቃብሯ ሲገኝ ዓይኖቿ ሳይበሰብሱ በደኅና በተአምር ተገኝተዋል።

🌿 ይህንንም ተከትሎ ስትሣል በሰሀን ላይ ዓይኖችን ይዛ ትሣላለች፤ ምሳሌነቱም ለዓይን ሕሙማን ረዳት እና ጠባቂነቷን ያመለክታል፡፡

🌿 በሲራከስ ገዢ አንገቷን በሰይፍ ተቆርጣ ታኅሣሥ 16 ቀን ሰማዕት ሆነች። (በሌሎች ሀገራት ደሞ ታኅሣሥ 4 ቀን ላይ ያከብሯታል።)
🌿

#ቅዱስ_አቡነ_መርቆሬዎስ

በውስጡ አጋንንት ያደሩበት ቁመቱ 170 ክንድ ወርዱ 9 ክንድ ከስንዝር የሆነ ሰይጣን ያደረበት ዘንዶ ቢመጣባቸው በጸሎት ወደ ፈጣሪያቸው አመልክተው ቅዱስ ሚካኤል በሰጣቸው መስቀል ዘንዶውን የገደሉት አቡነ መርቆሬዎስ ዘደብረ ድማኅ ዕረፍታቸው ነው።

እኚህም የአቡነ ኤዎስጣቴዎስ ለመንፈስ ልጅ ናቸው።

http://www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Forwarded from Biruk
ሰበር ዜና!
የኢትዮጵያ ወታደር በትናንትናው ዕለት በሶማሊያ ላይ ጥቃት ፈፀመ!
በጥቃቱ በርካታ የሶማሊያ እና በቁጥር ጥቂት የግብፅ ወታደሮችም መገደላቸው ተሰምቷል።
በተያያዘ መረጃ ባለፈው ሳምንት ሶማሌ ላንድ የሶማሌ ክልልን ህዝብ መጨፍጨፏን ዘግበን ነበር።
ዛሬም መከላከያ ወደ ቦታው በመግባቱ ጦርነቱ ተባብሶ ቀጥሎ ሳምንታትን አስቆጥሯል።
በርካታ የሶማሌ ክልል ጤና ጣቢያወች እና ሆስፒታሎች በቁስለኛ ተጥለቅልቀዋል!
ጦርነቱ ቀጥሏል!
ግዮን-ፕረስ
Audio
🇨🇬 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ፍርድ አዘል መግለጫ
ክፍል ሀ
16/04/2017
Audio
🇨🇬 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ፍርድ አዘል መግለጫ
ክፍል ለ
16/04/2017
Audio
🇨🇬 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ፍርድ አዘል መግለጫ
ክፍል ሐ
16/04/2017
2024/12/26 00:11:29
Back to Top
HTML Embed Code: