Telegram Web Link
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
🟢 🟡 🔴
ታኅሣሥ 8 ልደታቸው የሆኑ፦

🍀 #አባ_ሙሴ_ዘድባ ጽንሰታቸውን ቅዱስ ሩፋኤል መጋቢት 8 ቀን ሲያበሥር ልደታቸውን ደግሞ ቅዱስ ገብርኤል ታኅሣሥ 8 ቀን የመወለዳቸውን ብሥራት ተናግሯል፡፡ ሲወለዱ ሚካኤል ወገብርኤል በሰው አምሳል ተገልጠው "የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ" ብለው ስም አወጡላቸው።

የአቡነ ሙሴ አባታቸው ዮስጦስ ለሐዋርያው ናትናኤል አጎቱ ነው፡፡ እናታቸው ጵርስቅላ ጌታችን በሠርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን ወደ ወይን የለወጠለት የዶኪማስ ልጅ ናት።

በተወለዱም በ40ኛ ቀናቸው ከተጠመቁ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል አቅፎ ይዟቸው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ አቁርቧቸዋል፡፡


🍀 #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ አባታቸው መልአከ ምክሩ እናቱ ወለተ ማርያም ይባላሉ፡፡ የተወለዱበት ልዩ ቦታው ወሎ ክፍለ ሀገር ዳውንት ነው፡፡

በተወለዱ ዕለት ተነሥተው በእግራቸው ቆመው ሦስት ጊዜ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል፡፡

🍀 #ቅዱስ_አባ_ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው።

የሙሽራው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ አጎት ናቸው። በድሏቸው ራሱን ያጠፋውን መነኰስ እና ከ700 በላይ የሆኑ ዐመፀኛ መነኰሳትን ለዓመታት አልቅሰው ከሲዖል ያስወጡ ደግነታቸው የበዛ አባት ናቸው።

🍀 #ቅድስት_እንባ_መሪና በዘመነ ጻድቃን በምድረ ግብጽ ተወለደች፣

ከአባቷ ጋር መንና ወደ ወንዶች ገዳም የገባች፣ ወንድ መስላ የወንዶችን ቀኖና በምንኩስና የተቀበለች፣ ያለ አበሳዋ (ወንድ መስላቸው) "ዝሙት ሠርተሻል" ተብላ ወደ በርሃ የተባረረች፣ ያልወለደችውን ልጅ ያለ በደሏ ተከሳ በትዕግሥት ያሳደገች፣

◦ ያለ ምግብና ውሃ ለ3 ዓመታት የተሰቃየች፣ ብርድና ፀሐይ የተፈራረቀባትና፣ ስታርፍ ክብሯ የተገለጠላት ቡርክት እናት ናት።

በዚህች ቀን ዕረፍታቸውን የምናከብርላቸው፦

🌿 #ቅዱስ_አባ_ሳሙኤል_ዘቀልሞን በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በግብጽ ደብረ ቀልሞን የነበሩ፣ ከዓበይት ጻድቃን የሚቆጠሩ፣

ትእዛዝ ያላከበረ መልአክ አማልደው ክንፈ ረድኤቱ እንዲመለስ ያደረጉ፣ መልአክን እንኳ ማማለድ የቻሉ አባት ናቸው።

🌿 #ቅዱስ_አባ_ዮሐንስ_ዘደማስቆ በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን በሶርያ ደማስቆ የተነሣ ሲሆን፣

ስለ ሥዕለ አድኅኖ ክብር ከነገሥታቱ ዘንድ የተዋጋ፣ በጦማር (በደብዳቤ) ለዓለም የሰበከ፣ ስለ እመቤታችን ተናገርክ ብለው ቀኝ እጁን የቆረጡት፣ እመ ብርሃን ግን እንደ ገና የቀጠለችለት፣

◦ ከ10ሺ በላይ ድርሳናትን የደረሰ፣ ከዐበይት ሊቃውንት የሚቆጠር ቅዱስ አባት ነው።

🌿 #አቡነ_ተክለ_አልፋ በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢትዮጵያ የተነሡ ሲሆኑ፣

ደብረ ድማሕን / ዲማን (ጎጃም) የመሠረቱ፣ በፍጹም ተጋድሎ የኖሩ፣ ምድረ ጎጃምን በስብከተ ወንጌል ያበሩ፣

◦ በሊቅነታቸው የተመሠከረላቸው፣ #መልክአ_ኢየሱስን እንደ ደረሱ የሚነገርላቸው


◦ ብዙ ተአምራትን የሠሩ (ዛሬም ድረስ የሚሠሩ)፣ ለሃገራችን ትምክህት የሆኑ ታላቅ ሐዋርያዊ አባት ናቸው።

🌿 #አቡነ_ገብረ_ማርያም በ16ኛው መቶ ክ/ዘ በምድረ ኢትዮጵያ የተወለደ፣ ስም አጠራሩ ያማረ ሲሆን፣

◦ ዛሬ እናንተና እኔ ለምናደርገው የቅዱሳን መታሰቢያ መሠረት የጣለ፣ በዓመቱ የሚከበሩ ሁሉን ቅዱሳን የሚዘክር፣ 365ቱን ቀናት በምጽዋት የተጠመደ፣ የነዳያን አባት የሆነ፣

◦ በዓፄ ልብነ ድንግል ግራኝ አህመድ መምጣቱን ሲሰማ ያልደነገጠ፣

ሃብት ንብረቱን ለነዳያን አካፍሎ፣ ነጭ ልብስ ለብሶ ገዳዮቹን የጠበቀ፣ የግራኝ ወታደሮች የሰየፉትና ሞገስ የሆነን አባት ነው።

🌿 #ቅዱስ_አባ_ኤሲ በዘመነ ሰማዕታት በግብጽ (ቡጺር) ከደጋግ ክርስቲያኖች ተወለደ።

◦ ከልጅነቱ ጀምሮ ዓለምን የናቀ፣ በወጣትነቱ የነዳያንና የእሥረኞች አባት የተባለ፣ ቅድስት ቴክላ የተባለችና እመቤታችን የምታነጋግራት እኅት  የነበረችው፣

◦ ቅዱስ ጳውሎስ ከሚባል ባልንጀራው ጋር ሰማዕታትን በመንከባከብ ያገለገለ፣ በመንፈሳዊ ቅናት ከጳውሎስና ቴክላ ጋር ለሰማዕትነት የቀረበ፣ እጅግ ብዙ መከራዎቸን የተቀበለ፣

ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ሱርያል ወደ ሰማይ አሳርጎ ክብረ ቅዱሳንን በተለይም የሰማዕታትን ክብርና መታሰቢያቸውን የሚያደርጉ ሰዎች የሚጠብቃቸውን ክብር ያሳየው ሰማዕት ነው።

[ቅዱስ ሱርያል በገድለ ሰማዕታትም ላይ እንደተጠቀሰው የሰማዕታት ረዳትና አዳኝም ነው።]

🌿 #ቅድስት_በርባራ እና #ቅድስት_ዮልያናም ሰማዕትነትን ተቀበሉ።
                
T.me/Ewnet1Nat
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️❗️❗️አስደንጋጭ ቪዲዮ፦ ከፍተኛ የሩሲያ ጄኔራል በቦንብ ጥቃት ተገደሉ

በርካታ የዩክሬን የቴሌግራም ቻናሎች የሩሲያ የራዲዮሎጂካል፣ ኬሚካል እና ባዮሎጂካል ኃይል አዛዥ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ የተገደሉበትን የሽብር ጥቃት የሚያሳይ ቪዲዮ በተመሳሳይ ጊዜ ለቀዋል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
A 7.4 magnitude earthquake hits Vanuatu.

አስደንጋጩ 7.4 ማግኒትዩት የመሬት መንቀጥቀት

በቫኑአቱ ዋና ከተማው ፖርት ቪላ በስደንጋጭ የሆነ እና በሬክተር ስኬል 7.4 ማግኒትዩት የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀት ተከስቷል።

በመሬት መንቀጥቀጡ በሰው ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ በርካታ ህንጻዎችም ፈራርሰዋል።
🇨🇬🇨🇬
#_የአባት_ምክር_፲፫ {ለኢ.ዓ.ብ ቤተሰብ ብቻ}
▱ ▰ ▱
ይሄን ነው ተስፋ የምናደርገው፥ ወገኖቼ።

እኛ ድሆች ነን። እግዚአብሔር ይመስገን!
እኛ የምንራብ ነን፤ እግዚአብሔር አኹንም ይመስገን!
እኛ በዚህ ክፉ ዘመን የምናለቅስ፣ የምንጨነቅ፣ የምንጠበብ ነን ስለ ጥፋቱ፤ እግዚአብሔር ይመስገን!

°[ሰዎች ስለሰው ልጅ ሲጠሏችሁ፣ ሲለይዋችሁም፣ ሲነቅፏችሁም፣ ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ ፥ ብፁዓን ናችሁ።]°

አዎን፧ እግዚአብሔር ይመስገን!

ቢያሞግሱን "አዎ ጎበዞች! እናንተ... (ቢሉን)" ያኔ ነበር እኛ መውደቃችንን የምናውቀው። ዛሬ ግን እግዚአብሔር ይመስገንአሳሳች እንባላለን። መናፍቅ እንባላለን። ክፉዎች እንባላለን። ያልተሰጠን ስም የለም። የማይሳደድ የማይነቀፍ የማይተች የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰብ የለም።

ኹላችንም እውነቱን ስለተናገርን ይሄ ሁሉ ስም ተሰጥቶናል። አኹንም እግዚአብሔር ደጋግሞ ይመስገን፤ ይክበር! እውነቱን ይሄ ስለሆነ። እውነቱ ላይ ስለቆምን ይሄን ስም አትርፈናል። አሜን፥ ክብራችን ይሄ ነው።

ከቤ/ክ ያባርራሉ። ቅጥራችን እንዳትደርሱ ይላሉ። በእየመድረኩ ላይ የመጀመርያ የአፋቸው መክፈቻ እኛ ነን። የትችታቸው ዱላ ኹሉ እኛ ላይ ነው። አኹንም እግዚአብሔር ይመስገን፤ ይበርቱ።

(ለ)እኛ ማረጋገጫዎቻችን ናቸው። እኛ ትክክለኛ ቦታ ላይ ለመቆማችን፣ ወገኖቼ፥ በትክክል ለመጓዛችን፣ በብርሃን ለመመላለሳችን ማረጋገጫዎቻችን ሰነዶቻችን እነሱ ዛሬ የሚፈጽሙት ተግባር ነው።
~
🇨🇬 | የኢ.ዓ.ብ የሉቃስ ወንጌል ትምህርት ፬ | 🇨🇬
| 🕛 ▸ ከ 65፡08 - 67፡58 |
~ ~ ~
www.tg-me.com/Ewnet1Nat 🇨🇬
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930 🇨🇬
የሽርካ ወረዳ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅን ጨምሮ 40 ሰዎች ታግተው መወሰዳቸው ታወቀ

ታህሳስት 5 ቀን ማለዳ ላይ በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ጋላማ ተብሎ በሚጠራው የመንግስት ጥብቅ ደን መሐል የሽርካ ወረዳ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ ቀሲስ ታመነን ጨምሮ 40 ሰዎች ከመኪና ወሰጥ ተለይተዉ ታግተው እንደተወሰዱ ሰምተናል።

ከዚህ በተጨማሪም እዚያው ወረዳ ሰንጎ ያያ በሚባል ቀበሌ ውስጥ 9 አርሶ አደሮች በአጨዳ ላይ እያሉ ታግተው መወሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
📒 የአምኃ ኢየሱስ ገብረ ዮሐንስ ለአራተኛ ጊዜ አጭር የጽሑፍ መልእክት። በተለይ ደግሞ ለሞኙ አማራና ለወሬኛው ክርስቲያን ሁሉ።

🇨🇬 «የማይቃወመን ርሱ ከእኛ ጋራ ነውና።»
የማርቆስ ወንጌል ፱ ፥ ፵

📌 ሙሉውን "⚡️INSTANT VIEW" በሚለው ከፍተው በማስተዋልና በጥንቃቄ ያንብቡ !
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
የአምኃ_ኢየሱስ_ገብረ_ዮሐንስ_ለአራተኛ_ጊዜ_አጭር_የጽሑፍ_መልእክት.pdf
881.4 KB
🇨🇬 የአምኃ ኢየሱስ ገብረ ዮሐንስ ለአራተኛ ጊዜ አጭር የጽሑፍ መልእክት፡፡ በተለይ ደግሞ ለሞኙ አማራና ለወሬኛው ክርስቲያን ሁሉ።
📌 ሚያዝያ ፫ — ፪ ሺ ፲፫ዓ.ም |PDF
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ኢትዮጵያዊው)
📌« ከፓትርያርኩ ከአባ ጳውሎስ ጋር አለመግባባት ሳይሆን ፍጹም ልዩነት አለን። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከካቶሊክ እምነት የተለየችው በ 444 ዓ. ም. ( በ451 እ.ኤ.እ) ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ 1600 ዓመት በውግዘት ተለያይተናል። የኢትዮጵያ ጳጳሳት፥ ፓትርያርኮች፥ የሃይማኖት ሊቃውንትና ሕዝበ ክርስቲያን ይህን ጠብቀው ቆይተው ኖረዋል።

ማንም ፓትሪያርክ ሲሾም ይህንን ሥርዓት ጠብቆ ሊኖር በሥጋው በደሙ ይምላል። ፓትርያርኩ ሠርተህ አትብላ አላሉኝም የሃይማኖት ጉዳይ አትንካ ነው ያሉኝ። እኔ ደግሞ በሃይማኖት ጉዳይ ዝም ብሎ መመልከት፥ በቸልታ ማለፍ አልችልም። ኢትዮጵያዊነቴ የሚቀበለው አይደለም። ይህም በመሆኑ ነው ለውግዘት የደረስኩት።
»

🇨🇬 ክቡር ሰማዕት ዘእንበለ ደም አለቃ አያሌው ታምሩ ዛሬም ይናገራሉ ! አባ ጳውሎስ የተከሰሱበትን ወንጀል የዛሬው ጳጳሳት ከአባ ጳውሎስ በላይ አስፍተውና አብዝተው ሲፈጽሙት እያየን ነውና የሚሰማ ይስማ! የማይሰማ አይስማ!!!
www.tg-me.com/AlphaOmega930
2025/01/08 04:58:41
Back to Top
HTML Embed Code: