Telegram Web Link
#_አኹን_ስንት_ሰዓት_ነው?

አባ ዮስጦስ ዝምተኛው መነኩሴ በዘመናቸው "ስንት ሰዓት ነው?" እያሉ አብዝተው ይጠይቁ ነበር ። ብዙዎችም ግራ ይገባቸው ነበር።

ሲቆይ ግን ሁሉም ገባቸው። ስንት ሰዓት ነው ማለታቸው "በዚኽ ምድር ለመኖር የቀረን ስንት ሰዓት ነው?" ለማለት ፈልገው ነበር። "ቶሎ ብላችሁ፥ ጊዜ ሳታጠፉ ንስሐ ግቡ" ሲሉ ነበር።

አስቡት በአኹኑ ሰዓት ኾነን ብዙ ሰው እየሞተ ነው፤ እየተወለደም ነው። የሞት መምጫው ቀኑ አይታወቅም። አባ ዮስጦስ ግን የሞት መምጫውን በቀን ሳይሆን በሰዓታት ነበር የሚጠብቁት ።

× × ×
ስለዚኽ ለእስራኤል ቤት እንዲኽ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲኽ ይላል፦ #_ንስሐ_ግቡ_ከጣኦቶቻችሁም_ተመለሱ_ፊታችሁንም_ከርኵሰት_ኹሉ_መልሱ
[ ሕዝ. ፲፬ ፥ ፮ ]

× × ×
"በተወደደ ሰዓት ሰማዉኽ፤ በመዳንም ቀን ረዳዉኽ" ይላልና እነሆ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው። እነሆ #_የመዳን_ቀን_አሁን_ነው
[ ፪ ቆሮ ፮ ፥ ፪ ]

#_እና_ወገኖቼ_አኹን_ስንት_ሰዓት_ነው?
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዩጋንዳ ሴቶችን ለይቶ የሚያጠቃ “አስደናሽ” ወረርሽኝ ተከሰተ

በኡጋንዳ ምንነቱ ያልታወቀ እና ሴቶችን ብቻ ላይቶ የሚያጠቃ “የሚያስደንስ ወረርሽኝ” መከሰቱ ተሰምቷል።

ኡጋንዳውያን “ዲንጋ ዲንጋ” እንደ ዳንስ መንቀሳቀስ ሲሉ የሰየሙት ወረርሽኙ እስካሁን በ300 ሴቶች ላይ መከሰቱንም የጤና ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ወረርሽኙ ቡንዲቡግዮ በተባለ አካባቢ የተከሰተ ሲሆን፤ ከፍተኛ ትኩሳት እና መራመድ አለመቻልም የበሽታው ምልክቶች መሆናቸውን የጤና ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ኬይ ክርቶፈር ገልጸዋል።
Via_dagu
🟢🟡🔴
ታኅሣሥ 12 | የሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ሚካኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ያዳነበት መታሰቢያ በዓሉ ነው።

ይንኩት👇
ሠለስቱ ደቂቅን ያዳናቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው ወይስ ቅዱስ ራጉኤል ወይስ ቅዱስ ገብርኤል?
🍀

#መልአኩ_ቅዱስ_ሚካኤል የሁልጊዜ ጠባቂው የሆናቸው፣ በሁሉ ነገር ይራዳቸውና እንደ ጓደኛም ያማክራቸው የነበሩት #አባ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ዕረፍታቸው ነው።

ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አቡነ ሳሙኤል ዘዋሊ የተወለዱት በ1295 ዓ.ም በምድረ አክሱም ነው። ወላጆቻቸውም እስጢፋኖስና ዓመተ ማርያም ይባላሉ።

የዘር ሐረጋቸው ከካህናት ወገን ነውና ገና በልጅነት ምሥጢራተ ሃይማኖትን ጠጥተዋል። ወደ አቡነ መድኀኒነ እግዚእ ሔደው በእሳቸው እጅ መንኩሰዋል። ዋልድባ ገዳምም ጠፍታ ነበርና እንደገና አቀኗት።

አቡነ ሳሙኤል ከድንግል እመቤታችን ጋር ልዩ ፍቅር ነበራቸው። ዘወትር ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን በተመስጦ ሲያደርሱላት ከመሬት ክንድ ከፍ ብለው ይንሳፈፉ ነበር። ተከታዮቻቸው ሲርባቸውም ውሃውን በቅዳሴ ማርያም ነጭ ኅብስት ያደርጉት ነበር።

እመ ብርሃንም ስለ ፍቅር ነጭ እንቁ ሰጠቻቸው። ሰማያዊ ኅብስትን መገበቻቸው። ንጹሕ ዕጣንንም አበረከተችላቸው። ለ12 ዓመታትም ከሰማይ ካህናት ጋር አጠኑ። በ100 ዓመታቸው ዐረፉ።

መድኃኔዓለም የገባላቸው ቃልኪዳን

"እነሆ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የተካከለ መቀመጫህንና አክሊልህን አዘጋጀሁልህ፣ ዕድል ዕጣህም ከአሥራ ሁለቱ ቅዱሳን ሐዋርያቶቼ ጋር ነው።

ዐፅምህ በተቀበረበት፣ የገድልህ መጽሐፍ በተነበበት፣ መታሰቢያህ በተደረገበት፣ ሥፍራ ሁሉ ምሕረትና ድኅነት ይሁን። በጸሎትህ የሚታመነውን፣ መታሰቢያህን የሚያደርገውን ሁሉ ለአንተ አሥራት ሰጥቼሃለሁ።"
🍀

የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ልጅ #ዳግማዊ_ቂርቆስ ወደ ብሔረ ብፁዓን የገባበት በዓሉ ነው።

T.me/Ewnet1Nat
ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_ፍርድ_አዘል_መግለጫ.pdf
1.2 MB
🇨🇬 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ፍርድ አዘል መግለጫ
21/02/2017 ዓ.ም በድምፅ የተላለፈ
በቀን 12/04/2017 ዓ.ም ወደ ጽሁፍ የተቀየረ ።
🟢🟡🔴
ታኅሣሥ 13 | የመላእክት አለቃ #የከበረ_መልአክ_የሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱ ነው። እርሱም ከመላእክት አለቆች ሦስተኛ የሆነ ነው።

ይኸውም ከእስክንድርያ ውጭ በደሴት የታነፀች ቤተ ክርስቲያኑ በከበረ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምር የተገለጸባት የከበረችበት ነው።

ያቺ ደሴት በታላቅ አንበሪ ጀርባ ላይ የቆመች ናትና የሰዎች ብዛትም በከበደው ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያፈርሳት ዘንድ ሰይጣን አነሣሣው። ወደ ክብር ባለቤት እግዚአብሔርም በከበረ መልአክ ሩፋኤል ስም ጮኹ።

ያን ጊዜ ይህ የከበረ ሩፋኤል ያንን አንበሪ በጦሩ ወግቶ እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር አዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጽ ጸጥ ብለህ ቁም። አንበሪውም ጸጥ ብሎ ቆመ አልታወከም። በውስጧም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለሕሙማንም ፈውስ ሆነ።
- 🍀 -

● ቆቅ ሲመገቡ ያዩአቸው ሰዎች ቢያሟቸው አብስለው በገበታ ላይ ለምግብነት ያቀረቧቸውን ቆቆች ሦስት ጊዜ እፍ ቢሉባቸው ቆቆቹ ሕይወት ዘርተው በረው ወደ ጫካ እንዲሄዱ ያደረጉት ታላቁ አባት #አባ_መቃርስ ገዳማዊ ዓመታዊ የዕርገታቸው መታሰቢያ በዓል ነው፡፡

#አባ_ሚካኤል ዘደብረ ቀልሞን ዕረፍታቸው ነው፡፡

● በሰይጣን ላይ የተራቀቁበት ተጋዳይ መነኮስ
#አቡነ_አብራኮስ ዕረፍታቸው ነው፡፡

● ዳግመኛም እስላሞች አንገቱን ሰይፈው በሰማዕትነት የገደሉት
#ቅዱስ_በጽንፍርዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡

T.me/Ewnet1Nat
አይጋጩም፣ አይፋጩም።

ቢጋጩና ቢፋጩ እንኳን አይለያዩም።

ቢለያዪ ግን ከኹለት አንዱ ከዚያ በኋላ የእሱ አገልጋይ አይደሉም ።
#ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫ
#ምክርና ተግሳጽ
#ለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ትጉኃን መማክርቶች በሙሉ!
አንዳንድ፡የፅዋ፡ማህበር አመራሮች፡የትጉኃን፡ መማክርቶች፡የተሰጣችሁን፡ ኃላፊነት፡በአግባቡ፡እንድትወጡ፡እንመክራለን፡ በእምነት፡መመሳሰል፡የለም ከማያምኑ፡ጋር፡በማይመች፡ አካሄድ፡አትጠመዱ፡እንጅ፡አብራችሁ፡ተመሳሰሉ፡የሚል፡ቃል የለም፡ብርሃን፡ከጨለማ፡ጋር ህብረት፡የለውም፡ስለዚህ፡ በአመራር፡ላይ፡ያላችሁ፡ብርሃን፡ሁናችሁ፡መታየት፡እንጅ ለሌሉች፡ተመሳስላችሁ፡ተቸችላችሁ፡ሂዱ፡የሚል፡ምክር፡ የሚሰጥ፡እረኛ፡ካለ፡ይኸ፡እረኛ፡ ሳይሆን፡የተሳሳተ፡ሰው፡ነው በአስቸኳይ፡ንስሐ፡ገብቶ፡አቋሙን፡ ሊፈትሽ ፡ይገበዋል በእምነት ፡ድርድር ፡የለም መመሳሰል፡ የለም፡ የተኩላ፡ እረኛና ፡የቀበሮ፡ እረኛ ፡ሁለቱም ተኩላ ፡ናቸው ፡ቀበሮ ፡ናቸው፡ ሁለቱም፡ እረኞች ፡ሳይሆኑ፡ የበግ ፡ጸሮች ፡አጥፊዎች ፡ናቸው፡ የበግ፡ እረኛ ፡ትክክለኛ ፡እረኛ፡ከሆነ ፡ደግሞ ፡ከነዚህ ፡ጋር ፡ህብረት ፡የለውም ፡ከተኩላ ፡ጋር፡ ምን ፡ህብረት ፡ይፈጠራል ፡ከቀበሮ፡ ጋር ፡ምን ፡ህብረት፡ ይፈጠራል፡ ከአውሬ ፡ጋር ፡ምን፡ ህብረት፡ ይፈጠራል ፡ስለዚህ በጎችን ፡የምትጠብቁ ፡የኢትዮጵያ፡ የዓለም፡ ብርሃን ፡ቤተሰብን፡ ኃላፊነት ፡ወስዳችሁ፡ በመማክርትነት፡ የምትሳተፉ ፡ፅዋን ፡የምትመሩ፡ መማክርታን፡ አባሎችን ፡የምትመሩ ፡ሁሉ፡ በእምነታችሁ ፡ምሳሌ ፡የምትሆኑ፡ ጠንካራ፡ መሆን ፡ይገባችኋል።

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
መግለጫ
በሚያዚያ-1-2014 ዓ.ም የተለቀቀው ላይ የተወሠደ።
🇨🇬🇨🇬
#_የአባት_ምክር_፩ {ለኢ.ዓ.ብ ቤተሰብ ብቻ}
#_ከልባችሁ_ታዘዙ

🇨🇬 የኢ.ዓ.ብ መግለጫ ሚያዚያ ፩፥ ፳፻፲፬ ዓ.ም 🇨🇬
| 🕛 | ከ ፶፭ ኛው ደቂቃ ጀምሮ

እንግዲኽ፤ በማስተዋል፣ በጽናት፣ እግዚአብሔርን በመፍራት፥ ቃሉን በማድመጥ የተግባር ሰው፥ የተግባር፥ በተግባር የሚገለጽ የእምነት ሰው ኾናችሁ፣ ከልማዳዊ አካሄድ ወጥታችሁ፣ በተግባር በሚገለጽ የእምነት ሥራ እንድታደርጉ እመክራችኋለሁ።

... #_ጸንተን_እንቁም
#_ምክሮችን_ተግባራዊ_እናድርግ። የታዘዛችሁትን ምክሮች ኹሉ ታውቃላችሁ። አድርጉ የተባላችሁትን፣ ይጠቅማችኋል የተባላችሁትን ሁሉ ነግረናል። ይኽ ኹሉ የነገርናችሁ ከራሳችን አይደለም። እኛ አዋቂዎች አይደለንም። እኛ ጥበበኞች አይደለንም። እኛ ከሌላው ተሽለን የምንበልጥ ኾነን አይደለም።

እግዚአብሔር የመከረንን የነገረንን ግን ለናንተ ለወገኖቻችን አድርሰናል። #_መጠቀም_የእናንተ_ፋንታ_ነው
#_የእምነት_ሥራ_መሥራት_የእናንተ_ፋንታ_ነው
#_እግዚአብሔርን_በእምነታችሁ_አካሄድ_ማስደሰት_የእናንተ_ፋንታ_ነው

◦ ◦ ◦ | 🇨🇬

www.tg-me.com/Ewnet1Nat 🇨🇬
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930 🇨🇬
🇲🇿🌪 Death toll from Cyclone Chido in Mozambique rises to 94, local authorities report

According to the National Institute of Disaster Management, the cyclone-force winds and rains that hit Mozambique between December 15 and 19 also destroyed more than 110,000 homes. More than 500 people were injured and 329,000 were displaced in the provinces of Cabo Delgado, Niassa, Nampula, Tete and Sofala.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇦🇷 🌪 በአርጀንቲና የተቀረፀው ቀኑን ወደ ጨለማ የቀየረው አቧራ ያዘለው ንፋስ
🇳🇬 የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት በደቡባዊ ኦኪጃ ከተማና በመዲናዋ አቡጃ ከተማ እለት በተከሰተ የህዝብ መጨናነቅ በርካታ ሰዎች ሞተዋል ወይም ቆስለዋል ሲል ገለጸ

በአቡጃ 10 ሰዎች፣ በኦኪጃ ደግሞ "በርካቶች" መሞታቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
🇨🇩 በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ድልድይ ተደርምሶ መላ አካባቢው ላይ "ሙሉ ለሙሉ የመነጠል ስጋት" አስከተለ
2025/01/07 00:09:06
Back to Top
HTML Embed Code: