Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
📹 🇸🇾 ደማስቆ የሚገኘው የባሽር አል-አሳድ መኖሪያ ቤት መቃጠሉን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇸🇾 የሶሪያ ዋና የወደብ ከተማ በሆነችው ላታኪያ በሀገሪቱ የተፈጠረውን ሁኔታ ተከትሎ ዘረፋ ተጀመረ

ደማስቆ በሚገኘው የመንግሥት መቀመጫም ከፍተኛ ዘረፋ ተፈጽሟል።
እስራኤል በሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ ላይ የአየር ድብደባ ፈጸመች።
በሱዳን በደረሰ የቦምብ ጥቃት የ28 ሰዎች ህይዎት አለፈ

ሕዳር 30፣ 2017 በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በነዳጅ ማደያ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት 28 ሰዎች ሲሞቱ 37 ሰዎች ቆስለዋል፡፡ የደቡብ ካርቱም የድንገተኛ አደጋ ክፍል በሰጠው መግለጫ በነዳጅ ማደያው ላይ በተወረወረ ቦምብ ነው አደጋው የደረሰው፡፡
🇨🇬 ዛሬ የምታዩአት የድሆች ተምሳሌት ኢትዮጵያ ከእንግዲህ የእግዚአብሔርን የብርሃን መንግስት ለሺህ ዓመት ባለም ሁሉ ገና (ከብራ) በፍጹም የፈጣሪ ፈቃድ መርታ እምትጉአዝ ይሆናል፡፡ዓለምም ከሺህ ዘመን ፍጻሜ በኀላ ወደ መጨረሻው፡ፍርድን የዓለም መፈጸም ትደርሳለች ፡፡ ይህን ሁሉ ለምን አወቅህ የሚል በአንዳንዶች ህሊና ሊነሱ ይችላል፡፡ልታውቁት የሚገባው ስለ ሰዶም ጥፋት እግዚአብሔር ለአብርሃም ደበቀው ? አልደበቀውም፡፡አስቀድሞ ነገረው ስለ ምልጃውም ተለመነው እንጂ እግዚአብሔር ከወደዳቸው ፤ ከአከበራቸው፤ ከአጸደቃቸው ፤ በክቡር ደሙ ለገዛቸውና ላተማቸው ልጆቹ ምንም የሚደብቀው ምስጢር የለም፡፡
📌 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 4ገጽ 10፡፡
🟢 🟡 🔴
ታኅሣሥ 1 | ልደቱ ወአስተርእዮቱ #ለቅዱስ_ኤልያስ_ነቢይ

ይህ ቀናኢ ኤልያስ ከሌዊ ወገን የሆነ የአባቱ ስም ኢያስኑዩ የእናቱም ስሟ ቶና ነው።

ስለርሱም እንዲህ ተነገረ፦ በተወለደ ጊዜ ብርሃንን የለበሱ አራት ሰዎች ሲሰግዱለትና ሕፃናት በሚጠቀለሉበት ጨርቅ ፈንታ በእሳት ሲጠቀልሉት አባቱ አየ።

እርሱም ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ይህን ለካህናቱ ነገራቸው። እነርሱም ማደሪያው በብርሃን ውስጥ ይሆን፣ በቃሉም የሚቆርጥ ይሆን፣ ወይም እስራኤልን በሰይፍና በእሳት እየቀጣ ይገዛቸው ይሆን ተባባሉ።

በእስራኤል ንጉሥ በአክዓብና በሚስቱ በኤልዛቤል ዘመንም ለእስራኤል ከገዳሙ ወጥቶ ታየ። በልጁም በአካዝያስም ዘመን ያደረገው የተአምራቱ ዜና በመጽሐፈ ነገሥት ተጽፎአል። ወደ ሰማይ ያረገበት ዜናው ግን በጥር ወር በስድስት ቀን ተጽፎአል።
🍀

እንዲሁም #የኢይዝራኤላዊው_የናቡቴ መታሰቢያ ነው።

ይህ ናቡቴ በሰማርያው ንጉሥ በአክዓብ ቤት አጠገብ የወይን አትክልት ቦታ ነበረው። አክዓብም ናቡቴን ቦታውን ሽጥልኝ ቢለው የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም ብሎ መለሰለት።

በዚህም ንጉሡ ሲያዝን ሚስቱ ኤልዛቤል ብታይ የክፋትን ምክር አሰበች። ይህቺም ክፉ ሴት በደብዳቤ ቃል፦ "ጾምን ጹሙ፤ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት አስቀምጡት፤ የሐሰት ምስክሮችንም ሁለት ሰዎችን አስነሡበት። እግዚአብሔርን ሰደብከው፣ ንጉሥንም ረገምከው ብለው ይመስክሩበት። ከከተማም ወደ ውጭ አውጥታችሁ በደንጊያ ውገሩትና ይሙት" የሚል ነው። እንዲህም በግፍ ኤልዛቤል አስገደለችው።
🍀

በዚህች ቀን የንጉሥ ሰሎሞን እናት #ብጽዕት_ቤርሳቤህ መታሰቢያዋ ነው።

#_በረከታቸው_ትድረሰን
T.me/Ewnet1Nat
በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተውን ድንገተኛ በሽታ እሰካሁን ሊታወቅ አልቻለም‼️

የዓለም ጤና ድርጅት እና የአፍሪካው የጤና ተቋም ሲዲሲ በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተከሰተውን ድንገተኛ በሽታ መመርመር ጀምረዋለ።

በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ ውስጥ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ ከ 4 መቶ ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ የአለም ጤና ድርጅት እና የአፍሪካው ሲዲሲ የበሽታውን ምንነት ለማወቅ ምርመራ መጀመራቸው ታውቋል።

በኮንጎ በደቡባዊ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኘው ክዋንጎ ክፍለ ሀገር ውስጥ የተከሰተው ይህ በሽታ እስካሁን ከ 4 መቶ በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፉል።

ከእነዚህም አብዛኞቹ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው።

ሳል፣ትኩሳት፣ ከባድ ራስ ምታት፣ እና የመሳሰሉ ምልክቶች አሉት የተባለው በሽታው የተከሰተበት አካባቢ ከከተማ መራቅ ለጤና ተደራሽነቱን አስቸጋሪ እንዳደረገው ሲጂቲኤን አፍሪቃ ዘግቧል፡፡
''-በሽታዎች እጅግ አደገኛ በሆኑ ቫይረሶች እየፈሉ ይመጣሉ። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን የአዳም ዘር ምልእክት አልባ የሆኑትን ሁሉ ያጠፋሉ፤ ለረሃብተኞች ደራሽ ስለማይኖር ሚሊዮኖችን መውስድ ስራቸው ይሆናል። ምልክት አልባው ሁሉ የጥፋቶቱ ሁሉ ኢላማ ይሆናል።''

◆► ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 5 ገፅ-17▼
📌 ልዩ ልዩ link የያዙ ያልታወቁ መልዕክቶች በቴሌግራም ፤ በዋትሳፕ.... ከምታውቁቱም ከማታውቁትም ሰዎች እየተላኩ የሰዎች አካውንት እየተጠለፈ፡ እንዲጠፋ እየተደረገ ስለሆነ ምንም ይዘት ይኑረው ሕጋዊ ያልሆኑ links ከሰው ሲላክላችሁ #አትክፈቱት
እስራኤል በ48 ሰዓታት ውስጥ 4 መቶ 80 ጥቃቶችን በሶሪያ ላይ መፈፀሟ ተነገረ

የእስራኤል ጦር ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ 4 መቶ 80 ጥቃቶችን መፈፀሙ ተነግሯል ።
ጥቃቶችን የፈፀመችው በአየር ከባህርና ከየብስ ነው ተብሏል ።

እስራኤል ሶሪያን እየደበደበች  ያለችው የኬሚካል ጦር መሳሪያዎች በአማፅያን እጅ እንዳይገቡ ነው።

ይህንን ተከትሎ በመላው ሶሪያ የአየር ጥቃቶችን አጠናክራ ቀጥላለች።
🟢🟡🔴
ታኅሣሥ 3 | #በዓታ_ለእግዝእትነ_ማርያም ሆነ፨

እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ የሌላት ስለሆነች በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ከሴቶች ተለይታ ርቃ ትኖር ነበር ሽማግሌ ከሆነ ከኢያቄም ከባሏ ጋርም እጅግ የምታዝን ሆነች እግዚአብሔርም ኀዘናቸውን ሰማ። ቅድስት ሐናም እንዲህ ብላ ለእግዚአብሔር ተሳለች፦ የሰጠህኝን ፍሬ ለእግዚአብሔር አገልጋይ አደርገዋለሁ።

ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምንም በወለደቻት ጊዜ ሦስት ዓመት በቤቷ ውስጥ አሳደገቻት። ከዚህም በኋላ ከደናግል ጋር ትኖር ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደቻት በቤተ መቅደስም ምግቧን ከመላእክት እጅ እየተቀበለች ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረች። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም መጥቶ ከእርሷ ሥጋን እስከ ነሣ ድረስ።
🌹

ዳግመኛም በዚህች ቀን #የቅዱስ_ፋኑኤል_መልአክ መታሰቢያ በዓሉ ነው።

ይህም መልአክ እመቤታችን ለቤተ መቅደስ ብፅዓት ተሰጥታ ዕለቱኑ ምን እናበላታለን ብለው ሲጨነቁ ከመላዕክት አንዱ የሆነው መልዐኩ ቅዱስ ፋኑኤል ሰማያዊ ጽዋ አና ሰማያዊ ሕብስት ይዞ ረብቦ ታየ፡፡

ሊቀ ካህኑ ዘካርያስም ለሱ የመጣ መስሎት ቢጠጋ ሸሸው። ሕፃኒቱን እስቲ ተጠጊ ብለዋት ስትጠጋው መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክፉን ጋርዶ በሰው ቁመት ከመሬት ከፍ አድርጎ መግቧት አረገ፡፡
🌹

#አቡነ_ዜና_ማርቆስ ዕረፍታቸው ነው።

በሀገራችን በተለይ በምድረ ጉራጌ ብርሃን የሆኑ አባት ናቸው።

ጽንሰታቸው ሚያዝያ 30 በብሥራተ ማርቆስ ወንጌላዊ፣ ልደታቸው ኅዳር 24 ቀን በበዓለ ሱራፌል ካህናተ ሰማይ ነው። የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የአጎት ልጅ ናቸው።

አቡነ ዜና ማርቆስ ታኅሣሥ ሁለት ቀን የደቀ መዛሙርቶቻቸውን እግር ሲያጥቡ ውለው፣ መልአኩ እንደነገራቸው ታኅሣሥ ሦስት ቀን በ140 ዓመታቸው ዐርፈዋል።
🌹🌹
🟢🟡🔴
ታኅሣሥ 4 | ሐዋርያው #ቅዱስ_እንድርያስ ሰማዕት ሆነ።

ቅዱሱ ሐዋርያ ተወልዶ ያደገው በቤተ ሳይዳ አካባቢ ሲሆን የሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ትንሽ ወንድም ነው። አባቱም ዮና ይባላል።

ገና ከልጅነቱ ጀምሮ አሣ ማጥመድን ከትልቅ ወንድሙ ተምሯል። እድሜው ከፍ ባለ ጊዜ ኦሪትን ተምሮ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆኗል።

ከጌታ እግር ሥር ተምሮ፣ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀበሎ ምን ሃገረ ስብከቱ ልዳ ብትሆን ብዙ አሕጉረ ዓለምን ሰብኳል።

ቅዱስ እንድርያስ 30 ቀናት የሚፈጅ የባሕር ላይ ጉዞ ለማድረግ ከአርድእቱ ጋር ወደ ወደብ ቢሔድም መርከበኞች ሁሉ አናሳፍርም በማለታቸው የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወጣት መርከበኛ መስሎ ሐዋርያውንና አርድእቱን የሠላሳውን ቀን መንገድ በሰዓታት ልዩነት እንዲጨርሱ አድርጓል።

ቅዱስ እንድርያስም እንዲሁ ሰው መስሎት ለጌታችን ስለ ጌታችን ሰብኮለታል፤ መርቆታልም። መርከበኛው ጌታችን መሆኑን ሲያውቅም ደንግጦ አልቅሷል። ጌታችንም "አይዞህ እኔ ካንተ ጋር ነኝ" ብሎታል።

የቅዱስ እንድርያስ ሃገረ ስብከቱ ልዳ (ልድያ) ናት። ይህቺን ሃገር አስቀድሞ ሊቀ ሐዋርያቱ (ትልቅ ወንድሙ) ቅዱስ ጴጥሮስ አስተምሮባታል። ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ ሮም ሲዘልቅ ቅዱስ እንድርያስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ገብቶ ብዙ ደክሞባታል።

ቅዱስ እንድርያስ በዕድሜው የመጨረሻ ዘመናት ከልድያ ወጥቶ በብዙ አሕጉራት አስተማረ። ስሟ ባልተጠቀሰ አንዲት ሃገር ውስጥ ግን በእሳት ሊያቃጥሉት ሲሉ እሳት ከሰማይ ወርዳ በላቻቸው።

ድጋሚ ሌሎች ይዘው አሰሩት፤ ደበደቡት አሰቃዩት። በሌሊትም ጌታ መጥቶ አጽናናው። ታኅሣሥ 4 ቀን በሆነ ጊዜም ወደ ውጭ አውጥተው፣ ወግረው፣ አግድም በተመስቀለ መስቀል (X ቅርጽ ያለው) ላይ ሰቅለው ገድለውታል።

🌿
T.me/Ewnet1Nat
2025/01/01 08:14:15
Back to Top
HTML Embed Code: