Telegram Web Link
🟢🟡🔴
መስከረም 4 | #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊ ልደቱ ነው።

ቅዱሱ ሐዋርያ ከዘብዴዎስና ከማርያም ባውፍልያ ተወልዶ፣ በገሊላ አካባቢ አድጎ ገና በወጣትነቱ መድኃኔዓለምን ተከትሎታል።

በምንም ምክንያት ከጎኑ አይጠፋም ነበር። ስለ ንጽሕናውና በጎ የፍቅር ሕሊናው ሕጻን ሳለ በወንድሞቹ ሐዋርያት ዘንድ ሞገሱ ከፍ ያለ ነው።

ለጌታችን ባለው ቅናትና ከወንድሙ ጋር ሆነው ባሳዩት የኃይል ሥራ እንዲሁም የጌታችንን አምላክነት በመግለጡ #ወልደ_ነጎድጓድ ተብሏል።

ጌታችንን እስከ እግረ #መስቀሉ ድረስ በመከተሉ ድንግል እመቤታችንን ተቀብሏል። ከእርሷ ጋር ለ15 ዓመታት ቢቀመጥ መዝገበ ምሥጢር ሆነ። እንኳን ከሰው ልጆች ይቅርና ከልዑላኑ መላዕክትም ማዕረጉ ከፍ አለ።

ሰው ቢበቃ መላእክትን ሊያይ ይቻለዋል። ቅዱስ ዮሐንስን ግን መላእክት ሊያዩት ይከብዳቸዋል። ከፍጥረት ወገን ከእመ ብርሃን ቀጥሎ ክቡር እርሱ ነው።

ከጌታችን ዕርገት በኋላ አብዛኛውን ጊዜውን ያሳለፈው በኤፌሶን አካባቢ ሕዝቡን ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና በማምጣት ነው።

▬ ▬ ▬

በዚህች ቀን፦
🌼 የአሕዛብንም ነገሥታት ድል የመታ ታላቅ ነቢይ መስፍንና ካህን የሆነው #የነዌ_ልጅ_ኢያሱ መታሰቢያ በዓሉ ነው፡፡

🌼 በግብፅ 40 ዘመን ነግሰው ሳለ ንግሥናቸውን ትተው ወደ ኢትዮጵያ መተው 16 ፍልፍል ቤተ መቅደሶችን የሠሩት የድባው #አቡነ_ሙሴ ብፁዓዊ ዕረፍታቸው ነው፡፡

ጻድቁ ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር ገና ሳትታወቅና ሳትፀነስ የቅድስት አርሴማን ጽላት ያሠሩላት መሆናቸው ነው፡፡

በቃል ኪዳናቸው የታመኑትን ልጆቻቸውን መተትና መርዝ አይጎዳቸውም፡፡ ይህም ጌታችን የሰጣቸው ልዩ ቃልኪዳናቸው ነው፡፡

🌼 #አባ_መቃርስ ሊቀ ጳጳሳት ዕረፍታቸው ነው።

               T.me/Ewnet1Nat
                  🌼🍀🌼🍀🌼
📌 ባለመታዘዝ በእምነት ጉድለት የሚመጣ አደጋ
እስከ መጨረሻ በትዕግስት ያንብቡት!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

📌ባለመታዘዝ በእምነት ጉድለት የሚመጣውን አደጋ አንድ ምሳሌ ብቻ እንዳይበዛባችሁ ላንሳ።ንጉሥ ሳኦልን ሁሉም የሚያውቀው የመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ ነው።ሳኦል የእስራኤልን ሕዝብ በመራበት ዘመን የነበረው ነብይ ታላቁ ነብይ ሳሙኤል ነበር።በአንድ ወቅት ንጉሥ ሳኦል የእግዚአብሔርም የእስራኤልም ክፉ ጠላቶች የሆኑ አማሊቃዊያንን ያጠፋ ዘንድ ወደደና ጥያቄውን በመልካም በመንፈሳዊ አቀራረብ ከልዑል ፈቃድ በነብዩ ሳሙኤል በኩል ጠየቀ።እግዚአብሔር የሳኦልን ጥያቄ ወደደ ፤ፈቀደለት ።ነገር ግን ከዚህ የሚከተለውን ትዕዛዝ አዘዘ:-"ባሪያዬ ሳኦል ወደ አማሊቃዊያን ስትዘምት ማንንም እንዳትተው ሽማግሌውን:አሮጊቱን:ህፃኑን:ጎልማሳውን:ጎረምሳውን:ሴቱን:ወንዱን:ንብረቱን :ከብቱንም ሁሉንም ምንም ሳትተው አጥፋ።ትዕዛዜ ይች ናት!" ብሎ በነብዩ ሳሙኤል በኩል አስረግጦ አዘዘ።ሳኦል ደስ አለው ዘመተ።ልዑል ቀኙን ሰጥቶት ነበርና አማሊቃዊያንን አጠፋ።ነገር ግን የአማሊቃውያንን ከብቶች እጅግ ያማሩ ነበሩና የሳኦል ልብ ወደ ሥጋ ፈቃዱ አመራ።ሦስት መቶ(300) የሚጠጉ የሚያማምሩ የአማሊቃውያን በሬዎች ወደ አገሩ ይዞ መጣ።በእግዚአብሔር መሰዊያ መስዋት አድርጎ ሊያሳርግ ፥ወደ ቤተ መንግሥቱም ጉረኖ አጎራቸው ።ነብዩ ሳሙኤል ከድል የተመለሰውን ሳኦልን ሊጎበኝ ወደ ቤተመንግሥቱ መጣ።ገና ከውጭ ሳለ የበሬዎችን ጩኸት :ግሳት ሰማ ወደ ሳኦልም ዘንድ ገባ።ሳኦልም ነብዩን ተቀበለ።"አባቴ ይኸው ድል አደረግሁ፤ ልዑል እንደ አዘዘኝም አደረግሁ አጠፋሁአቸው አለ።" ነብዩ ሳሙኤልም" መልካም! ይህ የምሰማው የበሬዎች ግሳት ምንድን ነው?" አለው ።ሳኦልም " አዎን ጌታዬ ለእግዚአብሔር መስዋዕት ለማቅረብ ብዬ 300 የተመረጡ የአማሊቃውያን በሬዎች አምጥቻለሁ አለው።"
ነብዩም አዘነ ተቆጣ " በእውኑ የታዘዝኸው እንዲህ ነው?፤ የታዘዝኸውን ስለምን አልፈጸምክም?
በልዑል ፊት ከብዙ መስዋዕት ይልቅ መታዘዝ እንደሚበልጥ አታውቅም?"
አያችሁ! በልዑል ፊት ከብዙ መስዋዕት ይልቅ መታዘዝ እንደሚበልጥ አታውቅም?
ወገኖቼ ! ብትጾሙ ፣ብትጸልዩ፣ብትጮኹ፣ብትሰግዱ፣በሁሉም መንገድ በሰው ፊት ሁሉ ሌትም ቀንም ስትደክሙ ብትታዩ ከዚህ ሁሉ ግን አንዲቷ መታዘዝ እንደምትበልጥ ልታውቁ ይገባል።በልዑል ፊት ከብዙ መስዋዕት ይልቅ መታዘዝ እንደሚበልጥ አታውቅም ብሎ ነብዩ ሳሙኤል ለሳኦል ይህንን መርዶ አረዳው። ቀጥሎም ውሳኔውን ነገረው "ዛሬ ልዑል ናቀህ፣አቀለለህ መንግሥትህንም ለሌላ ለታመነ ባርያው አሳለፈ አለ ።"
ከዚያ ደቂቃ ጀምሮ የሳኦል የውድቀት ጉዞ ጀመረ፤የንጉሥ የታዛዡ የተስፋው ንጉሥ ዳዊት መንገድ ወደ ንግሥና ተቃና።
ወገኖቼ ! መታዘዝ ከብዙ መስዋዕት እንደሚበልጥ ተረዱት።አለመታዘዝ :ጥርጥር እኒህ አያድኑም፣አያተርፉም ያከስራሉ እንጂ።ሳኦል እግዚአብሔር ያዘዘውን ሳያጎድል ፣ሳይቀንስ ፣ሳይጨምር ቢያደርግ ኖሮ ባልወደቀ ነበር።ጥርጥር ደግሞ ያለመታዘዝ ታናሽ ወንድም ነው።ጥርጥር ከእምነት ጉድለት የሚመነጭ ነው።

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግጫ 3
ሚያዚያ /11/2012 ዓ.ም ከተላለፈው ላይ የተወሰደ።

አሁን ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ውጪ ያሉት እንዳለ ሁኖ እኛው እራሳችን እንደ ሳኦል ልቦናችን ወደ ሥጋ የአመራን ፣የማንታዘዝ ከታዘዝነው የምናጎል ብንስተካከል መልካም ነው።ይኼን የምናደርግ ስለአለን ነው እንደ ማዕከል እንኳ የሚተላለፉ ነገሮች ከትጉሐንም ከአባላት የማንሰማ የማናከብር አለን እኛ እኮ የምንታዘዘው የሚያስተላልፉትን ሰዎች ብለን አይደለም እግዚአብሔርን ነው።ደግሞም እግዚአብሔር ያከበረውን የመረጠውን ማክበር መታዘዝ ግዴታችን ነው።የሃይማኖት ሕጸጽ እስከሌለት ድረስ ማለት ነው።የእግዚአብሔር ባሪያ የሚናገረው የእግዚአብሔርን ቃል ስለሆነ እንደው ትንሽ እግዚአብሔር በቸርነቱ አንዳንድ ነገሮች እንደ ሙሴ እህት ማርያም ስለገለጸልን እራሷን ከሙሴ ጋራ እንደ አወዳደረችው ሳንሆን በትህትና መታዘዝ ይገባል እሷንም የደረሰባትን ስለምታውቁት ማለት ነው ።ዛሬ እንደ ሙሴ እህት ማርያም አይነት አለንና ብንስተካከል መልካም ነው ትንሽ ነገር እግዚአብሔር ስለአሳየን በዚያች በመመጻደቅ እራሳችን ኮፍሰን የቆምን እንስተካከል።
እግዚአብሔር እኮ ባሪያዬ ያለው ባሪያ ጌታው ከአዘዘው ውጪ አያደርግም አይሰራም የጌታውን ትዕዛዝ ይጠብቃል በዚያም ጌታው ይደሰታል ይታመንበታል ይመካበታል ሁሉን ነገር አሳልፎ ይሰጠዋል በኃላፊነት ላይ ኃላፊነትን ይሰጠዋል ልቡ ይታመንበታልና።ልጆቹን አሳልፎ በአደራ ይሰጠዋል ታማኝ ባሪያ ነውአ ።ዛሬም ይኼ ነው እየሆነ ያለው ለወደደው ለመረጠው ባሪያው በምድር ላይ ያለን ሁሉ አሳልፎ ሰጠው የሚወዳቸው ልጆቹንም ሰጠው እረኛ አደረገው ።ስለዚህ ባሪያውን መታዘዝ ማለት ለእግዚአብሔር መታዘዝ ማለት ነው በእሱ ላይ አድሮ የሚናገረው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነውና።
ስለዚህ እኛው የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ሳንታበይ በትህትና ሁነንን በጾም :በጸሎት: በስግደት እየበረታን ከምንም በላይ ግን በታዘዝነው መንገድ መሄድ ይገባናል።አለበለዚያ ልዑል እግዚአብሔር ንጉሥ ሳኦልን ንግሥናውን እንደቀማው አሳልፎ ለንጉሥ ዳዊት እንደሰጠው ሁሉ እኛም የተሰጠንን ቃልኪዳን እናጣዋለን እግዚአብሔር እንደ ሰጠ መውሰድም ይችላል።ስለዚህ በሁሉም ቦታ ያለን ትጉሐንም አባላትም እግዚአብሔር ባዘዘን መንገድ ብንሄድ መልካም ነው እላለሁ አንዳንዴ የሚሰጠን ምክር ሌላ እኛ የምናደርገው ሌላ የሚሰጠን በራዕይ ዮሐንስ 20 ማሳሰቢያና መግለጫ ሌላ እኛ የምንተገብረው ሌላ እየሆነ ስለሚታይ ነው።አንዳንዶቻችን እንደው በቅርብት ከወንድሞቻችን እህቶቻችን ጋር ስናወራ ስንገናኝ ይበልጥ በትህትና ከመታዘዝ ይልቅ ያን ወንድም ወይ እህት አለመታዘዝ ስለሚታይ ነው መታዋወቃችን ይበልጥ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም የምንበረታ የምንታዘዝ ፣የደከመውን የሚያበረታ ሊያደርግ ይገባል እንጅ የእግዚአብሔርን ባሪያ በቅርበት ስለአወቅን አለመታዘዝ የሚያመጣ መሆን የለበትም።አብዝተን በሥጋ ሕይወት ሥራ ስንኳትን የምንውልም ሥራ መስራቱ መልካም ነው ግን ደግሞ ለእግዚአብሔርም ጊዜ ልሰጠው ይገባል ዝም ብለን እድሜ ልካችንን ሥራ ሥራ እያልን የእግዚአብሔርን ቃል የሚተላለፈውን የማንሰማ ስለአለን ነው በቀን ለእግዚአብሔር የምንመድባት እሱ ከሰጠን ትንሽ ጊዜ ሊኖረን ይገባል።ምንም አዲስ ነገር ስሌለ አልገባሁም አላየሁም አልሰማሁም የሰማሁት ይበቃኛል አንዴ አምኛለሁ አይነት ነገር ይታያል።የእግዚአብሔር ቃል ሁሌም አዲስ ነው በዚያ ላይ እርግጠኛ ሁነን የምንናገረው መልዕክታቱን አልተረዳነውም ሰማነው እንጅ አላዳመጥነው እና ጊዜ ሰጠን እንስማው ።በዚያ ላይ እግዚአብሔር ለአገልግሎት ለምስክርነት የተመረጥን ቤተሰብ እስከሆንን ድረስ እያዳንዳንዷን ነገር መስማትና መማር ያስፈልጋል።
2017 ዓመተ ምሕረትን እግዚአብሔርን የምንታዘዝበት ዘመን ያድርግልን።
ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር።
ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም።
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን።
ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዥ።
   
🟢 ስብሐት ለእግዚአብሔር፥
🟡 ወለወላዲቱ ድንግል፥
🔴 ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።


መስከረም/4/2017 ዓ.ም
📌በእስላሞች ዘንድ በተለይም በዚሁ በመካ መዲና ዙሪያ እስላሞች ባሉበት ሁሉ የሚታመንና የሚነገር አንድ አባባል ወይም ትንቢት አለ ፡፡
እሱም እንዲህ ነው ፦
#ወደ ፊት በኢትዮጵያ ምድር የሚነሳ አንድ መላጣ የሆነ ንጉስ ይመጣል / ይነግሣል / ይህ ሰው እስልምናንና እንዲሁም ዋናውን ሥፍራ መካ መዲናን ያፈርሳል ጥቂት ሰው ብቻ ነው የሚተርፈው የተቀረው ይጠፋል ብለው ያምናሉ ፡፡

ይህን አባባል የቀደሙ በእድሜያቸው የገፉ አባት እስላሞች ባብዛኛው የሚያውቁት ነው ፡፡ ወጣቱ እስላም ብዙም ቦታ አይሰጠውም ነገሩ ግን እውነት ነው ፡፡ መቼም በየዘመኑ እግዚአብሔር የሚወደው አንዳንድ የዋህ ሰው ከየትኛውም ሥፍራ አይጠፋምና አንዱ የዋህ እስላም ተገልጦለት ይሆናል ፡፡ የሆነ ሆኖ እስልምና እጅግ ብዙ የንፁሃንን ደም ያፈሰሰ በመሆኑ በእርግጥም ይጠፋሉ ይጠረጋሉ ፡፡
ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት-ዘጠኝ ላይ የተወሠደ፡፡
🟢🟡🔴
መስከረም 5 | የከበሩ ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን አባቶቻችን

#አቡነ_መልክአ_ክርስቶስ

የሚያገለግላቸውን አህያ ጅብ ቢበላባቸው በአህያቸው ፋንታ ጅቡን #ለሰባት_ዓመት ውሃ እየቀዳ እንዲያገለግላቸው ያደረጉት ታላቁ አባት #_አቡነ_መልክአ_ክርስቶስ ሰኔ 26 ተፀነሱ፣ መጋቢት 27 ተወለዱ፣ መስከረም 5 በ86 ዓመታቸው ዐረፉ።

#አቡነ_አሮን_መንክራዊ

ቤተ መቅደሳቸው ጣራው ክፍት ሆኖ ዝናብ ግን ፈጽሞ የማያስገባው የመቄቱ #አቡነ_አሮን_መንክራዊ ዕረፍታቸው ነው፡፡

እርሳቸውም ዳዊታቸውን አዋሽ ወንዝ ወስዶባቸው ሳለ ከ7 ዓመት በኋላ መልሰው ከወንዙ ውስጥ አቧራውን አራግፈው የተቀበሉ ናቸው፡፡

አንችም ሜዳ ላይ እንደ ኢያሱ ፀሐይን በቃላቸው ገዝተው አቁመዋታል፡፡

ጻድቅ ንጉሥ #ዓፄ_ልብነ_ድንግል

ከ1500-1533 በቆየ ዘመነ ንግሥናቸው፦

🌼 ለድንግል እመቤታችን በነበራቸው ፍቅር

🌼 በደራሲነት (መልክዐ ኤዶም፣ ተፈስሒ ማርያም፣ ለአዳም ፋሲካሁ፣ ለኖኅ ሐመሩ፣ ስብሐተ ፍቁር ደርሰዋል)

🌼 በፍጹም ንስሐቸው (ባጠፉት ጥፋት ጌታ ግራኝን አስነስቶ ሲቀጣቸው በመጸጸታቸው)

🌼 ለነዳያን በመራራታቸው፣ ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ቀናዒ
🌼 ለጋብቻቸውም ፍጹም ታማኝ በመሆናቸው ይታወቃሉ።

በ1533 መስከረም 5 ቀን በደብረ ዳሞ (ትግራይ) ከማረፋቸው በፊት እመቤታችንን እያለቀሱ ሲለምኑ እንዲህ አሉ፦

"በእንተ ፍቅረ
አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኬንያ፥
እስእለኪ ማርያም በሃሌ ሉያ፥
ሐዘና ስምዒ ወብካያ፥
ለሃገሪትነ ኢትዮጵያ።"
(ስብሐተ ፍቁር)

እመቤታችንም "ልመናህን ተቀብየዋለሁ፡፡ ግን በምድር ደስታ የለህምና ለልጅህ ማር ገላውዴዎስ ኃይልን እሰጠዋለሁ፡፡ እርሱም የሃገሪቱን ክብር ይመልሳል" አለቻቸው፡፡ (ድርሳነ ዑራኤል)

🌼 www.tg-me.com/Ewnet1Nat 🌼
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ጎርፎች ታይተው በማይታወቅ  መጠን ይመጣሉ፡፡ ይጠርጋሉ ።"

⚡️ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 5 ገጽ 29 ተጻፈ መስከረም 21/2004 ዓ .ም

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Audio
መልክአ ቅድስት አርሴማ.
Audio
መልክአ ቅዱስ ኤልያስ ነብይ
Audio
መልክአ አቡነ ጰንጠሌዎን
Audio
መልክአ አቡነ ዘግሩም
Audio
መልክአ ቁስቋም ማርያም
🟢🟡🔴
መስከረም 7 | የተዋሕዶ እምነት አርበኛ #ቅዱስ_ዲዮስቆሮስ ሊቀ ጳጳሳት ዐረፈ።

ስለ ቀናች ሃይማኖትም ታላቅ ተጋድሎን ከተጋደለ በኋላ ዕረፍቱ በተሰደደበት በደሴተ ጋግራ ሆነ።
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
🟢🟡🔴 መስከረም 7 | የተዋሕዶ እምነት አርበኛ #ቅዱስ_ዲዮስቆሮስ ሊቀ ጳጳሳት ዐረፈ። ስለ ቀናች ሃይማኖትም ታላቅ ተጋድሎን ከተጋደለ በኋላ ዕረፍቱ በተሰደደበት በደሴተ ጋግራ ሆነ።
ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ሊቅ የተዋሕዶ ሃይማኖታችን ምሰሶ ነው። በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በግብጽ ተወልዶ አድጎ፣ በልጅነቱ መጻሕፍትን ተምሮ፣ የምናኔ ሕይወትን መርጧል።

ቆይቶም የታላቁ ሊቅ ቅዱስ ቄርሎስ ረድእ ሆኖ ተምሯል አገልግሎታል።

በጉባኤ ኤፌሶን ጊዜም ቅዱስ ቄርሎስን ተከትሎ ሒዶ ተሳትፏል። በ444 ዓ/ም ታላቁን ሊቅ ተክቶ የእስክንድርያ 25ኛ ፓትርያርክ ሆኖ ተሹሟል።

ለ7 ዓመታትም መጽሐፈ ቅዳሴውን (እምቅድመ ዓለምን) ጨምሮ ብዙ ድርሰቶችን ደርሷል። በመልካም እረኝነትም ሕዝቡን ጠብቋል።

ዘመነ ሰማዕታትን ተከትሎ የመጣው የመናፍቃን ዘመን ሲሆን ለ150 ዓመታት ያህል መናፍቃን እንደ አሸን ፈልተዋል።

በዚያው ልክ ከዋክብት ቅዱሳን ሊቃውንት ነበሩና በየጊዜው ጉባኤያትን እየሠሩ፣ መናፍቃንን አሳፍረዋል። ምዕመናንንም አጽንተዋል።

በ451 ዓ/ም የተፈጸመው ድርጊት ግን ዛሬም ድረስ ጠባሳው የሚለቅ አልሆነም። ንጉሡ መርቅያንና ጳጳሱ ልዮን የንስጥሮስን ትምህርት አለባብሰው ሊያስተምሩ ጀመሩ። ጉባኤም ጠሩ።

ቅዱስ ዲዮስቆሮስም ሲሰማ እንዲህም አለ፦ "ይህ ታላቅ ጉባኤ እስቲሰበሰብ ድረስ በሃይማኖት ላይ የተገኘው ጉድለት ምንድን ነው?"

ይህ ጉባኤ የተሰበሰበው በንጉሥ ትእዛዝ ነው አሉት።

እንዲህም አላቸው፦ "ይህ ጉባኤ ስለ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢሆን ኖሮ እኔ ተቀምጬ እግዚአብሔር በሰጠኝ በአንደበቴ እናገር ነበር። ግን የዚህ ጉባኤ መሰብሰብ በንጉሥ ትእዛዝ ከሆነ የሰበሰበውን ጉባኤ ንጉሡ እንዳሻው ይምራ።"

ከዚህም በኋላ አንዱን ክርስቶስን (ክብር ይግባውና) ከተዋሕዶ በኋላ 'ሁለት ባሕርይ ሁለት ምክር' የሚያደርግ (የካቶሊክ) የክህደት ቃል በውስጡ የተጻፈበትን የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ልዮን የላከውን ደብዳቤ የከበረና የተመሰገነ ዲዮስቆሮስ ቀደደ።

በመንፈስ ቅዱስ የሚናገር የከበረ ዲዮስቆሮስም በጉባኤው ፊት እንዲህ ብሎ አስረዳ፦

"ሰው እንደመሆኑ ወደ ሠርግ ቤት የጠሩት ጌታችን ክርስቶስ አምላክ እንደመሆኑ ውኃውን ለውጦ ወይን ያደረገው ከሀሊ ስለሆነ ሰውነቱና መለኮቱ በሥራው ሁሉ የማይለይ አንድ ነው።"

ቅዱስ ዲዮስቆሮስንም ወደ ንጉሥ አቀረቡት። ከእርሱም ጋር ታላላቅ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ከጉባኤው የሆኑ ነበሩ። ከጠዋትም እስከማታ እርስበርሳቸው ሲከራከሩ ዋሉ።

የከበረ ዲዮስቆሮስም የቀናች ሃይማኖቱን አልለወጠም። ንጉሡና ንግሥቲቱ በእርሱ ተቆጥተው እንዲደበድቡት አዘዙ። ስለዚህም ደበደቡት ጽሕሙን ነጩ፤ ጥርሶቹንም ሰበሩ።

ከዚህም በኋላ የተነጨውን ጽሕሙን ያወለቁትንም ጥርሱን ሰብስቦ ወደ እስክንድርያ አገር ላካቸው። እነሆ የቀናች ሃይማኖት ፍሬ ይህ ነው አላቸው።

ለጉባኤውም የተሰበሰቡ ኤጲስቆጶሳት በዲዮስቆሮስ ላይ የደረሰውን መከራ በአዩ ጊዜ እጅግ ፈሩ። በእርሱ የደረሰ በእነርሱ ላይ እንዳይደርስ ስለዚህም ከመናፍቁ ንጉሥ ከመርቅያኖስ ጋር ተስማሙ።

በጉባኤው የነበሩ 636 ጳጳሳት (የጉባኤ ኒቂያ 318 አባቶች እጥፍ) ስቃይና ሞትን ፈርተው በኑፋቄ መጽሐፍ ላይ በመፈረማቸው "መለካውያን" (ከእግዚአብሔር ይልቅ ለንጉሥ የሚታዘዙ) ተባሉ።

ጉባኤውም "ጉባኤ ከለባት" (የውሾች ስብሰባ): "ጉባኤ አብዳን" (የሰነፎች ጉባኤ) ተብሏል።

በሲኦል ውስጥ ይቆረጡት ዘንድ ባለው ምላሳቸውም (ክብር ይግባውና) "ለክርስቶስ ሁለት የተለያዩ  ባሕርያት አሉት" ብለው በንጉሡ መዝገብ ላይ በእጆቻቸው ጽፈው ፈረሙ።

ቅዱስ ዲዮስቆሮስም ተመልሶ ያን በውስጡ የጻፉበትን ደብዳቤ ያመጡለት ዘንድ ወደእሳቸው ላከ። እነርሱም ላኩለት። እነርሱ እንደጻፉ በውስጡ እርሱ የሚጽፍ መስሏቸዋልና።

እርሱ ግን፦ አባቶቻችን ሐዋርያት ከአስተማሯት ከቀናች ሃይማኖት፣ በኒቅያ የተሰበሰቡ ሃይማኖታቸው የቀና ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ኤጲስቆጶሳት አባቶቻችን ከሠሩት ሕግ የሚወጣውን ሁሉ በደብዳቤው ግርጌ ጽፎ አወገዘ።

በዚህ ምክንያት ወደ ጋግራ ደሴት ከ7 ደቀ መዛሙርቱ ጋር አሳደዱት። በዚያም ለ3 ዓመታት ቆይቶ በ454 ዓ/ም ዐረፈ።

ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ከማረፉ በፊት በተሰደደባት ደሴተ ጋግራ ለ3 ዓመታት ብዙ መከራ ከመናፍቃን ደርሶበታል። እርሱ ግን በትዕግሥቱና በትምህርቱ ብዙዎችን ወደ ሃይማኖት መልሷል።

የአባታችን ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጽናትና በረከት ይደርብን።

🌼 www.tg-me.com/Ewnet1Nat 🌼
በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ከባድ ዝናብ በ161 ነጥብ 5 ሄ/ር መሬት የደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት አደረሰ

በዋግ ኽምራ ብሔረ-ሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ 04 ቀበሌ መስከረም 5/2017 ዓ.ም በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ በ161 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት የ140 አርሶ አደሮች የደረሰ ሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ።

በሰቆጣ ከተማ አስተዳደር 04 ቀበሌ የተለላ ጎጥ አርሶ አደር ነዋሪ የሆኑት አቶ በላይ አለሙ መስከረም 5/2017 ዓ/ም ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት አካባቢ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ከ6 ጥማድ በላይ በሚሆኑ የደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳተ አድርሶብናል ብለዋል።

የማዳበሪያ ግብአት እና ምርጥ ዘር ተጠቅመን ማሳችን በዘር በመሸፈን ከራሳችን አልፎ ለገበያ የሚተርፍ በቂ ምርት የምናገኝበት ወቅት ነበር ያሉት አቶ በላይ ባልታሰበ ሁኔታ በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ፋታችንና ተስፋችን ከንቱ አስቆርቶታል ሲሉ ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት 26 ኬሻ ጭነት ገብስ እና 13 ኬሻ ጭነት ጤፍ የሚያገኙበት የገብስና የጤፍ ማሳ እንዲሁም የአተርና የባቄላ ማሳ ከጥቅም ውጭ ሆኗል።
2024/09/22 22:34:00
Back to Top
HTML Embed Code: