Telegram Web Link
Audio
ድርሳነ ቅዱስ ራጉኤል ዘወርኃ መስከረም
Audio
መልክአ ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
Audio
የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት እና ማሳሰቢያ
ከራዕይ ዮሐንስ 20
መስከረም/1/2017 ዓ.ም
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
እነሆ መድኃኒት ፤
የኃጢአት ስርየት ፤
መስከረም ኹለት፤
በዮሐንስ ምህረት።

የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ከፈጣሪው የተቀበለው ቃልኪዳን፦

{🌼} የመጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ገድል ሲነበብ ውኃ አምጥቶ በበላዩ ላይ አንብቦ፣ አስነብቦ፣ የገድሉ መጽሐፍ የተነበበበትን ውኃ የተጠመቀውን፥

በሚጠመቁ ጊዜ መጥምቁ ዮሐንስ ወደርሱ መጥቶ ፊቱን በትምእርተ መስቀል አርአያ በእርሱ ስም ዮሐንስ ብሎ ያትመዋል።

እስከ ሰማኒያ ዓመት የሠራው ኃጢአቱ ቀርቶለት ይሠረይለታል።
{🌼} በወር በወሩ መጠመቅ ባይቻለው መስከረም ሁለት ቀን ይጠመቅ የሠራው ኃጢአቱ ሁሉ ፈጽሞ ይሠረይለታል፡፡

#በእምነት_ተጠቀሙበት !!

www.tg-me.com/Ewnet1Nat

https://www.tg-me.com/christian930/5498
🟢🟡🔴
መስከረም 2 | የካህኑ የዘካርያስ ልጅ የከበረ #አጥማቂው_ዮሐንስ ሕግን አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ ሰማዕት ሆነ።

ይህም እንዲህ ነው፦

ቅዱስ ዮሐንስ ሄሮድስን የወንድሙን የፊልጶስን ሚስት ሄሮድያዳን ስለማግባቱና ሌላም ያደርገው ስለነበረ ክፉ ሥራ ሁሉ ይገሥጸው ነበር። ደግሞም በተግሣጽ ላይ ተግሣጽን ጨመረ። ስለዚህም ዮሐንስን ተቀየመውና በግዞት ቤት አኖረው።

ሄሮድስም ዮሐንስን ይፈራው ነበር። ጻድቅ ቅዱስ ሰው እንደሆነ ያውቅ ነበርና ብዙ ይጠባበቀውም ነበር። ሄሮድስ የተወለደባትን ቀን በዓል የሚያከብርባት ዕለት ነበረች። መኳንንቱን አለቆቹን መሣፍንቱን ሹሞቹን በገሊላ አገር ያሉትን ታላላቅ ሰዎች ግብር አገባ።

የሄሮድያዳ ልጅም ወደ አዳራሹ ገብታ ዘፈነች። ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው ከእርሱ ጋር በማዕድ የነበሩትንም ንጉሡም ያቺን ብላቴና የምትሺውን ለምኚኝ እሰጥሻለሁ አላት። እስከ መንግሥቱ እኩሌታ ድረስም ቢሆን የለመነችውን ሊሰጣት ማለላት።

ወጥታም እናቷን ምን ልለምነው አለቻት። እናቷም የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ አለቻት። ያን ጊዜም እየሮጠች ወደ ንጉሡ ገብታ የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በወጭት አሁን እንድትሰጠኝ እሻለሁ ብላ ለመነችው።

ንጉሡም ስለ መሐላው አብረውት ስለ ነበሩትም ሰዎች አዘነ፤ እምቢ ሊላት ግን አልወደደም።

ያን ጊዜም ባለወጎችን ላከ በእሥር ቤትም ሳለ የዮሐንስን ራስ ቆረጡ። ራሱንም በወጭት አምጥተው ለዚያች ብላቴና ሰጧት። እርሷም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች።

በዚያችም ቀን የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ከሄሮድያዳ ከእጆቿ ላይ ወደ አየር ስለ በረረች ታላቅ ድንጋፄ ሆነ።

ደግሞም ሄሮድስ ሆይ የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም አለች። ደቀ መዛሙርቱም በሰሙ ጊዜ መጥተው በድኑን ወስደው ቀበሩት።

#እንኳን_አደረሳችሁ
                  ◦🌿🌼🌿
ገድለ_ዮሐንስ_መጥምቅ_በጥቅምት_1988_ዓ_ም_የታተመ_!17_09_2014.pdf
39.4 MB
ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ ( PDF) በመካከለኛ የምስል ጥራት በአልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ !

በጥቅምት ፲፱፻፹፰ ዓ.ም የታተመ !
SIZE — 39 MB ብቻ !
🟢🟡🔴 www.tg-me.com/AlphaOmega930
🌿 የዓለም ብርሃን በክብረ ፈጣሪው የተከበበ ገባሬ ተአምራት ወመንክራት ሊቀ ሰማዕታት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ 🌹
Audio
መልክአ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት .
Audio
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ገድል የመስከረም .
አሜሪካ ለግብጽ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ወታደራዊ እርዳታ ሰጠች

ግብጽ በመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ የአሜሪካ ዋነኛ አጋር ናት።
አሜሪካ ከዚህ በፊት በግብጽ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ምክንያት ወታደራዊ እርዳታዋን ቀንሳ ነበር
“እግዚአብሔር የሚወዳችሁ አንድም እግዚአብሔርን የምትወዱት ወንድም እህቶቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሥጋ ከባረከን በላይ በነፍስ የባረከን ይበልጣልና ስለዚሁ ልናመሰግነው ይገባናል፤ ምድራዊ መጠጥን አንድም ምድራዊ መብልን ከመስጠት መንፈሳዊ መጠጥንና መብልን መስጠት ይበልጣልና፡፡ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለእሥራኤላውያን መናውን የሰጣቸው በኋላም እስራኤል ዘነፍስ  ለምንባል ለእኛ ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን የሰጠንም ስለዚሁ ነውና በሥጋ ከሰጠን ይልቅ በነፍስ የሰጠን ስለሚበልጥ እግዚአብሔርን እጅግ ልናመሰግነው ይገባናል፡፡

እግዚአብሔር በሥጋ ሲባርከን በዚያው (በሥጋዊው ነገር ላይ ብቻ) እንድንቀር አይደለም፤ የበለጠ ወደርሱ እንድንቀርብ ነው እንጂ፡፡ ሥጋዊውን ስጦታ ይዘን የምንቀር ከሆነ ግን ዓላማውን ስተናልና ልናስተካክል ይገባናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ! በአፍአ ከተባረክነው ይልቅ በነፍስ የተባረክነው ይበልጣልና ስለዚያ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ለምን? መንፈሳዊው ነገር ከእኛ ዘንድ ካለ፥ ሥጋዊ ነገር ቢቀርም ምንም አናጣምና፡፡ መንፈሳዊውን ካጣን ግን ከእኛ ዘንድ ምን ተስፋ፥ ምንስ መጽናናት ይቀርልናል? አስቀድመን መንግሥቱንና ጽድቁን እንድንሻ የተፈለገውም ስለዚሁ ነው፡፡

የምወዳችሁ ልጆቼ! አስቀድመን እውነተኛውን ሀብት ይኸውም ሰማያዊውን ሀብት እንለምን፤ ርሱንም ለማግኘት እንጣጣር ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ ሌላው ከዚያ በኋላ ይቀጥላል፡፡ እኛ ስለለመንን ሳይሆን ልቡናችን ዋናውን ስለፈለገ፡፡ ጸሎታችንን የምናገላብጠው ከሆነ ግን በነፍስ በሥጋ የተጐዳን እንሆናለን፡፡”

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)


መስከረም/3/2017 ዓ.ም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
A cashless society where everything runs from your smart phone, with just about enough battery life to last half a day.

Don’t be a victim of ignorance
Think while it’s still legal.
በሴኔጋል የባህር ዳርቻ በሰጠመው ጀልባ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 39 መድረሱን የሀገሪቱ ባህር ኃይል አስታወቀ

በጀልባ መገልበጥ አደጋው 26 ሰዎች እንደሞቱ የባህር ኃይሉ ማክሰኞ እለት አስታውቋል።

💬 "ጀልባው የተገለበጠው ምቦር ከተማ አቅራቢያ ነው። በተደረገው ፍለጋ… 39 አስከሬኖች ተገኝተዋል። የሀገሪቱ ባህር ኃይል ፍለጋውን ቀጥሏል" ሲል ባህር ኃይሉ ሐሙስ እለት በኤክስ የትስስር ገጹ ገልጿል።

ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ሙከራ ያደረገው ከ200 በላይ ሰዎችን ያሳፈረው ጀልባ ከሴኔጋል የባህር ዳርቻ በግምት 3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከእሁድ ምሽት እስከ ሰኞ ባለው ግዜ ውስጥ ተገልብጧል።
2024/09/23 00:24:58
Back to Top
HTML Embed Code: