Telegram Web Link
Audio
ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት ?
በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት እና መግለጫ
ክፍል -
5

ለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ብቻ!
ነሐሴ/10/2016 ዓ.ም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዓይነ ሥውር ካህን መሆን ይችላል?
አለቃ አያሌው ምን ምላሽ አላቸው?


#_ዝክረ_አለቃ_አያሌው_ታምሩ
            
#የአለቃ_ሳምንት

💚 አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
💛
www.tg-me.com/AlphaOmega930
❤️
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ነሐሴ 12 | የመላእክት አለቃ የከበረ #ቅዱስ_ሚካኤልን እግዚአብሔር ወደ ዕሌኒ ልጅ ወደ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ላከው።

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም ንጉሥ ቆስጠንጢኖስን በጦርነት ረድቶ በድል ያነገሠበት ዕለት ነው፡፡

ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ገና በወጣትነቱ አባቱ ስለሞተ የአባቱ ባለሟሎችና ህዝቡ ተስማምተው በ18 ዓመቱ ቆስጠንጢኖስን በአባቱ ቦታ ሐምሌ 25 ቀን 300 ዓ.ም በሮም ምዕራብ ክፍል በገላትያ አነገሡት፡፡

እርሱም በጦር ሜዳዎች ብዙ የጀግንነት ሥራዎች ስለሠራ በሠራዊቱ ይወደድ ነበር።

በተለይም በ312 ዓ.ም ከጠላቱ ከመክስምያኖስ ጋር ለመዋጋት እንደተነሣ በራእይ በሰማይ ላይ ‹‹በዚህ የመስቀል ምልክት ጠላትህን ድል ታደርጋለህ›› የሚል መስቀልና ጽሑፍ ስላየ ለሠራዊቱ ሁሉ የመስቀል ምልክት በመሣሪያቸውና በሰንደቅ ዓላማው ላይ እንዲያደርጉ አዘዘ፡፡

ወዲያው ጦርነት ቢገጥም በቲቤር ወንዝ ድልድይ ላይ ጠላቱን ድል ነሥቶ በጠቅላላው የሮም መንግስት ግዛቶች ሁሉ ገዥ ሆነ፡፡ ይኸውም የሆነው በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ረዳትነት ነው፡፡


ስለዚህም አባቶቻችን የቤተክርስቲያን መምህራን የከበረ የመላእክት አለቃ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን እናደርግ ዘንድ አዘዙን።

#ታላቁ_ንጉሥ_ቅዱስ_ቆስጠንጢኖስ በዚህች ቀን ወደ ሮሜ ገብቶ ነገሠ።


የቅዱስ ሚካኤል ዝክር በሕይወቷ የማታስታጉለው፣ በቅዱስ ሚካኤል እጅ ከሞተሎሚ እገታ ነጻ የወጣችው፣ የቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እናት #_ቅድስት_እግዚእ_ኃረያ ነሐሴ 12 ዕረፍቷ ነው።
{ቅዱስ መካነ መቃብሯ ኢቲሳ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ይገኛል}

🍀🍀🍀
#_እንኳን_አደረሳችሁ
T.me/Ewnet1Nat
Audio
ሊቀ ሊቃውንት አያሌው ታምሩ

🍀 በዓለ ቅዱስ ሚካኤል እና ስለ ተደረገላቸው ተአምራት 🍀

▬ ▭ ▬ ▭ ▬ ▭ ▬ ▭ ▬ ▭ ▬
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🍀 ቄስ ጳጳስን ማውገዝ ይችላል?

● «ከታች ማዕረግ ያለ ከላይ ያለውን ማውገዝ እንዴት ይችላል» ተብለው ሲጠየቁ ሊቁ ያስተማሩት እውነት በራሳቸው ድምፅ


#_ዝክረ_አለቃ_አያሌው_ታምሩ
            
#የአለቃ_ሳምንት

💚 አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
💛
www.tg-me.com/AlphaOmega930
❤️
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ነሐሴ 13 | በዓለ ደብረ ታቦር ❴ደብረ ምሥጢር ወደብረ በረከት

ከ18ቱ የመድኃኔዓለም በዓላት (9 ዐቢያን፣ 9 ንዑሳን) አንዱ እና በዓመቱ መጨረሻ ላይ የሚከበር በዓል ነው። በዚህም ጌታችን አምላክነቱን ለሐዋርያቱ ቅዱሳን ሙሴንና ኤልያስ በተገኙበት ገልጧል።

የጌታችን 9ኙ ዋና (ዐቢይ) በዓላት የሚባሉት፦

፩. በዓለ ብሥራት/ጽንሰት
፪. በዓለ ልደት
፫. በዓለ ጥምቀት
፬. በዓለ ደብረ ታቦር
፭. በዓለ ሆሳዕና
፮. በዓለ ስቅለት
፯. በዓለ ትንሣኤ
፰. በዓለ ዕርገት
፱. በዓለ ጰራቅሊጦስ


● ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ጌታችን ልክ ለእነ ቅዱስ ጴጥሮስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን እንደገለጠላቸው ሁሉ #ለአቡነ_ሊቃኖስም እንዲሁ በበዓታቸው ሣሉ ብርሃነ መለኮቱን ገልጦ አሳይቷቸዋል፡፡ ይህም በዓል በጻድቁ ገዳም በደብረ ቆናጽል በድምቀት ይከበራል፡፡

#የቅዱስ_ሙሴ_ሊቀ_ነቢያት ልደቱ ነው፣

● ተጋዳይ
#አባ_ጋልዩን ዐረፈ።

🍀🍀🍀
#_እንኳን_አደረሳችሁ
T.me/Ewnet1Nat
☘️🍀☘️
#በዓለ_ደብረ_ታቦር

አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደባት በዚያች በተወደደች ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ምሥጢርን ይማሩ ነበር።

ጌታም አምላክነቱን በየጊዜው በቃልም በተግባርም ይገልጥላቸው ነበር። ነገር ግን ገና እምነታቸው ሙሉ አልነበረም።

እጅግ ድንቅ ከሆኑት መካከል ደግሞ ቅድሚያውን ደብረ ታቦር ይይዛል። ጌታ ስለ ምን መለኮታዊ ክብሩን በደብረ ታቦር ገለጸ ቢሉ፦

1. ትንቢቱ ሊፈጸም (መዝ. 88፥12)
2. ምሳሌው ሊፈጸም (ባርቅና ዲቦራ በሢሣራ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋልና)

3. ሊቀ ነቢያት ሙሴ "ልይህ" ብሎ ከ1,500 ዓመታት በፊት ጠይቆ ነበርና እርሱን ለመፈጸም
4. አንድነቱን፥ ሦስትነቱን ለመግለጽ
5. ቤተ ክርስቲያንን በምሳሌ ለማሳየት
6. ተራራውን ለመቀደስ
7. የሐዋርያቱን ልብ ለማጽናት . . . ወዘተ ነው።


ጌታችን 12ቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ደብረ ታቦር ወሰዳቸው። ዘጠኙን ከተራራው ሥር ትቶ 3ቱን (ጴጥሮስን ዮሐንስንና ያዕቆብን) ይዟቸው ወጣ። እኒሕ ሐዋርያት "አዕማድ አርዕስት ሐዋርያተ ምሥጢርም" ይባላሉ።

በተራራው ላይ ሳሉም ድንገት የጌታችን መልኩ ከፀሐይ 7 እጅ አበራ፤ ከመብረቅም 7 እጅ አበረቀ። "ወኮነ ልብሱ ጸዐዳ ከመ በረድ" እንዲል ከታቦር የተነሣው ብርሃነ ገጹ አርሞንኤም ደርሷል። ያንን ተመልክተው መቆም ያልቻሉት ሐዋርያቱ ፈጥነው መሬት ላይ እንደ ሻሽ ተነጠፉ።

በደብረ ታቦር የጌታችን ብርሃነ መለኮት ያዩ 3ቱ ሐዋርያት ብቻ አይደሉም። እመ ብርሃን ካለችበት ሆና ስትመለከት 12ቱ ሐዋርያት ደግሞ በተራራው ሥር ሆነው በተደሞ ተመልክተዋል።

በዚያች ሰዓት ሙሴ ከመቃብር፣ ኤልያስም ከብሔረ ሕያዋን መጡ። አንዳንዶቹ ጌታን 'ነቢይ' (ሎቱ ስብሐት) ብለውታልና ሙሴና ኤልያስ ተናገሩ፦ "ስለ ምን አንተን ነቢይ ይሉሃል? እግዚአ ነቢያት - የነቢያት ፈጣሪ ነህ እንጂ" እያሉ ተገዙለት፤ አመሰገኑት።

ነገር ግን በቦታው ጸንተው መቆየት አልቻሉም። መለኮታዊ ብርሃኑ ቢበዘብዛቸው ቅዱስ ሙሴም ወደ መቃብሩ፣ ቅዱስ ኤልያስም ወደ ማደሪያው በድንጋጤ ሩጠዋል።

🍀🍀🍀
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍀 ቄስ ጳጳስን እና ሲኖዶስን ማውገዝ እንደሚችል ከሁለቱ የማኅበረ ቅ*ርኩሳን ሰዎች አንደበት የተገኘ ምስክርነት፨

የሊቀ ሊቃውንት አያሌው ታምሩ ውግዘት ይከበር!

#_ዝክረ_አለቃ_አያሌው_ታምሩ
            
#የአለቃ_ሳምንት

💚 አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
💛
www.tg-me.com/AlphaOmega930
❤️
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🍀🌼🌺
ጠያቂ፦ “የመንግሥትና የቤተ ክህነት ግንኙነት ምን መሆን አለበት ይላሉ?”

አለቃ አያሌው፦ “መንግሥትና ቤተ ክህነትማ በ፲፱፻፷፮ (በ1966) ዓ. ም. ተለያዩ፤ ሆድና ጀርባ ሆኑ። ትልቁ በሽታ የተፈጠረው ከዚያ ወዲህ ነው።

▸ የእብደት ዘመን ባተ፤ የዛር ዘመን ነገሠ። ቤተ ክርስቲያን ጠፋች። እግዚአብሔርና ኢትዮጵያ ተፋቱ። የተማሩ እየተጣሉ [ላልቶ ይነበብ] ያልተማሩ ተሾሙ። ማን በሞተበት ማን ይበላል? ተባለና ሹመቱ ሁሉ ለሌላ ሆነ። እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ጠፋች። አሁንም እንደ ጠፋች ነው።

▹▹ እሷን መልሶ ለመውለድ በቅድሚያ ራሳቸውን ለመንፈሳዊ ዓለም በሐቅ ያስገዙ ካህናትና መነኮሳት ያስፈልጓታል።


መንግሥትም በውስጥ ጉዳይዋ ጣልቃ መግባት የለበትም። ሲቸግራት ቢረዳት፥ ዐቅሟ ሲደክም ቢደግፋት ክፋት የለውም። በፖለቲካ መሣሪያነት ግን ሊጠቀምባት አይገባም።

▹ እሷም ብትሆን ሳይጠሯት አቤት እያለች ሕዝብ ለጠላቸውና በጉልበት ሥልጣን ላይ ለወጡ መሪዎች ማብደድ የለባትም። የግንኙነቱ መሥመር ይህን ነው መምሰል ያለበት።”


🇨🇬 ክቡር ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ታምሩ።

🟢 በረከታቸው ይደርብን !
🟡
www.tg-me.com/AlphaOmega930
🔴 #ዝክረ_አለቃ_አያሌው_ታምሩ
ዩክሬን ሁለተኛውን የሩሲያ ድልድይ ማውደሟን አስታወቀች

ዩክሬን በሩሲያ ኩርስክ ግዛት የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ በቀጠለችበት ሳምንት ውስጥ ሁለተኛውን ስትራቴጂካዊ ድልድይ አፈራርሳለች ። የዩክሬን ጦር እሁድ እለት ድልድዩ ሲያወድም የሚያመላክት የአየር ላይ ምስል አጋርታል። በዝቫኖኖ የሚገኘው ይህ ድልድይ በሴም ወንዝ ላይ የተገነባ ነበር። ጥቃቱ ከደረሰ ከሰዓታት በኋላ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተናገሩት ወታደራዊ ወረራው ወደ ኩርስክ የመግባት አላማ የሩሲያን ጥቃቶች ለማስቆም "የማቆያ ዞንን" መፍጠርን ያካታል ሲሉ ተናግረዋል።
🍀🌼🌹
ከነሐሴ ፲፩ — ነሐሴ ፲፯ | ፳፻፲፮ ዓ.ም
#_ዝክረ_አለቃ_አያሌው_ታምሩ

ውድ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች እንኳን ለሰማዕት ዘእንበለ ደም፣ ለታላቁ ሊቀ ሊቃውንት አባታችን ፲፯ኛ ዓመት የዕረፍት መታሰቢያ አደረሳችሁ ፤ አደረሰን !

💚 አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
💛
www.tg-me.com/AlphaOmega930
❤️ ፲፬ | ፲፪ | ፳፻፲፮ ዓ.ም
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
#ጸድቆ_አገኘነው

ከቤተልሄም ዘንድ ተክለ ሃይማኖት
ያኖርነው መልካም ዘር ወርቅና መክሊት
እንዴት ከርሟል ብለን ብንሔድ ልናየው
አትርፎ ሥር ይዞ ጸድቆ አገኘነው።

× | ነሐሴ ፳፻፩ ዓ.ም
ለኹለተኛ ዓመት መታሰቢያ የተገጠመ

▸ አባቴና እምነቱ፡ በሥምረት አያሌው ታምሩ ፥ ገጽ ፫፻፸፭
▰ ▰ ▰

www.tg-me.com/AlphaOmega930
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
@Orthodox_Books አባቴና እምነቱ.pdf
6.6 MB
📕 አባቴና እምነቱ

📌የአለቃ አያሌው ታምሩ የሕይወት ታሪክ (በልጁ ሥምረት አያሌው ሰኔ 2007ዓ.ም የተጻፈ) (መጽሐፉን በPDF በማግኘታችን እንኳን ደስ ያለን !)

🇨🇬 ሠማዕት ዘእንበለ ደም ታላቁ ሊቅና ነብይ ካህኑ አለቃ አያሌው ታምሩ ዘድማኅ ስመ ጥር የቤተ ክርስቲያናችን አርማ በኹሉም ወገን ተጠያቂ የነበሩ ሊቅ ናቸው።

👉 ይህን መጽሐፍ ስታነቡ በእርሳቸው ላይ ስለተፈጸመው ግፍና መከራ ስታስቡ እንባችሁ ካልመጣ ሰውነታችሁን ትጠራጠራላችሁ። ያን ያህል ግፍና መከራ ተሸክመው ግን ምእመናንን በማጽናናት፣ ለቤተ ክርስቲያን በመጸለይ፣ ልጆቻቸውን በማስተማር ብዙ ሥራ ሠርተዋል ።
📌 የገጽ ብዛት - 421
📌 አለቃ አያሌው ማን ናቸው ፣ ምን ሠሩ ፣ ምን ሆኑ ፣ ምን አወገዙ ፣ ምን ተደረጉ ... ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች ላይ ሙሉ መልስ ከመጽሐፉ ያገኛሉ ።

📚ብትችሉ መጽሐፉን ገዝታችሁ አንብቡ!

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
www.tg-me.com/AlphaOmega930
2024/09/23 22:30:46
Back to Top
HTML Embed Code: