Telegram Web Link
Audio
ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት ?
በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት እና መግለጫ
ክፍል - 4 ( ሀ
)
Audio
ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት ?
በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ተከታታይ ትምህርት እና መግለጫ
ክፍል - 4 ( ለ )
🟢🟡🔴
ሐምሌ 6 | የእኚኝ የከበሩ አባቶቻችን የዕረፍት በዓል ነው፨

🌿 ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ #ቅዱስ_በርተሎሜዎስ ከጴጥሮስ ጋር አልዋሕ ወደምትባል ቦታ ሄዶ በአትክልተኝነት ተሸጦ ወንጌልን ሰበከ። የውሻ ፊት ያላቸው (ገጸ ከለባት) እየታዘዙለት በብዙ ሀገራት ወንጌልን ሰበከ።

በኋላም የከሃዲው ንጉሥ የአግሪጳን ሚስትም ትምህርቱን ሰምታ በጌታችን አመነች፡፡

ንጉሡ አግሪጳም በዚህ እጅግ ተቆጥቶ ቅ/በርተሎሜዎስን ብዙ ካሠቃየው በኋላ አሸዋ በተሞላ ትልቅ ከረጢት ውስጥ ከቶ ከነሕይወቱ ባሕር ውስጥ እንዲጥሉት አደረገ፡፡

ምእመናንም ሥጋውን አውጥተው በክብር ቀብረውታል፡፡

🌿 ጳውሎስ የተባለ #ቅዱስ_መርቄሎስ ይህም ከ72 አርድእት ውስጥ ነው።

እርሱም ሐዋርያትን ያገለገለ፣ ወንጌልንም ለመስበክ ከእነርሱ ጋር የሔደ፣ የቅ/ጴጥሮስን መልእክቶች ያደረሰ ነው። ከእርሱም በመከራው ኹሉ አልተለየም።

ቅ/ጴጥሮስም በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ይህ ረድእ መርቄሎስ መጥቶ ከመስቀል ላይ አወረደው። በከበሩ ልብሶችም ከሽቱ ጋር ገነዘው። በሣጥንም አድርጎ ከምእመናን በአንዱ ቤት አኖረው።

የጴጥሮስ ደቀ መዝሙርም እንደሆነ በኔሮን ዘንድ ወነጀሉት። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዕውነተኛ አምላክ እንደሆነ ታመነ።

ስለዚህም ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ገረፈውም ዘቅዝቀው ሰቅለውም ከበታቹ ጢስን አጤሱበት።

ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኔሮን እንዲገርፉትና እንደ መምህሩ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት አዘዘ። የሰማዕታትንና የሐዋርያትን አክሊል ተቀበለ።

🍀 ጌታችን ተገልጦላቸው በፍቅር የተወጋ ጎኑን በእጃቸው እንዲዳስሱ የፈቀደላቸው፣ ምጽዋትን ከሰጡ በኋላ ሌላ የሚመጸውቱት ቢያጡ እርቃናቸውን እስኪቀሩ ድረስ የለበሱትን ልብሳቸውን እያወለቁ ለነዳያን የሚሰጡ መፍቀሬ ነዳያን #አባ_ዘግሩም ዕረፍታቸው ነው፡፡

T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሐምሌ 7 | #_ሥሉስ_ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡

ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡

ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡

አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡

በዚያው ሐምሌ 7 ቀን የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የወረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡

ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ (ዘፍ 18፥1-25፣ ሮሜ 4)

#_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ
ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ ጋስጫ ውስጥ ሐምሌ 7፥ 1358 ዓ/ም ነው። እንዲሁም ዕረፍቱ በዚሁ ቀን ሐምሌ 7፥ 1418 ዓ.ም ነው።

ትምህርት አልገባህ ቢለውም ቅን እና ታዛዥ ነበር። እመቤታችንን ተማጽኖም የብርሃን ጽዋን አጠጥታዋለች። 41 ድርሳናትንም ጻፈ።

#እንኳን_አደረሳችሁ
T.me/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
🟢🟡🔴
ሐምሌ 8 | የሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎት #_አባ_ኪሮስ ዐረፉ፨

#አቡነ_ኪሮስ የተወለዱት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው ነገሥታት ናቸው። ተወልደው ባደጉባት ሃገር ቁስጥንጥንያ ገና በልጅነት ምቾት ሳያሳሳቸው መጻሕፍትንና ትሕርምትን ተምረዋል።

ወንድማቸው (ታላቁ ቴዎዶስዮስ) በነገሠባቸው የመጀመሪያ ዓመታት በቤተ መንግስቱ ዙሪያ ግፍ በዝቶ ነበርና አቡነ ኪሮስ ከኃጢአት ለመራቅና ለጌታ ለመገዛት ከከተማው ጠፍተው፣ አሕጉር አቋርጠው ወደ ግብፅ #ገዳመ_አስቄጥስ መጡ።

እርሳቸውን ለመፈለግ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም። ይባስ ብሎ የንጉሡ ልጅ #ገብረ_ክርስቶስ ሙሽርነቱን ጥሎ ወደ ሌላ ሃገር መነነ። አቡነ ኪሮስ ለሙሽራው ገብረ ክርስቶስ አጎቱ ናቸው። አቡነ ኪሮስ በገዳም ውስጥ የታላቁ #አቡነ_በብኑዳ ደቀ መዝሙር ሆነው ለዘመናት ቆይተዋል።

ቅዱስ በብኑዳን አንበሳ በበላው ጊዜ በጣም አዝነው "ለምን ጌታ ሆይ?" በሚል መሬት ላይ ወድቀው አለቀሱ። "ምክንያቱ ካልተነገረኝ አልነሳም" ብለው ከወደቁበት መሬት ላይ ሳይነሱ ለ40 ዓመታት አልቅሰዋል። በዚህ ምክንያት ግማሹ አካላቸው አፈር ሆኖ ሣር በቅሎበታል። ጌታችን ተገልጦ ምክንያቱን ነግሯቸዋል። አካላቸውንም እንደነበረ መልሶላቸዋል።

አንድ ቀን ጻድቁ ለቅዱስ በብኑዳ ሞት ምክንያት የሆነው መነኮስ ታንቆ መሞቱን ሰምተው በጣም አዘኑ። ሱባዔ ገብተው፣ ፍጹም አልቅሰው፣ ከጌታም አማልደው፣ የዛን ኃጥእ ነፍስ ከሲዖል አውጥተዋል።

በሌላ ጊዜ ደግሞ ኃጥአን የሞሉበት አንድ ገዳም በግብጽ ነበርና መቅሰፍት ወርዶ ሁሉንም ባንድ ቀን ሲያጠፋቸው አዩ።

ጻድቁ በዚህም ምክንያት ለ30 ዓመታት አልቅሰው፣ ሙታኑን አስነሥተው፣ ንስሐ ሰጥተው፣ ገዳሙን የጻድቃን፥ ሕይወታቸውንም የፍቅር አድርገውታል።

ጻድቁ #እመቤታችንን ከመውደዳቸው የተነሣ በሥዕሏ ፊት አብዝተው ይሰግዱና ያለቅሱ ነበር። እመ አምላክም ተገልጣ ትባርካቸው ነበር።

ከዚህ በኋላ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ሒደው ለ57 ዓመታት ማንንም ሳያዩ ተጋደሉ። ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ (ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና) በየቀኑ ይጎበኛቸው፣ ቁጭ ብሎም ያወራቸው ነበር።

በመጨረሻም በዚህች ቀን ጌታ አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃን ሰማዕታትን፣ ድንግል እመቤታችንና ቅዱስ ዳዊትን አስከትሎ ወረደ።

"በስምህም ለድኆችና ለችግረኞች ምጽዋትን ለሚያደርግ ዓይን ያላየውን ጆሮም ያልሰማውን በሰው ልቡናም ያልታሰበውን በጎ ዋጋ እኔ እጥፍ ድርብ አድርጌ እሰጠዋለሁ።" የሚል እና ሌሎች ቃልኪዳኖችን ገባላቸው።

#ቅዱስ_ዳዊት ቀርቦ እያጫወታቸው፣ በበገናው እየደረደረላቸው፣ ከዝማሬው ጣዕም የተነሣ ነፍሳቸው ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች። ጌታችንም ታቅፎ፣ ስሞ ይዟቸው አረገ።

ሥጋቸውን #አባ_ባውማ ቀበሩት። የአቡነ ኪሮስ ቁመታቸው ቀጥ ያለ፣ ጽሕማቸውም የተንዠረገገ ነበር።

የአባ ኪሮስ፣ የአባ በብኑዳ፣ የአባ ሲኖዳ፣ የአባ ባውማ፣ የአባ ሚሳኤል በረከት ይደርብን።
#እንኳን_አደረሳችሁ
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
🇨🇬 ሐምሌ ፰፤ በዓለ እረፍቱ ለብጹዕ ወቅዱስ ባሕታዊ ማር አቡነ ኪሮስ ገዳማዊ፤ እንኳን አደረሳችሁ !
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
A fire broke out inside a factory in Kiryat Shmona, Israel after it was hit by a missile — local media reports
Forwarded from ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ
📌የክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ ልዩ ልዩ ታሪካዊ፣ ትንቢታዊ ትምህርቶች
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉የአለቃ አያሌውን ትምህርቶች በቀላሉ ለማውረድ(download ) ለመድረግ እነዚህን መስፈንጠሪያወች(links) ይጠቀሙ ፦
    👉ከጎግል ለማወረድ                                                                           📌 https://drive.google.com/drive/folders/1-uDfDVdeouGd8zg9iNnyZHUzOieChIeq?usp=sharing                                                         📌https://drive.google.com/drive/folders/1kQw8ifxKRGaYbdvGSLeO8-Y9AN2cPleI?usp=sharing
👉ከቴሌግራም ለማውረድ፦
📌https://www.tg-me.com/Yetewahedoarbegnoch/1970
📌 https://www.tg-me.com/aleqayalew/2185
#ሌሎች_ያጋሩ!
🟢 🟡 🔴
ሐምሌ 9 || አባታችን አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ በባሕር ውስጥ ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ መጸለይ የጀመሩበት እና ከ9 ዓመታት በኋላ የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለው ከባሕር የወጡበት ቀን ነው።

አምላከ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ይቅርታውን ያድለን።

T.me/Ewnet1Nat
ከሲኦል ነፍሳትን የማውጫ.pdf
328.3 KB
በአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቃልኪዳን የተገኘ [በአማርኛ]፦

ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡
ጸሎተ አቡነ እስትንፋሰክርስቶስ.pdf
675.4 KB
ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡
[ በግእዝ ]
2024/09/28 20:18:09
Back to Top
HTML Embed Code: