Telegram Web Link
Audio
የወንድማችን  ወልደ ጊዮርጊስ እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስአበባ
27/12/2016

👉 በሰማይም ንግሥት በምድርም ንግሥት ድንግል እናታችን ፤ የከበሩት በስላሴ በክብራቸው 
ፊት ዘወትር ለአገልግሎት የሚተጉት ቅዱሳን ሊቃነ መላእክት ፤ በሰማእትነት በታላቅ ተጋድሎ በቅድስና በእግዚአብሔር 
ከብረው ያለፉት ሁሉ ቅዱሳን አባቶቻችን እናቶቻችን ዘወትር የሚመሰገኑባት የሚዘከሩባት የስላሴ ምስጋና ውዳሴ እንደጅረት 
ውሃ ሳያቋርጥ የሚፈስባት ኢትዮጵያ ትነሳለች ፡፡ ለአለም ሁሉ ታበራለች ፡፡ ተዋህዶ እምነት ትፀናለች ፡፡ ትደምቃለች ፡፡ 
በብርሃናዊነቷ ለሰው ሁሉ ለትንሳኤው ለበቃው ሁሉ ታበራለች ታደምቃለች ያለማቋረጥ ከፈጣሪ / ከአብርሃሙ ሥላሴ / 
ከድንግል ከቅዱሳን ሊቃነ መላእክት ሁሉ ከቅዱሳን ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር የምታገናኝ የሕይወት የበረከት የደስታ ምንጭ 
የፈውስ ምንጭ ሁሉ ትሆናለች ፡፡

👉  ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አስር ገፅ 16 የተወሰደ።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
#ልዩ_ቃልኪዳን

አባታችን ይስሐቅም እንዲህ ብሎ ተናገረ፦

«ከዚህም በኋላ መልአክ ወደ  ሰማይ ወሰደኝ። አባቴ አብርሃምን አየሁትና ሰገድሁለት። እርሱም ሳመኝ። ንጹሕን ሁሉ ስለ አባቴ ተሰበሰቡና ወደ ውስጠኛው የአብ መጋረጃ ከበውኝ ከእኔ ጋራ ሔዱ እኔም ወድቄ ከአባቴ ጋራ ሰገድኩ።

የሚያመሰግኑ መላእክት ሁሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብሎ የሚመሰገን አሸናፊ እግዚአብሔር ምስጋናው በሰማይና በምድር የመላ ነው እያሉ ጮኹ።

አባቴ አብርሃምን እኔ በቦታዬ ልዩ ነኝ። ሰው ሁሉ ልጁን በወዳጄ ይስሐቅ ስም ቢሰይም በቤቱ ውስጥ በረከቴ ለዘላለም ይኖራል።

የቡሩክ ወገን የሆንክ አንተ ቡሩክ አብርሃም ሆይ መምጣትህ መልካም ነው። አሁንም በወዳጄ በልጅህ ይስሐቅ ስም የሚለምን ሁሉ በረከቴ በቤቱ ውስጥ ለዘላለም እንዲኖር ቃል ኪዳኔን አጸናለታለሁ አለው።

ትሩፋቱን ቅንነቱን ገድሉን የሚጽፍ ካለ ወይም በስሙ የተራበ የሚያጠግብ በመታሰቢያው ቀን የተራቆተ የሚያለብስ እኔ የማያልፈውን መንግሥት እሰጠዋለሁ።

አብርሃምም እንዲህ አለ፦ አቤቱ ዓለሙን ሁሉ የያዝክ አብ ሆይ ቃል ኪዳኑን ገድሉን ይጽፍ ዘንድ ካልተቻለው ቸርነትህ ትገናኘው። አንተ ቸር መሐሪ ነህና እንጀራ የሌለው ችግረኛ ቢሆንም።

ጌታም እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ በወዳጄ በይስሐቅ በመታሰቢያው ዕለት ከሌሊት ጀምሮ በጸሎት ይትጋ አይተኛ እኔም መንግሥቴን ከሚወርሱ ጋራ ከበረከቴ እሰጠዋለሁ

አባቴ አብርሃምም ሁለተኛ እንዲህ አለ። በሽተኛ ድውይ ከሆነ ቸርነትህ ታግኘው። ጌታም እንዲህ አለ፦

ጥቂት ዕጣን ያግባ። ዕጣንን ካላገኘ የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ፈልጎ በልጅህ በወዳጄ በይስሐቅ መታሰቢያ ቀን ያንብበው። ማንበብም የማያውቅ ከሆነ ወደሚያነቡለት ሒዶ እሷን አስነብቦ ይስማ። ከእነዚህም ይህን ማድረግ ካልቻለ ወደ ቤቱ ገብቶ ደጁን ይዝጋ፤ እየጸለየ መቶ ስግደቶችን ይስገድ። እኔም የሰማይ የመንግሥት ልጅ አደረገዋለሁ።

ለቁርባን የሚሆነውንና መብራትን ያገባ እኔ ያልኩትን ሁሉ የሚያደርግ እርሱ የመንግሥተ ሰማያትን ርስት ይቀበላል።

ቃል ኪዳኑንና ገድሉን ትሩፋቱን ለመጻፍ ልቡን ያበረታውን እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ በሺው ዓመት ምሳ ላይም ይገኛል።»

እግዚአብሔርም ይህን ብዙ ነገርን በተናገረ ጊዜ ያዕቆብ አይቶ በመደንገጥ ነፍሱ ተመሠጠች።

ይስሐቅም ያዕቆብን አንሥቶ ልጄ ሆይ ዝም በል አትደንግጥ ብሎ ጠቀሰው። ከዚህም በኋላ ሳመውና በሰላም አረፈ። ከኤሞር ልጆች በገዛው እናቱ ሣራ በተቀበረችበት በአብርሃም መቃብር ተቀበረ።

T.me/Ewnet1Nat
Audio
መልክዐ ቅዱስ አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️ቄስ ጳጳስን ማውገዝ ይችላል❗️

«ጉባኤያቸው/ሲኖዶሱ የሚወስነው ውሳኔ ግልጽ የሆነ የአስተምህሮ ስህተት ያለበት ሲሆን ያኔ ራሳቸውን ስለለዩ ሌላ አውጋዥ ራሱ አያስፈልጋቸውም! ራሱ ስህተቱን ሲፈጽሙ ከቤ/ክ ተቆርጠው ይወጣሉ!»
(የማኅበረ ድቁሳን "የቦሩ ሜዳ" ምስክርነት)

፩. አባ ጳውሎስ ካቶሊካዊ ለምን ይባላሉ?

(መልስ)
በቫቲካን ከካቶሊክ ጋር በጸሎትና በመዓድ ስለተባበሩ፣ እንደ ካቶሊክ አለቃ ራሳቸውን በመንፈስቅዱስ ቦታ ተክተው ከሲኖዶስ የበላይ የሚያደርጋቸውን ሕግ ስላወጡ፣ የምንፍቅና መጽሐፍ ስላሳተሙ፣

፪. ሲኖዶሳቸው ለምን ተወገዘ?

(መልስ)
እንደ ኬልቄዶን ጉባኤ በኅብረት ከአባ ጳውሎስ ክህደት ጋር ስለተስማሙ፣ ፓትርያሪኩን የሲኖዶስ የበላይ አድርገው በራሳቸው ላይ ጣዖት ስላደረጉ፣ የአባ ጳውሎስ የሃይማኖትና የሥርዓት ጥሰት እንዲሁም ሕገ ቤ/ክን ማፍረሳቸውን ሳይቃወሙ በመፈረማቸው እና በማጽደቃቸው፣

፫. አለቃ አያሌው በስሜት ነው ያወገዙት?

(መልስ)
በፍጹም! ሁለት ጊዜ

1. በጥቅምትና ኅዳር 1987 ዓ.ም በጽሑፍ ለሲኖዶሱ

2. በ1988 ዓ.ም (ጥቅምት እና ሚያዝያ ወር ላይ) ለሲኖዶስ ጉባኤ ችግሩን በጽሑፍ አባዝተው አጀንዳ አስይዘው፣ በአካል ሲኖዶስ ፊት ለፊት ስህተቱን ጥሰቱን አስረድተው የሚሰማ ሲጠፋ በእግዚአብሔር አዛዥነት በሥልጣናቸው አውግዘዋል።

ሲኖዶሱ ማረም ሲገባው አብሮ በሥርዓቱ ላይ ስላመጸ፣ ማኅበረ ካህናትም ዝም ስላለ እንደ ቅ/ዲዮስቆሮስ ብቻቸውን አወገዙ።

🍀 የአለቃ አያሌው ቃለ ውግዘት 👇
https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat/2959

🍀 ቃለ ውግዘቱ በራሳቸው ድምፅ 👇
https://www.tg-me.com/aleqayalew/4613

🍀 የአባ ጳውሎስ ምንፍቅና እና ያልተፈታው ውግዘት ማስረጃዎች 👇
https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat/11853
Audio
መልክአ አቡነ አፍጼ
Audio
መልክአ አቡነ ጉባ
Audio
መልክአ አቡነ ገብረ ናዝራዊ
Audio
መልክአ ቅድስት አርሴማ
Audio
መልክአ አቡነ እጨጌ ዮሐንስ
Audio
መልክአ ጻድቃን ዘማኀበረ ዴጓ
2024/09/26 21:48:20
Back to Top
HTML Embed Code: