Telegram Web Link
🍀 🌹 🍀 🌹 🍀 🌹
ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም

ቸር #እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ ጾም ነው። የሰማይና የምድር ፈጣሪ የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ በአርአያነት ከጥምቀት ቀጥሎ የሥራው መጀመሪያ ያደረገው ጾምን ነው።

ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 7 አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ፣ በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች። ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው።

"ፈለሠ" - ሔደ፣ ተጓዘ እንደ ማለት ሲሆን " #ፍልሠታ" ማለት የእመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው።

#እመ_ብርሃን በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ኖራ ካረፈች በኋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም።

ለጊዜው በዕፀ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነሥታ ዐርጋለች። እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና።

ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው #ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው። ከ7ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት።

ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል።

🍀 የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ፣ ውሃ እየተጎነጩ ክብርን ያገኛሉ።

🍀 ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን፣ በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጓሜውን፣ በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ።

🍀 ይህ ሁሉ ባይቻል በቤታቸው ክትት ብለው በትጋት ይጾሟታል።

#ጽንዕት_በድንግልና#ሥርጉት_በቅድስና #እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን።

አእምሮውን፥ ለብዎውን፥ ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን።


ጾሙን የፍሬ፣ የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን።
🌹🍀🌹🍀🌹

#እንኳን_አደረሳችሁ
T.me/Ewnet1Nat
በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት  የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
ዛሬ በ29/11/2016 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ የ11 ሰዎች አስከሬን መገኘቱንና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የካዎ ኮይሻ ወረዳ አስተዳዳሪ መግለጻቸውን የወረዳው መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ገልጿል።
አዲስ አበባ ጉርድ ሾላ አካባቢ በአንድ ቀን ዝናብ  ተጥለቅልቋል።
#ትግራይ

" በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ፅ/ቤቱ

በትግራይ ማእከላዊ ዞን ዓድዋ ወረዳ የመሬት መደርመስ አደጋ ተከስቷል።

የመሬት መደርመስ አደጋው በሰው ህይወት ያደረሰው ጉዳት ባይኖርም  የእህል አዝርእት ሙሉ በሙሉ አውድሟል።

የመሬት የመደርመስ አደጋ ያጋጠመው ሀምሌ 29/2016 ዓ.ም በዓድዋ ወረዳ በታሪካዊትዋ የይሓ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው።

የወረዳው የቁጠባ ዘርፍ ፅ/ ቤት ፤ " በአደጋው የ21 አርሶ አደሮች የተዘራ እህል ሙሉ በሙ ወድሟል " ብሏል። 

' ደምባፍሮም ' በተባለች መንደር የተዘራው ስንዴ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተመላክቷል።

" ከአሁን በፊት በትግራይ ያልተለመደ የመሬት የመደርመስ አደጋ አሁን አሁን መታየት ጀምሯል "  ያለው ፅ/ቤቱ " አርሶ አደሩ የክረምቱን ሀያልነት ከግምት ያስገባ ሁሉን አቀፍ ጥንቃቄ እንዲያደርግ " ሲል አሳስቧል።

ዘንድሮ በትግራይ ክልል ያለው ኃይለኛ ክረምት በንብረትና በእንስሳት አደጋ በማደረስ ላይ ይገኛል።

ባለፈው ሳምንት በክልሉ የራያ ጨርጨር ወረዳ ዝናብ ያስከተለው ኃይለኛ ጎርፍ በ106 የቤት እንስሳትና በ11 ሄክታር የእርሻ መሬት ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በጎርፉ 91 እንስሳት ሲወሰዱ ፣ 15 ቱ የአካል ጉዳት ደርሷቸዋል። በ11 ሄክታር የተዘራ እህል ከጥቅም ውጭ ሆኗል
በድሬደዋ አስተዳደር በደረሰ ድንገተኛ የመሬት መሽራተት አደጋ የአራት አርሶ አደሮች የእርሻ ማሳ መወድሙ ተገለፀ

በድሬዳዋ አስተዳደር ዋሂል ወረዳ ሁሉል ሞጆ ገጠር ቀበሌ ለመስኖ የሚውል ኩሬ በመሬት መንሸራቱቱ ሳቢያ 50 መኖሪያ ቤት ላይ ጉዳት በማድረሱ የአካባቢውን ዜጎች ወደ ተሻለ ቦታ የማስፈር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ተናግረዋል ።

በድሬዳዋ አስተዳደር ዋሂል ወረዳ ሁሉል ሞጆ ገጠር ቀበሌ አካባቢ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መሸራተት አደጋ ሳቢያ የ4 አባወራዎች የእርሻ ማሳ የወደመ ሲሆን ለመስኖ ሲውል የነበረ ግድብ በመሬት መንሸራተቱ ሳቢያ ሀምሳ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት በመድረሱ የአካባቢውን ነዋሪዎች ወደ ተሻለ አካባቢ ለማስፈር ስራ ተጀምሯል ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰደድ እሳት በካሊፎርኒያ ያደረሰው ውድመት‼️
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
🇨🇬 ስለ ደገኛው ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ መነሳትና መንግሥቱ ምን አይነት እንደሚሆን በቤተክርስቲያናችን ቅዱሳት መጽሐፍት ትውልዱ ይማርና ይጠብቀው ዘንድ ቅዱሳን አባቶቻችን በስውርም በግልጽም አትመው ለእኛ ትውልድ አድርሰውልናል። ይሁንምና "ኢይከብር ነቢይ በሃገሩ" ሆኖ ማንም እነሱ ያሉትን ሲያምንና ሲቀበል አይታይም። ይልቁንስ በዘመን መካተቻ ወቅት የተነሳው የእኛ ትውልድ አንዳንዱ በዲያብሎስ መንፈስ ተታሎ ያልሆነውን "እኔ ነኝ የምስራቁ ቴዎድሮስ ይመጣል የተባልኩት ንጉሥ" ሲል ብዙኃኑ ደግሞ "የምን ቴዎድሮስ የምን ንጉሥ በ21ኛ ክፍለ ዘመን" ሲል ይውላል ያድራል።

ቢሆንም እውነተኛው በቅዱሳት መጻሕፍት እልፍ ጊዜ ስሙ የተጻፈው ለዘመናት ሲጠበቅ የኖረው የኢትዮጵያ ትንሣኤ አብሳሪ በልዑል እግዚአብሔርና በእናቱ የተቀባው ንጉሠ ነገሥት ብርሃን ዘኢትዮጵያ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት መልዕክታት የተገለጠ በመሆኑ ልብ ያለው ልብ ይሏል፤ ሌላ የለም፡ አይኖርምም። መቼስ ሃሰተኛ መሲህ ክርስቶሶችና የሃሰተኛው መሲህ ቤተሰቦች ምድርን ስለከደኑ እውነተኛው የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስና እውነተኛ ክርስቲያኖች የሉም አይባልም። ይኼም ያው ነው። "እኔ ቴዎድሮስ ነኝ፤ እኔ የኢትዮጵያ መጻኢ ንጉሥ ነኝ፤ ከእኔ ውጭ ኢትዮጵያ ተስፋ የላትም" ብሎ የተናገረው ቀርቶ በልቡ ያሰበውም ቅጣቱን አይችለውም። ምክንያቱም ቴዎድሮስነት በጥረት የሚሆኑት ሳይሆን ከእግዚአብሔር የሚቀበሉት ስጦታ ነው። ይኽም ለአንድ ባርያው ከተሰጠ ከረመ።

👑 “አመድ ፡ ከዘነመ ፡ ከአራት ፡ ዓመት ፡ በኋላ ፡ የጌታችን ፡ የኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሰማዕት ፡ የሆነ ፡ በፊቅጦር ፡ በገድሉ ፡ መጽሐፍ ፡ እንደተነገረው፡ የስሙ ፡ ምልክት ፡ <ቴ> ተብሎ ፡ የተመለከተው ፡ ይነግሳል ፡፡”

👉🏿ድርሳነ ዑራኤል ዘጥቅምት 2፥44
2024/09/29 02:24:04
Back to Top
HTML Embed Code: