Telegram Web Link
🟢🟡🔴
ሐምሌ 25 | #ቅዱስ_መርቆሬዎስ የልደቱና የተአምሩ በዓል ነው፨

ይህም ሰማዕት ከእስልምና እምነት መልሶ ክርስቲያን ያደረገው አንድ እስላም ሰው አለ።

ይኸውም የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያኑ በተሠራችበት በምስር አገር የሚኖር ከመሳፍንት ወገን የሆነ ወጣት ነበረ።

ከብዙ ሰዎችም ጋር ሆኖ ወደ መሐመድ መቃብር ለመሄድ እንዳሰበ ለአባቱ ሲነግረው ስንቅ ሰንቀው በሰላም ወደ መካ መዲና ሸኙት።

መካ ደርሰውም ሥራቸውም ፈጽመው ወደቤታቸው እየተመለሱ ሰባት ቀን ተጓዙ። በሌሊትም ሲጓዙ ስለ ሥጋዊ ግዳጁ ያ እስላም ወጣት ከግመል ላይ ወርዶ ለመጸዳዳት ዘወር አለ።

እነርሱም አብሯቸው የሚጓዝ መስላቸው ስለነበር ባልንጀሮቹም በበረሃው ውስጥ ትተውት ሄዱ። እርሱም ወዴት እንደሚሄድ ስላላወቀ አራዊትም እንዳይበሉት ፈርቶ እጅግ ደነገጠ።

በዚያም ጊዜ በምስር አገር በአባቱ ቤት አቅራቢያ ያለች የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስን ቤተ ክርስቲያን አስታውሶ በልቡ ቅዱስ መርቆሬዎስን እንዲያድነው በመለመን ተሳለ። ወዲያውም ቅዱስ መርቆሬዎስ በፈረሱ ተቀምጦ ወደ እርሱ መጣና ‹‹ከወዴት ነህ? ከዚህ በረሃ ውስጥስ እንዴት ጠፋህ?›› አለው።

ወጣቱ እስላምም የሆነውን ነገረው። ቅዱስ መርቆሬዎስም ‹‹ና በኋላዬ በፈረሱ ላይ ተፈናጠጥ›› አለውና በአየር ላይ እየበረረ በምስር አገር ወዳለች የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ዐይን ጥቅሻ አደረሰውና እንደተዘጋች በውስጧ አስገባውና ከእርሱ ተሰወረ።

ይህም ወጣት በኋላ አምኖ ተጠምቆ ብዙ ሰማዕትነት ተቀብሏል። ገዳምም ገብቶ ብዙ ከተጋደለ በኋላ እንደገና ወደ አገሩ ተመልሶ ብዙዎችን ወደ ክርስትና አምጥቷል።

በቅዱስ መርቆሬዎስ ስም ቤተ ክርስቲያን አሠርቶ አበ ምኔትም ሆኖ ብዙ መነኮሳትን አፍርቷል።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Audio
ገድለ መርቆሬዎስ ዘወርኃ ሐምሌ
Audio
ገድለ ቅዱስ አቡነ አቢብ
🟢🟡🔴
ሐምሌ 26 | ጌታችን ያከበራቸው፦

🍀 መልካም ሽምግልና የነበረው የእመቤታችን ድንግል ማርያም እጮኛዋ ድካሟን ለመሳተፍ ክብር ይግባውና ለጌታችንም አሳዳጊው ለመሆኑ የተገባው #ጻድቁ_ዮሴፍ ዐረፈ።

🍀 «ስለ ትምህርትህና ስለ ስብከትህ ኢትዮጵያን ከጨለማ አውጥተህ በሃይማኖት ስለ አበራሃት…» ብሎ ቃልኪዳን የሰጣቸው #አቡነ_ሰላማ #ከሣቴ_ብርሃን ዕረፍታቸው ነው፡፡

ሜሮጵዮስ ሰው ወደ ሕንድ አገር ሊአልፍ ወዶ ከጢሮስ አገር መጣ። ከእርሱም ጋራ ዘመዶቹ ሁለት ብላቴኖች ነበሩ። የአንደኛው ስሙ ፍሬምናጦስ የሁለተኛውም ኤዴስዮስ ይባላል። ሲድራኮስ የሚሉትም አሉ።

በኢትዮጵያ በኩል ወዳለው ወደ አፍሪቃ ባሕር ወደብ ደረሱ ልቡ የተመኘችውን የኢትዮጵያን አገር መልካምነቷን ሁሉ ተመለከተ። 

ከዚህም በኋላ በድንገት ወንበዴዎች ተነሥተው በመርከብ ከአሉት ሁሉ ጋር ገደሉት። እኒህ ሁለት ልጆች ግን ተረፉ። የአገሩ ሰዎችም አገኟቸው፤ ወደ ንጉሥ አይዛና ወስደው አንድ እጅ መነሻ አድርገው እነርሱን ሰጡት። ንጉሡም ተቀበላቸው። 

የንጉሡም ልጆች አብርሃ ወአጽብሓ አድገው በነገሡ ጊዜ ኤዴስዮስ ወደ አገሩ ተመለሰ። ፍሬምናጦስ ግን ወደ እስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት አባ አትናቴዎስም ሔደ።

ስለ ኢትዮጵያውያንም ሃይማኖት ጳጳስ ሳይኖራቸው ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዴት እንዳመኑ ነገረው። 

አባ አትናቴዎስም በሰማ ጊዜ እጅግ አደነቀ። ፍሬምናጦስንም የነጻ ሕዝብ አገር ለሆነችው ለኢትዮጵያ አገር ጳጳስ ይሆን ዘንድ በግድ ሾመው

በኢትዮጵያም አገሮች ሁሉ የቀናች ሃይማኖትን ሰበከ። አስተማረም ክብር ይግባውና ክርስቶስን የጌትነቱን ብርሀን በሁሉ አገሮች ገለጠ። ስለዚህም ከሣቴ ብርሃን (#ብርሃንን_ገላጭ_ሰላማ) ተባለ። ሁሉንም አስተካክሎ በሰላም ዐረፈ።

T.me/Ewnet1Nat
Audio
መልክአ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ኢትዮጵያዊ የተክለሃይማኖት ወዳጅ🇨🇬🇨🇬🇨🇬)
🟢🟡🔴
ሐምሌ 27 |
#የቅዱስ_ላሊበላ ሚስት #ቅድስት_መስቀል_ክብራ ዐረፈች፨

ይኽች ቅድስት የትውልድ ሀገሯ ወሎ ላስታ ቡግና ነው። በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነገደ አገው ከሆኑት ከአባቷ ስምዖን እና ከእናቷ ሶፍያ ተወለደች።

የታላቁ ጻድቅ ንጉሥ የቅዱስም ላሊበላ ሚስት ናት። ከእርሱም ደገኛውን ይትባረክን ወልዳለች።

ቅዱስ ላሊበላን እና ቅድስት መስቀል ክብራን ሁለቱ እንዲጋቡ ያዘዛቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶ የሚያንጻቸውውን የሕንጻ ንድፎችንና ሌሎችንም ብዙ ምሥጢራትን ካሳየውና ወደ ምድር መለሰው።

በድጋሚ ተገልጦለት "እንዳንተ የተመረጠች ናት። እንደ ልብህም ትሆናለች፣ ሥራዋም ከሥራህ አያንስም። እርሷ የተመረጠች የእግዚአብሔር አገልጋይ ናትና" በማለት መልአኩ የቅድስት መስቀል ክብራን ንጽሕናና ቅድስና መስክሮላታል።

ቅዱስ ላሊበላ 11 እጅግ አስደናቂ የሆኑ ፍልፍል ቤተ መቅደሶቹን ከመላእክት ጋር ሲያንጽ ብታየው ልቧ በመንፈሳዊ ተመስጦ ተመልቶ፣ እርሷም እግዚአብሔር ፈቅዶላት አስደናቂውን የአባ ሊባኖስን ቤተመቅደስ ራሷ እንዳነጸችው መጽሐፈ ገድሏና ገድለ ቅዱስ ላሊበላ ያስረዳል።

ቅድስት መስቀል ክብራ ቅ/ገብርኤል በመንገድ እየመራ፣ ቅ/ሚካኤል ዘወትር እየጠበቃት በትግራይ ከሰው ተለይታ በታላቅ ተጋድሎ ኖረች። በቀን እልፍ እልፍ እየሰገደች በታላቅ ተጋድሎ ስትኖር ጌታችን ተገልጦ ክብሯ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት ጋር እኩል መሆኑን ነግሯታል።

ይኽችም ቅድስት ብዙ ሐዋርያዊ አገልግሎት ፈጽማለች። ለምሳሌ በመስቀል ጦርነት ጊዜ እስላሞች ከባሕር ማዶ እየፈለሱ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በፍቅር እየተቀበለችና እያስተናገደች ሃይማኖትንና ሕገ እግዚአብሔርን እያስተማረች ወደ ክርስትና እንደገቡና እንዱጠመቁ አድርጋለች።

T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሐምሌ 28 | ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ፣ ሐዋርያና ሰማዕት #አቡነ_ፊልጶስ ዐረፉ፨

የጻድቁ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሲሆኑ የተወለዱት በምድረ ሽዋ በ1266 ዓ/ም ነው። ከልጅነታቸው ጀምረው ምሥጢር ተመራማሪና መጻሕፍትን መርማሪ የነበሩት ጻድቁ የመነኑት ገና በ15 ዓመታቸው ነበር።

#በደብረ_ሊባኖስ በአሞክሮ ለ3 ዓመታት ቆይተው መንኩሰዋል። ለ22 ዓመታትም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሆነው አገልግለዋል።

አቡነ ተክለ ሃይማኖት በ1306 ዓ/ም ነሐሴ 24 ቀን ሲያርፉ የተተኩት አባ ኤልሳዕ ቢሆኑም ለ3 ወራት ቆይተው ዐርፈዋል።

ከ1307 ዓ.ም ጀምሮ ለ28 ዓመታት አቡነ ፊልጶስ የደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት (እጨጌ) ሁነዋል።

ከዚያም በዘመነ ዓፄ ዓምደ ጽዮንና በአፄ ሰይፈ አርዕድ እውነትን በመናገራቸውና ነገሥታቱን በመገሠጻቸው ብዙ ስደት፣ መከራ፣ እሥራትና ግርፋት ደረሰባቸው። በስደትም ለ6 ዓመታት ከ9 ወራት ቆዩ።

ሃገሪቱን በስብከተ ወንጌል ካበሩ #12ቱ_ንቡራነ_እድ አንዱ የሆኑት #እጨጌ_አባ_ፊልጶስ በተወለዱ በ74 ዓመት ከ9 ወራቸው በ1341 ዓ/ም ዐርፈዋል።


ባልና ሚስት የሆኑት ቅዱሳን እንድራኒቆስና አትናስያ ዐረፉ፨

#እንድራኒቆስና_አትናስያ በዘመናቸው ከልጅነት ጀምረው ቃለ እግዚአብሔርን የሚሰሙ፣ ለወላጆቻቸው የሚታዘዙ ነበሩ።

በእግዚአብሔር ፈቃድ በተክሊል ተጋቡ፤ 40 ቀን ጾሙ። እንደጨረሱ አብረው ሳይተኙ ለዓመታት እንግዳና ነዳያንን በመቀበል በፍቅር ኖሩ።

በኋላም ሁለት ልጆችን ወለዱ፤ በ12 ዓመታቸው ሞቱባቸው። ቅ/እንድራኒቆስ እያለቀሰ አመሰገነ፤ ቅ/አትናስያ ግን መቃብራቸው ላይ ስታነባ ልጆቿ ገነት እንደገቡ በራእይ አየች።

ስለዚህ ተስማምተው መነኮሱ። 12 ዓመት ተለያዩ። ኋላም በምንኩስና ጓደኛማቾች ሆነው ሐምሌ 28 ዐረፉ።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Forwarded from ቅድስት በርባራ ዘኒቆመዲያ Saint BarBara Αγία Βαρβάρα (ገድላት እና ስንክሳር)
ስለ አሁኑ ዘመን የአቡነ ፊሊጶስ ትንቢት፦

በወቅቱ የነበሩት ጳጳስ አባ ያዕቆብ በብዙ ልመናና ምክር አቡነ ፊሊጶስን ጳጳሱ ራሱ የሚለብሰውን የክብር ልብስ አልብሶ በሸዋ አገር ላይ ኤጲስ ቆጶስነት ሾመው።

ከተሾሙም በኋላ አቡነ ፊሊጶስን ‹ሌሎችን ሹምልን› የሚሉ በርካቶች ሲያስቸግሯቸው እሳቸው የሰጡት ምላሽ ‹‹በሥልጣን ፍለጋ ምክንያት ይህችን የትህርምትና የጽሙናን ቦታ (ደብረ ሊባኖስን) የጨዋታ የተድላ ቦታ እናደርጋታለን›› በማለት በወቅቱ ማንንም አልሾምም ብለው ነበር።

አያይዘውም በዚሁ በሹመት ሽኩቻ ምክንያት ወደፊት የሚፈጠረውን ነገር በመንፈስ ቅዱስ መነጽርነት አይተውት የሚከተለውን ትንቢት ተናግረዋል፦

‹‹እውነት እላችኋለሁ በመጨረሻው ዘመን ደጋጎች ሰዎችን ክፉዎችና ተሳዳቢዎች የሚያደርጉ፣ ሐሰተኞችና ዋዛ ፈዛዛ የሚወዱትን ደጋጎች የሚያደርጉ ሰዎች ይመጣሉ፡፡

«በመጨረሻው ዘመን ኃጥአን በጻድቃን ይመሰላሉ፣ ጻድቃንን ኃጢአተኞች ያደርጓቸዋል፡፡ በዚያን ዘመን እውነተኛዎቹ መምህራን አይሾሙም፣ ኃጢአተኞች መማለጃ ሰጥተው ወሬ እያቀበሉ ይሾማሉ፣ እንደ እባብ ክፉ ነገርን ለማድረግ ፍላፃቸውን ያሾሉ ደጋግ ሰዎችን በነገር ያጠፏቸው ዘንድ በእውነት ንጹሕ የሆኑትን ሰዎች አመፅን በተመላ አንደበታቸው ሹመትን ከመውደድ የተነሣ በቅናት ያጠፏቸዋል፡፡

«በዚያን ዘመን መጻሕፍትን የሚያውቁ አይሾሙም፣ ነገርን የሚያመላልሱና የአገሮችን ቋንቋ የሚያውቁ ከመኳንንትና ከነገሥታት ዘንድ ሔደው ነገርን የሚሠሩ ሰውን የሚያጣሉ በአመፅ ሹመትን የሚያገኙ ብቻቸውን ይሾማሉ እንጂ ደጋጎች አይሾሙም፡፡

«በሚመረጡበትም ጊዜ ከአባታቸው ከሰይጣን ጋር ሆነው ‹እገሌ መጻሕፍትን ያውቃል፣ የአገሮችን ቋንቋ የሚያውቅ ይሾም› ይላሉ፡፡

ያንጊዜም አመፅ ይበዛል፣ ፍቅርም ትጎድላለች፡፡ ከእኔ በኋላ የሚሆነውን እነሆ ነገርኳችሁ ይህንንም አውቃችሁ በልቡናችሁ ያዙ፡፡››

የአቡነ ፊሊጶስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን፡፡

🍀🍀🍀
ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሠ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
ድንግል ማርያም እሙ ወእምነ ንግሥተ ፅዮን ወንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ

በ 28/11/2016 ድንቃ ድንቅ አስተማሪ ምስክርነት ይለቀቃል 👇👇👇
Audio
የእህታችን አፀደ ማርያም እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስአበባ
28/11/2016

👉 ማንኛውም የኢትዮጵያ አለም ብርሃን ቤተሰብ ቅን ሕዝብ ሊተገብረው የሚገባውን
ጠንቅቆ ያውቃል ፡፡ በቅንነታችሁ በየዋህነታችሁ ያላችሁ በተለያየ ምክንያት በኛ ዘንድ ባትኖሩም በእምነት በእግዚአብሔር
ጉያ መሆናችሁን ተረድታችሁ ፅኑ ፡፡

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አስር ገፅ 50 የተወሰደ
የእህታችን ወለተ ብርሃን እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ኃይለ ገብርኤል እንዳቀረበው
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስአበባ
28/11/2016

👉 ሕዝቡም ከጭንቁ የተነሳ
ዓይኑ እያየው ቤቱ ንብረቱ ስለሚፈርስ፤ ሞትን አይፈራም። ስለሆነም በመንግሥትም ሆነ በሚታመንበት
ኃይል ላይ ዘምቶ መተላለቅ ይሰፍናል።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አምስት ገፅ 38 የተወሰደ
የወንድማችን ወልደ ገብርኤል እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከደቡብ አፍሪካ = ኦጊስ
28/11/2016

👉 ይህም ብቻ አይደለም
ትእግስትም ተሟጦ የመጨረሻው ምድር ከተፈጠረችበት ጊዜ አንስቶ ያላየችው ተደራራቢና ተከታታይ
የእሳትና የማዕበል የቸነፈር የምድር ነውጥ እሳተ ጎሞራ ፍጅት ብርቱ አውዳሚ በረዶ ጎርፍ የመጣበትና
የሚወርድበት መሆኑን ለማሳወቅ የመጣ ነው።

👉 የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ዘጠኝ ገፅ 27 የተወሰደ
እስካሁን የ11 ሰዎች አክስሬን ተገኝቷል።

በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ ዛሬ ረፋድ 5 ሠዓት አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

በተከሰተው አደጋ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ የ11 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል።

የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የካዎ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደር አሳውቋል።

ከቀናት በፊት በዚሁ አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ 1 ሰው ህይወቱ ማለፉ እና 1 ሰው ከባድ ጉዳት እንደረሰበት ይታወሳል።

*ወረዳው ኮሚኒኬሽን
◦●●●◦
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም፨

~❴ ሐምሌ ፴/30 ❵~
     በዚህች ቀን፦

● ሐዋርያው_ቅዱስ_እንድርያስ አስገራሚ ተአምር በማድረግ ማትያስን ሰውን ከሚበሉ ሰዎች እጅ ያዳነበት ዕለት ነው፡፡

● ስለ ጽድቅ ሲል ራሱን የሸጠው አባ_ጳውሎስ_መናኒ ዕረፍቱ ነው፡፡

● ቅዱሳን የገሊላ ሰማዕታት መርቆሬዎስና_ኤፍሬም ዕረፍታቸው ነው፡፡

● ቅዱስ_ሱርያል_መልአክ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ዕለት ነው፡፡

● ሃይማኖትን ከምግባር አስተባብራ የያዘች፣ ጾም ጸሎትን ገንዘብ በማድረግ በመንፈሳዊ ተጋድሎዋ የተመሰገነች ንግሥት፣ የንጉሥ ናዖድ ሚስት ንግሥት_ማርያም_ክብራ ዐረፈች።

◦●●●◦

    •• ቅዱሳን መርቆሬዎስ እና ኤፍሬም ••
                          ๏-❀-๏   

ሐምሌ ሠላሳ በዚች ቀን ቅዱሳን የገሊላ ሰዎች መርቆሬዎስና ኤፍሬም በሰማዕትነት ዐረፉ።

እሊህም ከአክሚም ከተማ የመጡ የሚዋደዱ በመንፈስ ቅዱስ ወንደማሞች በሥጋም ዘመዳሞች ነበሩ። መንፈሳዊ ስምምነትንም ተስማምተው በላይኛው ግብጽ ካሉ ገዳማት በአንዱ ገዳም መነኰሱ። በጾም በጸሎትና በስግደት እየተጋደሉ በገዳሙ ውስጥ ሃያ ዓመት ያህል ኖሩ። 

ከዚህም በኋላ ጠላት ሰይጣን በአብያተ ክርስቲያናት ላይ ከአርዮሳውያን ችግርን በአመጣ ጊዜ አርዮሳውያኑ በአርዮሳዊ ንጉሥ ትእዛዝ መሥዋዕትን ሊሠው ወደ ኦርቶዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገቡ። ቀንተው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገቡና አርዮሳውያን ያኖሩትን መሥዋዕት በተኑት። 

እንዲህም አሏቸው፦ በሥሉስ ቅዱስ ስም ያልተጠመቀ መሥዋዕትን ያሳርግ ዘንድ አይገባውም።

ያን ጊዜም አርዮሳውያን ይዘው ደበደቧቸው ታላቅ ግርፋትንም ገረፏቸው። ዐጥንቶቻቸውም እስኪሰበሩ ድረስ በምድር ላይ ጥለው ረገጧቸው። ነፍሶቻቸውንም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ሰጡ።

የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ። ምእመናንም መጥተው ሥጋቸውን ወሰዱ። በአማሩ ልብሶችም ገንዘው በመልካም ቦታ አኖሯቸው። ከእነሱም ለበሽተኞች ታላቅ ፈውስ ሆነ። 

                 ◦🌿🌿🌿

            •• ቅዱስ ጳውሎስ መናኒ ••
                          ๏-❀-๏

በዚህችም ቀን ክብርንና ብልጽግናን ንቆ የተወ ጳውሎስ ዐረፈ።

ይህም ቅዱስ ባለጸጋ ነበር። ደግ የሆነች ሚስትና የተባረኩ ልጆችም ነበሩት። መነኮስ ሊሆን ወደደ ሚስቱንና ልጆቹንም ጠርቶ፦

« እነሆ ክብር ይግባውና ስለ ክርስቶስ ፍቅር እሸጣችሁ ዘንድ ወደድኩ » አላቸው። እነርሱም አሳዳሪያቸን ነህና የወደድከውን አድርግ አሉት። 

ከዚህም በኋላ ገንዘቡን ሁሉ ወስዶ ለድኆችና ለችግረኞች በተነ። ሚስቱንም ወደ ደናግል ገዳም ወሰዳት። እመምኔቷንም ጠራትና እንዲህ አላት፦

« ለገዳምሽ አገልጋይ ትሆን ዘንድ ሚስቴን ልሸጥልሽ እወዳለሁ።» እርሷም እሺ አለችው። የመሸጫዋንም ደብዳቤ ጻፈ የሺያጭዋን ዋጋ ተቀብሎ ለድኆች ሰጠ።

ልጆቹንም ወደ አበ ምኔቱ ወስዶ እንደ እናታቸው ሸጣቸው። ለአበ ምኔቱም አሳልፎ ሰጣቸው። 

ከዚህም በኋላ ወደ ሌላ ቦታ ሔደ። ራሱንም ለገዳሙ አለቃ ሸጠ። አለቃውንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ብቻዬን ልገባ እሻለሁ አለው።

በገባም ጊዜ በሩን በላዩ ዘጋ። እጆቹንም ዘርግቶ ቆመ በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብሎ ጮኸ፦ አቤቱ በፍጹም ልቡናዬ ወዳንተ እንደ መጣሁ አንተ ታውቃለህ። 

ወደርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ፦ ሀሳብህን ሁሉ አወቅሁ፤ በፍጹም ልቤም ተቀበልኩህ።

ከዚህም በኋላ መነኮስ አስጨናቂ የሆኑ የገዳሙን ሥራዎች ሁሉ እንደ ባሪያ እየሠራ ኖረ ራሱንም ከሁሉ እጅግ አዋረደ፤ ነገር ግን ስለ መዋረዱ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገው።

ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ ከዚህም በኋላ በሰላም ዐረፈ።

                  ◦🌿🌿🌿
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሰቆቃወ  ጴጥሮስ
የሊቁ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ ዘኢትዮጵያ
ረድኤት በረከት ይደርብን።
2024/09/29 00:13:30
Back to Top
HTML Embed Code: