Telegram Web Link
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA)
« ከዘረኛ በላይ ክፉና ወንድሙን እጅግ የሚጠላ የዲያብሎስ ፈረስ የለም ። ዘረኛ በነገሰበት በየትኛውም የአገራችንም ሆነ የዓለም ሥፍራ ፍቅር ሰላም የተዋህዶ እምነት ምልክታቸውም አይኖርም ።»

🇨🇬 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን፥ ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ መልእክት 8 ገጽ 45 — ተጻፈ ታኅሣሥ 21/2011ዓ.ም
At least 32 people have been killed, and over 2,500 are injured in Bangladesh as violence escalated during student protests who are demanding quota system reform for government jobs.
ክራውድስትራይክ ለደንበኞቹ በለቀቀው የሶፍትዌር ማዘመኛ ጋር ተያይዞ ባጋጠመ እክል 8.5 ሚሊዮን ኮምፒዉተሮች ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ።

ክራውድስትራይክ ከተሰኘ የሳይበር ደህንነት ኩባንያ ለደንበኞቹ በለቀቀው የሶፍትዌር ማዘመኛ ጋር ተያይዞ ባጋጠመ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ስህተት ነዉ ጉዳቱ የደረሰዉ።

ከባሳለፈዉ ኃሙስ ማለዳ ጀምሮ የተከሰተው ችግር ባንኮች፣ አየርመንገዶች እና የሚዲያ ተቋማትን ስራ ማስተጓጎሉም ተገልጿል።

ይህንን ተከትሎ ማይክሮሶፍት ኩባንያ ባወጣው መረጃ ያጋጠመው የአይቲ እክል ከአገልግሎት ማስተጓጎል በተጨማሪ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱንም አስታውቋል።

በዚህም ከሶፍትዌር ማዘመኛ ጋር ተያይዞ ባጋጠመው አደጋ 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ያህል ዊንዶውስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ ኮምፒውተሮችና ሌሎች የቴክኖሎጂ ቁሶች ላይ ጉዳት ማድረሱን ማይክሮሶፍት አስታውቋል።

ማይክሮሶፍት በኮምፒውተሮቹ ላይ የደረሰው ጉዳት በታሪክ አስከፊው የሳይበር ጉዳት መሆኑን ነው የተጠቀሰዉ።
🟢🟡🔴
ሐምሌ 15 | የከበሩ አባቶቻችን፦

#ቅዱሳን_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ ተአምራት አደረጉ።

ቅዱሳኑ ሶርያ አካባቢ ውስጥ ወደምትገኝ አንዲት ሃገር ገብተው ሕዝቡን ከንጉሣቸው ጰራግሞስ ጋር አሳምነው አጠመቁ። ነገር ግን እነርሱ ሲወጡ ሰይጣን አስቶት አጥፊ ሰው ወደ መሆን ተመልሶ ንጉሡ ሐዋርያትን አሰቃየ።

ስለ ሐዋርያት ግን ፈረሶቹ ሰግደው፣ በሰው አንደበት ቅድስናቸውን መሰከሩ። በመጨረሻም ንጉሡን ከነ ሕዝቡና ሠራዊቱ በዓየር ላይ ሰቅለው ንስሐ ሰጥተውታል ። በእነዚህ ተአምራትም ሁሉም አምነው ለከተማዋና ለሕዝቡ ድኅነት ተደርጓል።

🍀 #ቅዱስ_ኤፍሬም ዘሶርያ ዐረፈ።

ይህም ውዳሴ ማርያምን የደረሰ ሊቅ ነው።

ቅዱስ ኤፍሬም ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች ሀገር ነው። አባቱም የጣዖት ካህን ነበር።

የእግዚአብሔር ቸርነት ቀሰቀሰችውና አነሳሥታ ወደ #ቅዱስ_አባ_ያዕቆብ ዘንጽቢን ወሰደችው።

እርሱም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው። በእርሱም ዘንድ በጾምና በጸሎት ያለማቋረጥ እየተጋደለ ለብዙ ዘመናት ኖረ።

እንደ ዛሬው የእመቤታችን ምስጋና በአንደበት እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበርና ቅዱስ ኤፍሬም ግን ከወንጌለ ሉቃስ በስድስተኛው ወርን (ይዌድስዋን) እና ጸሎተ ማርያምን አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ 64 ጊዜ ያመሰግናት ነበር።

እመቤታችንን ከልብ ከመውደዱ የተነሣ የእመቤታችን ምስጋናዋን አብዝቶ ይመኝ ነበር


በእግዚአብሔር ቸርነት “አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ” እስከሚል ድረስ ከእመቤታችን ውዳሴ ሌላ 14 ሺህ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ። ብዙውን ድርሰቱን መላእክት ደብቀውታል፣ ወስደውም ለምስጋና ተጠቅመውበታል

🍀 የዋልድባው #አቡነ_ተስፋ_ሐዋርያት ተሰወሩ።

በዋልድባ ከሳሙኤል ዘዋልድባ ቀጥለው በገዳሙ የተሾሙ ታላቅ አባት ናቸው

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
አሳዛኝ ዜና‼️

በጎፋ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የ20 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተነገረ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበል ሰኞ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምስክር ምትኩ አደጋውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥  እሰካሁን በተደረገው ፍለጋ ከ 20 በላይ አስከሬን መገኘቱንና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ገልጸዋል።
በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ  የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን አቶ ምስክር ተናግረዋል።

በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት እንደሚገኙ ተገልጿል።በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

የዞኑ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ መለሰ በበኩላቸው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት የነፍስ አድን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የጎፋ ዞን መንግስት ኮምንኬሽን መረጃ ያመላክታል።
🟢🟡🔴
ሐምሌ 16 | የኃያል፣ መስተጋድል፣ የሰማዕታት አለቃ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ የሥጋው ፍልሠት (ከልዳ ወደ እስክንድርያ) ሆነ


#አቡነ_ዳንኤል_ዘቦረና
እኚህ ጻድቅ አባት አንድ ትልቅ ግብር አላቸው፤ ይኸውም ዕድሜ ልካቸውን የእናትና የአባታቸውን ትውልድ ባለመናገር ዘረኝነትን ያራቁ ጻድቅ መሆናቸው ነው።

ግድ ብለው አጥብቀው ሲይዟቸው "እናቴ አክሱም አለች፤ አባቴም ልጇ ነው" በማለት ድንቅ መልስ ይሰጡ ነበር።

ቦረና ሳይንት ባለው ገዳማቸው ውስጥ የሚገኘውን ባለ ሦስት ዓምድ ገድላቸውን ደርቡሾች ከጠባቂው በትንሽ ገንዘብ ገዝተው ወስደውታል። እርሱም በመቅሰፍት ተመቶ ሞቷል።

ጻድቁ በሀገራችን ከ250 በላይ አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተዋል። መቃብራቸው በጋስጫ ይገኛል።


#ቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌሉ_ዘወርቅ

ቅዱሱ "ወንጌሉ ዘወርቅ" የተባለው ከሌሎች ዮሐንስ ከሚባሉ ቅዱሳን ለመለየት ቢሆንም ዋናው ምክንያት ግን እድሜ ልኩን የሚያነበው፣ ከእጁ የማይለየውና አቅፎት የሚተኛ በወርቅ የተለበጠ ወንጌል ስለ ነበረው ነው።

የቅዱስ ዮሐንስ ታሪኩ ከመርዓዊ (ሙሽራው) ገብረ ክርስቶስ እና ከቅዱስ ሙሴ ሮማዊ ጋር ተመሳሳይነት አለው። ይኸውም፦

ወላጆቹ ክርስቲያናዊ ናቸው። እሱንም በክርስትና ትምህርት በጥሩ አሳደጉት። አባቱም በልጁ ምኞት መሠረት በወርቅ የተለበጠ ወንጌል ሰጠው። ከወንጌሉም የማይነጣጠል ሆነ።

አንድ መነኰስ ለእንግድነት ቤታቸው ቢመጣ ልቡ ለምናኔ ተነሣሣ። ወላጆቹ ሊድሩት እያሰቡ ነበርና ከቤቱ ኮበለለና በረሃ ገባ።

በዚያም ከቆሻሻ ልብስና ከወንጌሉ በስተቀር ምንም ሳይኖረው ተጋደለ። በኋላም ወደ ቤተሰቦቹ ከተማ ተመለሰ።

መልኩና ሰውነቱ በተጋድሎ ተለውጧልና ማንነቱን ያላወቁት ወላጆቹ አዝነው ትንሽ መጠለያ ሠሩለት። በዚያም 7 ዓመታትን በታላቅ ተጋድሎ አሳልፎ ዐረፈ።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
2024/11/15 09:35:28
Back to Top
HTML Embed Code: