Telegram Web Link
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (የኔሰው @Ethiopia)
#ለፋኖ

#ለመላው_ይህንን_ትግል_ለምትመሩ_የፋኖ_መሪዎች

"ለመላው ይህንን ትግል ለምትመሩ የፋኖ መሪዎች ምክራችንን እንለግስ ። እግዚአብሔርን ፈርታችሁ ተጓዙ ። በመንገዳችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን አንግሱት። ጠይቁ እምነት አላችሁ አደለም ጠይቁ ። ምናለ ፆም ፀሎት ውሰዱና ጠይቁ ። ምንድነው ፈቃድህ ? እግዚአብሔር አምላካችን ሀሳብህ ምንድነው ? ከዚህ በኃላ ምንድነው ማድረግ ያለብን ? እስካሁን ድልን ሰጥተኸናል እስካሁን እዚህ አድርሰኸናል እስካሁን ጉልበት ሆነኸናል ከመጥፋት ታድገኸናል እነሆ በብዙ መንገድ እየገሰገስን ነው እንዴት ነው መሄድ ያለብን ? ወዴት ነው መሄድ ያለብን ? የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የሚል መልዕክት የሚተላለፍ አለ... ምንድናቸው እነዚህ ? እውነት ነው ወይ ? ካንተ ነው ወይ ? ፈቃድህ ነው ወይ መጠየቅ ? ምናለ ብትጠይቁ አልሰማ አላለ እግዚአብሔር ጠይቁት ወዴት እንጓዝ በሉት የነዚህ ምክር ትክክል ነው ወይ ? የወጣው መልዕክት ሁሉ ካንተ ነው ወይ ? ጠይቁ እግዚአብሔር ይመልሳል ። እሱ መልስ ካልሰጠ እኛ ምንናገረው ሀሰት ከሆነ ያኔ ትደርሱበታላችሁ ምናለ እውነትቱ ላይ ትደርሱበታላችሁ ያኔ አጥፊዎች ከሆንን እንቀጣለን። ስለ ቤተክህነትም ጠይቁ ቤተክርስቲያን ምን ላይ ናት? ምን ሆነች? የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ይኼን ይኼን ይላሉ ስለቤተክርስቲያን ይሄ ያንተ ድምፅ ነው ወይ? ይሄ ያንተ ቃል ነው ወይ ? እውነት ነው ወይ ? ይሄንን መጠየቅ መረዳት ነው ። ሶስተኛ የቃልኪዳን ምልክቱ ይሄ ይሄ ነው ብለው እየነገሩን ነው ይሄ እውነት ነው ወይ ? ይሄ መመሪያችን ይሁን ወይ ? መጠየቅ ነው በጥቅሉ እግዚአብሔር አምላካችሁን ፍቃዱን ጠይቁ ...እግዚአብሔር ወዴት እንደሚመራችሁ ቃሉን ጠይቁ ፈቃዱን ጠይቁት ሀሳቡን ጠይቁት :: አሁን ድንገተኛ እንዳይሆንባችሁ ድሉ በድሉ ላይ ድል በድል ላይ እያደረጋችሁ ትመጣላችሁ :: አሁንም ትገባላችሁ እንዴት ነው ምትሄዱት እንዴት ነው ወዴት ነው ምትራመዱት ከዛ ምንድነው ምታደርጉት ይሄ ብልጣብልጥ ምሁር ነኝ የሚል መጥቶ እንደገና ተኮልኩሎ ሕዝብ ላይ ታድያ ከየት እናምጣላችሁ ሌላ መመሪያ ያው ከምዕራቡ ዓለም ነው ዲሞክራሲ ነው ብሎ ፊጥ ሊልባችሁ ከሆነ እንዳትሳሳቱ መልሳችሁ እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ስራ ውስጥ እንዳትወድቁ እግዘብሔርን ጠይቁ ። ምክራችን ለናንተ ይሄ ነው ። በአመራሩ ላይ ያላችሁ በሙሉ በማስተዋል በትዕግስት በፍቅር በትህትና እግዚአብሔር በሰጣችሁ መረዳት ሕዝባችሁን ምሩት ወደ ነፃነትም የሚሄደውን ጉዞ በፍቅር አከናውኑት ልዪነታችሁን ከውስጣችሁ አውጡት አሁን የልዪነት ጊዜ አደለም ። የሐይማኖት ግጭት ፍጭት ለመፍጠር የሚፈልጉትን ሁሉ ውስጣችሁ ካሉ አስታግሷቸው ። እንዲታረሙ አድርጓቸው ። አሁን እንደ አንድ ልብ ሆናችሁ እንደ አንድ መካሪ ሆናችሁ እንደ አንድ ሀሳብ ሆናችሁ ለዓላማችሁ ለፍፃሜ መድረስ መታገል ነው ያለባችሁ ። ሕዝቡም ተስፋ እያደረጋችሁ ነው ። ብዙ ሕዝብ ተስፋ እያደረጋችሁ ነው ። የሕዝቡ ተስፋ እንዳይመክን በእግዚአብሔር ታምናችሁ ፀንታችሁ ጉዞዋችሁን ቀጥሉ ። ምንመክራችሁ ይሄንን ነው ። ለሁሉ ነገ ይደረስበታል ...እግዚአብሔር ከነገራችሁ በኃላ ሁሉንም ደግሞ እንነጋገርበታለን ጊዜው ሲፈቅድ እግዚአብሔር ሲፈቅድ ሁሉ ላይ ይደረስበታል። "

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ! ጥቅምት 21/2016 ከተላለፈው መልዕክት

ከ ክፍል ፪ ከ39 ደቂቃ:ከ35 ሰከንድ  እስከ 44 ደቂቃ:12 ሰከንድ ድረስ የተወሰደ
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
በጎፋ ዞን በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የሟቾች ቀጥር ከ146 ማለፉ ተገለፀ

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ትናንት ጠዋት ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ደርሷል። የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉንና የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ዞኑ አስታውቋል።

ዝርዝሩን ይመልከቱ፤ https://bit.ly/3LDgYBD
🟢🟡🔴
ሐምሌ 17 | ከ7ቱ ከዋክብት አባቶቻችን አንዱ፣ በትራቸው በቆሙበት ቦታ ሁሉ በተኣምራት ከጎኑ የወይን ዘለላ ፍሬ እያፈራ ይለቀም የነበሩ ታላቁ አባት #አቡነ_በትረ_ማርያም_ዘዘጌ የዕረፍታቸው በዐል ነው።
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
🟢🟡🔴 ሐምሌ 17 | ከ7ቱ ከዋክብት አባቶቻችን አንዱ፣ በትራቸው በቆሙበት ቦታ ሁሉ በተኣምራት ከጎኑ የወይን ዘለላ ፍሬ እያፈራ ይለቀም የነበሩ ታላቁ አባት #አቡነ_በትረ_ማርያም_ዘዘጌ የዕረፍታቸው በዐል ነው።
#አቡነ_በትረ_ማርያም የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ሙገር ነው። አባታቸው ቅዱስ ተክለ ማርያም እናታቸው ቅድስት ኢላርያ ይባላሉ።

ወላጆቻቸውም ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው። ነገር ግን ልጅ ስላልነበራቸው የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ዘወትር በጾም በጸሎት ይለምኑት ነበር።

ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ተኝተው ኹለቱም ተመሳሳይ ራእይ አዩ።

እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ ምዕመናንን ስቦ በወንጌል ጎዳና የሚመራ የተመረጠ ልጅ እንደሚወልዱ ነገራቸው።

መልአኩም በነገራቸው መሠረት አቡነ በትረ ማርያም ነሐሴ 16 ቀን ተፀንሰው ግንቦት 21 ቀን ተወለዱ

የተወለዱትም አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችን በደብረ ምጥማቅ ለክርስቲያኑም ለእስላሙም በምትገለጥበት ዓመታዊ በዓል ላይ ስለሆነ አንድም ይረዳናል ምርኩዛችን ይሆናል ብለው ወላጆቻቸው ስማቸውን በትረ ማርያም አሏቸው።

አቡነ በትረ ማርያምና ስድስቱ ወንድሞቻቸው ሰባቱ ከዋክብት ተብለው ይጠራሉ። እነዚህም ሰባቱ ከዋክብት ቅዱሳን እየራሳቸው ከገደሟቸው ጥንታውያን ገዳማት ውስጥ፦

፩. አቡነ በትረ ማርያም (መሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስን)

፪. አቡነ ኂሩተ አምላክ (ዳጋ እስጢፋኖስን)፣

፫. አቡነ ያሳይ (ማንዳባ መድኀኔዓለምን)፣

፬. አቡነ ዘካርያስ (ደብረ ገሊላን)፣

፭. አቡነ አፍቅረነ እግዚእ (ጒጒቤንና ጣና ቂርቆስን)፣

፮. አቡነ ታዴዎስ (ደብረ ማርያምን) እና

፯. አቡነ ዘዮሐንስ (ክብራን ገብርኤልን) ገዳማትን ገድመዋል።

አቡነ በትረ ማርያም ከበዓታቸው ወጥተው ወደ ሌላ ቦታ የሚሔዱት ለምነው ለነዳያን የሚሰጡትን ለመሰብሰብ ሲፈልጉና ገዳማትን ተሳልመው የቅዱሳንንም በረከት ለመቀበል ሲፈልጉ ብቻ ነበር።

ቅዱሳንን ጎብኝተው ወደ ገዳማቸው ዘጌ የሚመለሱትም ለነዳያን የሚሰጡትን ከሰበሰቡ በኋላ ነው።

ለነዳያን የሚሰጡትን ገንዘብ የሚሰበስቡትም እንደባርያ እየተሸጡ ለፈረስ ሳር በማጨድና የመንገደኞችን ዕቃ በመሸከም የሚከፈላቸውን ገንዘብ በማጠራቀም ነበር።

"ላጡ ለድኆች የሚሆን ምግብ ለማግኘት ሲሉ ለፈረስና ለበቅሎ ሣር ያጭዱ ዘንድ ባሪያ ሆነው የተሸጡበት ጊዜ አለ።

አቡነ በትረ ማርያም መልካሙን ተጋድሏቸውን ፈጽመው ሩጫቸውን ጨርሰው የዕረፍታቸው ጊዜ ሲደርስ የክብር ባለቤት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ ተገለጠላቸውና፦

"ወዳጄ በትረ ማርያም ሆይ! በዚኽች ዕለት ከኀዘን ወደ ደስታ፣ ከሕመም ወደ ሕይወት ልወስድህ ነፍስህንም አሳርፋት ዘንድ መጣሁ።

ቦታህን እንደ ኢየሩሳሌም አደረግሁልህ፤ በስምህ ቤተ ክርስቲያን የሠራ፣ ዕጣን የሰጠውን መብዓ ያቀረበውን፣ ሥጋህ የተቀበረበትን ዐፅምህ ያረፈበትን ገዳመ ዘጌን የተሳለመውን፣ ወንዱ በ40 ቀን ሴቷ በ80 ቀን ጥምቀተ ክርስትና የተቀበለውን፣ በቦታህ ቅዱስ ሥጋዬን ክቡር ደሜን የተቀበለውን፣ በስምህ ገድልህን የጻፈውን፣ ዐይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን ልብ ያላሰበውን እንደ አንተ ላሉት አባቴ ያዘጋጀውን አወርሰዋለሁ።

በገዳመ ዘጌ ላይ መብረቅና ነጎድጓድ፣ በምድር የሚሳቡ በመርዛቸው ሰውን የሚጎዱ እባቦች፣ በእግራቸው የሚሽከረከሩ አራዊቶች ሁሉ በዘጌ የሚኖረውንና በአንተ ያመነውን አይጣሉ (አይጉዱ)።

በገዳሙ የሚኖሩ መነኰሳትና ምእመናን እንደ መላእክት ኃጢአት የሌለባቸው ይሁኑ፣ ደምህ ከፈሰሰበት ከገዳመ ዘጌ መቃብርህ ላይ አፈር ቆንጥሮ የተቀባ ከሕማሙ ይፈወስ፣ መቃብርህን እጅ የነሣ የእኔን መቃብር እጅ እንደነሣ ይሁንልህ"


በማለት አስደናቂ የምሕረት ቃልኪዳን ከገባላቸው በኋላ ሐምሌ 17 ቀን በ89 ዓመታቸው በክብር ዐረፉ።

T.me/Ewnet1Nat
ጎፋ‼️😥

በጎፋ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የሟቾች
ቁጥር ከ265 በላይ መድረሱ ተነገረ


30 ሰዎች በአፈር ናዳ ውስጥ ይገኛሉ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበል በትላንትናው እለት ሀምሌ 15 ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የመሬት ናዳ የሟቾች ቁጥር ከ265 በላይ መድረሱ ተገልጿል፡፡

በቀበሌው ናዳው ከደረሰ በኋላ የሠው ህይወት ለመታደግ ወደ በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን  ከደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት የተገኘው መረጃ ያመላክታል። 

በትላንትናው እለት የወረዳው ፖሊስ አዛዥ የተለያዩ የፖሊስ አባላትን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ ተንሸራተው የነበረ ሲሆን በገመድ ተጓትተው  በህይወት መትረፍ መቻላቸው ተሰምቷል።

ከተለያዩ አካባቢዎች ለእርዳታ የመጡ ነዋሪዎች በቀበሌው በርካቶች በመሆናቸው የነዋሪዎች ቁጥር በውል እንደማይታወቅ ነው የተነገረው፤ በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገልፆል።
በኔፓል በደረሰዉ የአዉሮፕላን አደጋ አብራሪዉ ብቻ በህይወት መትረፉ ተሰማ

ማክሰኞ እለት ከኔፓል ዋና ከተማ ካትማንዱ ለመነሳት ሲሞክር የነበረዉ አውሮፕላን ተከስክሶ የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡በአሁኑ ወቅት በሆስፒታል ህክምና ላይ የሚገኘው ፓይለቱ ከአደጋው የተረፈው ብቸኛው ሰው ነው።የአየር መንገዱ የቴክኒክ ሰራተኞች እና ሁለት የአውሮፕላኑ ሰራተኞችን ጨምሮ 19 ሰዎች በሳውሪያ አየር መንገድ የሙከራ በረራ ላይ ነበሩ።

የኔፓል አቪዬሽን ኢንዱስትሪ ደካማ የደህንነት ታሪክ ያለዉ ሲሆን ይህም ላለፉት አመታት በበርካታ ምክንያቶች የተነሳ ነው፡፡ ከምክንያቶቹ መካከል ካልተጠበቀ የአየር ሁኔታ እስከ ደካማ ደንቦች ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡የሳውሪያ አየር መንገድ የሙከራ በረራ ወደ ታዋቂው የቱሪዝም መዳረሻ ወደ ፖክሃራ የሚያቀና ነበር፡፡በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተጋሩ ምስሎች መሰረት አውሮፕላኑ በእሳት እና በጭስ እንደተሸፈነ ያሳያል። አደጋው ከተከሰተ በኋላ የእሳት አደጋ መከላከያ ሞተሮች እና አምቡላንሶች በፍጥነት ወደ ቦታው ደርሰዋል፡፡

በኔፓል ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የፍለጋ እና ነፍስ አድን ማስተባበሪያ ማዕከል ባወጣው መግለጫ መሰረት አውሮፕላኑ ከትሪቡቫን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ አደጋዉ ደርሷል፡፡አውሮፕላኑ ወደ ቀኝ ከታጠፈ በኃላ በስተምስራቅ በኩል ተከስክሷል።"እሳቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን እና የነፍስ አድን ስራው ወዲያው መጀመሩ ተነግሯል" ሲል አክሏል።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🟢🟡🔴
ሐምሌ 19 | የትንሣኤ ዘመን አሻጋሪ ሊቀ መልእክ #ቅዱስ_ገብርኤል በዓሉ ነው።

በዚህችም ቀን ሕፃኑ
#ቅዱስ_ቂርቆስና እናቱ #ቅድስት_ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ። እርሱም ከእቶን እሳት አዳናቸው።

#ቅዱስ_ቂርቆስ 3 ዓመቱ ሳለ እናቱ መከራን ሸሽታ ወደ ሮሜ ሄደች። እዛም ግን መከራ ጠበቃት።

ከዚህም መኰንኑ በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ። የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ሆነ። ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት። ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። 

ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች። ከዚህም በኋላ ጸናች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነችው። ልጇንም "ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ፤ እኔም ልጅህ ነኝ" አለችው። 

ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት አለች። ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ። ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ
#ቅዱስ_ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና። 

ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጎትቷቸው አዘዘ። ከእግዚአብሔርም የታዘዘ
#መልአክ አዳናቸው።

መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው።

አምላከ #ቅዱስ_ገብርኤል እኛንም ከመከራ እሳት፣ ከኃጢአት ስጥመት ያድነን።

             #እንኳን_አደረሳችሁ
          ▸ T.me/Ewnet1Nat
በደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን በደረሰው ተከታታይ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለፀ‼️

ጽህፈት ቤቱ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ያገኘውን መረጃ መሠረት አድርጎ ባወጣው የሁኔታዎች መግለጫ ላይ ነው በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች አሃዝ እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል ያመለከተው።

እሁድ ሐምሌ 14 እና ሰኞ ሐምሌ 15/ 2016 ዓ.ም. በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ተቀብረው የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ሥራ ዛሬም ለአራተኛ ቀን እየተካሄደ ነው።

በአደጋው ስፍራ የሚገኙት የቢቢሲ ዘጋቢዎች እንደገለጹት ዛሬን ጨምሮ በአካባቢው እየጣለ ባለው ዝናብ ውስጥ ጭምር ከተንሸራተተው መሬት ስር ለማውጣት የሚደረገው የነፍስ አድን ጥረት ቀጥሏል።

ባለፉት ቀናት በተደረጉት የፍለጋ ጥረቶች በአደጋው ሕይወታቸው አልፎ የተገኙ ሰዎች ቁጥር 257 የደረሰ ሲሆን፣ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ስጋታቸውን መግለጻቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) አመልክቷል። አጠቃላይ 15,000 ሰዎች በመሬት መንሸራተት (landslide) አደጋው ተጎጂዎች ናቸው ያለ ሲሆን ለተጎጂዎች እርዳታ ማቅረብ መጀመሩንም ገልጿል።(ቢቢሲ)
ፎቶ ፦ ይህ የምትመለከቱት በካፋ ዞን ፣  በዴቻ ወረዳ፣ ሚዲዮ ጎምበራ ቀበሌ ትናንትና ምሽት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት የተከሰተው የመሬት መንሸራተት ነው።

በአደጋው 3 የአንድ ቤተሰብ አባላት ሞተዋል።

አንድ ሰው ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።

24 የአከባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

አደጋው በተከሰተበት አከባቢ ከጠሎ ወደ ቦንጋ የሚያስኬድ አስፓልት መንገድ ላይ በናዳ ተዘግቶ መጠነኛ ጉዳት ደርሷል። የአከባቢው አስተዳደር ከነዋሪዎች ጋር ተረባርበው መንገዱ ለትራፊክ ክፍት ማድረግ ችለዋል።


መረጃው ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ነው የተገኘው።
🟢🟡🔴
ሐምሌ 20 | #እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ከተወለደች በኋላ በሰማንያ ቀን ከርግብ ገላግልቶች ጋራ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው።

ለስም አጠራሯ ክብር ይሁንና እመ ብርሃን ድንግል ማርያም በዚህች ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ገብታለች።

በዓሉ ከሰላሳ ሦስቱ የእመቤታችን በዓላት እንደ አንዱ አይቆጠርም። ምክንያቱም ቅዱሳን ሊቃውንት በዓታ ከበዓታ ጋር ይስማማል ብለው የታኅሣሥ ሦስትን በዓል ከሰላሳ ሦስቱ ደምረውታል።

እመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ የገባችው ሁለት ጊዜ ሲሆን፦

1. ዛሬ የምናከብረውና በተወለደች በሰማንያ ቀኗ የገባችበት ነው። (ከግንቦት 1 ጀምረን እናስላው 80 ቀን ይመጣል)

ኦሪት እንዳዘዘው ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና ንጽሕት ሕፃን ድንግል ማርያምን ታቅፈው የርግብ ልጆች (ግልገሎች) ዋኖስም ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ ሒደዋል።

ካህናቱ ዘካርያስና ስምዖን ወጥተው በደስታ ተቀብለዋቸዋል። እመቤታችን ለወላጆቿ ማኅጸን የከፈተች በኩር ናትና በእግዚአብሔር ፊት አቅርበዋታል።

2. ከሦስት ዓመታት በኋላ እንደ ስዕለታቸው ወደ ቤተ መቅደስ ወስደው ለእግዚአብሔር ሰጥተዋት ተመልሰዋል።

እግዚአብሔር ዛሬ ያልቃል ነገ ይደቃል የማይባለውን የድንግል እናቱን ፍቅር አብዝቶ ያድለን። በረከቷም በእኛ ላይ ጸንቶ ይኑር።

                        🌹🌹🌹
🟢🟡🔴
ሐምሌ 21 | በቅድስት ቤ/ክ ትውፊት መሠረት ቅዱስ ዑራኤል #ድንግል_ማርያምን በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ አሳርጎ፣ በሠረገላ ብርሃን ጭኖ፣ በክንፎቹም ተሸክሞ፣ አስቀድሞ ገነትን ቀጥሎም ሲዖልን አስጎብኝቷታል።

በዚህም ምክንያት እመ ብርሃን ስለ ኃጥአን የምታለቅስ፣ የምትለምንና የምትማልድ ሆናለች። ለምናም አልቀረች የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች።


እመቤታችን ተገልጻ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ጽድቁን የመሰከረችለት ጻድቁ ንጉሥ #አቡነ_ላዕከ_ማርያም ዕረፍቱ ነው፡፡ እርሱም የዐፄ ናኦድ ልጅ ሲሆን መንግሥቱን ንቆ የመነነ ነው፡፡

በክፉዎች ምክር ተታሎ ንጉሥ አምደ ጽዮን የአባቱን ቅምጥ በማግባቱ እንደ ኤልያስና መጥምቁ ዮሐንስ ሄዶ ንጉሡን ስለገሠጸው በግዞት ብዙ ያሠቃየው ታላቁ አባት #አቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል ዕረፍታቸው ነው፡፡

በዚህም መከራ የተነሣ ከጾም፣ ከጸሎትና ከስግደት ባሻገር እንደ ሰማዕትም ይቆጠራሉ። ከብዙ የገድል ዓመታት በኋላም በ1330 ዓ.ም ሐምሌ 21 ትግራይ ውስጥ ዐርፈዋል።

● አጽፋቸውን እንደጀልባ ተጠቅመው የኢያሪኮን ባሕር ከደቀ መዛሙርቶቻቸው ጋር የተሻገሩት ታላቁ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ #አቡነ_ኤዎስጣቴዎስ ከፋሌ ባሕር ልደታቸው ነው፡፡

አባታቸው ክርስቶስ ሞዐ እና እናታቸው ሥነ ሕይወት ይባላሉ።

● ከንጉሥ ቴዎዶስዮስ መኳንቶች ውስጥ አንዱ የሆነውና ነዳያንን ይመግብ የነበረው ጃንደረባው #ቅዱስ_ሱስንዮስ ዕረፍቱ ነው፡፡

በሉቃስ ወንጌል ላይ (ሉቃ 23፥47) የምናገኘው የመቶ አለቃው #ቅዱስ_ዮራኖስ መታሰቢያው ነው።

ፍጹማን መነኮሳትን በተጋድሎ እስኪበልጣቸው ድረስ ከሚስቱ ጋር የተጋ #አቡነ_አወ_ክርስቶስ ዕረፍቱ ነው፡፡

እንግዶችን በመቀበል፣ ምጽዋትን በመስጠት፣ በመጾም በመጸለይ ኖሩ፡፡ በሌሊትም ማቅ ለብሰው ለየብቻቸው ይተኙ ነበር፡፡

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
📌 ሦስቱ መስማት የተሳናቸው

❖ ሦስት ደንቆሮዎች በአንድ ሰፈር ይኖሩ ነበር እና አንድ ቀን አንዱ ደንቆሮ ፍየል ትጠፋዋለች እና ፍየሉን ሲፈልግ አንዲት ደንቆሮ ሴት ልጅ አዝላ አረም ስታርም ያገኛታል እና "ፍየል አየሽ ወይ?" ብሎ ይጠይቃታል እርሷ ግን መስማት ስለማትችል "አረም እንዴት ነው?" ብሎ ይሆናል የጠየቀኝ ብላ በእጇ ያረመችውን እየጠቆመች "ይህን ይህን አርሜያለሁ" ትለዋለች፤ ጠያቂውም መስማት ስለማይችል "ፍየሏ በዚያ በኩል ነው የሄደችልህ" ያለችው መስሎት በጠቆመችው ቦታ ስሄድ ፍየሉን ተሰብራ ያገኛታል፤ ከዚያ የተሰበረች ፍየሉን ይዞ ወደምታርመዋ ደንቆሮ ይሄዳል፤ ከዚያ "በጠቆምሽኝ ጥቆማ መሠረት ፍየሌን አግኝቻታለሁ፤ ስለዚህ ለእኔ ብዙ ፍየሎች ስላሉኝ ይችን የተሰበረችዋን ፍየል ያገኘኋት በአንቺ ጥቆማ ስለሆነ ለአንቺ ሸልሜሻለሁ ለአንች ይሁንሽ ይላታል"

❖ ከዚያ እርሷ ደግሞ አንቺ ነሽ የሰበርሽው እያላት መስሏት "እኔ አልሰበርኩም እያለች" ስትመልስለት ይቆያሉ፤ ሁለቱ ማለትም ፍየል የጠፋው ደንቆሮ እና ልጅ አዝላ አረም ታርም የነበረችው ደንቆሮ እየተከራከሩ ሳለ ሌላ ሦስተኛ ደንቆሮ ይመጣል እና የተጣሉት ባዘለችው ልጅ ምክንያት መስሎት ፍየል ለጠፋው ደንቆሮ "አንተ ልጅ አትከራከር ይህ ያዘለችው ልጅ መልኩ ቁርጥ አንተን ስለሚመስል የአንተ ልጅ ነው እመን" አለው ይባላል።

❖ ሀገሬን የገጠማት እንዲህ ዓይነት ነገር ነው፤ መሬት ላይ ካለው እውነት ይልቅ ብዙው የየራሱን ይመስለኛል እውነት አድርጎ ነው እየኖረ ያለው፤ የራሱ መሰለኝ እያሳደደው ያለ ብዙ ሰው አለ፤ ከመሰለኝና ከግምት ዓለም እንውጣ፤ ለእውነት እንሙት በእውነት እንኑር ጽድቅ ትመውእ (እውነት ታሸንፋለች)

📌 ምንጭ
✍️ አለቃ አያሌው ከጻፉት መጽሐፍ ያገኘሁት                   
ዋግ ኽምራ 19 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

ትናንት ከቀኑ 6፡00 ገዳማ ከዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ስሃላ ሰየምት ወረዳ ወደ ዝቋላ ወረዳ በተከዜ ወንዝ በጀልባ ሲጎዙ ከነበሩት በግምት 26 ሰዎች ውስጥ 19 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የስሃላ ሰየምት ወረዳ ዋና  አሥተዳዳሪ ሲሳይ ብሩ ገልጸዋል።

ከ26ቱ ሰዎች አንድ ሕጻንን ጨምሮ 7 ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ሕይወታቸው ተርፏል ያሉት አቶ ሲሳይ የሟቾቹ ቁጥር ከዚያ በላይ ሊኾን ይችላል ብለዋል።

አደጋው ከደረሰ በኋላ የሟቾችን አስከሬን ለመፈለግ በተደረገው ጥረት እስከ ዛሬ ድረስ ሁለት ሰዎች ብቻ አስከሬን መገኘቱን ተናግረዋል።
2024/11/15 12:11:45
Back to Top
HTML Embed Code: