Telegram Web Link
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
A fire broke out inside a factory in Kiryat Shmona, Israel after it was hit by a missile — local media reports
Forwarded from ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ
📌የክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ ልዩ ልዩ ታሪካዊ፣ ትንቢታዊ ትምህርቶች
👇👇👇👇👇👇👇👇
👉የአለቃ አያሌውን ትምህርቶች በቀላሉ ለማውረድ(download ) ለመድረግ እነዚህን መስፈንጠሪያወች(links) ይጠቀሙ ፦
    👉ከጎግል ለማወረድ                                                                           📌 https://drive.google.com/drive/folders/1-uDfDVdeouGd8zg9iNnyZHUzOieChIeq?usp=sharing                                                         📌https://drive.google.com/drive/folders/1kQw8ifxKRGaYbdvGSLeO8-Y9AN2cPleI?usp=sharing
👉ከቴሌግራም ለማውረድ፦
📌https://www.tg-me.com/Yetewahedoarbegnoch/1970
📌 https://www.tg-me.com/aleqayalew/2185
#ሌሎች_ያጋሩ!
🟢 🟡 🔴
ሐምሌ 9 || አባታችን አቡነ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ በባሕር ውስጥ ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ መጸለይ የጀመሩበት እና ከ9 ዓመታት በኋላ የምሕረት ቃልኪዳን ተቀብለው ከባሕር የወጡበት ቀን ነው።

አምላከ #እስትንፋሰ_ክርስቶስ ይቅርታውን ያድለን።

T.me/Ewnet1Nat
ከሲኦል ነፍሳትን የማውጫ.pdf
328.3 KB
በአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቃልኪዳን የተገኘ [በአማርኛ]፦

ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡
ጸሎተ አቡነ እስትንፋሰክርስቶስ.pdf
675.4 KB
ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስን ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ ለአባታችን ነግሯቸዋል፡፡
[ በግእዝ ]
በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በድሬዳዋ አሥተዳደር ጀሎ በሊና ቀበሌ ቢርካ አካባቢ ሌሊት 6፡30 ገደማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

ከሟቾች በተጨማሪም በ10 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ድሬዳዋ አሥተዳደር ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

አደጋው የደረሰው ከድሬዳዋ ወደ ሐረር ሰው አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ “ዶልፊን” የሚባለው ሕዝብ ማመላለሻ በተቃራኒ መስመር ይጓዝ ከነበረ በተለምዶ “ሲኖትራክ” ተብሎ ከሚጠራው የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ

ዛሬ ሐምሌ 10/2016 ጌድኦ ዞን ጮርሶ ወረዳ ሻእሳ በተባለ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰው ህይወት ማለፉን ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል። ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረባቸው 4 ሠዎች ለህክምና ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ሲሉ ምንጮች ጠቁመዋል።
🟢🟡🔴
ሐምሌ 10 | የከበሩ አባቶቻችን፦

🍀 ስምዖን ቀለዮጳ የተባለው #ቅዱስ_ናትናኤል ሐዋርያ ስምዖን ቀለዮጳ በሰማዕትነት ዐረፈ።

ይህንንም ሐዋርያ አይሁድ የጌታችንን ወንድም ያዕቆብን ከገደሉት በኋላ ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ አድርገው ሐዋርያት ሾሙት። እርሱም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮ ከአይሁድ ብዙዎችን ጌታችንን ወደማመን መለሳቸው ተአምራትንም አድርጎአልና በሽተኞችንም አድኗልና።

ንጉሡ እንድርያስም ሴቶችን ከባሎቻቸው እንደሚለይ ንጽሕናቸውንም እንዲጠብቁ እንደሚአዝዛቸው ስለ እርሱ ሰማ ወደርሱም አስቀርቦ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው።

ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ ከእርሱም ጋር #ቅድስት_ቴዎና የምትባል አንዲት ድንግል ተገደለች።
🍀

#አቡነ_ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ልደታቸው ነው።

ጻድቁ እንድርያስና አርሶንያ ከሚባሉ የበቁ ደጋግ አባትና እናታቸው የተወለዱት በሸዋ ሀገረ ስብከት ቀድሞ ጽላልሽ ዛሬ ቡልጋ በሚባለው አውራጃ ነው፡፡

የወላጆቻቸው በጎ ምግባርና ሃይማኖት ቅዱስ ተክለሃይማኖትን ከደብረ ሊባኖስ አነሣስቶ በቤታቸው ሄደው እንዲስተናገዱ አድርጓል።

ልጅ ስላልነበራቸው ያዝኑ ነበርና አቡነ ተክለሃይማኖትም በጸጋ እግዚአብሔር ተገልጾላቸው ‹‹እግዚአብሔር ጣዖታትን የሚሰብር፣ አጋንንትን በጸሎቱ የሚያርቅ፣ ሕዝብን ከኃጢአት በሽታ የሚያድን፣ ፈጣሪውን የሚያስደስት ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ›› ብለው ትንቢት ነግረዋቸዋል፡፡

በትንቢቱም መሠረት አቡነ ሳሙኤል ሐምሌ 10 ቀን 1248 ዓ.ም ሲወለዱ መልካቸው በአራት ልዩ ልዩ ኅብራት ታይተዋል፡፡

አቡነ ተክለሃይማኖትም በ40 ቀን ክርስትና አንስተው ስመ ክርስትናውን ‹‹ሳሙኤል›› አሉት፡፡ ትርጓሜውም ‹‹እግዚአብሔር ጸሎቴን ሰማኝ›› ማለት ነው፡፡
🍀

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሐምሌ 12 |
#እግዚአብሔር #ቅዱስ_ሚካኤልን ያጠፋቸው ዘንድ ወደ ሰናክሬም ሠራዊት ላከው።

ይህም እንዲህ ነው፦ ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን በከበባት ጊዜ ሕዝቅያስንና ፈጣሪው እግዚአብሔርን እየዘለፈ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ። እንዲህም አለ፦ "እግዚአብሔር ያድናችኋል እያለ ሕዝቅያስ አያስታችሁ ከእጄ የሚያድናችሁ ማን ነው?"

የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስም እጅግ አዘነ። ወገኖቹንና ሀገሩ ኢየሩሳሌምንም ያድን ዘንድ ማቅ ለብሶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። እግዚአብሔርም ልመናውን ተቀብሎ ወደ ፋርስ ንጉሥ ወደ ሰናክሬም ሠራዊት የመላእክት አለቃ ሚካኤልን ላከለት።

በዚያችም ሌሊት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከሰማያት በግርማ ወርዶ የሰናክሬምን 185 ሺውንም የጦር ሠራዊት በአንዲት ሌሊት በእሳት ሰይፉ ፈጅቷቸው አደረ፡፡

በለኪሶ የነበረው ሰናክሬምም በጧት ቢነሣ ሠራዊቱን ሁሉ የአስከሬን ክምር ሆኖ አገኘው፡፡ በታላቅ ድንጋጤ ሆኖ ወደ ነነዌ በመሄድ ወደ ጣዖት ቤቱ ሲገባ የራሱ ልጆች በሰይፍ ገደሉት፡፡

ትዕቢተኛው ሰናክሬምም ለአሕዛብ ሁሉ መዘባበቻ ሆነ፡፡ ቅዱስ ሕዝቅያስ ግን በፈጣሪው ታምኗልና ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም ሞገስና ረዳት ሆኖታልና የዓለም ነገሥታት ሁሉ ፈሩት፣ እጅግ አከበሩትም፡፡

[2ኛ ነገ ምዕ 18 እና 19 ይነበቡ]

ስለዚህም የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ የሚካኤልን በዓል መታሰቢያ በዚች ቀን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ።

                      ◦☘️☘️☘️
#እንኳን_አደረሳችሁ
T.me/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
💾 የአባ አምኃ ኢየሱስ ገብረዮሐንስ መደበኛና ድንገተኛ አገራዊ መልዕክቶች
🟢🟡🔴
መልዕክት ፩
https://www.tg-me.com/christian930/2763

መልዕክት ፪ https://www.tg-me.com/christian930/2764

መልዕክት ፫ https://www.tg-me.com/christian930/2765

መልዕክት ፬ https://www.tg-me.com/christian930/2766

መልዕክት ፭ https://www.tg-me.com/christian930/3471

መልዕክት ፮ https://www.tg-me.com/christian930/3487

💾 PDF+Audio+Video ሁሉንም በአንድ ላይ ለማግኘት https://www.tg-me.com/christian930/4289

ድንገተኛ መልዕክታት (በፅሑፍ) https://www.tg-me.com/christian930/4290
📌 በስተመጨረሻ ግን ማሳረጊያ እንዲሆን በዚህ ሰዓት የምንግርህ!

ኢትዮጵያዊነትን በልብህ ካልተከልክ ፤ ተዋሕዶ እምነትን በልብህ ካላጸናህ ፤ ሰንደቋን ካላከበርክና ካልታመንክባት

በዚህ በሦስቱ ወድቀህ ከተገኘህ ወንድሜ እህቴ ማንም ሆናችሁ ማንም

በየትም ዓለም ኑር በየትም መዳኛዋ መሸሸጌዋ ማምለጨዋ መንገድ ይቺውና ይችው ብቻ ናት፡፡ ይሄንን ንቀሃል ይሄንን አቃለሃል፡፡

አዎ አንተ ቀለሃል ዋጋ ቢስ ሆነሃል፡፡ ከእግዚአብሔር ፍቅር ተቆርጠህ ወድቀሃል፡፡

ኢትዮጵያዊነት ዓለምን አሸንፏል፡፡

ደግሜ ልንገርህ ምን ብየ ኩርርር ብየ ልንገርህ
ኢትዮጵያዊነት ዓለምን ሁሉ አሸንፏታል፡፡

ተዋህዶ እምነት፡ ዓለምን ሁሉ የሞላውን እምነቶች ሁሉ እምነት ተብየዎችን ሁሉ አሸንፋለች፡፡
በእግዚአብሔር ፊት ከብራለች፡፡

አባቶቻችን ያጸኗት የለበሷት በልባቸው የተከሏት ለዘመናት የኖሩባት ሰንደቋ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አሸንፏል፡፡
የቃል ኪዳን ምልክቱ ነውና

በእነዚህ ሦስቱ ውስጥ ከሌለህ እግዚአብሔርንም ልታውቀው አትችልም፡፡
ኢትዮጵያዊነትን ስታውቅ
ተዋህዶን ስታውቅ
ሰንደቋን ስታውቅ
እግዚአብሔርን ታውቃለህ፡፡

እምነት ምን እንደሆነም ታውቃለህ፡፡

በእምነት መጓዝ ምን እንደሆነም ትረዳለህ፡፡

በእውነትና በመንፈስ መጓዝም ያስችልሃል፡፡

ቸሩ መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስንም ታውቀዋለህ፡፡

የአብርሃሙ ሥላሴንም ታውቃለህ፡፡

ድንግልም ታውቃለህ፡፡

ፍቅራቸውንም ታገኛለህ

ብዙ ዙረት ድካም አያስፈልግም፡፡

ማመን መታመን ንስሓ መግባት ወደ ጉያው መሰብሰብ ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ መቅረብ
የምነግርህ ይሄንን ነው፡፡

⚡️ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ሚያዝያ 19/2015 በድምፅ ከተለቀቀው
መግለጫ እና የሉቃስ ወንጌል ትምህርት ክፍል- 11- (ለ) መጨረሻው ላይ የተወሰደ፡
2024/11/15 07:47:47
Back to Top
HTML Embed Code: