Telegram Web Link
በዩክሬን "Kharkov" ወይም "Kharkiv" በተሰኘው አከባቢ ሩሲያ በቅርቡ በከፈተችው ጥቃት ምክንያት የሞቱ የዩክሬን ተዋጊዎች መቃብር
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 19 | በዚህ ቀን የከበሩ፦

● በወሎ ላስታ ሰውንና ዝንጀሮን በቃልኪዳን ያስተሳሰሩትና እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑት #የእንጂፋቱ_አቡነ_ዮሴፍ ዕረፍታቸው ነው፡፡

● ጌታችን 5 ጊዜ ከሞት ያስነሣው የ12 ዓመቱ ሕጻን ሰማዕት #ቅዱስ_ኤስድሮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ከእርሱም ጋር ማኅበርተኞቹ የሆኑ 8 መቶ 5 ሺህ ሰባት ሰዎች በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡

● ጌታችን ተገልጦ ‹‹ለእናቴ ዓሥራት የሰጠኋት፣ ለወዳጄ ለጊዮርጊስ፣ ለባለሟሌ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓሥራት የሰጠኋት ይህችን ቅድስት ሀገር ያሬድንና ጊዮርጊስን ያፈራችውን ኢትዮጵያን በጸሎትህ ጠብቅ›› ብሎ ያዘዛቸው #የአክሱሙ_አቡነ_ዮሴፍ ዕረፍታቸው ነው፡፡

● ስመ እግዚአብሔር ሲጠራባቸው ስለ ስሙ ክብር ሲሉ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው የሰጡት በጸሎታቸውም ውኃውን ደም ያደረጉት ታላቁ ተአምረኛው አባት #አቡነ_ዓቢየ_እግዚእ ዕረፍታቸው ነው፡፡

● ጸሎት ማድረግ ሲጀምሩ ሰማያት ተከፍተው የመላእክትን አገልግሎት በግልጽ ይመለከቱ የነበሩትና ሰይጣን ለመጀመሪያ ጊዜ ከጳውሎስ ሳምሳጢን ጀምሮ እስከ ንስጥሮስንና ልዮን ድረስ ያስተማራትን የክህደት ትምህርት ከሀገራችን ያጠፉልን የሐይቁ #አቡነ_ብስጣውሮስ ዕረፍታቸው ነው፡፡

● ጌታችን ቤተ መቅደሱን በባሕር ላይ እንዲሠራ የነገረውና በምድራዊ ስንዴና ወይን ያይደለ መላእክት ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ እያመጡለት 22 ዓመት ሥጋ ወደሙን ሲፈትት የኖረው ጻድቁ ንጉሥና ካህን #ቅዱስ_ይምርሐነ_ክርስቶስ ልደቱ ነው፡፡

● በአባ መቃርስ ገዳም የሚኖር ቅዱስ አባት #ቀሲስ_ይስሐቅ ዕረፍቱ ነው፡፡

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሠ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
ድንግል ማርያም እሙ ወእምነ ንግሥተ ጽዮን ወንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ

19/9/2016 ድንቃ ድንቅ አስተማሪ ምስክርነት 👇👇👇
Audio
የወንድማችን ወልደ ሐዋርያት እጹብ ድንቅ ምስክርነት
ከአሜሪካ
19/9/201
6

👉 እንሸሻለን፣ አናመልጣለን ብላችሁ አታስቡ፤ ይህ ድሮ ቀረ። ከአሁን በኋላ ሰው አምልጦ የሚድነው
ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በመጠለል ብቻ ነው። ስለዚህ ሽሽት ወዴት! እናንተ መሸሸጊያ ይሆናሉ ብላችሁ
በሥጋችሁ ያደራጃችኋቸው እነባቢሎን (አሜሪካ)፣ እነአውሮፓ፣ ወይም ኤሽያ፣ አረቢያም ሁሉም በእዚህም
ጽዳት ይካሄዳል። ምሽጉ የትጋ ነው! ራሳችሁንና ሥራችሁን ይዛችሁ በፈጣሪ እጅ መውደቅ ቅን ፍርዱን
መጠበቅ ብቻ ነው።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ሁለት የተወሰደ
20240520_215741.aac
4 MB
የእህታችን ፍቅርተ ማርያም እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስአበባ
18/9/2016

👉 ልብ በል እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦች የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች በምንታመንበት የአብርሃሙ
ሥላሴ በምንታመንባት ድንግል በእሳት ታጥረን ያለጭንቀት ያለሃሳብ ፈጣሪያችንን እያመሰገንን የነፃነት
በዓላችንን እናከብራለን። በደስታ እንዘምራለን። እኛ ጋ ለመለመን እንኳ በቤትህም በደጁም በሁሉም ስፍራ
የነገሠውን ሞት /የሞት ባሕር/ እንዴት ትሻገራለህ። እግዚአብሔር የወደዳቸው የታደጋቸው ያከበራቸው
የትንሣኤው ሙሽሮች ሲፈነጥዙ ታያለህ ግን ወደእነሱ መድረስ አትችልም። በመሃል አይምሬው ሞት
በሁለመናህ ነግሧልና! የሚሆነው ይህ ነው። ምን ይበጅህ አላጋጩ የዛሬው ትውልድ! ብርህ አያድን፤ ሕንጻህ
ዋሻህ ግንብህ ዘበኛህ ጠመንጃህ ታንክህ ጀትህ መርከብህ እኒህ ሁሉ አቧራ ይሆናሉ። ማን ያድንሃል?

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ዘጠኝ የተወሰደ
የእህታችን ወለተ ሚካኤል እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስአበባ
19/9/2016

👉 ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር !!!
ኢትዮጵያ ርስተ - ድንግል ማርያም !!!
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን!!!
ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ !!!
ምስክርነት_19-08-2016.aac
3.2 MB
የወንድማችን ገብረ መድህን እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ =ጉጂ
19/9/2016

👉 ያለ ወላዲት አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም
ያለወላዲት አምላክ አማላጅነት ሀገር አይድንም
ያለወላዲት አምላክ አማላጅነት ቤተሰብ አይድንም
20240124_141834.amr
680 KB
የወንድማችን ወልደ ሚካኤል አጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = ባህርዳር
19/9/2016

👉 ቅድመ
ጥንቃቄ ይኑራችሁ አደጋው በአካባቢያችሁ ሲከሰት እናንተም በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ላይ ሞት ሲወርድ
ሙሴ በሩን ዘግቶ ሞትን ከነወገኖቹ በምስጋና እንዳሳለፈ ሁሉ በራችሁን ዝጉ በበራችሁም ላይ የድንግልን
ማኅተም የቅዱሳን መላእክት ጥበቃና ፈጣሪያችሁን በማመስገን አሳልፉ።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ስምንት የተወሰደ
ምስክርነት (1)
<unknown>
የወንድማችን ተስፋ ሚካኤል እጅግ እጹብ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ
19/9/2016

👉 ጌታ በእናንተ የሕይወት ምስክርነት በፊቱ በብርሃንነት ልትመላለሱ ወዶአችኋል። አገራችን ኢትዮጵያን
የዙፋኑ ማረፊያ፣ የስሙ መመስገኛ፣ የበረከቱ መፍሰሻ ምንጭ ትሆን ዘንድ ወዷል። ከዓለም ሁሉ አብልጦ
ወደዳችሁ፤ የሚወዳትን እናቱን ለእናንተ እናት ትሁናችሁ አለ። ሚካኤልን፣ ገብርኤልን፣ ሩፋኤልን፣
ፋኑኤልን፣ የሁላችሁም ጋሻና የበረከት መፍስሻ አደረገ

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አራት የተወሰደ
ስርጉተ ገብርኤል
ከስዊዘርላንድ
19/9/2016
🟢 🟡 🔴

ግንቦት 21 | አምላክን የወለደች #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ ታላቅ በዓል ነው።

እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጎናጸፈች ናት። በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር፤ ይጋርዷታልም። ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥዋ ገናናነት ይሰግዳሉ። በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል።

አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ።

ሁለተኛ ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ፥ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል ።

ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ መርቆሬዎስ ነው። ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል። ደግሞ ጻድቃንም እንዲሁ።

ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል። በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ።

እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ "ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳዪኝ" ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች። ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል።

የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች። ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል።

እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል። ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል። እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ።

#_እንኳን_አደረሳችሁ
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
☘️☘️
🌹🌹🌹
አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኀምሰ ዕለታተ፣
ትእምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተ፣
ሚ መጠነ ማርያም ታሥተፌሥሒ ትፍሥሕተ፣ ኅድጊሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሁ መዓልተ፣
ብፁዕ ዘርእየኪ በሕልሙ ሌሊተ፤
🍀

የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለአምስት ቀናት ያህል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያህል ደስ ታሰኚ ኖሯል!

በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው፡፡"

~ ማኅሌተ ጽጌ ~
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 23 | #_አቡነ_ታዴዎስ ዘደብረ ጽላልሽ ልደታቸው ነው።

አቡነ ታዴዎስ ሲወለዱ ያዋለደቻቸው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። አባታቸው ቅዱስ ሮማንዮስ (የአቡነ ተክለ ሃይማኖት አጎት)፣ እናታቸው ደግሞ ቅድስት ማርታ ይባላሉ።

ሲወለዱ ሀገሩ ጨለማ ስለነበረ በብርሃን ተሞላ፤ ባዶ ጎተራዎች ከአፍ ሞልተው መሬት ይፈሱ ነበር፡፡ ሐምሌ 2 ቀን ክርስትና ሲነሡ ቤተ ክርስቲያን ቆመው እያሉ እመቤታችን ወርዳ ስማቸውን ታዴዎስ ብላቸዋለች፡፡

በዚህ ዕለት የተዘራው ዘር 40 ቀን ሳይሞላው ከቤተክርስቲያን ሲመለሱ ዘር እሸት ሆነ አጎመራ፤ ፍሬ ሆኖ ተበላ። ካህናት ሲወርቡ ከእናታቸው ጀርባ ላይ ሆነው እያዜሙ አብረው ያመሰግኑ ነበር።

ካደጉም በኋላ በጾም በጸሎት ከመጋደላቸው እና ከትሩፋታቸው ብዛት ተአምራታቸው ብዙ ነው።

● እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመርፌ ቀዳዳ 30 ግመሎችን አሾልከዋል።

● ሳጥናኤልን በአገረ ጽጋጋ ለ 7 ዓመት አስረውታል።

     ▸ የተሰጣቸው ቃልኪዳን

#_በሰማዕትነት_ደማቸው_በፈሰሰበት_ፀበል_ቦታ_የተጠመቀ_በኀልዮ_በነቢብ_በገቢር_የሠራውን_ኃጢአት_ሁሉ_ደምስሼ_በማየገቦ_እንደተጠመቀ_አደርገዋለሁ

#ወንድ_እንደ_40 ቀን #ሴትም_እንደ_80 ቀን ህፃን ይሆናሉ፡፡

๏ በጸበሉ ልዩ ልዩ ደዌ ሕሙማን ቢጠመቁ እፈውሳቸዋለሁ።

#_ዝክርህን_የዘከረ_ሲኦልን_አላሳየውም፤ እምረዋለሁ።

#_አንድ_አቡነ_ዘበሰማያት ቢደግም ስዕለቱን እሰማዋለሁ፤ እፈፅምለታለሁ"

ብሎ አምላካችን በማይታበል ቃል ኪዳን ቃል ገብቶላቸዋል።

የአቡነ ታዴዎስ በረከታቸው ይደርብን፣ እንኳን አደረሳችሁ።
                ◦🌿☘️🌿
          ▸ www.tg-me.com/Ewnet1Nat
2024/11/16 11:32:36
Back to Top
HTML Embed Code: