Telegram Web Link
Partner's Content: #EdTechMondays

Empowering educators to utilize culturally relevant EdTech tools is crucial for engaging students and enhancing their learning experiences. Let's make education accessible for everyone. Discover how we can integrate local languages and cultural narratives into educational technology, to create learning experiences that resonate with all Ethiopian students.

Tune in to Fana FM 98.1 on Monday, September 30th at 8:10 pm for insights.
በ2017 በጀት አመት በገበያ ላይ በሚገኙ 48 የምርት አይነቶች እና በ440 ፋብሪካዎች ላይ የጥራት ቁጥጥር ለማደረግ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ 16/01/2017ዓ.ም (ን/ቀ/ት/ሚ) በሀገር ውስጥ ተመርተውና ከውጪ ሀገር ተገዝተው በገበያ ላይ በሚገኙ እና የስጋት ደረጃቸው ከፍተኛ በሆኑ 48 የምርት አይነቶች እንዲሁም አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርት የወጣላቸውን ምርቶችን በሚያመርቱ 440 ፋበሪካዎች ላይ በ2017 በጀት አመት የጥራት ቁጥጥር ለማደረግ ዕቅድ ተይዞ እየተሥራ መሆኑን በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የጥራት ማረጋገጫ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ተከተል ጌቶ ገልፀዋል፡፡

Read More

Source: Ministryoftradeandregionalintegration
@Ethiopianbusinessdaily
Daily_Quiz

What happens when the demand for a product exceeds its supply?
Anonymous Quiz
84%
A) Prices increase
9%
B) Prices decrease
3%
C) The product becomes less valuable
4%
D) Supply increases to meet demand
#ለመረጃ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከሚሰጡ አገልግሎቶች የክፍያ ታሪፍ ማሻሻያ የተደረገባቸው ጠቅላላ ዝርዝር።

Source: theethiopianeconomistview
@Ethiopianbusinessdaily
ሁለት ዓመታትን የፈጀዉና 600 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት ግዙፉ የሲሚንቶ ፋብሪካ ወደ ስራ መግባቱ ተገልጿል

የኢትዮጵያን ሲሚንቶ ምርት 50 በመቶ የገበያ ፍላጎትን ለማሟላት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው የተነገረለትና ሁለት ዓመታትን የፈጀዉ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱ ታዉቋል።

600 ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ የተደረገበት ግዙፉ የሲሚንቶ ፋብሪካው በጠቅላይ ሚኒስትሩ መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም. መመረቁ ታዉቋል።

በአማራ ክልል ከአዲስ አበባ በ130 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የሲሚንቶ ፋብሪካው መቀመጫውን ሆንግ ኮንግ ያደረገው ዌስተርን ኢንተርናሽናል ሆልዲንግስ እና ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ በጋራ ኢንቨስትመንት ነው የተገነባው።

በታህሳስ 2022 በይፋ ከተጀመረ በኋላ የፕሮጀክቱ ዋና መሳሪያዎች ተከላ በአስራ አንድ ወራት ውስጥ መጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን 174 ሜትር ርዝመት ያለው በአለም ረዥሙ የሆነውን የቅድመ ማሞቂያ ማማ መያዙ ነዉ የተገለፀው ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በምረቃው ወቅት እንደተናገሩት "በቀን አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ኩንታል የማምረት አቅም ያለውን የለሚ ብሔራዊ የሲሚንቶ ፋብሪካ መርቀን ሥራ አስጀምረናል" ያሉ ሲሆን " በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገራችን ያሉ ተመሳሳይ ፋብሪካዎች ተደምረው የሚያመርቱትን ሃምሳ ከመቶ የሚያመርት ፋብሪካ እውን መሆኑን አስታዉቋል ።

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
በኢትዮጵያ የሱዙኪ መኪና አስመጪ ኩባንያ S-PRESSO የተባሉ ሞዴሎች በአስቸኳይ ለጥገና እንዲቀርቡ አሳሰበ

የመኪናዎቹ አስመጪው ታምሪን የተባለው ድርጅት በቅርቡ በተወሰኑ የ S-PRESSO መኪናዎች ላይ በተደጋጋሚ ለጉዳት ሊጋለጥ የሚችል የመሪ ዘንግ ክፍል እንዳለ የሱዙኪ አምራች መረጃ አድርሶናል ብሏል።

በመሆኑም ከላይ የተገለጸው ችግር ይኖርባቸዋል ተብለው የታሰቡ የምርት ባች ላይ ያሉትን S-PRESSO መኪናዎች በሙሉ ጥሪ በማድረግ ሊያጋጥም ከሚችል እክል ማስወገድ አስፈላጊ ሆኗል ያለው ድርጅቱ የመኪናው ባለቤት የሆኑ ኢትዮጵያውያን ተሽከርካሪዎቻቸውን ለጥገና እንዲያቀርቡ አሳስቧል።

ድርጅቱ በፌስቡክ ገፁ የሻንሲ ቁጥሮችን ያጋራ ሲሆን ቁጥራቸው በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያሉ ተሽከርካሪዎች በሙሉ ወደ ድርጅቱ የሰርቪስ ማእከል በመሄድ በኦርጂናል የሱዙኪ መለዋወጫዎች የመሪ ዘንግ አካላት ቅያሬ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

Source: MeseretMedia
@Ethiopianbusinessdaily
በኢትዮጵያ የሚገኙት በርካታ የቻይና ባለሃብቶች በሀገሪቱ እያጋጠመን ይገኛል ባሉት ተግዳሮቶች ወደ ጎረቤት ሀገራት እየሄዱ መሆኑን ገለፁ

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ላይ ጉልህ ድርሻ በመያዝ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ እያደረጉ የሚገኙት የቻይና ባለሃብቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያጋጠማቸው በሚገኘዉ ተግዳሮቶች ምክንያት ወደ ጎረቤት ሀገራት እየሄዱ እንደሚገኝ ነዉ ያስታወቁት።

እነዚሁ ባሀብቶች በመንግስት አመቺ የስራ ሁኔታዎች እየተሰጠ ባለመሆኑ ወደ ጎሮቤት ሃገራት ማለትም ወደ ኬንያ ፣ ኡጋንዳ እንዲሁም ታንዛኒያ እያማተሩ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ተወካይ እንደተናገሩት በብዙ ምክንያቶች ቻይናውያን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን ንግዳቸውን ወደ ጎሮቤት አገሮች አዙረዋል ።

Read More

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
Merkato, Africa's largest open-air market, is a bustling hub where a diverse array of goods and vendors thrive. From street vendors selling snacks to larger businesses dealing in machinery, the market is filled with an energetic mix of pedestrians, vehicles, and loud advertising.

Read More

Source: addisfortune
@Ethiopianbusinessdaily
Alvaro Piris, chief of the International Monetary Fund's (IMF) staff team, struck a bullish tone completing a two-week visit to Addis Abeba — an optimistic shift from his language of despair over the past three years. The change follows the conclusion of the first review of a four-year program agreed upon with Ethiopian authorities.

Read More

Source: addisfortune
@Ethiopianbusinessdaily
አለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የኢትዮጵያ ማክሮኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራው በመልካም ሁኔታ እየሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡

በዚህም የተቋሙ ቦርድ ማሻሻያው ተግባራዊ መደረግ በጀመረበት ሀምሌ 22፣ 2016 ዓም ካፀደቀው 3.4 ቢሊየን ዶላር  ድጋፍ ውስጥ 10 በመቶውን ማለትም 345 ሚሊየን ዶላር እንዲለቀቅ እንደሚያጸድቅ ነው የሚጠበቀው፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተግባራዊ መደረግ ሲጀም አንድ ቢሊየን ዶላር (30 በመቶ) የሚሆነው መለቀቁ ይታወሳል፡፡

የIMF ልኡክ ከመስከረም 7 እስከ 16 የማክሮኢኮኖሚ ማሻሻያው የትግበራ ሂደትን ለመገምገም በአዲስ አበባ ጉብኝት አድርጎ የነበረ ሲሆን፡፡

በዚህም ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን መረዳቱን ነው ያስታወቀው፡፡ ተቋሙ እንዳስታወቀው ማሻሻያው የውጭ ምንዛሬ ግብይቱ የህገወጥ የምነዛሬ ገበያው ከህጋዊው ጋር ማቀራረቡን ገልጾ፤ ለውጡ በኢኮኖሚው ላይ የፈጠረው ጫና ያነሰ መሆኑን በአዎንታዊ ጎኑ ጠቅሷል፡፡

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
The International Monetary Fund (0IMF) has reached a staff-level agreement with Ethiopian authorities on the first review of the Extended Credit Facility (ECF), allowing Ethiopia access to approximately $345 million in financing.

This agreement follows the successful implementation of Ethiopia's economic reforms, including a floating exchange rate regime adopted in July 2024, which has significantly reduced the gap between official and parallel market rates. The reforms aim to enhance macroeconomic stability and support sustainable growth amidst ongoing challenges such as inflation and foreign exchange shortages.

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
2024/11/15 17:51:12
Back to Top
HTML Embed Code: