Telegram Web Link
Kenya Doubles Electricity Imports from Ethiopia

Kenya’s electricity imports from neighboring Ethiopia have surged by 88% in the first half of 2024, according to a report released by the Kenya National Bureau of Statistics (KNBS). This increase marks a major shift in Kenya’s energy import strategy as the country seeks to meet rising electricity demand.

Read More

Source: 2merkato
@Ethiopianbusinessdaily
አዲሱ ደንብ መተግበሪያውን ለወንጀል የሚጠቀሙት ሰዎችን ቅስም የሚሰብር ይሆናል - ዱሮቭ

ቴሌግራም አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ የደንበኞቹን መረጃዎች ለሕግ አካላት አሳልፎ ሊሰጥ ነው።

በዚህም የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ፦
➡️ ስልክ ቁጥሮች፣
➡️ የኢንተርኔት አድራሻ
➡️ ሌሎችንም መረጃዎች በፖሊስ፣ በፍርድ ቤት በመሳሰሉ የሕግ ተርጓሚዎች በሚፈለግበት ጊዜ ሊሰጥ እንደሚችል ቴሌግራም አሳውቋል።

የቴሌግራም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፔቨል ዱሮቭ ይህ አዲስ ደንብ እንደሆነው አመልክተዋል።

ይህ አዲስ ደንብ መተግበሪያውን ለወንጀል የሚጠቀሙት ሰዎችን ቅስም የሚሰብር ይሆናል ብለዋል።

99.999% የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ከወንጀል ጋር የሚያያይዛቸው አንዳችም ነገር የለም። 0.001% የሚሆኑት ግን ለድብቅ ወንጀል እየተጠቀሙበት የቴሌግራምን ዝና እና ክብርን እያጎደፉት ይገኛሉ። ይህ ደግሞ ቢሊዮን የሚጠጉ ጨዋ ተጠቃሚዎቻችን የሚጎዳ ነው ብለዋል።

ዱሮቭ ባለፈው ወር በፈረንሳይ ፣ ፓሪስ ኤርፖርት በቁጥጥር ሥር ውለው እንደነበር አይዘነጋም።

በፖሊስ ከተያዙ በኋላ የቀረበባቸው ክስ መተግበሪያው ለወንጀለኞች መፈንጫ እንዲሆን ፈቅደዋል የሚል ነበር።

ሕገ ወጥ የሕጻናት ምስሎች ዝውውርና የአደገኛ እጽ አዘዋዋሪዎችን በሚያበረታታ መልኩ መተግበሪያው ለወንጀል ተግባር እንዲውል ፈቅደዋል በሚል የተከሰሱት ዱሮቭ ከሕግ አካላት ጋር ባለመተባበርም ተወንጅለው ነበር።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በበኩላቸው ሌሎች ለፈጸሙት ወንጀል እሳቸው ተከሳሽ መሆናቸው " አስደናቂ እና ግራ የሚያጋባ " ነገር ነው ሲሉ የፈረንሳይ ባለሥልጣናትን ወርፈው ነበር።

በኃላ ፍ/ቤት ዱሮቭ በዋስ ወጥተው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ማዘዙ ይታወሳል።

Source: tikvahethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ደንብ የኢትዮጵያን ወደ ውጭ የሚላኩ ሆነ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች እንዲያሽቆለቁሉ ሊያደረግ እንደሚችል ጥናት አመላከተ

የአውሮፓ ህብረት ከደን ጭፍጨፋ ነጻ የሆነ ምርት ወደ አባልአገራት ለማስገባት አቅዶ በቅርቡ ተግባራዊ አደርገዋለሁ ባለው የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ደንብ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ሊያዳክም እንደሚችል ይህ አለምአቀፋዊ ጥናት ትንበያ አመላክቷል ።

በለንደን የሚገኘው ታዋቂው የአለም አቀፍ ጉዳዮች ጥናትና ምርምር ኦቨርሲስ ዴቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት (ኦዲአይ) በቅርቡ ባደረገው የጥናት ትንበያ ከታህሳስ 2017 ጀምሮ ተግባራዊ ሊደረግ ያለው የአውሮፓ ህብረት ደንብ በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያ ላይ ሊኖረዉ የሚችለው አሉታዊ ተፅዕኖ አብራርቷል።

Read More

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
ኢትዮቴሌኮም ከቻይናው ኩባንያ ጋር በኢትዮጵያ ከፍተኛ አቅም እንዳለው የተነገረለትን የመረጃ ቋት ሊገነባ መሆኑን አስታውቋል ።

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት የሻንዶንግ ሃይ-ስፒድ ግሩፕ ኩባንያ ጀኔራል ማኔጀር ካይ ኩን ከፍተኛ አቅም ያለው የመረጃ ቋት (Hyperscale Data Center) ግንባታን በተመለከተ ስትራቴጂያዊ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

ይህም የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ከመሆኑ ባሻገር አስተማማኝ እና ሊሰፋ የሚችል የዲጂታል መሠረተ ልማት በማቅረብ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታውን ለማፋጠን ያስችላል ተብሏል።

እ.ኤ.አ. በ1997 የተመሰረተዉ የሻንዶንግ ሃይ-ስፒድ ግሩፕ ኩባንያዉ ቡድኑ በዋናነት በፍጥነት መንገዶች ፣በድልድዮች ፣በባቡር ሀዲድ ፣በባቡር ትራንዚቶች ፣ወደቦች ፣በመላኪያ እና በሎጂስቲክስ ኢንቨስትመንት እና ግንባታ ስራ ላይ ተሰማርቷል።

ራክሲዮ ፣ ዊንጉ አፍሪካ ፣ ሬድ ፎክስ እና ሳፋሪኮም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የመረጃ ማዕከላትን መክፈታቸው ይታወቃል ።

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
#የቴክኖ የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!

የአዲስ አመት ልዪ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ፣ ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማህበራዊ ገጾት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮችን እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡

- Tag ሲያደርጉን ለ Facebook @ TecnoEt ፣ ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia እና ለ TikTok @ TecnoEt ን  ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።)
- በተጨማሪም #TecnoEt2017 ን keyword መጠቀም እንዳይረሱ)
የኢትዮጵያ የተቀማጭ መድን ፈንድ በ2016 በጀት አመት ከፋይናንስ ተቋማት 6.5 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን አስታወቀ።

የሰበሰበውን ገንዘብ በዋናነት በግምጃ ቤት ሰነድ ላይ ኢንቨስት በማድረግ በተጠቀሰው አመት 185 ሚሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ነው የፈንዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ደሳለኝ አምባው (ዶር) የገለፁት።

የመድን ፈንዱ ዜጎች በፋይናንስ ተቋማት ለሚያስቀምጡት ገንዘብ ዋስትና ለመስጠት በመጋቢት 2015 ዓም መቋቋሙ ይታወሳል።

በዚህ የፋይናንስ ተቋማት ቢወድቁ እስከ 100 ሺ ብር ድረስ ሽፋን እንደሚሰጥ ነው የገለፀው።

አሁን ላይ ከጠቅላላ አስቀማጮች 97 በመቶ የሚሆኑት ከ 100 ሺ ብር በታች ያስቀመጡ በመሆኑ ፈንዱ የዜጎችን ሃብት ሙሉ ለሙሉ ከመመለስ አንፃር አስተማማኝ ቦታ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
Partner's Content: #Mesirat

የዲዛይን አስተሳሰብን በመቆጣጠር ሀሳቦችን ወደ ተጨባጭ ምርቶች እና አገልግሎቶች መለወጥ ይቻላል! 🚀💡

"የንድፍ አስተሳሰብ" በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የቨርቹዋል ሥልጠና ላይ ተገኝተው አስፈላጊ መፍትሄዎችን ይፍጠሩ!
🗓 መስከረም 20, 2017 ዓ.ም
🕒 ከቀኑ 8:00 እስከ 11:00 ሰዓት

https://forms.gle/6aurE6Q8nAZQdNz18 በኩል ይመዝገቡ
ቲክ ቶክ በአፍሪካ የአማካሪ ቡድን ማቋቋሙን አስታወቀ።

ቲክቶክ የተሰኘው የቪድዮ ማጋሪያ የማህበራዊ ሚዲያ በአፍሪካ የአማካሪ ምክር ቤት ማቋቋሙን ተገልጿል። በዚህ ምክር ቤት ፕሮፌሰር መድኅኔ ታደሰን ጨምሮ 8 አባላት ያሉት ነው።

መተግበሪያው የሀገራትን ባህልና እሴት እንዲጠብቅ ሲደርስ ለነበረበት ጫና ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ አማካሪ ቡድን የቲክቶክ ፖሊሲ ከአፍሪካ ሀገራት ህጎች ጋር አብረው እንደሚሄዱ፤ እንዴት ሀሰተኛ እና ጥላቻ ንግግሮቾን መቆጣጠር እንደሚችል፤ ከአከባቢው ማኅበረሰብ ጋር  መተባበር በሚቻልበት መልኩ እና የዲጂታል ክህሎትን ከማሳደግ አንጻር ያማክራሉ ተብሏል።

Source: tikvahethmagazine
@Ethiopianbusinessdaily
ውድ የ @Ethiopianbusinessdaily ቤተሰቦች ፣

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!
Partner's Content: #Mesirat

📢 ሐዋሳ፣ ወደ እናንተም እየመጣን ነው!

በቴሌግራም ቦት በኩል የምንሰጠው ስልጠና ሙያችሁን ለማሳደግ እንዴት እንደሚረዳችሁ ለማወቅ ተሳተፉ! 🚀

🗓 መስከረም 20, 2017 ዓ.ም
🕒 ከቀኑ 7:30 እስከ 11:00 ሰዓት
📍 ሳውዝ ስታር ሆቴል (South Star Hotel)፣ ሐዋሳ

ቁልፍ ርዕሶች፦:
🔹የመስራት ፕሮጀክት አጠቃላይ እይታ እና ግቦቹ
🔹የመስራት የሙያ ማጎልበት ፕሮግራም እና ጥቅሞቹ
🔹ለመስራት ቴሌግራም ቦት እንዴት እንደምትመዘገቡ እና ለየት ያሉ ስልጠናዎቻችንን እንዴት እንደምትካፈሉ

https://forms.gle/TemQSkS6k7rPLNa57 ተመዝገቡ!

#GigEconomy #Mesirat #Upskilling #CareerBoost #Hawassa
#WollegaDevelopment State Minister for Finance, Eyob Tekalign (PhD), is urging financial institutions to support the four areas of Wollega as part of Prime Minister Abiy Ahmed's (PhD) desire to modernise infrastructure and urban landscapes. The Nekemte-centred corridor project is set to commence, marking a step towards the region's infrastructure upgrade.

Read More

Source: addisfortune
@Ethiopianbusinessdaily
Key concerns include the availability of terminal stations, maintenance garages, and gas stations, which are critical for successful implementation. Ayalew noted that addressing these infrastructure needs is essential to maximize new rules and regulations being pushed by city leaders.

Read More

Source: addisfortune
@Ethiopianbusinessdaily
ይህ እስካሁን በሚድያ ምንም ያልተነገረለት የህንፃ ግንባታ መመርያ በአዲስ አበባ የግንባታ ታሪክ ከፍተኛው ተፅእኖ ፈጣሪ ይመስለኛል፣ የደብዳቤውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ችያለሁ

መስከረም 3 ተፈርሞ ለሁሉም ክፍለ ከተሞች በተላለፈው በዚህ መመርያ መሰረት ከ15 ሜትር እና በላይ ስፋት ያላቸው መንገዶች የሚያዋስኗቸው ይዞታዎች ዝቅተኛው የቦታ ስፋት ሴት ባክ (set back) ከተቀነሰ በኋላ ቢያንስ 500 ሜትር ካሬ መሆን እንዳለበት ይደነግጋል፣ ካልሆነ የግንባታ ፈቃድ አይሰጥም ማለት ነው።

በሌላ በኩል በነዚህ መንገዶች ላይ ዝቅተኛው የህንፃ የጎን ስፋት (frontage) ከ20 ሜትር ያላነሰ መሆን አለበት ይላል፣ ይህም ካልተሟላ የግንባታ ፈቃድ አይሰጥም ማለት ነው።

በዚህ ምክንያት በመቶ (ምናልባትም በሺዎች) የሚቆጠሩ ግንባታዎች እንዲቆሙ እየተደረገ ነው።

Source: eliasMeseret
@Ethiopianbusinessdaily
ኢትዮጵያ የጀመረችው የቁም እንስሳትን በባቡር የመላክ ስራ ከፍተኛ ፍላጎት እየታየበት ነው - ኢንጂነር ታከለ ኡማ

ኢትዮጵያ የጀመረችው የቁም እንስሳትን በባቡር ወደ ውጭ የመላክ ስራ ከውጭ ሀገራት ከፍተኛ ፍላጎት እየታየበት መሆኑን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለፁ፡፡

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ከአዳማ ወደ ጂቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ስራ ጋር ተያይዞ ለወደፊት ብዙ የቁም እንስሳትን ለማስተናገድ እየተሰራ ያለውን የማስፋፊያ ስራ መጎብኘታቸውን ገልፀዋል።

ከመጀመሪያው የቁም እንስሳትን በባቡር የመላክ ስራ በኋላ ከውጭ ሀገራት ከፍተኛ ፍላጎት መምጣቱን የገለፁት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ይህንን እያደገ የመጣውን ፍላጎት ለማሟላት የአቅም ማስፋፊያ ያስፈልጋል ብለዋል።

በዚህ የማስፋፊያ ስራ ላይ በበዓላት ቀን ጨምሮ እየሰሩ ለሚገኙ ሰራተኞች ኢንጂነር ታከለ ኡማ ምስጋና አቅርበዋል።

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዳማ ወደ ጂቡቲ የቁም እንስሳት የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ይፋ መደረጉ ይታወሳል፡፡

Source: EBC
@Ethiopianbusinessdaily
2024/11/15 15:44:03
Back to Top
HTML Embed Code: