Telegram Web Link
ዘመን ባንክ የተከፈለ ካፒታሉ ወደ 7.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታዉቋል

የባንክ ኢንደስትሪዉን ከተቀላቀለ 16 ዓመታትን ያስቆጠረው ዘመን ባንክ የተፈረመ ካፒታሉ ወደ 15 ቢሊዮን ብር መድረሱንና የተከፈለ ካፒታሉ ደግሞ ወደ 7.5 ቢሊዮን ብር መጠጋቱን አስታዉቋል።

ባንኩ በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት ህጋዊ መጠባበቂያዉ ወደ 1.7 ቢሊዮን ብር ማሳደግ መቻሉን ያስታወቀዉ ከ 200 በላይ በባንኩ ረዥም ጊዜ አብረውት ሲሰሩ የነበሩ ደንበኞችን እና አጋሮቹን እዉቅና በሰጠበት መድረክ ላይ ነዉ ።

የባንኩ ዋና አስፈፃሚዉ አቶ ደረጀ ዘነበ እንደተናገሩት የፋይናንስ ዘርፉ እና አገልግሎቶቹ ነፃ እየሆኑ ባለበት በአሁኑ ጊዜ ከደንበኞቹ እና አጋሮቹ ጋር መስራት በመቻላችን እድለኞች ያደርገናል ብለዋል።

ከዘመን ባንክ እዉቅና የተሰጣቸው በንግድና ኢንቨስትመንት ፣ አበባ እርሻ ልማት ፣ በቴክኖሎጂ ፣ በአየር ትራንስፖርት ፣ በሆቴል እና በቱሪዝም ላይ የተሰማሩ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ደንበኞች መሆናቸዉ ተነግሯል ።

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
የዶላር ምንዛሬ ዋጋ ከፍ ያለ ጭማሪ አሳይቷል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ7 ቀናት ጭማሪ ያልታየበት ወጥ የምንዛሬ ዋጋ ነበር።

ባንኩ ዛሬ ሲያገበያይበት የነበረው የምንዛሬ ዋጋ ከፍ ያለ ጭማሪ የታየበት ነበር።

አንዱ የአሜሪካ ዶላር መግዣው ወደ 112 ብር ከ3957 ሳንቲም ደርሷል።

የመጫው ዋጋም 124 ብር ከ7592 ሳንቲም ገብቷል።

በፓውንድ ላይም ጭማሪ ተመዝግቧል።

አንዱ ፓውንድ መግዣው 141 ብር ከ6314 ሳንቲም ተቆርጦለት ውሏል። መሸጫው 157 ብር ከ9487 ሳንቲም ነበር።

ዩሮ መግዣው 125 ብር ከ0177 ሳንቲም መሸጫው 138 ብር ከ7697 ሳንቲም ሆኖ ውሏል።

የUAE ድርሃም መግዣው 30 ብር ከ6030 ሳንቲም መሸጫው 33 ብር ከ9693 ሳንቲም ገብቷል።

Source: tikvahethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
NBE Launches Campaign to Boost Remittance Revenue and Foreign Currency Flow

The National Bank of Ethiopia (NBE) has unveiled a strategic initiative to enhance foreign currency inflows by launching a six-month campaign aimed at increasing remittances. The campaign, which involves government agencies, financial institutions, diplomatic missions, and the diaspora, is part of broader efforts to stimulate hard currency generation.

Source: 2merkato
@Ethiopianbusinessdaily
Ethiopia Unveils First-Ever Tourism Satellite Account

Ethiopia has launched its first-ever Tourism Satellite Account (ET-TSA), a strategic initiative designed to unlock the full economic potential of the country's tourism sector.

Source: 2merkato
@Ethiopianbusinessdaily
The Traffic Management Authority has introduced a series of measures to ensure compliance, including licensing requirements, safety protocols, and standardised parking indicators. Officials plan to conduct a comprehensive impact assessment and engage with the public to gather feedback and address concerns.

Read More

Source: addisfortune
@Ethiopianbusinessdaily
ብሉምበርግ ሚዲያ ኢኒሼቲቭ አፍሪካ (BMIA) የፋይናንሺያል ጋዜጠኝነት ስልጠና ፕሮግራም በኢትዮጵያ ጀመረ።

በመጀመሪያው ቡድን ውስጥ 55 ከመገናኛ ብዙሃን፣ ከፋይናንስ እና ከመንግስት ሴክተሮች የተውጣጡ ሰልጣኞች ይሳተፋሉ።

ፕሮግራሙ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ዘገባ ላይ በማተኮር የንግድ እና የፋይናንስ ጋዜጠኝነትን ለማሳደግ የተነደፈ ነው።

ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ እና ከስትራትሞር ዩኒቨርሲቲ (ቢዝነስ ት/ቤት በኬንያ) ጋር በመተባበር ይሰጣል።

ተሳታፊዎች በመረጃ ትንተና፣ በካፒታል ገበያ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በፐብሊክ ፖሊሲ ​​የሚሰለጠኑ ይሆናል።

የ BMIA ፕሮግራም ከ2015 ጀምሮ በመላው አፍሪካ ከ900 በላይ ጋዜጠኞችን አሰልጥኗል።

Source: stockmarketet
@Ethiopianbusinessdaily
ኢንቨስት ስናደርግ ምናይነት የአደጋ ስጋት መከላከያ መንገዶችን መጠቀም ይኖርብናል?

- የመጀመሪያው ኢንቨስት ምናደርግበትን ሰነደመዋለንዋዮችን ብዝሃነት መጨመር ነው። “Don’t put all your eggs in one basket” እንደሚባለው ያለንን ገንዘብ በሙሉ በተመሳሳይ ነገር ላይ ኢንቨስት ማድረግ የለብንም።

- ኢንቨስት ያደረግንባቸው ነገሮች ፈጣን የዋጋ ለውጥ እንዳይታይባቸው መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ለምሳሌ ኢንቨስት ያደረግነው አክሲዮንና ቦንድ ላይ ከሆነ አክሲዮኖች በብዛት ለvolitility የተጋለጡ ስለሆኑ portfolio ውስጥ ቦንዶችንም በመጨመር ይህንን ማመጣጠን አለብን።

- በቋሚነት ኢንቨስት ማድረጋችንን አለማቆም። ትርፍ ለማግኘት, "ትክክለኛ" አክሲዮን መምረጥ እና "በትክክለኛ" ጊዜ መሸጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ ሁሉ በትዕግስት እና በረጅም ጊዜ እቅድ ላይ የተመሰረተ ነው።

- የኢንቨስትመንት ሪስክን በአግባቡ በማጤን በቁጥራዊ ስሌቶች ልናስቀምጠው የምንችለው ሪስክ ማድረግ መቻል ይኖርብናል። ሁሉም ሪስክ ልንለካው በምንችለው መንገድ ልኬት ማስቀመጥና ቀጣይ እርምጃዎች ላይ የተጠና ስልት መከተል ይኖርብናል።

- በተጨማሪ ደግሞ margin of safety ለኢንቨስትመንታችን ማስቀመጥ ይኖርብናል። ይህም ማለት አንድ ባለሀብት ዋስትናዎችን የሚገዛበት የገበያ ዋጋቸው ከድርጅቶቹ ውስጣዊ እሴት በታች ከሆነ ብቻ የሚገዛበት የኢንቨስትመንት መርህ ነው።

- በመጨረሻ ደግሞ አቅማችን ሚችለውንና ልንቋቋም የምንችለውን የሪስክ መጠን (maximum loss plan) ማወቅ አስፈላጊ ነው።

Source: stockmarketet
@Ethiopianbusinessdaily
ኢትዮ ቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት የቴሌብር ደንበኞችን ቁጥር በ15.7% በመጨመር 55 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱን በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው የሦስት ዓመት ስትራቴጂ እና የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የቢዝነስ ዕቅድ መግለጫ ላይ ጠቅሷል።

ኩባንያው፥ የቴሌብር ወኪሎችን ቁጥር በ28% በማሳደግም 275 ሺህ ለማድረስ እንዲሁም በቴሌብር ግብይት የሚፈጽሙ ነጋዴዎችን (Merchant) ቁጥር በ102% በማሳደግ 367 ሺህ ለማድረስ በእቅዱ እንደተቀመጠም ጠቅሷል።

በተጨማሪም፥ የኤሌክትሮኒክ ንግድ ክፍያዎችን፣ አለም አቀፍ የኦንላይን ክፍያዎችን፣ ተጨማሪ አጋሮችን በማሳተፍ የሃዋላ አገልግሎቶችን ለማሳደግ እንደሚሰራም ነው የገለጸው።

Source: tikvahethmagazine
@Ethiopianbusinessdaily
Partner's Content: #Mesirat

ገቢዎን እና ወጪዎን እንዴት ማስተዳደር እንደሚችሉ ይማሩ! 📊💡

"የግል በጀት አወጣጥ መሠረታዊ ነገሮች" በሚል ላዘጋጀነው የኦንላይን ስልጠና ይመዝገቡ!

🗓 መስከረም 10, 2017 ዓ.ም
ከቀኑ 8:00 እስከ 11:00 ሰዓት
💻 https://forms.gle/t2KczdEpPrNstvjz5 በመጠቀም ይመዝገቡ!

ይህ አጋጣሚ እንዳያመልጥዎ!
Ethio Telecom Rolls Out $1 Billion Budget for Massive Expansion

Ethio Telecom, the state-owned telecom provider with 130 years of service, has unveiled a formidable budget of around $1 billion as it gears up to launch 260 new products and services in the coming year.

Read More

Source: shegamedia
@Ethiopianbusinessdaily
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ የታሪፍ ማሻሻያ እንደሚኖር ፍንጭ ሰጡ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተቋሙን የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ይፋ አደረጉበት መግለጫ ላይ ከታሪፍማሻሻ ጋር ተያይዞ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

“ዋጋ ሳታስተካክሉ እናንተስ መቀጠል ትችላላችሁ ወይ ለሚለው ጥያቄ፤ ተገቢ እና ትክክለኛ ነው” ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፤ “ዘለን ታሪፉን ያለስተካከለው የደንበኞቻችንን እንዲሁም በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ እንዲረጋጋ እና ጤናማ እንዲሆን ስለምንፈልግ ነው” ብለዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ፍሬህወት ታምሩ በመግለጫቸው ላይ “በጣም በተጠና መልኩ የደንበኞችን የመክፈል አቅም ታሳቢ ያደረገ መጠነኛ የሆኑ የዋጋ ጭማሪዎች ይኖረናል፤ ነገር ግን በሁሉም ደንበኞች ላይ ተፈጻሚ አይደረግም” ብለዋል።

Source: seleda
@Ethiopianbusinessdaily
Ethiopian Reinsurance Saves USD 50 Million in Foreign Currency

Ethiopian Reinsurance, established eight years ago with an initial capital of Birr 1 billion, announced that it has saved the country USD 50 million in foreign currency. The company, which provides reinsurance services to Ethiopian insurance companies, has played a crucial role in retaining funds that were previously spent abroad.

Read More

Source: 2merkato
@Ethiopianbusinessdaily
Partner's Content: #Gebeya

ኤክስፐርት ለመሆን እና ከፍተኛ ተፈላጊነት ባላቸው ሙያዎች የምስክር ወረቀት ማግኘት ይፈልጋሉ? የ Safaricom Talent Cloud ትክክለኛው ቦታ ነው፡

https://bit.ly/3Re7G22

በመረጡት የትምህርት ዘርፍ እውቀትን ለመገንባት በጥሩ ሁኔታ ከተዘጋጁ ኮርሶች በተጨማሪ የሚከተሉትን ያገኛሉ፡-

- በመረጡት የሙያ መስክ የላቀ ለመሆን እንዲረዳዎ በባለሙያዎች የተመረጡ የትምህርት ካሪኩለሞች
- እጅግ ታዋቂ ከሆነው Pluralsight የonline መማሪያ ድህረገጽ ሰርተፍኬት
ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚመሩ የስልጠና ቡድኖችን
- በየወሩ ነጻ የ6 GB የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚም ይሆናሉ

እነዚህን ተጨማሪ ጥቅማጥቅሞችና ግልጋሎቶች በማግኘት በፍጥነት ያሎትን እዉቀትና ክህሎት በማሳደግ በስራ ዘርፎ ዉጤታማ መሆን ይችላሉ። https://bit.ly/3Re7G22 ይጎብኙ!

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራሞ ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://www.tg-me.com/+3nNaOCMHiXgyMTA0
የቤቶች ኮርፖሬሽን በዚህ ዓመት በድሬደዋ የመኖሪያ ቤት ግንባታ እንደሚያካሂድ ገለጸ።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በድሬዳዋ አስተዳደር በወሰደው መሬት ላይ የነበረው የይገባኛል ክርክር በመቋቸቱ በዚህ ዓመት የመኖሪያ ቤት ግንባታ ሊያካሂድ መሆኑ አስታዉቋል።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከዚህ በተጨማሪ በድሬዳዋ እና በአዲስ አበባ በዚህ አመት ለሚያከናውኗቸው የልማት ስራዎች 7 ቢሊዮን ብር በጀት መያዙን የኮርፖሬሽኑ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ እዉነቱ ወርቅነህ ገልጸዋል።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በድሬዳዋ ከተማ ወደ 1993 ቤቶችን ያስተዳድራል። ከነዚህም ዉስጥ 541 የንግድ ቤቶች ናቸዉ። የተቋሙ ሀላፊ እንደሚሉት በ2016 ዓ.ም የንግድ ቤቶች ላይ መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ በዓመቱ መጨረሻ 38 ሚሊዮን ብር መሰብሰብ ተችሏል።

Source: tikvahethmagazine
@Ethiopianbusinessdaily
Partner's Content: #የቴክኖ
የአዲስ ዓመት ልዩ የበዓል ስጦታ!


የአዲስ አመት ልዪ ስጦታ ከቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ፣ ከየትኛውም የቴክኖ ሱቅ የቴክኖ ስማርት ስልክን ሲገዙ አብሮት ካለ ወዳጅ ዘመድ ወይም ጓደኛ ጋር ፎቶ በመነሳት የማህበራዊ ገጾት ላይ በመለጠፍ እና ብዙ ላይክ በማግኘት የዱባይ ደርሶ መልስ የቢዝነስ ክላስ የአውሮፕላን ትኬት፣ ላፕቶፖች፣ የቴክኖ ስማርት ስልኮችን እና ገደብ አልባ የኢንተርኔት ፓኬጆችን ይሸለሙ፡፡

የውድድሩ መመሪያ
1. የቴክኖ ኢትዮጵያን ፌስ ቡክ ፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክ ገጾችን ፎሎው ያድርጉ፡፡
2. የተነሱትን ፎቶ በመረጡት ማህበራዊ ሚዲያ ሲለጥፉ የቴክኖ ኢትዮጵያን ገፅ ከፖስቶት ጋር ታግ ያድርጉ፡፡ ብዙ ላይክ እና ኢንጌጅመንት ያገኘው ተሸላሚ ይሆናል፡፡

- Tag ሲያደርጉን ለ Facebook @ TecnoEt ፣ ለ Instagram @ TecnoMobileEthiopia እና ለ TikTok @ TecnoEt ን  ሜንሽን ማድረግ እንዳይረሱ።)

- በተጨማሪም #TecnoEt2017 ን keyword መጠቀም እንዳይረሱ)
ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ ከተጣለው የማህበራዊ ልማት #ቀረጥ_ነጻ የሚሆኑ እቃዎችን ለመወሰን ገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ አውጥቷል።

ይኸው መመሪያ" መመሪያ ቁጥር 1023/2017" ይሰኛል።

በዚህ መመሪያ መሰረት ፥ ለህብረተሰቡ በነጻ የሚሰጡ የትምህርት እና የጤና አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እንዲሁም በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን ለመርዳት ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች የማህበራዊ ልማት ቀረጥ የተጣለበትን አላማ ለማሳካት የሚያግዙ በመሆኑ ከቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጓል።

ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ የተደረጉ እቃዎች?

የሚከተሉት እቃዎች ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ ሆነው ወደ ሀገር ይገባሉ፡፡

1. ለሚከተሉት የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከውጭ አገር በእርዳታ የሚላኩ እቃዎች :-
.
.
.
Read More

Source: theethiopianeconomistview
@Ethiopianbusinessdaily
የገንዘብ ሚኒስቴር በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ለአደጋ ጊዜ እርዳታ የሚለገሱ ሸቀጦች ከቀረጥ ነፃ እንዲገብ የሚፈቅደውን መመሪያ ማዉጣቱን አስታዉቀዋል ።

ሚኒስትሩ ያወጣዉ አዲሱ መመሪያው
"ከማህበራዊ  ልማት  ቀረጥ ነፃ የተደረጉ ዕቃዎችን ለመወሰን" የሚል ሲሆን ይህም የትምህርት፣ የጤና እና የአደጋ መከላከል ስራዎችን ለመደገፍ ዓላማ ያለዉ መሆኑ ተመላክቷል።

በዚህ መመሪያ ዉስጥ ከውጪ የሚገቡ ቁልፍ የመከላከያ እና የህዝብ ደህንነት ዕቃዎች፣ ለምሳሌ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፖሊስ ሃይሎች እና የብሄራዊ መረጃ አገልግሎቶች መሳሪያዎች፣  ከቀረጥ ነጻ የሆኑ እቃዎች ዝርዝር መካከል ይገኝበታል ።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከማህበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ ለማድረግ ዓላማ ባደረገዉ መመሪያ ቁጥር 1023/2024 መሰረት ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና ህጻናትን፣ ሴቶችን፣ አዛውንቶችን እና አካል ጉዳተኞችን የሚረዱ ድርጅቶችን ጨምሮ ለመንግስት ተቋማት የተበረከቱ እቃዎች ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ ይገባሉ ተብሏል።

የጉምሩክ ኮሚሽኑ  ከቀረጥ ነፃ የወጡ ዕቃዎችን አጠቃቀም በቅርበት ተከታትሎ የሩብ ዓመቱን ሪፖርት ለገንዘብ ሚኒስቴር  እንደሚያቀርብ ተገልጿል።

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
Partner's Content: #Mesirat

⚠️ ሐዋሳ ውስጥ ከሆናችሁ! ⚠️

ቢዝነስዎን ስኬታማ ለማድረግ እንደግፍዎታለን!

https://forms.gle/RFt2RTUhznLSi7np9 ተመዝግበው ቦታዎን ያሲዙ።

🗓 መስከረም 20, 2017 ዓ.ም
🕒 ከጠዋቱ 3:30 እስከ 6:30
📍 በኬር አውድ ኢንተርናሽናል ሆቴል (Ker-Awud International Hotel), ሐዋሳ

የመስራት ስራ ፈጠራ ፕሮግራም Info Session ጥቅሙ ምንድን ነው?
     - መስራት ምን እንደሆነና ቢዝነስዎትን እንዴት እንደሚደግፍ ያውቃሉ፣
     - ፕሮግራሙን እንዴት መቀላቀል እንደሚቻል ያውቃሉ፣
     - ስለሚሰጡት ድጋፎች እና ለሚኖርዎት ጥያቄ መልስ ያገኙበታል።
     - በቴሌግራም ቦት በኩል ለሚሰጥ ሥልጠና መመዝገብ ይችላሉ።
Ethiopia’s IMF Program Pins on Digitization for Success

Ethiopia’s four-year economic reform program, supported by a 3.4-billion-dollar Extended Credit Facility (ECF), entails thorough digitization across multiple public sectors.

Read More

Source: shegamedia
@Ethiopianbusinessdaily
ግዙፉ መንግስታዊ የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ሊያደርግ እንደሚችል አስታዉቋል

ተግባራዊ ከተደረገ አንድ ወር ያለፈዉ የማክሮኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተከትሎ የደበንኞችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ መታሰብ ተቋሙ ገልጿል።

የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት ሁሉም ደንበኞች እና አገልግሎቶች ላይ ዋጋ አንጨምርም ነገር ግን የደንበኞችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ በአንድአንድ ምርትና አገልግሎቶች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል ብለዋል።

የኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ ወዲያዉ ያልተስተካከለበት ምክንያት የደንበኞቹን አጠቃላይ ደግሞ የማክሮኢኮኖሚ ለዉጥ እንዲረጋጋ በማሰብ መሆኑ ተነግሯል ።

ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የብር ዋጋ ከ750% በላይ ሲቀንስ ኢትዮቴሌኮም ባለፉት ስድስት አመታት በከፍተኛ ደረጃ የዋጋ ቅናሽ በማሳየቱ ዋጋው ከአለም ዝቅተኛው እና ለተጠቃሚዎች በጣም ተመጣጣኝ እንዲሆን አድርጎታል። 

እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገለፃ እ.ኤ.አ በ 2018 ላይ ከ 40 እስከ 50 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ ያደረገ ሲሆን በሂደትም የተለያዩ የታሪፍ ማሻሻዎችን ማድረጉን እንዲሁም ፤ የቅርብ ጊዜ ሪፖርቶችንም ደግሞ ከተመለከትን ኢትዮ ቴሌኮም ዝቅተኛ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ነው የሚያሳየው ብለዋል።

አሁን ላይ ተቋሙ በተለይ በድምፅና በዳታ አገልግሎት ላይ የሚያስከፍለዉ ታሪፍ ርካሽ እንደሆነ ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አዲስ የታሪፍ ለማድረግ እንደታሰበ ከመናገር ዉጪ መቼ እንደሚተገበር ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
2024/11/15 07:47:31
Back to Top
HTML Embed Code: