Telegram Web Link
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
" መጣህ ረዩ? " እናቱ ናት ቁጭ ብላ ልብስ እያነጣጠፈች ነበር።
" ቆይ ላግዝሽ..." ሄዶ አጠገቧ ቁጭ አለ።
" ፈተና አሪፍ ነበር? "
" አልሀምዱሊላህ አሪፍ ነበር...አባ አልመጣም እንዴ? "
" አዎ ገና ተጨማሪ ሶስት ቀን ሳይቆይ አይቀርም። " አባቱ ብዙውን ጊዜ ፊልድ ስለሚወጣ ቤት የሚሆንበት ቀን በጣም ትንሽ ነው።
" ቆይ አንናፍቀውም እንዴ? እንዴት ይሄን ያህል ቢዚ ይሆናል? "
" ምነው ናፈቀሽ እንዴ እናቴ? "
" እድሜዬ እየሄደ ነው። ቤት ውስጥ ብቻህን ስትውል ቤቱ ራሱ ይቀዘቅዛል...ከዛም አልፎ ሊበላህ ነው የሚደርሰው። ለነገሩ አሁንማስ አንተ አለህልኝ...ከፈለገ አይምጣ..." ከልቧ እንዳልሆነ ያውቀዋል።
" ያው ስራ ሆኖበት ነው እንጂ መቼስ በኛ የሚጨክን አንጀት እንዴለው ታውቂያለሽ..." ተነስቶ አቀፋት።

" እኔ ምልሽ እማ ባለፈው ወ/ሮ ኸዲጃ ለክረምት ወደ ድሮ ከተማቸው ሊሄዱ እንደሆኑ ስትነግርሽ ሰማው ልበል.."
" አዎ ከአንድ ሳምንት በኋላ መሰለኝ እንሄዳለን ያለችኝ..."
" ሁሉም ናቸው የሚሄዱት? "
" አዎ..ምነው? " ለምን እንደሚጠይቃት ግራ ተጋብታለች።
" ኧረ ምንም እንዲው ለማወቅ ነው..."
" እም..ግን አይመስልም..." ፊቱን ሲያዞር አይኑን ለማየት በዞረበት እየዞረች ፈገግ ማለት ጀመረች።
" እማ ደሞ ምን አስበሽ ነው? እኔ ዝም ብዬ ነው የጠየኩሽ። በቃ ዩኒፎርሜን ልቀይር.. " ወድያው ተነስቶ ወደክፍሉ ገባ። አይኑን ካየች ልታውቅበት ስለምትችል...

ክፍሉ እንደገባ ዩኒፎርሙን ሳያወልቅ አልጋው ላይ ሄዶ ተዘረረ። ክረምቱን አልፎ አልፎ ከነፋሩቅና ሰብሪን ጋር ሆነው ለማሳለፍ አስበው ነበር። ግን ምን ያደርጋል አምሪያ ልትሄድ ነው። ለወራት ያክል ጭራሽ እንደማያያት ሲያስብ በጣም ከፋው ፤ ገና ከአሁኑ ትናፍቀው ጀመር።

ስልኩን አውጥቶ ደወለላት። አታነሳም ... ደግሞ ደወለላት አሁንም አላነሳችም። ስልኩን አልጋው ላይ ወርውሮት ለመተኛት መሞከር ጀመረ።
ብዙም ሳይቆይ ግን የቤታቸው በር ተከፍቶ እናቱ ከአንድ ሰው ጋር ስታወራ ሰማች። የአምሪያ ድምፅ ወድያው ነበር ጆሮ ውስጥ የገባው። ከተኛበት ተስፈንጥሮ ተነስቶ ከክፍሉ ወጣ።
" እንዴ አምሪያ መተሻል እንዴ? " በአጋጣሚ የወጣ ለማስመሰል ወደ ኪችን ሄዶ ውሀ መጠጣት ጀመረ። ምን እንደሆነ ባያውቅም የሆነ እቃ ይዛላት ነበር የመጣችው። እቃ ልታቀብል ስለመጣች ልትቆይ እንደማትችል ሲያስብ ተናደደ።
" እንዴ ትንሽ ተጫውተሽ ነው እንጂ የምትሄጂው...ረዩ እስኪ የሚጠጣ ነገር ይዘህላህ ና..." እናቱ እንደዚ ስትል ወድያው ፊቱ በፈገግታ ተለወጠ። በልቡ " የውስጥ አውቅ እኮ ነሽ! " እያለ ከፍሪጅ ውስጥ እርጎ ይዞላት መጥቶ እሱም እዛው ተቀመጠ።

እስከመግሪብ ድረስ እዛው ከቆየች በኋላ እየመሸ ስለነበር ወደቤት ሊሸኛት ወጣ።
" መች ነው የምትሄዱት? "
" እስኪ ኢንሻአላህ በዚ ሳምንት እንሄዳለን ብለዋል። ከመሄዴ በፊት መጥቼ ሰላም እላችኋለው..." ቀና ብላ አየችው ፊቱን ጥሎታል።
" እዛ ከሄድሽ በኋላ ደሞ ደውዪ እኔም እደውላለው..." ሲያወራት እንደበፊቱ አይደለም። አነጋገሩ ላይ ያየችው ለውጥ አስገርሟታል።
" እሺ የተከበሩ እደውላለሁ! " ቤታቸው ጋር ደርሳ ስለነበር " ደና ደር " ብላው ሄደች።

በዚ ሰአት እንዳትሄድ የሚያደርግ ስልጣን ቢኖረውና ባይለቃት ምነኛ ደስ ባለው ነበር። ሳይፈልግም ቢሆን ሸኛት።

አምሪ ወደክፍለሀገር ከሄደች እንደቀልድ 2 ሳምንት ተቆጠረ። ለረያን ግን እንደሁለት አመት ነበር ጊዜው የረዘመበት። አልፎ አልፎ በስልክ ቢያወሩም ናፍቆቱን ግን አልቻለውም ነበር። የአምሪያ ስለማይታወቅባት ነው እንጂ እሷም ከሱ ባልተናነሰ ነው የናፈቃት። ሲደዋወሉ ስለሀገሩ ፣ ስለእረፍት ምናምን እንጂ ስለነሱ አንድ ቀንም አውርተው አያውቁም። ረያን ቢያንስ ናፍቆቱን ሊነግራት ይልና አፉ ተሳስሮበት መልሶ ሳይነግራት ይተወዋል። ከዚ በላይ መያዝ ግን የሚችል አልመሰለውም።

*

" አምሪያዬ ነይ ሰው ይፈልግሻል..." አያቷ ናቸው ውጪ ቁጭ ብለው ፀሀይ እየሞቁ ነበር።
" ማነው..." እያለች ከቤት ወጣች።
አያቷ ለመጣው ሰው ተቀምጦ እንዲጠብቃት ወንበር እየሰጠችው ነበር። አምሪያ ስታየው ደነገጠች። ጭራሽ ያልጠበቀችውን ሰው ባልጠበቀችው ቦታ ላይ ነው ያየችው።

#ክፍል_ስድስት ( ⓺ ) ይቀጥላል...
❦ ════ •⊰❂⊱• ════ ❦

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🃏𝙼𝚎𝚔𝚒🀄)
Telebirr

17 kutr yalaw in box yawaragn


@Meki3
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━━━─╝



#ክፍል_ስድስት ( ⓺ )
❦•⊰❂⊱• ════ ❦

" በአላህ እኔ እኮ አላምንም! አንተ ልጅ አለህ ግን? ለነገሩ ምን ልጅ እላለው ሰውዬ ልበል እንጂ..." ወንበር ስባ ከሀያቷ ጎን ተቀመጠች።
" ምን? ይሄን ያህል ተለውጫለው እንዴ? "
" እንዴ ቀላል...እኔ ሆኜ ነው ራሱ ያስታወስኩህ ..." ሳሊም...ስታለቅስ ያባበላት...በልጅ አንደበቱ መክሮ የለወጣት! ልርሳው ብትል እንኳን ልትረሳው የማትችለው ሰው ነው። እሱ 8ተኛ ክፍል እስከሚጨርስ ድረስ አንድ ትምህርት ቤት ነበር የተማሩት። 9 ሲገባ ትምህርት ቤቱ ያለው እስከ 8 ብቻ ስለነበር ሌላ ትምህርት ቤት ቀየረ።

የዛኔ አምሪያን በአንድ ክፍል ይበልጣት ነበር። አሁን ላየው ግን ጭራሽ 19 አመቱ አይመስልም። ፊቱን የሞላው ፂሙ ትልቅ ሰው አስመስሎታል።
" ደና ነህ ግን በአላህ? " አሁንም እንደተገረመች ነው።
" አልሀምዱሊላህ ደና ነኝ...ደሞ እኔን ትያለሽ አንቺ ራሱ በጣም ተለውጠሻል እኮ! " እሱም በግርምት ያያታል።
" አያቴ አታስታውሺውም? ልጅ እያለን አንድ ሁለቴ እኮ እዚ ቤት መጥቶ ያውቃል..."
" ኧረ እኔንጃ ልጄ..." ደረታቸው ላይ የተንጠለጠለውን መነፅር አይናቸው ላይ አርገው በደንብ ለማየት ሞከሩ።
" ችግር የለውም ከዚ በኋላ በደንብ እንተዋወቃለን...ኢንሻአላህ " ፈገግ ብሎ ተመለከታቸው።
" ታድያ ምነው ግባም አትዪውም እንዴ? በሉ ኑ ወደውስጥ እንግባ ፀሀይዋም እየጠነከረች ነው..." ተያይዘው ወደቤት ገቡ። የአምሪያ እናቷም አባትና ወንድሟም ሰው ለመጠየቅ ወተው ስለነበር ከአያቷና እሷ ውጪ ማንም ቤት አልነበረም።

አምሪያ ምግብ ለማቀራረብ ጉድ ጉድ ስትል ሰሚርና አያቷ መጨዋወት ጀመሩ።
" የዚው ሀገር ልጅ ነህ? "
" አዎ ሰፈሬም ከዚ ብዙ አይርቅም..."
" እዚ እኛ ጋር...? የማን ልጅ ነህ? "
" አባቴ ሀሰን ይባላል እናቴ ደሞ ራቢያ..."
" ሀጂ ሀሰን ነው? ከተማው መሀል ትልቅ ህንፃ ያለው?"
" አዎ ያውቁታል? "
" እንዴ ምን ሆነሀል እሱን የማያውቅ ማን አለ? ዘመዴን ነዋ የተዋወኩት..." እጁን ከፍ አርገው ሳሙት።
" እህትና ወንድሞችስ አሉህ? "
" ኧረ አያቴ ህዝብ ቆጠራ አደረግሽው እኮ..." አምሪያ እየሳቀች መጥታ ምግቡን ጠረንጴዛ ላይ አስቀመጠች።
" አንቺ ሞጥሟጣ ትልቅ ሰው ሲያወራ መሀል አትግቢ አላልኩሽም? "
" ኧረ አያቴ ትልቅ ሰው ይመስላላ? አንድ አመት ከምናምን ወር ብቻ እኮ ነው የሚበልጠኝ..." ጎንበስ ብላ እጇን አስታጠበቻት። ሰሚርን ልታስታጥበው ስትል ብድግ አለ።
" ኧረ በአላህ ቁጭ በል...ማንን ለማሳጣት ነው? " ሲነሳ ወድያው ቁመቱ ነበር ያስደነገጣት። አጠገቡ ስትቆም ነው ምን ያክል ረጅም እንደሆነ ያስተዋለችው። በትክክል ትከሻው ጋርም አትደርስም።
ከስንት ክርክር በኋላ ቁጭ ብሎ አስታጠበችው።

ምሳ ከበሉ በኋላ ቡና አፍልታላቸው ቤቱን ድምቅምቅ አደረገችው።
" እና ሳሊሞ ኢንትራንስ እንዴት ነበር ታድያ? " በእጇ የያዘችውን ቡና ጠረንጴዛው ላይ እያስቀመጠችለት...
" አሪፍ ነበር እስኪ ኢንሻአላህ ዱዓ አርጉልኝ እናንተም..."
" ይኸው አያቴ እያለች...አያቴ ዱዓ አርጊለት ፈተና ተፈትኖ ውጤት እየጠበቀ ነው...ካለፈ ወደ ዩንቨርስቲ ነው የሚገባው። "
" ውጤቱን ኸይር ያርግልህ ልጄ.. ያሰብከውን ያላህ ያሳካልህ ..."
" አሚን.. አሚን..." ከልቡ ነው አሚን ያላቸው።
" አብሽሪ ይሳካል..." ጥንካሬውን አምሪያ በደንብ ታውቀዋለች።
" እንደአፍሽ ያርግልኝ..."

የአስር ሰላት አዛን ሲል ሳሊም ወደመስጂድ ለመሄድ ተነሳ።
" በል አትጥፋ ደሞ እየመጣህ ዘይረን..." አምሪያ ከግቢ እስከሚወጣ ሸኝታው ስልክ ተለዋውጠው ተመለሰች።

*
ሙሉ ክረምቱን እዚ ስላሳለፈች እነረያንን ፣ ካየች 2 ወር አለፋት። ቴሌግራም ላይ የራሳቸውን ግሩፕ ከፍተው ማታ ማታ ስለውሏቸው በደንብ ያወሩ ነበር። ረያንና ፋሩቅ ሁሌም አንድ ላይ ነው የሚውሉት ማለት ይቻላል። ከሰብሪን ጋር ደሞ አልፎ አልፎ ይገናኙ ነበር።

ክረምቱ ተገባዶ ትምህርት ሊጀመር ሲል ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ። ረያን መጥታ እስከሚያያት ድረስ ሰአቱ ራሱ አልሄድ ብሎት ነበር።
" ወደሰፈር ስትደርሱ ንገሪኝ " ብሏት ስለነበር ሰፈር እንደገቡ ቴክስት አደረገችለት። ከክፍሉ እየሮጠ ወጣ።
" አባ ምን ተፈጠረ በሰላም ነው? " እናቱ ደንግጣ ተከተለችው።
" ይቅርታ እማ አስደነገጥኩሽ? እቃ ልገዛ እየወጣው ነው..." እስከሚወጣ በጣም ተቻኩሏል።
" ታድያ ሱቅ ለመሄድ ነው እንደዚ ሩጫ...በል ቀስ ብለህ ሂድ..." እናቱ ተመልሳ ከገባች በኋላ በሩጫ ወጣ። እነሱን ከርቀት እንዳያቸው ፍጥነቱን ቀንሶ ዱብ ዱብ ማለት ጀመረ።
" አቶ ቶፊቅ እንኳን ደና መጡ። " አጋጣሚ እንዳገኛቸው ሰው ሄዶ ሰላም አላቸው። አምሪን በአይኑ ሰላም አላት። በዚ ሰአት ከሁሉም በላይ እሷን ተጠምጥሞ ሰላም ቢላት ደስታው ነበር። ናፍቆቶ አይኑ ውስጥ ራሱ በደንብ ይነበባል።
" ወዴት ነው በዚ ሰአት " አለችው እየሳቀች። እሷ ጋር እንደመጣ የምታውቀው እሷ ብቻ ናት።
" ትንሽ ዱብ ዱብ ልበል ብዬ ነው..." ቀድሞ የተዘጋጀበት ይመስል ሰከንድም ሳይቆይ ነበር የመለሰላት። ፈገግ አለች...
ረያን እናቷ የያዙትን እቃ ተቀብሎ አብሯቸው ወደቤት ተመለሰ።

ዛሬ የሱ ቀን ይመስላል። ከ2 ወር በላይ አለመገናኘታቸውን አስመልክተው እነአምሪያ ቤት ሙሉ ቤተሰቡ የእራት ግብዣ ተጠርተዋል። ከዚ በፊት ቢለመን እንኳን የማይሄደው ልጅ ዛሬ ከነሱ ቀድሞ ጨርሶ በሩ ጋር ቆሞ ሲጠብቃቸው ነበር።

እስከምሽቱ 4 ሰአት ድረስ በጣም ደስ የሚል ጊዜ እነአምሪያ ቤት አሳለፉ። በተለይ ለረያን ልዩ ምሽት ነበር። ምሽቱን ሙሉ አይኑን ከሷ ላይ መንቀል አልቻለም ነበር። ቤት ውስጥ ያላት ስርዓት ደሞ በተመሳሳይ ሰአት እብደቷ ፤ ተጫዋችነቷ ፤ እነሱን ለማስተናገድ ጉድ ጉድ ስትል የተላበሰችው የሚስትነት ግረማ ፤ አንድ ላይ ተደማምረው አቅሉን ሊያስቱት ነው። ሌላው ቢቀር እንደዚ ውብ እንደሆነች እስካሁን አለማወቁ ገርሞታል። ፈገግታዋ ልብን እንደሚያበራ አለመረዳቱ አናዶታል። መኖሯ ድምቀቱ እንደሆነ የገባው አሁን ነው። በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለትዳር አሰበ። ልቡን ፍቅር ሲገባው በደንብ ተሰማው። ከዚ በፊት ከቤተሰቦቹ የመጣለትን የጋብቻ ሀሳብ ሳያቅማማ ለመቀበል ወሰነ። አምሪን የራሱ ለማድረግ...

ወደቤት ከሄዱ በኋላ ረያን ለአምሪያ ቴክስት ላከላት። መኝታ ክፍሏ አንድ እቃ እንዳስቀመጠላትና ሄዳ እንድታየው የተላከ ቴክስት ነበር። ወድያው ወደክፍሏ እየሮጠች ሄደች። በሩ ጀርባ አንድ እቃ ተቀምጧል። በምን ሰአት እንዳስቀመጠው ግራ ገባት። ስታስታውስ ቅድም መፀዳጃ ልሂድ ብሎ ሄዶ ነበር። የዛኔ ነው ሊሆን የሚችለው። ይሄን እቃ ይዞ ገብቶ ይዞት እንዳልወጣ ግን ማንም አላስተዋለውም ነበር። እሱም እንዳይታወቅበት እየጣረ ስለነበር።

ምን ሊሆን እንደሚችል ለማወቅ ጓጉታ ፌስታሉን ከፈተችው። ጫማ ነው። ከዚ በፊት ከትምህርት ቤት ሲመለሱ ሱቅ ውስጥ አይታው በጣም እንደወደደችው ነግራው ነበር። እሱን ጫማ ነው የገዛላት። ስጦታው ምንን አስመልክቶ እንደሆነ ባይገባትም ግን በጣም ተደስታለች።
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
ደወለችለት...
" ወደድሽው? " ገና ከማንሳቱ ነው የጠየቃት። እሱም እስከምትደውል እየጠበቃት ነበር።
" በጣም ወላሂ...አመሰግናለው..."
" ትምህርት የምንጀምር ቀን የማወራሽ ነገር ስላለ በጠዋት ውጪ..."
" ስለምን ጉዳይ? "
" እሱን የዛኔ ታውቂዋለሽ...ይኸውልሽ ብትረሺው የሞመቻሽ ቀን ነው የሚሆነው..."
" ወይ መርሳት? ምሽቱን እንቅልፍ እንደሚወስደኝ ራሱ እርግጠኛ አይደለሁም... ቆይ አሁን በዚ ሰአት ሆድ ቁርጠት ቢይዘኝ ምን ትጠቀማለህ? " እንዲነግራት መቅለስለስ ጀመረች።
" አብሽሪ እኔ አሳክምሻለው... እንዳትረሺው እጠብቅሻለው። " ሁለቱም ስለደከማቸው ብዙም አላወሩም። ተሰነባብተው ስልኩ ተዘጋ።

*

የ12ተኛ ክፍል የትምህርት አመት የመጀመሪያው ቀን...እንደተለመደው ረያን ከአምሪያ ቀድሞ ወጥቶ በር ጋር እየጠበቃት ነበር። አምሪያም አልቆየችም በፊት ከሚገናኙበት ሰአት ነው ቀድማ የወጣችው። ባለፈው ስጦታ የሰጣትን ጫማ አርጋዋለች።
" አምሮብሻል..." አርጋው ስለመጣች ደስ ብሎታል።
" አመሰግናለው... እ ደሞ ምንድን ነው አናግርሻለው ያልከኝ? " ሌላ ወሬም እንዲያወራ እድል አልሰጠችውም። ያን ሁላ ቀን ራሱ እንዴት እንደጠበቀች እሷ ናት የምታውቀው። ስለምን ሊሆን እንደሚችል ብዙ ነገር ስታስብ ነበር የቆየችው።
" አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ፈልጌ ነበር..."
" እኮ ጠይቀኛ...ይባስ ልቧን አንጠለጠለው
" በደንብ አስበሽ መልሺልኝ... "
" ኧረ በአላህ ረያን...!" ሳታስበው ጮኸችበት።
" እ...እንትን..." መንተባተብ ጀመረ። ማታ ያሁላ ቃል ሲለማመሳድ እንዳላደረ አሁን ጭራሽ ምላሱ ከዳው። አምሪያ አፍጣ ታየዋለች።

" እንዴ ሰዎች..." አንድ ሰው የረያንን ትከሻ ሲመታው ሲመታው ከሰመጠበት ሀሳብ ወድያው ወጣ። ዞር ብሎ አየው። ሚኪያስ ነበር...
" በዚ ጠዋት ደሞ እዚ ሰፈር ምን ትሰራለህ? "
" ትናንት እናንተ ሰፈር ያለችው አክስቴ ቤት ነበር ያደርኩት...ገና ወደቤት ሄጄ ቦርሳ ምናምን ማምጣት ስላለብኝ ነው በጠዋት የወጣውት..."
" ካልጠፋ ቀን ዛሬ? " ረያን ብቻውን ያጉረመርማል...
" ምን አልከኝ? "
" እዚው ነው...እንሂዳ በቃ..." አምሪያም ረያንም በጣም ተናደዋል። ትምህርት ቤት ደርሰው እስከሚለያዩ ድረስ ሚኪ ብቻውን ሲለፈልፍ ቆየ። ሁለቱም አጭር መልስ ከመመለስ ውጪ ምንም አላሉትም ነበር።

ክፍል እንደገቡ አንዲት ልጅ ብቻዋን መስኮቱ ጋር ቆማ ወደውጪ ትመለከታለች። ረያን ቦርሳውን አስቀምጦ ኳስ ለመጫወት ወጣ። አምሪያ ሰብሪን እስከምትመጣ ድረስ እዛው ቁጭ አለች።

መስኮቱ ጋር የቆመችውን ልጅ በደንብ ለማየት ሞከረች። አዲስ ተማሪ ናት። ወድያው ተነስታ ወደሷ ጋር ሄደች።
" አሰላም አለይኩም..." አጠገቧ ሄዳ ቆመች
" ወአለይኩም አሰላም "
" አዲስ ተማሪ ነሽ መሰለኝ..."
" አዎ..."
" እንተዋወቃ...አምሪያ እባላለው..." እጇን ለሰላምታ ዘረጋችላት።
" ሂዳያ..." አቀፋ ሰላም አለቻት። ስለመጣች ደስ ብሏታል። አዲስ ተማሪ ሆኖ ብቻ እንደመዋል የሚያስጠላ ነገር የለም።

ሂዳያ ጠይም...ረዘም ያለች ልጅ ናት። ስትስቅ የሚሰረጉዱት ጉንጮቿ አይደለም ወንድን ሴትንም ያፈዛሉ። አጠቃላይ ደስ የምትል ልጅ ትመስላለች።
" እና ለምን ትምህርት ቤቱን ዞር ዞር ብለን አናይም..." ብላት ተያይዘው ወጡ።

አምሪያ ሰብሪን ከግቢ ስትመጣ ስላየቻት ሄደው ተቀበሏት። ለረጅም ሰአት ተቃቅፈው ሰላም ተባባሉ። አምሪያ ከክፍለ ሀገር ከመጣችም በኋላ በስልክ ብቻ ነበር የተገናኙት። ሰብሪንን ከሂዳያ ጋር አስተዋውቃት ግቢውን ሲያዩ ቆይተው ሲደወል ወደክፍል ገቡ።

ሂዳያ ከአምሪያና ከሰብሪን ጋር ተደርባ እንድትቀመጥ አደረጉ። በዚ መልኩ የነሱ አዲስ የግሩፓቸው አባል ሆነች።

የመጨረሻው ክፍለጊዜ ላይ ረያን አንድ ወረቀት ጠቅልሎ ለአምሪያ አቀበላት።
" የጠዋቱን ጉዳይ አሁን ብንጨርሰውስ? "
" በምን ሰአት? " መልሳ ፅፋ አቀበለችው
" ወደቤት ሰአት ላይ... ሁሉም እስከሚሄዱ ድረስ እንዳትወጪ..."
" እንዴ እነሰብሪንን ምን ብለናቸው እንቀመጣለን? ይጠብቁናል እኮ ..."
" ችግር የለውም ትንሽ ቆይተን እንመጣለን እንላቸዋለን...ዞሮ ዞሮ ቆይቶም ማወቃቸው አይቀርም..." ተስማማች። እሷም ቢሆን ሊያዋራት የፈለገው ስለምን ጉዳይ እንደሆነ ለማወቅ በጣም ጓጉታለች።

ከተደወለ በኋላ እነፋሩቅን ውጪ ጠብቁን ብለዋቸው ሁሉም እስከሚወጡ ድረስ ክፍል ቀሩ።
ፋሩቅና ሰብሪን የሄዱ ከመሰሉ በኋላ ትንሽ ቆይተው ቀስ ብለው ተመልሰው መጡ። በሩ ግድግዳ ላይ ጆሮአቸውን አስደግፈው የሚያወሩትን ለመስማት ይጥራሉ። ሂዳያ የነሱ ጉዳይ እንደሆነ ስለገባት ተሰናብታቸው ሄደች።

ረያን ንግግሩን ጀመረ።
" ስለኔና ስላንቺ ጋብቻ ምን ታስቢያለሽ" ?
" ማለት? " ጥያቄው ግራ አጋብቷታል። ቤተሰቦቻቸው ያሉትን ጋብቻ በዚ ሰአት አላሰበችውም ነበር።
" አያቶቻችን የገቡትን ቃል... እኔን ማግባት ትፈልጊያለሽ? " ጥያቄውን አፈረጠው። ምን እንደሚሰማው እንኳን ቀድሞ ሳይነግራት ቀጥታ ስለጋብቻው ነበር የጠየቃት።

አምሪያ በጣም ደነገጠች። የእውነትም ይሄን ጥያቄ አልጠበቀችም ነበር። ወድያው ክፍለሀገር እያለች በአጋጣሚ ከሳሊም ኪስ ወድቆ ስላነበበችው ወረቀት አሰበች። በዚ ሰአት ስለሳሊም ለምን እንዳሰበች ለራሷ ራሱ ግራ ገብቷታል።
" እ አምሪ? አትወጂኝም? " አምሪያ ከገባችበት ሀሳብ ወጣች። ቀና ብላ ተመለከተችው...

#ክፍል_ሰባት...⓻...ይቀጥላል
✿❯────「✿」────❮✿

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━━━─╝



#ክፍል_ሰባት( ⓻ )
✿❯────「✿」────❮✿

ክፍለ ሀገር እያለች ሳሊም ቤት የመጣ ቀን በአጋጣሚ ከኪሱ ወድቆ ያገኘችውን ወረቀት አስታወሰች። ለሷ የተፃፈ ደብዳቤ ነበር። የፍቅር ደብዳቤ... ሳሊም ያፈቅረኛል ብላ አንድም ቀን አስባ አታውቅም ነበር። የዛኔ ስታየው በጣም ነበር የደነገጠችው ፤ ግን 2 ወር ቆይታ እዚ እስከምትመጣ ድረስ አንድም ቀን ስለሱ ጉዳይ ስላላነሳባት ሳያውቀው ወድቆበት እንጂ ሆን ብሎ ትቶት እንዳልሄደ አረጋግጣ እሷም ባላየ አለፈችው።

ረያን መልሷን ጥበቃ አይን አይኗን ይመለከታል። አምሪ ዝም ብላ እንዳቀረቀረች ቆየች።
" በቃ ተዪው ይሄን ያህል እንድትጨነቂ አልፈልግም...." እንደምትወደው አስቦ ነበር። ለጥያቄው መልስ ለመስጠት ይሄን ያህል ስትቆይ ግን ስሜቷን እንዳልተረዳ አሰበ። ቦርሳውን ከወንበሩ ላይ አንስቶ ወደበሩ መሄድ ጀመረ።

አምሪ ለምን ዝም እንዳለች ለራሷ ግራ ገብቷታል። እንደምትወደው እያወቀች ለምን ምላሷ ተሳሰረ? በዚ ሰአት ረያንን መልቀቅ ልክ እንዳልሆነ ተሰማት። እየሮጠች ሄዳ ፊትለፊቱ ቆመች። ረያን አይኖቹ መቅላት ጀምረው ነበር። አንገቱን ወደመሬት አድርጎ ቆመ።
" ትወደኛለህ? " አለችው። ቀድማ የሱን ስሜት በደንብ ማወቅ ፈልጋለች። ቀና ብሎ አያት። ፊቷ ላይ ያለው ፈገግታ መልሷን ቀድሞ ነገረው። ደስታዋ ወድያው ተጋባበት።
" የመጀመሪያ ነሽ እኮ...የፍቅርን ትርጉም ያየውብሽ! አዎ በጣም ወድጄሻለሁ...በጣም! የኔ እንድትሆኚ እፈልጋለሁ! "
አምሪ ፍቅሩን ከአንደበቱ ስትሰማው ልቧ በደስታ ሲመታ ተሰማት። እቀፊው...እቀፊው አሰኛት።
ቀና ብላ አይን አይኑን ማየት ጀመረች።
" የኔንስ ልንገርህ? " አለችው እየተንተባተበች።
" አይ አትንገሪኝ...መልሱን አይንሽ ውስጥ በደንብ አይቼዋለሁ! " ከንፈሯ ቃል ለማውጣት ሲንቀጠቀጥ እያያት ነበር። በመጨረሻም እንደምንም ታግላ " እወድሀለው! " የሚለውን ቃል አወጣችው።

ወድያው ፋሩቅና ሰብሪን እየሮጡ ወደክፍሉ ገቡ። አጠገባቸው ቆመው በጭብጨባ ይቀውጡት ጀመር። አምሪያና ረያን ያወሩትን እንዳለ እንደሰሙ ስላወቁ በአፍረት አይናቸውን ሰበር አደረጉት።
" በጣም ደስ ብሎኛል ወላሂ..." ሰብሪና አምሪን አቅፋ ደስታዋን ገለፀችላት።
" እኛን አስወጥታችሁ እዚ ፍቅራችሁን ትኮመኩማላችኋ... እንግዲ አልተሳካም...ከኛ የሚያመልጥ አንድም ነገር የለም። " ፋሩቅ ሙድ እየያዘ ያቅፈዋል።
" ይሄ ሁላ ጊዜ ፍቅረኛ አልይዝም ብለህ እንዳልከረምክ በስተመጨረሻም ወደዛው ልትሄድ ነዋ..."
" No, አምሪ እኮ ፍቅረኛዬ አይደለችም..ሚስቴ ናት ያውም የልጅነት..." ፈገግ ብሎ አምሪን ተመለከታት።
" አይ serious ፍቅረኛ መያዝ በጣም እንደምትጠላ አውቃለው እና እስከምትጋቡ ድረስ እንዴት ልትቆዩ ነው? ወይስ እሱንም እኛ ሳንሰማ በሹክሹክታ አውርታችሁ ጨርሳችሁታል? "
" ቀላል እኮ ነው...ኒካህ እናስራለን። " አይደል? አላት ወደአምሪያ ዞሮ... ስለዚ ጉዳይ በደንብ ሳያወሩ ነበር እነፋሩቅ የመጡባቸው።
" አዎ የኔም ሀሳብ እንደዛ ነው! "
" ግን ቤት የሚስማሙ ይመስላችኋል? ማለት መጀመሪያ ትምህርት ጨርሱ ቢሏችሁስ? " አለች ሰብሪን ደስታቸው በምንም ሁኔታ እንዲከፍሽ ስላልፈለገች ሀሳብ ገብቷታል።
" እናቴ በኔ እድሜ ነው እኔን የወለደችኝ...እንደውም በደስታ ነው የምትቀበለኝ..." አለች አምሪ ከአሁኑ እርግጠኛ የሆነች ትመስላለች።
" ሀራሙን ትተን ሀላሉን ስለመረጥን ነው እንቢ የሚሉት? እንደውም ሊኮሩብን ነው የሚገበው...ብቻ እስኪ ኢንሻአላህ እኔንም እንቢ የሚሉኝ አይመስለኝም... " አለ ረያንም።

በዚ ሁኔታ ኒካህ ለማሰር ተስማሙ። ወደፊት ሁሉንም ነገር አስተካክለው በጋብቻ አብረው መኖር እስከሚጀምሩ ድረስ በኒካህ መቆየት ነው ትልቁ አማራጭ! በዚ ሳምንት ሁለቱም ቤተሰቦቻቸውን ለማናገርና ኒካህ የሚያስሩበትን ቀን ለመቁረጥ ተስማሙ።

የመጀመሪያውን የቤት ስራ አምሪያ ጀመረችው። እናቷም አባቷም ቤት ስለነበሩ " የማናግራችሁ ነገር አለ..." ብላ ሳሎን ተሰብስበዋል። ግን ምን ብላ እንደምትጀምር ግራ ገብቷት ቁጭ ብሎ አይን አይናቸውን ታያለች።
" አምሪዬ በሰላም ነው? ደና አይደለሽም እንዴ? " እናቷ መጨነቅ ጀመረች።
" አትናገሪም እንዴ ምን አይን አይናችንን ታያለሽ? " አባትም ግራ ተጋብቷል።

" እ..ኒካህ ማሰር እፈልጋለሁ..." እንደምንም እየተንተባተበች ነገረቻቸው።
" ከማን ጋር? " እናቷ ያለችውን ማመን አልቻሉም።
" ከረያን ጋር... ትጋባላችሁ ያላችሁን እራሳችሁ አልነበራችሁም? " ንግግሯን ሳትጨርስ እናቷ በእልልታ ቤቱን ቀወጠችው።
" ኧረ ተረጋጊ...ጉሮሮሽ ተዘግቶ የሰርጉ ቀን የምትቀውጪበትን ድምፅ እንዳታጪ " አባቷም እንደተስማማ በተዘዋዋሪም ቢሆን አሳውቋል።
" ኡፈይ አልሀምዱሊላህ! " አለች በልቧ ረያን ሀላሏ የሚሆንበትን ቀን በሀሳቧ እየሳለች።

ወድያው ወደክፍሏ ገብታ ለረያን ደወለችለት።
" አሰላም አለይኩም ሚስትየው..." እንደደወለች ባልነቱን አረጋገጠላት።
" ወአለይኩም አሰላም...ደና ነህ? "
" አልሀምዱሊላህ አለውልሽ ...ድምፅሽ ምንድን ነው? የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ? በጣም ደስ ያለሽ ትመስያለሽ..."
" ስለኒካሁ እኮ ነገርኳቸው..."
" እና? " አላት ውሳኔውን ለመስማት እየጓጓ
" እማ ከአሁኑ እልልታዋን ጀምራልሀለች! "
" ወላሂ? "
" አዎ አባ...አንተስ ነገርካቸው? "
" የኔ እኮ ምንም ጥያቄ የለውም..ነገ ባገባሽ ራሱ ደስ ይላቸዋል። "
" መች ነገርካቸው? " አለች ፍጥነቱ ገርሟታል።
" ትናንት እንደገባሁ ነው ማታ ላይ የነገርኳቸው። ሽማግሌ ሁላ መርጠው ጨርሰዋል። አንቺን ነው እየጠበኩሽ የነበረው። እና የሚመቻቸውን ቀን ትነግሪኝና ሽማግሌ እልካለው የተከበሩ። "
" ከነገ ወድያ እሁድ ጠዋት ብትልክስ? "
" እሺ እነግራቸዋለሁ..."

እንዳለው እሁድ ጠዋት አምሪያ ጋር ሽማግሌዎችን ላከ። ህጉን ለመጠበቅ ነው እንጂ እነሱ ቀድመው አውርተውበት ስለነበር ጉዳዩን ለመጨረስ ብዙ ጊዜ አልፈጁም።
ኒካሁ ላይ ከቤተሰቦቻቸውና ከነሱ ቅርብ ጓደኞች ውጪ ማንም ስለማይኖርና በጣም አነስ ያለ ምሳ ስለሆነ የሚያዘጋጁት ከሳምንት በኋላ ለማድረግ ተስማሙ።

*

የኒካሁ ዋዜማ ቅዳሜ ለት አምሪያ ከሰብሪንና ሂዳያ ጋር ሆነው ልብስ ለመከራየት ወጡ። የሙሽራዋንም የሚዜዎቹንም ልብስ ካገኙ በኋላ ፀጉራቸውን ሲሰሩ ፣ በሜሽና በሂና እራሳቸውን ሲያደምቁ ዋሉ። ነገ ላለመቻኮል ነበር ዛሬ መጨራረስ የፈለጉት።
ለነገ ሜካፕ የሚሰሯቸውን እና ዲኮር የሚሰሩላቸውንና ሰዎች አናግረው ወደ 10 ሰአት አከባቢ ቤት ተመለሱ። ድግሱ እነአምሪያ ቤት ስለሆነ ቤት ያለው ድባብ ከአሁኑ ደስ ይላል። የሰርግ ነሺዳ ከፍተው ቤቱን አድምቀውታል። ሂዳያና ሰብሪንም እነአምሪያ ቤት ስላደሩ የሚሰራራውን ስራ ሲያግዙ ቆዩ። ከምሽቱ 6 ሰአት ሲሆን ነበር ሁሉም ወደ እንቅልፍ የሄዱት።
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
.
ትናንት ደክሟቸው ስለዋሉ 12 ሰአት ሲሆን ነበር ከእንቅልፋቸው የተነሱት። ወድያው ሱብሂ ሰላትን ሰግደው ቁርስ እንደነገሩ ቀማመሱ። 1 ሰአት ላይ ሜክፕ የምትሰራዋ ልጅ መጣች። ብዙ ባልተጋነነ ቀለል ባለ ሁኔታ ሙሽራዋንም ሚዜዎቹንም አስዋበቻቸው። እነሱ እየተሰሩ መሀል ላይ ዲኮር የሚሰሩት ሰዎች መጥተው ስለነበር ቤቱን ድምቅምድ ማድረግ ጀምረዋል። 4 ሰአት ሲል ሁሉንም ነገር ጨራርሱ።

በኒካህ ቀን ሙሽራዋን ይዟት ወደቤት ስለማይገባ እነረያን ቤት ድግስ አልነበረም። እሱም ከሚዜዎቹ ፋሩቅና ሚኪ ጋር ሲዘገጃጅ ቆየ። 6 ሰአት ሲሆን ነው ወደንግስቱ ጋር ለመሄድ ያሰቡት። ረያን ሰአቱ አልገፋ ብሎታል። በተደጋጋሚ የእጅ ሰአቱን ያያል።
" ኧረ ሙሽራው በዚ ሁኔታህ አሁን ካልሄድን ብለህ ቁርስ አብልተኸን እንዳትመልሰን..."
" የኔ ሰአት ግን ልክ አይደለም መሰለኝ። እስኪ ያንተን እይልኝ..."
" 4፡ 30 ነው...1 ሰአት ከ30 ደቂቃ ብቻ ነው የቀረህ..."
" ብቻ ነው ያልከው? አንተማስ ምን አለብህ? " ረዩ ናፍቆቱን አልቻለውም። ሄዶ ከጎኗ እስከሚቆም መረጋጋት አቃተው። ለነገሩ እንዴት አይቸኩል። ሚስቱ የሚያረግበት የሚነግስበት ቀን አይደል።
" አምሮብኛል አይደል? " ዞሮ እራሱን በመስታወት እያየ ያረጋግጣል።
" ዛሬ ሳይህ አይደል እንዴ እስካሁን ነጫጭባ ሆነህ እንደኖርክ የገባኝ..." ሚኪ እንዳማረበት በ negative መንገድም ቢሆን ገለፀለት።
" አሁን ቆይ እናንተ ናችሁ ሚዜዎቼ? ይኸው እዛ ሄደን ታዋርዱኝና..."
" አያስቡ ንጉስ ሆይ ያለርሶ ፍቃድ ምንም ነገር አናደርግም! " ፋሩቅ መጥቶ ትከሻውን ነካ ነካ ያረገዋል።
" እሺ አሁን ስንት ሰአት ሆነ በአላህ? " የራሱ ሰአት ስላናደደው ማየት አልፈለገም።
" 4፡40 " አሉት ሁለቱም አንድ ላይ እየሳቁ።

*

የነአምሪያ ቤት ሆይሆይታው መቅለጥ ጀምሯል። መኝታ ክፍል እሷና ሚዜዋቿ ፣ የሙሽሪትና የሙሽራው እናት እና ሌሎች የተወሰኑ ሴቶች ተቀምጠዋል። ወንዶቹ ሳሎን ቁጭ ብለው ሙሽሮቹን እየጠበቁ ነው።

ሴቶቹ ቤት ውስጥ ነሺዳ እያወጡ አምሪያን ማሞገስ ጀምሩ። ሰብሪን ነሺዳ ስታወጣ ሌሎች ይቀበላሉ
" እዚም የወሬ...የወሬ
እዛም የወሬ...የወሬ
እደር ይሉሀል አትደር
አምሪዬን ይዘህ ሽር በል " ሂዳያ ቀጠለች

" እዚም የወሬ...የወሬ
እዛም የወሬ...የወሬ
ተመርቆ አድጎ በእናቱ
አምሪዬን ሰጠው ፀሎቱ " እናቶች በእልልታና በጭብጨባ አድምቀውታል።

እነረየን ወደግቢ እየመጡ እንደሆነ ሲያዩ የመጨረሻ ነሺዳቸው ማለት ጀመሩ።

" አምሯል ዲናችን ኧረ አምሯል ዲናችን
ባውሮፓው ቀርቶ ሆኗል በሱናችን
አምሯል ዲናችን...የኛማ አምሪዬ
አምሯል ዲናችን...ኖራለች በሱና
አምሯል ዲናችን...ይኸዩ ረዩ መጣ
አምሯል ዲናችን...ሊወስዳት ባደራ "

ሰብሪን ጎንበስ ብላ የሙሽሪትን ልብስ በደንብ አስተካከለችው። ፊቷ ላይም ምንም የተበላሸ ነገር እንደሌለ አረጋገጠችላት። ንጉሷ ሲመጣ እንድታስበረግገው።

ረያን በወንዶቹ ታጅቦ ወደሳሎን ክፍል እየመጣ ነው። አሁን ደሞ የወንዶቹ ተራ ነው ፋሩቅ እያለ ሌሎቹ ይቀበላሉ።
" መጣ ሙሽራው ተቀበሉት በእልልታ
ደርሷል ሙሽራው ስጡት የክብር ቦታ
ደርሷል ሙሽራው ከሚዜዎቹ ጋር
እዩት ንጉሱን እንደፀሀይ ሲያበራ።

ወንዶቹ ሳሎን ቁጭ ብለው ሙሽራውን እያሞገሱ ቤቱን እያደመቁት ነው። ፊርማውን አስፈርሟቸው ሁሉንም ጉዳይ ከጨረሱ በኋላ ወንዶቹ እዛው ሳሎን እንደሆኑ ሴቶቹም መኝታ ክፍላቸው ሆነው ምሳቸውን በሉ። ረያን ግን ምሳ ባይበላ ራሱ ደስ ባለው ነበር።

በዛሬ ቀን ሙሽራው ይዟት ወደቤቱ ስለማይገባ ምሳ በልተው ትንሽ ከቆዩ በኋላ ሙሽራዋና ሙሽሪት ከሚዜዎቻቸው ጋር ወጥተው ተዘናንተው እንዲመለሱ ወስነው ነበር። ቦታውም ቀድመው አዘጋጅተው ጨርሰዋል።

ሰአቱ እንደምንም እየተንጓተተም ቢሆን የሚወጡበት ሰአት ደረሰ። ሙሽራው ከሚዜዎቹ ጋር ሆኖ ንግስቱን ለመውሰድ ወደ ክፍል ገባ። ፊቷን ተሸፍና ነበር ቁጭ ያለችው። አጠገቧ ሲደርስ ልቡ መምታት ጀመረ። አምሪም እስክታየው ጓጉታለች። ሄዶ በርከክ ካለ በኋላ የተሸነችበትን ገለጠው። ሲያያት ከአይኑ እንባዎች ሊወርዱ አጎበጎቡ። በጣም አምሮባታል። ዙሪያዋን የከበበው ቀዩ ቀሚሷ ከፊቷ ጋር በደንብ የሚሄድ ነበር። በእጁ የያዘውን አበባ አስረከባት። አይኑን አይኗ ላይ ተክሎ በስስት ተመለከታት። ታሳሳለች...ረዩ እንደዚ ደስተኛ የሆነበትን ቀን አያስታውሰውም። ቀና ብሎ ግንባሯን ሳማት። ከንፈሩ ግንባሯን ሲስማት አምሪ ነዘራት። ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውነቱ ከሰውነቷ ጋር ተነካካ። ስሜቱን ከሁለቱ ውጪ ማንም ሊረዳው አይችልም!

ጊዜ መፍጀት አልፈለገም። ክንዱን ከክንዷ ጋር አጠላልፎ ቶሎ ይዟት ወጣ። ለነሱ ተብሎ በተዘጋጀው ሶስት መኪና ወደሚጠብቃቸው ቦታ አቀኑ። ቦታው ላይ እንደደረሱ እየተሯሯጡ ወደውስጥ ገቡ። ከካሜራ ማኑና ከነሱ ውጪ ሌላ ማንም ግቢ ውስጥ የለም። ፎቶ ተነስተው ከጨረሱ በኋላ እሱም ተሰናብቷቸው ሄደ።
እንደልጅነታቸው ጊቢው ውስጥ ሲቦርቁ ሲጨዋወቱ ለትንሽ ደቂቃ ቆዩ።

ረያን አምሪን ሚዜዎቻቸው ወደሌሉበት ቦታ ይዟት ሄደ። ግቢው ውስጥ ከተሰራች ትንሽዬ ጎጆ ቤት ውስጥ አስገባት። ቤቱ በሱ አዛዥነት በአበባዎችና በመብራቶች ተውቧል። አምሪ ስለዚ ቦታ ምንም ነገር አታውቅም ነበር።

ለትንሽ ደቂቃ ዝም ብለው ተያዩ።
" ልታስቀምጠኝ ነው እንዴ ይዘኸኝ የመጣኸው? " ከገቡ ጊዜ ጀምሮ ምንም አላላትም።
" ውበትሽን ለመግለፅ እኮ ቃላት እየፈለኩ ነው..."
" እና እስከስንት ሰአት ልጠብቅህ..."
" ለምን በተግባር አላሳይሽም? "
" እንዴት ነው በተግባር የምታሳየኝ? " ረያን ወደሷ ጠጋ አለ። ከንፈሯንና አይኗን እያፈራረቀ ይመለከታል። አምሪ ምን ሊያደርግ እንደሆነ ገብቷታል። የልብ ምቷ ጨመረ። ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ ሲል ይሰማታል። አሁን ሚስቱ ናት... ሀላሉ! ምንም ቢያደርግ መብቱ ነው! ረያን ቀስ እያለ ወደከንፈሯ መጠጋት ጀመረ...

#ክፍል_ስምንት ( ⓼ )... ይቀጥላል
✿❯────「✿」────❮✿

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━━━─╝

#ክፍል_ስምንት ( ⓼ )
✿❯────「✿」────❮✿

ረያን ቀስ እያለ ወደከንፈሯ መጠጋት ጀመረ። እሱ በቀረባት ቁጥር የአምሪም የልብ ምት አብሮ እየጨመረ ይሄዳል። ታፋዋ ላይ ተቆላልፈው የተቀመጡትን እጆቿን በእጁ ጭምቅ አድጎ ያዞ ከንፈሩ ከከንፈሯ ጋር አገጣጠመው። የዛኔ ሊወጣ ደርሶ የነበረው ልቧ በአንዴ ቀለጠ። አይኗን ጨፍና እሷም በደንብ ሳመችው።

" ሩዩ...አምሪ...ኧረ ሙሽሮቹ የት ሄደው ነው? " እነፋሩቅ ስማቸውን ጮክ ብለው ይጠሩአቸዋል። የሁለቱም ስልክ ሚዜዎቻቸው ጋር ስለነበር ደውለው ማግኘት አልቻሉም። ድምፃቸውን ሲሰሙ ረዩና አምሪ ከገቡበት ሙድ ወጡ። ቀና ብለው ተያይተው ሳቁ...የአፍረት እና የደስታ ሳቅ....

እነፋሩቅ እነሱ ካሉበት ቦታ ትንሽ እስከሚርቁ ድረስ ጠብቀው ከጎጇቸው ወጡ። ሰብሪን በአጋጣሚ ወደኋላ ስትዞር ነበር ያየቻቸው። ወድያው እየሮጡ እነሱ ጋር ተመለሱ።
" እናንተ የት ሆናችሁ ነው እንደዚ የምታስጨንቁን? "
" እናንተን እንጠይቃችሁ እንጂ...ታግተን እንደዛ ስንሰቃይ የት ከርማችሁ ነው? አታፍሩም እኮ እራሳችሁንም እንደሚዜ ነው የምታዩት... " ረዩ ወደአምሪ ጠጋ ብሎ " ደና ነሽ አይደል? ብዙ አልጎዱሽም አይደል? " እያለ ፊቷን ይነካካታል።
" አዎ አንተ በጣም ጎድተውህ አይደል እንዴ? በምን እንደመቱህ ባላውቅም ቀለሙ ግን ከንፈርህ ላይ ራሱ እንዳለ ነው..." እነፋሩቅ ተያይተው ሳቁ። የት እንደጠፉ ገብቷቸዋል። ረዩ ወድያው በእጁ ከንፈሩን ጠራረገ።
" ባይለቋቹ ይሻል ነበር እኛም እንገላገላለን..." ሰብሪን ቀደም ብላ ስትሄድ ሌሎቹም ተከተሏት። ሰአቱ እየመሸ ስለነበር እቃቸውን አስተካክለው ወደቤት ወደሚወስዳቸው መኪና ሄዱ። ሹፌሩ ሁሉንም በየሰፈሩ እየሄደ ይጥላቸዋል። መጨረሻ ላይ አምሪና ረያን ብቻ ነበር የቀሩት። በዚ ሰአት ቻው መባባል ለነሱ በጣም ከባድ ነው። እዛው መኪና ውስጥ እንደሆኑ ለረጅም ሰአት ተቃቅፈው ቆዩ። መለያየቱ ግን ግድ ነውና ለማልቀስ ትንሽ በቀረው ፊታቸው ሁለቱም ወደቤታቸው ገቡ።

በጣም ደስ በሚል ሁኔታ የኒካሁ ቀን አለፈ። ለሁሉም በተለይ ደሞ ለረያንና ለአምሪያ ልዩ ቀናቸው ነበር።

*

አምሪ በቅርቡ በሚካሄደው የስዕል ውድድር ላይ ትምህርት ቤቷን ወክላ ለመወዳደር ዝግጅት ላይ ናት። በትምህርቱ ቤቱ የተደረገውን ውድድር ስላሸነፈች ነው በክፍለ ከተማ ደረጃ ለሚደረገው ትልቅ ውድድር ላይ የተመረጠችው። ላለፈው ውድድር የትምህርት ቤቷን ግቢ ነበር የሳለችው ለዚኛው ግን በምን ስዕል እንደምትወዳደር እስካሁን አልወሰነችም። ከባሏና ከጓደኞቿ ጋር ብዙ ሀሳቦችን ሲያነሱና ሲጥሉ ቆይተው በአንድ ሀሳብ ተስማሙ።

የውድድሩ ቀንም ደረሰ። አምሪ እንደዚ አይነት ትልቅ ውድድር ላይ ስትሳተፍ የመጀመሪያ ጊዜዋ ነው። አዳራሽ ውስጥ በሞሉት ሰዎች ፊትለፊት መድረክ ላይ ሆነው ነው የሚስሉት። አምሪ ከአሁኑ ፈርታለች። ከየትምህርት ቤቱ የተወጣጡት ሁሉም ተማሪዎች በየተራ ስም እየተጠራ ወደመድረኩ መጋበዝ ጀመሩ። የአምሪ ተራ ደርሶ ሄዳ ቦታዋን ያዘች። ሰአት ተይዞ ውድድሩ ተጀመረ። አምሪያ ብሩሿን አነሳች። የሌሎቹን አንዴም ቀና ብላ ሳትይ ነበር ስዕሏን ስላ የጨረሰችው።

ውድድሩ ተጠናቆ አሸናፊውን ለማሳወቅ መድረክ መሪው ወደመድረኩ ወጣ። አምሪ አጠገቧ የነበረው ልጅ ሲስል የነበረውን ስዕል አይታለችና እሱ ሊበልጣት እንደሚችል እየደጋገመች ለረያን ትነግረዋለች።
" አብሽሪ ተሸነፍሽ ማለት እኮ አትችዪም ማለት አይደለም እማ...በቃ ካልሆነ አልሆነም ነው...ገና ብዙ ውድድሮች ከፊትሽ ይጠብቁሻል። ለነዛ በደንብ መዘጋጀት ነው። እንደዚማ አትጨናነቂ..." አንገቷን ይዞ ትከሻው ላይ አስተኛት።

" የውድድሩን አሸናፊ ለመወሰን ዳኞች በጣም ተቸግረው እንደነበር ሰምቻለሁ። መድረክ መሪው ንግግር ጀመረ። " አሸናፊውን አሁን አሳውቃለው..." የአምሪያ የልብ ምት እየጨመረ መጣ...
ከመድረኩ መሪ " አምሪያ..." የሚል ቃል ሲወጣ ማመን አልቻለችም። ረያን ነው ወደመድረክ እንድትወጣ ሲየስነሳት የባነነችው። የሳለችውን ስዕል ለታዳሚው አሳዩ። ምሽት ላይ የሚታይ ውብ ሰማይ...በሚያማምሩ ኮከቦች የተከበበች አንዲት ጨረቃ ሸራው ላይ ይታያል። ስዕሉ የእውነት እስከሚመስል ድረስ ውበቱን ለመግለፅ አዳጋች ነው። አምሪያ ለትምህርት ቤቱ ዋንጫና ለግል የሚሰጠውን 5000 ብር ሽልማት በክብር ተቀበለች።

" ኦ...ኦ ዛሬማ ግብዣ አለ..." አለች ሰብሪን ከውድድሩ ቦታ ወደትምህርት ቤት እየተመለሱ ነው። ሁሉም አምሪያን ያሟጋግሷታል። የብሯ ነገር...
" ዛሬማ ከኔ ጋር ነሻ..." ሰብሪን ሄዳ ስትጠመጠምባት ሂዳያ አስለቀቀቻት
" እስኪ አታስጨንቂያት ልጅቷን...አምሪዬ ዝም በያቸው እነሱን..." እሷም ለራሷ ማመቻቸት ጀመረች።
" እኔ እኮ የናንተ መሽቃበጥ ነው የሚገርመኝ...ሲጀመር እኔና እሷ ተነጋግረን ጨርሰናል..." ፋሩቅ በተራው ወደሷ ጠጋ አለ።
" በምን ሰአት ነው የተነጋገራችሁት? " ፋሩቅ ገፍትሮ ከአምሪያ አጠገብ ካስኬደው በኋላ አጠገቧ ቆመ።
" አታስቡ ግብዣውን ተስማምቻለሁ። ይሄን ያህል መልፋት አይጠበቅባችሁም..." ከክላስ መልስ ልታጋብዛቸው ተስማሙ።
. ወደቤት ሰአት ላይ ገና ከክፍል እንደወጡ ነው የሚበሉበትን ቦታና ምግብ መከራከር የጀመሩት። ልክ ከግቢው ሲወጡ አምሪያ ሳሊምን ቆማ አየችው። " አንዴ መጣው..." ብላቸው ወደሳሊም ጋር ሄደች።

" አሰላም አለይኩም...ሳሊም ነህ ወይስ አይኔ ነው? " እንዴት እንደመጣ ግራ ገብቷታል።
" ወአለይኩም አሰላም...አይንሽ አይደለም እኔው ነኝ። " ሲያወራት በትልቅ ፈገግታ ነው።
" ደና ነህ? ምንድን ነው ደሞ እዚ ምን ትሰራለህ? "
" ሰርፕራይዝ ላርግሽ ብዬ ነው ያልነገርኩሽ። ዩንቨርስቲ እኮ አዲስ አበባ ደርሶኝ እዚ ነው ያለሁት አሁን። "
" በአላህ? በጣም ደስ ይላል...Congra ብያለው "
" በይ አያትሽንም አመስግኚልኝ...የሳቸውም ዱዓ አለበት። "
" እንዴ ቀላል እነግራታለሁ...በቅርቡ ስደውልላት ራሱ ' ያ ልጅ ደና ነው ወይ ስትለኝ ነበር...' በዚው አጋጣሚ ሰላምታዋንም አድርሻለው።

እነሰብሪን ከሩቅ ሆነው እየጠበቋት ነው። ሁሉም አይናቸውን እነሱ ላይ ጥለዋል። ረያን መናደድ ጀመረ።
" ቆይ ማነው? ታቁታላችሁ? " አላቸው። ግን ማንም የሚያውቀው አልነበረም።
" ደሞ ይሄ ሁሉ ሰአት ስለምንድን ነው የሚያወሩት? ደሞ ካወራችውስ እዚው እኛ ፊት አታወራውም ለምን ለብቻቸው መሆን አስፈለጋቸው? " ከንዴት አልፎ ወደ ንጭንጭ ገባ።
" የምንሄድበት ቦታ እንዳለ እረሳችው መሰለኝ..." ሊሄድ ሲል ፋሩቅ አስመለሰው።
" ኧረ ረዩ ተረጋጋ...እንዴ የምር ተናደህ ነው? ስትመጣ ትጠይቃታለህ። "
" ሚስትህን አታምናትም እንዴ? ወይስ ቅናት ነው? እ... " ሂዳያ ሙድ ስትይዝበት ይባስ ተናደደ።

ትንሽ ቆይታ አምሪያ ከሳሊም ጋር መጣች።
" ተዋወቁት በፊት የነበርኩበት ሀገር የትምህርት ቤት ጓደኛዬ ነው..." ሁሉንም ተራ በተራ ስሙን እየተናገረና ስማቸውን እየተቀበለ ተዋወቃቸው። ሳሊምም የዛሬውን ግብዣ እንደሚቀላቀል ነግራቸው ተያይዘው ሄዱ። ረያን ቶሎ ንዴቱ አለቀቀውም። ከሱ ውጪ ሁሉም አሪፍ ጊዜ አሳልፈው ተመለሱ። ረያን ገና በመጀመሪያው ቀን ሳሊምን ጠላው።

*

በነጋታው አምሪና ረያን በጠዋት ነበር ወደትምህርት ቤት የመጡት። እሷ ስለትናንቱ ውድድር ለማውራት ቢሮ ነይ ተብላ ወጣች። ረያን ብቻውን መሆን ስለደበረው በመስኮት በኩል ቆሞ ውጪ ኳስ የሚጫወቱትን ተማሪዎች ይመለከታል።

አንድ ሴትከኋላ በጀርባው በኩል እጇን ወደፊት ሰዳ አቀፈችው። አምሪያ ስለመሰለችው እጇ በእጁ ያዘው።
" ምን ሆነሽ ነው እስካሁን የቆየሽው? "
" ምነው እየጠበከኝ ነበር እንዴ? " ረያን በጣም ደነገጠ ድምፅዋ የአምሪያ አይደለም። ማን እንደሆነች ለማየት ሊዞር ሲል ሆዱን በጣም አጥብቃ ስለያዘችው አልቻለም።
" ይቅርታ ትለቂኝ..." ለማስለቀቅ ቢሞክርም አልተሳካም።
" እኔ እኮ ሴት ሰላም አትልም ብዬ ስለማስብ ነበር እስካሁን ስንቴ ላቅፍህ እየፈለኩ ሳላቅፍህ የቀረሁት...ቢያንስ አምሮቴን ልወጣ..." ጀርባው ላይ ተመቻችታ ተኛች።
" እና ማንን ስነካ ነው ያየሽኝ ታድያ? " አሁን ማን እንደሆነች በደንብ አውቋታል።
" አምሪያን..." አለችው አሁንም አጥብቃ እንዳቀፈችው ነው።
" እሷ እኮ..." ብሎ የሚያወራውን መለሰው። ከጓደኞቻቸው ውጪ ትምህርት ቤት ማንም እንዳያውቅ ተባብለዋል።
" እሷ እኮ ምን? "
" እሺ ልቀቂኝና እናወራለን...አሁንም ቢሆን ሴት አልነካም..." አላት። በዚ መሀል ነበር አምሪያ ወደክፍል የገባችው።

#ክፍል_ዘጠኝ (⓽ )... ይቀጥላል
✿❯────「✿」────❮✿

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━━━─╝

#ክፍል_ዘጠኝ ( ⓽ )
✿❯────「✿」────❮✿

አምሪያ ስታያቸው በጣም ተናደደች። ረያን አይደለም እንደዚ ሊተቃቀፍ ሴት ራሱ የሚነካ ልጅ እንዳልሆነ ነው የምታውቀው። ታድያ አሁንስ ምንድን ነው እየተፈጠረ ያለው። ምንም አልገባትም።

ባሏን ያቀፈችውን ልጅ በደንብ ለማየት ሞከረች። ጄሪ መሆንዋ ይባስ ንዴቷን ጨመረው። ሄደሽ ምቻት ምቻት አሰኛት። ግን ሁኔታውን እስከመጨረሻው ድረስ ማየት ስለፈለገች እንደምንም ብላ ንዴቷን ለመቆጣጠር ሞከረች። ኮቴዋን አጥፍታ ቀስ ብላ ከክላሱ ተመልሳ ወጣች። በሩ ጋርም ተደብቃ የሚያደርጉትን ትከታተል ጀመር።

" ጄሪ ልቀቂኝና እናውራ...አሁንም ቢሆን ሴት አልነካም። " በስንት መከራ ለቀቀችው።
" እና አምሪያስ ወንድ ናት? "
" ለሷ የራሴ ምክንያት ስላለኝ ነው... "
" ምን አይነት ምክንያት ነው ባክህ የሀይማኖትህን ህግ እንድትጥስ ያደረገህ? ወይስ ይሄ ሁላ ጊዜ አውቀህ ነው ስትፎግረኝ የነበረው? " አፈጠጠችበት።
ረያን በዚ ሰአት እውነቱን ከመናገር ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለው አወቀ።
" አምሪ ሚስቴ ናት..." ጄሪ ከት ብላ ሳቀችበት።
" ሌላስ የምትለው የለህም? "
" እየቀለድኩ አይደለም። በእርግጥ ተጋብተን አንድ ላይ መኖር አልጀመርንም ግን ቀለበት አስረናል..." እስካሁን ያላስተዋላችውን እጁ ላይ ያለውን ቀለበት ከፍ አድርጎ አሳያት። የዛኔ ጄሪ ላይ የነበረው ሳቅ ወድያው ወደሀዘን ተለወጠ። ፊቷ መቀያየር ጀመረ። አንገቷን ወደመሬት ሰብራ ለደቂቃዎች ዝም አለች።
" መቼ ነበር? " እንዳቀረቀረች ጠየቀችው።
" ብዙም አልቆየም...ከጓደኞቼ ውጪ ማንም አያውቅም። ላንቺም የነገርኩሽ ስለማምንሽ ነው..."
" እኔስ? " ከአይኖቿ የሚፈሱትን እንባዎች በእጇ እየጠረገች ቀና ብላ ተመለከተችው። ረያን እንባዋን ሲያይ በጣም ደነገጠ።
" እስካሁን እንደምወድህ አታውቅም ነበር? " መልሱን ፍለጋ አይኗን አይኑ ላይ አንከራተተችው። ረያን ምን እንደሚላት ግራ ገባው። የእውነትም ጭራሽ እንደምትወደው አያውቅም። አይደለም ማወቅ የጠረጠረበትን ቀን ራሱ አያስታውሰውም። ምርጥ ጓደኛው እንደነበረች ብቻ ነው የሚያውቀው። እንደዚ ስታለቅስ አይቷት አያውቅም። የምር አሳዘነችው...
" አሞኝ ልትጠይቀኝ የመጣህ ጊዜ ስለምወደው ልጅ ስነግርህ ምን እንዳልከኝ ታስታውሳለህ? " መልሱን ሳትጠብቅ እንባ በተናነቀው ድምፅዋ ንግግሯን ቀጠለች።
" ' ቶሎ ዳኚና ወደልብሽ ንጉስ ሂጂለት። በውበትሽ አስደንግጠሽ በመልካምነትሽ ደሞ ግዢው። እርግጠኛ ነኝ አንቺ ጠይቀሽው እንቢ የሚል ወንድ አይኖርም! ' ነበር ያልከኝ። ይኸው እኮ ታድያ መጣው። በውበቴ አልደነገጥክም? በመሰከርክለት ባህሪዬስ አልተሳብክም? ማንም ጠይቄው እንቢ እንደማይለኝ ነግረኸኝ ነበር እኮ...ታድያ አንተስ? " ማልቀሷን ቀጠለች።
" ጄሪ..." ገና ከማውራቱ አስቆመችው።
" ተወው... ለካ አንተ የዛኔ ለማፅናናት እንጂ ከልብህ አልነበረም እንደዛ ያልከኝ። እኔ እኮ እሱ ንግግርህ ነበር ያጠነከረኝ። ድጋሚ አንተን ለማየት ፣ ካንተ ጋር ለማጥናት ፣ እንደበፊቱ አብሬህ ለመደሰት ፣ አብሬህ ለመሳቅ እጓጓ ነበር። አቃለው እንዳረፈድኩ...ግን አንተም ተለወጥክ። እንደበፊቱ ለኔ ጊዜ መስጠት አቆምክ! ሁሌም ከጓደኞችህ ጋር ነህ። ከኔ ጋር ለማጥናት የምጠቀምበትንም ቦታ እንኳን አምሪያ እንደወሰደችው ገባኝ። እንደበፊቱ ላገኝህ አልቻልኩም። "

የተናገረችው ንግግር እውነት ነበር። ረያን መለወጡ በደንብ ገባው። ሳያስተውለው የድሮ ጓደኛውን ሲገፋ እንደነበር ታወቀው። የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማው ጀመር።
" ይቅርታ! " አላት ድምፁን አለስልሶ። ሌላ ምንም ሊላት አልፈለገም። እንድታወራና ህመሟ እንዲወጣላት ዝም ብሎ ለማዳመጥ ፈለገ።
" ይቅርታ ለምኑ? እየወደድኩህ ስላልተረዳኸኝ ወይስ ሌላ ሴት ስላገባህ? "
" ጄሪ... ሁሉም ሰው እኮ የተፃፈለት የራሱ ሰው አለው...አይደል? የኔ ደሞ አምሪ ናት። ልቤን የከፈተችው...ለመጀመሪያ ጊዜ ስለፍቅር እንዳስብ ያደረገችኝ ልዩ ሴት ናት። በጣም እወዳታለሁ። ላጣትም ስለማልፈልግ ነው በቶሎ የራሴ ያደረኳት። ጄሪ የእውነትም ስለተለወጥኩብሽ በጣም ይቅርታ! ፍቃደኛ ከሆንሽ የድሮውን ጓደኝነታችንን ልንመልሰው እንችላለን። በፍቅር ግን እኔ ያንቺ መሆን አልችልም። ባይሆን አዳምሽን አብረን እንፈልገዋለን። " አንዳንድ ተማሪዎች ወደ ክላስ መግባት ስለጀመሩ ንግግሩን አቆመ። ጄሪ ፊቷን ያጠበውን እንባዋን በሹራብዋ እየጠራረገች ወደመቀመጫ ቦታዋ ሄደች።

አምሪ በዚ ሰአት ምን ማድረግ እንዳለባት ይበልጥ ግራ ገባት። ለማን እንዳዘነች ባይገባትም ውስጧ ግን ሲያዝን ይታወቃታል። ወደክፍል መግባት አልፈለገችም ወደ መጣችበት ተመለሰች።

ከደቂቃዎች በኋላ እዛው ቢሮ አከባቢ እንደቆመች ጄሪ ወደሷ ጋር ስትመጣ አየቻት። ፊቷን አዙራ ቆመች። ጄሪ አምሪያን አልፋት ወደቢሮ ሄደች። ወደክፍል እንዲገቡ ደውል ስለተደወለ አምሪያ ባትፈልግም ወደክፍል ገባች። ቦታዋ ጋር ለመቀመጥ ስትሄድ እነሰብሪን ረያን ዙሪያ ቆመው እያወሩ ነበር።
" ምንድን ነው? የሆንከው ነገር አለ ለምን ታስጨንቀናለህ? " ፋሩቅ ለ2ተኛ ጊዜ ይጠይቀዋል።
" ምንም አልሆንኩም አልኳቹ አይደል? "
" ምንም አለመሆን እንደዚ ነው እንዴ? ፊትህን እኮ ጥለኸዋል..." ሰብሪንም ብትጠይቀው ረያን ግን ምንም አልሆንኩም ብሎ ደረቀ። አምሪያ ምንም ሳትል ሄዳ ተቀመጠች። እሷ ስትመጣ ሁሉም ፊታቸውን ወደሷ አዞሩ። ሰላም ሳትላቸው እንደተቀመጠች እረስታዋለች። የሁለቱን ሁኔታ ሲያዩ ሁሉም ተጣልተው ነው ብለው ነበር ያሰቡት። ጉዳዩን ገና ሰፋ አድረገው ማየት እንዳለባቸው ስላወቁ ለአሁን ዝምታን መርጠው ወደቦታቸው ተመለሱ።

ብዙም ሳይቆይ ጄሪ ወደክፍል ገባች። አልተቀመጠችም... ቦርሳዋን አስተካክላ ይዛ ወጣች። በእጇ ትንሽዬ ወረቀት ይዛ ስለነበር ፍቃድ ጠይቃ ወደቤት ልትሄድ እንደሆነ ያስታውቃል። ረያንና አምሪያ እስከምትወጣ ድረስ በአይኗ ሸኟት። ህመሟን ያውቁታል...

እረፍት ሰአት ላይ ረያን የተወሰነ መረጋጋት ሲጀምር አምሪን ብቻዋን ጠርቶ የተፈጠረውን ነገር ነገራት። ቀድማ ሁሉንም ሰምታ ስለነበር ስላልዋሻት ደስ ብሏታል። በእርግጥ በፊትም በሱ ሙሉ እምነት አላት። ቅድምም ታማኝነቱን በደንብ አይታለች።

ጄሪ ከዚ በፊትም በጣም ታማ ስለነበር በድጋሚ ህመሟ እንዳይነሳ ነበር የፈራው።
" አብሽሪ ምንም አትሆንም..." አቅፋው አጠገቡ ቁጭ አለች።
. ጠዋት ላይ አምሪ ከቤት ስትወጣ ረያን አልነበረም። ለመጀመሪያ ጊዜ ስትቀድመው መሆኑ ነው።ተገረመች... ለትንሽ ደቂቃ ቆማ ብጠብቀውም ረዩ ግን ሊመጣ አልቻለም። ወደቤት ተመልሳ ሄዳ ስልክ ደወለችለት። ስልኩ አይነሳም። አምሪ መጨነቅ ጀመረች። ስልኩን ደጋግማ ከሞከረች በኋላ በመጨረሻም ተነሳ
" ረዩ በሰላም ነው? " ጭንቀቷ በድምፅዋ በደንብ ያስታውቃል።
" አሰላም አለይኩም አምሪያዬ ነሽ አይደል? " ረያን ሳይሆን የረያን እናት ነበረ ስልኩን ያነሳችው።
" ወአለይኩም አሰላም...ረዩ ደና አይደለም እንዴ? " ጭንቀቷ ከቅድሙ ባሰ።
" አስጨነቀሽ አይደል? ትንሽ እኮ አሞት ተኝቶ ነው...ማታ እንቅልፍ እንቢ ብሎት ቅርብ ሰአት ነው የተኛው...ወይ ልቀስቅስልሽ? "
" አይ...ይተኛ በቃ..." ከትምህርት ቤት መልስ ቤት እንደምትመጣ ነግራት ተሰነባብተው ስልኩ ተዘጋ።

ክፍል ገብታ ግን ሀሳቧ ረዩ ጋር ሆኖ መማር አልቻለችም። " ምኑን ነው ያመመው? የትናንትናው ጉዳይ አስጨንቆት ይሆን? " የሚለው ጥያቄ ከጭንቅላቷ አልወጣም አላት። እረፍት ሰአት ላይ አሞኝ ነው ብላ አስፈቅዳ ወጣች። ባሏን ሳታይ መዋል አልቻለችም!

ሰፈር እንደደረሰች ቀጥታ ወደሱ ቤት ነበር የሄደችው። በሩ ጋር ደርሳ አንኳኳች። ትንሽ ከቆመች በኋላ ረያን በሩን ከፈተላት።
" ክላስ አልሄድሽም እንዴ? " በዚ ሰአት እዚ ቦታ ላይ መገኘቷ አስገርሞታል። እንዳመመውም የምታውቅ አለመሰለውም። ወደውስጥ እንድትገባ ጋበዛት።
" አሁን ይሄ በዚ ሰአት የሚጠየቅ ጥያቄ ነው? እንዴት ነህ ግን አሁን? " ሄዳ ተጠመጠመችበት።
" ደና ነኝ! ቆይ እንዴት እንዳመመኝ አወቅሽ? "
" ስልክህን አላየኸውም እንዴ? ጠዋት እኮ ደውዬ ነበር...እናትህ ናት የነገረችኝ..."
" ዝም ብለሽ እኮ ነው የተጨነቅሽው እማ...ትንሽ ራሴን ነው የያዘኝ እንጂ ደና ነኝ። "
እጇን ወደ ግንባሩ ልካ ሙቀቱን ማየት ጀመረች።
" ደና ነኝ ትላለህ እንዴ? በጣም እኮ ነው የምታቃጥለው..." እጁን ይዛው ሄዳ ሶፋው ላይ አስተኛችው።
" እናትህ የለችም እንዴ? " ወድያው ሄዳ ውሁና ጨርቅ ይዛ መጣች። ከጎኑ ቁጭ ብላ ጨርቁን በውሀ እያራሰች ግንባሩንና አንገቱ ስር እያደረገች ታቀዘቅዘዋለች። የተወሰነ ሙቀቱ ከቀነሰ በኋላ አስቀመጠችው።
" እሺ ምግብስ በልተኸል? " ህመሙ ከሱ በላይ እሷን ነው ያስጨነቃት።
" አልበላሁም ግን አሁን መብላት አልፈልግም እማ። "
" አትጨማለቅ..." ተነስታ ምግቡን ለማዘገጃጀት ወደኪችን ገባች።

ትንሽ ቆይታ ሾርባውን ይዛ መጣች። ቀና ብሎ እንዲቀመጥ ካደረገችው በኋላ እራሷ እያጎረሰችው የተወሰነ በላ።
" እ እንዴት ነው? "
" እንደዚ ባለሞያ ሚስት እንዳለኝ አላውቅም ነበር..." ፈገግ እያለ መለሰላት። ምግቡን እንደጨረሰ ፊቱ የደከመው ስለሚመስል ወደቤት ለመሄድ ተነሳች።
" ወዴት ነሽ? "
" ደክሞሀል ብዬ እኮ ነው..."
" እና ቢደክመኝስ? "
" ትንሽ ተኛበታ..."
" እሺ እስከምተኛ አብረሽኝ ሁኚ.." እጇን ይዞ አጠገቡ አስቀመጣት። እንደደከመው በደንብ ትረድታው ነበር ብዙም ሳይቆይ እንቅልፍ ወሰደው። አምሪያ እጇን ቀስ ብላ ከእጁ መሀል አስለቅቃው ለመውጣት ተነሳች።

ከመነሳቷ የረያን ስልክ ሲደወል ሰማች። ከእንቅልፉ እንዳይቀሰቅሰው ብላ ዘጋችው። ስልኩ ተመልሶ ተደወለ አሁንም መልሳ silent አደረገችው። ቁጥር ብቻ ስለሆነ የሚደውለው ማን እንደሆነ ማወቅ አልቻለችም።

ስልኩ አልነሳም ሲላቸው ቴክስት ላኩ። አንስታ አነበበችው።
" ረዩ ዛሬስ አትመጣም? " የሚል ነበር። አምሪ ግራ ተጋባች። ቴክስቱ ከማን ነው? ወደየትስ ነው የሚሄደው? ቴክስቱ በተላከበት ቁጥር መልሳ ደወለች....

#ክፍል_አስር ( ⓾ ) ይቀጥላል...
✿❯────「✿」────❮✿

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━━━─╝



#ክፍል_አስር ( ⓾ )
✿❯────「✿」────❮✿

አምሪ ባሏን በደንብ ታምነዋለች። ምንም ነገር ቢፈጠር እንደማይደብቃት ታውቃለች። አልነገራትም ማለት ያንን ነገር እስከሚያስተካክለው ወይም ትክክለኛው ጊዜ እንስከሚደርስ እየጠበቀ ነው ማለት ነው። ያንን ደሞ ከዚ በፊት አሳይቷታል። የተላከውን ቴክስት ካነበበችው በኋላ ብዙ ማሰብ አልፈለገችም ነበር። ስልኩን ትታው ልትሄድ ፈለገች ፤ ግን ሙሉ በሙሉ መተው አቃታት።
" ምን አልባት እዚ ነገር ውስጥ የኔ መኖር ጉዳዩን ያስተካክለው ይሆናል። " ብላ አሰበች። ወድያው ቴክስቱ ወደተላከበት ቁጥር መልሳ ደወለች ፤ ግን አልተነሳም። መልሳ ብትደውልም ሊነሳ አልቻለም። አሁን ይባስ ግራ ተጋባች። ደጋግመው ሲደውሉ ከዛም አልፎ ቴክስት ሲልኩ ከነበረ ደቂቃዎች ነው ያለፉት አሁን አምሪያ ስትደውል ለምን አላነሱም? የምትደውለው እሷ እንደሆነች አውቀው ይሆን? ሰዎቹ እዚሁ ቅርብ ያሉ ናቸው እንዴ? የረያን እናት ውጪ ላይ ከሰው ጋር ስታወራ ቀድማ ድምፅዋን ስለሰማች ስልኩን አስቀምጣ ወጣች። ጥያቄው ግን ፍፁም ከአዕምሮዋ አልወጣ ብሏታል።

ከትምህርት ቤት መልስ ፋሩቅና ሰብሪን ረያንን ሊተይቁት ቤቱ መጡ። ይዘው የመጡትን ፍራፍሬ ጠረንጴዛው ላይ አድርገው አጠገቡ ተቀመጡ።
የረዩ እናት ኩኪስ ነገር ካቀረበችላቸው በኋላ
" በሉ ልጆች ተጫወቱ በቃ። እነአምሪያ ቤት ደርሼ ልምጣ...በዛውም አምሪን እጠራላችኋለው። " ብላቸው ወጣች።
አምሪም ብዙ ሳትቆይ መጣች።
" እኔ ምለው ሂዳያ ዛሬ ትምህርት ቤት አልመጣችም እንዴ? " አላቸው ረያን ሁሌም ከነሱ ጋር ስለምትሆን...
" አዎ... አንተም ፣ ጄሪም ፣ ሂዳያም ተመካክራችሁ የቀራችሁ እኮ ነው የሚመስለው። " አለ ፋሩቅ ካመጡት ፍራፍሬ ውስጥ አንድ ብርቱካን እየወሰደ።
" ቆይ ግን ረዩ ትናንትም ትክክል አልነበርክም። ምንድን ነው የተፈጠረው? ለምንድን ነው የማትነግረን? ወይስ መደባበቅ ጀመርን? " ሰብሪን አፈጠጠችበት።
" አዎ እውነቷን ነው ለምንድን ነው የተፈጠረውን ነገር የማትነግረን? አምሪ ራሱ እንዴት ዝም አለሽው? " ሁለቱም ቀና ብለው አይዋት። እንድታግዛቸው ነበር...
" ወይስ ላንቺ ነግሮሻል? " አላት ፊቷ ላይ ምንም የጉጉት ስሜት አይታይባትም።
" ረዩ ልክ ናቸው ንገረን..." አለች እየተቅለሰለሰች። ከነሱ ቀድማ መስማታቸው እንዳያናድዳቸው ብላ። መቼም በዚ ሰአት ሚስቱ እንደሆነች አያስቡም እንደጓደኝነት ለሁሉም እኩል እንዲነግራቸው ነው የሚጠብቁት።

ረያንም የተፈጠረውን ነገራቸው።
" እኔኮ ብዬ ነበር አልሰማ አላችሁኝ እንጂ...ድሮውንም እንደምትወደው እገምት ነበር " አለ ፋሩቅ።
" አሁን ስላለፈው ነገር አይደለም ማውራት ያለብን። ከዚ በኋላ ሊያስጨንቀን የሚገባው ቀጣይ ምን እናድርግ የሚለው ነገር ነው። በዚ ምክንያት ታማ ከትምህርቷ መስተጓጎል የለባትም። ታውቃላችሁ ደሞ የታመመች ጊዜ አያቷ ገንዘቡን እንዴት እያመጡ ያሳክሟት እንደነበር...በዛ ላይ አቅማቸውም ደከም ያለ ነው። እሷን በደንብ ሊንከባከቧት አይችሉም። ስለዚ ይሄ ነገር በፍፁም መፈጠር የለበትም! " ፋሩቅ እንደዚ ሲል አምሪያ ደነገጠች።
" ከአያቷ ጋር ነው እንዴ የምትኖረው? "
" አዎ እናቷ እሷን ስትወልድ ነው የሞተችው። አባቷ ደሞ ልጅ እያለች ነው እናቷን ተከትለው የሄዱት። ከፎቶ ውጪ ሁለቱንም በደንብ አታውቃቸውም። የእናቷ እናት ናቸው ወስደው ያሳደጓት። " አላት ረያን።

ረያን መታመሙን ፤ እነሱም የመጡት እሱን ለመጠየቅ መሆኑን እረስተውታል። ሁሉም ትኩረታቸውን ጄሪ ላይ አድርገው ስለሷ ሲጨነቁና ሲወያዩ ቆዩ።
" እና ምን ለማድረግ ወሰናችሁ? " አለቻቸው አምሪያ ስለቤተሰቦቿ ከሰማች በኋላ ይባስ ለጄሪ አዝናለች።
" በቃ ያው ነገ እሁድ ስለሆነ ወይ ሰኞን እንይና ትምህርት ቤት የማትመጣ ከሆነ ቤቷ ሄደን እናያታለን። " ረያን ባመጣው ሀሳብ ተስማሙ። ሁሉም እንዳትታመም በልባቸው ዱዓ እያደረጉ ነበር።

11፡30 ሲሆን ፋሩቅና ሰብሪን ወደቤታቸው ተመለሱ። አምሪያ እናቱ እስከምትመጣ ድረስ ተቀመጠች።
" ሄዱ እንዴ ጓደኞችህ? " እናቱ በሩን ከፍታ ወደውስጥ ገባች።
" አዎ እማ አሁን ቅርብ ሰአት ወጡ። "
" እና አሁን እንዴት ነህ አንተ? " እናቱ አጠገቡ ሄዳ ደባበሰችው።
" ደና ነኝ እማ አትጨነቂ! "
" በቃ ልሂድ አንቺ እስከምትመጪ እየጠበኩ ነበር። " አምሪያም ሰላም ብላቸው ወደቤቷ ተመለሰች።

ቤት ስትገባ እናቱና ታናሽ ወንድሟ ሰሚር እየተከራከሩ ነበር።
"እንቢየው እኔም መሄድ እፈልጋለው " ይላል ሰሚር እየተነጫነጨ...
" አይሆንም እህትህ ብቻዋን ትሆናለች። "
" እማ የት ልትሄዱ ነው? " አለች አምሪ ምንም የምታውቀው ነገር የለም።
" ወ/ሮ ፋጡማን አወቅሻቸው? "
" ፋጡማ...? ፋጡማ..." ለማስታወስ እየሞከረች ነበር...
" የድሮ ከተማችን ጎረቤት የነበሩት...እንደውም ባሏ ናዝሬት ስራ አግኝቶ ሙሉ ቤተሰቡ ወደዛ አልሄዱም? "
" አዎ አዎ አወኳቸው..."
" እና ልጃቸው ሀሊማ ልታገባ ስለሆነ ሰርግ ተጠርተናል። እነግራችኋለው እያልኩ ርስት አረኩት..."
" እኮ እኔም እሄዳለው። " ሰሚር አሁንም ይነጫነጫል።
" ይሂድ እማ ምን ችግር አለው? እሁድ አይደል ትምህርትም የለውም። " አምሪያም አገዘችለት።
" አንቺስ ታድያ ብቻሽን አይደብርሽም? "
" ኧረ እማ አይደብረኝም። ከደበረኝም እነረዩ ጋር እሄዳለሁ። " አለቻት ፈገግ እያለች። ባል እንዳላት የረሱት ስለመሰላት ለማስታወስ ያክል...

*

ለሊት 11 ሰአት ላይ ነበር ተዘገጃጅተው የጨረሱት። ገንዘብ ካስፈለጋት አስቀምጠውላት ቢበዛ እስከ ምሽት 3 ሰአት እንደሚመለሱ ነግረዋት ወጡ።

እሷም ከ11 ሰአት በኋላ መተኛት ስለማትወድ ሰላቷን ሰግዳ ማጥናት ጀመረች። ቁጭ ባለችበት ፀሀይ ወጣች። ሰአቱ እንደዚ መሄዱን አላስተዋለችም ነበር። 1 ሰአት ላይ ቁርሷን እንቁላል ጠብሳ እየበላች እያለ በሯ ተንኳኳ። ረያን ነበር በእጁ የተከደነ ሳህን ይዟል።
" ባልየው ምነው በጠዋቱ " እጁ እቃ ስለያዘ ከፍ ብላ ጉንጩን ሳመችው።
" እማ እኮ ናት ' ቤት እሷና ወንድሟ ብቻ ናቸው ያሉት ቁርስ አድርስላቸው ' ብላኝ ነው። ትናንት የመጣች እናንተ ጋር ጊዜ አውርተው ነበር መሰለኝ..." ጫማውን አውልቆ ወደ ውስጥ ሲገባ ጠረንጴዛው ላይ ምግብ ተቀምጦ አየ።
" አንቺስ በሆድሽ ቀልድ አታውቂም...ገና በለሊቱ ተያይዘሽው የለ እንዴ? " እሱ ያመጣውንም ምግብ አጠገቡ አስቀመጠው።
" ወረኛ 1 ሰአት እኮ ሆኗል። ይሄኔ እራስህ ሰልቅጠህ መተህ ነው..."
" ገና ከእንቅልፌ እንደተነሳው ነው ከነሱ ጋር ብላ ብላ ምግቡን እስይዛ የላከችኝ። የታል ወንድምሽ ታድያ? " እጁን ታጥቦ ወንበሩ ላይ ቁጭ አለ።
" የለም እኮ እሱም አብሯቸው ሄዷል። " አጠገቡ ተቀመጠች።
" እና ብቻሽን ነሽ? ለምን አልነገርሽኝም ታድያ? "
" ብነግርህስ ቀደም ብለህ ትመጣ ነበር? አታስብ አልፈራም..." ሳቀችበት
" ነገረኛ...እኔ እንዳይደብርሽ ብዬ ነው። " ያመጣውን ፍርፍር በትንሹ ተቅልሎ አጎረሳት።
" ትንሽ ቆይቼ እኮ እናንተ ጋር እመጣለው ብዬ ነበር። ኡሚ ብቻ ናታ ያለችው? "
" አዎ በቃ እንብላና አብረን እንሄዳለን። "
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. ምግቡን እየተጎራረሱ በልተው ጨረሱ። ከዛ ምንም ሳይቆዩ ነበር ወደሱ ቤት የሄዱት። ሲገቡ እናቱ ቀርስ በልታ ጨርሳ እቃ እያጠበች ነው። አምሪ ሄዳ አግዛት አብረው ማጠብ ጀመሩ።ሲጨርሱ ቡና ለማፍላት ስለፈለጉ ረያን ቡና ሊገዛላቸው ወጣ።

ረያን ቡናውን ገዝቶ ሲመለስ አምሪና እናቱ ቁጭ ብለው የፎቶ አልበም እያዩ ነበር። የረያንን የህፃንነት ፎቶ እያዩ ይሳሳቃሉ። እንደመጣ ምን እንደሚያዩ ለማየት ፊለፊታቸው ቆመ። ቁምጣ አርጎ የተነሳውን ፎቶ አምሪ በእጇ ይዛዋለች።ልጅ እያለ በጣም ቀጫጫ ነበር በዛ ቅጥነቱ ላክ ቁምጣ... በጣም ያስቅ ነበር።
" የፎቶ ስታይልህን ወድጄዋለው..." አለችው አምሪ ቀና ብላ እያየችው።
" ማን ነው ልጅ እያለ የተነሳውን ፎቶ የሚያስታውሰው? " አልበሙን እና እጇ ላይ የያዘችውን ተቀብሏቸው ተናዶ ሄደ።

አምሪያ በቡና አትታማም እንደሁሌው ምርጥ ቡና አፍልታ አጠጣቻቸው።ስለ ልጅነታቸው፣ ስለወደፊት እቅዳቸው ሲጨዋወቱ ከቆዩ በኋላ ረፈድፈድ ሲል እናቱ " የምሄድበት ቦታ አለ " ብላቸው ወጣች።

አምሪ የቡናውን እቃ እስከምታነሳሳ ድረስ ረያን መፅሀፍ እያነበበ ነበር።
" ቲቪ ማየት እችላለዋ? " ሄዳ አጠገቡ ቁጭ አለች።
" ለምን ታስፈቅጂኛለሽ? ቤትሽ እኮ ነው..." ብሏት ወደመፅሀፉ ተመለሰ። አምሪያ የቲቪውን ሪሞት ፈልጋ አጣችው።
" ሪሞቱን አይተኸዋል? "
" እዚ አከባቢ ነበር..." ሲያዋራት መፅሀፉ ላይ እንዳፈጠጠ ነው። እሷን ቀና ብሎም አላያትም።
" ደብቀኸው ነዋ? "
" ምን ለመሆን ነው ደሞ ሪሞት የምደብቀው? " አይቷት ሳቀ።
" እንደዛ ከሆነ እሺ ተነስ..."
" አትረብሺኝ አሁን ላንብበት..." እየኮረኮረች ከተቀመጠበህ አስነሳችው። ሪሞቱ ከስሩ ነበር ይዞት ተነሳ።
" እሺ በቃ ከደረሽበት ውሰጂው..." ብሎ እጁን ከፍ አድርጎ ያዘው።
" በኋላ ግን እንዳታለቅስ..." እንደምትወስደው እርግጠኛ ሆናለች። ይባስ ሙድ ትይዝበት ጀመር።
" እንዳታለቅስ ያልሽው እኔን ነው? ወይስ ጆሮዬ ነው? " ንግግሩን ሳይጨርስ ሆዱን በእጁ መታው ዝቅ ሲል ተቀበለችው።
" ሃሃሃ ...ለአመታት ከወንድሜ ጋር ልምድ የወሰድኩበት ስራ እኮ ነው! " እየሳቀች ቁጭ አለች።
" አሁን መፅሀፍ እያነበብኩ ልትረብሺኝ ነው አይደል? " ተመልሶ አጠገቧ ሄዶ ቁጭ አለ።
" እሺ እና ቆይ እኔ ሌላ ምን ልስራ? "
" አብረን እናንብብ..." እግሩ ላይ ትራስ አድርጎ እንትደገፍበት በእጁ ምልክት ጋበዛት።አላንገራገረችም ሄዳ ጋደም አለችበት። እግሩ ላይ እንደተኛች መፅሀፉን አብረው ማንበብ ጀመሩ።

6 ሰአት ሲሆን ረያን ተነሳ።
" ወዴት ነው? "
" ምሳ ልስራ...ወይስ ትፆሚያለሽ? "
" ግን ትችላለህ? "
" ባልችል ልትሰሪልኝ ነው? " ወደቦታው ሊመለስ አለ...
" ብቻ የሚበላ ነገር ስራ ምን አገባኝ..." እንደማትሰራለት ስላረጋገጠ ወደኪችን ገባ።

ዙሁር አዛን ሲል ለመጀመርያ ጊዜ እሱ እያሰገዳት ከኋላው ሆና ሰገደች።ደስ የሚል የራሱ የሆነ የተለየ ስሜት አለው።
" አላህ አንቺን ስለሰጠኝ አመሰግነዋለሁ! " መስገጃውን እያነሳ ነበር ዞሮ ግንባሯን ሳማት።
" ምሳውን ማረሻሻ ነው? በል ቶሎ አቅርብ ርቦኛል..." ፈገግ እያለች መስገጃውን ተቀብላው አስቀመጠች።

" እ እንዴት ነው ይጣፍጣላ? " ካጎረሳት በኋላ አስተያየቷን እየጠበቀ ነው።
" ይጣፍጣል! ጨው ግን በምንድን ነው የጨመርከው በአላህ? " ውሀ አንስታ ጠጣች።
" ፆምሽን መዋል ካልፈለግሽ እንግዲ አርፈሽ ብዪ ..." እንደምንም የቀረበላትን ጨረሰችው።
" በይ እኔ ከሰራው ተነስተሽ እጠቢ..."
" አንተ ደሞ ህግህ በዛ። እኔ ደክሞኛል " እጇን ታጥባ ሶፋው ላይ ሄዳ ቁጭ አለች።
" እሺ አቦሰም እንጣል የተሸነፈ ያጥባል..." እጁንም ሳይታጠብ ወደሷ ሄደ። ግን እራሱ ተሸንፎ እቃውን አሳጠበችው።

ሰአቱ እንደቀልድ ይሄዳል። ማታ ሁለት ሰአት ላይ እናቷ ቤት እንደገቡ ደውላ ነገረቻት። ረያን ወደቤት አድርሷት ተመለሰ።

*

ሰኞ ጠዋት.... ሁሉም በጊዜ ነበር ትምህርት ቤት የመጡት። በሩ አከባቢ ቁጭ ብለው የጄሪን መምጣት ይጠባበቃሉ። ሂዳያ ስለጉዳዩ ባታውቅም እንደመጣች ተቀላቀለቻቸው። እሷ በቅርቡ የመጣችና ያለፈውን ህይወት ምንም ስለማታውቅ ይሄንንም አስፈላጊ አይደለም ብለው አልነገሯትም። በነሱ መሀል ብቻ የሚቀር ሚስጥር ነው።

አስተማሪው ክፍል ገብቶ ትምህርት እስከሚጀምሩ ድረስ ተስፋ ሳይቆርጡ እየጠበቋት ነበር ግን ጄሪ አልመጣችም። የክላሱ ተማሪ በሙሉ የጄሪን ሁለት ቀን መቅረት ስላስተዋሉ ታማ ይሆን እንዴ እያሉ ማውራት ጀምረዋል። እነረያን ጨንቀታቸው ይባስ እየጨመረ መጣ። ወደቤት ሰአት ደርሶ ሄደው እስከሚያይዋት ድረስ መረጋጋት አቃታቸው። እንዲው በጭንቀትና በድብርት ነበር ቀኑን ያሳለፉት።

አይደርስ የለ በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው ሰአት እየተሟዘዘም ቢሆን ደረሰ።ሁሉም ቦርሳቸውን ቀድመው አስተካክለው ነበር ገና ከመደወሉ እየተሯሯጡ ወጡ። ሂዳያ ' ሌላ የምሄድበት ቦታ አለ ' ብላ ከነሱ ጋር አልሄደችም።

ወደጄሪ ቤት ለመሄድ የአንድ ታክሲ መንገድ አለው። ቦታው ጋር ደርሰው የታክሲውን ሰልፍ ሲያዩ እንባቸው ነበር የመጣው ፤ ግን ምንም አማራጭ የላቸውምና ሰልፉን ተቀላቀሉ። ፀሀዩ ከጭንቀታቸው ጋር ተደምሮ ራስ ምታት ይለቅባቸው ጀመር። በተደጋጋሚ ፊታቸውን እየታጠቡ ሙቀቱን ለመቀነስ ይሞክራሉ። እንደምንም ተራቸው ደርሶ ወደጄሪ ቤት ጉዞ ጀመሩ።

ረያን ለሁሉም ከፍሎ መዳረሻው ጋር ሲደርሱ ከታክሲው ወረዱ። ከአምሪያ ውጪ ሁሉም የጄሪን ቤት ያውቁታል። ቀጥታ ቤቷ ጋር እንደደረሱ የግቢውን በር አንኳኩ። በተደጋጋሚ በሀይል ቢያንኳኩም የሚከፍትላቸው አልነበረም። አምሪያ በበሩ ጥግ በኩል መሬት ላይ የታጠለውን ገመድ አየችው። ከበሩ ጋር የተያያዘ ይሆናል ብላ አስባ ገመዱን ጎተተችው። ወድያው በሩ ተከፈተ።

እየተጣደፉ ወደውስጥ ገቡ ፤ ግን ሳሎን ውስጥም ማንም አልነበረም።
" የት ሄዳ ይሆናል? "
" ምን አልባት ሆስፒታል ትሆን እንዴ? "
" ጎረቤት እንጠይቅ ወይስ በፊት የታከመችበት ሆስፒታል ሄደን እንጣራ? " የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ሲመካከሩ ቆዩ። በመጨረሻም በፊት የታከመችበት ሆስፒታል ለመሄድ ተስማሙ።

ከሳሎን ሊወጡ ሲሉ ግን አንድ ድምፅ ሰሙ።ወድያው ድምፁን እየተከተሉ ወደ አንድ ክፍል ደረሱ። ስልክ እየጠራ ነበር። ሰው ሊኖር ይችላል ብለው ስላሰቡ የክፍሉን በር ከፈቱት። የጄሪ ክፍል ነው...በሩን እንደከፈቱ ያዩትን ማመን አቃታቸው። እነአምሪያ ባሉበት ደርቀው ቀሩ...

#ክፍል_አስራአንድ ( ⓫ ) ይቀጥላል...
✿❯────「✿」────❮✿

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━━━─╝



#ክፍል_አስራአንድ ( ⓫ )
✿❯────「✿」────❮✿

እነአምሪያ ወደክፍል ሲገቡ ጄሪ መሬት ላይ ተዘርራ ወድቃለች። ሁሉም በድንጋጤ ባሉበት ደርቀው ቆሙ። ረያን ግን እየሮጠ ወደጄሪ ጋር ሄደ። ዝግ ብሎ ትንፋሿን ካዳመጠ በኋላ
" በህይወት አለች " አላቸው ባገኘው ደስታ ፊቷ እየበራ። ወድያው አጠገቧ የወደቀውን ብርጭቆ አንስቶ አሸተተው።
" ብዙ ጊዜ የለንም...ፋሩቅ እዚ አከባቢ ሀኪም ቤት አለ እንዴ? " ሁሉም ረያን ምን እያደረገ እንደሆነ ባይገባቸውም ዝም ብለው ያዩታል።
" አዎ ሁለተኛው መታጠፊያ ጋር አንድ ሆስፒታል አለ..." ወሬውን ሳያስጨርሰው ረያን ጄሪን አቅፏት እየሮጠ ከቤት ወጣ። አይኑ ማልቀስ እስከሚቀረው ድረስ ቀልቷል። አምሪያ ቀድማው ሄዳ የግቢውን በር ከፈተችለት። እሱን ተከትለው ሁሉም እየተሯሯጡ ወደ ሆስፒታል ሄዱ።

" የምትድን ይመስላችኋል? " ሰብሪን አግዳሚው ወንበር ላይ ሄዳ ቁጭ አለች።
" እንግዲ እሱን አላህ ነው የሚያውቀው ከኛ የሚጠበቀው ዱዓ ማድረግ ነው..." አምሪያም አጠገቧ ሄዳ ተቀመጠች። ረያን ቁና ቁና ይተነፍሳል። ላብ ሰውነቱን አዝፍቆታል።
" ኢንሻአላህ ትድናለች! " ፋሩቅ ገዝቶ የመጣውን ሀይላንድ ውሀ ለረያን አቀበለው።
ጄሪን ወደድንገተኛ ክፍል አስገብተዋት ቁጭ ብለው ውጤት እየጠበቁ ነበር።

ሁሉም መረጋጋት አቅቷቸው ይቁነጠነጣሉ። ከብዙ ደቂቃዎች በኋላ ዶክተሩ ከሁለት ነርሶች ጋር ከድንገተኛ ክፍሉ ወጣ። ሁሉም ከተቀመጡበት ተስፈንጥረው ተነስተው ወደነሱ ጋር ሄዱ።
" ዶክተር ደና ናት አይደል? " አለ ረያን መልካም ዜናን ከዶክተሩ አፍ ለመስማት እየጓጓ።
" እናንተ ምኗ ናችሁ? "
" ጓደኞቿ ነን..." ሁሉም በአንድ ላይ መለሱለት።
" ትንሽ ብትቆዩ ታጧት ነበር..."
" ኡፍፍፍ አልሀምዱሊላህ..." ረያን አጠገቡ ያለው ግድግዳ ላይ ተደግፎ ተቀመጠ።
" ለማንኛውም ትንሽ ቆይታችሁ ገብታችሁ ማየት ትችላላችሁ።" ብሏቸው ሄደ። ሁሉም ምስጋናቸውን ለፈጣሪያቸው አደረሱ።

እንደተባሉት ትንሽ ከቆዩ በኋላ አንድ ላይ ወደጄሪ ክፍል ገቡ። ነቅታ ነበር
" ማን ነው ያመጣኝ? " አለቻቸው በሲቃ ድምፅ ሁሉንም ተራ በተራ እያየች።
" ለምን ጄሪ? ለምን እንደዛ አደረግሽ? " ባንቺ መሞት የሚጎዱትን ሰዎች ለምን አላሰብሽም? " ረያን በስስት ይመለከታታል። በሱ ምክንያት እራሷን አጥፍታ ቢሆን ኖሮ እስከእድሜ ልኩ ከልቡ የማይጠፋ ጠባሳ ፤ ከህሊናው ፈፅሞ የማይሸሽበትን ፀፀት እንደሚያተርፍ ሲያስብ በመትረፏ ደጋግሞ ያመሰግናል።

" ግን እንዴት መጣችሁ? " አለቻቸው። አሁንም ግራ ተጋብታለች።
" ትምህርት ቤት ስትቀሪ ምን ሆና ነው ብለን ልንጠይቅሽ ነበር የመጣነው...ግን አያትሽ የት ናቸው? ቤት ሲያጡሽ እንዳይረበሹ...ወይ ደውለን እናረጋጋቸው ስልካቸውን ንገሪኝ..." አምሪያ ለመደወል ከቦርሳዋ ውስጥ ስልኳን አወጣች።
" አይ አትደውዪ...አያቴ ጠዋት ነው ለቅሶ ገጥሟት ክፍለሀገር የሄደችው። ስለዚ ምንም የምታውቀው ነገር የለም። "
"ቢሆንም ስልክሽ እዚ የለም ደጋግመው ደውለው አተውሽ ይሆናል። ቢያንስ ደና መሆንሽን ልትነግሪያቸው ይገባል። ቆይ ስልክሽን ይዤልሽ ልምጣ። " ረያን ሲወጣ ፋሩቅም ተክትሎት ሄደ።

ረያንና ፋሩቅ የጄሪን ስልክ ይዘው ሲመለሱ አምሪያ ከዶክተሩ ክፍል እየወጣች ነበር።
" ምን አለሽ? አዲስ ነገር አለ?።" አላት ረያን
" የጠጣችው መድሀኒህ ብዙም አልጎታድም ፤ ይልቁንም እሞታለሁ የሚለው ሀሳብ ነበር ይበልጥ ያስደነገጣት! ግልኮሷን ትጨርስና ይዛችኋት መሄድ ትችላላችሁ ብሎኛል። አሁን እኔን ያስጨነቀኝ በዚ ሁኔታ ለጄሪ ቤቷ መሄድ አስቻጋሪ አይሆንም? አንደኛ ማንም የሚንከባከባት ሰው የለም...በዛ ላይ ብቻዋን ስትሆን ድጋሚ እራሷን ላለመጉዳቷ ማስተማመኛ የለንም። "
" ታድያ ምን ይሻላል? " ፋሩቅ ሰብሪንን ቀስ ብሎ ጠራት። እንዲመካከሩ...
" ብዙ ነገር ካሰቡ በኋላ በመጨረሻም ጄሪ አምሪያ ጋር እንድትቆይ ተስማሙ። "

የመውጫ ሰአቷ ከደረሰ በኋላ ጄሪ " ወደቤት መሄድ ነው የምፈልገው " ብላ ብዙ አስቸግራቸው ነበር ፤ ግን እንደምንም ተቆጥተው አሳመኗት። ቤቷ ጎራ ብለው ስልኳንና አንዳንድ የሚያስፈልጓትን ነገር አምሪያና ሰብሪን ይዘው ሄዱ።

*

ጄሪ አምሪያ ቤት ስትመጣ ቤተሰቦቿ ምንም አልተቃወሙም ነበር። ይልቁንም በጣም ይንከባከቧት ጀመር። ጄሪና አምሪያ አንድ ክፍል ነበር ለሁለት የተጋሩት።

አምሪያ ትምህርት ቤት የምትሄድ ቀን ጃሪ ከእናቷ ጋር ትውላለች። ከትምህርት ቤት መልስ ደሞ ሁሉም እነአምሪያ ቤት መተው ሲጨዋወቱ ቆይተው ይመለሳሉ። ጄሪ ሙሉ በሙሉ እስከሚሻላት አያቷም ወደቤት እስከምትመለስ 3 ቀናትን እነአምሪያ ቤት አሳለፈች። በዚ ምክንያት ከአምሪያ እንዲሁም ከሙሉ ግሩፑ ጋርም በደንብ ተቀራረበች። ከዚ በኋላም በጓደኝነት አብረዋት እንደሚሆኑና ብቻዋን እንደማይተዋት ቃል ገቡላት።
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
ጄሪ የረያን ፍቅር በጣም ጎድቷት የነበረ ቢሆንም በጓደኝነታቸው ግን ተካሰች። የአምሪንና የረያንን ፍቅር እና መልካምነት ስታይ ከዚ በኋላ በነሱ መሀል ጣልቃ ላለመግባት ወሰነች።

የአምሪያና የረያን ፍቅር እየጨመረ ፣ የሁሉም ጓደኝነት እየጠነከረ ፣ ሰብሪንና ፋሩቅም ጭቅጭቃቸውን ሳይተውት ጊዜያቶች አለፉ።

" የዚ ልጅ ግን እዚ መምጣት አልበዛም? " አላት ወደቤት ሰአት ላይ ሳሊም አምሪያን ለመጠበቅ እንደመጣ ሲያይ...
" ባልየው ቀናህ እንዴ? አብረን መሆናችንን እኮ ያውቃል። ምን ያስባል ብለህ ፈርተህ ነው? "
" አላውቅም ግን ደስ አላለኝም። ጊዜዬን እየተሻማብኝ ነው። "
ሳሊም አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ አምሪያን ብዙ ጊዜ ለማግኘት ሲሞክር አስተውሎታል።
" ታድያ አትምጣ አልለው ነገር? ምንም ቢሆን ጓደኛዬ እኮ ነው። ወይስ አታምነኝም? " ተነጫነጨችበት።
" ሳላምንሽ ቀርቼ ሳይሆን በቃ እንዲው ደስ ስለማይለኝ ነው። "

" ምንድን ነው? ደሞ ዛሬም በሳሊም ምክንያት ነው የምትከራከሩት? " ሰብሪንና ፋሩቅ ከነሱ ቆይተው ነበር ከግቢ የወጡት። ሳሊም ሁሌ ሲመጣ ቁጭ ብሎ የሚጠብቃት ቦታው ተቀምጦ አይተውታል።
" አንቺ ልጅ ግን ይሄን ልጅ ለምን አታስተዋውቂኝም ? " አለች ሰብሪን ወደ አምሪያ ጠጋ ብላ።
" ጉብዝና...ውበት...ምርጥ ፀባይ አንድ ላይ ሲሰጥ አይቼ አላውቅም ነበር። " ሰብሪን ሳሊምን ማሞገስ ቀጠለች።
" ኧረ ከፈለግሽማ አስተዋውቅሻለው..."
" ቆሞ ለማውራት የሚሆን ጊዜ አልተረፈኝም። ሄጃለው..." ፋሩቅ ሰብሪንን ገፍትሯት አለፈ።
" ያምሀል እንዴ? " እየጮኸችበት ተከተለችው። አምሪያ ሳሊምን ሰላም ለማለት ስትሄድ ረያንና ሂዳያም እነፋሩቅን ተከተሏቸው።

ረያን በሳሊም ምክንያት ፍቅራቸው ንፋስ እንዳይገባበት በጣም ይፈራል።

*

" የተባባልነውን እንዳትረሱ.. ስህተት መስራት አይደለም ምንም የሚያስጠረጥር ነገር ማድረግ እንኳን የለብንም! " አንዲት ሴት ፊትለፊቷ ለተቀመጡት ሁለት ሰዎች ይሄንን በተደጋጋሚ እያለች ታስጠነቅቃቸዋለች።
" አታስቢ...ላንቺ ሳይሆን ለራሴ ስል ነው የማደርገው። " ከሁለቱ አንደኛው ሰው መለሰላት።
" ልክ ነህ ጥቅሙ ላይ እኩል ተጋሪዎች ስለሆንን ለራሳችን ስንል በደንብ እንሰራዋለን። እና መች ነው ልታገኛት ያሰብከው? " አለችው ከተቀመጠችበት እየተነሳች።
" ዛሬ ማታ እቃ ላቀብልሽ ነው ብዬ አስወጣታለው። "
" በጣም አሪፍ...አጋጣሚው አንዴ ስለሆነ በፍፁም እንዳያመልጥህ! " ወደአንደኛው ሰው ዞራ በተራው ለሱም የሚሰራውን ስራ አብራራችለት። ሶስቱም ስራቸውን ተከፋፍለው ተለያዩ።

*

ማታ ላይ ረያን ከሚስቱ ጋር ለረጅም ደቂቃ መኝታ ክፍሉ ቁጭ ብሎ ስልክ ያወራል። እሷን እያወራ በተደጋጋሚ ሌላ ስልክ እየገባ ሲያስቸግረው ለአምሪ መልሶ እንደሚደውልላት ነግሯት ስልኩን ዘጋው። የተደወለለትን ስልክ ተመለከተው። ከዚ በፊት ብዙ ጊዜ ሲደወልለት የነበረው ስልክ ነው።
" ከትምህርት መልስ ሰፈር ያለው ካፌ እጠብቅሀለው ና " የሚል ቴክስትም ሲላክበት የነበረው ቁጥር።
ወደ ቁጥሩ መልሶ ደወለ...አነሱት።
" በተደጋጋሚ ከሂወቴ እንድትወጪ ነግሬሻለው አይደል? ቆይ ለምን አትተዪኝም? " አላት በጣም ተናዷል። ለመጀመሪያ ጊዜ የተደወለለት ቀን ነው ሴት እንደሆነች ያወቀው። ላግኝህ ስትለው እንደማይፈልግ ቢነግራትም በየቀኑ ግን " ዛሬስ አትመጣም? " የሚል ቴክስት ትልክለት ነበር።
" ቴሌግራም ላይ የላኩልህን ፎቶ ተመልከተው " ብላ ስልኩን ዘጋችው። ወድያው የተላከለትን ፎቶ ገብቶ አየው። ያየውን ስላላመነ አይኑን አሻሽቶ መልሶ ተመለከተው።
ሳሊም አምሪያን ሲስማት የሚያሳይ ፎቶ ነበር። ረያን ንዴቱን መቆጣጠር አቃተው። አምሪያ ቁጭ ብላ ብትጠብቀውም መልሶ ሳይደውልላት ተኛ።

#ክፍል_አስራሁለት (⓬) ይቀጥላል...
✿❯────「✿」────❮✿

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━━━─╝

#ክፍል_አስራሁለት ( ⓬ )
✿❯────「✿」────❮✿

አምሪያ መልሳ በተደጋጋሚ ብትደውልለትም ስልኩን አላነሳም። ተኝቶ ይሆናል ብላ ብዙ አላሰበችም ነበር ፤ ጠዋት ወደትህምርት ቤት ለመሄድ እሷ ቀድማው እንደወጣች እስከምታይ ድረስ። ሁሌም እሱ ነው ቀድሟት የሚወጣው። እሷ ቀደመችው ማለት የሆነ ትክክል ያልሆነ ነገር አለ ማለት ነው። ግራ እየተጋባች ወደቤቱ ሄደች። እናቱ ነበረች የግቢውን በር የከፈተችላት። ሰላም ከተባባሉ በኋላ ረያን ደህና ስለመሆኑ ጠየቀቻት።
" ረዩ እኮ ቆይቷል ከወጣ። አብራችሁ አልሄዳችሁም እንዴ? " አለቻት እናትየውም ግራ እየተጋባች።አምሪያ አሁን ይባስ አሳሰባት።
" አይ ዛሬ ትንሽ አርፍጃለው። ስቆይ የሄድኩ መስሎት ይሆናል። " ምንም እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል ሞከረች።

ትምህርት ቤት እስከምትደርስ ድረስ እራሷን በጥያቄ እያጨናነቀች ነበር የሄደችው። ደርሳ አይኑን እስከምታየውና እስከምታዋራው ቸኩላለች። ክፍል ስትገባ ባሏና ፋሩቅ ቁጭ ብለው አገኘቻቸው።
" አንተ ምን ሆነህ ነው ጥለኸኝ የሄድከው? ዛሬማ ቅጣት አለብህ? " እንደበፊቱ እየተቅለሰለሰች ወደሱ ጋር ሄደች።
ረያን ግን ገና እሱ ጋር ሳትደርስ ፋሩቅን ኳስ ልጫወት ነው ብሎት በጎና አልፏት ሄደ። አምሪያ ደንግጣ ባለችበት ቆመች።
" ሰላም አይደላችሁም እንዴ? " አላት ፋሩቅ ወደሷ ጋር እየመጣ።
" እኔ እስከማውቀው ነን...ወይስ የሆነ ጨዋታ እየተጫወታችሁብኝ ነው? " ቦርሳዋን ጠረንጴዛው ላይ አስቀምጣው ከፋሩቅ ጋር ሊያናግሩት ወጡ።

ቀጥታ ወደ ኳስ ሜዳ ነበር የሄዱት ግን ኳስ የሚጫወቱት ተማሪዎች ጋር ረያን አልነበረም። ግራ እየተጋቡ ግቢውን ዞረው ፈለጉት ጭራሽ ሊያገኙት አልቻሉም። ደውል ተደውሎ የመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ ሲጀመር ወደክፍል መጣ። አምሪያ ልታናግረው ብትፈልግም አስተማሪ ስለነበር ምንም ማለት አልቻለችም። ፋሩቅ ምን ሆኖ እንደሆነ እየተንሾካሾከ ቢጠይቀውም ሊመልስለት መልስ ሳይሰጠው ወደትምህርቱ ገባ።

*

ረያን ከዚ በፊትም ቢሆን ሳሊምን አይወደውም ነበር። በተደጋጋሚም ለአምሪያ ነግሯታል። በሱ ምክንያት በመሀላቸው ንፋስ እንዳይገባ ሁሌም ይፈራ ነበር። " የፈሩት ይደርሳል ፣ የጠሉት ይወርሳል " ሆነና ነገሩ እሱም የፈራው ደረሰ። አምሪያ ልታናግረው ብትሞክርም ፊት ነሳት። ጓደኞቹም ስለተፈጠረው ነገር እንዳይጠይቁት አስጠነቀቃቸው።

አንድ ትምህርት ቤት ያውም አንድ ክፍል ውስጥ ተጣልቶ መዋል ለአምሪያም ብቻ ሳይሆን ለሙሉ ጓደኞቹ በጣም ከብዷቸው ነበር። ረያን እንደዚ ሲሆን አይተውት አያውቁም። በዚ ምክንያት በአምሪያና ረያን መካከል ትልቅ ክፍተት መፈጠር ጀመረ።

*

እሁድ ቀን ረያን ከቤት ሳይወጣ ነበር የዋለው። 11 ሰአት አከባቢ ላይ ሂዳያ ስልክ ደወለችለት።
" አሰላም አለይኩም ረዩ " ድምፅዋ በጣም የቀነሰ ነበር።
" ዋአለይኩም አሰላም...ምነው ድምፅሽ ደና አይደለሽም እንዴ? "
" አዎ ትንሽ እያመመኝ ነው። አጋጣሚ እናንተ ሰፈር ነበርኩኝ ለአምሪያ ስደውልላት ስልክ አታነሳም...እያዞረኝ ስለሆነ መሄድ አልቻልኩም..ላስቸግርህ...? "
" የት ነሽ አሁን? "
" ትልቁ ካፌ አከባቢ ቁጭ ብያለው..."
" መጣው..." ስልኩን ዘግቶት እየሮጠ ከቤት ወጣ።

አንድ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብላ እየጠበቀችው ነበር።
" አሁንስ እንዴት ነሽ? " አጠገቧ ሄዶ ቆመ። ለመነሳት ስትሞክር ስላዞራት መልሳ ቁጭ አለች።
" ከዚ በፊት ያምሽ ነበር እንዴ? " ምን እንደሚያደርግ ግራ ገብቶታል።
" ኧረ አያመኝም ዛሬ ገና ነው..."
" ወይ ሀኪም ቤት እንሂድ? " አላት ሰው ታሞ ሲያይ በጣም ይጨነቃል።
" አይ ችግር የለውም። ባይሆን ታክሲ ጥራልኝና ወደቤት አድርሰኝ። " አለችው።
ከነሱ ትንሽ ርቆ ካፌው በር ጋር አንድ የቆመ Ride ነበር።
" ሰው እየጠበቀ ካልሆነ ያንን መኪና ላናግረው..." ብሏት ሄደ።

ብዙው ሳይቆይ አናግሮት ተመልሶ መጣ።
እንደተስማማ ነግሯት ቦርሳዋን ተቀብሏት ደግፏት ወደ መኪናው ጋር ሄዱ። ልክ ካፌው ጋር እንደደረሱ አምሪያና ሳሊም ከካፌው ሲወጡ ፊትለፊት ተገጣጠሙ።
ረያን ሳሊምን ሲያየው ወድያው ፊቱ ተቀያየረ። መረጋጋት አልቻለም። ወደሳሊም ተንደርድሮ መቶ በቦክስ ፊቱን መታው። ሁሉም ደነገጡ። አምሪያ መሀል ገብታ አስቆመችው። ሳሊም ከአፉ ደም ይተፋል።
" ያምኸል እንዴ? " ረያን ላይ ጮኸችበት።
" ከመሬት ተነስተህ የሰው ሰው የምትመታው ማነኝ ብለህ ነው? " በጣም ተናዳበታለች።
ረያን ምንም ሳይል እንደቆመ ነው።
" ትሰማኛለህ ከኔ ጋር ያለብህን ችግር ከኔ ጋር ፍታ። በመሀል ሌላ ሰውን እንድትጎዳ አልፈቅድልህም! " ረያንን ባለበት ጥላው ወደካፌው ተመልሳ ገባች። ሳሊምና ረያንን እንደተፋጠጡ ናቸው።ሂዳያም ምን ማለት እንዳለባት ግራ ስለገባት ዝም ብላ ቆማለች። ሳሊም አምሪያን ማስከፋት ስላልፈለገ ለተሰነዘረበት ቡጢ ምላሽ አልሰጠም። አምሪያ ሀይላንድ ውሀ ይዛ መጥታ ሳሊምን አስታጠበችው።

" እየጠበቀችህ እኮ ነው... እስካሁን እዚ ምን ትሰራለህ? " ድጋሚ ስታየው ንዴቷ ጨመረ። በዚ ሰአት ከሂዳያ ጋር ያውም ደግፏት ማየቷ እንደሚያናድዳት አላሰበውም ነበር። የራሱን ህመም ነበር ሲያዳምጥ የነበረው። ረያን የመኪናውን በር ከፍቶ ሂዳያን ከኋላ ካስገባት በኋላ እሱ ከፊት ተቀምጦ ለሹፌሩ እንዲሄዱ ነገረው።
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. ከዚ ቀን በኋላ ነበር በአምሪያና በረያን መካከል የነበረው ክፍተት ጭራሽ እየጨመረ የመጣው። ጓደኞቻቸው ሊያስታርቋቸው ቢሞክሩም ሊሳካ አልቻለም። አሁን ላይ ረያን ብቻም ሳይሆን አምሪያም ረያንን ለማናገር ፍቃደኛ አይደለችም። የተፈጠረውን ነገር ነግሯት ከሷ ጋር ማውራት ሲችል ዝምታን መምረጡ ይበልጥ አናደዳት። ባሏን እንደዚ አልነበረም የምታውቀው። ምንም እንደማይደብቃት ፤ ሁሉንም ነገር እንደሚያማክራት ነበር የምታስበው። አሁን ግን ፍፁም የማታውቀው ረያን ሆኖባታል።

*

" እኔ ምላችሁ ሂዳያና ረያን የት ሄደው ነው? " አለች ጄሪ ከአምሪያ ፣ ሰብሪንና ፋሩቅ ጋር ተሰብስበው ክፍል ቁጭ ብለዋል።
" ሂዳያ አስጠናኝ ብላው ወደላይብረሪ ሄደው ነው። " ሲወጡ በር ጋር ከፋሩቅ ጋር ተገናኝተው ነግረውት ነበር። አምሪያ ጠረንጴዛው ላይ ተደግፋ ተኝታለች።
" ግን ይሄን ሰሞን በሁለቱ መካከል የማየው ቅርርብ እኔን ብቻ ነው ያስገረመኝ? " አለች ሰብሪን።
" ልክ እኮ ነሽ። ሂዳያ ለማጥናትም እቃ ለመግዛትም ከረያን ጋር ነው የምትሄደው። " ፋሩቅም የሰብሪንን ሀሳብ ደገፈ። አምሪያ ስለረያን መስማት ስላልፈለገች ተነስታ ከክፍል ወጣች።

እነሰብሪን ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ተጋብተዋል። መሀል ቤት ሆነው ተሰቃዩ።
" እኔ ግን የነሱ ጥል ላይ የሂዳያ እጅ እንዳይኖርበት ነው የምፈራው። " ጄሪ በሰሞኑ የሂዳያና የረያን ቅርርብ ሂዳያን መጠርጠር ጀምራለች።
" ግን ምን ላግኝ ብላ? ወይስ ወዳው ነው ብላችሁ አስባችሁ ነው? " ፋሩቅ ከዚ በፊት ሂዳያ ረያንን ልትወደው እንደምትችል አስቦ አያውቅም። እንደዛ አይነት ምልክትም ሂዳያ አሳይታ አታውቅም።
" ከዚ በፊት በወንድ እንደተጎዳችና በአሁን ሰአት ስለፍቅር ማሰብ እንደማትፈልግ የነገረችንን እረስታችሁት ነው? " ፋሩቅ አሁንም ቢሆን ሂዳያ ረያንን ትወደዋለች ብሎ አያስብም።
" ታድያ ምን ላድረግ ቢጨንቀኝ እኮ ነው። "
" ልክ ነሽ ጄሪ...መጠርጠሩ አይከፋም። ለማንኛውም ማጣራት ያለብን ጉዳይ ሳይኖር አይቀርም። " ረያንና ሂዳያ ወደክፍል እየገቡ ስለነበር ሰብሪን ንግግሯን አቋረጠች።
" አምሪስ? " አለች ሂዳያ ከተሰበሰቡት መሀል እሷን ስላጣቻት።
" ወጥታ ነው ትመለሳለች። ምነው ፈለግሻት? " አለች ሰብሪን ጄሪ ያለችው ሀሳብ እውነት ቢሆንስ ብላ እያሰበች ትናደድባት ጀመር።
" ኧረ እንዲው ነው ስላላየኋት ነው። " ወንበሯ ጋር ሄዳ ቁጭ አለች።

ረያን አምሪያን ለማናደድ ይመስል ብዙ ጊዜ ከሂዳያ ጋር መታየት ጀምሯል። አምሪያ ደሞ በተቃራኒው ከሳሊም ጋር እንደድሮ መገናኘት እንኳን አቁማለች። ካፌው ጋር ተገናኝተው ሳሊምን ከመታው በኋላ የተጣላት በሱ ምክንያት ነው እንዴ ብላ ስታስብ ነበር። ግን ዝምታው አሁንም ቢሆን ልቧን እያቆሰለው ነው።

*

" አንቺ ልጅ አትነሺም እንዴ? ዛሬ ትምህርት ቤት አትሄጂም? " የአምሪያ እናት ወደክፍል ገብታ ትቀሰቅሳታለች። ያለመደባትን እስከዚ ሰአት ድረስ መተኛቷ ግራ ገብቷታል።
" አምሪ...አንቺ አምሪ..." በተደጋጋሚ ልትቀሰቅሳት ሞከረች። ትንሽ ቆይታ አምሪያ ባንና ተነሳች። እናቷ በጣም ደንግጣ ሄዳ አቀፈቻት።አምሪያ ሰውነቷ በሙሉ ላብ በላብ ሆኖ ነበር። ከረጅም ጊዜ እንቅልፍ በኋላ የተነሳች ነው የመሰላት።
" እማ ህልም ነበር? " አለች ከአይኗ የሚፈሱትን እንባዎች እየጠራረገች።

#ክፍል_አስራሶስት (⓭) ይቀጥላል...
✿❯────「✿」────❮✿

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━


#ክፍል_አስራሶስት (⓭)
✿❯────「✿」────❮✿

" እማ ህልም ነበር ይሄ ሁሉ? " አለች ከአይኗ የሚፈሱትን እንባዎች በእጇ እየጠራረገች። እናቷ ደንግጣ ሄዳ አቅፋት ቁጭ አለች።
" ምን አይተሽ ነው? "
" ከረዩ ጋር..." ብላ እንባ መልሶ ሲተናነቃት ዝም አለች።
" ከረዩ ጋር ምን? " አለች እናቷ ከዚ በፊት ስለተጣሉት ነገር ምንም አታውቅም።
" ከረዩ ጋር ተለያይተን ነው መሰለኝ... ወደ ዪንቨርስቲ ቀድሞኝ ገብቶ ነበር። እኔም ወደሱ ዩንቨርስቲ ሄጄ ጠራውት... ብዙ ሰው ስለነበር ሻንጣዬን ይዞ ብቻችንን የምንሆንበት ቦታ ወሰደኝ። እጄን እንኳን መያዝ አልፈለገም ነበር። ሲያወራኝ በጣም ተለዋውጣል። ብቻ
" እወድሀለው! አሁን ስጠራህ ትመጣለህ ብዬ አላሰብኩም ነበር ምናምን እለዋለው። እያወራውት ትቶኝ ሊሄድ ነበር። ይዤ አስቆምኩትና " አትወደኝም ወይ? ብዬ ጠየኩት..." ከማንም ጋር መሆን አልፈልግም። አሁን ሁለታችንም የራሳችን ህይወት አለን ከዚ በኋላ እኔን ለማግኘት እንዳትመጪ " ነበር ያለኝ። ከዛ " የሆነ ሚስጥር ልንገርህ..." ብዬው ነበር ግን መልሶ ሳያየኝ እንኳን " ወደዶርምሽ ግቢ ብሎ ጥሎኝ ሄደ። በጣም እያለቀስኩ ነበር። ምንድን ነው እማ? " አለች ፊቷን ወደእናቷ መልሳ።
" ኸይር ነው የኔ ልጅ...ያለቀሽው ልትደሰቺ ነው። " አለቻት። " ህልም እንደፈቺው ነው " አይደል የሚባለው።
" ረዩ ግን ያውቃል? " አለቻት ተነስታ የክፍሏን መስኮት እየገለጠች።
" ምኑን እናቴ? "
" እንደዚ እንደምትወጂው ነዋ? በህልም ተለያየን ብለሽ እንደዚ የተንሰቀሰቅሽለት..." አምሪያ ፈገግ ብላ ተመልሳ ወደብርድ ልብሷ ገባች።
" ትምህርት የለም ብዬ ነው ዝም ያልኩሽ በይ ተነሽ ይበቃሻል..." ብላት ወጣች።

አምሪያ ግን ቶሎ አልተነሳችም። እዛው እንዳለች ከራሷ ጋር ማውራት ጀመረች።
" እንደዚ አይነት ህልም ያየውት ምን አልባት አሁን የተጣላነው እስከመጨረሻው ልንለያይ ይሆን እንዴ? ረዩ ለምን እንደዚ ጨከነ? ቆይ ምን ባደርገው ነው? ያ አላህ እባክህን አንተ አግራው! " እዛው ቁጭ ባለችበት በሀሳብ ተጓዘች። ከዚ በፊት ከረያን ጋር ስላሳለፈችው ጊዜ ወደኋላ ተመልሳ ማሰብ ጀመረች። አብረው እያጠኑ ስትሳሳት የሚመታት ፣ እሷ ስታጠፋ እሱ የሚቀጣላት ፣ ጠዋት ጠዋት እየተከራከሩ ወደትምህርት ቤት ሲሄዱ ፣ ስትታመም እንዴት እንደሚጨነቅ ፣ ከሳሊም ጋር ሲያያት የሚቀናው ነገር ...ሁሉም በሀሳቧ መተው እየተመለሱ የነበሩትን እንባዎቿን ድጋሚ ጠሯቸው። ረያን በጣም ናፍቋታል! እናቷ እንዳትሰማ አፏን በትራስ አፍና ተንሰቀሰቀች።

*

" እ አንቺ ልጅ ጥናት እንዴት ይዞሻል? " ከሰብሪን ጋር በስልክ እያወሩ ናቸው።
" ኧረ ባክሽ ምንም አልጠና ብሎኛል። አንቺ እያጠናሽ ነው? "
" ወይ ማጥናት...ከማሚ ጋር እቃ ልገዛ እየዞርኩ ነው። አንቺ ግን ስነስርዓት ያዢ...አርፈሽ አጥኚ..."
" ያልተነካ ግልግል ያውቃል የተባለው እውነት ነው...ታቂያለሽ ደብተሩን ስከፍተው ከረዩ ጋር አብረን ስናጠና ያለው ጊዜ ነው ትዝ የሚለኝ..." አለች ስለሱ ስታወራ አይኖቿ ቀድመው ለመመለስ ይዘጋጃሉ።
" አምሪዬ ግን ለምን አታወሪውም? "
" እያወቅሽ...መች ጊዜ ይሰጠኛል? እንደዚ ያደረገውን ጉዳይ እንድጠይቀው እንኳን መች ፈቀደልኝ እንዴት ብዬ ላዋራው? "
" እስኪ ዛሬ ቤት ሄደሽ ለማዋራት ሞክሪ። "
" እናቱ አለቻ...ስለዚ ጉዳይ እኮ ቤተሰቦቻችን ምንም አያውቁም ሰብሪ..."
" ለሱ መላ አይጠፋም..." ትንሽ ካሰበች በኋላ ንግግሯን ቀጠለች።
" ይኸውልሽ እናትሽ ቡና እንድታፈላና የረዩን እናት ቡና እንድትጠራት አድርጊ። ከዛ አንቺው ራስሽ ሄደሽ ጥሪያትና እሷ እናንተ ቤት ስትመጣ አንቺ እዛው ረያንን ብቻውን ታናግሪዋለሽ። " ሰብሪን በትንሽ ደቂቃ ውስጥ በጣም ምርጥ ሀሳብ ነበር ያመጣችው። አምሪም በሀሳቧ ተስማማች።

እንደተባባሉት አምሪያ ተነስታ ቡና ማቀራረብ ጀመረች።
" እንዴ ጥናት የለም እንዴ? " አለቻት እናቷ እሷ ልታፈላ መስሏት።
" ኧረ አጠናለሁ እማ...ትንሽ የከበደኝ ነገር ስላለ ከረዩ ጋር ልናጠና እሱ ጋር ልሄድ ስለሆነ ነው። አንቺ እንዳይደብርሽ ቡና አፍዪና የረዩን እናት እጠራልሻለው። "
" እ...እንደዛ ነው ነገሩ... " እናቷ ሙድ እየያዘች ቡናውን ለማፍላት ተነሳች። አባቷ ጉዳይ ገጥሞት በጠዋት ስለወጣ ፣ ሰሚር ደሞ አንዴ ስልክ ከያዘ ማንንም ስለማያይ እንዳይደብርሽ ያለቻት አሪፍ ምክንያት ሆኖላታል።

የተወሰነ ደብተርና መፅሀፏን ይዛ ወደባሏ ቤት መሄድ ጀመረች። ገና ቤቱ ጋር ሳትደርስ የረያን እናት ከግቢ ስትወጣ አየቻት። ሄዳ ሰላም ካለቻት በኋላ ቡና እንደተጠራች ነገረቻት።
" እኔም ቡና ለመግዛት ወደሱቅ እየሄድኩ ነበር...ገላገልሽኛ..." አለቻት ፈገግ እያለች። አምሪ የግቢውን በር አልፋ ወደውስጥ ገባች። ልቧ በጣም እየመታ ነበር... ከዚ በፊት ልታዋራው ስትሞክር እንዴት ይሆንባት እንደነበር ስታስታውስ አሁን ይበልጥ ፈራች።
" ልመለስ አልመለስ? " ከራሷ ጋር ግብግብ ፈጥራ ወደውስጥ የሚያስገባው በር ጋር ለደቂቃዎች ቆመች። በመጨረሻም ለመግባት ወስና በሩን ልትከፍተው ስትል የረያንን ድምፅ ከውስጥ ሰማች
" ወዬ...እሺ እሺ መጣሁ..." ብቻ ነበር ያለው። ሊወጣ እንደሆነ ስለገመተች እየሮጠች ወደጓሮ ሄደች።
እንዳለችውም ረያን ትንሽ ቆይቶ ወጣ።
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
ወዴት ሊሄድ እንደሆነ በጣም ማወቅ ፈልጋለች። ውስጧ ለምን " ሴት ጋር ነው የሚሄደው..." እንደሚላት አታውቅም። ብቻ ሳትፈልገው ተጠራጣሪ መሆን ጀምራለች። የያዘችውን ደብተርና መፅሀፍ አስቀምጣ ቀስ እያለች ከኋላው ተከትላው ወጣች።

በተደጋጋሚ ስልክ እያወራ ነበር የሚሄደው። አምሪ በትንሽ ርቀት ሆና መከተሏን ቀጥላለች። የሆነ ሰፈር ውስጥ ሲደርስ ቆሞ ስልክ ደወለ። ስልኩን እያወራ አንድ ወንድ ወደሱ ጋር መጥቶ ሰላም አለው። ማን እንደሆነ ለማወቅ ትንሽ ቀረብ አለች። ሚኪ ነበር።

በአጉል ጥርጣሬዋ እየተናደደች ፣ ጥርጣሬዋ ደሞ እውነት ስላልሆነ ደስ እያላት ወደቤት ተመለሰች።
በዚ ምክንያት ዛሬም ረያንን ሳታናግረው ቀረች።

*

የኢንትራንስ ፈተና ሊፈተኑ 2 ሳምንት ብቻ ነበር የቀራቸው። ትምህርት ስለተዘጋ እንደበፊቱ ረያንን አታየውም። ምን እያሰበ እንደሆነ ግራ ገብቷታል። እስካሁን ምንም ያላት ነገር የለም።

ዛሬም ከእንቅልፏ አርፍዳ ነበር የተነሳችው። ሰላት ስላልነበራት ነው እስከ ጠዋቱ 4 ሰአት የተኛችው።ተነስታ ከተጣጠበች በኋላ ለሷ የተቀመጠላትን ቁርስ አሙቃ በላች። እናቷ በጠዋቱ የቤቱን ስራ ጨራርሳ ስለነበርና የምትሰራው ስራ ስለሌለ ተመልሳ ወደክፍሏ ገባች።

ሀሳቧን ሰብስባ ለማጥናት እየታገለች ነው። በመሀል ስልኳ ጠራ። ስታየው በጣም ደስ አላት። ረያን ነበር የደወለው። ቶሎ ብላ አነሳችው።
" አንድ ጊዜ ላናግርሽ እፈልጋለው ከተመቸሽ ቤት ነይ..." ብሏት ስልኩን ዘጋው። በአነጋገሩ ብትናደድም ቢያንስ ላዋራሽ ስላላት ግን በጣም ደስ ብሏታል። ልብሷን ቀይራ እየሮጠች ወጣች።

የነሱ ቤት ጋር ደርሳ ልታንኳኳ ስትል በሩ ቀድሞውኑ ተከፍቶ ነበር የጠበቃት። እየተጣደፈች ወደሳሎን ገባች።
ክፍሉ በፊኛዎች፣ በተለያዩ አበባዎችና በመብራቶች ደምቋል። አምሪያ በጣም ግራ መጋባት ጀመረች። ወድያው ረያን ከመኝታ ክፍሉ ወጥቶ ወደሷ ጋር መጣ። በጣም አምሮበታል! ሳታየው ለብዙ ጊዜ ስለቆየች ናፍቆቱ ይሆን ባታውቀውም ከበፊቱ ይበልጥ ውበቱ ጨምሮ ነበር የታያት።ገና ስታየው ልቧን ደስታ ይወረው ጀመር።

አጠገቧ መጥቶ እንድትቀመጥ ከጋበዛት በኋላ እሱ እግሯ ጋር ተንበርክኮ ቁጭ አለ።
" አምሪዬ በመጀመሪያ በጣም ይቅርታ አድርጊልኝ! እንደዚ ልሆን አይገባም ነበር! " አላት።
የምትለው ግራ ገብቷት ዝም ብላ አይን አይኑን ትመለከተዋለች።
" አቃለሁ በጣም እንዳስቀየምኩሽ ግን በአላህ ዝም አትበዪኝ... በቃ የፈለግሽውን ነገር አርጊኝ እና ይቅርታዬን ተቀበዪኝ...እ ሚስቴ? " ይቅርታዋን ፍለጋ ይቅለሰለስ ጀመር።
" ቢያንስ እንደዚ የሆንክበትን ምክንያት ንገረኝ..." አለችው።
ስለፎቶውና ስለተፈጠረው ነገር ነገራትና የተላከለትን ፎቶ አሳያት። አምሪ በጣም ደነገጠች።
" አዎ የዛን ቀን አንተን ከማግኘቴ በፊት ሳሊምን አግኝቼው ነበር። ግን እኮ አልሳመኝም..." የተፈጠረውን ነገር ለማስታወስ ሞከረች።
" አውቃለው የኔ ውድ እንዳልሳመሽ...እኔና አንቺን ለማጣላት የሞከሩትን ልጆች ሁሉንም ነገር ደርሼበታለሁ። " አላት።
አምሪ ይባስ ግራ ተጋባች። ይሄን ያህል ደስታዋን ሊያደፈርስ የሚችል ጠላት ይኖረኛል ብላ አስባ አታውቅም ነበር።
" እና ማነው እንደዚ ያደረገው? " አለችው መልሱን በጉጉት እየጠበቀች።

#ክፍል_አስራአራት (⓮) ይቀጥላል...
✿❯────「✿」────❮
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
​​💌🌹

💗 . . .
#እምነት . . . 💖

በሁለት ሰዎች መሀከል ያለ ግንኙነት ሊቆምም ሆነ ሊጠነክር ሚችለው ሁለቱ እርስ በእርስ ባላቸው መተማመን ተመስርቶ ነው፡፡ እምነት የቃል እዳ ስትሆን ቃል የነብስ እዳ ነች፡፡ ቃላቸውን መወጣት ማይችሉ ሰዎች ቃል በገቡለት ሰው ልብ ውስጥ ያላቸው እምነት ቃላቸውን ባጠፉ ቁጥር እየተሸረሸረ ይመጣል፡፡ቃል ሲታጠፍ እምነት ሲሸረሸር ወዳጅነት እየራቀ ይሄዳል፡፡
ሰዎች በቃላቸው ሲገኙ በሰው ልብ ውስጥ እምነትን እየፈጠሩ ይሄዳሉ፡፡ እምነት እየጠነከረ ሲመጣ ወዳጅነት እየጠበቀ ይሄዳል፡፡

💕 መልካም አዳር💕

👇🀄️🀄️ሉን 👇

🌹....🌹
@ethioleboled 🌹....🌹

💬ʝσιи & Ѕнαяє💬
Selam family ✨️

Bzi selahonku nw inam ezi channel lay abrogn masrat mefalg sew kala comment tsafulgn

Melkam msht
2024/11/14 12:04:20
Back to Top
HTML Embed Code: