Telegram Web Link
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
●●●ነጠብጣብ●●●♥️

            💞ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ቀርቶታል

                          
#ክፍል_17


ራሴን አረጋጋሁ እና ኢክሩ ልታናደኝ ፈልጋ እንጂ እንደዚህ የምታደርግ ልጅ እንዳልሆነች ብዙ ምክንያቶችን እየሰጠሁ ራሴን አሳመንኩት።
እንደዉም እኔ እወድሻለሁ ስላት አይኗን ወደ ሰማይ እየሰቀለች "ፈዉዛኔ የኔ ድመት አንተ ትወደኛለህ። እኔ ላንተ ያለኝ ፍቅር ግን ካንተ በጣኣኣኣም ይልቃል።" ያለችዉን አስታወስኩ።
ኢክሩ በሁለት ወር ዉስጥ ይሄን ፍቅሯን ከልቧ አስወጥታ ከነገስኩበት የልቧ ዙፋን ላይ ሌላ ሰዉ እንደማታስቀምጥ ለራሴ ነገርኩት።
"ምንም ችግር የለዉም። መብትሽ ነዉ!" ብዬ መለስኩላት። አልተናደድኩልሽም እንደማለት ነበር ያሰብኩት።
እኔ ፍቅረኛ ይዤ ከሆነ ጠየቀችኝ እንዳልያዝኩ ነገርኳት።
.
ወደ ማታ ላይ ብሩኬን አግኝቼ የተፈጠረዉን ነገር ነገርኩት። ኢክሩ ፍቅረኛ ይዛ ከሆነም ሁለቱን ለመነጣጠል ስል የፍቅር ግንኙነት ከሷ ጋር ልጀምር እንደምችል ነገርኩት። ማንም እንደኔ ሊያስብላት አይችልም ብዬ አምናለሁ። ቢያንስ ከኔ ጋር ከሆነች ዝሙት ላይ አትወድቅም። ሌላ ወንድ ኢኩ ላይ ስሜቱን ሲያስታግስ መመልከት አልፈልግም። ኢኩ ንግስት ሆና ባል ስታነግስ ነዉ መመልከት የምሻዉ።
አንገቴን አቀርቅሬ "ብሩኬ ኢኩ የእዉነት የፍቅር ግንኙነት ጀምራ ከሆነ እኔ ኢኩን እና ልጁን ለማጣላት ከሷ ጋር የፍቅር ግንኙነት እስከመቀጠል ድረስ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ።" አልኩት
ብሩኬ እንደመቆጣት እያለ "በቃ ተዋት የራሷን ህይወት ትኑርበት!!" አለኝ
ሳግ እየተናነቀኝ "ብሩኬ እኔ እኮ እንድታገባ እንጂ ከማንም ጋር እንድትንዘላዘል አይደለም የተዉኳት!!" አልኩት።
"በቃ ተዋት አይመለከትህም!!" አለኝ አሁንም ቆጣ እንዳለ ነዉ።
ብሩኬ ይሄን አቋሜን ስላልደገፈልኝ ተበሳጨሁ። ከዚህ በኋላ የምወስዳቸዉን እርምጃዎች እሱን ሳላማክር ለመዉሰድ ወሰንኩ።
.
ፊርደዉስ ክረምቱን በተደጋጋሚ እየደወለች እንድንገናኝ ትጠይቀኛለች። እኔ ግን ዉርርዷን ልትፈፅምብኝ እንደሆነ ስለማስብ ላገኛት ፈቃደኛ አልሆን አልኳት። እዉነት ለመናገር በኔና በሷ መካከል ሀይማኖት እና ማህበራዊ ስርዓታችን ልቅ መሳሳምን ባያወግዝ ኖሮ እኔ ነበርኩ ከንፈሯ እንደ ኢክሩ እስኪያብጥ የምስማት!! ግን ሰዉ እንደመሆኔ እንደ እንስሳ ማሰብ የለብኝም። ስጋዬ ይፈልጋል አልዋሽም!! ግን ፈጣሪዬን ማስቆጣት አልፈልግም። እሱን ካስቆጣሁ አንዷን ፊርደዉስን አግኝቼ ጌታዬን ላጣ እችላለሁ። እሱን ባስደስት ግን ጌታዬ የፊርደዉስ አይነት ሴቶች ካዝና በእጁ ነዉ።
አንድ ቀን ሀሙስ እለት ፊርደዉስ ደዉላ የጓደኛቸዉን ልደት ስለሚያከብሩ እንድገኝ ጠየቀችኝ። ሙስሊም ስለሆንኩ ልደት እንደማላከብር ነገርኳት።
"ኧረ ፈዉዛኔ ይሄን ያህልማ አታካብደዉ!!" አለችኝ።
በሷ ቤት አክርሬባት ሞታለች።
"ፊርደዉስ እኔ ሙዴ እንደዚህ ነዉ!! እንደየሙዳችን ብንሆን ይሻላል ከምንከራከር!" አልኳት
"እሺ በጣም ጥሩ!! በርዝደይ ፓርቲዉ ላይ እኔም አልገኝም። ካንተ ጋር መገናኘት እፈልጋለሁ።" አለችኝ።
ተስማምተን ቀጠሮ ያዝን።
.
ፊርደዉስ ስትስቅ ጉንጮቿ በጣም ይሰረጉዳሉ። በጣም ታምራለች። ሳር ቤት አካባቢ ተገናኘን። መኪና ይዛ ነበር የመጣችዉ። ገቢና ገብቼ ከዚህ በፊት ገብቼበት ወደማላዉቀዉ መናፈሻ ይዛኝ ሄደች። ቦታዉ በጣም ቆንጆ ነዉ። መኪናዋን ቦታ አስይዛ ካቆመችዉ በኋላ ከመኪናዉ ወርደን ዉቡ የሳር መናፈሻ ላይ የተቀመጡት ወንበሮች ላይ ተቀመጥን።
"ፈዉዛኔ እኔ ማንንም ወንድ እንዳንተ ተለማምጬ አላዉቅም። ይህን ሁሉ የማደርገዉ እንድስምህ ስለተወራረድኩ ብቻ መስሎህ ከሆነ ተሳስተሀል! አንተ የራስህ አቋም አለህ። እንቢ ማለት መቻልን አስተምረኸኛል። እኔ ደግሞ አላማ አለኝ። ይሄን አላማዬን ለማሳካት ካንተ የተሻለ አማካሪ የማገኝ አይመስለኝም።" አለችና በረዥሙ ተነፈሰች
ፊርደዉስ የኮምፒዩተር እዉቀቷ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ከነገረችኝ እቅዶቿ ተረዳሁ። ያለማቋረጥ ለአንድ ሰዓት እቅዷን ነገረችኝ። አሁን ፊርደዉስን በጣም አከበርኳት። በምችለዉ ሁሉ ላግዛትም ቃል ገባሁላት።

.
የኢድ አል አድሀ ማለትም የሀጅ ስነ ስርዓት እንዳለቀ ያለዉ የኢድ በዓል ደረሰ። ሁልጊዜም እንደማደርገዉ በስም ቅደም ተከተል ሰዎች ጋር እየደወልኩ እንኳን አደረሳችሁ እያልኩ በኢ ተርታ ያሉት ጋር ደርሼ ኢክራም ጋር ደወልኩ።
የዛሬን አያድርገዉና ሌላ ጊዜ መጀመሪያ እሷ ጋር ደዉዬ ነበር ቀሪዎቹ ጋር በስም ቅደም ተከተላቸዉ የምደዉለዉ።
አነሳችዉ "ኢኩዬ እንኳን አደረሰሽ!!" አልኳት።
"እ ንኳን አብሮ አደረሰን!" አለችኝ እየተንጠባረረች
"በዓል እንዴት ነዉ?" አልኳት
"ጥሩ ነዉ አለችኝ" በአጭሩ።
በመልሷ በጣም ተበሳጨሁ በስርዓቱ ተሰናበትኳትና ስልኩን ዘጋሁት። እኔ የስነ አእምሮ ተማሪ ነኝ ኢክራምን እንዲህ ያንጠባረራት ጉዳይ እንዳለ ተገለፀልኝ። አዎ ኢክራም ፍቅረኛ ይዛለች። ካንተ ሌላ ላፈር ስትለኝ የነበረችዉ ኢኩ በሁለት ወር ዉስጥ ሌላ ሰዉ ለምዳለች። ሰዉዬዉ ማን እንደሆነ ማወቅ ፈለግኩ። ኢክራምን በቅርብ ርቀት መሰለል ይኖርብኛል።
ትኩረቴን ሙሉ ኢክራም ላይ አደረግኩ። አሁን ስላለችበት ሁኔታ በአምስት ቀናት ዉስጥ ሙሉ መረጃ ሰበሰብኩ። አዎን የኢክራም ህይወት ባልገመትኳቸዉ መንገዶች ሁላ ሳይቀር ተለዉጧል። ማመን የማልችላቸዉን መረጃዎች አገኘሁ።...

  
ብዙ ሰዎች ኢክሩ በፍፁም ጥፋተኛ እንዳልሆነች ነዉ የሚያስቡት። "ሳይቸግርህ ጭረሀት" "አንተ ነህ የተዉካት!!" ምናምን ይሉኛል። መተዉ ምን ማለት ነዉ? እኔ እኮ ኢክሩን በጊዜዉ ለማግባት ስለማልችል እንድታገባ ብዬ ነበር የተለየኋት። አደራ ያልኩት እኮ ፈጣሪዬን ነበር። እኔ እሷን የመናፈቅ እሳቴን አፍኜ ይብቃን ስላት ለሷ የወደፊት ህይወት ማማር እየተሰዋሁ እንደነበር ለምን አይገባቸዉም? ተዋት ይላሉ እንዴ? አቅሜን አዉቄ ለፈጣሪ አሳልፌ በሰጠሁ ገፋት ይላሉ እንዴ? አስመሳይ ሁላ!! ለነገሩ የነሱ ወሬ ለኔ ምንም ነዉ። ያመንኩበትን ነገር እንጂ አላደርግም! ስሜት ያወረዉ ትዉልድ የሚታይ ድርጊት እንጂ የታፈነ ስሜት አይገባዉም። ኢክራም እንደተሰዋሁላት እንዲገባት ከፎቅ ላይ ራሴን መፈጥፈጥ አይጠበቅብኝም። ማንም ሳያዉቅ በልቤ እንደታፈንኩ እኖራለሁ። በኔ ዝምታ ዉስጥ ብዙ ትርጉም ነበር። እሷን በመተዌ ያሳለፍኩትን ስቃይ እኔ ነኝ የማዉቀዉ። እስከዛሬ ጠረኗ የማይረሳኝ ሰዉ እኮ ነኝ!! ከሷ በኋላ ማንንም ያላየሁ!! አዎ የሱመያን የድምፅ መስረቅረቅ አድንቄያለሁ ፣ የፊርደዉስን ዉበት አሞግሻለሁ ግን አንዳቸዉንም ከምላሴ አሳልፌ ልቤ ዉስጥ አላስገባሁም። በሁሉም ሴቶች ዉስጥ የምትታየኝ ኢኩዬ ነበረች። ሁሌም ቃሌን አስታዉሳለሁ። ስንለያይ ለራሴ የገባሁትን ቃል!! የማግባት የስነ ልቦና እና የገንዘብ አቅም ሲኖረኝ መጀመሪያ ኢኩዬን ፈልጌ ካላገባች ላገባት ለራሴ የገባሁትን ቃል!! ተዋት ይላሉ እንዴ? ለሷ አልጋዉን አደላድዬ እኔ መሬት ላይ በተኛሁ ገፋት ይላሉ እንዴ? ወረኛ ሁላ!! ሲጀመር እነሱ የመዉደድን ልክ የወደዱትን የራስ ከማድረግ አሻግረዉ መመልከት አልቻሉም። እኔ ዉዴታዬ በዝቶ ለኢክሩ ባል ተመኘሁላት!! ኢክሩ ንግስት እንድትሆን ከነክብሯ እንድትለየኝ አደረግኩ። ጌታዬን አስደስቻለሁ እሷ የፈለገችዉን ትበል ግድ የለም። እንደኔ ያሰበላት፣ ወደፊትም የሚያስብላት ሰዉ ግን የሚኖር አይመስለኝም።

እንዳተኙ 4 ሰአት ላይ ቀጣዩን ክፍል ይጠብቁን ነጠብጣብ ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል

እስከዛ Like share
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️

            💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞

                         
#ክፍል_18


ኢክራም ፍቅረኛ ይዣለሁ ያለችኝ ልታናደኝ ፈልጋ መስሎኝ ነበር። የኢድ ቀን ስደዉልላት በንግግሯ ዉስጥ የሰማሁት ኩራት እና ንቀት ግን ኢኩ የእዉነት ፍቅረኛ ይዛለች ወደሚለዉ ድምዳሜ ስላደረሰኝ ነበር ለአምስት ቀናት ስለሷ መረጃ ያሰባሰብኩት።
ኢክራም በህይወቷ ላይ ብዙ ለዉጦች አስተናግዳለች።

ያቺ የጅልባቧን እጄታ ይዛ ጅልባቧን በጥርሷ ነክሳ እያየችኝ ስትስቅ ትዝታዋ የማይረሳኝ ኢክራም ጅልባቧን አሽቀንጥራ ጥላ የቱርክ ፋሽን ማራገፊያ ሆናለች። ያቺ ወንድ የማትጨብጠዋ ኢኩ ማንም እንዳሻዉ የሚያቅፋት ተራ ሴት ሆናለች።
ኀሌላዉ እነ ኢክሩ ሰፈር ቀይረዉ እነ ሄኖክ ሰፈር ገብተዋል። እናቷ አግብታለች።
በጣም ቀፈፈኝ!! ለማንም ያላረከስኩትን እኔነቴን ያረከስኩላት ሴት ከማንም ጋር እየተንዘላዘለች ነዉ። ከቻፒስቲክ ያለፈ የማትቀባዋ ኢክራም ሜካፕ ይሉት ዱቄት ማራገፊያ ሆናለች አሉኝ።በዚህ ሰዓት አጠገቧ ሆኜ ልረዳት ባለመቻሌ በጣም ተሰማኝ። ሱመያን በቻለችዉ ኢክሩ የተሻለ ሰዉ እንድትሆን እንድትረዳት ተማፀንኳት።

ሱመያ ነገሩ ለጊዜዉ እንደሚከብድ ነገረችኝ። ከሰፈሩ መራራቅ ባሻገር ለነሱመያ አልተበላሸሁም ትላቸዉ ስለነበር በግልፅ እስከሚያገኟት መጋፈጡ ከብዷቸዋል።
ኢክሩን ፌስቡክ ላይ አንዳንድ ነገሮችን አወራኋት ፍቅረኛ የሚባለዉም ነገር ቢቀርባት እንደሚሻል መከርኳት።

ሁሉም ወንድ እንደኔ ነዉ ብዬ አላምንም!! ኢክራም ላይ ማመን የምችለዉ ወንድ እኔን ራሴን ብቻ ነዉ። ለምክሩ አመስግናኝ የራሷን መስመር መከተል ጀመረች። እኔ ግን አሁን ላይ ማወቅ የምፈልገዉ ኢክሩዬን እንደዚህ ያዘቀጣትን ፍቅረኛ ተብዬ ነዉ። ግን በየት በኩል? እንዴት ልወቀዉ? ለጊዜዉ ጭንቀቴን በስልክ ለረዊና ሁሉንም ነገር እየተነፈስኩላት አስታግስ ነበር።
.
የሁለተኛ አመት ተማሪ ሆነን አራተኛዉ ወር ተጀምሯል።ረዊናም ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እየተማረች ነዉ።
ብሩኬ የግል ካምፓስ አካዉንቲንግ ተመዝግቦ እየተማረ ነዉ። ግን ትምህርት ቤቱ የሱሰኞች እና የሴሰኞች መናኸሪያ ስለነበር ብሩኬ አይኔ እያየ ጫት ሙዱ ሆነ። ስለሴቶች አዉርቶ አይጠግብም!!
"ፈዉዛኔ የእዉነት ሴቶች ርካሽ ናቸዉ!አለኝ አንድ ቀን አብረን ተቀምጠን
"እንዴት ብሩኬ?"አልኩት በጅምላ ሲፈጃቸዉ ደንግጬ
"ፈዉዛኔ እኛ ግቢ ያሉት ሴቶች እንዴት
ሱሰኛ እንደሆኑ ብታይ፣ ደሞ ሴክስ በቃ እንደሰላምታ ነዉ!" አለኝ።

ዝም አልኩት!በንግግሩ ዉስጥ ተግባሩን እየኮነነዉ ቢመስልም እንደወደደዉ ተረድቻለሁ ሴት ብቻዋን እንዴት ትረክሳለች?አብሯት የሚንፈራገጥ ወንድ ግዴታ ያስፈልጋል። ይሄ ማለት ደግሞ ሁለቱም ረክሰዋል ማለት ነዉ። ወይስ ወንድ የማይረክሰዉ ሲጀመርም ክብር ስለሌለዉ ነዉ?እኔ የነብሩኬ ሎጂክ አይገባኝም።ነገር ግን የብሩኬ አካሄድ እያማረኝ ስላልሆነ አንድ ቀን ከትምህርት ስመለስ ቁጭ አድርጌ እንደ ከብት እንዳይነዳ እና እንቢ ማለት መቻል እንዳለበት መከርኩት። ነገር ግን የነብሩኬ ትምህርት ቤት መዓበል ብሩኬን ወደ ጠጪነት መደብ ወረወረዉ!! እኔ እንዳልሰማ ይጠነቀቃል።ይቅማል፣ይጠጣል!

በቀን እንደቁምነገር ከጓደኞቹ ጋር መጠጥ ቤት ይዉላል። ብሩኬን ለማዳን አልቻልኩም!! በሰዓቱ ትኩረቴን ሙሉ በሙሉ ትምህርቴ ላይ አድርጌ ነበር።ዉጤቴን ለማሻሻል ታላቅ ትግል ላይ ነበርኩኝ።
.
ጁምዓ(አርብ)ቀን ፊርደዉስ ከትምህርት ስወጣ ልታገኘኝ እንደምትፈልግ ነገረችኝ። ተገናኝተን ከሷ እቅድ ጋር በተያያዘ ብዙ አወራን። የተቀመጥንበት ካፌ ዉስጥ ከመቀመጫዋ ተነስታ ወንበሯን እየጎተተች ከጎኔ ተቀመጠች። ፊርደዉስ ሽቶ አልተቀባችም። አጠገቤ እንደተቀመጠች

"ፈዊዬ የሆነ ነገር በህይወትህ ዉስጥ አልተፈጠረም? እስኪ ካንተም ልስማ ንገረኝ!" አለችኝ።
የኔና የኢኩን ታሪክ እስኪሰለቻት ተረኩላት።አሁን ላይ ፍቅረኛ ተብዬዉ ማን እንደሆነ ማወቅ እንደምፈልግ እና ማወቅ እንዳልቻልኩ ነገርኳት።
ፊርደዉስ ከአይኖቿ እንባ እየፈሰሰ "ፈዊ በጣም ጥሩ ሰዉ ነህ። እሷ ብትረዳዉም ባትረዳዉም አንተ ለህሊናህ ታምነሀል!"አለችኝ።

ወዲያዉ እንባዋን እየጠረገች "ፈዉዛኔ እኔ በቀላሉ ፍቅረኛዋ ማን እንደሆነ እንድታዉቅ እረዳሀለዉ!" አለችኝ።
አይኗን እያየሁ "እንዴት?"አልኳት።
ፊርደዉስ ወደኔ ጠጋ እያለች
"ፈዉዛኔ ኢክራም የፌስቡክ አካዉንት እንዳላት እርግጠኛ ነኝ። ፍቅረኛ ተብዬዉም አይ ቲንክ ይኖረዋል። እና በፌስቡክ መጀናጀናቸዉ ኢቲ ኢዝ ኦቪየስ!! እኔ የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ተማሪ እንደመሆኔ የፌስቡክ አካዉንት ለመጥለፍ የሚያስችል ማስፈንጠሪያ(Pheshing link) እሰራልሀለሁ።

አንተ በቅርብ እሷ በምታዉቀዉ ስልክ ቫይበር ላይ ሊንኩን ልከህ የሷ ፎቶ ስላለዉ እንድታየዉ ትነግራታለህ። ታዲያ በራስህ ስልክ ሳይሆን እሷ በምታዉቀዉ የሌላ ሰዉ ስልክ መሆን አለበት።እሷ ሊንኩን ስትከፍተዉ ለመግባት ኢሜይል እና ፓስወርዷን እንድታስገባ ይጠይቃታል። እሷ ፓስወርዷንና ኢሜይሏን ስታስገባ ከማስፈንጠሪያዉ ጋር በተያያዘዉ የጂሜይል አካዉንት እኛ ፓስወርዱን እና ኢሜይሉን እናገኛለን። የዛኔ አካዉንቷ ላይ በነፃነት ገብተህ ጉዷን መበርበርም ሆነ ፍቅረኛዋን ማወቅ ትችላለህ!ክሊር?" አለችኝ።

በጣም ግልፅ ነዉ። የኔ እብድ ምናለ እስከአሁን በነገርኩሽ ኖሮ!" አልኳት እንደ ህፃን ልጅ እየቦረቅኩኝ።
.
የሰዉን የግል የህይወት መስመር ተላልፎ የግል መረጃዎቹን መበርበር አግባብ እንዳልሆነ አዉቃለሁ።

ግን ኢክሩ ከማን ጋር እየተንዘላዘለች እንደሆነ ለማወቅ እና ዉስጤ ላይ የሚሰማኝን መረበሽ ለማስወገድ ያለኝ የመጨረሻ መንገድ ስለሆነ የኢክሩን የሚስጥር ጓዳ ለመፈተሽ እና የግለኝነት መብቷን ለመግፈፍ ወሰንኩ።
ፊርደዉስ በሶስት ቀናት ዉስጥ የፌስቡክ ፓስወርድ መስረቂያ ሊንኩን (Pheshing link) ሰርታ ላከችልኝ። አሁን ለኢክራም ሊንኩን ልኮ እንድትከፍተዉ ለማድረግ አንድ የምታዉቀዉ ሰዉ ስልክ ያስፈልጋል። አዎ አዩብ!

አዩብን ስልኩን እንዲያዉሰኝ ማድረግ እችላለሁ!! የሪም ፍቅረኛ አዩብ!! ለኢክራምም ቅርብ ስለሆነ በሱ ስልክ አታልዬ ሊንኩን መላክና እንድትከፍተዉ ማድረግ እችላለሁ።

ቅዳሜ ማታ ላይ አዩብን መስጂድ አገኘሁት። የዛን ቀን ማታ ላይ ስልኩ እኔ ጋር እንዲያድር ጠየቅኩት። እሱም የዛን ቀን ይፈልገዉ ስላልነበር ለምን እንኳ ሳይለኝ ጠዋት ለፈጅር ሰላት(ለንጋት ስግደት) እንዳመጣለት ነግሮኝ ስልኩን ሰጥቶኝ ሄደ።

ገና መንገድ ላይ ሆኜ የአዩብን ቫይበር ከፈትኩት ኢክራም ኦን ላየን አለች። ሰላም ብያት በቅርቡ ስላገባች አንድ ጓደኛቸዉ አወራኋት።እሷ ከአዩብ ጋር እንደምታወራ ነዉ እያሰበች ያለችዉ። አሁን ለሰርጉ የተነሱትን ፎቶ እንዳየሁት ነግሬያት ማስፈንጠሪያዉን ተጭና እንድታይ ነግሬ የፌስቡክ ፓስዎርድ መስረቂያ ሊንክ (Pheshing link)ላኩላት። ይመስለኛል አሁን ፓስወርድና ኢሜይሏን አስገብታለች።

አሁን ከመስረቂያ ሊንኩ ጋር በተያያዘዉ ጂሜይል አካዉንት ሁሉም መረጃ ፊርደዉስ እጅ ላይ ይገባል።
ወዲያዉ ለፊርደዉስ ያደረግኩትን በቴክስት ሚሴጅ ነገርኳት። እሷም የጂሜይል አካዉንቱን ቼክ አድርጋ መረጃዉ እጃችን ላይ መዉደቁን አበሰረችኝ። በነጋታዉ ተገናኝተን ጉዱን ለማየት ተቀጣጠርን።...


ነጠብጣብ ከ ጥቂት ደቂቃ በኋላ ይጠብቁን በቃላችን መሰረት ዛሬ ይጠናቀቃል ስላልን ቃላችንን ለማክበር ከደቃዎች በኋለ ፍፃሜውን እንሰጠዋለን እናተም Like በማረግ አብሮነታችሁን አሳዩኝ
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
እሱም የቀድሞ ፍቅረኛዉን የሪሀናን ጓደኛ እና የአስር አመታት ጓደኛዉን የእኔን የትዳር ቅዠት ሲያማግጥ ህሊናዉ እንዴት ዝም አለዉ? ደግሞ እኮ ቃል በቃል "ኢክሩ እንድታገባ እንጂ ከማንም ወንድ ጋር እንድትንዘላዘል አይደለም የተዉኳት!" ብዬዋለሁ።

አደራ ብዬዉም ነበር! ጌታዬ ሆይ በከለከልከኝ መንገድ ላይ ተጉዤ የነገድኩት ንግድ ኪሳራን እንጂ አላተረፈልኝም!
.
ፊርደዉስ ቁርሱን ሰርታ አቀራርባ እንድንበላ ልትጠራኝ ስትመጣ አልጋዉ ላይ ተዘርሬያለሁ። ከአይኔ እንባ ይጎርፋል። እንሰቀሰቃለሁ።
"ፈዉዛኔ ምን ሆንክብኝ?" አለች እየተንደረደረች መጥታ አንገቴን ቀና እያደረገች።

በጣቶቼ ላፕቶፑን ጠቆምኳት። ሄዳ አነበበችዉ። ፊቷ ደም እንደለበሰ ወደኔ ዞራ "ብሩክ አንተን ከዳህ?" አለችኝ ስለ ብሩክ ታዉቅ ነበር።
ፊርደዉስ ከኔ በላይ መበሳጨት ጀመረች።

"ለኢክራም እኮ መልአክ ነበርክ ፈዊ! ምላሿ ይሄ ነዉ?" አለችኝ ንዴቷ ይበልጡኑ እየተቀጣጠለ።
አልጋዉ ላይ ከወገቤ ቀና ብዬ ተስተካክዬ እየተቀመጥኩ "ብዙ ጊዜ ያለመድሽዉ ዉሻ ነዉ የሚነክስሽ!" አልኳት።

"ፈዊ ኢክሩን ቆንጆ ቅጣት ልትቀጣት ይገባል!" አለች ፊርደዉስ ግድግዳዉን እየደበደበች
እንደ እብድ ጮክ ብዬ እየሳቅኩ "ኢክራም እኮ ቅጣት አያስፈልጋትም እኔን ከድታ ብሩኬ ላይ የወደቀች ቀን ራሷን ቀጥታለች። ንፁህ ልቤን ረግጣ ፊልም ላይ ስትመለከተዉ የኖረችዉን ዝቅጠት ለመተግበር ስትሞክር እና ከቅዱሳን ተራ ስትወጣ ያኔ ራሷን ቀጥታለች። እኔ መቅጣት አይጠበቅብኝም።

የሚታዘንላት ለንግስትነት የታጨች ዉብ ከመሆን ማንም እንዳሻዉ የሚጨልፋት ርካሽ መሆንን ስትመርጥ ያኔ ራሷን ቀጥታለች።" ንግግሬ ሲያልቅ ሰዉነቴ መንዘፍዘፍ ጀመረ። እየተንሰቀሰቅኩ አለቀስኩ። በህይወቴ እንዲህ ያለቀስኩባቸዉ ቀናት ዛሬ እና ኢክሩ ልታገባ ስትል ናቸዉ። ሁለቱም በኢክሩ ምክንያት! ደካማ ጎኔ ሴት ናት! ከሴት ደግሞ ኢክራም!

ፊርደዉስ ለቅሶዬ ሲበረታ አልጋዉ ላይ ከጎኔ ቁጭ ብላ ማባበል ጀመረች። በእጆቿ እንባዬን ጠረገችልኝ። ደንዝዣለሁ። ብደበደብም የሚሰማኝ አይመስለኝም። ፊርደዉስ እጆቿን ወደ አንገቴ ወሰደቻቸዉ። ከንፈሬ ላይ ተለጠፈች።

እኔ አያታለሁ ላስቆማት አልቻልኩም ደንዝዣለሁ! አይኔ እያየ ስልኳን አዉጥታ ከንፈሬ ላይ እንደተጣበቀች ሰልፊ ፎቶ አነሳች። ፊርደዉስ ዉርርዷን ፈፀመችብኝ። አደነቅኳት። ምንም የስነ አእምሮ ምሁር ብትሆን ሴት ልጅን ተንኮል አትበልጣትም። ዛሬ ካፌ ሳይሆን ቤት እንድንገናኝ ያደረገችዉ አጋጣሚዉን ለመጠቀም ብላ ነበር። በንፁህ አእምሮ ብሆን ኖሮ ሁሉም ይገባኝ ነበር። ግን የኢክራምን ጉድ ለማየት መጓጓቴን ፊርዱ ተጠቀመችበት። ፊርዱ ባደረገችዉ ነገር ምንም አልተቀየምኳትም። እልህ ተያይዘን ነበር! እሷ አሸነፈች አለቀ!
አእምሮዬ ሲረጋጋ ፊርዱን በአክብሮት እንድታቆም ጠየቅኳት። ወዲያዉ አቆመች። አየኋት ቆንጆ ናት! ከኢክራምም የበለጠች ቆንጆ! ግን በሰዓቱ በፍፁም ስለሴት ማሰብ ስላልፈለግኩ ትቻት ወደ ሳሎን ሄድኩ። ፊርዱ የሰራችዉ ቁርስ ላይ እልሄን ተወጣሁበት! ፊርዱም መጥታ አብረን በልተን ተያይዘን ከቤቱ ወጣን!
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
.              ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️

            💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞

                   
#የመጨረሻው_ክፍል

...🖊ፊርደዉስ የተሰማኝን መሰበር ስለተረዳችዉ ያን ሰሞን ከጎኔ አትጠፋም ነበር። ትምህርት እየቀረች ሁላ እኔ ትምህርት የሌሉኝን ሰዓቶች አብራኝ ታሳልፋለች። የኢክራም መንፈስ እየለቀቀኝ ነዉ መሰል ግጥም ፃፍኩ! ለፊርዱ አነበብኩላት

"ፀሀዩ ጠቋቁሮ ፣ ሰማይ ጠል ለበሰ፣
የክህደትሽ ክፋት ብዕሬን ነቅንቆ ጉድሽን አዳረሰ።
ዱላ አልማዘዝም ከድታኛለች ብዬ፣
እችልበታለሁ በብዕር መቅጣቱን በፍቅር አባብዬ"
.
እኔ ከጀርባዬ ሲሰራ የነበረዉን ድራማ እንዳወቅኩ ብሩኬም ሆነ ኢክራም እንዲያዉቁ አልፈለግኩም። ትንሽ ጊዜ ብሩኬ እና ኢክራም ላይ መዝናናት ፈለግኩ። ብሩኬን እንደድሮዉ በስርዓቱ አገኘዋለሁ! ቤቱ ሳይቀር እየሄድኩ አብሬዉ አሳልፋለሁ። የማዉቃቸዉን ነገሮች እጠይቀዋለሁ፣በዉሸቱ እዝናናለሁ። ኢክራምን ፌስቡክ ላይ እንደድሮዉ አወራታለሁ።

ልክ ምንም እንዳልተፈጠረ! በነገራችን ላይ ፊርዱ የኢክራምን የፌስቡክ ፓስወርድ አሳይታኝ ስቄ አላባራሁም። "ብሩክ" ነበር ፓስወርዷ! ብሩክ የሚል ስም ይዞ አሁን ሰዉ እንደዚህ አይነት ተግባር ይፈፅማል? ለነገሩ በስም ከተባለ የነብይ ስም ይዘዉ እንዲህ ርካሽ ተግባር የሚፈፅሙም አይጠፉም። እምነት አንዴ ከተሸረሸረ መልሶ ማምጣት አይቻልም። ፈረንጆቹ እምነት እንደ ድንግልና ነዉ አንድ ጊዜ ከጠፋ መልሶ ማምጣት አይቻልም! የሚሉት ለዚህ ይመስለኛል።
ጊዜዉ እየገፋ ሲመጣ ህመሙን ዉስጤ ማመቁ ስለሰለቸኝ ብሩኬን ላናግረዉ ወሰንኩ።
.
ብሩኬ ጋር ደወልኩለት! እነ ሄኖክ ሰፈር እንደሆነ እና ሲመለስ እንደሚደዉልልኝ ነገረኝ። እነ ሄኖክ ሰፈር ማለት እነ ኢክራም ሰፈር ማለት ነዉ።

ከሷ ጋር እንደሆነ እርግጠኛ ሆንኩ። ሲመለስ ደወለልኝ። አገኘሁት። ሳየዉ ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ።
እየሳቅኩ "የት ነበርክ?" አልኩት።
በጥርጣሬ አይን እያየኝ "እዚሁ ነበርኩ ባክህ ማደያዉ ጋር!" ምናምን ብሎ ቀባጠረ።

ዛሬ እዉነት እዉነቷን እንድናወራ ስለፈለግኩ በአይኔ የት እንደነበረ እንደማዉቅ የሚያሳይ ምልክት ሰጠሁት። የስነ አእምሮ ተማሪ ነኝ! ሰዉን በንግግሩ ዉስጥ ችግሩን ተረድቶ ማከም ነዉ የምማረዉ።
ያወቅኩ መሆኑን ስለጠረጠረ እየሳቀ! "ባክህ ከሚስትህ ጋር ነበርኩ!" አለኝ። የሚስትነት ስሟን ለኔ፣ ተግባሩን ደግሞ ለሱ ከፋፍሎት መሆን አለበት ከሚስትህ
ጋር ያለኝ!

"ሚስትህ ስትል አስታወስከኝ ባይዘዌይ ሰሞኑን የሆነ ሰዉ አካዉንቷን ሀክ አድርጎት ነበርና ከብዙ ሰዉ ጋር ያደረገቻቸዉ ምልልሶች በሶፍት ኮፒ ተዘጋጅተዉ ሊላኩልኝ ነዉ!" አልኩት።
ብሩኬ ደነገጠ! "ማነዉ ይሄ ባለጌ የሰዉ አካዉንት ሀክ የሚያደርገዉ?" አለኝ እየተበሳጨ።

በዉስጤ እስቃለሁ።
"አላወቅኩም ግን የሚጠቅምህን ነገር አግኝተንበታል ነዉ ያሉኝ! እነሱ ከኔ የሚፈልጉት ነገር ስላለ ጊቭ ኤንድ ቴክ መሆኑ ነዉ!" አልኩት ፊቱን እያነበብኩ።
ከብሩኬ ጋር እያወራን የነበረዉ ዎክ እያደረግን ነበር። ዎክ እያደረግን እነ ረዊና ቤት አካባቢ ደረስን!
ብሩኬ ወሬ ለማስቀየር ይሁን አላዉቅም

"አንተ ግን እምነትን ልብላት ስልህ እምቢ አልክ አይደል?" አለኝ። የረዊናን እህት እምነትን ነዉ።
ፈገግ ብዬ "ብሩኬ ቆይ ስንቱን ልተዉልህ?" አልኩት!
ብሩኬ እንደድንጋይ ደርቆ "ማንን ተዉክልኝ?" አለኝ።
እየሳቅኩ "ከእምነት ሌላ ምድር ላይ ያሉትን ሴቶች ሁሉ ትቼልሀለሁ!" ብዬ አስቀየስኩ።
.
ብሩኬ የኢክራም አካዉንት ሀክ መደረጉ በጣም አንገብግቦታል።
"ፈዊዬ ጓደኛህ አይደለሁ! ቢያንስ የኔን እንዳይልኩልህ አድርግ!" አለኝ።
"ያንተማ ቢላክልኝም ምንም ሚያስጨንቅህ ነገር የለም። እኔ ነኝ ማነበዉ! አንተ ከኔ ደብቀህ ከኢክራም ጋር የምታወራዉ ነገር ስለሌለ አትጨነቅ።" አልኩት።

ከጀርባዬ ጭንቅላቱን ይዞ ቆሞ "ፈዉዛኔ ካነበብከዉ ያጣላናል!" አለኝ። የእዉነት እኔን ከመረጠ መጀመሪያ እሷን እንቢ አይልም ነበር! አንቺዉ ታመጪዉ አንቺዉ ታሮጪዉ አሉ!
መጫወቱ ሲበቃኝ ወደ ብሩኬ ዞር ብዬ አይን አይኑን እያየሁ "ግን ምኗን ወደድከዉ?" አልኩት።

ብሩክ ሁሉንም ማወቄን አረጋገጠ። "በቃ ሁሉንም እነግርሀለሁ!" አለኝ።
ድራማዉ ከጀርባዬ ላለፉት ስምንት ወራት እየተተወነ እንደነበር ነገረኝ። ኢክራም ስለምታሳዝነኝ ነዉ ምናምን ብሎ ቀባጠረ! የእዉነት ቢያዝንላት የኔን ዉሳኔ እንድትተገብር ነበር ሊያበረታታት የሚገባዉ።
"ብሩኬ እኔ ይቅርታ አድርጌልሀለሁ! ኢክራምን የምትወዳት ከሆነም ግንኙነታችሁን መቀጠል ትችላላችሁ!" አልኩት።

ብሩኬን ላለፉት አስር አመታት አዉቀዋለሁ! በአንድ ሴት ምክንያት በቃኸኝ ልለዉ አልችልም። ምንም ዛሬ ቢከዳኝም ብዙ ከባባድ ጊዜዎቼን አብሬዉ አሳልፌያለሁ። ለኔ መልካም ሰዉ ነበር። ግን አንድ ፈተና ማለፍ አቃተዉ።
.
በቀጣዩ ቀን ከብሩኬ ጋር ተገናኝተን ስናወራ ስለሷ አዉርቶ መዘባረቅ ሲጀምር "ቆይ ግን እኔን እንደዛ እወድሀለሁ እያለች የከዳችኝ ኢክራም አንተን ዞራ እወድሀለሁ ስትልህ ነገ ወደ ሌላዉ እንደማትዞር በምን እርግጠኛ ሆንክ? ቢያንስ በኔ አትማርም?" አልኩት።
"ባክህ እኔ አልወዳትም!" አለኝ።
"ታዲያ ለምን እሺ አልካት?"
"እሷ እወድሀለሁ አለችኛ!"

በጣም ተበሳጨሁ! ቢያንስ ኢክራምን ወዷት ሴትነቷ አሳስቶት ቢከዳኝ እሺ! ግን እንዲሁ ለመንዘላዘል ነዉ ክህደት የሰራብኝ? ከምር አበሳጨኝ! እምቢ ማለት አለመቻል ትልቁ ዝቅጠት ነዉ። ጠጣ እሺ! ቃም እሺ! ጓደኛህን ክዳ እሺ! በጣም ያሳፍራል።

ከብሩኬ ጋር እንደድሮዉ ለመሆን ብሞክርም በፍፁም ሊሳካልኝ አልቻለም። እምነት ከተሸረሸረ ትልቅ አደጋ ነዉ።
.
ኢክራም ያደረገችዉ ነገር ምንም አስቀያሚ ቢሆንም ልቤ ዉስጥ ቅንጣት ጥላቻ ሊፈጠር አልቻለም። አሁንም በጣም ታሳዝነኛለች።

ምናልባት ፈጣሪዬ ከሱ ቀድቼ ለኢክራም የተናገርኩትን ወዶልኝ ይሆን? "ያለፈዉንም የሚመጣዉንም ጥፋትሽን ይቅር ብዬሻለሁ!" ያልኳትን። አይ እንደዉም የወደፊቱን ይቅር ማለት ከሱ ሌላ ማንም እንደማይችል እያሳየኝ ነዉ የሚሆነዉ! ግን አሁንም ለኢክራም ያለኝ እዝነት አልቀነሰም።

አንድ ቀን ሁሉንም ነገር ማወቄን ፌስቡክ ላይ ነገርኳት። በጣም ደነገጠች። እኔ አሁንም የድሮዋን ጨዋዋን ኢክራም ለመሆን ብትሻ ላግዛት ዝግጁ ነኝ።

ግን ኢክራም ክህደቷን መቋቋም አቃታት መሰለኝ ከፌስቡክ ብሎክ አደረገችኝ። የተበደልኩት እኔ! ዘራፍ ባዩ ሌላ! ይገርማል። ፈጣሪዬ ግን ማገናኘት ካሻዉ ማንም አያግደዉምና ብሎክ ባደረገችኝ

በነጋታዉ መንገድ ላይ ተገጣጠምን። ዉስጤ ላይ ምንም ጥላቻ የለም። ልክ እንደድሮዉ ፈገግ አልኩላት! ፈገግታዬን ስታይ ወደኔ መጣች። ሰላም ከተባባልን በኋላ ስለትምህርቷ አወራን! እሷ ግን ከመወዛገቧ የተነሳ ስለያዝኩት ቦርሳ ዘባረቀች። ኢክራምን ከረጅም ጊዜ በኋላ በአካል አገኘኋት! እንደሚሉት የተጋነነ የአለባበስ ለዉጥ አላስተዋልኩም! በርግጥ ጅልባቡ ወልቆ ቀሚሱም ጠቧል። የጠበቅኩት የተጋነነ ስለነበር ነዉ መሰለኝ ብዙም አልደነገጥኩ
ም!

.
አሁን የሚቆጨኝ እኔ ስበላሽ ከጎኔ ሆና ያረመችኝን ኢክራምን ዛሬ የክህደት እና የስነ ምግባር ዝቅጠት ዉስጥ ስትዘፈቅ ልታደጋት አለመቻሌ ነዉ።
ለሰዉ ልጅ ክብር ወሳኙ ነገር ከማንነት መስመር የወጣን አፈንጋጭነት እንቢ ማለት መቻል ነዉ።
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
የመጀመሪያዉ ስህተት የኔ ነበር! ከፈጣሪ ትዕዛዝ ዉጪ ሴት ስተዋወቅ! ህይወቴ ዉስጥ ልጨምራት ከፈጣሪ ተጋፍቼ ያመጣኋት ኢክራም የነበረኝን ብሩክንም አሳጣችኝ። ጌታዬ ልክ ነበር! ተሳስቶም አያዉቅም! አይሳሳትምም!
ኢክራም ዛሬም መልካም ለመሆን ቅንጣት እንኳ አልረፈደባትም። ወደለመዱት መልካምነት መመለስ ለኢክራም አይከብድም። ዛሬም የኢክራምን መልካም ስብዕና እናፍቃለሁ።

የጋብቻ የጥሪ ካርዷን ስትልክልኝ አልማለሁ! እሷ ራሷ ከዘቀጡበት ፈልጋ ሰብስባ ያፀዳቻቸዉ ነብሶች ዛሬ እሷን እንደመታደግ ሲጠቋቆሙባት ሳይ እበሳጫለሁ። ኢክራም ከነክህደቷ ብዙ ንፁሀንን አፍርታለች። በጨዋዋ ኢክራም እጅ ንፅህናን የተቀበሉ በሙሉ ኢክራምን ወደነበረችበት ከፍታ የመመለስ ግዴታ አለባቸዉ።
ብሩኬም መልካም ለመሆን ጊዜዉ አልረፈደበትም።

ብሩኬ ለመበላሸቱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች ለማጤን ሞክሬ ነበር። ዋናዉ ፊልም ነዉ። ፊልሞቹን በከፊል ወስጄ ተመለከትኳቸዉ። ስሜት ተኮር ናቸዉ። "የሰዉ ልጅ የተመለከተዉን ነገር ይተገብራል" ይላል ስነ አእምሮ! የሰዉ ልጅ ባህሪዉን የሚገነባበት አንዱ መንገድ ሲደረግ ያየዉን በመማር (imitation) ነዉ።

ብሩክ ለመበላሸቱ ይመለከታቸዉ የነበሩት ፊልሞች ግንባር ቀደም ምክንያት ናቸዉ።
ሁለቱም ሰዎች ናቸዉ ተሳሳቱ! እኛ ስህተት ባይኖርብን ፈጣሪ እኛን አጥፍቶ ሌሎች የሚሳሳቱ ህዝቦችን ይፈጥር ነበር። ግን ዋናዉ ነገር ጥፋትን ተረድቶ ለመፅዳት መሞከር ነዉ። ጥፋቱ ክህደት ሆኖ ወንጀላቸዉን አገዘፈዉ እንጂ ብዙ መልካም ነገር ይኖራቸዋል።
.
ብርጭቆ መሬት ላይ ወድቆ ሲሰበር ከነበርኩበት የሀሳብ ሰመመን ነቃሁ! አንዱ ጠረዼዛ ላይ ያሉት ጥንዶች ናቸዉ የሰበሩት።

ካፌዉ ዉስጥ አራቱ ቴብሎች ላይ ጥንዶች ተቀምጠዋል። ረሂማ እየሳቀች ወደኔ መጣች! ከኪሴ ልከፍል ብር እያወጣሁ ነበር።
ረሂማ እየሳቀች "ወተቱስ?" አለችኝ።
ወይኔ ለካ ቅድም ልታሞቀዉ ወስዳዉ ነበር እርስት አድርጌዋለሁ።
"እሺ የታለ?" አልኳት እየሳቅኩ!
"አሙቄዉ እዛ ቴብል ላይ ወተት ታዞ ነበር እና ለሱ የታዘዘ መስሏቸዉ ወሰዱት! አንተም ሙድህ ስለወረደ አዉቄ ነዉ ዝም ያልኩህ!" አለችኝ እየሳቀች።
.
ካፌዉ ዉስጥ ያሉትን ጥንዶች ተመለከትኳቸዉ! ይስቃሉ ፣ይጎነታተላሉ! እስከሚጣሉ ይጎነታተሉ አልኩ በልቤ! አዎ ተዋደዱ፣ከነፉ፣ተጣልተዉ አረፉ! ነዉ ከትዳር ዉጪ ያለ ፍቅቅሮሽ መዳረሻ።

ሲከፋም የወንዱም የሴቷም ክብር በዝሙት ይገፈፍና ለንፁሀን የተከለከሉ ቆሻሻ መሆንን ነዉ የሚያተርፈዉ።
.
ፊርደዉስ ደወለችልኝ። አነሳሁት!
"አንተ እዛ መቆዘሚያ ካፌህ ነህ አይደል?" አለችኝ።

"አዎ ምነዉ ፊርዱ?" አልኳት
"በዚህ ስሜት ዉስጥ ሆነህ መጠየቁ አግባብ ይሁን አይሁን አላዉቅም! ግን ፈዊ ፈቃደኛ ከሆንክ ካንተ ጋር ኒካህ ማሰር እፈልጋለሁ! ገንዘብ ምናምን የሚለዉ አያሳስብህ ነብዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) የመጀመሪያ

ሚስታቸዉን ኸዲጃን(ረዐ) ሲያገቡ እሷ በጣም ሀብታም ነበረች! የእዉነት ሀይማኖተኛ ከሆንክ ይሄ አይጠፋህም" አለችኝ።

የኔ አንበሳ ይሄን ታሪክ ማወቋ በራሱ አስገርሞኛል። እንዴት እንዴት ነዉ ያገናኘችዉ? ቆንጆ ፖለቲከኛ ይወጣታል። ደሞ ለሷ ኒካህ ምን አላት? እድሜ ለአባቷ! ገንዘብ እንደልቧ ነዉ። እኔ የማስተዳድራት እንጂ የምታስተዳድረኝ ሴት ማግባት አልፈልግም።

"ፊርዱዬ ከኔ ጋር ወንድምነቱ ይሻለናል እሺ! እኔ ለጋብቻ ብቁ ነኝ ብዬ አላምንም!" አልኳት። ለጋብቻ ብቁ ሆኜ ቢሆንማ ኢክራምን እስከአሁን አግብቼ ነበር።
"ፈዉዛን እኔ ምን ያንሰኛል? ዉበት ከፈለግክ ማንም አይጠጋኝም ታዉቃለህ! ገንዘብ አለኝ እንደፈለግክ አድርገዉ! ከማንም እኔ እሻልሀለሁ።" አለች እየተነጫነጨች። በራስ መተመመኗ እና ግልፅነቷ በጣም ደስ ይለኛል።

"ፊርዱ እኔ አንቺ ምንም ይጎድልሻል አላልኩም ግን እኔ ብቁ አይደለሁም! ለሌላ ጊዜ ብቁ ስሆን ግን ከዉበትሽ እና ከገንዘብሽ በላይ ሀይማኖትሽ ላይ ያለሽን አቋም ስለምፈልገዉ እሱን አሻሽይ!" አልኳት እየሳቅኩ።
"እሺ በቃ እንደድሮዉ!" አለችኝ እንዳንኮራረፍ ፈርታ።
"እሺ ፊርዱ ፈታ በይ!" አልኳትና ስልኩን ዘጋሁት።

ረሂማ ሚስተናገድ ሰዉ የለም መሰለኝ አጠገቤ መጥታ "አንተ ግን ዛሬ ምን ሆነህ ነዉ?" አለች። መልሴን ሳትጠብቅ ወዲያዉ ስልኬን ከጠረጴዛ ላይ አንስታ ሰዓት አየች። እግረ መንገዷን ሰሞኑን የፃፍኩትን ግጥም ዋልፔፐር አድርጌዉ ስለነበር አየችዉ። እየሳቀች ጮክ ብላ አነበበችዉ

"ስምሽ ጎዳደፈ አነሱሽ በክፉ፣
ከንፈር ማሳበጤ ይሄ ነዉ ወይ ትርፉ?
ደግሜ ብስምሽ ይፀዳ ይሆን ወይ የህሊና እድፉ!"
አሽኮረመመችኝ! ረሂማ ወዲያዉ ተስተናጋጅ ስለመጣ ትታኝ ሄደች። ወዲያዉ ስልኬ ጠራ! ረዊና ነበረች። አነሳሁት።

"ፈዉዛኔ የት ነህ? አዲስ አበባ መጥቻለሁ!" አለችኝ።
ረዊና ንፁህ እህቴ ናት! ሁሉንም ነገር ለሷ መተንፈስ ነበር የሚቀለኝ።

"ስማ ከትምህርት ቤቱ ጀርባ ያለዉ ልብስ ቤት ነኝ! አትመጣም?" አለች!
"መጣሁ!" ብያት ከካፌዉ ተነስቼ ወጣሁ። ከመሸሸጊያዬ ወጣሁ! የወዳጅ ጦር ቅርብ ርቀት ላይ ነዉ። ንፁህ እህትነት! ረዊና!

         
#ተፈፀመ

እውነተኛ ታሪክ ስለሆነ  እንደድርሰት ልቦለዶች መጨረሻቸውን  አላሳመርነውም ምክንያቱም እውነተኛ ታሪክ  የእውነት ስለሚቀመጥ
 
ሁሉም ታሪኮች ፍፃሜያቸው አያምርም 
ከታሪኩ የምንማረውን እንማራለን የምንቀስመውን እንቀስማለን።

አንብባችሁ ከወደዳችሁት  ያላችሁን ሀሳብ አስቀምጡልኝ Like አርጉልን እኛ ሺ ፊደል ተጭነናል


       

              ,,,
✦━━
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
4 any comment @Meki3
⚡️HamsteKombat

ከNotcoin ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነው መልቲ ታፕ ስላላው እንደ Tapswap አሪፍ ነው ይሄኛውም

⚡️ በቅርቡ እስከ 50$ Reward ይኖራል ከአሁኑ ጀምሩ

🔗 https://www.tg-me.com/hamster_kombaT_bot/start?startapp=kentId6405623892

Bot ውስጥ እንደገባቹ play in 1 click የሚለውን ነክታቹ አስጀምሩ
ታስኮችን በመስራት ኮይን ማሳደግ ትችላላችሁ።
ትንሽ ኮይን እንደሰበሰባቹ Boost የሚለው ውስጥ በመግባት ታፕ የምትደረገው እና Recharge Speed አሳድጉ።
Premium user 25k coin
😊 Normal user 5k coin

@ethioleboled
የዛሬው combo ላልጀመራቹ ጀምርዋት


https://www.tg-me.com/hamster_kombat_bOt/start?startapp=kentId5875888757
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━━━─╝


ክፍል አንድ ( ⓵ )
❃•❃ ════ ❁

<< በነበር ቢቀየር ፣ ምን እንኳ ቢረሳም፣
ባልሆነ አልልም ፣ ደስታዬን አልገፋም! >>

*

ቀኑ ፀሀያማ ነው... ደስ የሚል ድባብ ያለው ቀን። አከባቢው ላይ ሻንጣቸውን እየጎተቱ የሚሄዱ ብዙ ሰዎች ይስተዋላሉ።
አምሪያ ከነዛ መሀል አንዷ ናት። ወገቧ ላይ አንድ ቦርሳ አዝላ በእጇ ደሞ በጣም የምትወደውን ቢጫ ሻንጣ እየጎተተች በፍጥነት ትራመዳለች። ሁሉም ሰዎች እዚ ቦታ ላይ የመጀመሪያ ቀናቸው እንደመሆኑ ተደናብረዋል። አምሪያ ግን እዚ ቦታ ላይ የመጀመሪያ ቀኗ አይመስልም። ወዴት እንደምትሄድ በደንብ ታውቀዋለች። ብቻ ሻንጣዎን እየጎተተች በሩጫ በማይተናነስ ፍጥነት ትራመዳለች...

አምሪያ የወንዶች ዶርም ጋር እንደደረሰች ቆመች። ወደአንድ ህንፃ መስኮት ጋር ጠጋ ብላ አንድን ሰው ጮክ ብላ መጣራት ጀመረች።
" ረያን... ረያን...መጣሁ እኮ ... ረያን..." ድምፅዋ በጣም ይሰማል። አከባቢው ላይ ያሉ ተማሪዎች ባሉበት ቆሙ። በምታደርገው ነገር ግራ ስለተጋቡ ከበው የሚፈጠረውን ነገር ይመለከታሉ።

ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ከኋላዋ " አምሪያ " የሚል ድምፅ ሰማች። ድምፁ የረያን እንደሆነ ለመለየት ጊዜ አልፈጀባትም። ዞረች...አንድ ወጣት ልጅ ክብ ሰርተው ከቆሙት ሰዎች ኋላ ቆሟል። ጠይም... ረዘም ያለ... ቆንጆ ወንድ ። አዎ ረያን ነበር። አምሪያ ስታየው ልቧ መምታት ጀመረ። ደስታዋ ፊቷ ላይ በደንብ ይነበባል።

ረያን ክብ የሰሩትን ሰዎች አልፎ ወደ አምሪያ ጋር በቀስታ እየተራመደ መጣ። የዛኔ ግማሹ ተማሪ ስልኩን እያወጣ መቅረፅ ጀመረ። ሊፈጠር የሚችለውን ገምተው ነው። ምናልባት Tiktok ላይ ይሄንን የፍቅር scene post ቢያደርጉት ብዙ like ያተርፉበት ይሆናል። ረያን አምሪያ ጋር እንደደረሰ ቆመ። ለትንሽ ደቂቃ ዝም ብለው ከመተያየት ውጪ ምንም አላወሩም ነበር። ረያን የያዘችውን ሻንጣ ተቀብሏት እንድትከተለው በአይኑ ምልክት ከሰጣት በኋላ ሻንጣውን ይዞ ሄደ። የብዙ ሰው አይን ውስጥ ስለገቡ ሰው ወደሌለበት ቦታ እስከሚደርሱ ድረስ ምንም ሳይላት ከፊት ከፊት እየተራመደ በዝምታ ነበር የሄደው።

ብዙ ሰው ወደሌለበት ቦታ ጋር ከደረሰ በኋላ ቆሞ እስከምትደርስበት ድረስ ጠበቃት። እዛው ጋር መቀመጫ ቦታ ስለነበር ቁጭ አሉ።

" ረዩ...ስላየውህ በጣም ደስ ብሎኛል! " አለች አምሪያ ደስታዋ አሁንም አልቀነሰም። ረያን ግን ምንም መልስ አልሰጣትም ነበር።
" ስደውልልህ አታነሳም...መልዕክትም አትመልስም...አሁንም ስጠራህ አትመጣም ብዬ አስቤ ነበር..." ረያን አሁንም ምንም አልመለሰላትም።
እሷም ንግግሯን ቀጠለች " ላገኝህ የፈለኩት አንድ ነገር ልነግርህ ፈልጌ ነው..."
" ምንድን ነው " መሬት መሬት ብቻ ነው የሚመለከተው።
" እወድሀለው! አንድ ጊዜም እንኳን ወደኸኝ አታውቅም ነበር? " ፊቷ ላይ ስስት አለ...ህመም ...ደሞ በተመሳሳይ ሰአት ደስታ...
ረያን ፈገግ አለ...ግን የደስታ ፈገግታ አልነበረም የሆነ ግራ የሚያጋባ አይነት ፈገግታ እንጂ " አምሪያ እኔ በአሁን ሰዓት ከማንም ጋር የመሆን ሀሳብ የለኝም " ይሄ መልስ እንደሚያስከፋት ያውቃል ቢሆንም ግን አለው። " ደክሞሻል... ገብተሽ እረፊ...እናም ትምህርትሽ ላይ ብቻ አተኩሪ...ድጋሚ እኔን ለማግኘት እንዳትመጪ " ከተቀመጠበት ተነሳ። ከኋላ ሹራቡን ይዛ አስቆመችው።
" ወደዚ ዪንቨርስቲ አብረን ለመምጣት እኮ ቃል ተግባብተን ነበር። አሁን ቃሌን ሞልቻለው። አንድ ጥያቄ ብቻ ልጠይቅህ? አትወደኝም ነበር? "
" ' አዎ' ወይ ' አይ ' የሚለው መልስ ለውጥ ያመጣል ብለሽ ታስቢያለሽ? "
ፊቱን ወደሷ መለሰው " ይኸውልሽ አምሪያ አሁን ሁለታችንም የራሳችን ህይወት አለን። " ቀና ብሎ ተመለከታት። አይኗ ቀልቷል...ፊቷ በእንባ መርጠብ ጀምሯል። ሊናገር የነበረውን ነገር መልሶ ዋጠው።
" ረዩ የኔ ሚስጥር ምን እንደሆነ ልንገርህ " እንባዋን በእጇ እየጠረገች በስስት ትመለከተዋለች። እስካሁን አፍና ይዛ የነበረውን ሚስጥሯን ዛሬ ለሱ ልትነግረው ፈለገች። ምን አልባት ቢረዳት...

ስታለቅስ ማየት አልቻለም። አይኑን ወደመሬት መለሰ። " እየመሸ ነው... ወደዶርም መመለስ አለብኝ..." ተመልሶ ሳያያት ጥሏት ሄደ። የሱም አይን እንባ እንዳቆረ ግን አላስተዋለችም ነበር። ከእይታዋ እስከሚሰወር ደረስ በአይኗ ሸኘችው።

*

" ከ2 አመት በፊት "

መስከረም 4 , 2010...የድሮ ከተማቸውን ተሰናብተው ወደ አዲስ አበባ እየመጡ ነው። አምሪያ፣ እናቷ ወ/ሮ ኸዲጃ፣ አባቷ አቶ ቶፊቅ፣ እና ታናሽ ወንድሟ ሰሚር። ለአምሪያ እዚ ሁሉም ነገር አዲስ ነበር። የህይወቷ አዲስ ምዕራፍ...

አዲሱ ቤታቸውን ካስተካከሉ በኋላ ምሽት ላይ እራት ለመብላት ወደ ተጋበዙበት ቤት ተሰብስበው ሄዱ። የነ አቶ ጀማል እና ዘምዘም ቤት ነበር። በፊት የነበሩበት ከተማ ጎረቤታሞችና የረጅም አመት ጥብቅ ወዳጆች ናቸው። እነ አምሪያ ልጆች እያሉ ነበር እነሱ ወደ አዲስ አበባ የመጡት። እዚ ከመምጣታቸው በፊት ሁሉንም ነገር አስተካክለው የጠበቋቸው እነ አቶ ጀማል ነበሩ። አሁንም እንኳን ደህና መጣችሁ ለማለት ነው እራት የጋበዟቸው። እነሱም ጥሪያቸውን አክብረው በሰዓታቸው ተገኝተዋል።

" ሁሌ የማወራላችሁ ዘምዘም ማለት እሷ ናት " አሉ የአምሪያ እናት ወ/ሮ ዘምዘምን ለማስተዋወቅ ወደ አምሪያ እየተመለከቱ።
" ውይ ይቅርታ ግን እናቴ በፍፁም ስላንቺ ነግራን አታውቅም..." በውስጧ ነው ያለችው...በእርግጥ የተወሰነ ነገር ስለነሱ ሰምታ ብታውቅም ሁሌ የሚለው ቃል ግን ባይገባ ጥሩ ነበር...
" ሳያዉቋችሁ ራሱ በጣም ነበር እነንተን ማግኘት የሚፈልጉት ...አይደል? " አለች በፈገግታ በድጋሚ ወደአምሪያ እየተመለከተች።
" እ አዎ...ስላገኘዋቹ በጣም ደስ ብሎኛል...ከእናቴ ስላንቺ ብዙ ሰምቻለው..." አንገቷን ወደመሬት እንዳቀረቀረች
" በጣም አድጋቹሀለው...አቅፌሽ እላዬ ላይ ትሸኚ የነበረውን ነው የማስታውሰው...አጂብ ጊዜው በጣም ይሮጣል..." ሁሉም ሳቁ...ሰሚር በአይኑ ሙድ ይይዝባታል። ሰው ቤት ስለሆኑ ምንም ማለት አልቻለችም። ንዴትዋን አፍና ከመያዝ ውጪ...ረጅም ሰአት ሰላም ተባብለው ናፍቆታቸውን በትንሹ ከተወጡ በኋላ ወደ መመገቢያ ጠረንጴዛው ሄደው ተሰበሰቡ።

" ረዩ ና እንጂ እንግዳዎቹ እኮ መተዋል..." እናቱ ናት ጮክ ብላ ትጣራለች። ወዲያው ሁለት ልጆች ከላይኛው ፎቅ ወረዱ። የረያን ጓደኞች ነበሩ። ሚኪያስና ፋሩቅ...
" ረያንስ? "
" ቅድም እንደተኛ ነው...ቀስቅሰነው ነው የመጣነው አልተነሳም መሰለኝ "
" በሉ ቀስቅሱት እንጂ...እንግዳ እንደሚመጣ ነግሬው
" አንተ ረያን ትመጣለህ ወይስ እኔ ልምጣ? " ሚኪያስ ነው እኔ ልምጣ ሲል ውሀ ሊረጭበት ማለቱ ነው። ያው መርጨት ሳይሆን መድፋት... እርስ በእርስ ለመቀስቀስ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው።
ረያን ምንም ደቂቃ አልቆየም አይኑን እያሻሸ ከክፍሉ ወጣ።
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
" ሰላም በላቸው ረዩ... ወ/ሮ ኸዲጃ እና አቶ ቶፊቅ ናቸው...ሁለቱ ደሞ ልጃቸው አምሪያና ሰሚር .."
ሄዶ ሁሉንም እያቀፈ ሰላም ካለ በኋላ አምሪያን በአየር ላይ ሰላምታ ሰቷት ተቀመጠ።
ምግብ መብላት ትንሽ እንደጀመሩ የረያን እናት ጨዋታ ጀመረች።
" ሁለታቹ ታስታውሳላችሁ ልጅ እያላችሁ አብራችሁ ነበር የምትጫወቱት..."
" አዎ አሁን እንደዚ አድጎ በጣም ቆንጆ ልጅ ሆኗል..." የአምሪያ እናትም ጨዋታውን ተቀላቀለች። አምሪያና ረያን አንገታቸውን ደፍተው የሚያወሩት ከመስማት ውጪ ቀና ብለው እንኳን አልተያዩም። ትንሽ እፍረት ነገር...
" አሁን እንደዚ አድገው...ጊዜው በጣም ይሄዳል "
" አሁንማ የፕሪፕ ተማሪዎች ሆነዋል..."
ጨዋታቸውን እንደቀጠሉ ነው...
" የማትሪክ ውጤትሽ ከፍተኛ እንደነበረ ሰምቻለው...ስንት ነበር ያመጣሽው" አለች ዘምዘም ወደ አምሪያ እየተመለከተች።
" 3.8 "
" ማሻ አላህ በጣም ጥሩ ውጤት ነው "
" አዎ ለሊት ሁላ ሳተኛ ነበር የምታጠናው። እረፍት የሚባል አታውቅም " እናቷ ኸዲጃ ናት።
" ያንተስ ውጤት ስንት ነው? " የአምሪያ እናትም በተራዋ ረያንን ጠየቀችው።
" 3.6 "
" በርታ ጎበዝ ልጅ ...እናንተም የረያን የክፍል ጓደኞቹ ናችሁ አይደል... የናንተስ ውጤት ስንት ነው "
" እኛ..." ሚኪና ሰሚር ተፋጠጡ። ረያን አይቷቸው ፈገግ እያለ " ያው ነጥቡ አይደለም ወሳኙ ነገር ዋናው ማለፋችን ነው...አይደል? " ሸፈነላቸው
" አዎ ልክ ነህ! ዋናው እሱ ነው። ከዚ በኋላም ደሞ አብራችሁ ነው የምትማሩት...በደንብ ትተጋገዛላችሁ..." የአምሪያ እናት ናት። አነጋገሯ ላይ አምሪያና ረያን በደንብ እንዲቀራረቡ የፈለገች ትመስላለች።
" ኢንሻአላህ በደንብ ይተጋገዛሉ..." ወይዘሮ ኸዲጃም ሀሳቧን ደገፉ።

ትንሽ ደቂቃ ዝም ካሉ በኋላ የረያን እናት ዝምታውን ለመስበር እንዲህ አለች
" ህፃን እያሉ ሀያቶቻቹ ስታድጉ እናንተን ለማጋባት ቃል ተግባብተዋል..."
በዚ ሰአት ሁሉም ደነገጡ። ረያንም ይሁን አምሪያ ስለዚ ነገር ጭራሽ ሰምተው አያውቁም ነበር። ሚኪና ሰሚር ረያን ላይ አፈጠጡበት። ረያን እና አምሪያም ድንጋጤያቸው ፊታቸው ላይ በደንብ ይነበባል።
" አሁን ለምን አነሳሽ ይሄን ጉዳይ.." ባሏ ነው አቶ ጀማል
" እሱማስ ልክ ናት። ያው አሁን ገና ናቸው በሚለው ነው እንጂ እኛም አልረሳነውም " አሉ አቶ ቶፊቅም በተራቸው።
" አዎ አዎ... ልክ ነው አሁን ትምህርታቸው ላይ ነው ማተኮር ያለባቸው..." ሁሉም ፈገግ እያሉ ርዕሱን ለመቀየር ሞከሩ።

" ይሄንን ቃል ለመስበር ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ? " ረያን ነው። ይሄንን ሲል ሁሉም ጋር በአንዴ ዝምታ ሰፈነ። ያልጠበቁት ጥያቄ ነበር።

" ረያን ለምን ይሄን ጥያቄ ጠየቀ? አምሪያን ገና ከአሁኑ ጠልቷት ነው ወይስ ማግባት የሚፈልጋት የራሱ ሴት አለችው? " አብዛኛዎቹ ጋር የተፈጠረ ጥያቄ ነበር...

#ክፍል_ሁለት ( ❷ ) .. ይቀጥላል....
┍──━──━──┙◆┕──━──━──╝

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━━━─╝

. #ክፍል_ሁለት (❷)
┗•━•━•━ ◎ ━•━•━•┛

" ይሄንን ቃል ለመስበር ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ? " ረያን ነው። ይሄንን ሲል ሁሉም ጋር በአንዴ ዝምታ ሰፈነ። ያልጠበቁት ጥያቄ ነበር።

" አንተ እኮ ይሄን ለማሰብ ገና ነህ። ደሞ እናትህ እየቀለደች ነው። የምር አረከው እንዴ?" አባቱ ሁሉም ጋር የተፈጠረውን መደናገጥ ለማጥፋት ሞከሩ።
" እኔም ቀልዱን ልቀላቀል ብዬ ነዋ። አብሽሪ አላመረርኩትም..." ቀልዱ ከማሳቅ ይልቅ በተቃራኒው ኮስተር ቢያደርጋቸውም ነገሩም ለማረሳሳት ሲሉ ሁሉም ፈገግ አሉ።
" ሲጀመርስ ማን ይፈልግሀል አንተን? " አምሪያ ንዴቷን በውስጧ ትገልፃለች።

እሱ የቀልዴን ነው ብሎ ቢያልፈውም አምሪያ ግን አልተዋጠላትም። በዚ ሰአት እንደዚ ማለቱም አናዷታል። በእርግጥ በጋብቻው ሀሳብ ተስማምታ ሳይሆን እንደማይፈልግ ለቤተሰቦቹ ነግሮ ከነሱ ጋር መመካከር እየቻለ ገና ከመስማቱ ሰው መሀል እንደዛ ማለቱ የመናቅ ስሜት ፈጥሮባታል። ከዚ በፊት ለትዳር ቤተሰቦቿ ጋር የመጡትን ወንዶች ብታስተዋውቀው ደስ ባላት ነበር። በእርግጥ አምሪያ በጣም ቆንጆ ባትባልም ሰዎችን የሚስብ ሀይል ግን በተፈጥሮ የተሰጣት ናት። የቀይ ዳማ የፊት ከለር ከተስተካከለ የሰውነት ውፍረት ጋር ያላት ሴት ናት። " ቆይ ራሱን እንዴት አድርጎ ነው የሚያስበው? " ንዴቱ አሁንም አለቀቃትም።

ረያን ትንሽ ቆይቶ ከመቀመጫው ተነሳ።
" ምነው አትበላም እንዴ? " አለችው እናቱ ከመጣ ራሱ ብዙ አልቆየም።
" ጠገብኩ...እናንተ ብሉ...ትንሽ እራሴን እያመመኝ ስለሆነ ገብቼ ልረፍ። ይቅርታ! " ብሏቸው ሊሄድ ሲል ሚኪያስና ፋሩቅም " እኛም ጠግበናል " ብለው ተከትለውት ወደክፍል ገቡ።

ምግቡን በልተው ከጨረሱ በኋላ መጅሊሱ ዙሪያ ተሰብስበው መጨዋወት ጀመሩ። የአምሪያ ወንድም ሰሚር በእናቱ ስልክ game ሲጫወት አምሪያ ደሞ ስልኳን እየነካካች አልፎ አልፎ ደሞ የነሱን ጨዋታ ትቀላቀላለች።

ሰሚር ወደ አምሪያ ጋር መቶ በጆሮዋ ወደመፀዳጃ ቤት መሄድ እንደሚፈልግ ሲነግራት ቦታውን ጠይቃ ይዛው ትሄዳለች።
ሰሚርን ካስገባችው በኋላ እስከሚወጣ ድረስ እዛው ግድግዳ ተደግፋ ቆመች። ድንገት ግን አጠገቧ ካለው ክፍል አንድ ድምፅ ሰማች።
" የኛ አምሪ በጣም ጥሩ ልጅ ናት ፤ አንድ ቀንም አሳስባኝ አታውቅም ፤ የኛ አምሪ ሁሉንም ነገር ታውቃለች...የኛ አምሪ " ሁሉም ሳቁ.... በአምሪያ ማሾፉ ነው የፋሩቅ ድምፅ ነበር።
" እናቷ ግን አምሪያ የሌለ ነው ከረያን ጋር እንድትሆን የፈለገችው "
" ማነው ቆይ በአሁን ጊዜ ጭራሽ በልጅነታቸው ወደፊት እንዲጋቡ የሚስማማው? ጉድ እኮ ነው " ሚኪም ፋሩቅን ማገዝ ጀመረ። አምሪያ ወደበሩ ጠጋ ብላ የሚሉትን በደንብ መስማት ቀጠለች።
" እ ሙሽራው...አሁንማስ ሚስት አለህ...ምን ተሰማህ? " ፋሩቅ በእጁ የያዘውን ሀይላድ እንደማይክራፎን ተጠቅሞ ይጠይቀዋል።
" ሂድ እስኪ ወደዛ አትጃጃልብኝ..." ረያን ቁጭ ብሎ ስልኩን ከመነካካት ውጪ ምንም አላላቸውም ነበር።

አምሪያ ከዚ በላይ እንዲያወሩ አልፈለገችም በሩን አንኳኳች። ፋሩቅ ተነስቶ ከፈተ። ሲያያት በጣም ነው የደነገጠው ያወራውን ሰምታ ከሆነ በሚል...
" አፉወን ትንሽ ጉንፋን ይዞኝ ሶፍት ፈልጌ ነበር.. ካለ ላስቸግርህ..." ያወሩትን እንደሰማች ለማሳወቅ ያክል እንጂ ሶፍት እንኳን እሷ ጋር ራሱ ነበር።
" ረያን ሶፍት ፈልጋ ነው ስጣት..." ፋሩቅ ረያንን አጋፍጦ ዘወር አለ።

ረያን ሶፍቱን ይዞላት መጣና ሰጣት።
" አሁን ያወራነውን ነገር እንዳለ ሰምተሻል አይደል? " ረያን በባህሪው ድብብቆሽ አይወድም። የተሰማውን በግልፅ ነው የሚናገረው።
" አታስብ እኔም ማግባት አልፈልግም እላቸውና ቃሉን እናፈርሰዋለን። አሁንስ ደስ አለህ? "
" አዎ! " አላት ፈገግ እያለ እሱም የሚፈልገው እሱን ነበር።
" ኦው እንደዛ ከሆነ ቃላቸውን አከብራለው። አላፈርሰውም። "
በስንቱ ነገር ትቃጠላለች "አንተን ደስ እንዲልህማ አላደርግም። " እያለች ባለበት ጥላው ወደሳሎን ተመለሰች።

*

በዚ መልኩ ነበር በአዲሱ ከተማዋ የመጀመሪያ ቀንዋን የጀመረችው። ግብዣቸውን ጨርሰው ወደቤት ከተመለሱ በኋላ የጋብቻውን ጉዳይ ማንሳት ስላልፈለገች ቀጥታ ወደመኝታ ከፍሏ ገብታ ተኛች።

ጠዋት ላይ 11 ሰአት ሲል ከእንቅልፏ ተነሳች። ሁሌም 11 ሰአት ላይ አምሪያን ተኝታ ማግኘት የማይታሰብ ነው። አንዳንዴም ከዛ በፊት ትነሳለች።የትናንቱ ድካም እንዲለቃት ተነስታ ሻወር ከወሰደች በኋላ የሱብሂ ሰላትን በዛው ሰገደች። 2 ገፅ ቁርዓን ከቀራች በኋላ እዛው መስገጃዋ ላይ ጋደም አለች። ከፈጣሪዋ ጋር ለማውራት...

በፊት ላይ አምሪያ ከቤተሰቦቿ ጋር ያን ያህል ቅርርብ አልነበራትም። በተለይ ከዛሬ 7 አመት በፊት ማለትም አምሪያ የ10 አመት ልጅ በነበረችበት ጊዜ ሰሚር ከተወለደ በኋላ እናትና አባቷ ለሷ የነበራቸውን ትኩረት እሱ ጠቅልሎ እንደወሰደው ነው የምታስበው። እሱ ከተወለደ በኋላ ለሱ የተለየ እንክብካቤ ሲሰጥ እያየች ነው ያደገችው። በእርግጥ እነሱ ጠልተዋት እንዳልሆነ በደንብ ታውቃለች ግን ህፃን ነው በሚል ለሱ የሚሰጠው የተለየ እንክብካቤ በልጅነት አዕምሮዋ የአልወደድም ስሜት ፈጥሮባታል።

አብዛኛው የልጅነት ትውስታዋ ማታ ማታ በእንባ የምታረጥበው ትራሷ ነው። ቤት ውስጥ ምንም ቢፈጠር ጥፋተኛ እሷ ናት ፤ ከወንድሟ ጋር ከተጣላች ሁሌም እሷ ናት በዳይ ሁሌም እሷ ናት ተከሳሽ! በዚ ምክንያት ከቤተሰቦቿ ጋር ያላት ቅርርብ እየቀነሰ መጣ። ከነሱ ጋር ከምታሳልፈው ጊዜ ይበልጥ ብቻዋን ክፍሏ የምታሳልፈው ጊዜ ይበልጥ ነበር። እያደገች ስትመጣ ህመሞቿን ከፈጣሪዋ ጋር ማውራት እሱን ማማከር ጀመረች። የዛኔ የብቸኝነት ስሜት አይሰማትም ፤ የልቧን ስትነፍስ እላይዋ ላይ የተጫነ የሚመስላት ሸክም ይራገፋል ፤ ተስፋ ልቧ ውስጥ ይሞላል ፤ እሱን ስታዋራ ሁሌም ፈገግ ትላለች። በዛ ምክንያት የመጣ ልምድ ነበር...
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
አሁን ያ ታሪክ ነው። መቼስ እናት የልብን ታውቃለችና የአምሪያ ከነሱ መራቅ በጣም ስላስጨነቃት አናግራት ነበር። አምሪያም ልትደብቃት አልፈለገችም የሚሰማትን በሙሉ ነገረቻት። የዛን ቀን እናቷ ያነባችውን እንባ ዛሬም ድረስ አትረሳውም። እንደዚ እንዲሰማት አድርገው ስላሳደጓት ይቅርታ ጠየቋት። ከዛ በኋላ በአላህ ፍቃድ ነገሮች እየተቀየሩ መጡ። እሷም ብቻዋን መኮራመት አቁማ ጊዜዋን ከነሱ ጋር ማሳለፍ ጀምራለች።

*

" አሰላም አለይኩም...አሙዬ ተነስተሻል አይደል.." እናቷ የክፍሏን በር ከፍታ እየገባች
" ወአለይኩም አሰላም...አዎ እማ ተነስቻለው። "
" ድምፅሽን እኮ ሳጣው ጊዜ የተኛሽ መስሎኝ ልቀሰቅስሽ ነበር። "
" ውይ እማ እኔ ነኝ በዚ ሰአት የምተኛው...ባይሆን ሳላግዝሽ ..."
" ኧረ እንኳንም አልመጣሽ። እኔ መች አንስና ለስራው... ቁርስ ደርሷል ነይ እንብላ..."
መስገጃዋ ላይ ጋደም ብላ ሰአቱንም አላስተዋለችውም ነበር።
" እሺ እናቴ መጣው..." ተነስታ መስገጃዋን አነጣጥፋ ተከትላት ወጣች።

ቁርስ ከበሉ በኋላ አምሪያ ቡና አፍልታላቸው ረፈድ እስከሚል ድረስ ሲጨዋወቱ ቆዩ። ነገ አዲስ አመት ትምህርት ስለሚጀምሩ ወደ 5 ሰአት ላይ ለነገ የሚያስፈልጋቸውን ያልጨረሱትን ነገር ለመገዛዛትና በዛውም ትምህርት ቤታቸውን ለማየት ወጡ። የሰሚር ትምህርት ቤት እዛው ሰፈራቸው ያለ ስለነበር አያስቸግራቸውም። የአምሪያ ግን ከቤታቸው ትንሽ ይርቃል። ረያን የሚማርበት ትምህርት ቤት ነው። ሰሚር ልጅ ስለሆነ እንዳይርቅ ስለፈለጉና እሱ የገባበት ትምህርት ቤት እስከ 8 ብቻ ስለሆነ ነው አንድ ትምህርት ቤት ያልገቡት። እዛ የነበሩ ጊዜ አባታቸው ስለሆነ እዚ ያለውን ያስመዘገባቸው ትምህርት ቤቱን ያውቀዋል። ከዚ በፊትም ለስራ ወደ አዲስ ይመላለስ ነበር። እንዲው ቀኑን ሙሉ ሲዞሩ ውለው አመሻሽ ላይ ወደ ቤት ተመለሱ። አምሪያና ሰሚር ከተማውን ጭራሽ ስለማያውቁት ለነሱ ጥሩ አጋጣሚ ነበር።

*

ብርሀኑ በጨለማ ተተክቶ መልሶ ደሞ ብርሀን ማንጨላጨል ሲጀምር አምሪያ እንደልማዷ ከእንቅልፏ ተነሳች። ሰላቷን ከሰገደች በኋላ ከእናቷ ጋር ቁርሱን አዘገጃጁ። 1 ሰአህ ላይ ከሌሎች ቀደም ብላ ቁርሷን በልታ ሁሉንም ነገር በጊዜ ጨራርሳ ቁጭ አለች። አምሪ የጠዋት ሰው ናት። ማርፈድ አትወድም። ለመውጣት ጫማዋን እያደረገች እያለ ስልኳ ሲጮህ ሰማች።
" አርጊ አንቺ ቆይ እኔ አመጣልሻለው..." ብላ እናቷ ስልኳን ይዛላት መጣች። ቁጥሩን አታውቀውም...ግራ እየተጋባች አነሳችው...
" ሄሎ "
" በሩ ጋር ነኝ ቶሎ ውጪ..." ስልኩ ተዘጋ። የደወለው ወንድ ከመሆኑ ውጪ ምንም ያወቀችው ነገር የለም። እዚ ከተማ አዲስ ናት ማንም አያውቃትም።
" ያመዋል እንዴ? " ስልኳን ከየት እንዳገኘው ራሱ ግራ ገብቷታል...
" ምነው? ማነው ቆይ? "
" እኔንጃ እማ ተዪው የዞረበት ነው...በቃ ክፍሌ መልሺልኝ...እኔም ልውጣ ይረፍድብኛል። " ግንባሯን ስማት እየተጣደፈች ወጣች።
የግቢውን በር ከፍታ እንደወጣች እውነትም አንድ ሰው በሩ ጋር ቆሞ እየጠበቃት ነበር..

#ክፍል_ሶስት ( ⓷ ) .. ይቀጥላል....
┍─━─━─┙◆┕━─━──╝
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━━━─╝



. #ክፍል_ሶስት ( ⓷ )
┗•━•━•━ ◎ ━•━•━•┛

" ሰውዬ ስራ የለህም እንዴ? በጠዋቱ ሰው በር ላይ ምን ይገትርሀል? "
" ኧረ አሰላም አላይኩም ማለት ይቀድማል..."
" ምን ላድርግ? ገና አንተን ሳይህ ነው ደሜ መፍላት የሚጀምረው! "
" የሚፈላውን ደምሽን በዚ አብርጂው። " በእጁ የያዘውን እቃ ወርውሮ አቀበላት።
የሰጣትን ፌስታል ከፈተችው። የለውዝ ቅቤ የተቀባ ዳቦ... በጣም የምትወደው ምግብ ነው። ፈገግ እያለች ተመለከተችው። " አታፍጪ እኔ አይደለውም እናቴ ናት የላከችልሽ..."
ፊቱን በአንዴ ቀየረችው " አንተማስ ድሮውንም የሰውን ጨጓራ ከመላጥ ውጪ ሌላ ምን ታውቃለህ? ቆይ ግን ይሄን ልትሰጠኝ ነው ስጠብቀኝ የነበረው..."
" ረዩ እስካሁን እዚ ናቹ እንዴ? " እናቱ ወደነሱ ጋር መጣች። " አሰላም አለይኩም አምሪያዬ...ደና አደርሽ "
" ወአለይኩም አሰላም...እንዴት አደሩ የረያን እናት..."
" ' የረያን እናት!? ' ኧረ እንደዛ እያልሽማ አታርቂኝ...እናቴ ብለሽ ጥሪኝ። ወይስ ከእናትሽ ውጪ ሌላ እናት አትፈልጊም? "
" ኧረ እንደዛ ማለቴ አይደለም..."
" በሉ በቃ አላስረፍድባችሁ ሂዱ። መቼስ እሱ እያለ ብቻሽን አልክሽም ብዬ ነው። ለከተማው አዲስ ነሽ ፤ በዛ ላይ ሴት ነሽ..ከሰው ጋር መሆኑ ነው ጥሩ። "
" አዎ ልክ ነሽ እናቴ አመሰግናለው። "
" ሱቅ እየሄድኩ ነው አብረን እንውጣ እስከሱቁ ድረስ..."

ሱቁ ጋር እንደደረሱ እናቱን ሰላም ብለው እነሱ ይሄዳሉ።
" ቅድም የጠየቅሽኝን ጥያቄ መመለስ የሚጠበቅብኝ አይመስለኝም...ከእናቴ ሰምተሽዋል። " ምንም አላለችውም። የተሰጣን እየበላች እንዲው ዝም እንደተባባሉ ትምህርት ቤት ይደርሳሉ።

ግቢ ከገቡ በኋላ ረያንን እየተከተለች ወደመማሪያ ክፍላቸው ገቡ።
" ኧረ በለው..እዚ ጋርማ የሆነ ለውጥ አለ..." አብረው መምጣታቸው ግራ አጋብቶታል። ፋሩቅ ነው። " ማነው ደሞ ዛሬ ፈቶ የለቀቃችሁ...ሰላምታም የሚባል አልፈጠረባችሁም..." ሰላም ካለው በኋላ ፋሩቅ የጠቀመጠበት ጋር ተቀመጠ።
" ጭራሽ የረያን ሲያንስ ከፋሩቅ ጋርም አንድ ክፍል ነን... አምሪያ ተቃጠልሽ ዘንድሮስ..." ብቻዋን ማጉረምረም ጀመረች። " ምን አልሽ አላት ረያን " እሱን እያዋራች መስሎታል። " ኧረ ምንም " እነረያንን አልፋ ባዶ ቦታ ፍለጋ ሄደች።
" ወዴት ነሽ ነይ እንጂ..." ቦርሳውን ጎትቶ መለሳት።
" ይኸው እዚ ጋር ቁጭ በይ...አብራሽ የምትቀመጠዋ ልጅ ትንሽ ቆይታ ትመጣለች። " እንደአወራራቸው ከሆነ የሚቀመጡበትን ቦታ ቀድመው አዘጋጅተዋል።
" ይኸው እንደውም መጣችልሽ..." አምሪያ ወደ በሩ ጋር አይኗን ወረወረች። በትንሹ ወፈር ያለች ቀይ ቆንጅዬ ልጅ እነሱ ወዳሉበት ጋር እየመጣች ነው።
" አሰላም አለይኩም ሰዎች..." ወደነሱ ጋር መታ ቆመች።
" ወአለይኩም አሰላም...ምንድን ነው ገና በመጀመሪየው ቀን ማርፈድ.." ፋሩቅ ቦርሳውን ተቅብሎ ከፊታቸው ያለው ወንበር ላይ አስቀመጠላት።
" ታክሲ አጥቼ እኮ ነው በአላህ...ደሞ ዘንድሮም እዚ ነን" የተቀመጡበትን ቦታ እያየችው። በየአመቱ የገቡበት ክፍል መስኮት ያለው መደዳ መጨረሻ አከባቢ ነው የሚቀመጡት። አምሪያ አሁን የሶስቱ ቅርርብ በጣም የቆየ እንደሆነ ተረድታለች።
" ኧረ ረዩ ክረምቱ ደሞ ተስማምቶሀል እ..አምሮብሀል..."
" አዎ በጣም ተስማምቶኝ ነበር መጨረሻ ላይ ተበላሸ እንጂ..." ቀና ብሎ አምሪያን ተመለከታት።
" አምሪያ ማለት እሷ ናት ተዋወቁ..."
" ኦ አንቺ ነሽ ሚስቱ...ማለቴ አብሮአደጉ..." ተጠምጥማ ሰላም አለቻት።
ረያን ፋሩቅ ላይ አፈጠጠባት። ከሱ ውጪ ማንም ሊነግራት እንደማይችል ያውቀዋል። ፋሩቅም ለምን እንደሚያፈጥበት ገብቶታል " አታፍጥብኝ ሰብሪንን ምንም እንደማልደብቃት ታውቃለህ..." አምሪያ እያጠናቻቸው ይመስል ዝም ብላ እነሱን ከመመልከት ውጪ ምንም አታወራም።

እንደተቀመጡ " ከፋሩቅ ጋር አብሮአደጎች ነን...በጣም ስለምንቀራረብ ነው የነገረኝ...አልደበረሽም አይደል? " አለቻት። ዝምታዋ የደበራት ስለመሰላት ጨንቋታል። እሷም መጠየቅ የፈለገችው ጥያቄ ነበር። ቀድማ ስለነገረቻት እንደውም ደስ አላት። " ኧረ አልደበረኝም አብሽሪ... " አሁን ፈገግ ማለት ጀመረች። እዚ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ቀኗ ቢሆንም አብራቸው ስለምትውለው ጓደኞች ግን ምንም የሚያስጨንቃት ነገር የለም። ረያን ፣ ፋሩቅ ፣ ሰብሪን። ደስ የሚል ጓደኝነት ያላቸው ይመስላል። እሷም የዚ ግሩፕ አባል ስለሆነች ደስ ብሏታል። በነገራችን ላይ የነረያን ጓደኛ ሚኪያስ በዚ አመት ሰፈር በመቀየሩ ምክንያት ትምህርት ቤትም ስለቀየረ ነው እንጂ እሱም የዚ ግሩፕ አባል ነበር።

*

የአራቱም ቤት አቅጣጫ አንድ መስመር ስለሆነ ከትምህርት ቤት መልስም አብረው ነው የሚሄዱት። መሀል ላይ ሰብሪን ቀድማ ከተሰናበታቸው በኋላ ሰፈር ሊደርሱ ትንሽ ሲቀረው ፋሩቅ ይገነጠላል።።

ከፋሩቅ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቁበት መንገድ ደስ ባይልም አሁን ግን እንደዛ አይደሉም። ፋሩቅ ጭራሽ የረሳው ነው የሚመስለው። ሰብሪንም ጓደኝነታቸውን ካየች በኋላ ከዚ በፊት የተፈጠረውን እረስታ ጥሩ ጓደኛቸው ለመሆን እየሞከረች ነው። የመጀመሪያ ቀን ውሎዋ እንደጠበችው ሳይሆን በተቃራኒው ደስ የሚል ነበር።
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. ከቀን ወደ ቀን ከረያን ጋር ያላቸው ቅርርብ በትንሹም ቢሆን እየጠነከረ ሄደ። በጓደኞቿም በጣም ደስተኛ ሆነች።

" ይሄን ሰሞን ግን አምሪያ ላይ በጣም ትኩረትህን ስታደርግ እያየውህ ነው..." ፋሩቅ ነው ጠያቄው።ክፍል ውስጥ አምሪያና ሰብሪና ስላልነበሩ አሪፍ አጋጣሚ ስላገኘ ነው አሁን የጠየቀው ።
" አንድ ክፍል ነን። በዛ ላይ ቤተሰቦቻችን በደንብ ይተዋወቃሉ። ያው ልጠብቃት ግድ ነው... እና ችግሩ ምኑ ጋር ነው? "
" no no እኔ እንኳን እንደዛ አይመስለኝም...የሆነ ነገርማ አለ... ወደድካት እንዴ? "

" ምንድን ነው የምትቀባጥረው..." ረያን ነገሩን በቀለድ አርጎ ለማለፍ ቢሞክርም ፋሩቅ ግን አልፋታ አለው።
" እኔን ልትደብቀኝ ባልሆነ... " ፋሩቅ ኮስተር ለማለት ይሞክራል።

በዚ ሰአት አምሪያና ሰብሪና ወደክፍል እየገቡ ነበር። እነረያን ፊታቸውን በመስኮት በኩል አውጥተው ስለነበር እያወሩ ያሉት የነ አምሪያን መምጣት አላስተዋሉም። ለጥያቄው መልስ ከሰጠው በኋላ ነበር ወደመቀመጫቸው ሊሄዱ ሲሉ የነአምሪያን ፊት አይተው የመለሰለትን መልስ እነአምሪያ እንደሰሙ ያወቁት።

#ክፍልአራት..⓸ ይቀጥላል....
┍──━──━──┙◆┕──━
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━━━

. #ክፍል_አራት ( ⓸ )
❦•⊰❂⊱• ════ ❦

" እኔን ልትደብቀኝ ባልሆነ... " ፋሩቅ ኮስተር ለማለት ይሞክራል።
" እየደበኩህ አይደለም ግን በዚች አጭር ጊዜ ምን ይፈጠራል ብለህ ጠብቀህ ነው? "
" ማነው ደሞ ፍቅርን በጊዜ ቀጠሮ ያደረገው? አሁን አጭር መልስ ነው የምፈልገው...ወደሀታል? ወይስ አልወደድካትም? "
" አልወደድኳትም...እኔን ስታቀኝ በቀላሉ ፍቅር የሚይዘኝ አይነት ሰው ነኝ? ሲጀመር ምን የሚወደድ ነገር አላትና ነው? "
" በለውውው...ለዛ ነዋ ባለፈው መፅሀፍ ያላመጣ ሲቀጣ ያንተን መፅሀፍ ሰተሀት የተቀጣህላት...እ? ምንም የሚወደድ ነገር ስለሌላት ነው ጠዋት ጠዋት ምግብ የምትሰጣት? ቤት የማያበሏት ይመስል..." ፋሩቅ የሹፈት ሳቅ ይስቅበታል።
" ምግቡን እናቴ ናት የምትልክላት... ደሞ ነገረኛ ሚስት አግብቼ ልቃጠል እንዴ? ለጠላቴም አልመኘው..."
" እንዲ ነው የሚያደርገው እኮ ሲጀማምር..."
" በዞረበትም አልዞርም "
" እሱን አብረን እናያለን "

ወደመቀመጫቸው ሊሄዱ ሲሉ እነአምሪያን አይዋቸው። " እናንተ ደሞ ኮቴም የላችሁም እንዴ? " ሁለቱም ነበር የደነገጡት። እነአምሪያ ምንም መልስ ሳይሰጡአቸው እንዳልሰማ ሰው ወደወንበራቸው ሄደው ተቀመጡ።

*

ብዙ ቀናቶች አልፈው የሴሚስተሩን የመጀመሪያው ፈተና ውጤት እየተቀበሉ ነበር። አምሪያ በፊት የነበረችበት ከተማ ጎበዝ የምትባል ተማሪ የነበረች ቢሆንም እዚ ከመጣች በኋላ ግን የተወሰነ ከብዷት ነበር። ረያን ደሞ በተቃራኒው የክፍሉ ሰቃይ ልጅ እንደሆነ የሰማችው በቅርቡ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ የደረጃ ተማሪ ነበር። እዚም ብዙ ቦታዎች ላይ ተወዳድሮ ለትምህርት ቤቱ ብዙ ዋንጫ እንዳስገኘ ስትሰማ ማመን ከብዷት ነበር። የማትሪክ ውጤታቸው የሷ ከሱ ይበልጥ ስለነበር ይሄን ያህል ጎበዝ ይሆናል ብላ አልጠበቀችም። ያው የአንድ ጊዜ ፈተና ሰውን በትክክል አይገልፅም።

" ይሄ ሁሉ ልዩነት!? " የሷንና የረያንን የፈተና ውጤት አንድ ላይ አስቀምጣ ታስተያያለች።
" የተሳሳትሻቸውን ጥያቄዎች መጠየቅ ትችያለሽ.." አላት።
" ክላስ ውስጥ በትክክል ራሱ አታዳምጥም...ቆይ በምን ዘዴ ነው እንደዚ ሰቃይ የሆንከው? "
" ፀባይሽ ታይቶ ወደፊት ይነገርሻል..." ፈገግ ብሎ አያት። እሷ ግን ፊቷን እንዳጠለች ነው።
" ይሄ እኮ ገና የመጀመሪያ ፈተና ነው። ቀጣይ ታስተካክያለሽ ኢንሻአላህ " እንደደበራት ሲያይ ለማፅናናት መሞከር ጀመረ።
" ታውቃለህ...? ልጅ እያለው በጣም ሰነፍ ተማሪ ነበርኩ። ሌሎች ልጆች በቀላሉ በቃላቸው የሚይዙትን ነገር እኔ ከአንድ ወር በላይ ታግዬ ነው የምይዘው። የሆነ ጊዜ ፈተና በጣም ዝቅተኛ አምጥቼ ሳለቅስ ሳሊም የሚባል ልጅ መጦ አፅናናኝ። ምን እንዳለኝ ታውቃለህ? ' ሌሎች ሰርተውት አንቺ መስራት የማትችዪው ምንም ነገር የለም። ያንን ነገር መስራት አልቻልሽም ማለት በደንብ አልጣርሽም ፤ በደንብ አልታገልሽም ማለት ነው። ' ንግግሩ ቀላል ይመስላል ግን እውነት አለበት። በዛን ሰአት የሱ ንግግር በደንብ አጠንክሮኝ ነበር። ሌሎች ተማሪዎች አንድን ስራ ለመስራት 1 ሰአት ከፈጀባቸው እኔ ደሞ 2 ሰአት ወስጄ በደንብ እሰራዋለው። "
" አሀ ሁሌ ማታ ማታ ይሄ ሁላ ሰአት ስለምትፈጂ አርፍደሽ እየተኛሽ ነው ትምህርት ቤት መተሽ የምታንቀላፊው ለካ... "
" ሁሉም ሰው እንዳንተ መሰለህ እንዴ? አንድ ጊዜ ብቻ አንብቦ በደንብ የሚያስታውሰው..."
" እኔና አንቺ መሀል ያለው ልዩነት የምንጠቀመው ዘዴ ነው። ለማንኛውም ለአሁን ያጣሻቸውን ጥያቄዎች ላስረዳሽ..."
" እናንተ አትነሱም እንዴ? ሰአት እኮ እየሄደ ነው..." ሰብሪና ቦርሳዋን እየዘጋጋች ተነሳች።
በፈተናው ውጤት ሀሳባቸው ተወስዶ ቀኑ ጁምዓ መሆኑን እረስተውት ነበር። ሁሉም እቃቸውን ወደቦርሳቸው በፍጥነት ከተው ተነሱ።

ጁምዓ ቀን ሳይደወል በፊት ነው እነሱ ቀድመው የሚወጡት። ለአስተማሪያቸው ለሰላት መውጫ የተሰጣቸውን ካርድ ገና ሳያሳዩት አጠገቡ እንደደረሱ " እስካሁን ምን እየሰራችሁ ነው? አልረፈደም " ፈገግ እያለ እንዲወጡ ፈቀደላቸው። በደንብ ስለሚያውቃቸው እና ሁሌም ጁምዓ ቀን የሚያደርጉት ነገር ስለሆነ ያውቀዋል። ክፍል ውስጥ ሌሎች ሙስሊም ተማሪዎች በሙሉ ቀድመው ወጥተው ነበር።

ወደ መስጂዱ አከባቢ ሲደርሱ ፋሩቅ የዩኒፎርሙን ሹራብ አውልቆ ለሰብሪን ሰጣት። ለምን እንደሰጣት ሁሉም ግራ ስለተጋቡ አፈጠጡበት።
" ለሰላት እግርሽን እድትሸፍኚበት ነው..." ያረገችው ክፍት ጫማ ስለሆነ ከቁርጭምጭሚቷ በታች እግሯ ይታይ ነበር።
" አመሰግናለው! " ብላው እነረያን ወደወንዶች መግቢያ ሲሄዱ እነአምሪያ ደሞ ወደሴቶቹ መግቢያ ተገነጠሉ።

*

ቀጣይ ቀን ጠዋት ላይ ረያን ከግቢ ሲወጣ እሷም ከግቢ እየወጣች ተገናኙ። " ቁርስ..." በእጇ የያዘችውን ትንሽ ምሳቃ ሰጠችው። እሱም ያዘጋጀውን ጁስ ሰጣት። ሁሌም ጠዋት ጠዋት አንዳቸው ለአንዳቸው ምግብ ወይም መጠጥ ማምጣት ግዴታ የተደረገባቸው ይመስል ሳያመጡ ቀርተው አያውቁም።

" ፈጠን ፈጠን እያልሽ መራመድ ትችያለሽ? ምንድን ነው የሚያንቀራፍፍሽ? ኤሊ ነሽ እንዴ? " ከሷ ጋር መከራከር ደስ ይለዋል።
" ቦርሳዬ ከባድ ስለሆነ ነው ባክህ..."
" ከቤት የተባረርሽ ይመስል የመፅሀፍ መአት ይዘሽ እየዞርሽ ባይከብድሽ ነበር የሚገርመኝ። "
እዛው እንዳዘለችው ቦርሳውን በእጁ ከፍ አድርጎ ያዘላት። ቦርሳው እሷ ጀርባ ላይ ሆነ እንጂ ሙሉ በሙሉ የያዘው እሱ ነው። እዛው እንዳቀረቀረች ፈገግ አለች።

እስከትምህርት ቤት ድረስ እንደዛው ከሄዱ በዋላ " በቃ አሁን እራሴ ይዘዋለው " ብላ አስለቀቀችው።
ልክ መግቢያው ጋር እንደደረሱ እነረያን ያሉበት ጋር ከአንድ መኪና ውስጥ አንዲት ልጅ ወረደች።
" ረያን..." እሷ ናት የጠራችው።
" ጄሪ..."
" ደና ነህ? " ስታወራው ጥርሷ ብቻ አይደለም ፊቷም ሙሉ ይስቃል። አምሪያ አጠገቡ እንደቆመች ነው።
" አልሀምዱሊላህ...አሁን በደንብ ተሻለሽ? "
" አዎ ግን ትምህርት ብዙ አምልጦኛል..."
" አይዞሽ...ላንቺ አይከብድሽም። እኛም እናግዝሻለን።
" አመሰግናለው...በቃ በኋላ እንገናኛለን..." ቀድማቸው ሄደች።

" እሷ ናት ባለፈው ሀኪም ቤት ሄዳችሁ የጠየቃችኋት? " ትምህርት የተጀመረ ሰሞን የክፍሉ ነባር ተማሪዎች ተሰብስበው አንዲትን ተማሪ ለመጠየቅ እንደሄዱ ሰምታ ነበር።
" አዎ..እየሩስ ትባላለች "
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
ክፍል እንደገቡ ፋሩቅ እየሮጠ ወደ ረያን ጋር መጣ። ሰብሪን ከኋላው ተከትላው ገባች።
" ጄሪ መጣች የሚባለው ነገር እውነት ነው እንዴ!? "
" አዎ አላየኸትም እስካሁን? "
" ኳስ እየተጫወትኩ ነበር ባክህ..."
" አይዞህ ትንሽ ቆይታ ትመጣለች ወደቢሮ ሄዳ ነው "
" የቱ ጋር ነው የምትቀመጠው?"
ረያን በእጁ አመልክቶ አሳየው።
" ደሞ ታማ የቆየች አትመስልም በጣም አምሮባታል አሉ...አጠገቧ የሚቀመጠውን ልጅ ቦታ ቀይረኝ ልበለው እንዴ? " ሰብሪን ሳታውቅ አስመስላ እረግጣው አለፈች።
" አንቺ ያምሻል እንዴ? "
" ውይ አፉወን አላየውህም...ምነው ቆየህ ሂድና ቀይረዋ? " ተናዳለች።
ረያንና አምሪያ ተያይተው ተሳሳቁ።
" ብታይ አምሪ ሀይስኩል እያለን ጄሪ እና ረዩ በጣም ነበር የሚቀራረቡት...አይደል? " ወደረያን ዞረ...ረያን ምንም ሳይለው ከቦርሳው መፅሀፍ አውጥቶ ማንበብ ጀመረ።
" እረስተኸው ባልሆነ? ኧረ ሁላ የግቢው ተማሪ እንዳለ በጣም ይቀናባቸው ነበር..."አነጋገሩ አምሪያን ለማናደድ ይመስላል።
" እሷም ጎበዝ ተማሪ ስለሆነች በጥናት እንተጋገዝ ነበር። ያው ሰውን ታውቂው የለ? ነገሩን ወደሌላ ነገር ወስደውት ነው እንጂ ምንም ነገር በመሀላችን የለም። " ሲያወራ አምሪያን እየተመለከተ ነው።
" እኔ እኮ ነኝ የጠየኩህ ለምንድን ነው ለአምሪያ የምታብራራላት " ብቻውን መሳቅ ጀመረ። ሰብሪ አሁንም እንደተናደደች ናት። አምሪያም ትኩረት እንዳልሰጠችው ስላስመሰለች ዝምታ እንደሚያዋጣው አስቦ ሄዶ ተቀመጠ።

ትንሽ እንደቆዩ የክፍላቸው አላፊ ወደክፍል ገባ።
" ያው እንደምታውቁት ብዙ ክበቦች አሉን። እና በዛ ክበብ ላይ መሪ የሚሆነው ተማሪ በየአመቱ ከክፍል ክፍል ይቀያየራል። በአሁኑ አመት ደሞ የኛ ክፍል ነው። እናም ዛሬ በተለያዩ ክበቦች ላይ መሪ የሚሆን ሰው እንመርጣለን። መሪዎች ከተመረጣችሁ በኋላ አባል መሆን የሚፈልግን ተማሪ ከነገ ጀምሮ መመዝገብ ትችላላችሁ። ማወቅ ያለባችሁ ነገር እነዚ ክበቦች ላይ መሪ ሆናችሁ ስትሰሩ መጨረሻ አመት ላይ የምስክር ወረቀት ይሰጣችኋል። የምስክር ወረቀት ደሞ ዝም ብሎ ነገር አይደለም ለምሳሌ scholar መሞከር ለምትፈልጉ ልጆች በጣም ይጠቅማችኋል። ከዛ ውጪም ወደፊት ስራ ለመቀጠር ይዛችሁ ከምትሄዱት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱ እሱ ይሆናል። ምክንያቱም ትጉ ሰራተኞች ፣ ምርጥ አለቃዎች እንደነበራችሁ ያ ወረቀት ስለሚመሰክር። ከዛም በተረፈ በትምህርት ቤት ላይ ጉዞዎች ሲኖሩ ለናንተ ያለ ምንም ክፍያ ነው እንድትሄዱ የሚደረገው። እና መስራት እችላለው የምትሉ ሰዎች እድሉን ተጠቀሙበት። "

አስተማሪው ተራ በተራ የክበቦችን ስም እየጠራ መሪዎችን መመዝገብ ጀመረ።
የስፖርት ክበብ ጋር ሲደርስ ወድያው ፋሩቅና ሰለሞን ከመቀመጫቸው ተስፈንጥረው ተነሱ።
" ኧረ ቁጭ በል በናትህ..." ፋሩቅ ሊለምነው ፈለገ...
" ለምን ቁጭ እላለው...እኩልነት የሚባል ነገር እኮ አለ..." ሰለሞንም አልተስማማለትም።
" ባለፈው የጠየከኝን የመረብ ኳስ እሰጥሀለው..."
" አምንሀለው...መልካም የስራ ዘመን " ወድያው ቁጭ አለ። የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ ሳቁ።
" እንግዲ ምንም አታስቡ ተወዳዳሪ የሌላው ክበብ እንሆናለን! " ሁሉም አጨብጭበው መሪነቱን አስረከቡት።

ቀጣዩ የኪነጥበብ ክበብ ነበር። ሰብሪና ወደኋላ ዞራ አምሪን ተነሺ እያለች ትጨቀጭቃታለች። የሆነ ጊዜ ቤቷ ሄዳ የሳለቻቸውን ስዕል አይታ ነበር። ከዛም ውጪ በትልልቁ ተስለው መኝታ ክፍሏ ላይ የተሰቀሉም ነበሩ። ህይወት ካላቸው ነገሮች ውጪ ሁሉንም ትስላለች። Calligraphy ላይም በጣም ጎበዝ ናት።

አምሪያ ልትነሳ ስትል ጄሪ ቀድማት ተነሳች።
" መፃፍና መተወን በጣም እወዳለሁ! ባለፈው አመት በግጥም ትምህርት ቤቱን ወክዬ ተወዳድሬ አሸናፊ ሆኜ ነበር። እኔን ከመረጣችሁኝ ሁሉንም ሰው በታማኝነት አገለግላለሁ። በጥበብ አብረን እንጓዛለን! " እንዲ ከማለቷ ወድያው አምሪያ ከመቀመጫዋ ተነሳች "እኔም ለጥበብ ልዩ ፍቅር አለኝ! እኔን ከመረጣችሁኝ የእውነት ከልባችን እንሰራለን። መድረኮችን እንቆጣጠራለን! በውድድሮች ላይም አሸናፊ እንሆናለን! ኢንሻአላህ። "

" ያው ሁለት ሰው መሪ መሆን አይችልም እናም ግዴታ በድምፅ ብልጫ እናደርገዋለን። " አስተማሪው አምሪያ ትሁን ያሉትን ሰዎች ድምፅ መቁጠር ጀመረ። 15 የሚል ብላክቦርዱ ላይ በትልቁ ፃፈ።
ቀጣይ ጄሪን የመረጡትን ሰዎች ድምፅ መቁጠር ጀመረ። አሁንም 15 የሚል ቁጥር ደግሞ ፃፈ። በሚገርም ሁኔታ የሁለቱም ድምፅ እኩል ነበር።

ረያን ለሁለቱም ድምፅ አልሰጠም ። ጄሪ የእውነትም ጎበዝ እንደሆነች ያውቃል። ተማሪም ብቻ ሳይሆን አስተማሪም የሚመሰክርላት ለትምህርት ቤቱ ዋንጫ ያስገኘች ልጅ ናት። በዚ ዙሪያ ስለአምሪያ ግን ምንም የሚያውቀው ነገር የለም። ብቻ ከአንድ በላይ ድምፅ መስጠት ስለማይቻል እና ሁለቱም እየጠበቁት ስለነበር አንዳቸው እንዳይቀየሙት ብሎ ለሁለቱም ድምፅ አልሰጠም። ሰብሪንና ፋሩቅ ለምን ለአምሪያ ድምፅ እንዳልሰጠ ግራ ተጋብተው ያዩታል።

" ቅድም ከሰጣችሁት ድምፅ ሀሳባችሁን የምትቀይሩ ወይም ቅድም ያልሰጣችሁ አሁን መስጠት የምትፈልጉ ካላችሁ...በናንተ ነው የውድድሩ ውጤት የሚወሰነው። " አለቃዋ ለጄሪም ለአምሪያም ድምፅ የሰጡትን ተማሪዎች ስለመዘገበች ማንም ማጭበርበር አይችልም። ለትንሽ ሰከንድ ከቆዩ በኋላ ረያን ለመምረጥ እጁን አወጣ። ሌላ ድምፅ የሚሰጥ ሰው ከሌለ እሱ የሚመርጠው ሰው ነው አሸናፊ የሚሆነው። ሁሉም የሱን መልስ ጥበቃ አይናቸውን ወደሱ ወረወሩት...

#ክፍል_አምስት ( ⓹ ) ይቀጥላል...
❦ ════ •⊰❂⊱• ════ ❦

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. " ስላንቺ "
[ ፀሀፊ፡ ሶፊያ አህመድ ]
╚─━━━━░★░━━━━─╝

. #ክፍል_አምስት ( ⓹ )
❦•⊰❂⊱• ════ ❦

ከሱ ውጪ ሀሳቡን የቀየረም ሆነ ሌላ ድምፅ የሰጠ ሰው ስላልነበር በረያን ድምፅ ምክንያት አሸናፊው ተወሰነ።

" መልካም የስራ ዘመን የተከበሩ " ፈገግ እያለ ተመለከታት። ምንም መልስ አልሰጠችውም ነበር ፈገግታውን በፈገግታ ከመመለስ ውጪ። አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ስሜቶች በቃላት ብቻ አይገለፁም። ለዛም ይሆናል አምሪ ምን ማለት እንዳለባት ግራ የገባት።

ለሷ እሷን መምረጡ ተራ ነገር አልነበረም። ስለክበቡ መሪነት ሳይሆን ስለልቡ መሪነት ነበር አብልጣ ያሰበችው። ከዚ በፊት ስለ ረያንና ስለጄሪ ብዙ ወሬዎችን ስለሰማች የእውነትም ፈርታ ነበር። በቀላሉ እንኳን ጄሪን እንደሚያወራት አንድ ቀንም እሷን አውርቷት አያውቅም። ይልቁንም ብዙ ጊዜያቸውን በክርክር ቢያሳልፉ እንጂ...አሁን ግን ስለሱ ብቻ ሳይሆን ስለራሷም ስሜት እንድታስብ ነው ያደረጋት።

" ከጄሪ ይልቅ እኔን መምረጡ ይሄን ያህል ለምን አስደሰተኝ? ቆይ ምን ሆኜ ነው? እየወደድኩት ነው እንዴ...? " አንገቷን አቀርቅራ ከራሷ ጋር ሙገት ገጠመች።
" ገና ስራ ሳይጀመር እንደዚ መጨናነቅ ተገቢ ነው? " በያዘው ደብተር ጭንቅላቷን መቶ ከገባችበት ሀሳብ አባነናት።
" አብሽሪ ብዙ አታስቢ በእድላቸው ያድጋሉ.."
" እነማን? "
" ልጆ..ቻችን...ማለቴ ልጆችሽ..." አንገቱን ወደመሬት አቀረቀረ።
" ቀልደህ ሞተኸል..." እሷም ፊቷን እሱ ወደሌለበት አቅጣጫ አዞረችው። ልቧ አከባቢ ግን የሆነ አዲስ ስሜት ተሰምቷታል። ዞራ ረያንን አየችውና ለራሷ ፈገግ አለች...

*

" ከወራቶች በኋላ "

የአመቱ የማጠቃለያ ፈተና ወቅት ስለነበር ሁሉም በጥናት ተጠምደዋል። የትምህርት ቤታቸው ላይብረሪ ውስጥ ተሰብስበው እያጠኑ ነው። ፋሩቅ መፅሀፍ አጠገቡ ያስቀምጥ እንጂ ከገባ ጀምሮ እስካሁን ድረስ መጀመሪያ ከገለጠበት ገፅ እንኳን ንቅንቅ አላረገውም። ረያን ይዞት ስለመጣ እንጂ እያጠና እንዳልሆነ ግልፅ ነው። ሰብሪን የተወሰነ ለማንበብ እየሞከረች ነው። ውጤቷ ከፋሩቅ በደንብ የተሻለ ቢሆንም እሷም ግን ብዙ ትኩረት የምትሰጥ አይነት ልጅ አይደለችም። በተቃራኒው የአምሪያ ጠረንጴዛ ላይ ብዙ መፅሀፎት ተበታትነዋል። እራሷን በጣም busy ለማድረግ እየሞከረች ነው።
ረያን መች እንዳጠና ባይታወቅም ጨርሶ እነሱን ለማገዝ ነው የመጣው። በእርግጥ አምሪያ ብቻ ናት ጥያቄ የምትጠይቀው። ይተኛና እሷ ስትጠይቀው ይነሳል።
ጥናቱ ለአምሪያ ቀላል አልነበረም። እሷም ግን ተስፋ መቁረጥ አልፈለገችም።ፈተና እስከሚደርስ ድረስ ጠዋትም ማታም እጇ ላይ ማስታወሻ ደብተር ወይም መፅከፍ ጠፍቶ አያውቅም።

ከሶስት የትግል ቀናት በኋላ የፈተናው ቀን ደረሰ። ጠዋት ላይ አራቱም ቀድመው ክፍል ተሰብስበው ያጠኑትን ለመፈተሽ እርስ በእርስ ጥያቄ መጠያየቅ ጀመሩ። በመሀል ግን አምሪያን ያማት ጀመር። ቀስ ብላ ሰብሪንን ጠርታት በጆሮዋ የሆነ ጥያቄ ጠየቀቻት። ሰብሪንም በአንገቷ " አይ " የሚል መልስ ሰጠቻት። ረያንና ፋሩቅ ሴቶቹ ለምን እንደሚንሾካሸኩ ግራ ተጋብተው ያዩአቸዋል።
" በጣም አሞሻል እንዴ" ? ተነስታ አጠገቧ ተቀመጠች።
" እያመመሽ ነው እንዴ? " አላት ረያን ፊቷ በአንዴ ሲቀየርበት ደንግጧል።
" ምኗን አሟት ነው? " ፋሩቅ በአንዴ መታመሟ ግራ አጋብቶታል። አምሪያ ምንም ሳትላቸው ሆዷን በእጇ ጨምቃ ጠረንጴዛው ላይ ጋደም አለች። ይሄን ሰሞን በፈተናው ተጠምዳ ቀኑን ስለረሳችው ነበር ምንም ነገር ያልተዘጋጀችው።

ሁሉም የሚሰሩትን አቆሙ። ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ ተጋብተዋል። ቀድሞውኑ ለፈተናው ስትጨናነቅ ነበር አሁን ደሞ ጭራሽ እያመማት መሆኑ ከሷም አልፎ ሁሉንም ረበሻቸው።

ሁሉም ዝም ብለው ሲተያዩ ረያን ተነስቶ ወጣ። ሰብሪን አጠገቧ ቁጭ እንዳለች ጀርባዋን ታሻሻታለች። ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ረያን በወረቀት አንድ እቃ ይዞ መጣና አምሪያ አጠገብ አስቀመጠላት። አምሪያ እንደተኛች ከፍታ አየችው። ሞዴስ ነበር...
" ከየት አግኝተህ ነው? " ድምፅዋ መዘጋት ጀምሯል።
" ከክሊኒክ ወስጄ ነው..."
" ከሴቶች ውጪ ለማንም አይሰጡም ነበር... እንዴት ሰጡህ? " አለች ሰብሪና ግራ እየተጋባች።
" አዎ እኔን እንቢ ብለውኝ ጄሪን ተቀበይልኝ ብያት እሷ ተቀበለችንኝ..." በጣም እንደተጨነቀ አይኑ ውስጥ በደንብ ይነበባል።

ወድያው ሰብሪን ደግፋት ተያይዘው ወጡ። አምሪም ትንሽ እንዲቀላት ፊቷን ተጣጥባ ሰብሪን እንደደገፈቻት ተመለሱ። እነሱ ጥያቄያቸውን እንዲቀጥሉ ነግራቸው መልሳ ተኛች።

የፈተና ሰአት ደርሶ አስተማሪው ወደክፍል ሲገባ ሁሉም የመፈተኛ ቦታቸውን መያዝ ጀመሩ። ሰብሪን እና ፋሩቅ " አይዞሽ " ብለዋት ወደቦታቸው ሄዱ። ረያን ግን በዚ ሰአት ብቻዋን ጥሏት ባይሄድ ደስ ይለው ነበር። ግን ምንም ማድረግ አይችልም መሄዱ ግድ ነው።
" አብሽሪ ብዙ አትጨነቂ... የቻልሽውን ብቻ ስሪ እሺ። " ከላይ ደርቦት የነበረውን ጃኬት አውልቆ አልብሷት ወደመቀመጫው ሄደ።

የመጀመሪያ ቀን ፈተናዋን በህመሟ ምክንያት ትኩረት ማድረግ ስላልቻለች ብዙም አልሰራችም ነበር። ሁለቱን ቀን ግን የለፋችውን ያክል ባይቀላትም እንደመጀመርያው ቀን አልከበዳትም። ዛሬ የመጨረሻ ፈተናቸውን ተፈትነው እየወጡ ነው። በሩ ጋር ተጠባብቀው ከተገናኙ በኋላ ፈተናው እንዴት እንደነበር ይጠያየቃሉ። አምሪያ ጭራሽ የረያንን የፈተና ወረቀት ወስዳ ማስተያየት ጀመረች። ከሱ ጋር ተመሳሳይ በሆነችው መልስ እየተደሰተች በማይመሳሰለው ደሞ ትናደዳለች።
" ኧረ በአላህ በቃችሁ! እንዴ የት ብሄድ ነው ይሄን ወረቀት የማላየው..? " ፋሩቅ ' ፈተና እንዴት ነበር? ' የሚለው ጥያቄ ራሱ ሰልችቶት ነበር። ከአምሪያ ላይ ወረቀቱን ነጠቃትና እየሮጠ ሄደ።
" እሺ በቃ አቆማለው..መልስልኝ እንዳትጥለው..." ከኋላው እየሮጠች ተከተለችው። ሰብሪንና ረያንም ተቀላቀሏቸው።

የፈተናቸው የመጨረሻ ቀን ስለሆነ ሁሉም በጣም ተደስተዋል። ወደቤት ከመሄዳቸው በፊት ትንሽ ጊዜ አብረው ለማሳለፍ ተስማሙ። ዝሁር ሰላት ደርሶ ስለነበር ረያን፣ ፋሩቅና ሰብሪን ወደመስጂድ ሲሄዱ አምሪያ እዛው አከባቢ ያለ ምግብ ቤት ምሳ አዛ ጠበቀቻቸው። ረጅም ሰአት ሲጫዋወቱ ቆይተው 10 ሰአት አከባቢ ሲል ወደ ቤት ተመለሱ።
2024/11/14 12:25:54
Back to Top
HTML Embed Code: