Telegram Web Link
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
" መጣህ ረዩ? " እናቱ ናት ቁጭ ብላ ልብስ እያነጣጠፈች ነበር።
" ቆይ ላግዝሽ..." ሄዶ አጠገቧ ቁጭ አለ።
" ፈተና አሪፍ ነበር? "
" አልሀምዱሊላህ አሪፍ ነበር...አባ አልመጣም እንዴ? "
" አዎ ገና ተጨማሪ ሶስት ቀን ሳይቆይ አይቀርም። " አባቱ ብዙውን ጊዜ ፊልድ ስለሚወጣ ቤት የሚሆንበት ቀን በጣም ትንሽ ነው።
" ቆይ አንናፍቀውም እንዴ? እንዴት ይሄን ያህል ቢዚ ይሆናል? "
" ምነው ናፈቀሽ እንዴ እናቴ? "
" እድሜዬ እየሄደ ነው። ቤት ውስጥ ብቻህን ስትውል ቤቱ ራሱ ይቀዘቅዛል...ከዛም አልፎ ሊበላህ ነው የሚደርሰው። ለነገሩ አሁንማስ አንተ አለህልኝ...ከፈለገ አይምጣ..." ከልቧ እንዳልሆነ ያውቀዋል።
" ያው ስራ ሆኖበት ነው እንጂ መቼስ በኛ የሚጨክን አንጀት እንዴለው ታውቂያለሽ..." ተነስቶ አቀፋት።

" እኔ ምልሽ እማ ባለፈው ወ/ሮ ኸዲጃ ለክረምት ወደ ድሮ ከተማቸው ሊሄዱ እንደሆኑ ስትነግርሽ ሰማው ልበል.."
" አዎ ከአንድ ሳምንት በኋላ መሰለኝ እንሄዳለን ያለችኝ..."
" ሁሉም ናቸው የሚሄዱት? "
" አዎ..ምነው? " ለምን እንደሚጠይቃት ግራ ተጋብታለች።
" ኧረ ምንም እንዲው ለማወቅ ነው..."
" እም..ግን አይመስልም..." ፊቱን ሲያዞር አይኑን ለማየት በዞረበት እየዞረች ፈገግ ማለት ጀመረች።
" እማ ደሞ ምን አስበሽ ነው? እኔ ዝም ብዬ ነው የጠየኩሽ። በቃ ዩኒፎርሜን ልቀይር.. " ወድያው ተነስቶ ወደክፍሉ ገባ። አይኑን ካየች ልታውቅበት ስለምትችል...

ክፍሉ እንደገባ ዩኒፎርሙን ሳያወልቅ አልጋው ላይ ሄዶ ተዘረረ። ክረምቱን አልፎ አልፎ ከነፋሩቅና ሰብሪን ጋር ሆነው ለማሳለፍ አስበው ነበር። ግን ምን ያደርጋል አምሪያ ልትሄድ ነው። ለወራት ያክል ጭራሽ እንደማያያት ሲያስብ በጣም ከፋው ፤ ገና ከአሁኑ ትናፍቀው ጀመር።

ስልኩን አውጥቶ ደወለላት። አታነሳም ... ደግሞ ደወለላት አሁንም አላነሳችም። ስልኩን አልጋው ላይ ወርውሮት ለመተኛት መሞከር ጀመረ።
ብዙም ሳይቆይ ግን የቤታቸው በር ተከፍቶ እናቱ ከአንድ ሰው ጋር ስታወራ ሰማች። የአምሪያ ድምፅ ወድያው ነበር ጆሮ ውስጥ የገባው። ከተኛበት ተስፈንጥሮ ተነስቶ ከክፍሉ ወጣ።
" እንዴ አምሪያ መተሻል እንዴ? " በአጋጣሚ የወጣ ለማስመሰል ወደ ኪችን ሄዶ ውሀ መጠጣት ጀመረ። ምን እንደሆነ ባያውቅም የሆነ እቃ ይዛላት ነበር የመጣችው። እቃ ልታቀብል ስለመጣች ልትቆይ እንደማትችል ሲያስብ ተናደደ።
" እንዴ ትንሽ ተጫውተሽ ነው እንጂ የምትሄጂው...ረዩ እስኪ የሚጠጣ ነገር ይዘህላህ ና..." እናቱ እንደዚ ስትል ወድያው ፊቱ በፈገግታ ተለወጠ። በልቡ " የውስጥ አውቅ እኮ ነሽ! " እያለ ከፍሪጅ ውስጥ እርጎ ይዞላት መጥቶ እሱም እዛው ተቀመጠ።

እስከመግሪብ ድረስ እዛው ከቆየች በኋላ እየመሸ ስለነበር ወደቤት ሊሸኛት ወጣ።
" መች ነው የምትሄዱት? "
" እስኪ ኢንሻአላህ በዚ ሳምንት እንሄዳለን ብለዋል። ከመሄዴ በፊት መጥቼ ሰላም እላችኋለው..." ቀና ብላ አየችው ፊቱን ጥሎታል።
" እዛ ከሄድሽ በኋላ ደሞ ደውዪ እኔም እደውላለው..." ሲያወራት እንደበፊቱ አይደለም። አነጋገሩ ላይ ያየችው ለውጥ አስገርሟታል።
" እሺ የተከበሩ እደውላለሁ! " ቤታቸው ጋር ደርሳ ስለነበር " ደና ደር " ብላው ሄደች።

በዚ ሰአት እንዳትሄድ የሚያደርግ ስልጣን ቢኖረውና ባይለቃት ምነኛ ደስ ባለው ነበር። ሳይፈልግም ቢሆን ሸኛት።

አምሪ ወደክፍለሀገር ከሄደች እንደቀልድ 2 ሳምንት ተቆጠረ። ለረያን ግን እንደሁለት አመት ነበር ጊዜው የረዘመበት። አልፎ አልፎ በስልክ ቢያወሩም ናፍቆቱን ግን አልቻለውም ነበር። የአምሪያ ስለማይታወቅባት ነው እንጂ እሷም ከሱ ባልተናነሰ ነው የናፈቃት። ሲደዋወሉ ስለሀገሩ ፣ ስለእረፍት ምናምን እንጂ ስለነሱ አንድ ቀንም አውርተው አያውቁም። ረያን ቢያንስ ናፍቆቱን ሊነግራት ይልና አፉ ተሳስሮበት መልሶ ሳይነግራት ይተወዋል። ከዚ በላይ መያዝ ግን የሚችል አልመሰለውም።

*

" አምሪያዬ ነይ ሰው ይፈልግሻል..." አያቷ ናቸው ውጪ ቁጭ ብለው ፀሀይ እየሞቁ ነበር።
" ማነው..." እያለች ከቤት ወጣች።
አያቷ ለመጣው ሰው ተቀምጦ እንዲጠብቃት ወንበር እየሰጠችው ነበር። አምሪያ ስታየው ደነገጠች። ጭራሽ ያልጠበቀችውን ሰው ባልጠበቀችው ቦታ ላይ ነው ያየችው።

#ክፍል_ስድስት ( ⓺ ) ይቀጥላል...
❦ ════ •⊰❂⊱• ════ ❦

~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🃏𝙼𝚎𝚔𝚒🀄)
Telebirr

17 kutr yalaw in box yawaragn


@Meki3
2024/09/23 07:23:25
Back to Top
HTML Embed Code: