Telegram Web Link
አባቴ ድሃ ታግሎ ኗሪ ነበር ። ነፍስ እስካውቅ የሆነ ኮት ነበረው ፤ ዘወትር ነበር የሚያደርገው ፤ እሱን ኮት ሳይለብስ ከመንገድ ባገኘው የማልፈው ሁላ ነው የሚመስለኝ ።

ረጋ አባባሉ የሞላለት ያስመስለዋል ።
በትንሽ በትልቁ አይናደድም ፤ በትንሽ በትልቁ አይመክረኝም ። ከሰው ጋ ሲጣላ አጋጥሞኝ አያውቅም ።

ሰላማዊ ሰው ነው ፤ ሁሉንም ሰው በሙሉ ስም ነው የሚጠራው እኔንም ጭምር ። እናቴን ግን ያቆላምጣታል ። እሷ ጋ ሲደርስ የሚሆነው መሆን ለየት ይላል ፤ ይቀልዳል ፣ ያሾፍባታል ግንባሯን ይስማታል ።

አጠገባችን ላሉ እጅግ ከእኛ የበለጠ ደሃ ለነበሩት እማማ አዛሉ እና ከእኛ ቤት ፊት ለፊት ሰፊ ትልቅ ግቢ ላላቸው ለዲታው ጋሽ ይልማ የሚሰጠው ሰላምታም ተመሳሳይ ነው።

አባቴ ችግር ሲያወራ አይቼው አላውቅም ፤ ዝም ብሎ የቻለውን ያደርጋል ፤ ምን አልባት ለእኔ ማውራት አያበድረኝ ፣ አይሞላልኝ ብሎ ይሆናል እንዳልል ስራ ላለው ለታላቅ ወንድሜም እንኳን አያወራም ።

ስራ በያዝኩ በሶስተኛ ወሬ በአንዴ አራት ሙሉ ልብስ ገዛሁለት ። ደስ አለው በጣም ።
እጄን ይዞ
አትጣ
ሞገስ ልበስ
የአንተ የሆነ ሁሉ ይባረክልህ ብሎ መረቀኝ

በአራተኛው ቀን ........ከገዛህልኝ ሁለቱን ሙሉ ልብስ ለወዳጄ እና ለበሪሁን መስጠት ፈልጌ ነበር አለኝ (ወዳጄ እና በሪሁን ወንድሞቹ ናቸው)

ቅር ይልህ ይሆን ብሎ አይን አይኔን አየኝ

አጠያየቁ አስተያየቱ የሆነ የሚያሳዝን ነው ፤ አንጀቴን በላው

ከእነሱ ጋ በጋራ መዘነጥ ፈልጎ ከእነሱ ተለይቶ ላለመድመቅ ነው መሰለኝ

ሌላ ቃል ስላጣው አይ ጋሼ ብዬ እጁን ሳምኩት!!!
© Adhanom Mitiku
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
🦅 ከንስር ልንማራቸው የሚገቡ ሰባቱ የአዕምሮ ለዋጭ ባህሪያት 🦅

1⃣ #ንስሮች_ብቻቸውን_በታላቅ_ከፍታ_ይበራሉ

ንስሮች ከእርግቦች፣ ከድንቢጦች ወይም ከትናንሽ የወፍ ዝርያዎች ጋር አብረው አይበሩም።

📝 ትርጉም:- ጠባብ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ራቅ። ከአቅምህ በታች እንድትበር ያደርጉሀል። ንስሮች ሲበሩ ሊታዩ የሚችሉት ከንስር ጋር ነው። በአካባቢህ እንዲሆኑ የምትፈቅድላቸው ሰዎች ለአንተ ማንነት መለያዎች ናቸው። ጥሩ ጓደኞችን አጥብቀህ ያዝ።

2⃣ #ንስሮች_ታላቅ_የማየት_ችሎታ_አላቸው

ከአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሆነው አንድን ነገር በአትኩሮት መመልከት ይችላሉ። የተመለከቱትንም እንቅፋት ቢኖር እንኳ እስከሚያገኙት ድረስ አትኩሮታቸውን አይለውጡም።

📝 ትርጉም፡-  በህይወትህ የራስህን አላማ ያዝ። እንቅፋቶች ቢኖሩም ከአለምከው ነገር ፍንክች አትበል።

3⃣ #ንስሮች_ፍርሀት_የለሽ_ናቸው

ንስሮች በሚያድኑት ታዳኝ ጥንካሬ እና ግዝፈት አይበገሩም። ታዳኛቸውን ለማሸነፍ ወይንም ግዛታቸውን ለማስመለስ ሁልጊዜም ይፋለማሉ።

📝 ትርጉም፡- የገጠመህ ችግር ምንም ያህል ትልቅ ወይንም አዳጋች ቢሆን ተስፋ አትቁረት። ይልቁንም ተጋፈጠው። ስኬታማ ሰዎች የማይፈሩ ናቸው። ችግሮቻቸውንም በቀጥታ የሚጋፈጡ ናቸው።

4⃣ ንስሮች_ግትር_ናቸው።

ንስሮች ማዕበልን ይወዳሉ። ዳመናዎች ሲሰበሰቡ ንስሮች በደስታ ይሞላሉ። የማዕበሉንም ንፋስ በመጠቀም ወደ ከፍታ ይወጣሉ። ሀይለኛ ንፋስም ካለ ከዳመና በላይ እንዲያወጣቸው ይጠቀሙበታል።  ከዳመና በላይ መሆንም ለክንፋ እረፍትን ይሰጠዋል። ሌሎቹ አዕዋፋት ግን እራሳቸውን በቅርንጫፎች እና በዛፎች ደብቀው ይቆያሉ።

📝 ትርጉም፡- ስኬታማ ሰዎች በሚገጥማቸው ማዕበል በፍርሀት ከመዋት ይልቅ  ማዕበሉን ለትርፋማነታቸው ይጠቀሙበታል።

5⃣ #ንስሮች_የሞቱ_ነገሮችን_አይመገቡም

ራሳቸው ያልገደሉትን ካልሆነ ሞቶ የተገኘን ነገር አይመገቡም።

📝 ትርጉም፡- ባለፉ ስኬትህ ደስተኛ ሆነህ አትርጋ ይልቁንም አዳዲስ ወሰኖችን ለመግዛት እራስህን አዘጋጅ። ያለፈውን ነገር ቦታው አስቀምጠው። ቦታውም ኋላ ነውና።

6⃣ ንስሮች_እራሳቸውን_ያሰለጥናሉ

ንስሮች ላባቸውንና የሚኖሩበት ጎጆ የተሰራበትን ሳር ያስወግዷቸዋል። ምክንያቱም አዳዲሶቹ ጫጩቶች ለመብረር የሚያደርጉትን ጥረት አዳጋች ለማድረግ ብለው። ጫጩቶቹም በሚኖሩበት ጎጆ ውስጥ መቆየት ሊቋቋሙት የማችሉት ደረጃ ላይ ሲደርስ መብረር ይጀምራሉ።

📝 ትርጉም፡- የምቹነት ቦታህን (Comfort Zone) ለቀህ ውጣ። ምክንያቱም በዚያ እድገት የለምና።

7⃣ #ንስሮች_ህያውነትን_ይተገብሩታል

ንስሮች በሚያረጁበት ሰዓት ላባቸው በጣም ደካማ ይሆንና የሚፈልጉት ቦታ በሚፈልጉት ፍጥነት መሄድ ያዳግታቸዋል። ይህም ሞቱን የሚያፈጥን ስለሆነ ራቅ ብሎ 🗻 ተራራ ላይ ይወጣና ደካማ ላባዎቹን ይነቅላቸዋል። መንቁረንና ጥፍሩን ሙሉ በሙሉ ራቁቱን እስከሚሆን ድረስ ከአለቶች ጋር እያጋጨ ይሰባብራቸዋል። ከከፍተኛ ህመም በኋላም ድብቅ ስፍራ በመሄድ ላባው፣ ጥፍሩ እና መንቁሩ እንደአዲስ እስከሚበቅሉ በዚው ይቆያል። ከዛም ከዚህ በፊት ያልወጣውን ትልቅ ርቀት መጓዝ ይጀምራል።

📝 ትርጉም፡- ምንም ያህል ከባድ ቢሆን ከዚህ በኋላ በህይወትህ ለውጥን የማያመጣልህን ወይንም የሚያቃጥሉህን መጥፎ ልማዶች አስወግዳቸው ምክንያቱም ውድቀትህን ያፋጥኑታልና።


📚 @ethioleboled
18+

ክፍል አንድ- ፩

ወንድ ልጅ ሆዱን ይወዳል ፦

ላጤ ህይወት አሰልቺ የሚያደርገው ጠዋት ማታ ወጥ መቀቀሉ ነው መሰለኝ ።

መጀመርያ ስድስት ቀን ስራዬ ብዬ ወጥ እየሰራሁ፣ ባለሙያ ነኝ፣ እያልኩ እየሸለልኩ ነበር ፤ ሰለቸኝ። መሰልቸቴን እና ርሃቤን ለማስታረቅ ሉሊት የምትባል ተመላላሽ የምታግዘኝ ልጅ ቀጠርኩ።

ምን ልስራ እያለች አንድ ሶስቴ ስትወተውተኝ ፤
ይሄውልሽ ሉሊት ዱባ እና ቂንጬ ብቻ አትስሪ እንጂ ምንም አይነት ምግብ እበላለሁ አልኳት ። ዱባ ወይ ቂንጬ ትወዳለች መሰለኝ አብዝተን የምንወደውን አብዝተው የሚጠሉ ሰዎች ሲገጥመን የምናየው አይነት ነው ያየቺኝ።

እኛ የምንወደውን የማይወዱ ሰዎችን ማክበር የስልጣኔ ምልክት ነው አይደል ?

በርግጥ ሉሊት እኔ የምወደውን መቃወም አትችልም አለቃዋም አይደለሁ ። በርግጥ ስልጣኔ ወደ ታች ብቻ ማክበር አይደለም ወደ ላይም እንጂ !

ሉሊት እና እኔ ብዙ ግዜ አንገናኝም ወጥ ሰርታልኝ ፣ ቤት አፅድታልኝ ፣ ልብስ አጥባልኝ ትሄዳለች

የሰራችሁ ወጥ ብዙ ካልተበላ
" አልጣፈጠህም? ፣ ምነው ጨው በዛ? ፣ ምን ሆነ ምን ላስተካክልልህ ? ... "ትለኛለች።

"ኧረ ቆንጆ ነው ሰሞኑን ግብዣ እየገጠመኝ " ገለመሌ አይነት ምክንያት እነግራታለሁ ።

የተቀበሉትን ሃላፊነት በዋዛ አለመመልከት ሉሊትን ይመስለኛል ።

ሉሊት አስቤዛ የጎደለ ቀን ስልኬን ፋታ አትሰጠውም ቴክስት ታደርጋለች ደጋግማ ትደውላለች ።

ኋላፊነቷን ለመወጣት ይሉኝታ የላትም !

በቀደም እለት ከአራት ሰዓት ጀምሮ ስልኬን መቀጥቀጥ ጀመረች ። "ሉሊት እየነዳሁ ነው ሳቆም እደውላለሁ" ቴክስት ላኩላት ።

አስራ አንድ ሰዓት ላይ አልጨረስክም ወይ ብላ ከሚስቅ ስቲከር ጋር ቴክስት ላከችልኝ።
የሚስቀው ስቲከር ምን ያደርጋል ? ?

የላኩትን ቴክስት መልሼ አየሁት

"እየበዳሁ ነው መልሼ እደውላለሁ ነው የሚለው።"

ክው አልኩ ምን ልበላት : እምለው አጣሁ ።

"ሉሊት ያው ቃላት ገድፌ ነው
እ ...እየነዳሁ ነው ለማለት" የሚል ቴክስት እያንዳንዶን ቃላት በጥንቃቄ አይቼ ደጋግሜ አንብቤ ላኩ

ጥንቃቅያችን ከሰራነው ስህተት ይመነጭ የለ !?

"ገብቶኛል ኧረ አብሽር፤ ሙሉ ቀን ስትበዳ ማለቴ ስትነዳ እንደማትውል እገምታለሁ" አለችኝ።

ሌላ መደንገጥ፦

ሃሙስ ከሰዓት የሆነ ዶክመንት አስፈልጎኝ እቤት
ስሄድ ሉሊትን ወጥ እየሰራች አገኘኋት።

እንደ ድሮ ሰፊ ቀሚስ ሻሽ ሹራብ አለበሰችም ። ቱታ እና ቲሸርት ነው የለበሰችው ።

የበቀደምለታው ቴክስት መቀመጫዋን፣ ጡቷን፣ ዳሌዋን እንዳየው መራኝ።

ሞንዳላ ናት፣ ዳሌዋን፣ መቀመጫዋን፣ ጡቷን ላለማየት አይኔን ወደ ቁምሳጥኑ፣ ጥግ ላይ ወዳለው መወልወያ፣ ወደ መፅሃፍ መደርደርያ ጠርዝ... እልከዋለሁ ብዙ አይቆይም አይኔን ሉሊት መቀመጫ ወይ ጡት ላይ አገኘዋለሁ።

ወንድ ልጅ የተሞናደለ ይወዳል !

መቀመጫዋ፣ ጡቷ፣ ፊቷን እንዳስተውለው ገፋኝ
ያይኗ ሽፋሽፍት ያምራል ። ቅላቷ ያምራል ፣ ከንፈሯ ያምራል፣ ሉሊት ቆንጆ ናት መልኳ ድህነቷን ድል አድርጎታል።

ሉሊት የተሟላች ነች ለካ። ሙያዋ ....መልኳ.... ከሁሉ ከሁሉ መሞናደሏ ...!

ከአራት ወር በኋላ ሉሊትን አዳም ሄዋንን እንዳወቃት ለማወቅ ሻትኩኝ ።

ተሳስቼ የፃፍኳት ሆሄ የተሞናደለ ሰውነቷን ውበቷን ገላለጠልኝ።

ኤጭ እንኳን ተሳሳትኩ
ከምታነብ ሴት ጋር አትከራከር!

ካደኩበት ሀይቅ ዳር አካባቢ ከሁሉ የተለዩ የሚመስሉኝ አንድ አሳ አጥማጅ ባልና እጅግ በጣም አንባቢ የሆነች ሚስቱን አውቅ ነበር፡፡

✍️አንድ ቀን ታዲያ አሳ አጥማጁ ባል ደክሞት ለማረፍ ወደ ቤቱ መጣና ከሶፋው ላይ ወድቆ እያንኮራፋ እንቅልፉን ይለጥጠው ጀመር፡፡ ሚስት ማንበብ አልቻለችም ስለዚህ ለየት ያለ ነገር ማድረግ አሰበችና መጽሃፏን ይዛ ከቤት ወጣች፡፡

✍️የባሏን ጀልባ ወደ አንድ ጸጥተኛ የሀይቁ ክፍል ቀዘፈችና በስሱ በሚዳብሰው ነፋሻማ አየር እየተዝናናች መጽሃፏን ገልጣ ማንበቧን ቀጠለች፡፡

✍️ከጥቂት ቆይታዎች በኋላ በድንገት የባህሩ ላይ ጠባቂዎች ጀልባ ከች አለ፡፡ ኮስታራው ፖሊስም ማይክራፎኑን በእጁ አንከርፍፎ ይለፈልፍ ጀመር

✍️‹‹ምን እያደረጉ ነው እመቤቴ!››
‹‹መጽሃፍ እያነበብኩ!›› (ምን እንደማደርግ አይታየውም እንዴ! በማለት እየተገረመች!)

🎮‹‹ እመቤቴ በተከለከለው የሀይቁን ክፍል ላይ ስለሚገኙ በፍጥነት አካባቢውን ይልቀቁ!››
‹‹ምን አጠፋሁ ጌታው!›› አለች ደርባባዋ እመቤት
‹‹በዚህኛው የሀይቁ ክፍል አሳ ማጥመድ አይፈቀድም እመቤት!››

🤔‹‹እሱን አውቃለሁ ጌታው! ሆኖም እንደሚያዩኝ አሳ እያጠመድሁ ሳይሆን መጽሃፍ እያነበብኩ ነው!››

🟠ፖሊሱ ፈገግ ብሎ ‹‹እንደማየው ጀልባዎ በአሳ ማጥመጃ መሳሪያዎች ተሞልቷል፤ ስለዚህ እኛ በሌለንበት በማንኛዋም ደቂቃ መረብዎን ጥለው እንደሚያጠምዱ እገምታለሁ፡፡ ስለዚህ አሁኑኑ አካባቢውን ጥለው የማይሔዱ ከሆነ ባልተፈቀደ ቦታ አሳ በማጥመድ በሚለው አንቀጽ መሰረት በቁጥጥር ስር የማውሎት መሆኑን ይገንዘቡ!››

✍️ሴትየዋም ፈገግ ብላ አየችውና ‹‹ጌታው እንዲያ የሚያደርጉ ከሆነ እኔም ጾታዊ ትንኮሳና አስገድዶ መድፈር በሚለው አንቀጽ መሰረት የምከስዎ መሆኑን ይወቁ!›› አለች ኮምጨጭ ብላ

✍️‹‹አይቀልዱ እመቤቴ ይህ የስራ ጉዳይ ነው! እንኳን ልተነኩስዎና ልደፍርዎ ቀርቶ አጠገብዎ እንኳን እንዳልደርስኩ ያውቃሉ!››

✍️‹‹ እውነት ነው አውቃለሁ፡፡ ሆኖም ያንን ለማድረጊያ (መድፈሪያና መተንኮሻ ይሆን!) የሚያገለግል ማንኛውንም አይነት መሳሪያ እንደያዙና ጭር ሲልልዎ በማንኛዋም ደቂቃ ያን ሊያደርጉ እንደሚችሉ እገምታለሁ!›› አለች ደፋሯ እመቤት

🛡ፖሊሱም ጥቂት አሰብ አደረገና ‹‹ መልካም ቀን ይሁንልዎ እመቤቴ! ይጠንቀቁ!›› የጀልባውን ሞተር ኮርኩሮ ጉዞውን ቀጠለ፡፡

➡️ከአንባቢ ሴት ጋር አትከራከር!
ብልህና አስተዋይ ስለምትሆን ትቀጣሃለች
!
ግልድፍድፍ ያልኩኝ ነኝ ። የሃይማኖት እወቀት የለኝም ። ሚስጥረ ሥላሴ አይገባኝም የመላዓክት እና የሰማዓታት ድርሻ አላውቅም ።

የሃይማኖት ጉዳይ ላይ ተመራምሬም ጠይቄም ተምሬም አላውቅም ። ክብረ በዓል ሲደርስ እሳለማለሁ ።

በቃ እንዲ ነኝ!

ፈሪሃ እግዜር ያለኝ ኢ አማኝ ነው የምመስለው ።
አልፀልይም ፣አልፆምም ፣ተስዬ አላቅም ።

ዝም ብዬ የሆነልኝ መልካም ነገር ከጌታ ጋ አገኘናኛለሁ ። ደስ ሲለኝ ተመስገን፣ ተመስገን እላለሁ ፦

በቃ ይቺ ብቻ ነኝ ።

ሚስቴ ምጧ መጥቶ የመንግስት ሆስፒታል ገባች ። ምጧ በረታ .....ስትጮህ ሰማኋት ። አጯጯኋ ሆዴን አንጀቴን ገለባበጠው ....ከሞተች አስር አመት የሆናትን እናቷን አልማ.....ዜ. እና...ቴ እያለች ትጣራለች .....

ተ...ሼኤኤኤ( ተሼ እኔ ነኝ) ድረስልኝ ሞትኩብህ ስትለኝ እምባዬን እያፈሰስኩ አጠገባችን ወደ ነበረው ቤተክርስትያን ሄድኩ ።

አጠገቧ እኮ ነው መሆን ያለብኝ ግን አቃተኝ ።

ጌታዬ ጋ ልነግረው እየሆነ ያለውን ሄድኩ። በሩ ላይ ስደርስ መሬት ላይ ተዘርፍጬ ጌታዬ ሚስቴ ልትወልድ አይደል?? ምጡ በረታባት እርዳት እንጂ....🙏እርዳን እንጂ ...

በሰላም ከተገላገለች አንድ ጥላ አስገባለሁ ...እንደውም ሁለት... ምን ይሄ ብቻ ፍስለታን እፆማለሁ ...እምባዬ አላስለምን አለኝ

ጌታዬ ካንተ በቀር ማን አለን ....

ተመልሼ እየሮጥኩ ወደ ሃኪም ቤት ደረስኩ ወደ ውስጥ መግባት አቃተኝ እግሬ ብርክ ያዘው ልቤ ዝም ብሎ ድው ድው ይላል

ከስንት ደመነፍሳዊ እርምጃ በኋላ

በር ላይ ደረስኩ ። ዘመዶቿ ተሰብስበው እንኳን ደስ አለህ ሴት ልጅ ተገላገለች አሉኝ አሁንም እምባዬ ዝም ብሎ ፈሰሰ።

ወደ ውስጥ በምልክት አስፈቀጄ ገባሁ ሚስቴን
አየኋት እንቅልፍ ሸለብ አድርጓት ፣ ህፃኔን አየኋት

ሌላ ሳግ ሌላ እምባ

ሌላ ምስጋና ሌላ መባባት ሌላ ደስታ

ጌታዬ ሆይ ተመስገን ደሞ በጭራሽ ስለቴን አልረሳም
የቷ?

ይቺ:-

ሊነኩት ሊዳስሱት እንደሚጓጉለት ውድ ነገር ናት። ሁለመናዋ ሚያሳሳ የሆነ ህልም ብጤ ።

የልብሶቿ quality ህያው የሚመስሉ። ንግግሯ፣እውቀቷ፣ውበቷ፣ትህትናዋ፣ሀብቷ፣ልግስናዋ ሁሉን አሟልቶ የሰጣት(ወይስ ዋጋ ከፍላ ያገኘችው? እንጃ)

ብቻ ህመም፣ለቅሶ፣ስቃይ፣ብቸኝነት፣ተስፋ መቁረጥ እንኳን ሊደርሱባት ሰምታ የምታውቅ የማትመስል(የሷ ለሊቶችስ እንቅልፍ አልባ ቢሆኑስ?አንተ ህልም ናት ብትልም ህልሟ ገና ካልተፈታላትስ ማን ያውቃል) 

ያቺ:-

ምን ገዷት የአለም ጣጣ።መንፈሳዊውስ ቢሆን ለሷ ያው ነው ለሷ መሆን ካልቻሉ (ወይስ እሷ ናት እንዲ ብላ ምታስበው?)

ያም ሆነ ይህ እሷ ስለምን ትጨነቃለች ስለ ልብስ፣ስለ     ሀብት፣ቤተሰብ፣ባህል፣ልማድ፣ሀይማኖት፣ሀገር፣ያለፈው፣የሚመጣው ይሄ ሁሉ ለሷ ምንድናቸው?ምንም በቃ የትም ውላ ይመሽላታል ደሞ ይነጋላታል የት? አንዱ ዛፍ ስር ደሞ ደግነቱ አውሬ አይነካት ብርድ አይቀስፋት በቃ ትኖራለች?በምንም።

ስትለፈልፍ የሰማት ደስ ያለው ብር ይሰጣታል ወይ ሚጎረስ ነገር በቃ ትኖራለች ።ያውስ መኖር ቢሉ መኖር ነው ምትፈልገውን አውርታ ያውም በነፃነት የወር የአመት ቀለብ የለባት ልጅ የላት ድስት በቃ እንዲሁ መኖር። የሷ የምናገር ነፃነት ከድፍን አለም ህዝብ አይበልጥም ብላችሁ ነው?

በመሀል:-

"አለች አንዲት ምስኪን" ተብሎ የህይወት ታሪኳ ሚጀምር ።በቃ ኑሮ ሳይሆን ችግር ምትኖር።

ሁሌም የትም የበታች የሆነች ምትበላው በባሏ ልግስና የሆነ ፤በአናት በአናቱ ወልዳ ተስፋ ቢስ የሆነች ፤ገና መኖር ሳትጀምር ያረጀች፤ ሰዎች የመረጡላትን ብቻ የምትኖር ፤ብትለብስ ብትወልድ ብትኖር ሰዎች ስለፈቀዱ ነው።

ህልም የሚታለም እንጂ የሚኖር አደለም ብለው ያሳመኗት (ፈርደውባት ወይስ ፈቅዳ እንጃ?)

ግን ማንስ ቢሆን ምገፋትን ይወዳል?ሁሌ አዳፋ የልጆቿ ማደግ እንጂ የሷ መጎስቆል ማይታያት አለች በመሀል

ታዲያ የትኛዋ ቀልብህን ገዛችው? የትኛዋ አሳዘነችህ? በየትኛዋ ቀናህ? መልስህ ምንም ይሁን ምን እኔ ግን ይቺን ወይ ያቺን እሆናለሁ እንጂ በመሀል ከመዋለል ሞት አይሻልም እንዴ? ብላ ጥላኝ ሄደች

ሆሆ ይሄ ሁሉ ዝብዘባ እኮ ምን አይነት ሴት መሆን ትፈልጊያሽ ብያት እኮ ነው የሆነች ወፈፌ

©nani
ያደረግኩትን ካደረግኩ በኃላ ፈገግ አለች....በስነስርአቴ የተደሰተች መስሎኝ ደስ አለኝ....አብሬያት አገጠጥኩ....


"ለምንድን ነው የሳቅከው..."....ስትለኝ የምመልስላት አጣሁ..."ስትስቂ ነው የሳቅኩት... "..ይባላል....?

"እኔንጃ.... ስለሳቅሽ መሰለኝ....".....ሳቋን ደገመችው...አሁን ነው ያስተዋልኳት...ሳቋ ላይ ፌዝ አለ....

"ምን ያስቃል....?"

"ቅድም ነበር ይሄን መጠየቅ የነበረብህ...."

"አሁን ጠየቅኩሻ...."....ስናደድ በማወጣው ድምፅ ነው ይሄን ያልኳት...

"ይልቅ ስለ ቅድሙ ሳቄ ልንገርህ...."....አለችኝ ረጋ ብላ...ለመስማት ተመቻቸሁ....

"ቅድም ምንድን ነው ያደረግከው..."

"ምን አደረግኩ....?....."....ከልቤ አላደረግኩትም መሰለኝ ከመቅፅበት ረሳሁት...

"የወደቀውን እንጀራ አነሳኸው...ከዛ ሳምከው...ከዛ ጣልከው..."

"እና ምን ያስቃል...ሲደረግ አይተሽ አታውቂም...እንጀራ ሲረገጥ ግፍ እንደሆነ አታውቂም...."....ከዚህ ንግግሬ በኃላ ሳቋ አላባራ አለ......


"አልመለስሽልኝም ምን ያስቃል...."....ጮህኩባት....

"የሹፈት ሳቁን ምን አመጣው...."...ሳቋን አልገታ ስትለኝ ጥያቄ ደገምኩ...

"ልትጥለው ለምን ሳምከው...."...መልሳ ጠየቀችኝ....

"እንዳይረገጥ...."...መለስኩ

"ግፍ ፈርተህ ማለት ነው...."....አዎ አልኳት በአንገቴ ንቅናቄ....ዝም ብዬ ሳያት እስቲ ዝም ብዬ ልከራከረው..ላናደው....ልቃረነው ብላ እኔ ጋር የምትመጣ ይመስለኛል....ብዙ ጊዜ አይቻታለሁ ግን ልትገባኝ አልቻለችም....



"ለማንኛውም ተረጋጋ...ይሄ ነገር ስለማይገባኝ ነው...መልሰህ ለምትጥለው መሳሙን ምን አመጣው...ላትበላው ነገር አቧራውን ማራገፉ ምንድን ነው...ከመሬት ላታላቅቀው ጥግ ማስያዙ ምን ይፈይዳል...እንጀራው ነብስ ቢኖረው ስታነሳው የሚሰንቀው ተስፋ ...ካፍህ ስታስጠጋው ደግሞ አስበው...ቤቱ ጠፍቶበት መንገድ የወደቀን ህፃን አንተ ቤቱን እያወቅከው አንስተህ ልብስ ገዝተህ መልሰህ ጥግ አስይዘህ እንደመጣል ነው..."

በተራዬ ከት ብዬ ሳቅኩ....."ለምን ትስቃለህ...ምን ያስቅሀል...?"...ብላ እንድትጠይቀኝ ጠበቅኩ...እሷ እኔን ትታ አየር አየሩን ታያለች....


"ምን ያስቅሀል አይባልም...?"

"ምን እንደሚያስቅህ እያወቅኩ ምን አሰጠየቀኝ...."

"እሺ አትናደጂም...?"

"ካንተ ከዚህ የተሻለ አረዳድ ስለማልጠብቅ አልናደድም....".....

"ምን ማለት ነው...."....በገንኩ....

"ኡፍ አቤል ሳትጠይቅ ለመረዳት ሞክር...አንዴም ተረድተኃኝ ስለማታውቅ እንድትረዳኝ አልጠብቅም...ባልጠበቅከው ነገር ደግሞ አትናደድም...."

ዝምታ መሀላችን ተመቻችቶ ተቀመጠ.....ቡናችን ከእጣን ጢስ ጋር መጣ....አስተሳሰቧ ያስደነግጠኛል....ስታስተውል ጉድ ታስብላለች...ቡናዬን ሳማስል ሳይቀር እየተጠነቀቅኩ ነው...ደግሞ ምን ትላለች እያልኩ...ብዙ አትከራከረኝም...የዛሬ ሁለት አመት የነበረው ጭቅጭቃችን በርዷል....ተስማምተን ወይም አንድ ሆነን አይደለም...ሁሉ ነገሬን አስተውላ ደክሟት ነው.....አንዳንዴ እንትጨቀጭቀኝ እና ለምን እንትለኝ እያወቅኩ አጠፋለሁ...የእርሷ መልስ ዝምታ ወይንም የሹፈት ሳቅ ነው....


"ታውቃለህ አቤላ አሁን አንስተህ ስለጣልከው እንጀራ ስናወራ የሆነ ቁም ነገር ታስተውላለህ ብዬ ነበር...ማለት አንድ አንዴ እንኳን ታስባለህ ብዬ አስብ ነበር...."

"ምን ማለት ነው አንዳንዴ ታስባለህ ማለት..."....ድምፄ ላይ ንዴት አለ....

"ኡፍ አቤል ኡፍ...."....ከተቀመጠችበት ተነሳች....ተከትያት ስነሳ ላየኝ ሰው በእሷ መቀመጫ የምጠቀም ነው የምመስለው...

"ምን እየሆንሽ ነው...."

"እየሄድኩ...."

"መሄድን ምን አመጣው...."

"ፍራቻ...እና ስልቸታ...."

"ምን እንደሰለቸሽ አውቃለሁ....ግን የምን ፍርሀት ነው....."

"ስመህ እንደጣልከው እንጀራ ትጥለኛለህ የሚል ፍራቻ...."

"ኧረ ሄሉ ተረጋጊ...ብለን ብለን በእንጀራ እንጣላ...ከዚህ በኃላ የምን ማንሳት የምን መሳም አሽቀንጥሬ ነው የምጥለው....ቁጭ በይ እናውራ...."

"መቼም አይገባህም...ደነዝ ነህ አንተ....".....ብላኝ ፈረጠጠች....


ከገባችሁ አስረዱኝ...እኔ ምንም አልገባኝም...🤷‍♂









https://www.tg-me.com/ethioleboled
የዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ፤

ታህሳስ - 1947 ዓ.ም

አዲስ አበባ

#ታሪክን_ወደኋላ
ነበር......1




"ብቸኝነት እየተሰማኝ ነው...እንደውም አንዳንዴ ከሌላ ፕላኔት የመጣሁ እስኪመስለኝ ድረስ "....


ከብዙ ጊዜ በኃላ ይቺን አለ...ላለፉት 6 ወራት ዝምታ መርሁ ነበር...ዝምምምም...በቃ ጭጭጭጭጭ...አንዳንዴ ብቻ ከመኝታ ቤቱ ከሚወጣው ሙዚቃ በቀር ምንም አይሰማም... የእሱ የሚባል ድምፅ ካለ ሲያስነጥስ አልያም ሲያስል የሚሰማ ነበር...

"ምነው ልጄ ብትተው...ከሰው ተፈጥረህ እንደ አውሬ ብቻህን ...ምነው ሳንሞት ገደልከን ...አሄሄሄሄ"....ከሚል የእናቱ ምሬት ጀምሮ

"ምነው በማምሻችን የወላድ መካን ባታደርገን ..." ከሚል የአባቱ ወቀሳ

"ቀለል አርገው እንጂ ...ያጋጥማል...just learn from it and move on with your life"....ከሚል የተመልካች አስተያየት ጭምር...


"ተበላሸ ...አይይይይ ተስፋም የለው...መጋኛ አግኝቶታል መሰል ...አይይይ ተምሮ ተምሮ መና..."...እስከሚሉ ሽሙጫዎች ...ሁሉንም ጠግቧል።


ለምን ለነዚህ እረፍት ለሚነሱ ድምፆች ትኩረት ነሳ...? ማንም አያውቅም..ደፍሮ የሚጠይቀውም የለም....ለታ ከእነዚህ ሁሉ ድምፆች የሚልቅ ድምፅ አእምሮው ውስጥ ስለሚደጋገም ለእነዚህ ድምፆች ባዳ ነው....


"ጓደኛዬ ጥለኧኝ አትሂድ..."...የክብሮም ድምፅ.......

"ያንተን ሚስትማ ያሳየኝ ካካካ እኔኮ ግርም የምትለኝ ከዝንጀሮ ትንሽ መለስ ብለህ አይኗ ፣ጥርሷ፣ ወገቧ...ምናምን ካካካ ምንድን ነው እንዲህ ያዙኝ ልቀቁኝ"...የክብሮም ተረባ

"የመጀመሪያ ሚዜህ እንዳታደርገኝ አደራ....ሙሽራው ማነው ምናምን ሲባል አስበኧዋል..."....የተለመደ ጨዋታው...

"አለውልህ..."....የሚያሳርፍ ተገንነቱ.....

"ለታ አትተወኝ...."....የመጨረሻ ንግግሩ...በቃ አእምሮው በእሱ ድምፅ ታጭቋል....



"ልጄ የክብሮም እናት መጥተዋል...እንደው እኛ መሄድ ሲገባን...በዚህ ሀዘናቸው ላይ ሊጠይቁን መጡ...በል ና እና ሰላም በላቸው..."

"የክብ...ማለት እቴቴ...ለምን....?ስለ እኔ ጠይቀውሻል...ስለዛን እለት..የክብ"....ተንተባተበ.....እናቱ ደነገጡ....ደርቀው ቀሩ...

"ምነው ልጄ ደነገጥክ...."....አሉ የሞት ሞታቸውን...

"አይ እማዬ...በቃ የለም በያቸው ...."...ከቅድሙ መርበትበቱ ላይ መንቀዥቀዥም አከለበት...ጠባብ ክፍሉን በቅፅበት ፈረስ የሚያስጋልብ ሜዳ አረጋት ተንጎራደደባት.....


"ምን ሆነሀል...ልጥራው ብዬ መጥቼ...ምነው ልጄ በዚህ እድሜዬ በአንድ አፍ ሁለት ምላስ ይኑርሽ ባትለኝ...ትንሽ አጫውተሀቸው ትመለሳለህ...ደግሞም ብቻቸውን መሆኑ ከብዷቸው ይሆን ይሆናል እንጂ ወጉማ እንዲህ አልነበረም...ልጅን ቀብሮ ሰው ጥየቃ አሄሄሄሄሄ ተወው እስኪ..."

"እማዬ እባክሽ...ተኝቷል ...አሞታል...ከፈለግሽም ሞቷል...የለግሽውን በያቸው በቃ በቃ እማ የፈለግሽውን...".....ተርበተበተ...


"የዲማው ጊዮርጊስ....ምነው አንተ ምነው ልጄ ...አዬዬዬዬዬ ወልዶ መና ወልዶ መና...አበደ ልጄ ለየለት...."....ይሄን ጊዜ እዛው ለቅሶ ጀመሩ...ድምፃቸው እንኳን ሳሎን ቤት ከተቀመጡትን እንግዳ ሊደበቅ ቀርቶ ጎረቤት የሚረብሽ ሆነ...

"አንቱ...አንቱን እኮ ነው የምጠራው...አዳነ ኧረ አንቱ ሰውዬ...."...ባለቤታቸውን አንቱ ብለው የሚጠሩት እናቱ ድምፃቸው ከቅድሙ እጥፍ ሆነ።


ከክብሮም እናት ሊደበቅ የተናገራት ንግግር ለሙሉ ጎረቤቱ አጋለጠው...


"አይ እርኩስ መንፈስ...".....ይላሉ አንደኛዋ...

"አዎ አይነ ጥላ ማይሰራው የለ..."...አይነቱን ደግሞ ሌላኛዋ ይወስናሉ...

"አይ ይሄ የሰው አይን ነው...የቡዳ መዘዝ ቀልድ መስሎሻል..."...ያርማሉ ሌላኛዋ...

"ኧረ ይሄ አይነጥላ ነው...የሰው አይን እንዲሁ ጠቁሮ ከተደቦለለ ነገር ያርፋል እንዴ ተያ...እርሱን በልቶ ማን በቃር ይሞታል...."....በአይነጥላ ላይ specialized ያረጉት ዶክተር ቢቸግር አሁንም አልተረቱም...

"አወቅሽ አወቅሽ ሲሉሽ ኤድያ...ያንቺም ልጅ የቡዳ መድሀኒት አስሮ ይሄዳል...አሁን እግዜር ያሳያችሁ ቢበላ ቢበላ የእርሷ ልጅ...ሆሆሆ"....

"ከልጄ አናት ወረድ...እንደውም ልጄን የቀረጠፍሽው አንቺ ነሽ...'የእርሷ ልጅ አይበላም' ኧረ አፈር ከድሜ ብይ ...እኔ አስካለ አይደለሁም ደቼ ካላበላሁሽ...ቱ..."....ሙያተኞቹ ሀሜታቸው ወደጥል ተቀየረ....

"ምን ታመጫለሽ...እስኪ እናይሻለን...ልጅ አለኝ ትያለሽ ደግሞ...ይሄ ሌባ ...ደግሞ የሰረቃትን ማንደጃዬን ቁጭ ካላረገ እሰራለታለሁ...."

"መኩሪያዬን ነው ሌባ ያልሽው...?..."...ብለው ቀሚሳቸውን እና ከስር ያሉ ተጨማሪ 3 ውስጥ ልብሳቸውን ሰብስበው ሰፈሩባቸው....በዚህ መሀል ለታ ከአባቱ እና ከእናቱ ንትርክ አረፍ አለ... ለአፍታም ቢሆን የማሰቢያ እና ከክብሮም እናት የማምለጫ ጊዜ አገኘ...... ከመሀላቸው ከአንድ ሰው በቀር ሁሉም ትኩረቱ ተሰረቀ...



ለታ ይሄን አጋጣሚ እንደ ቀላል አላየውም....ግርግሩን ተጠቅሞ ጥግ ጥጉን ሄዶ የጊቢው በር ላይ ደረሰ.....ደስ አለው...የገነትን ቁልፍ ያገኘ ያህል....በሩን ከፍቶ አንድ እግሩን እንዳስወጣ ከኃላ ድምፅ ሰማ...ከጫጫታው የተገነጠለ ድምፅ...የተረጋጋ...


"አቡ...."......'አቡ' የሚሉት የክብሮም እናት ብቻ ናቸው.....ባለበት ደርቆ ቀረ።






ይቀጥላል.....ኮመንት ማድረግ እንዳይረሳ🙏




Shewit dorka





https://www.tg-me.com/ethioleboled
ከነገ ጋር



"አልፈራህም..."


"እንዴት...."


"አልፈራህማ በቃ...."


"እኮ እንዴት"


"በቃ አልፈራህም አትነዝንዘኝ!"


"ከነገ ጋር ግን እንዲህ መሳፈጥ ልክ ነው...?"


"አካሄዴ ከፈጠረኝ ጋር ስለሆነ አንተ ጥሩ ነገሮችን ይዘህ ከመምጣት ውጪ አማራጭ የለህም..."


"በእኔ እንዲህ እርግጠኛ መሆን አትችይም!!!"


"ያንተ ደራሲ ፈጣሪ ነው...እርሱ ነው ጌታህ...እሱ ካለህ ዝንፍ አትልም....ከእሱ መራቅ የጀመርኩ እንደሆነ ያኔ አትጠራጠር ያለቅጥ እፈራሀለሁ!...."


"እኔ ራሴ ፈራሁሽ"


"ወደህ ነው"



😊በርቱ💪



Shewit dorka
ነበር.....2




የግዱን አንገቱን ሲያዞር የክብሮም እናት የክብሮም እናት አልመስልህ አሉት...ወይዘሮ ሙሉ ሞላ ያለ ሰውነታቸው ተነፍቶ እንዳፈነዱት ፊኛ ተሟሿል...ጥርት ብሎ የሰላሳ አመት ጎልማሳ የሚያስመስላቸው የፊታቸው ቆዳ ማድያት ወሮታል...ከማድያቱ ሌላ የፊታቸው መጥቆር ላየ ፊታቸው ከፊትነት በዘለለ ከሰል መዛቂያ ነው የሚመስለው...ሁለ ነገራቸው ተቀይሯል......

"ሰላምም አትለኝ...ደግሞ ወዴት ነው ሩጫው..."

"ኧረ አይ እ እ..."....በውስጡ የሚለውን እያሰበ በአፉ ተንተባተበ...

"ና ልጄ ...የክብሮሜ ምትክ..."...ብለው አገለባብጠው እስኪስሙት ምንም አላለም...

"ልጄ ደህና ነህ እ...."

"ደህና ነኝ...ደህና ነኝ...እርሶ እንዴት ኖት..."

"እሱን እንኳን ተወው ...ልጅ ቀብሮ ደህንነት ከየት ይመጣል..."...የሚለው ጠፋው....

"ና ግባ ልጄ..እናት አባትህን በማምሻቸው አታሰቃያቸው...የሚሉህን ስማ...መቼስ ላንተ ብለው ነው..."

"አይ እቴቴ አስቸኩዋይ ጉዳይ ገጥሞኝ ነው...እመለሳለሁ..."

"በባዶ እግር....?".....አሉት ደንግጠው...ለታ በግርግር ማምለጡን እንጂ ባዶ እግሩን እንደነበር አላስተዋለም ነበር.. ለታ ከእሳቸው እኩል ደነገጠ....


"ልጄ በል ና እንግባ...."....ይሄን ብለው አንተ ቅደም የሚመስል መቆም ቆሙ...ላመል ገርበብ ብለው በአንገታቸው ወደ ቤት እየጠቆሙ...እርሱም ምንም ሳይል ከፊታቸው ቀድሞ ሄደ...


ከሶፋዎቹ መሀል ካለ በርኩማ እንዲቀመጥ ተፈረደበት...እናቱ ፣አባቱ፣የክብሮም እናት እና ሌሎች አሮጊቶቹን የማገላገል ስራ ላይ ያልተሳተፉ የሰፈር ሰዎች ከበቡት...



አስተያየታቸው የሚያውቁትን ለታ የሚያዩ ሳይሆን ጣዕረ ሞትን እንዳዩ ነገር ነው.....


"ምን አርግ ነው የምትሉኝ..."...ጠየቀ....ይሄኔ እናቱ እንደ አዲስ ማልቀስ ጀመሩ...አባቱ እሱን ማየት ተስፋ አስቆርጧቸው መስኮት መስኮቱን ያያሉ...የሰፈሩ ሰው አንዴ እሱን አንዴ እናትና አባቱን ያያል...


"ምንድን ነው የሆንከው ልጄ...?" እናቱ ናቸው።


"ምንም አልሆንኩም ...ምንም...ይኧው ጤነኛ ነኝ...እራመዳለሁ...እበላለሁ..እጠጣለሁ...እተኛለሁ...ከፈለጋችሁ አስመርምሩኝ...ሙሉ ጤነኛ ነኝ"...

"6 ወር ሙሉ በር ዘግቶ መቀመጥ ጤነኝነት ነው...አንደኛውን የሞተው ክብሮም ይሻላል...ሙልዬ አንቺ ሞቶ ቀብረሽዋል...የኔው በቁሙ ነው የሞተው አሄሄሄ..."...


"እሺ በለንና ፀበል እንሂድ...እዚህ ሜክሲኮ አዲስ የፈለቀ ፀበል አለ...ክፍለ ሀገሩንስ እሺ አትለንም ብለን ነው እንጂ እዚያ ምንጃር ..."


የከተማውን ሴት ከከተማው ናይት ክለብ እየመለመለ በአንድ ሰሞን ' አለም ' ያለውን ሞት ያጣጣመበት ጊዜ ታወሰው...እንደው እኔ እሺ ብል ፀበሉ እኔ ስገባበት አይደርቅም ይሆን...? ሲል አሰበ...ሀጥያቱ ከአለም ሀጥያት እንደሚበልጥ እያውጠነጠነ ለደቂቃዎች ዝም አለ....ዝምታው በረዘመ ቁጥር የከበቡት ሰዎች ፍርሀት ጨመረ....


"የትም አልሄድም...!!!"...

"ትሄዳለህ!!!!"....አሁን አባቱ ናቸው...ደንገጥ እንዲል በማሰብ ተቆጥተውት...

"አልሄድም!!!"....እሱ ወይ ፍንክች...ጭራሽ ደገመላቸው።


"በየትኛው ሀጥያቴ ነው በልጅ የሚቀጣኝ...."

እናቱ ናቸው ይሄን ያሉት...


"አቡ ና እስኪ..."....የክብሮም እናት እንደ ልጅነቱ እጁን ይዘው ወደ መኝታ ቤቱ አቀኑ...


ለታ እሳቸው ጋ ሲደርስ ከበረዶም የሚቀዘቅዘው ነገር አለው...ዝም አለ...አይኑ ፣ አካላቱ ፣ ድርጊቱ ሁላ ረገበ...ከክብሮም ሞት በኃላ ከእርሱ ጋር የተያያዘ ማንኛውም ሁኔታ ዝም ያስብለዋል...ማውራት ግድ ከሆነበትም እንደ ጨቅላ ህፃን ያንተባትበዋል....ክብሮም ክብሮም የሚሸት ነገር ሁሉ ያቅበዘብዘዋል...አልያም እንደ ሎጥ ሚስት የጨው ሀውልት ያረገዋል....ስሜቶቹ እንደ ወተት ይናጣሉ...ከየት እንደሚወግኑ ግራ ይገባቸዋል...እንደ ጀማሪ ነፍሰ ጡር ያጥወለውለዋል...ከዚኛው ጠረፍ ወደ እዛኛው ጠረፍ...ከዚኛው አለም እዛ ክብሮም ወዳለበት አለም መጓዝ ያምረዋል......


አእምሮው ለክብሮም እናት ጥያቄ የሚመልሰውን አያውቅም...ነገራቶቹ ሁሉ ከእርሱ ርቀዋል...ተነዋል....እንደ በግ እየተነዳ ከክፍሉ ዘለቀ....ዘልቆም የራሱ አልጋ የእሩቅ እንግዳ መሰለው...ሲጋደምበት እንዳልከረመ ቢቀመጥበት 'አንተ ክፉ' ብሎ ሚያሰምጠው መሰለው...'ቢያሰምጠኝማ በምን እድሌ' አለ መልሶ....


"ቁጭ በል...."...ቁጣ የተቀላቀለበት ትዕዛዝ....




አላለቀም....



ከወደዳችሁት react እና share እንዳይረሳ......



እና እየገባችሁ😊👉
https://www.tg-me.com/ethioleboled





Shewit dorka
ነበር....3





"እቴቴ..."...ደነገጠ።

"አሁኑኑ ልብስህን ሰብስብ...."....አሁንም ትዕዛዝ...

"ለምን...?"....ጠየቀ...

"ምንም የመጠየቅ መብት የለህም...የምልህን አድርግ!!!"....ይሄን ሲሉ እርሱ የሚያውቀው እንስፍስፍ ድምፃቸው ተለይቷቸው ነበር....

"እቴቴ አልገባኝም..."

"ሁሉንም ነገር አውቃለው..."....ይሄን ሲሉ ደግሞ ከድንጋጤም የላቀ ድንጋጤ...ከበድንነት የባሰ መበደን...ነብሱ ከስጋው ተላቀቀ....

"ማለት...እ...ምንድን ነው ምታውቂው..."...

"ስለ ሁሉም..."

"አታውቂም....አይይይ እቴቴ ምንም አታውቂም...ብታውቂማ....ብታውቂ...እ...እ..."....እንባው ከቃላቶቹ ጋር እሽቅድድም ገባ....


"ሽሽሽሽሽ....አትጩህ....ሁሉንም አውቃለሁ...ልብስህን ያዝና እንሂድ.."....አሉት ለእርሱ ብቻ በሚሰማ ድምፅ...ከመኝታ ቤቱ በር ላይ ተለጥፈው ከሚያዳምጡት ሰዎች ጆሮ ለማምለጥ...ለታ ከቅድሙም መበደኑ ያሁኑ ባሰ...ደነዘዘ....አይኑ ቀና ብሎ ሊያያቸው ድፍረት አጣ...


ይሄኔ የክብሮም እናት እሱን ትተው ከቁም ሳጥኑ አናት ላይ ወዳለው ሻንጣ ሽቅብ አማተሩ...ከዛም ቁም ሳጥኑን ከፍተው መርጦ እንዲለብሰው ሳይሆን እንዲሁ ሻንጣው እንዲሞላ ብቻ ጠቀጠቁት.....


"እንሂድ!"...አሉት ጀርባቸውን ለእርሱ ፊታቸውን ለበሩ ሰጥተው...
"ወዴት..."...ጠየቀ...
"ልጄ ወደ ሄደበት!!!!"


ከመኝታ ቤቱ ተያይዘው ወጡ....


ከዋናው በር ሳይወጡ ድንገት ለታ "እማ" ብሎ ተጣራ......አኳሀኑን አይተው ስንብቱ ፀበል ሳይሆን ለዘላለም ከማይመለስበት የሚሄድ የመሰላቸው እናቱ እንባቸው የሚገራ አልነበረም....አባቱ ዝም እንዳሉ ናቸው...የእሳቸውን መልስ የሚጠብቅ በረከተ....እሳቸው ግን በመመለስ ፈንታ ከነዝምታቸው አቀረቀሩ። የክብሮም እናትና እናቱ ተቃቅፈው መላቀሳቸውን ጀመሩ....


ይመስላል እንጂ የክብሮም እናት እንባ ለለታ አልነበረም....እንደዋዛ መጣሁ ብሎ ለቀረ ልጃቸው እንጂ....


"አይዞሽ እታግዬ..እኔ እናቱ እያለሁለት..."..ይላሉ የክብሮም እናት

"ግድ የለሽም እኔም አብሬያችሁ ልምጣ...ደግሞ አልጠመቅም ብሎ ሊያስሸግርሽ ይችላል...እናቱ አይደለሁ አመሉን አውቃለሁ..."....ይላሉ የለታ እናት....

"በትግል ነው ያሳመንኩት እታግዬ ደግሞ ከእኔ ውጪ ማንም አብሮት እንደማይመጣ በክብሮሜ ምዬለታለሁ...".....ድምፃቸውን ቀስ አድርገው ከለታ እናት ጆሮ ስር ቃላት ወረወሩ....

ጎረቤቱ በሩን ግጥም አርጎ ዘግቶ የሚፈጠረውን ያያል...በመሀል የክብሮም እናት እንደ ሙሴ በትር ሰልፉን ሰንጥቀው ወጡ....ለታ ከተገተረበት አለ....እናቱ እያገለባበጡ ይስሙታል....

"ተይ እንጂ ሆዱን አታባቢው...ና ልጄ ና...".....ለታ አሁንም ካለበት ንቅንቅ አላለም....የክብሮም እናት ተመልሰው ሄደው እጁን ይዘውት ወጡ...ለታ አሁን ሰው አይደለም...አሻንጉሊት ነው...ለታ አሁን በክብሮም እናት ብቻ የሚሰራ ማሽን ነው...ለታ አሁን የክብሮም እናት ብቻ የሚያጫውቱት ከረንቡላ ነው።


ተያይዘው ወጡ።



የለታ ቤተሰቦች ልጃቸውን ለክብሮም እናት አስረክበው መላቀሳቸውን ተያይዘውታል...በአንድ በኩል የልጃቸው መገራት እና ወደ ፀበል መሄድ አንዳች እፎይታን አላብሷቸዋል...እንዲሁ ግን ግር ያላቸው ነገር አለ...እንዴት የለታ ሀሳብ በቅፅበት ተቀየረ...? አያውቁም...ቢሆንም እንደ ሁለተኛ እናቱ በሆኑት የክብሮም እናት ላይ ሙሉ እምነት አላቸው...የገቡበት ራይድ ከአይናቸው እስኪሰወር ቆመው በአይናቸው ሸኙት.....


ሹፌሩ ከማናቸውም ጋር ምንም አላወራም...ዝም ብሎ መንገዱን ይሄዳል...



ለታ ሹፌሩ የክብሮም እናት ቅጥረኛ እንደሆነ ጠረጠረ...ቢሆንም ምንም ከማለት ተቆጠበ....መኪናው ወደነ ክብሮም ቤት አይደለም የሚሄደው...ቀስ በቀስ መኪናም ሰውም እየቀነሰ ሄደ....የልቡ መራድ ሲያይልበት መዳረሻቸውን ለመጠየቅ ደፈረ...


"ወዴት ነው ምንሄደው..."...አለ አንዴ ሹፌሩን አንዴ የክብሮም እናትን እያየ...


"እቴቴ..."....ተጣራ...አሁንም መልስ የለም....እሳቸው እንኳን አቤት ሊሉ ቀርቶ ወደ እርሱ ቢያዩ የሚረገሙ ይመስል ፊት ነስተውታል....




*



"ፍትህ ግን ቆንጆ ናት አይደል...."...ለታ ነው ይሄን ባዩ

" ቆንጆ አታውቅም "...መለሰ ክብሮም..

"እያት እስኪ ምን ይወጣላታል"

"ወደሀታል...?"...ክብሮም ጠየቀ...

"አልወጣኝም...እንዲሁ ነው..."

"አደራህን እንዳይወጣህ...እኔ የፉንጋ ጓደኛ መሆኔ ሳያንስ ደግሞ የፉንጋ አጎት መሆን አልፈልግም...ካካካካ...ልጃችሁን አሰብኩት...ካካካካ"


"በለው ከምኔው አጋብተኧን ከምኔው ወለድን...."...ለታ በክብሮም ተረባ ውስጡ አይረበሽም...ፉንጋነቱንም አይክድም...ፍትህ ፉንጋ መባሏና በክብሮም አይን ማነሷም አልጎረበጠውም...በትንሹ በእርዋ ላይ secure የመሆን ስሜት ሽው አለበት....


ከስራ ባልደረባቸው ከፍትህ ልደት ላይ ተገኝተው ጥግ ይዘው ያወራሉ...


"ግን የምሯን 25 አመቷ ነው"...ለታ የግርምት በሚመስል ድምፀት ይቺን አለ።

"ምነው አትመስልም አይዞህ አታስብ...በደንብ ትፈለፍላላችሁ...አታይም አቀለጣጠፏን...እኔን ወንድሜ አሳሰበህ አይደል ሜኖፖዝዋ ካካካካ"...

"ኧረ በፈጠረህ ድምፅህን ቀንስ..."....ለታ በክብሮም ድምፅ ተሳቀቀ...

"ለማንኛውም ወደ ቁም ነገሩ ስንገባ ትክክለኛውን ሰው ነው የጠየቅከው...ና ጠጋ በል"...አለ ክብሮም በሹክሹክታ...

"ስማ....25 አመት ንዑስ ቁጥር D ላይ ናት....

"ምን ማለት ነው ደግሞ ይሄ...."

"ማለትማ 25ተኛ አመቷን ለአራተኛ ጊዜ እያከበረች ነው...ምን አልባት E ካልገባ ቀጣይ 26 የመብላት ተስፋ አለን...ካካካካካ..."....ይሄኔ ለታ ሳቁን መቆጣጠር አቃተው....ቦታ ተቀያየሩና የለታ ሳቅ የፍትህ ትኩረት ጋር ደረሰ...


"ኧረ በፈጠረህ ለታ ፍትህ አኳሀናችን ግራ እያጋባት ነው እያየችን ነው"....ክብሮም ይሄን ሲል ለታ ሳቁን ባንዴ ቆረጠው...

"ኧረ ጓዴ ለዚህ ነበር ያዙኝ ልቀቁኝ..."


"ካየችን ይደብራታል ብዬ እኮ ነው..."


"በዚህ አይነት ሌላም ነገር ስታቋርጥ አትቸገርም ካካካካ..."....የሁለቱም ሳቅ ጣሪያ ነካ...





አላለቀም....ኧረ react....ዝም ብዬ ከምፅፍ ስሜታችሁን ልወቀው....ከወደዳችሁት 👍 ተጫኑ




Shewit dorka





https://www.tg-me.com/ethioleboled
ግርማዊ ጃንሆይ (ቀ.ኃ.ሥ) ከልጃቸው ልዕልት ፀሐይ ጋር ፤

ጳጉሜ/ 1928 ዓ.ም

ኢንግላንድ -- ለንደን

#ታሪክን_ወደኋላ
ነበር...4






"ፍትህ ግን እንደስሟ ናት..."....አለ ለታ ከርቀት አተኩሮ እያያት...አስተያየቱን ላየ ሰው ሳይሆን የፀሀይ ወገግታን የሚመለከት ይመስላል....

"ካካካካ እንደስሟ...ስትል"....ክብሮም ከሳቁ በኃላ ስለ ፍትህ ፍትህነት እንዲብራራለት ጠየቀ...ለታም ማብራራት ያዘ....

"የህፃን ልጅ ልብ ነው ያላት...እንደህፃን ልጅ የለሰለሰ ገላዋን እንጂ ማንም ልቧን አያይም...."....


"አየኧው እኮ አንተ...አይበቃም ካካካ....መቼ ነው ደግሞ ውጯን ጨርሰህ ወደ ውስጧ የገባኧው ካካካካ...."

"ድሮም ቁም ነገር ሲወራ ችግር አለብህ..."...ለታ በክብሮም ቀልድ ለመጀመሪያ ጊዜ ተበሳጨ....

"የምሬን እኮ ነው...ፍትህ እንደስሟ ፍትህ ናት ስትለኝ እንድታብራራልኝ እድሉን ሰጠሁህ...ከዛ አንተ ምን አልከኝ 'የህፃን ልጅ ልብ 'ምናምን...it doesn't make sense..."

"ምኑ ነው ውሀ ማያነሳው...?"...ለታ ጠየቀ....

"ህፃን ልብ አላዋቂ ነው...ፍትህ ደግሞ ከማንም በላይ አዋቂ ነው...ህፃንነት ለእኔ ብቻ የሚል ጥሬነት ነው...ፍትህ ግን ብስል ነው...ፍትህ የለሰለሰ መሬት ብቻ አይደለም...አንዳንዴም ከእሾህ መሬት የበለጠ አድሚ ነው...."

"ኧረ ክብሮም ተረጋጋ ምንድን ነው ይሄ ሁሉ ፍልስፍና...."

"ይሄን ለማወቅ መፈላሰፍም መጠበብም አያስፈልግም....በቀላሉ አይንህን መክፈት ብቻ ነው ሚጠበቅብህ....ፍትህን ቀለል አርገህ 'እንደ ስሟ ናት' እንድትል ያደረገህ የማላውቀው ትውውቅ ካለ ንገረኝ...ካልሆነ ግን የለሰለሰ ገላዋን ከጠራው ቆዳዋ ጋር ደምረህ ከዛም እንደ ባዘቶ የጠራ ጥርሷን እንደማስረጃ ተጠቅመህ ምንም ስለማታውቀው ልቧ ማውራት አትችልም...."....ክብሮም ይሄን ሲል ለታ የሆነ ቦታ ጋር እንዳዳለጠው ገባው....ምነው ምላሴን በቆረጠው አለ በልቡ...

"አልገባህም ...አንተ ምኑም አልገባህም...."....ለታ ይሄን ካለ በኃላ ከክብሮም የሚሰነዘርበትን ጥያቄ እያሰበ በላብ ተጠመቀ...ክብሮም ከጨዋታ አዋቂነቱ ሌላ ቁም ነገረኛም ነው...በምክንያታዊነት ያምናል...

"ምኑ ነው ያልገባኝ...."....የክብሮም ጥያቄ ተከተለ....ይሄኔ ለታ የያዘውን ቢራ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠ...ክብሮም የጓደኛውን አኳሀን አይቶ ፍቅር ቢጤ ነገር ጀማምሮት ይሆናል አለ በልቡ...


"በጣም እየመሸ ነው...ብንሄድ ይሻላል..."....ለታ ነው ይሄን ባዩ...ከጥያቄው ሽሽት እንጂ ገና ከምሽቱ ሁለት ሰአት ነበር....ክብሮም ምንም ነገር ማለት አልፈለገም...

'ፍቅር ውስጥ ነው...ክብሮም በቃ ጓደኛህን ከራሱ ጋር ተወው'....ብሎ ራሱን ገሰፀ።



**



መኪናቸው መጓዙን አላቆመም....


"እቴቴ...."....አለ እየፈራም እየተባም

"እቴቴ አትበለኝ....!!".....ጭራሽ እርሱ አይቶአቸው የማያውቅ ሌላ ሰው ሆኑበት።


"...አንዴ መኪናውን አቁምልኝ...."


ሹፌሩ መልስ ነፈገው....ያለው አማራጭ ዝምታ ብቻ እንደሆነ እያሰበ አይኑን ወደ መስኮቱ ሰደደ...ሰማዩ እንደማልቀስ እያለ ነው...ከመኪናው መውጣት ብችል እና ለቅሶውን ብቀላቀለው ብሎ ተመኘ... ...የሰማዩ ለቅሶ እያየለ መጣ...አሁን ከመኪናው ወርዶ የሰማዩን ለቅሶ ካልተቀላቀለ ሰማዩ ለቅሶ በላኸኝ ብሎ የሚወቅሰው መሰለው....


እየሄዱ ነው....


ሹፌሩ ተንጠራርቶ በለታ በኩል ያለውን የመኪና መስኮት ዘጋው...በመኪናው መስኮት ተሞርኩዘው ከዝናቡ ጋር የሚያወሩት የለታ አይኖች አጫዋች አጡ...የዝናቡ ወሬ ቆረፈደ....ምናል ንፋስ እንኳን እንዲያዋራኝ ትንሽ ሽንቁር ቢተውልኝ አለ በልቡ.....


"እባክሽ እቴቴ የሆነ ነገር በይኝ...."

"ደርሰናል"...





አላለቀም......



Shewit dorka





https://www.tg-me.com/ethioleboled
አንተነትህን ሙሉ የሚያረግህ ሰው ሳይሆን አንተን ሙሉ በሙሉ የሚቀበልህ ሰው ነው የሚያስፈልግህ።

😌 ቡድሁ😌

📚 @ethioleboled
ፍቅር ማለት የተናገርካቸው ሳይሆን የተገበርካቸው ነው።

💡ቡድሀ💡

📚 @ethioleboled
2024/09/22 23:26:30
Back to Top
HTML Embed Code: