Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአረም የተወረረ እርሻ አትሁን!

አንዳንድ ሰው የአረም እርሻ ነው። ብዙ የማይጠቅሙ ሃሳቦችን ተሸክሞ ይዞራል፣ አንተ ግን የማይጠቅሙ ሃሳቦችን ከአእምሮህ ጓዳ ቶሎ ቶሎ አጽዳ!

በረከቶችህን እንጂ ጉዳቶችህን አትቁጠር፣አእምሮ ሰነፍ ጮማ ስጋ ነው። መጥፎም ይሁን ደግ የተነገረውን ለቀም ነው።ለአእምሮህ የምትነግረው ደግ ደጉን ይሁን። አለዚያ መጥፎ ሃሳብ ከሰጠኸው ያንን ይዞ ይመርዝሃል።

አዘውትረህ የምታስበው ሃሳብ በውስጥህ ይደድራል። ውሎ አድሮም ይገዝፋል፣ ሃሳብ ለአእምሮ፣ ስፖርት ለጡንቻ እንደሆነው ነው።መጥፎ ምግብ ሰውነትን ይመርዛል።መጥፎ ሃሳብ አእምሮን ይመርዛል።በመጨረሻም ሰውየውን ገላፈቻ (ከጥቅም ውጭ) ያደርገዋል።

መጥፎ ሃሳብን አታመንዥክ የጥላቻ ሃሳብን አታመንዥክ። ይልቅስ መጥፎ ሃሳቦችን ከአእምሮህ እያጸዳህ በመልካም ሃሳቦች ተካቸው፣ስለሰው ስታስብ የሰውየውን መልካም ጎን ለይተህ ለማሰብ ሞክር፣ ችግርን ተጋፈጥ። መልካም ሃሳብን ዝራ፣ መጥፎን በመልካም ሃሳብና ድርጊት ተዋጋ።

ይህ ሁሉ ሆኖ ከመጥፎነት አልመለስ ለሚሉ በመጥፎ ሃሳባቸው እንዳትጠመድ ከእነርሱ ራቅ። ሁሌም ደግ ደጉን እናስብ። ደግ ደጉን እንሥራ። መልካምነት ሌላው ቢቀር የአእምሮ ሰላም ይሰጣል። ከጨጓራ ህመም ያተርፋል።

ነገ ሲነጋልህ፣  ተነስና በረከቶችህን ቁጠር። ለጤናህ ፈጣሪህን አመስግን። ለቀጣዩ ቀን ውሎህ ሰላምና ስኬት ፈጣሪህን በጥበባዊ ጸሎት ለምን። በዚህ ምን ትጎዳለህ? የተሻለ ምርጫስ አለህ?

የቀን ውሎህን አቅድ። ለሥራህ ተዘጋጅና ቆፍጠን ብለህ ውጣ። ፈገግታ ከፊትህ አይጥፋ! ጎበዝ ገበሬ ሁን! የጎበዝ ገበሬ እርሻ ከአረም የጸዳ መልካም ቡቃያ ነው።

Getu k toughe

ውብ ጊዜ❤️

@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
A SHORT LIFE LESSON!

💎 Someone graduated at the age of 22, but waited 5 years before securing a good job.

📍 Someone became a CEO at 25, and died at 50, While another became a CEO at 50, and lived to 90 years.

💎Someone is still single, while someone from his school group has become grandfather.

📍Obama retired at 55 & Trump started at 70, Everyone in this world works based on their time zone.

💎People around you might seem ahead of you & some might seem to be behind you. But everyone is running their own race, in their own time, Do not envy them.

📍They are in their time zone, and you are in yours.

So, relax.

You're not late.You're not early.
You are very much on time, and you will achieve your desired goals for Life (Be Encouraged).

Happy Saturday❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
📍በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰውዬ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መጠቀም ይጀምራል። ታዲያ በመሐል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል። በዚህ ቅፅበት አውሮፕላኑ በሐይል መንገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀመራል። ሰውዬውም ደንግጦ ወይኔ ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ሕዝብ ጨረስኩኝ ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኃላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል። ሁሉም ሰው "አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!" ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም።

  📍መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው ቀስ እና ስቅቅ ብሎ "ይቅርታ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻቹ ነበር አይደል?" ይለዋል።  ሰውዬውም "አረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያሕል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይደረጉም ...ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። በአጋጣሚ ትንሽ የአየሩ ሁኔታ አስቸጋሪ ስለሆነ ነው አውሮፕላንኑ የተንገጫገጨው" ይለዋል።

  📍ብዙ ጊዜ ሰዎች እንደዚህ ያስባሉ። የሆነች ነገር ነክተው ሕይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያክል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን የሕይወትህ ካፒቴን ጋር እንዳለ ነው። እንደዛማ ባይሆን ኖሮ ቀይዋን ነገር እየጠቀጠቁ ሕይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና እንደዚሕ አይነት ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮችን በሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል።

💎ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር፣ ሰማያዊ ጥበብ በጆሮ አይሰማም። እምነት በዓይን አይታይም።

ሁሉንም ክብርና ምስጋና የፈጠረን ይውሰድ።

📖አርምሞ

ወብ አዳር ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
ወዳጄ  ሆይ

💡በራስህ መስታወት የራስህ አቅም የቱንም ያህል ጉዙፍ መስሎህ ቢታይህም በሕይወትህ ረጅም መንገድ የለህምና የወደቀውን በማንሳት ፈንታ በውድቀቱ አትሳቅ፣በእብደቱ አትሳለቅ ፣ በማጣቱ አትፈንድቅ ፣ እብሪት የውድቀት ዋዜማ ነው ፣ በኋላም ሆነ ነገ ጊዜ ባንተ ላይ ምን እንደሚያመጣ አታውቅምና ስትኖር ጥላቻ ሳይሆን ፍቅርን፣ በቀል ሳይሆን ይቅርታን፣ትዕቢትን ሳይሆን ትህትናን በልብህ ሰንቅ።

ወዳጄ ሆይ

💡ዛሬን ማግኘትህ ትልቅ ስጦታ ነውና በጥልቅ ሀሴት ተሞልተህ ደስ ይበልህ፤ የፈጠረህን በእጅጉ አመስግን፣ በትንሹ ለፀሐይ ብርሃን፣ለምትተነፈሰው አየር ክፈል ብትባል ቅንጣቱን እንደማትችል ሁሉ አስበህ ከማንም እንደማትበልጥ፤ከማንም እንደማታንስ አውቀህ ተራመድ ፣ በተሰጠችህ እያንዳንዷ ቀን በመልካምና በደስታ ለመኖር ሥጋህን ተጠንቀቀው፤ነፍስህን ቁጠራት፣እምነትህን ጠብቀው፡፡

የትም ግባ፣የትም ውጣ በነገሮች አትደነቅ፣ብርቅ አይሁንብህ ዓለምን በሩጫም በእርምጃም ብታስስ ከድካምህ ባለፈ አዲስ ነገር አታይም ፣ ደግሞም ለምድሪቱ ትልቅ  ስራ ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ መውደድ ነውና ዋጋ ለማታወጣበት ነገር ለማንም ያልተጓደለ ክብር ስጥ፣ፍቅር አሳይ፡፡

ወዳጄ ሆይ

💡ዕድሜህ ሃያ ዓመትህ ስለሆነ ብቻ ከዚህ በኋላ ብዙ ቀሪ ዕድሜ እንዳለህ እያሰብክ አትኮፈስ በሆነ ገጠመኝና ክስተት ዛሬን ሳያገኙ በምሽቱ ምድሪቱን የተሰናበቱ አያሌ ናቸውና፡፡ ደግሞም ባለህ አያሌ ሀብት፣ባለህ የተንጣለለ ህንፃ፣ባለህ ሠፊ ዕውቀት፣ባለህ ችሎታህ፣ባለህ ጉብዝናህ፣ባለህና በተማመንክበት ሁሉ ዛሬን ለማለፍ ዋስትናህ አይደለምና ከሚሆነው ነገር ተጠበቅ፣ከምታደርገውም ነገር ተጠንቀቅ፡፡

እናም ወዳጄ

💡ተግባርህ በመልካም የተሞላ ይሁን፣አንድ ዳቦ አጥተው ጎዳና የወደቁ ሠዎች መኖራቸውን ባይንህ እያየህ ባንክ ላጠራቀምከው ሚሊዮን ብሮች ከሳሳህ ሠው የመሆን ድርሻህ ምንድነው? ምድር ላይስ የመቆየት ዓላማህ ምን ይሆን? የገነባህው ህንፃ፣ያጠራቀምከው ገንዘብ፣ያነፅከው መኖሪያ ቪላ ከሠዎች ማግኘት ማጣት፣መብለጥ ማነስ በሚል ስሌት አትስራበት፡፡ በመኖርና በመሞት መካከል ያለው ርቀት የቅፅበት ያህል ነውና፡፡

🔑 በዓለም ላይ የትኛውንም ያህል የገንዘብ ብዛት አንድ ቀንን ገዝቶ የአንተንም ዕድሜ፣የዓለምን ፍፃሜ የማራዘም አቅም የለውም።  ስለዚህም በምድር ነገር መኩራራትህን ትተህ፣ባለ ነገር መኮፈስህንም አቁመህ፣ምንም ይዘህ እንዳልመጣህና፣ምንም ይዘህ እንደማትሄድ ከገባህ መሽቶ በነጋ ቁጥር ፈጣሪህን ታመሰግናለህ !!!

     ዛሬ በሕይወት ስላለህና ይህንንም መልዕክት በማንበብህ ዕድለኛ ነህ.. ደስ ይበልህ!! ይህንን ካነበብክ በኋላ ምን ተሰማህ??

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሚያሳዝነው እኛ ሰዎች ሙሉ ሕይወታችንን መኖር ለመጀመር በመጠባበቅ ላይ ሆነን ሳንኖር መሞታችን ነው። Eckhart Tolle

“ይህንን ባገኝ ደስተኛ እሆን ነበር” የሁላችንም መፈክር አይደለም? ወይም የለመድነው የኑሮ ሂደት። ከላይ የሰፈረው የኤካርት ቶሌ አባባል ይህንን አኗኗራችን በደንብ ይገልጸዋል ብዬ አስባለው ። ሰዎች ኑሮን ለመጀመር እየጠበቁ ኑሮን ሀ ብለው ሳያጣጥሙ የእድሜያቸው ጀንበር ትጠልቃለች። ጥሩ ስራ ሲኖረኝ፤ ትዳር ስመሰርት፣ አላማዬን ሳሳካ ደስተኛ እሆናለው እያለን ለኑሮዋችን ቀጠሮ ስንሰጥ፤ ያሰብነው እስኪሳካ ደስተኛ ላለመሆን እየወሰንን ነው።

የሰው ልጅ ምኞት ማለቂያ የለውም። በጠየቅን ቁጥር ፈጣሪ ያልነውን ቢሰጠን እንኳን እንደሰው እረክቶ ለመኖር ይከብደናል። ለዚህ ነው ደስታችንን ነገ ከምናገኛቸው ነገሮች ጋር መቋጠር ዛሬን በሰመመን እንድንኖር የሚያደርገን፣ ያሰብኩት እስኪሳካ ደስተኛ መሆን አልችልም ማለት ነው “አስከዛው አልኖርም” ማለት ነው። የነገው ህይወታችን ትልቅ ትርጉም አለው፤ ዋጋው ግን የዛሬን ያህል በፍጹም አይሆንም።

በዚች አጭር ፁሁፍ እንለያይ፣

ለመኖር ስሟሟት ነበር :-
"በመጀመሪያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ለመጨረስ እና ኮሌጅ ለመጀመር ስሟሟት ነበር፣ ከዚያም ኮሌጅ ጨርሼ ሥራ ለመጀመር ተሟሟትኩ

ቀጥሎም አግብቼ ልጅ ለመውለድ ስሟሟት ነበር ፣ከዚያም ልጆቼ አድገው እድሜያቸው ለትምህርት  እንዲደርስ እኔም ወደ ሥራ ቶሎ ለመመለስ ስሟሟት ነበር።

ከዚያም ጡረታዬ ደረሰ እሱንም ለማግኘት ተሟሟትኩ ፣አሁን ግን መሸብኝ እኔም እየሞትኩ ነው።በሕይወቴ ውስጥ ለነገዬ ስሟሟት፣ዛሬን መኖርን እንደረሳሁ ድንገት ገባኝ" ይላል ፀሀፊው።

እናም ወዳጄ ውብ አሁን! 😊

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
📍ልብን እና አዕምሮን ማቆሸሽ ራስን እንደመጣል ይቆጠራል፡፡ ሕሊና ቢስ መሆንም ሕሊናን በራስወዳድ ሃሳብ ማጨቅየት ነው፡፡ አስተሳሰብን ማጠልሸት፣ አመለካከትን ማጨለም አንጎልን በቆሻሻ መበከል ነው፡፡

ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶ በነበረበት ጊዜ፣ ነቢዩ ኢሳይያስ ለጆሮ በሚከብድ  ቃል እንዲህ ብሎት ነበር:: "ንጉስ ሆይ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"

ንጉስ ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ወደፈጣሪው ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም ፣ ነገር ግን ፈጣሪ ልቦናውን አይቶ እድሜ ጨመረለት። ንጉስ ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ሲሉ ይጠይቁታል

ንጉስ ሕዝቅያስ ግን ከአልጋው ሳይወርድና ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ "ልቡን" ነበር::

አንተም ፈጣሪን የሚፈራ ልብ ይኑርህ ፣ ፈጣሪ ባህሪና ተግባራችንን ያያል። ከሰው የወሰድነውን ከሰውየው ብንደብቅ ከአምላክ አንደብቅም። ዓሣ  ከውኃ ወጥቶ ከቆየ ወዲያው እንደሚሞት ሰውም ከህሊናው ከፈጣሪው ከወጣ እንደዚሁ ይሞታል፡፡ ዓሣው ቶሎ ተምልሶ ወደ ውኃው ሲገባ እንደሚድን ሰውም ከልቡ ሆኖ ይቅርታ ሲጠይቅ ፣ፈጣሪ የይቅርታውን በር ይከፍትለታል።

🔑ወዳጄ ሆይ  ልቦናህን አጥራው፣ ስሜትህን ግራው፣  ሕሊናህን ዘወትር በአዲስና በበጎ ሃሳብ ሞርደው፣ ምን ዘንካታ ብትሆንና አለባበስህ ቢያምር ሕሊናህ ከቆሸሸ በሚያምር  ቤትህ ውስጥ ቆሻሻ እንደመከመር ነው፡፡ አንተ ግን ልብህን ካስተካከልክ ቤትህ፣ ስራህ፣ ቤተሰብህ፣ ትዳርህ፣ በዙሪያህ ያሉ ችግሮችህ እና የሚያስጨንቁህ ነገሮች ሁሉ ይስተካከላሉ።

          ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
ለውብ ቀንህ

ፍሬድርክ ኒቼ በደስታና በፈንጠዝያ የምፎልሉትን እንሰሳት ተጠጋና ጠየቃቸው።

"ለምንድነው እንደዚህ ደስተኛ ልትሆኑ የቻላችሁት?" የሚል ነበር ጥያቄው። እነሱም
ባንድነት፣ ባንድ ቃል መለሱለት።

ምንም ሳይወያዩ፣ ምንም ነገር ሳይፎካከሩ፣ መንፍሳቸውም ሳይቀናና፣ አንዱም ሌላውን
ሳይተች፣ ደመ-ነሳቸው በሚነግራቸው መሰረት፣ " ከሳለፍነው ታሪክ ጋር ምንም ቁርኝት (Attachment) ስለሌለን ነዋ!" አሉት።

ከአፍታ በሁዋላ "ምን አላችሁኝ? እስኪ ድገሙልኝ?" ሲል
ጥያቄዎቹን አዥጎደጎደባቸው ።

እነሱ ግን የሰጡት መልስ አጭርና አስገራሚ ነበር።

"ምኑን ነው የምንደግምልህ?" የሚልና
ክው አድርጎ የሚያስቀር ………ፎቶው ከፅሁፉ ጋር የሚገናኘው ምኑ እንደሆነ ታውቃላችሁ?

እኛም በየቀኑ አዳዲስ የሆኑ እድል ይሰጡናል። የትናንት ጭንቀቶች አጥብቀን ምንሸከም ከሆነ ግን ዛሬን በሙሉ ሀይላችን መኖር አይቻለንም ፣ዛሬ የትናንት ተማሪ ነው፡፡ ዛሬ ነገን ውብ ቀን ለማድረግ የሚሰራ በእጃችን ያለ መክሊታችን ነው፡፡ የትናንትን ኋላቀርነት የሚደግም የዛሬ ቀን ለዛሬም አይሆንም፣ ለነገም አይተርፍም፡፡ ያለፈውን ደካማ ነገር መሻር ሲገባ የምንደግም ከሆነ ወደፊት መራመድ አንችልም፡፡ ትናንትን ወደነገ የሚያሻግረው ዛሬ ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ የትናንት ምርጥ ተማሪ ካልሆነ ነገውን ውብ ማድረግ አይችልም፡፡

ሕይወትን አስደሳች እና ቀላል አርጎ መኖር ይችላል። የተሸከመከውን የሀሳብ ክብደት ለመተው ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅብሀል፣ የሕይወት እውነተኛ ክስተት  አሁን ነው። አሁን ባለህ ጊዜ  ሰላም ፍጠር! ዛሬን እንደዛሬ በአዲስ ለመመልከት ፣ ትናንትህን መልቀቅ አለብህ፣ እራስህን አትጋርድ።

           ውብ አሁን❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@Ethiohumanitybot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መረጋጋት የውሃ ተፈጥሮን በጥሩ ሁኔታ ይወክላል።ለእኛ ለሰው ልጆች አርአያ ሊሆነን ይገባል ምክንያቱም ውሀ ሀይሉን የሚሰበሰበው በእርጋታ ነው። 

ራሳችንን የመቀየር ሀሳብ ካለን ቅድሚያ አስተሳሰባችን ምን እንደሚመስል መቃኘት አለብን። ረጋ ብለን ለደቂቃ በጥሞና ውስጣችንን ብንሰማ፤ እጅግ እንገረማለን። ሃሳባችን አንዴ ከትላንት፤ አንዴ ከዛሬ አንዴ ከነገ፤ ሳያቋርጥ ይጋልባል፣ልክ ያለማቋረጥ እንደሚማሰል ኩሬ መንፈሳችንን ያደፈርሰዋል።

አእምሮአችን ያለ ማቋረጥ ሀሳብ ሲያበዛ ጭንቀትና ድካም ያስከትላል፣ ውሃን ብቻውን ስንተወው ሳይታወክ ጥርት ረጋ ይላል፣ የረጋ ውሀ ለአናጢው እንኳን ሳይቀር በውሀ ልክ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፣ግንባታን እኩል ያረጋል።

ውሃን ካስተዋልከው ይፈሳል ምንም ጠንካራ ነገር ከመጓዝ አያቆመውም፣ ሁልጊዜ ወደፈለገበት ቦታ ይሄዳል፣ውሃ ትግል አያቅም እንቅፋት ሲገጥመው ዞሮ ያልፋል፣ጠብ እያለም ድንጋይ ይንዳል፣ ስናየው ስስ ነው ግን እሱን የሚያህል ጠንካራ ነገር የለም።በእርጋታ ጊዜ ውሃ እንዲህ ተአምር ከሰራ የሰው ልጅ መንፈስ ረጋ ቢል ምን ውጤት ያመጣል ብለህ አስብ?

ወዳጄ  ሆይ አንተም አስታውስ ግማሽ አካልህ ውሃ ነው ፣በእርጋታህ ሀይል መሰብሰብ ትችላለህ ፣እንቅፋት ውስጥ ማለፍ ካልቻልክ አትታገል በዙሪያው እለፍ ፣ በሁኔታዎች አትታሰር ግትር መሆን ጅልነት ነው። በብዙ አቅጣጫ መንቀሳቀስ ደግሞ ብልህነት ነው።

💧ብልህነት ሁል ጊዜም እንደ ጅረት ውሀ መፍሰስ ነው፣ ነገ የገዛ ራሱን አጋጣሚ ይዞ ይመጣልና የትላንቱ ሃሳብህ ላይ የሙጥኝ አትበል፣የሰው ልጅ እራሱ ከሚፈጥራቸው የመንፈስ ካቴናዎች ነጻ ወጥቶ የመኖር አቅም አለው።የህይወት ለውጦችን ከመቃወም ይልቅ ራስን አስተጋብሮ መራመድ ጥበብ ነው።

         ውብ ጊዜ❤️

@Ethiohumanity

@Ethiohumanitybot
💡ከዜሮ መጀመር ትችላለህ

📍ያለንን ነገር ሁሉ ብናጣ ፡ የተመካንባቸው ሰዎች ቢርቁን ፡ በሽታ ቢያሰቃየን ፡ የባንክ አካወንታችን ባዶ ቢሆን ፡ ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ቢከሰቱብን ፡ ሁሌ ከዜሮ መጀመር ይቻላል።

እድሜያችን ቢገፋ እንኳን በልጅነታችን የተመኘነውን ማንነት በየትኛውም ጊዜ መገንባት እንችላለን ። ከኛ የሚጠበቀው ለመለወጥ ያለን ቁርጠኝነታችን ፡ ፅናታችን ፡ እምነታችንና ትዕግስታችን ነው። ማትኮር ያለብን ችግሩ ላይ ሳይሆን ወይም ስለችግሩ ማልጎምጎም ሳይሆን ችግሩን ለመፍታት የሚረዱንን መሰረታዊ ጽንስ ሀሳቦች ቁርጠኝነት ፡ ጽናትና ፡ ትዕግስት ላይ ነው።

💡 የሕይዎትህ መለወጫ መሪ ያለው በራስህ እጅ ላይ ነው። ሌሎችንና ሌላ ጊዜን አትጠብቅ። ጊዜው አልፏል ብለህም አትቁም ፡ ያንተ ጊዜ አሁን ነው። ጉዳይህ ያለቀና ያበቃለት ቢመስልም አንተ ከጠነከርክ እንዲሁም ከልብህ ፡ እኔ አሁንም ተስፋ አለኝ ብለህ ከባዶ የመነሳቱ ድፍረቱ ካለህ ያኔ አንተ አንፀባራቂ ብርሀንን ታያለህ። ራስህንም ድሮ ከነበርክበት ባዶነት አውጥተህ እንደገና ሕይዎትን የመኖር ፅንሱን ውስጥህ ትፀንሳለህ።

ያኔ አንተ ተቆርጠህ ከተጣልክበት ትቢያ እንደገና አገግመህና ፡ አቆጥቁጠህ ትታያለህ። ልምላሜህም ከበፊቱ የበለጠ ይሆናል። ቅርንጫፎችህ ፡ ተቆረጡ እንጂ ዋናውን የሕይዎት ምስጢር የያዘችው አንተን ከአፈሩና ፡ ከውሃው የምታገናኝህ ስራህ አልተቋረጠችምና እንደገና ትለመልማለህ። እንደገና እራስህን በእድገት ምናብ ከዋጀኽው በድጋሚ ታብባለህ።

📍በድጋሚ ቀንበጥ ፡ ቀንበጥ የሆኑ የሚያስጎመጁ ፡ አረንጓዴ ቅጠሎችንና ፡ ቅርንጫፎችን ፡ ታቆጠቁጣለህ። ግመል በበረሓ ስትጓዝ በረሓው ላይ ውሃ እንደሌሌ ታውቃለች። ግን ወደ በረሓው እንድትገባና ፡ እንድትጓዝ ስናደርጋት ፡ ወደ ኋላ አታፈገፍግም ወይም አትፈራም። ምክንያቱም ፡ የሻኛው ጮማ ውስጥ በቂ የሆነ ምግብና ፡ ውሃ እንዳለ እርግጠኛ ስለሆነች እሷ የምትዘጋጀው ከበረሓው ፡ ከመግባቷ በፊት ውስጧ ምግብ በማጠራቀም ነው።

አንተም እንደ ግመሏ ውስጥህ ላይ አትኩር። ሌሎችን የበረሓው ግለት ፡ የበረሓው ንዳድ ፡ የበረሓው አሸዋና ፡ የበረሓው መጨረሻ መራቅ ተስፋ ቢስ ሲያደርጋቸው ፡ አንተ ግን ለድል አነሳሳቸው ፡ ውስጣቸው ያለውን የአሸናፊነት  ጮማ ፡ የተስፋ ጮማ ፡ የፍቅር ጮማ ሻኛ እንዳለ ንገራቸው። አንተ ከፊት ሆነህ ባለህ የዕውቀት ፡ የፅናት ፡ የትዕግስት ፡ ብረሀንህ ጉዟቸውን አቅልጥላቸው።

💡አንተ ራስህን ከምንምና ፡ ከባዶ አንስቶ ለትልቅ ደረጃ ፡ የሚያበቃ አቅም በውስጥህ አለ። አንድ ልታውቀው የሚገባህ ትልቅ ቁምነገር ፡ ዜሮ ፡ የቁጥሮች መጨረሻ ሳይሆን ፡ የቁጥሮች መጀመሪያ መሆኑን ነው። ያለህ ነገር ሁሉ ዜሮ የሆነ ከመሰለህ ፡ እንግዲያው አንተ ደስ ሊልህ ይገባል። ምክንያቱም ፡ በህይዎትህ ያለህ ደስታ ሁሉ ፡ ያለህ ሀብት ሁሉ ፡ ያለህ ዝና ሁሉ ፡ ያለብህ ገንዘብ ሁሉ ፡ ያለህ ተቀባይነት ሁሉ ፡ እንደገና ከዜሮ ፡ መጨረሻ ፡ ወደሌለው ቁጥር "ሀ" ብሎ ሊንደረደር ነውና !!!

                             📓የኔ ስጦታ
ብሩክ የሺጥላ

ውብ ምሽት❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@Ethiohumanitybot
❤️ቅናት አንድ ሰው በሚወዳቸው ሰዎች በምላሹ ተወዳጅ እንዳልሆነ ሲያስብ የሚሰማው ህመም ነው፣ ቅናት ሁሌም የሚመነጨው ከንፅፅርና ከውድድር ነው።

ከልጅነታችን ጀምሮ እያነፃፀርንና እየተነፃፀርን መኖር ለምደናል። ስንማረው ኖረናል ። የሆነ ሰው የተሻለ ቤት አለው ። ውብ የሆነ ሰውነት ይኖረዋል። አንዳንዱ ከሌላው የበለጠ ገንዘብ አለው። ሌላው ደግሞ መስህብ ያለው የስብዕና ባለቤት ነው፣ እነዚህን ነገሮች እየተመለከትን ከእነዚህ ሰዎች ጋር እራሳችንን እያነፃፀርን ነው የኖርነው።

📍ማወዳደር ትልቅ በሽታ ነው፣  የራስህን ሕይወት በፍጹም ከማንም ጋር አታወዳድር ። ምክኒያቱም እራስንህን ከሌሎች ጋር ስታወዳድር የምታገኘው ውጤት ከዛ ሰው የተሻልክ ከሆነ ኩራት ሲሆን ከዛ ሰው የምታንስ ከሆነ ደግሞ ቅናት ነው የሚሆነው ። ሁለቱም መጥፎ ውጤቶች ናቸው፣ ቅናት ደግሞ ከንፅፅራዊ ባህሪ የሚመነጭ ተረፈ ምርት ነው። እራስህን ማነፃፀር ካቆምክ ግን የቅናት ስሜትህ ሙሉ ለሙሉ ይጠፋል፣ ከምንም በላይ ውበት የሚገለጸው  እራስን በመሆን ነውና ።

💎ቅናት፤ ተንኮል፤ ጥላቻ እና ቂም የሰውነትን ውበት እና ግርማ የሚሰርቁ ቀማኞች ናቸው። ፈገግታ የራቀው ኮስማና ፊት እንደው ዝም ብሎ የሚመጣ ነገር አይደለም፤ ኮስማና ሃሳቦችን ከማሰብ የሚመጣ እንጂ፣ ሰዎች ደስ የሚሉ ሃሳቦችን ሲያስቡ፤ ሰውነታቸው በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለ ይናገራል፤ የውስጥ ደስታቸው ደስ የሚል ግርማን ያላብሳቸዋል። ሰውነታችን በቀላሉ እንደአስተሳሰባችን ይለዋወጣል። መልካም እና ክፉ አስተሳሰቦች የየራሳቸውን ተጽዕኖ ያሳድሩበታል።

💡ከንጹህ ልብ፤ ንጹህ ሰውነት ይገኛል፤ ከጤነኛ አስተሳሰብ ጤነኛ ሰውነት ይወለዳል፣ መልካምነት ከማንም በላይ ላራስ ነው ጥቅምና ፍይዳው። ቅን ሀሳብ አሳቢውን ይባርካል። ሴራ፣ ተንኮል እና ክፍት ህሊናና ልብህን ከሞላው ግን መንገድህ መሰናክል ይበዛዋል ፣ እናም በልብህ ጥላቻ ሳይሆን ፍቅርን፣በቀል ሳይሆን ይቅርታን ፣ ቅናት ሳይሆን ቅንነትን ፣ ስስት ክፋት ሳይሆን ደግነትን ፣ ትዕቢት ሳይሆን ትህትናን፣ ሁሌም በልብህ ብትሰንቅ ነገ መልሶ የህይወት ስንቅ ይሆናሃል።

           ውብ አሁን!!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
📍መስጠት ዋና ስራህ ይሁን

ብዙ በመልፋት ብዙ በመጣር ትልቅ ውጤት ልታመጣ ወይም በሀብት ደረጃ ልትበለፅግ ወይም የምትፈልገውን አይነት ሀብት ልታገኝ ትችላለህ፣ ነገር ግን ከበፊቱ የተለየ የተሻለ ቆንጆ ምግብ ትመገብ ይሆናል እንጂ ልኩ አይጨምርም። ስላለህ ብቻ ሰው መብላት ከሚችለው መጠን በላይ አትበላም በአንድ ግዜ ብዙ ልብስ አትለብስም ሁለት መኪና ባንዴ አትነዳም የምትኖረውም አንድ ቤት ላይ ነው፣ ነገር ግን ለሰው ልጅ ስታካፍል እነዚህን ሁሉ ባንዴ ማድረግ ትችላለህ፣ በመስጠትህ ከራስህ ወጥተህ ሰፋ ብለህ ህይወትን ትኖራለህ።

❤️ የተራቡ ስታበላ እርካታው ሚሊዮኖች ከሚበሉት በላይ ነው፣ የታረዙትን ስታለብስ ከለበስከው በላይ ሙቀት ከለላ ይሆንሀል ባንዴ በብዙ ልብስ ታጌጣለህ። ህይወትም ትርጉሟ የሚጨምረው ለሌሎች መኖር ስንጀምር ነው !ሁሌም በጎ በጎውን ማድረግ ስትለማመድ መልካም ገበሬ ትሆናለህ።ለሌላው የሚጠቅም መልካም ድርጊት ወደ ዓለም ስትልክ መልካምነትህ ዞሮ ይከፍልሃል፣ ብድራቱን ታገኛለህ።

የጣልከው አልያም ያካፈልከው ሁሉ መልሶ ብድራቱን ይከፍልሃልም። መልካም መሆንህ ምንም ኪሳራ የለውም። ያንተ መልካም ስነምግባር ሌላውን ተመልካች ከተኛበት የመቀሰቀስ መግነጢሳዊ የስበት ኃይል እንዳለው አንተ አታውቅም ይሆናል። በዚህ ምድር ላይ የተዘራ ማንኛውም ነገር እንዲሁ ወድቆ የሚቀር ላይሆን ይችላል።

💡ወሳኙ የምንሰጠው መጠን ትንሽነትና ትልቅነት ሳይሆን በምንሰጠው ነገር ላይ የምንጨምረው ፍቅር ነው፣ ስላለን ስለሞላን ብቻም ሳይሆን ካለን ማካፈልንም መልመድ እንጀምር። የህይወት መሰረት የሚጣለው ሁሌም ከዛሬ ነው ፣ ከዛሬም አሁን!

ዛሬ ትንሽ መስጠት ነገ ትልቅ ወጋ አለው።
ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
💡ሰውየው በቤቱ አንድ ትልቅ ዛፍ ነበረው አሉ፤ ይህ ዛፍ ህልውናው እንዳይጠፋ በእጅጉ ይንከባከበው ነበር። በቀን በቀን፤ ሲመሽም ሲነጋም ወደ ዛፉ እየሄደ ምርጥ ጊዜ ያሳልፋል። ከእለታት አንድ ቀን ግን፤ ይህን ግዙፍ ዛፍ ትክ ብሎ ሲመለከተው  አንዳንድ ቅጠሎቹ ቀለማቸውን እየቀየሩ እየጠወለጉ መምጣታቸውን ተመለከተ፤ ሰውየው ሃዘን ገባው። ምንም  እንኳን ዛፉ ትልቅ እና ግዙፍ ቢሆንም፤ እንደምንም ከዛፉ እላይ እየወጣ፤ የጠወለጉትን ቅጠሎች በውሃ ማራሱን ተያያዘው። ተመልሰው ነፍስ እስኪዝሩ ድረስ፤ ሽቅብ ወደ ላይ እየወጣ ቅጠሎቹን እየወለወለ በውሃ ያርሳቸዋል።

......ለብዙ ቀን እንዲህ ሲለፋ ቆየ፤ ምንም እንኳን የተቻለውን ያህል ቢለፋም ቅጠሎቹ አንድ በአንድ ከመድረቅ እና ከመጠውለግ አልዳኑም። በመጨረሻ ሰውየው ከልፋቱ ብዛት ደከመው፤ የነበረውም ውሃ በሙሉ አለቀበት። ቀስ በቀስ ዛፉ መሞት ጀመረ……..

📍ይህ ሰው ሃይል እና ጉልበቱን እንዲሁም ሃብቱን በከንቱ አባከነው። የዛፉን ስር ውሃ እንደማጠጣት፤ የጠወለጉት  ቅጠሎች ላይ ጊዜውን በማጥፋቱ፤ ዛፉን በሙሉ አበላሸው። ምን አልባት ብልህ ሆኖ ስሩን በውሃ ቢያርሰው ኖሮ፤ የጠወለጉት ቅጠሎች መልሰው ባበቡ፤ ሌሎችም ከመጠውለግ በዳኑ ነበር።

💡አብዛኛዎቻችን እንዲህ ነን፤ ህይወታችን መታደግ የሚያቅተን፤ ትኩረታችን ሁሉ፤ ስራችን ላይ ሳይሆን ቅጠላችን ላይ ስለሆነ ነው። ቅጠሎቻችን ምንድን ናቸው? ባህሪያችን፤ ልምዳችን፤ ወይም ሌሎች የአስተሳሰባችን ውጤት የሆኑ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ስራችን ግን ማንነታችን የሚበቅልበት አስተሳሰባችን ነው። ባህሪዎቻችን ወይም ተግባሮቻችን ሲጠወልጉ፤ ስራችንን እንደማስተካከል፤ ጊዜ እና ጉልበታችንን ለውጥ በማያመጡ ነገሮች ላይ እናጠፋለን።

📍የሁላችንንም ቅጠል የሚያጠወልገው ነገር ይለያያል፤ አንዳንዶቻችን በሱስ እንጠወልጋለን፤ አንዳንዶቻችን በስንፍና፤ አንዳንዶቻንች በቂ ፍቅር ስለሌለን፤ አንዳንዶቻችን በራሳችን ባለመተማመናችን፤ አንዳንዶቻችን ተስፋ በማጣት፤ ብቻ በተለያይዩ ምክንያቶች መጠውለግ እንጀምራለን። መጠወለጉ ሲያንገፈግፈን እና እንደገና ለማበብ ስንወስን ደግሞ መላው ይጠፋብናል። በለፋን ቁጥር ይበልጥ እንጠወልጋለን፤ ልፋታችን ከንቱ ይሆንብናል። ምክንያቱም ብዙዎቻችን እንደ ሰውየው፤ ጊዜያችንን የምናጠፋው ለውጥ በማናገኝባቸው ነገሮች ላይ ነውና።

💡የሁሉም ነገር መሰረት አይምሮዋችን ነው። የጠወለገውን ክፍላችንን እንደገና ህይወት መስጠት የሚያስችለን ብቸኛው መፍትሄ አስተሳሰባችን መቀየር ብቻ ነው። እራሳችንን እንደዛፉ ብንመለከት፤ የትኛው የህይወታችን ክፍል ነው እየጠወለገ ያለው? ልፊያችንስ ከተበላሸው ባህሪያችን ማለትም ከጠውለገው ቅጠላችን ጋር ነው ? ወይስ ስር ከሆነው አስተሳሰባችን ጋር ነው?

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
ለማግኘት በምናደርገው ጥረት ውስጥ የማጣት ሥጋት፣ ዕረፍትን በመናፈቅ ውስጥ የሕመም ፍርሃት፣ ክብርን በመሻት ውስጥ የውድቀት ሥጋት፣ ሕይወትን በማፍቀር ውስጥ የሞት ፍርሃት፣ ድልን በመጠበቅ ውስጥ የሽንፈት ውጥረት በብርቱ ይታገለናል::

💎 ንቁ አእምሮ ያለው ሰው በራስ የመርካትም ሆነ ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ አይታይበትም:: የዘመኑን መርዶ አዘል ዜናዎች ቢሰማም ለመኖር ከሚያሳየው ጉጉትና ጥረት አይቦዝንም:: የሕይወትን አስቸጋሪ ገጽታዎች ቢጋፈጥም “አበቃልኝ” አይልም:: ይልቁንም የወደፊት ተስፋው በፈጣሪ አስተማማኝ እጆች ውስጥ ፍጻሜ እንዳለው ስለሚያውቅ እያንዳንዱን ዕለት በብልሃት በጭምትነትና በመታዘዝ ያሳልፋል:: አመለካከት የሕይወትን ስኬትና ውጤት ይወስናልና አስተሳሰባችን የቀና ከሆነ ስኬታማነታችንም የተረጋገጠ ነው::

💫 ማናኛችንም ብንሆን መታወክ የሌለበት ከፈተናና ከውጣ ውረድ የጸዳ መሻታችን ሁሉ የተሟላበት ኑሮ ቢኖረን እንፈልጋለን፣ ነገር ግን ሠው በመሆናችን ብቻ ደስታና ሃዘን፣ ማጣትና ማግኘት፣ መውደቅና መነሣት፣ ማመንና መከዳት እንዲሁም ውጣ-ውረድ የተሞላበት መሠናክል ይፈራረቁብናል፡፡ ዋናው ነገር በነዚህ ነገሮች ተፈትኖና ነጥሮ መውጣት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

ፈጣሪ ይህንን ድንቅ አዕምሮ ወይም ልዩ መክሊት ሲሠጠን በመጣው ወጀብ እንድንወሠድ ሳይሆን በጥበብና በዕውቀት ችግሮችን ፈትተን፣ ትምህርት ወስደን፣ እንደወርቅ በእሳት ተፈትነን በማስተዋል ነጥረን እንድንወጣ ነው፡፡

💎አስደሳች ፍጻሜ አጠብቅ ፣ህይወት ሁሌም ሁለትዮሽ ናት፣ መኖርን ምሉዕ የምናደርገው ሁለት ተቃራኒዎችን በሚዛን በመከወን ነው፡፡ እንባም ሳቅም፣ ደስታም ኀዘንም ፣ መስጠትም መቀበልም ፡፡  መሙላትም መጉደልም። ሲጠቃለል ፣ ሕይወት ኅብረ ቀለሟ ያማረ ቀስተ ደመና ነች።
ውብ ጊዜ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
📍አንዳንድ ወቅት አለ ስሜት የሚነዳ ፤ የሂወት ድግግሞሽ እንደጦስ ዶሮ የሚያዳክር፤  እጅ እና እግር እንደተጠፈረ  አቅም አልባነት የሚበላ ፤ አካባቢ ላይ ምን እንደተካሄደ የማይገባህ ።

አንዳንድ ወቅት አለ ማጤን ማመዛዘን ያንተ የማይሆንበት ፤ የመረጥከው ምርጫ የሚያድሞከሙክኽ።  መባተልን የምትመስልበት፤   የመጣህበት መንገድ አሳስቶህ የማትመለስበት ።

አንዳንድ ወቅት አለ ምርጫ የሚያባትልህ ፤   የመፍዘዝ ስሜት የሚሰማህ ፤   ሰው ሁሉ  የጠላኽ የሚመስልህ ፤  ኃላ  የመቅረት ስሜት የሚንጥህ ።

አንዳንድ ወቅት አለ  ማድረግ እንደሌለብህ እያወክ  የምታከናወነው ፤ የስሜትህ ባርያ የምትሆንበት ፤ መገኘት እንደሌለብህ እያወክህ የምትገኝበት  ።

እንዳንድ እለት አለ ብልጥ ነኝ ባዮች የሚበልጡ ፤ አራዳ ነኝ ባዮች የሚያሞኝህ፤ በዝባዦች የሚበዘብዙህ፤ ባለጡንቻዎች አቅማቸውን የሚለኩብህ

እንዲም ሁሉ ሆኖ ሳለ

በግዜ እናምናለን ። ግዜ ሃያል ነው ። ሁሉም ይስተካከላል፣ መስመር መስመር ይይዛል  ።አይነጋም ያልነው ጨለማ ስንቴ ነግቷል።

አድሃኖም ምትኩ

ውብ አዳር ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
     
2024/09/27 01:25:46
Back to Top
HTML Embed Code: