Telegram Web Link
❤️በዓለማችን ሰላም እንዲኖር በሃገራት መሃል ሰላም መኖር አለበት፤ በሃገራት መሃል ሰላም እንዲኖር በመንግስታት መሃል ሰላም መኖር አለበት፤ በሃገር ውስጥ ሰላም እንዲኖር በከተሞች ሰላም መኖር አለበት፤ በከተሞች ውስጥ ሰላም እንዲኖር በመንደሮች ውስጥ ሰላም መኖር አለበት፤ በመንደሮች ውስጥ ሰላም እንዲኖር በቤተሰብ መሃል ሰላም መኖር አለበት... የዚህ ሁሉ_ሰላም መነሻ ግን የኛው ልብ ነው።
- Lao Tzu ላኦ ትዙ

📍የግዙፍ ውቅያኖስ አካል ነን፣ እኛም ሆንን በዙሪያችን ያለው የተፈጥሮ ስንክሳር የውቅያኖሱ አንድ ጠብታ ነው፣ የሰላምህ እርግብግቢት የሰላማችንን ንፋስ ይጠቅሳል ፣ የሕመማችን ትንፋሽ የደስታህን መንፈስ ይበርዛል ፣ ምክንያቱም እኔም’፣ ‘አንተም’፣ ‘እርሷም’፣ ‘ሁላችንም' አንድ ነንና።

በ ዕውቀቱ በአንድ ድንቅ ግጥሙ ላይ እንዲህ ብሏል :-
ይችላል ይሉሃል ፍልሚያ ማዘጋጀት፣
ያባት አጥንት ወስዶ ስሎ ጦር ማበጀት፣
አንተው ጦር ወርውረህ አንተው ቀድመህ ወደቅህ፣
አካሌ ደረቴ መሆንህን መች አወቅህ?፣

♦️አንዳንዴ የሰላምን ዋጋ የምናውቀው ሰላም ማጣት የሚያስከፍለውን ዋጋ ስናይ ነው። የጤንነትን ዋጋ የምንረዳው ጤናን ማጣት ያለውን ጣጣ ስናጤን ነው። ካስተዋልን የሁሉም ነገር መነሻ የኛው ሰላም ነው.. ሰላማችንን ስንጠብቅ ሁሉም ጊዜውን ጠብቆ የኛ ይሆናል። ከሰላም በላይ ዋጋ ያለው ነገር በዓለማችን ላይ የለም።

ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💡ዜን ከህልም ዓለም ወጥተህ አሁን የምትኖርበትን ቅፅበት በሙሉ ንቃት
እንድትኖር የሚያለማምድ መንፈሳዊ አስተምህሮ ነው፡፡ እንደ ታዋቂው የዜን ማስተር Shunryu Suzuki አገላለጽ፣ “ዜንን ለመረዳት የዜንን መጽሐፍ በጥልቀት ማንበብ አይጠበቅብህም፡፡ማንኛውንም ጽሑፍ፣እያንዳንዷን ቃል እና አረፍተ ነገር በአዲስ እና በንፁህ አዕምሮ ማንበብ በቂ ነው፡፡”ይላል ሱዙኪ “አክሎም፣ “ይህንን ለማድረግ ከማይንድ መውጣት ያስፈልጋል፡፡

💡ከዜን እይታ አንጻር ሁሉም ነገር በውስጡ  እውነተኛ የአእምሮ  አስተሳሰብ አለው፣ይህም ነቅቶ መገኘትን፣ንፁህ ግንዛቤን እና ህሊናን ያቀፈ ተፈጥሮ ነው፡፡ ይህ ተፈጥሮ በመጀመሪያ ባዶ ፣የተረጋጋና ፀጥ ያለ  እና የማይለወጥ ማስተዋል ነው። የቁሳዊ እና የአዕምሮ ዓለማችን በተለዋወጭ ክስተቶች የተሞላ ነው። በእነዚህ ክስተቶች ላይ ራሳችንን ጥገኛ ስናደርግ ማንነታችንን በማደናቀፍ ጥላቻን እናዳብራለን። ከአስተሳሰብ ቅዥት ከእንቅልፋችን ስንነቃ ለእራሳችን የሰጠነውን የውሽት ግምት እናገኘዋለን፣  እውነተኛው ተፈጥሮአችንን ስናስተውል በተግባር እና ግንዛቤ አማካኝነት በዚህ ተፈጥሮ ልንጸና እንችላለን ፣በሰላም ከሁሉም ጋር መፍሰስ እንጀምራለን ፡፡

🌗 ዜን በቀጥታ ወደ ትክክለኛ የአዕምሮ ተፈጥሮው ይጠቁማል፣የእኛ ስብዕና እውነተኛ ተፈጥሮ ከሰው ልጆች ሁሉ እውነተኛ ተፈጥሮ ጋር አንድ መሆኑን በመረዳት ርህራሄ በውስጣችን እንዲሰርፅ ያደርጋል። እኛ የሚመለከተን ዛሬ የምንኖርበት ህይወት እንጂ ወደፊት ይኖራል ብለን የምንጠብቀው ዓለም  አይደለም። እያንዳንዱ ድልድይ ደርሰህበት መሻገር ስትጀምር ስለድልድዩ ታስባለህ ገና ያልደረስከበትን ግን በሩቁ ማሰብ ከንቱ ድካም ይሆናል።

         ውብ ቅዳሜ!❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@Ethiohumanitybot
🕰የሰው ልጅ ሕልውና ምድር ላይ ሀ ብሎ ሲጀምር ጊዜ አሀዱ ብሎ መቁጠር እንደጀመረ ይገመታል። ምክንያቱም ሰው ከመፈጠሩ በፊትና ከሞተ በኋላ ስላለው አያውቅም፣ስለዚህ ህልውና ሲጀምር ጊዜ ጀመረ ፣ጊዜ ማለት በእጅ ውስጥ ያለ ነው። ትናንት አልፏል። ነገም ደግሞ አያስተማምንም። ስለዚህ ጊዜ ዛሬ ነው። በተለይ ደግሞ አሁን ።

🌗ልማድ ብቻ ይዘን የትም ልንደርስ አንችልም፣ ባዶ ኩራት ይዘን እንቀራለን፣ ህልውናን መገመት ያለብን በስራ እንጂ በእድሜ: በሀሳብ እንጂ በትንፋሽ፡ በስሜት እንጅ በከንቱ የሚባክኑ ደቂቃዎች አይደለም ፣ ጊዜን የምናሰላው በልብ ትርታ መሆን አለበት።በስራ የማይገልጡትን ነገር በአፍ ብቻ መናገር ምላስን ማባለግ ነው።የባለገች ምላስ ህሊና ላይ ታምፃለች። እምነትና ድርጊት ከተለያዩ ምሰሶው በምስጥ እንደተበላ ቤት መዛግ ከዚያም መፍረስ ይመጣል ወና ቤት መሆን ነው።

💡ከተማራችሁት ወጣቶች የሚጠበቀው'ኮ ያገሪቷን ችግር በጥሞና አስተውላችሁ ዘላቂ መፍትሄ መሻት ነው፣ ለግልቢያውማ ማሀይምስ ብልጭ ካለበት ይጋልብ የለም እንዴ! ወደፊት ልንራመድ የምንችለው በወሬ በፍልስፍና በስራ በማይገለጥ የመፅሀፍ እውቀት አይደለም። ስርየታችን ስራ ነው፣ ስልጣን ይዞ በመኮፈስ ስልጣንን እንደ እውቀት በመቁጠር፣ ስልጣንን እንደ ሃላፊነት ሳይሆን እንደ መብት በማየት አይደለም በስራ እንደገና መወለድ ያስፈልጋል።

🔑 የኔ ጥሪ ስራ ነው። መናገር አላውቅም። ያ የጥሪ ሰዓት ሲደርስ በቆራጥነት መነሳቱ ሀጢያት አይደለም። ከማፍረስ መገንባት ፤ ከብዙ ምልልስ ትንሽ ስራን ፤ ከበቀል ይቅርታን ፤ከጥላቻ ፍቅርን ፤ ከማይምነት እውቀትን እመርጣለው።

በዓሉ ግርማ

ውብ አሁን❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@Ethiohumanitybot
📍ወዳጄ ሆይ መቆም ከፈለክ ሌሎችን አትጣል

💡የምትሔድበት የስኬት መንገድ ሺህ ጊዜ ይርዘም እንጂ ቶሎ ለመድረስ ብለህ አቋራጭ መንገድ አትጠቀም። ልብህ በእውነት ላይ ተረማምደው በሰዎች ትከሻ ላይ ተንጠልጥለው ፣ በአቋራጭ ባደጉ ሰዎች እንዳይቀና! የግፍንም እንጀራ እንዳትበላ ተጠንቀቅ ፣ትግስትን ገንዘብህ አድርጋት አምላክ ለአንተ ያዘጋጀዉ ነገር አለውና። በዕውነት ፣ በሃቅና በራስ አገዝ አዋጭ መንገድ ከተራማድክ እመነኝ በያንዳንዱ እርምጃህ ስኬትህን እየገነባህ ነው።

ሀሴትህ በቀናነትህ መጨምር ይበዛል፣ ከክፋት ትርፍ አይሰበሰብም፡፡ የምትሆነው ብታጣ እንኳ ጨካኝነትን ብቸኛው ምርጫህ አታድርግ፡፡ የሚመረጥ ስላጣህም የማይመረጥ አትምረጥ ፣ የምትመርጠው ከሌለ አለመምረጥም ጥሩ ምርጫ ነው፡፡ ማስተዋልህን ባለማስተዋል አትጠቀምበት፡፡

ወዳጄ ሆይ

ከብረህ ሳለም ቀለህ መኖርን አትውደድ፡፡ በከፍታ እንጂ በዝቅታ እያሰቡ መኖር አይመጥንህም ጭካኔ የሕሊና ሰላምህን ያቀነጭራል፡፡ የውስጥህንም ሰላም ያመክናል፡፡ጊዜአዊ እንጂ ዘላለማዊ የዚህች ምድር ነዋሪ አይደለህምና በደጉ ጊዜህ መሰልህን አትበድል፡፡

📍ነገ የአንተ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን በውል አታውቅምና ነግ በእኔ ማለትን እወቅ፡፡ በቁንጮነት ዘመንህ የፍጡራንን መብት አትግፈፍ፡፡ የሌላው ውድቀት የአንተን መቆም አያረጋግጥምና ፣ መከራ በታጨቀባት በዚህች ጠፊ ዓለም መልካምነትን የመሰለ ሰላም ሰጪ ተግባር የለም፡፡ በመሆኑም ዛሬህ ላይ ነገ የማትፀፀትበትን ምግባር አብዛ፡፡

ነፃ የሆነ ነፃነት እንዲሰማህ ፤ በጭንቀት የታጨቀ ኑሮህን በቅንነት ቀይር፡፡ ከሁካታ እርካታ አይመነጭም እፎይታ ለሚሰጡህ ተግባሮች ራስህን ስጥ፡፡
ሐዋዝ

ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity

@Ethiohumanitybot
❤️ከስሞች ሁሉ ምርጥ ስም  ከሰው ልጅ ከናፍራት ከወጡ ውብ ቃላት አንዱ " እናት" ነው ።

የጥሪዎች ሁሉ ምርጡ  ጥሪ " እማ" ቃላቱ በፍቅር , እና ተስፍ የተሞላ ነው ፣የምትጣፍጥ ቃል ከሰው ልጅ ጥልቅ ልብ የወጣች ናት።እናት ሁሉ ነገር ናት ፣ በችግር ሰአት አማካሪያችን ናት በጭንቀት ሰአት ተስፍችን ናት በድክመት ሰአት ጥንካሪያችን ናት እሷ እኮ የፍቅር , የእዝነት , የርህራሄ, ምንጭ ናት።

እናት እንደ መሬት ሁሉን ቻይ ናት። ብትረገጥ ታግሳ ለወግ ማረግ ታበቃለች። ብትነቀፍና ብትተችም ፈገግታዋ አይከስምም። የዘሩባትን መልካም አድርጋ እንደምታበቅል እርሻ ልበ ንፁሁ እንዲሁም መልካም ፍሬ እንደምታፈራ ዛፍ አብራኳ ለምለም የሆነ የውበት የምጨረሻዋ ምእራፍና የመጨረሻዋ እውነተኛ ዓረፍተ ነገር ነች እናት። ልቧ ከፍቅር ድርና ማግ የተሸመነ ነውና ምን ቢያስቀይሟት የጥላቻ ጥርስ አትነክስም። ፊት ቢነሷት ፊት አትነሳም ።

❤️ሰው የመሆን የመጨረሻው ደረጃ ነው። ቅድስና በእናትነት መንገድ የሚደረሰበት የህሊና ንቃት ነው። እናት  የፍጥረት ሁሉ የመጅመሪያ ምሳሌ ናት ሙሉ የሆነ ውበት እና ፍቅር ተምሳሌት ናት ከሁሉም በላይ እናት የሚተመንላት ዋጋ የላትም፡፡ ከዋጋ በላይ ናትና።

የእናት ፍቅር የመጨረሻዋ የፅድቅ ፅዋ ነች።

ውብ የእናቶች ቀንን ተመኘን❤️
                  
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቃል አልባው ቃል ኪዳን!

እውነተኛ ጓደኝነት ያስደምመኛል! እንደዛሬው ማህበራዊ ድረ ገፁ "ጓደኛ" የሚለውን ቃል ሳያልከሰክሰው በፊት ...ጓደኝነት ቀለል ተደርጎ የሚወሰድ ግን ደግሞ እጅግ ጥልቅ የሆነ የመንፈስ ትስስር ያለውን ግንኙነት መግለጫ ቃል ነበር! ጓደኝነት መሠረቱ ውበት አይደለም ፣ ጥቅም አይደለም፣ ወሲብ አይደለም፣ ማህላና ቃል ኪዳን አይደለም፣ ተስፋም አይደለም! ከፍቅረኝነት  በላይ የሚያስደምም ነገር አለው!

ጓደኞች በመካከላቸው ያለው ግንኙነት ንፁህ የነፍስ መዋደድ ብቻ ነው! አንዱ ለሌላኛው መቆም ነው! ላልከዳህ ላልከዳሽ የሚል ማህላ የለበትም! ከመሀላ የጠነከረ ያለመካካድ እና የእድሜ ልክ አብሮነት ግን በውስጡ አለ! ጓደኝነት ፆታ ፣ ባህል፣ እምነት፣ ርቀት የኑሮ ደረጃ አይወስነውም! አንዱ ለሌላው ህይወትን እስከመክፈል የሚደርስ ፍቅር በጓደኝነት ስሜት ውስጥ አለ!

ጓደኝነት ብዙ ያልተዘፈነለት፣ ብዙ ያልተገጠመለት ብዙ ያልተፃፈለት ብዙ ፊልም ያልተሰራለት ግን ደግሞ በህግ ያልታጠረ እውነተኛ ፍቅር የተሞላበት ስሜት ነው! ጓደኝነታችሁን አታፍርሱ! ቃል አልባ ቃልኪዳን ነውና ለጓደኞቻችሁ ሚስጥርና ሁለንተናዊ ደህንነት ታምናችሁ አብሮነታችሁን አጠንክሩ!

አሌክስ አብርሃም

ውብ አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@Ethiohumanitybot
💡ፀጥታህ በጩኸት መሃል ካሌለች፤ ሰላምህም በግርግር ካልተገኘች፤ ተመለስ አልደረስክም!

ሰማዩን ተመልከተው ፀሓዩዋን እያት፣ ዛፎቹን እያቸው። ነፋሱን አስተውል። በመንገድ የሚጓዙትን የሚተምሙትን መኪኖችና ሰዎች ልብ በል። ወፎቹን አዳምጥ። ሌሎች እንሰሳቶችንም ተመልከት። ምን ይሰማኃል?
ልክ እንደ ጨቅላ በሀሴት ተሞሽረህ ምናብህን ስታበረታ ሁሉም ነገር በቀና ይሄዳል፣ ሰከን በል! ተረጋጋ! አስተውል፣ ወደውስጥ ስትገባ አንተነትህ ሁሌም አዲስ ሆኖ የሚታደስ ድንቅ ፍጥረት ሆኖ ይታይሃል፡፡ የተፈጥሮ አካል አንድ ህዋስ ነህ፡፡

💎ወዳጄ ዓለም እና የሰው ልጅ ተፈጥሮ በብዙ ስንክሳር የተሞሉ ናቸው። ባሳለፍከው ህይወት ብዙ ክስተቶች ታይተዋል። የሚያሳዝንም የሚያስደስቱም ሁኔታዎች የህይወት ገጾች ናቸው። ሁሉ ይመጣል፣ ሁሉም ይሄዳል። ያለፈውና የሚሄደውን በሰላም ሸኘው። አሁን ካለው ጋር በሰላም ተከባብረህና ተሳስበህ ኑር። ታመን፣ እመንም። የሚመጣውን በልከኛ ተስፋ ተቀበለው። ዘልዓለማዊ ክስተት የለም፣ ለውጥ እንጂ።ባንተ ጭንቀት አንዲቷ ችግርህ አትፈታም፡፡ ባንተ ማስተዋል ግን የሁሉ ሰንሰለት ይበጠሳል፣ የራስህ ሳይሆን የብዙሃን ነፃ አውጪ ነህ፣ ከሁኔታዎች በላይ መሆንን እወቅበት። መረጋጋት መልካም ነው።

💡ይህ ሁሉ ሲሆን፣ ነገሮች ሲለዋወጡ ህይወትን በእርጋታ ማጣጣም የቻሉ ግን ጥቂቶች ናቸው። ህይወትን ለማጣጣም ሀብት የግድ አይደለም፣ ቢኖር ግን ጥሩ ነው፣ ግን በልክ። ህይወትን ለማጣጣም ዘመድና ጓደኛ ቢኖሩ ጥሩ ነው፣ግን በልክ። ህይወትን ለማጣጣም ጊዜ ማግኘት አስፈላጊ ነው። ጊዜህን መጠበቅና መቆጣጠርን እወቅበት።

ውብ አሁን❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@Ethiohumanitybot
❤️ትዳርና ኃላፊነት

ትዳር ፍቅር ብቻ አይደለም። ትዳር ኃላፊነትም ነው።

🔺በትዳር ውስጥ ብዙ የሚገመቱም የማይገመቱም ጉዳዮች ሊያጋጥሙ ይችላል። ያልጠበቃችሁት እና የሚያናድዳችሁ ጉዳይ ቢያጋጥማችሁ እንዴት ታስተናግዱታላችሁ? ትቆጣላችሁ? ትጣላላችሁ? ታግሳችሁ በዝምታ ታልፋላችሁ? በይቅርታ እና እርቅ ታልፋላችሁ? ወይንስ ወደ ፍቺ ትሄዳላችሁ?

በትንሽ በትልቁ ወደ ፍቺ የሚሮጡ ባለትዳሮች በመንፈስና በአስተሳሰብ ያልበለጸጉና ራስ ወዳዶች ናቸው። አንዳንዶች ተጋብተው አንድ ዓመት እንኳ ሳይቆዩ ወደ ፍቺ ይሄዳሉ። ይሄ ልዩነትን መሸከም አለመቻል ነው፣ አለመብሰል ነው። ልዩነትን ማስተናገድ ሳትችሉ ወደ ጋብቻ አትሩጡ።

🔺ትዳር ስትመሰርቱ ኃላፊነት ያለው አኗኗር ውስጥ መግባታችሁን አስቡ። ትዳር የራሳችሁን ፍላጎት ለሌላው ማስገዛት መሆኑን እወቁ። ትዳር በሌላ ሰው ቁጥጥር ስር ራስን ለማስገዛት መፍቀድ መሆኑን ተረዱ። ትዳር ውስጥ ስትገቡ ነጻነታችሁን በተወሰነ ደረጃ እንደምትተዉ እመኑ።

🔺ትዳር ውስጥ ልጆች ይመጣሉ። ልጆች በነጻነትና በደስታ እንዲያድጉ የራስን ስሜት መግዛትና እኔ ያልኩት ብቻ ይሁንልኝ ከማለት ራስን ማቀብ ያስፈልጋል፣ልጅ ወልዶ የራሱ ጉዳይ ብሎ በትኖ የሚሄድ ከእንሰሳም ያነሰ ሰብዕና ያለው ነው። ፍሬ ለማፍራት ስንዴዋ እንኳ ራሷ እንዴት እንደምትፈርስ አታዩምን? ታድያ ከስንዴ እንኳ ታንሳላችሁ?

ኃላፊነትን ለመቀበል ካልተዘጋጃችሁ ወደ ትዳር አትግቡ፣ ትዳርን ቸኩሎ ኃላፊነትን ለመሸከም ብቁ ሳይሆኑ መያዝ አይገባም። ትዳር የዕቃ ዕቃ ጨዋታ አይደለም። ትዳር የፉክክር ቤትም አይደለም ፣ ትዳር ራስን አሳልፎ መስጠት ቢጠይቅም፣ በጥበብ ከተያዘ ደግሞ ፈተናዎች ሁሉ ቀላል ናቸው።

♦️ትዳር በህይወት የሚከሰቱ ለውጦችን የማስተናገድ አቅም ይጠይቃል። ህመም፣ የኢኮኖሚ ችግር፣ እስር ጥጋብ፣ ውስልትና፣ ንዴት፣ ጦርነት፣ ግጭት፣ ሹመት፣ ማግኘት፣ ማጣት፣... ትዳርን ይፈትናሉ። ግን ላወቁበት፣ ለበሳሎችና ኃላፊነት ለሚሰማቸው ትዳር ለማፍረስ ምክንያት አይሆኑም።

ትዳር ለመያዝ ማናችንም የመጀመሪያም ይሁን የመጨረሻም ሰዎች አይደለንም። ትዳር ውስጥ ያለ አለመግባባትም ያለና የነበረ የሚኖርም ነው። እናንተ ያጋጠማችሁ በሌሎችም የደረሰ እንጂ አዲስ አለመሆኑን እወቁ። ቁም-ነገሩ ችግርን መፍታት እንጂ ችግርን ማውራት አለመሆኑን ተገንዘቡ። ችግርን ታግሳችሁ ፍቱ።

🔺ከትዳር በፊት ሁለት ዓይናችሁን፣ ከቻላችሁም ሦስተኛውን ከፍታችሁ በደንብ እዩ፣ ፈትሹ፣ በአእምሮ ተዘጋጁ፣ ለኃላፊነት ተዘጋጁ። ትዳር ውስጥ ከገባችሁ በኋላ ግን አንድ ዓይን ብቻ ይበቃችኋል። ትዳር ውስጥ ሁሉን ካልሰማሁ ሁሉን ካላወቅሁ አትበሉ። ሁሉን ማወቅ አይጠቅማችሁም።

🔺መጀመሪያ አይታችሁና አምናችሁ ለኃላፊነት ተዘጋጅታችሁ አግቡ። እንደተጋባችሁ ለመውለድ አትቸኩሉ። ምንም ምንም ምንም ቢሆን ግን ወልዳችሁ አትፋቱ፣ ከፀሓይ በታች አዲስ ነገር የለም! ወልዶ የሚፋታ ግለሰብ ፣ ቤተሰቡን ብቻ ሳይሆን አገር ያፈርሳል።

Getu k. Toughe

         ውብ ምሽት❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@Ethiohumanitybot
♦️ለመኖር የመጓጓታችንን ያህል መኖራችን ውስጥ የተሰጠንን ፀጋ ምን ያክል እናስተውላለን? ከውልደት እስከ ሞት የሚዘረጋው የስብዕናችን ተረክስ ሁነኛ ልኩ ምንድነው?

የህይወት ዳርቻ ስትደርስ ጨለማውን ታየዋለህ።  ተስፋ ካልተለየህ ጭላንጭሏ ላይ ታተኩራለህ። እሷ እንዳታመልጥህ ትታገላለህ።  ካመለጠችህ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ መውደቅህን ታውቃለህ ፣ ሰው አንዳንዴ የተስፋው ጭላንጭል ስትሟጠጥ እና የህይወቱ ገመድ ተገዝግዛ ልትበጠስ ስትደርስ የመጨረሻው ንቃት ላይ ይደርሳል፣ ታድያ በዚች ቅፅበት ጨለማውን የሚገፍ የተስፋ ብልጭታና እንደገና ጨብጦ የሚወጣበት የምርጫ ገመድ ሲያገኝ የሚፈጠረው ለውጥ አቻ አይኖረውም።

🔷ዛሬ ብንሞትስ ብለህ አስብ እስኪ
ለነገ ያሳደርካቸው ብዙ ሀሳቦች አብረውህ ይሞታሉ  ፣ ለነገ ያቆየሀቸው ስንት ግቦች መቃብር ይወርዳሉ  ፣ዛሬ ሳታወጣው የደበቅከው ተሰጥኦህ አብሮህ ይቀበራል ሳይፈነጥቁ የቆዩ ብዙ ተስፋዎች ይቀጫሉ ፣ ለሰዎች ያላሳየሃቸው ስንት ደግነቶች አፈር ይበላቸዋል ያልተነገሩ ስንት ይቅርታዎች ይሞታሉ ነገ እደሰታለሁ ብለህ ቀን ስትጠብቅ ቀኑ ይጨልምብሀል  ስለዚህ አስብ እየአንዳንዷን ቀን እንደ መጨረሻ ቀን ቁጠራት ማድረግ ያለብህን ዛሬ እያደረክ ተደሰት።

🔶መኖር ጥሩ ነው።  ሌላው ትርፍ ነው።አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' አይምሰልህ ፣ ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል። ለህይወትህ በይበልጥ ዋጋ የምትሰጠው ልክ የአንበሳ መንጋጋ ገብቶ በተአምር እንደ ተረፈ ነብይ ወይም ጻድቅ ነው። 

🔷ከክፉ በሽታና ከሞት ጥግ መመለስ ራሱ ጽድቅ ነው፣ የደረሰበት ብቻ ያውቀዋል፣  ያወቅክ የመሰለህ ያላወቅኸው ብዙ አለና። ዋናው ነገር ለተሰጠህ ለምታውቀውም ለማታውቀውም በረከት ፈጣሪህን አመስግን ፣ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት። ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!

              ውብ አሁን❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@Ethiohumanitybot
📍ፈጣሪ ለምን ፈጠረኝ ብለህ አስበህ ታውቃለህ?

እኛ የሰው ልጆች ፈጣሪ ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ አናውቅም!! እሱ በጣም ድንቅ አንጎል እና ስሜት ያለበት አፍቃሪ ልብ ሰጥቶናል፣ለመናገር እና ስሜታችንን ለመግለጽ በሁለት ከንፈሮች ባርኮናል፣ ውበትን የሚያዩ ሁለት ዓይኖች፣ በሕይወት መንገድ ላይ የሚራመዱ ሁለት እግሮች፣ ለእኛ ሁለት የሚሠሩ እጆች፣ እና የፍቅር ቃላቶች የሚሰሙ ሁለት ጆሮችን ሰጥቶናል።

ፈጣሪ ሰውን ሲፈጥር የራሱን ትክክለኛ ባህሪ እንዲላበስ ነው ፤ የፈጣሪ ባህሪ ርህራሄ ቸርነት ፣ ይቅርታ ፣ ፍቅር እና ደስታ ናቸው። እኛም እሱ እንደፈጠርን ሰው ሆነን መኖር ይገባናል።

♦️ሰው ሁኖ መኖር ማለት፦ ከራስ አልፎ ለሌሎችም ማሰብ መቻል ነው፡፡ ሰው ሁኖ መኖር ማለት ሰውን መግደልና መግፋት ሳይሆን ማዳንና መደገፍ ፣ ማበረታታትና ማረጋጋት ነው፡፡ ሰዎችን ገንዘብንና ስልጣንን ፣ ጉልበትንና ጊዜን ተጠቅመው መከራ የሚያሳዩ ሰዎች ሰው ሁነው ተፈጥረው ዳሩ ግን ሰው ሁነው መኖር ያልቻሉ ወገኖች ናቸው፡፡

♦️ሰው ያለሰው ፤ ሰው ያለዙሪያው ህይወትን ሙሉ በሙሉ ሊኖራት አይችልም። ሰው ስንል ግዴታ በአንድ ጣሪያ ስር የሚኖርን ወዳጅ አይደለም፤ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ እንጂ። እኛ ከአለም ውጪ አለም ከእኛ ውጪ አንደኛችም መኖራችን አይረጋገጥም ። ለሰው ማሰብ አለመቻል ኅሊና ማጣት ነው፡፡ አንተ ያስፈለገኽና የሚያስፈልግኽ ለሌሎች የማያስፈልጋቸው የሚመስልህ ከሆነ ራስህን ፈትሽ።

ሰው አድርጎ መፍጠር የፈጣሪህ ድርሻ ሲሆን ሰው ሁኖ መኖር ግን ያንተ ድርሻ ነው፣ ማንነትን የመርሳት መድሀኒቱ ፈጣሪ ስለሆነ በምንችለው መንገድ ሁሉ ወደእርሱ በመቅረብ ማንነትን ከመርሳት በሽታ እንፈወስ!

ውብ አዳር ❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@Ethiohumanitybot
💔 ወርቃማው ጥገና!

በጃፓን ሃገር ውስጥ ለብዙ መቶ አመታት የከረመ ልምምድ አለ፡፡ ጃፓኖች አንድ ከሸክላ የተሰራ እቃ ሲሰበርባቸው እንደገና የመጠገኑን ስራ “ኪንሱጊ” (Kintsugi) ብለው ይጠሩታል፡፡

ይህ ቃል የሁለት የጃፓንኛ ቃላት ጥምረት ነው፡ “ኪን” (Kin) ማለት ወርቃማ ማለት ሲሆን፣ “ሱጊ”(Tsugi) ማለት ደግሞ ጥገና ማለት ነው፡፡ የእነዚህ ሁለት ቃላት ጥምረት የሚሰጣቸው ይህ “ኪንሱጊ” (Kintsugi) የተሰኘ አንድ ቃል ትርጉም አንድ ነገር ከተሰበረ በኋላ እንደገና በወርቅ መጠገንን የሚያመለክት ነው - ወርቃማ ጥገና!

ከዚህ ልምምዳቸው የተነሳ አንድ የተሰበረ የሸክላ እቃ እንደገና ሲጠገን ይህ የጥገና ሂደቱ በእቃው ታሪክ ውስጥ ትልቁን ስፍራ ይይዛል፡፡ እቃው በመሰበሩ የተነሳ እንደገና ሲጠገን በሶስት መልኩ የላቀ ሆኖ ይወጣል፡- 1) ጥንካሬው ይጨምራል 2) ዋጋው ይጨምራል፣ 3) ውበቱ ይጨምራል፡፡

በሕይወታችሁ ልባችሁን ሰብሮና ስሜታችሁን አቁስሎ የነበረ ያለፈ ልምምድ ካለ፣ አሁንም ተመሳሳይ ልምምድ ውስጥ በማለፍ ላይ ካላችሁና ወደፊትም በሚሰብር ልምምድ ውስጥ ስታልፉ ይህንን የጃፓኖችን የጥገና ሂደት አትዘንጉ፡፡ በሁኔታው ተስፋ በመቁረጥና ተሰብራችሁ ለመቅረት ራሳችሁን ካልጣላችሁ በስተቀር እንደገና ትጠገናላችሁ፡፡ ከተጠገናችሁ በኋላ ግን ከበፊቱ ይልቅ ጠንካራ ሰዎች፣ ዋጋችሁ የከበረና ከበፊቱ ይልቅ እጅግ ውብ ሆናችሁ ነው የምትወጡት፡፡

ሆኖም፣ ጥገና ጊዜን እንደሚፈልግ አትዘንጉ፡፡ ጥገና ያለፈውን ረስቶ ፈጣሪን በመታመን ወደፊት የመገስገስን ቆራጥነትም እንደሚፈልግ አትርሱ፡፡

Beauty can be found in imperfection.

ዶ/ር እዮብ ማሞ

ውብ አዳር ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔱 እርግጠኛ ነሽ አርግዘሻል?

ዝሆን እና ውሻ በተመሳሳይ ጊዜ ፀነሱ፡፡ ከሶስት ወራቶች በኋላ ውሻዋ ስድስት ቡችላዎችን ወለደች፡፡ ዝሆኗ እንዳረገዘች ከስድስት ወር በኋላ ውሻዋ እንደገና ፀነሰች ፣ ዘጠኝ ወር ደግሞ ሌሎች ብዙ ቡችሎች ወለደች፡፡ የእርግዝና ስርዓቱ ቀጠለ ፡፡ ውሻዋ በየሦስት ወሩ መውለዷን ቀጠለች።

በአሥራ ስምንተኛው ወር ውሻዋ ወደ ዝሆኗ ጥያቄ ይዛ ቀረበች ፣

“እርግጠኛ ነሽ ነፍሰ ጡር ነሽ? አሁን በሆድሽ ጽንስ አለ? ምክንያቱም በተመሳሳይ ቀን ነፍሰ ጡር ሆነናል ብለን ነበር፣ ከ16 በላይ ቡችሎች ወለድኩኝ እና አሁን ግማሾቹ በዚህ ሰዓት አድገው ትልቅ ውሾች ሆነዋል ፣ ግን አንቺ አሁንም ነፍሰ ጡር ነኝ ትያለሽ፡፡ ምን እየሆነ ነው?

ዝሆኗም “እኔ እንድትረጂ የምፈልገው አንድ ነገር አለ፣ በማህጸኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነው ፡፡ እኔ በሁለት ዓመት ውስጥ አንዱን ብቻ እወልዳለሁ፡፡ የምወልደው ግን ተራ እንስሳ ስላልሆነ ልጄ መሬቱን ሲመታ ምድር ይሰማታል፡፡ ልጄ መንገዱን አቋርጦ ሲሻገር የሰው ልጅ ቆሞ እያደንቀው ይመለከታል ፣ እርሱ ሲንቀሳቀስ ሁሉም ይንቀጠቀጣል፣ የኔ ልጅ የፍጥረትን ትኩረትን ይስባል ፡፡

ሌሎች እንደ መቅስፈት በሚመስል ጊዜ ነገራቸው ሲቀየርና የተሳካላቸው ሲመስልህ በነሱ አትቅና፣ እምነትህም አይጥፋ በፍጹምም ተስፋ አትቁረጥ፣ ምክንያቱም የአንተም ጽንስ የሚወለድበት ጊዜ ይመጣል፣ ምንም ጊዜ ወስዶ የማይመጣ ቢመስልም የተሻለው መምጣቱ የማይቀር ነው፣ እናም ሲመጣ ሰዎችን ሁሉ የሚያነጋግርና የሚያስደንቅ ይሆናል! የዘገየው የተሻለ ስለሆነ ነውና የራስህን ጉዞ ከሌላ ከማንኛውም ሰው ጋር አታነፃፅር !

ውብ የስኬት ጊዜ❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@Ethiohumanitybot
SHEGER SHELF JULY 31_154591_Default_1545919870.mp3
ስብዕናችን {@ABYSINIA}
❤️እኛ ኢትዮጵያውያን

🔶ኢትዮጵያዊያን የሰው ክብረቱ ስራ እና አእምሮ መሆኑን ገና አላወቅንም። ሰርዐት የሌለው ህዝብ የደለደለ ሀይል የሌውም። ምግባር የሚባለውን ነገር በአፍ ካልሆነ በቀር በተግባር አናውቀውም። የተማርነው ነገር ቢኖር በአደባባይ ሰው መስሎ መታየትን ነው፤ በአደባባይ የምናጠልቀው ጭንብል ይህ ነው።  የግብዝነት ጭንብል አጥልቀን ነው የምንኖረው።

ያለ ጭንብል እናስቀይማለን... ወይም እናምራለን፤ አይታወቅም። ያለ ጭንብል ታይተን አናውቅማ!
                     በዓሉ ግርማ

🔷 ያለፈው ታሪክ የድሮውም የአሁኑም ኑሮዋችን እጅግ ያሳዝናል። በመላው አለም ላይ ሰላም ሲሰፋ አእምሮም ሲበረታ እኛ በጨለማ እንኖራለን። እርስ በእርሳችን መጠራጠርን አልተውነም። ህዝቦች ሁሉ እርስ በርሳቸው በፍቅር ተቃቅፈው ስለ ልማታቸው ሲደክሙ እኛ አንድ ዘርና ወንድማማች መሆናችን ገና አልተገለፀልንም። እርስ በርሳችን መፋጀት እስከ ዛሬ ጀግንነት ይመስለናል።

♦️ዘወትርም በስምምና በፍቅር አድረን ብንሆን እስከ ዛሬ ድረስ ብዙውን ትልልቅ ነገር መፈፀም እንችል እንደነበር ጥርጥር የለውም። ፈጣሪ ብዙ በረከት ሰጥቶናል ፣ ካለመስማማታችን የተነሳ ግን ሌሎች ህዝቦች በአእምሮና በጥበብ እየበረቱ ሲሄዱ እኛ ወደ ኋላ ቀረን። እንደ አረመኖች እስኪቆጥሩን ድረስ።

♦️ምነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእንቅልፍህ መቸ ትነሳለህ? በአለም ላይ የሚደረገውን ነገር ለማየትስ ዓይንህን መቸ ትከፍታለህ? ለውጥንስ መቸ ትናፍቃለህ?

ነጋድራስ ገ/ሕይወት ባይከዳኝ

      ውብ አዳር ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
🔴 ሕይወት በሚታይና በማይታይ ማዕበል የተከበበች ናት!

ሰው ሃሳቡ በግንባሩ ላይ ቢጻፍ ማን ማንን ቀና ብሎ ያያል? ደግነቱ በውስጣችን ያለውን ማንም አያውቅብንም። የምናስበውን አስበን፤ የፈለግነውን አሳውቀን የምንደብቀውን ደብቀን የመኖር ጥበቡ ለሰው ልጅ ብቻ የተሰጠ ጥበብ ነው። ልብ በሃዘን ደምቶ ፊት በፈገግታ ሲፈካ ፤ ግንባር ኮስተር ብሎ ልብ በሃሴት ሲሞላ ፤ ጉልበት ተንበርክኮ ልብ በትዕቢት ሲቆም ፤ አፍ እንደ ማር ጣፍጦ ልብ እንደ እሬት ሲመር ፤ ማን ማንን ያውቃል ያሰኛል?!

የሰው ልጅ በሚታየውና እና በማይታየው ማዕበል ውስጥ ያልፋል፤ የሚታየው ማዕበል ሌሎች የሚረዱት እና የሚያዩት ችግራችን ሲሆን፤ የማይታየው ማዕበል ደግሞ ከሌሎች ደብቀን ለብቻችን የምንጋፈጠው ችግር ነው”።

ሌሎች የማውቁት ምን አይነት ጭንቀት ይሆን እያንዳንዳችን በውስጣችን ያለው? ምን አይነት የማይታይ ማዕበል እየተጋፈጥን ይሆን?

🔷አዎ በሰው ፊት እንስቃለን ለብቻችን ግን እንባችንን በገዛ መዳፋችን ያለማቋረጥ እናብሳለን። ከሰው መሃል ደምቀን ለብቻችን ስንሆን መግቢያ እናጣለን። ከህዝብ ፊት ከብረን በቤታችን ግን የሰው ያህል የሚቆጥረን የለም። ጠንካራ መስለን፤ ልባችንን ግን በክህደት ስብርብሩ ወጥቷል። ከላይ ሰላም የሰፈነብን እንመስላለን፤ ውስጣችን ግን በተስፋ መቁረጥ ማዕበል ይተራመሳል። ከውጪ ሲታይ ቤታችን የደመቀ ቢመስልም ውስጡ ግን እንደ ዋሻ ቀዝቅዟል። ተለቀም አነሰም ሁላችንም ለሌሎች የማይታይ ለብቻችን የምንጋፈጠው ማዕበል አለን።

🔵እናም በየመንገዳችን ስንተላለፍ ልብ እንበል፤ ሌላው ከኛ ያነሰ ትግል የሚታገል እየመሰለን ፊት አንንሳው፤ እየረገጥን አንለፈው። የኔ ችግር እና ጭንቀት ከሌላው ይበልጣል የሚል አስተሳሰብ ሲኖረን ለሌሎች የምንዘረጋው እጅ ያጥረናል። ትኩረታችን ሁሉ የራሳችን ችግር ላይ ሲሆን ይበልጥ እናማርራለን፤ ሌሎች ለብቻቸው የሚገፈጡትን ማዕበል ስለማናይ “ምነው እኔን ብቻ” እያለን የሃዘናችንን ጉድጓድ ይበልጥ ወደታች እንቆፍረዋለን።

♦️ከትዳር አጋራችን ጋር ክንድ ተንተርሰን እያደርን፤ እርስ በርሳችን የምንፋለመውን ትግል አናውቅም። ለዚህ ነው ጭቅጭቅ ሲነሳ መሸናነፍ እና እርቅ ማውረድ የሚከብደን፤ ማን የማንን ማዕበል ያያልና? እናም በየመንገዳችን የሚያጋጥሙን ሰዎች ሁሉ የራሳቸው የሆነ ታሪክ አላቸው፤ በጫማቸው ሳንቆም አንፍረድ። በደቂቃ ውስጥ ያየነውን ምግባራቸውን ተንተርሰን አንፍረድ።

🔴ሌላውም እንደኔ ስሜት አለው የሚል አስተሳስብ መያዝ ስንጀምር፤ የሌላው ህመም ይሰማናል እናም ብዙ ስህተቶችን ከመፈጸም እንድናለን። ምናልባት ለብቻሽ/ ለብቻህ የምትጋፈጠው ማዕበል ካለህ በርታ… አጋዥ የለኝም ብለህ አትስጋ ፈጣሪ የማትችለውን ችግር አይሰጥህም። አንተ/አንቺ ብቻ ከሰው የተለየ መከራ አልተሰጠሽም/አልተሰጠህም እንደየአቅማችን ለሁላችንም የታደለን ነው እንጂ……ከምንም በላይ ግን እርስ በርሳችን እንተጋገዝ፤ እየተገፈታተርን መተላለፉን እናቆም ምክንያቱም ሁላችንም ለየብቻችን በምንጋፈጠው ማዕበል ደክመናልና።

                      ሚስጢረ አደራው

            ውብ አሁን ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
📍ወዳጄ ሆይ

ብሩህና መልካም ነገር አስብና! ተነስ
ወደፊት ስለሚሆነው አትጨነቅ ሁሉንም ነገር እንደ ችግር አትመልከት። በራስህ ችግር አትፈጠር። እያንዳንዱ ፈተና ታርሞ ውጤት እንደሚሰጠው ሀሉ ያንተም ችግር እንደተጋፈጥቀው መጠን ለስኬትህ ግብአት እንደሆነ አስብ፣ ስኬት የተለያዩ ደረጃዎች እንዳሉት እወቅ።

📍የስኬት መጨረሻ የውድቀት መጀመሪያ እንደሌለ እወቅ ፣ ስኬት በተገኘ ነገር ላይ በመርካት እንደሚለካ አስብ። ስኬትን ከአእምሮ እርካታ ጋር እንጂ ከቁስ ጋጋታ ጋር አታዛመድ፣ የሰው ልጅ እራሱን ሊያስደስት የሚችለው በመልካም ባህሪውና በሚሰራው ጥሩ ሥራ እንጂ የሚያምር መልክና አቋም ወይንም በርካታ ሀብት ስላለው አይደለም ... የሚያምር አቋምህና ሀብትህ ምድር ላይ ቀሪ ናቸው ..መልካም ስራህ ግን ለነገ ስንቅ ይሆንሐል ! ባለህበት የህይወት ደረጃ መርካት ከቻልክ በራሱ ስኬት እንደሆነ እወቅ።

እናም ወዳጄ

🔑 ሰውን ለመርዳት ጥግ አትያዝ እራስህን ሆነህ ደግ ስራ። በዚህ ምድር ትልቁ ነገር ሰው ሁኖ መፈጠር ሳይሆን ሰው ሆኖ መገኘት ነው ፣ ባለህ ነገር ተደሰት ፣ ተጨማሪ ቁሰ የአኗኗር አማራጭ እንጂ የህይወት ግዴታ እንዳልሆነ እወቅ። ማግኘት የምትችለውን ቁስ እንጂ አንተን የሚፈጥርህ ቁስ ለማግኘት አትጨነቅ ፣  እጅና እግሮችህ ሀብት እንደሆኑ እወቅ ፣ ህልውናህ ብቻውን ስኬት እንደሆነም ላፍታ አትዘንጋ፣ ሁሉም ነገር ሚሆነው አንተ ስትኖር ነው፣ ስለዚም በህይወት ሳለህ ወሳኝ" እና "ጠቃሚ" ሰው ሁነህ ተገኝ ሰዎችን እርዳ። መልካም ሰው መሆን በተግባር  እንጂ በትንታኔ ወይም በምላስ አይገለፅምና ፣በምትኖረው ህይወት ቁም-ነገር ያለው ጥሩ ነገር ሰርተህ እለፍ።

            ውብ ጊዜ ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
💎 ለመቶ ሚሊየን ሰው 1 ፀሀይ ነው የምትወጣው እንጂ ለሁሉም የተለያየ ፀሀይ አይወጣም፡፡ ፀሀይ ስራዋ መውጣት ነው መሞቅ ያንተ ፋንታ ነው፡፡ አዲሷ ፀሀይ አዲስ እድል አዲስ ተስፋ አዲስ ስኬት ይዛ በማለዳው ህይወትህን ልታሞቀው ስትወጣ አንተ ዛሬም በትላንት መጥፎ ታሪክህ በእንባ ጥላ ተጠልለህ ትደበቃታለህ፡፡ ሳታሞቅህ ዜናዋን ሳታበስርህ ትገባለች፡፡

💡ተፈጥሮ ሁሌም ለሁሉም እኩል ናት ፡፡ ለሁሉም አንድ ፀሀይ ነው የሚወጣው ዛሬም በፍቅር ከመኝታህ ተነስ የዛሬዋን ፀሀይ በተስፋ ሙቃት አትደበቃት ከውድቀትህ እንቅልፍ እራስህን ቀስቅስ፣ብርሃን የድምቀት መገለጫ ነው ፣ደማቅ ቀን በብርሃን ውስጥ ደግሞ ደጋግሞ ያበራል። የሚሰጠህ ውስጣዊ ስሜት በፈጠርከው ብሩህ ቀን ይወሰናል ተግባር የእምነት ፍሬ ናትና ።

💎 ወዳጄ ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰው ጊዜው ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለውን ሊሰጥህ ይሆናል። ስኬትህ የመንገድህ ጥግ ላይ ነው፣ ከምታስበው በላይ ቀርብ ነህ፣ ትንሽ መዘግየቱ የሚመጣው ነገር ስለሚበልጥ ነው፣ ትንሽ ታገስህ መንገድህን ቀጥል ፣ ድልህ ቅርብ ይሆናል።

💡አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ ታገሰህ ተራመድ ፤ የህይወትህ ፀሀይ መውጣቷ አይቀርም! ከጨለማው ምሽት በኋላ ሁል ጊዜ ፀሀይ ትወጣለች፣ አንተም በውስጥህ ያለውን ጥንካሬ ሰብስበህ ቀጥል።

ውብ ቅዳሜ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ወገኖቻችን በሙሉ እንኳን ለ1444'ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ!❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
2024/11/15 17:38:07
Back to Top
HTML Embed Code: