Telegram Web Link
     ወዳጄ ሆይ

🔷ያለፈ ነገር አይቀዪርም ፣ ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው ፣ ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር ፣ ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነትአይገልፅም ፣ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው ፣ መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና ለሁሉም ጊዜ አለው ።

📍 በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው ።በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ ፣ ክፉ አትመኝ ፣ በሃዘናቸውም አብረህ እዘን ሲያዝኑ አትደሰት ፣ ሰው ከሆንክ የሰው ነገር ይሰማህ ፣ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ተደሰት ማለት አይደለም ። ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋሁን ፣ አስተውል ።

♦️ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም አንተም ጊዜው ይቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት ፣በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን ። የስራ ጉዳይ ውስጥህ የሚችለውናየሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ ? ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ ? አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁ ፤አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለችም እየኖረች ያለችው፣ በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት ፤ አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ አውጣው ፣ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው ፣ "ምን ይሻለኛል ?" እያልክ አታመንታ ጊዜህ እንዳያልቅ ፣በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው ።

🔷አስተውል ፣ መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን አይደለም ፣ ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀዪር ብቃት አለው ። ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል ፣አስተውል ። መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው ፣ መጥፎነት ከአንተ ይራቅ ፣ ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም ።

♦️የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል ፣ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል ። "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን አስታውስ ፣
ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ራስህን አትሸውድ ። ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ ። ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።

ወዳጄ ሆይ!

♦️ለራስህ ስትል መልካም ሁን ፣ በጎውንም አስብ። ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም። ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም ። አትፍረድ ፣ የመፍረድ ሃላፊነት በፍፁም የለህም ። ፍርድ የፈጣሪ ነው፣ ለመፍረድ እንከን አልባ መሆን ያስፈልጋል ፣ ፍጥረት ሁሉ ፍጥረት በመሆኑ ብቻ እንከን አለበት ፣ ጎደሎ አለበት ። የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ ዝም በል ።

📍ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣አበረታታው፣እንደማይጠቅም አትንገረው ፣ ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን ። መልካም ጓደኛ ከፈጣሪ የሚሰጥ ጸጋ ነው ። መልካም ጓደኛ ፣ የማይቀና አሳቢና መካሪ ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ተባርከሃል ታድለሃል ። ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ።

♦️ያለ መጠን ማሰብ ጭንቀትን ፣ ሀዘንን ያስከትላል ።ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ ፣መመለስ በማትችለው ነገር ላይ አትወጠር ፣ የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ። አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄወች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ ።

🔷ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር ።ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው ፣ "ያስከፍላል"ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ። ደግ ሁኑ ፣ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም ፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ በረከታቸው ሰላማቸው ልክ የለውም።

📘ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ ፣ ያ ነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ ሲርቅ ወይም
ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል ። ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ ናቸው ። በራስህ በአፈጣጠርህ ደስ ይበልህ ፣ውለህ በመግባትህ ደስ ይበልህ ። በአለህ ትንሽ ነገር ደስ ይበልህ ።

♦️ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ ። በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም።  እድሜህን በተመለከተ ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው ። ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳዪኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው።

📍የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ’ረስተን ፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው ፣ ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል ። በማማረር መባረክ የለም ።

              ሰላምና ጤና ፣
ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለዪ።

            ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
💡ውሎህ የት ነው?

📍ሕይወት ሥነ ምህዳር ነው። የሰጠኸው ነገር ተመልሶ ይመጣል።የዘራውን ታጭዳለህ የምትሰጠውን ታገኛለህ በሌሎች ውስጥ የምታየውን በአንተ ውስጥ ታገኘዋለህ ፡፡ ሕይወት ሁሌ የሰጠሀትን መልሳ ትሰጠሀለች መልካም አድርግ መልካም ታገኛለህ እንደሚባለው ሁሉ።

ውሎህ አንተን ይገልፃል መልካም ቦታ ከተገኘህ በመልካም ይገለፃል በመጥፎ ቦታ ከዋልክ እንዲሁ ይሄንን የሚገልፅ ልናስተውለው የሚገባ አንድ ተረት አለ እንዲህ ይላል:-

🐝አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት
ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ ? ቤታቸው
ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል።
የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ያረፍኩበትን ቦታ
ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል::

አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል ደግሞም
መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ንብን
ጥያቄዋን አቀረበች
በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ አለቻት
ውሎሽ የት ነው?

📍ሰው ጠላን፣ ገፋን፣ ናቀን እያልን እንደ ዝንቧ ጥያቄን አዝለን ከምንጓዝ ውሏችንን በደንብ እንይ ወሏችን ተመልሶ እኛነታችንን ይገልፃል ውድቀታችንን ለማረምም ይሁን ብርታታችንን ለማብዛት ውሏችንን እንቃኝ ሀሳባችን ስራችንን፣ ስራችን ውጤታችንን፣ውጤታችን እኛነታችንን ይገልጽልናልና። የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለችና፣ራስን መፈተሽ መልካምም ነውና ወሎችን የት ነው?

   ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity
     
@EthioHumanitybot
💡ገበሬዉ ሁለቱን አህያዎች አንደኛዉን ጨዉ አንደኛዉን ባዶ በርሜል ጭኖ እየሄደ ነዉ።
ወገቡ ሊቆረጥ ደርሶ የሚንገዳገደዉ የጨዉ ኩንታሎችን የተሸከመዉ አህያ: ባዶ በርሜል የያዘዉ አህያ በፍጥነት ሲጓዝ ሲመለከት ጊዜ ከችግሩ ለመዉጣት አንድ ነገር ለማድረግ
ወሰነ።

💡 "ወንዝ አካባቢ ሲደርሱ ዉሃ ዉስጥ በመዉደቅ ሸክሙን ማቃለል!" ከጥቂት ጉዞ በኋላ ወንዝ ጋር ደረሱና ጨዉን የተሸከመዉ አህያ እንዳቀደዉ አደረገ። እቅዱ ተሳክቶለትም ዉሃዉ በኩንታሉ ዉስጥ ያለዉን ጨዉ በከፊል አጥቦ ወሰደዉ፣ከቆይታ በኋላ ከወደቀበት ሲነሳ ከገመተዉ በላይ ሸክሙ ቀለለዉ። እንደ ጓደኛዉም ዘና ብሎ በፍጥነት መሄድ ቻለ።

📍ይህን የተመለከተዉ በርሜል ተሸካሚ አህያ ከመጀመሪያዉ የበለጠ እንዲቀለዉ በመሻት ልክ እንደጓደኛዉ ዉሃ ዉስጥ ተዘፈቀ።ግና ከቆይታዎች በኋላ ሲነሳ ወገብ ዛላዉ ሊቆረጥ ምንም አልቀረዉም።ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ በርሜሎቹ በዉሃ ተሞልተዉ ስለነበር የጉዞዉ እጣ-ፈንታ በብርክ፣ምጥና እንፉቅቅታ ወድቆ እየተነሳ መኳተን ሆነ።

💡ሌላዉ የጠቀመዉና የለወጠዉ የህይወት መንገድ እኛን ላይጠቅመን ይልቁንስ ሊጎዳን ይችላልና የሌላን ሰዉ እርምጃ ከመከተላችን በፊት ምክንያትና ዉጤቱን ማመዛዘን ይገባናል! ማንኛዉም ችግር ሲገጥመን ማንኛዉንም እርምጃ ከመዉሰዳችን በፊት አዕምሯችንን ማሰራትና ቆም ብለን ማሰላሰል ካልቻልን ለነጻነት ያሰብነዉ መንገድ የባሰ ጭንቅና መከራን ሊያመጣብን ይችላል!

📍በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል እንዲሉ እኛ ዘንድ ያለዉን ጸጋ ማየት ተስኖን ዓይናችን የባተለበትን ሩቅ ማለም የነበረንን ሊያሳጣን ይችላልና ማመስገንን እልመድ! ጭፍን ተከታይነት ለራስም ሆነ ለሌላዉም እዳ እንጂ ትርፍ የለዉም!

ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
💡መንቃት ህይወት ነው!

የነቁት ሰዎች ለመኖር የተለየ ትርጉም አላቸው፡፡ ትርጉማቸው ንቃትን የያዘ ነው:፣ እየተነፈሳችሁ ስለሆነ እየኖራችሁ  ነው ማለት አይደለም ፤ደማችሁ እየተዘዋወረ ስለሆነ እየኖራችሁ ነው ማለት አይደለም። በህይወት የምትኖሩት የነቃችሁ ከሆናችሁ እንደሆነ ነው::

💡ዝም ብለህ ራስህን በተመስጦ ስታነብ ውስጠትህ ረጥቦ ሕይወትህ ይለመልማል፣ ምስጠት ማለት መታዘብ ነው፣ ይቺን ሀሳብ በቀላሉ የምታስረዳ አንድ ምሳሌ አለች። የኩሬ ውሃ ጭቃ ሞልቶት ቢደፈርስ እየነካካን አናጠራውም፣ በነካካነው ቁጥር ይበልጥ እየደፈረሰ ነው የሚመጣው። መፍትሔው ኩሬውን አለመንካት ነው፤ መፍትሔው ኩሬው ዳር ተቀምጦ የተፈጥሮን ትንግርት ማስተዋል ነው። ኩሬው ለራሱ ሲተው እየጠራ ፣ እየጠራ ይመጣና ኩልል ያለ ንፁህ፣ የተጣራ ውሃ ይሆናል።

❤️አእምሯችን እንደ ተንጣለለው ኩሬ በሃሳብ ጭቃ ደፍርሷል።ኩሬውን እየነካካን እንደማናጠራው ሁሉ አእምሮንም በሃሳብ ጉልበት መግራት አይቻልም። ኩሬው ራሱ በራሱ እንዲጠራ እንደምንተወው ሁሉ፣ አእምሮም ንቃት ላይ እንዲደርስ፣ ከሃሳብ ግርግር አሳርፎ ለራሱ ምትሃታዊ አርምሞ መተው አለበት። በጥልቅ አሰላሳዩም ተፈጥሮ በአእምሮ ላይ የራሱን ተአምር ሲሰራ በዝምታ ተውጦ ያስተውላል። በጥልቅ ማሰላሰል ሌላ ምንም ውስብስብ ነገር የለውም፣ በአጭሩ ከሃሳብ ነፃ ሆኖ ወደ መሆን ማእቀፍ [Consciousness] መሸጋገር ነው።

💡እናም የተረጋጋ ታዛቢ አመለካከት ይኑራችሁ ፣ በመመሰጥ ነፃነትን እና ደስታን ታገኛላችሁ። ንቁ፣ አንፀባርቁ ፣ ተመልከቱ ነገሮችን በእርጋታ ከውኑ በመንገዱ ውስጥ ኑሩ ፣ውስጣዊ ብርሃናችሁ በራሱ ጊዜ ያድጋል፡፡

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
አንዳንዴ ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ ስለምንሻ ነገሮች እንዳሰብናቸው ካልሆኑ ደስታችንን ያጎድሉብናል። ሰዎችን ሳይወዱን መውደዱን አናውቅበትም፤ ብናውቅበት እንኳን ሞኝነት ይመስለናል፣ሰዎች ይቅር ሳይሉን ይቅር ማለቱን አንችልበትም ፤ ብንችልበት እንኳን ገር የሆንን ይመስለናል።ሰዎች ሳያከብሩን ማክበሩን አንችልበትም፤ ብንችልበት እንኳን የተዋረድን ይመስለናል።

🌗ስንሰጥ ምላሽ ካልጠበቅን ሰዎች ክፉ ቢሆኑብን ግር አይለንም። ስንወድ ለመወደድ ብለን ካልሆነ ፤ ፍቅራችን ሲገፋ አይከፋንም፣ስንረዳ ለክፉ ቀናችን ብለን ካልሆነ፤ ሰዎች እርዳታቸውን ሲነፍጉን አይደንቀንም። የምናደርገው ነገር ሁሉ ከልባችን ሲሆን፤ ደስታችን ሌሎች በሚሰጡን ምላሽ ላይ አይወሰንም።

🌓ስትሰጥ መስጠት ስላለብህና ስለሚያስደስተህ ብቻ እንጂ በምላሹ ግብር ጠብቀህ መሆን የለበትም፣ የዜኖች የህይወት ፍልስፍና ሚጠቅሰው አንዱ ነገር ይህንን ነው! ምንም ነገር ቢያደርጉ ማድረግ ስላለባቸው እንጂ ገና ለገና ይሰጠኛል ብለው ስላልሆነ! ሰጥተን ከጠበቅን መስጠታችን ትርጉም አልባ ነው፣ ምላሽ ጥበቃ ከሆነ የነፍስያ [Ego] እንጂ፥ እውነተኛ መስጠት አያደርገውም።

💫ስጥ፣ ስትሰጥ ግን ምስጋናን ፈልገህ አትስጥ። ስጥ፣ ስትሰጥ ግን ምላሽን ጠብቀህ አትስጥ።ስጥ፣ ስትሰጥ ግን ዛሬ መስጠትህ ነገ ትርፍ እንደሚያመጣልህ አስበህ አትስጥ፣የሌላውን ምላሽ ሳትጠብቅ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ከቻልክ ከራስህ ላይ ትልቅ ቀንበር አንስተሀል ማለት ነው።

ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
💡የፈለገውን ያህል ብትሰራ የሰው ልጅ ስምህን ለማጠልሸት አንድ ስህተት ይበቃዋል ። የሚገርመው የቅፅበት ስህተትህን የዘላለም ባህሪህ አድርጎ አንተ ራሱ እስኪገርምህ በርቱዕ አንደበቱ ቀምሞ ያቀርብልሃል፣ ታሪክህን ጨርቅህ ላይ  ስምህን ልብስህ ላይ ለማንበብ ይሽቀዳደማሉ፣ጉድፍህንና ነቀፋህን ለሚከታተሉ ብዙ ቦታ አትስጥ፣ ለእነርሱ አንተ በውሃ ላይ መራመድ ብትችል እንኳ አስማት እንጂ ቅድስና አይመስላቸውም፣ እንዲያውም ዋና ስለማይችል ነው ሊሉህ ይችላሉ፣አለም እንደዚህ ናት ለስኬትህ ሳይሆን ለውድቀትህ ትፈጥናለች።

📍እኔ ትንሽነቴን አልረሳም ማወቄም አያመፃድቀኝም ።እኔ  የእናንተ የመምጣት እና መሄድ አሻራ ነኝ ፣ የእኔ መጉደል መጉደላቸሁ  እንከናችሁም አንከኔ  ነው፡፡ ጀግና ማለት ታግሎ የጣለ ሣይሆን ታግሎ ያለፈ ነው። ሁሌም ቢሆን እራስህን ተመልከት። የምትወድቀው ሌላውን ለመጣል የሞከርክ ቀን ነው፣ልትጥለው የሞከርከው ሰው ግን ገልብጦህ ከላይ ሆኖ ታገኘዋለህ።ሰው ምንም ብልህና አዋቂ ቢሆን በራሱ ሥራ ብቻ ራሱን ችሎ እንደማይኖር ዕወቅ:: ነገር ግን ሁሉም በየሥራው ጸንቶ እርስ በርሱ በሥራ ይፈላለጋል:: ስለዚህ ሰውን ሁሉ አክብረህ ኑር እንጂ ሰውን አትናቅ ሥራውንም አትንቀፍ::

💎ሁሉንም በገንዘብ እገዛዋለው ብለህ አታስብ በገንዘብ የምትገዛው ርካሹን ነገር እንጂ ውድ ነገሮች የዋጋ ተመን የላቸውም።የዋህነት እና ንፁህነት በእውቀት ብዛት ወይም በጥበብ ጥልቀት ተፈልጎ የማይገኝ በራሱ ንፁህ ስጦታ ነው፡፡ በገንዘብ የማይገዛ፤ በሀይልም የማይጠፋ፤በመከራም የማይደበዝዝ ለተወደደ የሚሰጥ የፈጣሪም ችሮታ ነው፡፡ 

        ለፍቅራችን፣ ውብ ቅዳሜ! ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
🔑 ፍርሀት  በአእምሮአችሁ ውስጥ ሊኖር የሚችል ሀሳብ ነው።ይህን ሃሳብ በጠንካራ እምነት፣በስኬትና በድል አድራጊነት ሃሳቦች በመተካት ከስሩ ፈንቅላቹ ልታወጡት ትችላላችሁ።ሁል ግዜም  በራሳችን ላይ እምነትን ካሳደርን፣የማናሸንፍበትና ደስተኞች የማንሆንበት አንዳችም ምክንያት አይኖርም።ደስታህን በራስህ ፈልገው።

ፍርሃታችንን ብንከታተለው .ጥበባችንንም እዛው ማግኘታችን አይቀም። ለዚህም ነው ልትገባበት የምትፈራው ዋሻ ውስጥ ነው ሀብትህን የምታገኘው የሚሉት። የመረጋጋት ችሎታ በጣም አስፈላጊ እና ብዙ ጊዜ ሰዎች ጋር የማይታዩ የህይወት ችሎታዎች አንዱ ነው። በጣም መጥፎውን ውሳኔ የምንወስነው ሰላማችንን አጥተን ወይም ስንጨነቅ እና ግራ ስንገባ ነው።

💡ፍርሃት እውነተኛና መሰረታዊ ችግሮችን የመፍታት አቅማችንን በእጅጉ ሊያጠፋው ይችላል። ተረጋጋክ ማለት ሁሉም ነገር በጥሩ ሁኔታ እና በደስታ ያበቃል ማለት አይደለም።ነገር ግን በተሻለ የአዕምሮ ሁኔታ የህይወታችንን እውነተኛ ፈተናዎች እንጋፈጣለን ማለት ነው።

🔑ታዋቂው ፈላስፋ አለን ዋትስ ፍርሀትን ስለማሸነፍ  ያተናገረውን ድንቅ ንግግር ከስር ባለው ቪዲዮ ተጋበዙልን

           ውብ አሁን❤️
https://youtu.be/587YJMUwobQ
ወዳጄ ሆይ

አንዳንድ ጊዜ አጠገብህ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን በቀላሉ ሲያገኙና በትምህርት ፣ በሥራ በትዳር ... ቶሎ ስኬትን ሲጨብጡ ታያለህ። አንተ ግን አንድ ቦታ ቆመሃል። ወቅቱ የእነርሱ ነውና ከመቅናት ይልቅ ባገኙት ስኬት የደስታቸው ተካፋይ ሁን። ለእነርሱ ያደረገ አምላክ ላንተም እንደሚያደርግልህ እመን።

ይኸውልህ ፤

🌗የማንጎ ዛፍ የቡርቱካን ዛፍን ከርሱ ወቅት ቀድሞ ምርትን ስለሚሰጥ አይጨነቅም። ስኬት፣ በወቅት የሚታጨድ መኸር ነው፣ወቅትህ ሲሆን ምንም ነገር ከመንገድህ ሊቆም አይችልም። የአንበሳ በዝግታ መራመድ ስንፍናን ወይንም ድካምን አያመለክትም፤ ያለመውን አደን በእጁ ለማስገባት እርምጃውን እያሰላ እንጂ። የሰዎች ፈጥነው መራመድ አያውክህ።

የራስህን ኑሮ ኑር!

ፈጣሪህን ታመን። ልብ በል፤ ቤትህን በፍጥነት ሠርተህ መጨረስህ ሳይሆን ንፋስና ጎርፍን መቋቋም የሚችል ጠንካራ አድርገህ መሥራትህ ነው ቁምነገሩ። በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ። የእውቀት ሰውና ጠንካራ ሠራተኛም ሁን! ደግሞ ሁሉንም አታገኝም!አንተ የተሳፈርክበት አውሮፕላን መሬት ሲያርፍ፣ ከዛ መሬት የሚነሣ አውሮፕላን አለ፤ ሌሎች ደግሞ ለመነሳት በሂደት ላይ ይገኛሉ። ሁሉም መዳረሻቸው የተለያየ ነው፤ ምናልባትም ወዳንተ መነሻ ሊሆን ይችላል። አየህ ህይወት እንዲ ናት፤ "ደረስኩ" ብለህ ስታስብ ሌሎች ያንን ሥፍራ "ጥለው" ሲነሱ ታገኛቸዋለህ። አንዳንዶቹ አንተ ወደ ተነሳህበት፣ ሌሎቹም ወደ ሌላ።

🌗በልጅ ማጣት ምክንያት ቀን ማታ የሚያለቅሱ ሰዎች እንዳሉ በልጆቻቸው ምክንያት ቀንና ማታ የሚያለቅሱ ሰዎች አሉ፣ባል ባለማግባታቸው የሚጨነቁ ሰዎች እንደገጠሙኝ ሁሉ በማግባታቸው የሚጨነቁም ሰዎች ገጥመውኛል። በሥራ እጥረት ምክንያት የታመሙ እንዳሉ በሥራ ብዛት ምክንያት የሚታመሙ አሉ። ልጆቻቸው ፈተና ላይ ጥሩ ውጤት እንዲያመጡላቸው የሚጨነቁ እንዳሉ፣ ልጆቻቸው ጥሩ ትምህርት ቤት እንዲገቡላቸው የሚጨነቁ አሉ።

እናም ወዳጄ

ህይወት እንዲህ ነው፤ በቃ! ሁሉንም የኛ ልናደርግ አንችልም!፣ ንፋስን አባሮ እንደመያዝ ነውና። ሁሉንም ነገር የራስህ እንዲሆን ከመድከም ይልቅ ባለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን ሞክር። ከአንዱ ምእራፍ ወደ ሌላው ምእራፍ እንደሚያሸጋግርህም ፈጣሪህን ታመን። ሁልጊዜም በአምላክህ ደስ ይበልህ! በእምነትም ኑር!

መልካምነት ለራስ ነውና

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

የተሰማችሁን አድርሱን @EthioHumanityBot
💡ቅንነት ከልምምድ፣ ልምምድም ከዕውቀት፣ ዕውቀትም ከጥረት ይገኛል፡፡ ቅንነት ኮሌጅ በመበጠስ፣ ዲግሪ በማብዛት እውን የሚሆን አይደለም፡፡ አባቶቻችን ዘመናዊውን ትምህርት ሳይማሩ በቅንነት ተዋደውና ተፋቅረው የሐገራቸውን ጥበብና አንድነት አስጠብቀው ኖረዋል፡፡ የእኛ ዘመን ትውልድ ግን በአውቃለሁ ትርክት ጠፍቶ አባቶቻችን ያቆዩልንን ታሪክና ጥበብ ከመጠቀም ይልቅ ለመለያያት ሴራ እንጎነጉንበታለን፡፡ ቅንነት በየደቂቃውና በየሠዓቱ ሌሎችን በበጎ ዓይን ማየትና ሕመማቸውን የራስ ሕመም አድርጎ በመውሰድና የሌላውን ሠቆቃ በመካፈል የሚገኝ ነው፡፡

📍ብዙ ቅን ምሁራን አሉ፡፡ እልፍ ቅን ሃይማኖተኞች አሉ፡፡ ጥቂት የማይባሉ ኢአማኝ በጎ ሠዎች አሉ፡፡ ነገር ግን ቅን ሁሉ አዋቂ እንዳልሆነው ሁሉ፤ አዋቂ ሁሉ ቅን አይደለም፡፡ ሃይማኖተኛ ሁሉ መልካም አሳቢና አድራጊ አይደለም፡፡ ኢአማኝ ሁሉ ደግ ነው አይባልም፡፡ አዋቂዎች በሙሉ፣ አማኙም ኢአማኙም ሁሉ ቅን ቢሆኑ ዓለማችን የት በደረሠች ነበር፡፡

ቅንነት በአስተሳሰብ ብቻ የሚገለፅ ሳይሆን በተግባር መሬት ወርዶ የሚታይ ካልሆነ፤ እንዲሁም ቅን አሳቢ ቅን አድራጊ መሆን ካልቻለ ማሠቡ ብቻ ቅን አያስብለውም፡፡ ብዙ ጊዜ በአብዛኞቻችን ላይ የሚታየው ባህሪ ይሄ ይመስለኛል፡፡ በሃሳብ ቅን በተግባር ግን ሌሎች ነን፡፡ ‹‹ጧት ጧት ቅዱስ፤ ማታ ማታ እርኩስ!›› እንዲል ብሒሉ፡፡

❤️ከፈላስፎች አንዱ፡- ‹‹ሥራው መልካም ካልሆነ ጥበቡም መልካም አይደለም፡፡ ጥበበኛው ሠውዬ ቅን ካልሆነ ጥበቡም ቅን ሊሆን አይችልም፡፡ ለክፉም ለበጎም ጥበብ አለና፡፡›› በማለት ተግባሩ ሃሳቡን፣ ምግባሩ ጥበቡን መግለፅ ካልቻለ ጥበበኛ ሁሉ ቅን አይደለም ይለናል፡፡ እውነት ነው ቅንነት በጎነት የሌለው ጥበበኛ ጥበቡ ለክፉ እንጂ ለመልካም አይውልም፡፡

ፈላስፋው ዲዮጋንስ፡- ‹‹ከንጉስ ይልቅ በሃብት እኔ እበልጣለሁ›› ሲል ‹‹አንተ በሃብት ከንጉሱ የበለጥከው በምንድነው?›› ብለው ሲጠይቁት ዲዮጋንስም፡-

‹‹በንጉሱ ዘንድ ካለ ብዙ፤ በእኔ ዘንድ ያለ ጥቂት ይበቃልና ነው›› አለ፡፡ ይህ ፈላስፋ ካንዲት ቀፎ መሣይ ማደሪያ ቤት፣ ከአንድ ውሻ፣ ውሃ ከሚጠጣበት ቅል፣ ከአንድ ምርኩዝ ወይም በትር በስተቀር ሌላ ሃብት አልነበረውም፡፡ ቅሊቱንም እንኳ አንድ ትንሽ ልጅ በእጁ እፍኝ ውሃ ሲጠጣ አይቶ ‹‹ለካስ ቅልም ትርፍ ነገር ኖሯል›› ብሎ ጥሏታል፡፡

💡ወዳጆች ብዙዎቻችን ትርፍ ስናስብ ዋናውን ነገር ጥለናል፡፡ ፈላስፋው ዲዮጋንስ ትርፉን ጥሎ ዋናውን ነው የያዘው እኛ ግን ዋናውን ጥለን በትርፉ እንባክናለን፡፡

📍በመጀመሪያ ሠብዓዊ ማንነታችን አሽቀንጥረን ጥለናል፡፡ ታሪካችንን፣ ወግና ባህላችንን ንቀን የፈረንጁን አንጠልጥለናል፡፡ አብሮነታችንን፣ አንድነታችንን በዘመን አመጣሽ ቀሽም የዘረኛ ፖለቲካ አደጋ ላይ አውለነዋል፡፡ ዋናውን ጥለን ትርፉ ላይ እንተራመሳለን፣ እርስበርስ እንበላላለን፡፡ ትርፍ ነገሩ ውስጣዊ ሕይወታችን ላይ የሚጨምረው አንዳች ነገር የለውም፡፡ ልባችንን የሚያሞቅ፣ ሕሊናችንን የሚያጠግብ፣ ሠብዓዊነታችንን የሚያረጋግጥ ቅንነት፣ ፍቅርና አንድነት ብቻ ነው፡፡

❤️ፍቅር ካለ አንድ ቂጣ ለዘጠኝ ሠው ይበቃል እንዲል ብሂሉ ባይኖረን እንኳን ቅን ከሆንን ክፉ ጊዜን ማለፍ እንችላለን፡፡ የሐገራችን ችግር የቅንነት ችግር ነው፡፡ የሐገራችን መከራ የዕውቀት ዕጦትም ብቻ አይደለም፡፡ የአዙሪታችን ጉዳይ የአመለካከትም ኋላቀርነት ነው፡፡ ቅን ከሆንን ግን ዕውቀቱንም፣ ክህሎቱንም፣ ቁሱንም ማግኘት እንችላለን፡፡ ዕውቀት፣ ሐብት፣ ክህሎት፣ ወዘተ ኖሮን ቅንነት፣ ፍቅር፣ በጎነት፣ ሌላውን እንደራስ ማየት የሚያስችል አመለካከትና ሕሊና ከሌለን ሁሉም ከንቱ ነው፡፡

💛ሕይወት ትርጉም የሚኖረው ቅን ሆኖ በፍቅር ተስማምቶ መኖር ሲቻል ነው፡፡ ተስፋም ሆነ ትዝታው ጣፋጭ የሚሆነው የወደፊቱን ጊዜ በበጎ አስተሳሰብ ዋጅተን ስንጠብቀው ነው፣ ያለፈውን ደግሞ በመልካም ትዝታ መለስ ብለን ስንጎበኘው ነው፡፡ ዛሬ ያልኖርበት ቅንነት ነገ መልካም ትዝታ ይዞ አይመጣም፣ ነገም የተሻለ የቅኖች ቀን አይሆንም፡፡

❤️ለዚህ ነው መቼም ቢሆን ‹‹አሉታዊ አዕምሮ አዎንታዊ ሕይወትን አይሠጠንም›› የሚባለው፣ቅን እንሁን! ፍቅር ይኑረን! በዘረኝነት አስተሳሰብ እርስበርስ አንጠላላ፣ አንገፋፋ! አንድ እንሁን! ኢትዮጵያዊነት ትለምልም!

እሸቱ ብሩ ይትባረክ

ውብ ቅዳሜ❤️
@EthioHumanity
@Ethiohumanity

@EthioHumanitybot
🌗መጥላት አልወድም፡፡ ስጠላም ለምወደው ነገር ስል ነው፡፡ የምወዳቸው ነገሮች እንዳይጐዱብኝ ጐጂውን በጥላቻ ማራቅ አለብኝ፡፡ እውነተኛ መውደድ ከብዙ ቅርፊት የተሰራ ነው፡፡ አንደኛው ቅርፊት በወረት ወይንም በጥላቻ ተቀርፎ ሲወድቅ አዲስ የመውደድ ቆዳ ከስር ብቅ ይላል፡፡

ለሰው ልጅ ያለኝ ጥቅል ውዴታ የዚህ ተምሳሌት ነው፡፡ ብዙ አይነት ስም ያላቸውን ግለሰቦች ወድጄ ጠልቻለሁ፡፡ እንደ ቅርፊቱ፡፡ በሰው ልጅ ስም የሚጠራውን ማንነት ግን ልጠላው አልችልም፤ አልፈልግምም፡፡

የጥበብ ስራን እወዳለሁ፤ ስለ ጥበብ ሰሪው ግን ግድ የለኝም፡፡ የጥበብ ስራውን በመውደዴ የጥበብ ሠሪው ተወዳጅ እንዲሆን ሊያደርግልኝ የቻለ ማንም የለም፡፡...ስሪቱ ከሰሪው በላይ ነው፡፡
ከማውቀው ሰው ይልቅ የማላውቀውን ሰው የበለጠ እወዳለሁኝ፡፡ ሰውየውን ሳላውቀው እኔ ነኝ በምናቤ የቀረጽኩት፤ የተጠበብኩበት፡፡ ሰውዬውን ሳውቀው እኔ የሰራሁት መሆኑ አከተመ፡፡

🌗የተፈጥሮው ሰው፦ ሆዳም ነው፣ ራስ ወዳድ ነው፣ ፈሪ ነው፣ ወይንም ሞኝ ነው፣ ሲያወራ ይጮሃል፣ ሲያላምጥ ይንጣጣል፣ ውሃ ካጣ ይግማማል... ማለቂያ የለውም... ወዘተ ወዘተርፈ፡፡ ከሰው ሰው ከስህተት የስህተት አይነት ይለያያል፡፡ ከጥላቻ በራቀበት እና ወደ መውደድ በቀረበበት መጠን የተሻለ ሰው ይባላል እንጂ ትክክል ግን የለም፡፡ የተሻለ ስህተት ትክክል አይደለም፡፡

💫የማላውቀውን ሰው እንጂ የማላውቀውን ስራ ግን ወድጄ አላውቅም፡፡ ስራውን ለመውደድ ስራውን ከሰራው ሰው ጋር ሳይሆን ከስራው ብቻ ጋር መተዋወቅ አለብኝ፡፡ መዋደድ በእዳ መልክ ግንኙነት በተቆራኙት መሀል ሊፈጥር ይችላል፡፡

የማይነጠል ቁራኛን መጥላት አያዋጣም፡፡ መውደድ ብቻ ከሆነ አማራጩ መዋደዱ የዕዳ ባህርይ የተላበሰ ይሆናል፡፡ የስጋ ዝምድና ወይንም የስጋ ዝምድናን ለመመስረት ሲባል የሚፈጠር የስሜት ቁርኝት፤ ..መውደድ.. በእዳ ...ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡ መውደድ በዕዳ እንጂ መጥላት በዕዳ ግን የለም፡፡

ጥበብን መውደድም እዳ የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ በተለይ በሚያስጠላ አመት ውስጥ መውደድን ተሸክሞ መጓዝ ግዴታ ሲሆን፡፡

🌓ሰማዩን አሁንም እወደዋለሁ፡፡ (እርግጥ ካየሁት ወደ አንድ አመት ከመንፈቅ አልፎኛል እንጂ፡፡ ቀና ብዬ ሰማዩን ባየው እንደ ድሮው በክዋክብት አበባ እና በፌንጣ ጩኸት እና በልብ ፀጥታ የተሞላ ሳይሆንልኝ ቢቀር፤ እጠላዋለሁ፡፡ ከምጠላው በድሮ ትዝታዬ ሆኜ መውደዴን ብቀጥል ይሻላል) ለውጥን እወዳለሁ፡፡ ግን የምወደው በምኞት ብቻ እንዳይሆን እሰጋለሁ፡፡ በጽንሰ ሐሳብ፣ በቲዎሪ ብቻ፡፡ ቲዎሪው ተግባር ሆኖ ለውጥ ሲመጣ ግን ሆዴን ባር ባር ይለኛል (Bar ፈልጌ ፉት እልበታለሁ)

ድሮ ያደኩት ሰፈር መንገዱ እንዴት እንደነበር ማስታወስ ተስኖኛል፡፡ መለወጡን በተስፋ ወድጃለሁ፡፡ ሲለወጥ ባዶ ሆኖ አስጠልቶኛል፡፡
መውደድ እና መጥላት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው ወይ? ብዬ ግር እሰኛለሁ፡፡ ምኞትን መውደድ? ምኞቱ ተወልዶ በእግሩ ሲሄድ ለመጥላት ነው እንዴ? በምኞት ደረጃ የተወደደ ምኞቱ የተሳካ ለት ይጠላል፡፡ በምኞት ደረጃ የተጠላ በስኬት ደረጃ ይወደዳል ማለት ነው...ምን አይነት ዲያሌክቲክስ ነው ጃል? ይኼ ማለት እኮ በምኞት ..መልካም አዲስ አመት.. ያልነው ምርቃት መጥፎ አሮጌ አመት ሆኖ በእርግማን ይሸኘናል ማለት ነው፡፡

🌗ለማንኛውም ግን ጥበብን እወዳለሁ፡፡ መጥላት የምወዳቸው ብዙ ሌላ መውደዶች አሉኝ፡፡ ግን ለጥበብ ይሄ አይሰራም፡፡ ጥበብን ስመኘውም እንደ ተግባሩ እወደዋለሁ፡፡ ጥበብን ከእውነታ ጋር ለማቆራኘት መሞከሩን ነው የምጠላው፡፡
.
ጠዋት በእግሬ እያዘገምኩ ማሰብ እወዳለሁ፡፡ የምጠላው ከብዙ ጉዞ በኋላ የሚሰማኝን ድካም ነው፡፡ ፎቶግራፎችን በሙሉ እወዳለሁ፡፡ ዘመናት ባለፉ ቁጥር ጥበብ ይሆናሉ፡፡ ባዶ ክፍል ውስጥ ከሀሳቤ ጋር መቀመጥ እወዳለሁ፡፡ ሌላ ጭንቅላት ሲያንኮራፋ በማልረበሽበት፡፡ የአሮጌ መጽሐፍትን ሽታ እና ክብደት እወዳለሁ፡፡ ቴሌቪዥን እየተመለከትኩ በቴሌቪዢኑ ውስጥ የራሴን ቴሌቪዥን ከፍቼ መመልከት እወዳለሁ፡፡

🌗ትርጉም ያላገኘሁላቸው መውደድ እና ጥላቻዎችም በብዛት አሉ፡፡ እንዴት ልደረድራቸው፣ ወይንም ላስወግዳቸው እንደምችል ፍቺ ያላገኘሁላቸው ነገሮች፡፡ ትርጉም የዋጋ መለኪያ አንዱ መስፈርት ነው፡፡ የሰዎችን (የሰው ልጆችን) ቆራጥነት፣ ታጋይነት፣ ጠንካራነት፣ ቀዳዳ ፈላጊነት ብዙ አዎንታዊ መገለጫዎቹን እወዳለሁ፡፡ ግን አንዳንዴ ደግሞ ቆራጥ፣ ታጋይ፣ ጠንካራ የሆኑለት ነገርን (አላማን) የተሳሳተ እምነት ሲሆን እጠላለሁ፣የምወደውን ነገር ከምጠላ ግን የጠላሁትን ነገር በአዲስ እይታ ተመልክቼ ብወድ ይሻለኛል፣ ምናልባት መውደድ ከመጥላት ይሻል ይሆናል ፣ወዳጅም ደግሞ ከጠላት፡፡

     📖 "መጥላት የማልወዳቸው"
ከሚል መጣጥፍ የተቀነጨበ።
                      ሌሊሳ ግርማ

              ውብ አዳር❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
🌝ፈገግታ መንፈስን የሚያነቃ የተቀመመ መደሃኒት ነው ብንል ውሸት አይሆንም ፣ በፈገግታ የታጠነ ገፅ መመለከት ሰፍሮብን የነበረውን የብሽቀት ጋኔን ድራሽ አባቱን ያጠፋል ። ሰው ፈገግ እያለ በጥፊ ቢመታህ እንኳን ለፈገግታው እንጂ ለጥፊው ምላሽ አትሰጥም እመነኝ ቢያምህም ፈገግ ትላለህ ፣ ፈገግታ ሀያል ነው ፣ ፈገግታ የሀሴት መርጫ ስሪንጅ ነው ፤ ፈገግታ ብርሃናማ ቀለማት መሳያ ሸራ ነው .... ፈገግ በሉ !!!

ፈገግታ ካለህ ጠላት አይኖርህም፣ ሞት እንኳን አፍጦ ቢመጣብህ ፈግግበት😁፣  ፈገግታ ነፍስን ይከፍታል ፣ እርካታና መዝናናትን ይፈጥራል። የውቅያኖስ ንፋስ ጭጋግን እንደሚበታትነው ሁሉ ፈገግታም ውስጥህ ያለውን ሀዘንና ጥላቻን ይገፋል። ለሰፊው ባህርም የመሬት ቀዝቃዛ ንፋስ ፈገግታው ነው፣ ባህር በንፋስ ላይና ታች እያለ ካልተጫወተ ውበቱን ያጣል፣ ሃይለኛ ሽታም ይፈጥራል። የሰው ልጅም መጥፎ ጠረን የሚጸዳው በፈገግታው ነው።

ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል፣ የልብ ሀዘን ግን መንፈስን ይሰብራል እንዲል ቃሉም፣ ፈገግታ ሱና ነው እንዲል ሀዲሱም። በዓለም ላይ የሌለን ነገር ሁሉ ተደምሮ ያለንን ነገር አይበልጠዉም፣ሁሌም ለዓለም ሳቁ ፣ ስትስቁ ያን ጊዜ ውብ ናችሁ።

ዛሬን ትላንት አልኖርነውም ፣ ወደፊትም ፈፅሞ አናገኘውም ፣ ዛሬን በሃዘን አትግደሉ ፈገግታ ስጦታ ነዉ፣ፈገግ ስትሉ ኑሩልን😇

ለፍቅራችን፣ ውብ ቅዳሜ! ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
❤️ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፦ እንኳን ለትንሳኤ በዓለ በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን !

በዓሉ ፦ የሰላም ፣ የፍቅር፣ የደስታ ፣ የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት እና የአንድነት በዓል እንዲሆን እንመኛለን።

(መልካም ትንሳኤ፤ መልካም በዓል!)❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
ሀሳብ ይፈውሳል...ሀሳብ ያጠፋልl

💡መጠየቅ፣ ማሰብ፣ ማሳሰብ፣ የጠየቁትን ነገር መናገር፣ የተናገሩትን ነገር መጠየቅ፣ የሚያስቡትን መፃፍ፣ ያሰቡትን መፃፍ በርካታ ውጤቶች አሉት። ግን ውጤቱ ምን አልባትም በህይወት አለመኖርንም ጭምር ሊሆን ይችላል። የሆነ ሆኖ ግን ካልጠየቅን ነቃሽም ወቃሽም መሆን ስለማንችል። መጠየቅን መለማመድ አለብን።

ለመጠየቅ ግን በቃ መጠየቅ ነው ያለብን፣ ሀሳብ እና ማሰብ በተለይም ደግሞ ምክንያታዊ አስተሳሰብና አመለካከቶች ልክ እንደ መርዝ ናቸው። ይፈውሳሉ ወይም ይገድላሉ። ወይ እራስንና ትውልድን ያስመልጣሉ ወይም ያጠፋሉ የአንተነትህ ምስል የአስተሳሰብህ ስዕል ነው፡፡ እይታህ የሚወለደው ከአመለካከትህ ነው፡፡ሃሳብህ ከተበላሸ፣ የዘራኸው ከመከነ ፍሬህ አይጎመራም፡፡ የአዕምሮህ መጥፎ ሀሳብ ካሸነፈ አንተንም ሆነ ሌሎችን ይመርዛል።

💡ሀሳብ ያለመልማል ያጠፋልም። ልክ እንደ መርዝ ነው። ልክ እንደ መድሀኒት ነው ይሽራልም ያሽራልም። የመግደልም የማዳንም አቅም አለውና። ለምናስበው ሀሳብ ለማሰቢያውም እንጠንቀቅ። ሀሳባችን ጤነኛ እና ንጹህ ከሆነ መላ ሰውነታችን፣ ግንኙነታችን፣ ስራችን ወጥቶ መግባታችን በሙሉ ጤነኛ ይሆናሉ። በተቃራኒው ከሆነ ሀሳብ መርዝ ነውና ብትንትናችንን ያወጣናል..

📖 "ሔምሎክ...ገጽ 19-20"
ዮናስ ዘውዴ ከበደ

ውብ አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot

💫እንኳን ለ 1444ኛው የዒድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

❤️በመላው አለም የምትኖሩ የእስልምና እምነት ተከታይ ሙስሊም ወገኖቻችን እንኳን ለ1443ኛው የዒድ በአል በሰላም አደረሳችሁ፣አደረሰን።

የዒድ በአል የእዝነት ÷ የመተሳሰብ ÷ አብሮ የመብላትና የመፈቃቀር በአል በመሆኑ በየ አካባቢያችን በችግር ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን እያሰብን እንዋል።

ዒድ ሙባረክ !!!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity
💡ስኬት ሌላ ሳይሆን ፣ የሕይወት ማዕቀፍን መኖር መቻል ማለት ነው፣ የአንተን ማንነት ከተሳለው መድረኩ ጋር ማጣጣም መቻልህ ስኬት ነው። ማንነት የመኖር መሆን ነው፣የተሳትፎ መድረኩ ሕይወት ነው። ሁለቱ ተመጣጣኝ ሲሆን የሕይወት ማዕቀፍ ነው። ማንኛውም ዓይነት ሕይወት ችግር አይደለም። ችግረኛ የሆነ ነዋሪም የለም። የሕይወት ችግሩ የሕይወት ማዕቀፍን መኖር አለመቻል ነው።

💎ሕይወት ልክ እንደ ሸሚዝ በልክህ ተዘጋጅታ የምትኖራት ብቻ ሳትሆን ፣ በየጊዜው ራሷ በምትሰጥህ የኑሮ ልክ ራስህን እየጠረብክ እያስተካከልክ የምትኖርባት መድረክህ ናት፣የጎደለውን በሙሉ፥ ሙሉውን ደግሞ በጎዶሎ እያቻቻልክ እንጂ ከሕይወት ሙሉነትን አታገኝም፣ ሁሉም ሰው ለክቶ የሚኖረው የሕይወት ማዕቀፍ አለው፣ የምታደርገው ጫማ የሚመችህ በልክህ የተሠራ ከሆነ ብቻ ነው። በጣም ትልቅ ከሆነ ሸክም ነው በጣም ትንሽ ከሆነ ስቃይ ነው የሕይወት ማዕቀፍም እንዲሁ ነው ።

💡በማንኛውም አኗኗር ውስጥ ብትሆን በልክህ የምትኖረው ሕይወት ማዕቀፍ ካለህ የአንተ ትክክለኛ ሕይወት እሱ ነው። የሕይወት ማዕቀፍ የኑሮ ቀለምና ቅርፅን ከሁኔታው ጋር አዛምዶ የመኖር ጉዳይ ነው [FLEXIBILITY] ፣ ለመኖር የማትችለውን ቀለም አትምረጥ፣ ሕይወት የስኬት ገበያ ናት! በብልጠት ተገበያይ! ከአቅምህ በላይ ለሆነው ትግል ውስጥ አትግባ ለጊዜው እሱ ላንተ አልተፈቀደምና ፣ ራስህን ከሁኔታዎች ጋር እያወሃድክ መኖርህን ቀጥል።

📖 ሰው መሆን

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
2024/09/27 07:28:46
Back to Top
HTML Embed Code: