Telegram Web Link
+ቤተ ክርስቲያን+
ወርቅ በእሳት በተፈተነ ቁጥር ጥራቱ እየጨመረ ይሄዳል። እንዲያውም በትርጓሜያችን ወርቅን ሰባት ጊዜ በከውር (በወርቅ ማቅለጫ) ሲያቀልጡት ከወርቅ የበለጠ ዕንቍ ይሆናል ይላል። ሰውም እንዲሁ ነው በመከራ በተፈተነ ቁጥር እንደ ወርቅ እየጠራ ይሄዳል። ሰማዕታት መከራውን አልፈው ቅድስናቸውንና ንጽሕናቸውን ገለጡ። ከመ ወርቅ በእሳት ፈተኖሙ የተባሉ ሰማዕታት ናቸው። እሳቱ የበለጠ ቢነድ ወርቁን የበለጠ ያጠራዋል። እሳት የሚያስፈራው ገለባን እንጂ ወርቅን አይደለም።

ቤተክርስቲያን ንጽሕት ናት። የንጽሕናዋ ምንጭ ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ከውስጥም ከውጭም የሚፈትኗት ብዙዎች ቢሆኑም ይህ ፈተናና መከራ ንጽሕናዋን የበለጠ ይገልጣል እንጂ በፈተናው አትጠፋም። የቤተክርስቲያን ራሷ ክርስቶስ ነው። በእርሱ ሁልጊዜ ደስ ይለናል።

ቤተክርስቲያን ለክፉዎች ሰይፍ ናት። እርሷን ተመርኩዘው በስሟ ቢነግዱ የሚጎዱት ራሳቸው ናቸው እንጂ ቤተክርስቲያን አይደለችም። በሽተኞች መድኃኒታቸውን ቢያቃጥሉ በሽተኞች ራሳቸው ይሞታሉ እንጂ መድኃኒቱ አይጎዳም።

ፈተናዎች እስከ ዕለተ ምጽአት መልካቸውን እየቀያየሩ ቢመጡ እኛ የበለጠ እየጠነከርን መሄድ አለብን እንጂ ተስፋ መቁረጥ አይገባም። "ዝናብም ወረደ፥ጐርፍም መጣ፥ነፋስም ነፈሰ፥ያንም ቤት ገፋው በአለት ላይም ስለ ተመሠረተ አልወደቀም" ማቴ. ፯፣፳፭። ራሳችንን ዐለት በተባለ በክርስቶስ አስተምህሮ ላይ መመሥረት አለብን።

© በትረማርያም አበባው

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ተጠያቂው ማን ነው?

ከሰሞኑ በቀዳማዩ አቡነ ጴጥሮስ ሕይወት ዙሪያ ፊልም እሠራለሁ ያለ አንድ አካል ስማቸውን በልጅነታቸው በቤተሰብ ይጠሩበት በነበረው ስም እየተጠቀምሁ ፊልም እሰራለሁ ማለቱን ተከትሎ (ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እንዳነበብኩት ነው) ቤተ ክህነታችን ተቃውሟል። ይህን ተከትሎም ብዙ ሰዎች ድርጊቱን እያወገዙት ነው፤ መወገዝም አለበት። በርግጥ ቤተ ክህነት የከለከለበትን ምክንያት በይፋ ስላላየነው ለመደምደም ሊያስቸግር ይችላል።

የሚያስወግዘውም ሆነ ተቃውሞውን ያመጣው ስማቸው የተለወጠ ከፖለቲከኞች አንዳንዶቹ እንደሚሉት የእርሳቸው የሚባለውን ማንነት ወደማያሳይ የተለወጠውን ስም መልሶ በማምጣት ለዚያ ለእርሳቸው ለተሰጠው ማንነት ማዳመቂያ ለማድረግ ታስቦ ነው በሚል ነው። መነሻ የተደረገውም የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አቀንቃኞች ከነበሩት አንዳንዶቹ የያዙትን መስቀል ረስተው ጳጳሳት ለምን በኦሮሞ ስም አልተሰየሙም ብለው ካነሡት ፖለቲካዊ ትግል ውስጥ ይመስለኛል። ይህን ሁሉ ያሉት የተደረገው ሁሉ እነርሱ ሊያደርጉት እንደሚፈልጉት ጥንቱንም በፖለቲካ ምክንያት የተደረገ መስሏቸው ሊሆን ይችላል፤ ወይም ደግሞ እንዳልሆነ እንኳ ቢያውቁ አሁን የሚፈልጉትን ለማድርግ የቀደመውንም ፖለቲካዊ አድርጎ ማቅረብ የስልቱ አካል ስለሆነ ሊሆን ይችላል። ለሁሉም እውነታውን እናስቀድም።

ምንኩስና ውስጥ ሲገባ ይልቁንም ደግሞ ከቅዱስ ጳኩሚስ በኋላ ጎልቶ በሚታወቀው ሥርዓተ ጳኩሚስ መሠረት ምንኩስና ሦስት ደረጃዎች አሉት ። እነዚህም ረድዕነት፣ (ልብሰ) ምንኩስና እና ሥርዓተ አስኬማ ናቸው። እነዚህ ደረጃዎች ደግሞ የራሳቸው ትርጉም ያላቸው ከመሆኑም በላይ በደረጃዎቹ የሚጠበቁ ለውጦች አሉ።

የመጀመሪያው የረድእነት ደረጃ ራስን የመካድ ደረጃ ነው። አንድ ሰው ወደ ምንኩስና ሲመጣ “ማንም ሊከተለኝ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ ፣ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” /ማር 8 ፡ 34/ ከሚለው የጌታ ትእዛዝ ውስጥ የመጀመሪያዋን መፈጸም አለበት ። ምንም እንኳ ይህ የወንጌል ትእዛዝ ለሁሉም ክርስቲያኖች የታዘዘ እና ሁላችንም ልናደርገው የሚጠበቅ ቢሆንም ወደ ምንኩስና የሔደ ግን ያለማንገራገር ይህን ከመፈጸም መጀመር ይኖርበታል። በዚህም መሠረት ራስን መካድ ማለት፣ ለራስ ደስታ፣ ለራስ ጥቅም፣ ለራስ ማድላት፣ ለራስ ቅድሚያ መስጠትን ሙሉ በሙሉ ሲተው ራሱን ካደ ይባላል። ይህም ማለት ገዳም ገብቶ በረድእነት ያለ ሰው የታዘዘውን ይሠራል እንጂ የፈለገውን አይሠራም። ራሱን ክዷል ማለት ፈቃዱን ትቶ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በሚያዙት ሰዎች በኩል በመታዘዝ ይፈጽማል። ለገዳሜ፣ ለወንድሜ፣ ለአባቴ፣ በአጠቃላይ ለሌሎች ይሁን ይደረግ ይላል እንጂ ለእኔ ማለትን ለማቆም ይለማመዳል። የተሰጠውን ይጠቀማል እንጂ የመብት ጥያቄም አያነሣም። ሥርዓተ ገዳም፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እና ሕገ እግዚአብሔር እንዳይጣስ ይጠይቃል እንጂ ፍላጎቱን ለማሟላት ሊጠይቅ አይችልም። ይህን ሲያደርግ ደግሞ ወደ እርሱ ፍላጎት እና ፈቃድ እንዲመለስ የቀደመ ልምዱም ሆነ ሰይጣን ፈተና ቢያመጡበት ዕርፍ ይዞ ወደ ኋላ ማረስ የለምና ምን ማድረግ እንዳለበት ወይም ፍላጎቱን፣ ዓለምንና ሰይጣንን እንዴት መዋጋት እንዳለበትም ልክ እንደ አንድ ወታደር ልምምድ የሚያደርግበት የምንኩስና ቀዳሚ ደረጃ ነው፤ ረድእነት ። ይህን በአግባቡ የሚወጣ ረድእም ረድእ ዘበኅድአት ይባላል። ጸጥ ብሎ የሚታዘዝ ራሱን በትክክል የካደ ማለት ነው። ስለዚህም ወደሚቀጥለው ተጋድሎ እንዲገባ ይፈቀድለታል።

ይህን የረድእነት ደረጃ ቢያንስ ለሦስት ዓመት አንዳንዴ ደግሞ ከዚህ በታች ወይም ከዚህ በላይ ለሆነ ጊዜ ከቆየ በኋላ ወደ ምንኩስናው ይሄዳል። በዚህ ጊዜ ደግሞ በረድእነት ራሱን እንደካደ አሁን ደግሞ ዓለምን ጨርሶ ይክዳል። ይህም ማለት ራሱን ለዚህ ዓለም እንደ ሞተ ይቆጥራል። “ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል” / ያዕ 4 ፡ 4/ የሚለውን እያሰበ ከእግዚአብሔር ጋር ለመሆን ሲል ዓለምን ይክደዋል። ለዚህም ከዚህ ዓለም ጋር የሚያገናኙትን ክርሮች በሙሉ ይቆርጣል። ስለዚህም ልክ እንደሞተ ሰው ሥርዓተ ግንዘት ተደርጎለት የፈቃድ ሞቱን ይቀበላል። ከዚህ በሁላ ዘመዴ ወገኔ፣ ሀገሬ፣ ቋንቋዬ፣ መንደሬ ይቀራል። ንብረት ማፍራት፣ በዚህ ዓለም ጉዳይ እንደ ዓለም ሰዎች ሆኖ ጣልቃ መግባት ሁሉ ይቀራል።

በዚህ ዓለም ጉዳዮች ከገባም የሚገባው ልክ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ከአድሎ ነጻ ሆኖ ከፈቃደ እግዚአብሔር ጋር ሳይቃረን ከገባበት አዲስ ዓለም ሳይወጣ ብቻ ይሆናል ማለት ነው። ልክ አንድ አምባሳደር በሚኖርበት ሀገር የሚያደርገው ሁሉ የወከለውን ሀገር ጥቅም፣ ክብር እና ደረጃ የጠበቀ እንደሚሆነው ሁሉ መነኩሴም እንዲያ ነው የሚሆነው። የቀደመ ስሙ የሚቀረውም በዚህ ምክንያት ነው። ሌላ ስም ይሰጠዋል። አዲሱ ስሙ የገባበት አዲስ ዓለም ውስጥ ለሚኖረው ሕይወት የሚሰጥ ያንን የሚመለከት ስም ነው። ለዚህ ዓለም ሙቶ ለዓለመ መላእክት ተወልዷልና። ስለዚህም አክሊለ ሦክ (ቆብ) ይደፋል፣ ልብሰ ምንኩስና ይለብሳል፣ በዚህም ከዚህ ዓለም ፈጽሞ ይለያል። ይህን ዓለም ክዶ ያኛውን ዓለም ተቀልቅሏል። ከዚህ በኋላ በአዲስ ዓለም ወዳለው ከፍተኛ ደረጃ ለመድረስ ትግሉን አበርትቶ ይቀጥላል። ያ የመጨረሻ ደረጃም አስኬማ የተባለው ደረጃ ነው።

አንድ መነኮስ ለአስኬማ የሚበቃው ከላይ እንደጠቀስነው መስቀል ከመያዝ መስቀል ወደ መሸከም ሲደርስ ነው። በዚህ ጊዜም እኔን ሊከተለኝ የሚወድድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ ከሚለው ቃል ውስጥ የመጨረሻው መስቀል መሸከም ላይ ይደርሳል ማለት ነው። ይህም ማለት በፈቃዱ መከራ ይቀበላል። ሥጋ መብላት ፈጽሞ ያቆማል። መሬት ላይ አንጥፎ መተኛት ያቆማል። ልክ ጌታ በደብረ ዘይት ተራራ ሲጸልይ ያድር እንደነበረው ሲጸልይ ይውላል ያድራል። በአእምሮው ሙሉ በሙሉ ተዘክሮ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርን ብቻ ማሰብ) እና ልክ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ለመምሰል ወይም ጌታን በመምሰል ይኖራል ማለት ነው።

በዚህ ምክንያት ለአስኬማ የሚበቃ አንድ መነኮስ ሥርዓተ አስኬማ ይፈጸምለታል። በጥንቱ ትውፊት መሠረትም ቅናተ ዮሐንስ ይታጠቃል፣ ይህም ዮሐንስ መጥምቅ የበረሃ ማር እንደበላ እና ከዚህ ዓለም ነገር ምንም እንዳልወሰደው ከምንም ነገር ይለያል። በንጽሕናው እና ተጋድሎው እንደ መልአከ እግዚአብሔር ወይም እንደ ዮሐንስ መጥምቅ ይሆናል ማለት ነው። ከዚያም መስቀል እና ሌሎች ከስቅለተ እግዚእ ጋር የተገናኙ ነገሮች የተጠለፉበት ቀሚስ ወይም ደግሞ አሁን በቅዳሴ ጊዜ እንደሚደረገው ሞጣህት ያለ ይለብሳል። በከፍተኛ ዝምታ (አርምሞ) ውስጥ የመኖር ግዴታ ውስጥ ራሱን ያስገባል። በስቅለቱ ጊዜ ከተቆጠሩ ነገሮች በቀር ጌታ ምንም እንዳልተናገረ ለዚህ መዓርግ ወይም ደረጃ የበቃ መነኮስም ከአስፈላጊ እና የግድ በእርሱ በቻ ሊነገሩ ከሚገባቸው ጉዳዮች ውጭ አይናገርም። ቢነቅፉትም፣ ቢሰድቡትም፣ ቢያምሰኙትም፣ እንደ አንሥተ ገሊላ ቢያለቅሱለትም ዝም በቃ ዝምምም ይላል። ይህ ሁሉ የሚሆነው መስቀል ለመሸከም መብቃቱን ለመናገር ነው። በሌላ ቋንቋ ለአስኬማ የደረሰ ማለት ጸዋሬ መስቀል የሆነ ማለት ነው። “ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ” /ገላ 6 ፡14/ ሲል ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው ራሱን መስቀል ላይ ያውላል፤
ትምክህቱም ያ መስቀል ይሆናል ማለት ነው።

በዚሁ አጋጣሚ ሞጣህት ራሱ ልብሰ አስኬማ ባይሆንም ያን የሚያሳይ ዓለምን ክጄ መስቀል ተሸክሚያለሁ ለማለት የሚደረግ ነበር እንጂ በዓለም ካለው ጌጥ የተሻለውን ተጠቅሞ ለፕሮቶኮል ወይም ልብስ ለማሳመር የሚደረግ አልነበረም ሲሉ ሰምቻለሁ። አሁን ደግሞ ሁሉ የሚያደርገው መሆኑ ከሚያሳዝናቸው የሰማሁት ነው። ይሁን አንድ ቀን ወደዚያ ስቦ ያደርሰን እንደሆነ ማን ያውቃል?

ታዲያ እስካሁንም ድረስ (ለምሳሌ በምሥራቅ ኦሮቶዶክሶች) በአስኬማ ጊዜ ለሁለተኛ ጊዜ ስማቸውን የሚለውጡ አሉ። በእኛ ግን ከአስኬማ በኋላ ስማቸው እንደገና የሚለወጥላቸው ወደ ጵጵስና የሚሔዱት ብቻ ናቸው። በሌላ ቋንቋ ጳጳሳት ሊሆኑ የሚገባቸው በተጋድሏቸው ለአስኬማ የደረሱ መሆን አለባቸው ወይም ነበረባቸው ለማለት ነው።

አቡነ ጴጥሮስም የተሰየሙት ቁልቁል ተሰቅሎ የጌታውን መስቀል ገንዘብ ባደረጋት በቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት ስም ነው። ስሙንም ያወጣው ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው /ማቴ 16 ፡ 18/ ። ጴጥሮስ የሚለው ስም በግሪክ ቋንቋ ነው እንጂ ትርጉሙ ዓለት ማለት ነው። ስለዚህ ስም የመቀየሩን ትውፊት የጀመረው ጌታ ሲሆን ስሙንም የሰጠው አንተ ብፁዕ ነህ፣ ይህን ሥጋና ደም አልገልለጠልህም በሰማይ ያለ አባቴ እንጂ በማለት ስያሜው ሰዎች ለጠቀስነው መዐርግ ሲበቁ ከሥጋና ደም ሲላቀቁ እንደተባለው ለጸዊረ መስቀል ሲበቁ መሆኑን አብሮ የመሠረተው ጌታ ነው።

ስለዚህ እርሳቸውም በዚህ ስም የተሰየሙት ራሳቸውንና ዓለምን ክደው ንጽሐ መላእክትን ገንዘብ አድርገው መስቀለ ክርስቶስን እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ተሸክመውታል ለማለት ነበር። መስቀላቸውን ተሸክመው በፋሺስት ወታደር በጥይት ሲደበደቡ ዓይናቸውን ሳይጨፍኑ እና ሳያፈገፍጉ ሞተ መስቀልን የቀመሱ በርግጥም ጸዋሬ መስቀል አማናዊ ጴጥሮስ ነበሩ።

እንግዲህ የአቡነ ጴጥሮስን ስም እንለውጠው የሚለው ሀሳብ ይህን ሁሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ተምረው፣ አውቀው እና አምነውበት በፈቃዳቸው ራሳቸውን ለክርስቶስ ሰጥተው በተግባር መስቀል የተሸከሙበትን ሕይወት ይህን እንዳላደረጉ ይቆጠር የሚል ክህደት መሆኑን ባለፊልሞቹ ያወቁ አይመስለኝም። በርግጠኝነት ለመናገር ባልደፍርም ይህን ማድረግ የሚፈልጉ ቢያንስ ጥቂቶቹ ሰዎች ይህ ስም በዓለም አቀፉ ጥንታዊ ክርስትና ውስጥ እንዲህ እንደ ነበር እና አሁንም እንደሆነ የሚያውቁ አይመስለኝም። በፖለቲካ ፐሮፓጋንዳ ስሙ የተቀየረ አማራ ለማድረግ ነው ብለው የነገሯቸው እውነት መስሏቸው እንጂ ስማቸውን ጌታ በመጽሐፍ ቅዱስ ያወጣው ፣ ቃሉም ግሪክ እንደሆነ እርሳቸውም ይህን ሰም የተቀበሉት ግብጽ ወርደው ሲሾሙ በግብጻውያን ጳጳሳት እንደሆነ አውቀው አይመስለኘም።

ለእነርሱ ይህ ሁሉ ትግል እና ፖለቲካ ነው። ሰውም ደግሞ ይሰማቸዋል። “እነርሱ ከዓለም ናቸው፤ ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ ዓለሙም ይሰማቸዋል” /1ኛ ዮሐ 4 ፡5/ ተብሎ የተጻፈው ለእነዚህ ነውና።

እኛም ድርጊቱን የምንቃወመው ለእነርሱ እንደመሰላቸው ይህ ስም እነርሱ የእኛ የሚሉትን የብሔር ስም ስለናቀ ሳይሆን እራሳቸው አቡኑ ራሳቸውንና ዓለምን ክደው በብፅዕና ያገኙት ስለሆነ ነው። እነርሱ ግን ስማቸውን ቢለውጡት ይህን ሁሉ አልደረሱበትም፣ ከዓለማቸውም አልወጡም ፣ ልክ እንደማንኛችንም ተራ ናቸው ብለው ሰማዕትነታቸው እያቀለሉ፣ ገድላቸውን እየካዱ እንደሆነም የሚገባቸው አይመስለኝም። እንዲህ ያለው ድርጊት አንድ የተወለደን ሕጻን ከመጸነሱ በፊት እናቱ ማሕፀን ሳለ እንቁላል፣ አባቱም ወገብ ሳለ ዘር ይባል ነበርና አሁን ሰውነቱ ቀርቶ በቀደመ እንቁላልነቱ ወይም ዘርነቱ ይጠራ የሚል ሞኝ ሰውን እንደሚያስመስል ባይረዱት ይሆናል።

የእነርሱ ይሁንና ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ማን ነው? አስኬማን ቀርቶ ምንኩስናን የጣላት ግን ማን ነው? ለሹመት የሚጋደልባት ማን ነው? ሀብት እና ንብረት የሚያፈራባት፣ ድርጅት ከፍቶ የሚነግድባት፣ ውርስ የሚያከፋፍልባት ማን ነው? በንብረት ፍርድ ቤት የሚሟገትባት ማን ነው? ከገዳም አውጥቶ የከተማ አስተዳደር ውስጥ የከተታት ማን ነው? በወንዝ እና በጎጥ በተቧደኑ ፖለቲከኞች እግር ሥር እየሮጠ እነርሱን በልጦ ለመታየት የሚታገለው ማን ነው? ከዚህ ሰውየ በላይ የሕይወት ዘመን ፍጻሜ ፊልም የሠራባት ማን ነው? ያን ሁሉ ውርደት እና ቅሌት እኛ ባናሳያቸው እነዚህም በየት አውቀውት ይመጡ ነበር? እንዴትስ ሊዳፈሩ ይችሉ ነበር?

የአቡነ ጴጥሮስን ስም ለማስከበር የሚቻለው አስኬማቸውን ማስከበር ሲቻል ይመስለኛል። ለፖለቲካም ይሁን ለገንዘብ፣ ለባህልም ይሁን ለታሪክ ፊልም ሊሠራ የተነሣው ሰው ድርጊቱን አውቆ እና አክብሮ መሥራቱ የበለጠ የሚጠቅመው ራሱን መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህ ሁሉ የመጣው ግን በእኛው ድክመት ነው። ጅቡ የገባው እኛው በቀደድነው አጥር በኩል ነው። የእርሱ ፊልም ቢቆም የቤታችን የሕይወት ዘመን ፊልም ግን አሁንም ይቀጥላል። ስለዚህ ተጠያቂነቱን ወስደን የቀደድነውን እንስፋ፣ የጣልነውን እናንሳ፣ ሥርዓቱ ይጠበቅ፤ ያን ጊዜ ወደ በረታችን ሾልኮ የሚገባ አውሬ አይኖርም። ስለዚህ ተጠያቂነቱን እገሌ እገሌ ሳንባባል ሁላችንም ቀድመን እንውሰደው።

እኔ እንደሚመስለኝ እንዲህ ያሉት ሰዎች እንዲያውም ማሳያዎች ቀስቃሾችም ይመስሉኛል። እግዚአብሔር ምን ያህል እንደአዘነብን፣ ምን ያህል እንደተቀየመን፣ ሁሉ ነገር መጫዎቻ እንደሆነ፣ ምንኩስና ፣ አስኬማ፣ ክህነት፣ ጵጵስና ሳይቀር መጫዎቻ እየሆነ መሆኑን አውቀን እንድንነቃ ከጥፋቱ በፊት የተላኩ መጥሪያዎች ቢሆኑስ? መቼ ነው ሥርዓት የምንገባው? ምንስ ሲሆን ነው የምንነቃው? መቼስ ነው የምንታረመው? እውነት እንናገር ከተባለ ጌታን የሰቀሉት አይሁድ ቢመጡ አይገረሙብንም? ፈሪሳዊያንስ አይስቁብንም? ሌላው ቀርቶ ጲላጦስና ሔሮድስስ አይደነቁብንም?

ታዲያ ተጠያቂው ማን ሊሆን ይገባዋል? እንግዲያውስ ለዚህ ሰውዬ የወጣችው ትእዛዝ ለሁሉም ቀላጆች ትውጣ ። እርሱን ብቻ ሳይሆን ከእርሱ በፊት የአቡኑን ስም ያረከስነውን ሁሉም ትሟገተን። ተጠያቂነቱ ለሁላችንም ይሁን። ካልሆነ የዛሬው ቢቆም ነገ በሌላ መንገድ ይቀጥላል። በአንዱ ተው ብንል በሌላው ይተገበራል። ባለፈው ጥቂት የማይባሉ ምእመናን ጉዳቱ በእውነት የቋንቋቸው የነገዳቸው ጉዳት የመሰላቸው እኮ አስኬማቸውን በተግባር የጣሉ ሰዎች ስለጠሯቸው ነው።

እውነት እንናገር ከተባለ አስኬማ የወለቅችው ከተገነዙባት የምንኩስና መግነዝ አምልጠው የወጡ ሰዎች ሕገ ቤተ ክርስቲያን ላይ ለኤጲስቆጶስነት ምርጫ የጎሣና የአካባቢ ሁኔታ ያስገቡ ጊዜ ነው። ያንን ተከትሎ ሰዎች በተወለዱበት አካባቢ ብቻ ይወዳደሩ፣ ይመደቡ፣ … የተባለ ጊዜ ነው ነገረ አስኬማ ስመ አስኬማ የተበላሸው። አስኬማ የወደቀችውማ ለጵጰስና የደረሱት ሳይቀር በብሔር እና ቋንቋ ተሰባስበው መንበር መሠረትን ሲሉ ነው። የጳጳሳትን ስም መጣል እና ማርከስ የጀመሩትም ጥቂት ቢሆኑም ጳጳሳት ናቸው። አስኬማማ የወደቀው እንደ ዮሐንስ ዓለምን ትተው በንጽሕ በበረሃ ሊኖሩ ከታጠቁት ቅናት በኋላ በየመንደር ፓርቲ ውስት ገብተው በየሰፈራቸው ሲሰባስቡ አይደለምን? በየሀገረ ስብከቱ ካለው መሳሳብ ፣ ሙስናና እና ጎጥኝነት በላይ በአስኬማ ላይ የሚሠራ ፊልም እና ስም አጥፊ ተግባር ይኖር ይሆን? ይህ ሁሉ ለጎጠኝነት ዕውቅና ክሚሰጠው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ጉድለት ሀ ብሎ የሚነሣ ይመስለኛል። ያን ጊዜ ነው አጥሩ የተቀደደው። እና ቀዳዳ ሲገኝ እንዴት አይገባ? መጀመሪያ የራስን አጥር ማጥበቅ፣
የቀደዱትን መስፋት ሳይኖር ዛሬ ለምን ገባህ ቢባል ምን ትርጉም አለው? ስለዚህ ነው ተጠያቂው ማን ነው የሚል ጥያቄ የረበሸኝ።

ማስታወሻ፦ ይህ ጽሑፍ ሆድ ብሶት ለመቀስቀስም ሆነ አሁን ቤተ ክህነቱ የያዘውን የሕግ ማስክበር ለመሞገት የተጻፈ አይደለም። የተጻፈው ጉዳዩ ቀዳዳችንን የሚያሳይ ስለሆነ እርሱ ይደፈን ለማለት እና ሌላ የባሰም ሳይመጣ አውቀን እንታረም ለማለት ያህል ብቻ የተጻፈ ነው። ካለበለዚያ ጊዜውን እየጠበቀ ኡ ኡ የሚያስብል ነገር እንደሚከታተል ለመናገር ነቢይ መሆን አይጠይቅም። አበቃሁ።

© ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ እንደጻፈው
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ዜና እረፍት

የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በኩረ ትጉኃን ዘርዓዳዊት ኃይሉ ባልታወቁ ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት አረፉ !

ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ጎንደር)

+++

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በኩረ ትጉኃን ዘርዓ ዳዊት ኃይሉ ባልታወቁ ኃይሎች በደረሰባቸው ጥቃት አረፉ !

ምንጭ:ተዋህዶ ሚድያ ማዕከል
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
Forwarded from Quality move bot
ተዋህዶ ሀይማኖቴ ነው ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ መረዳት መጻህፍትን ማንበብ እፈልጋለው የየእለቱን ስንክሳር ማንበብ እፈልጋለው ያለ ሁሉ ሊቀላቀላቀላቸው ሚገባ ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል 3 ቻናሎች
👇 ከታች Join በሉ
ሥርዓተ ማኅሌት ዘበዓለ ቅዱስ ኤልያስ ታኅሣሥ"፩"

የታህሳስ ኤልያስ

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሉ አለም፤በአሐቲ ቃል።

መልክአ_ሥላሴ፦
ሰላም ለእራኃቲክሙ እለ አኀዛ ዓለመ፤ደኃራውያን
ሥላሴ ወእለ ነበርክሙ ቅድመ፤ውስተ ልብየ አዝንሙ ዝናመክሙ ሰላመ፤ኤልያስሰ ኢወሀበኒ ዝናመ፤እምነ አሐዱ ገራህት ዘያረዊ ትልመ፡፡

ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ለአብ ንሴብህ ወልደ ዘንበሪ ለበዓል ሐነፀ፤ሃሌ ሉያ ለወልድ ወለመንፈስ ቅዱስ ለአማልክቲሁ ይሡቅ ቀነፀ፤ኤልያስ ነቢየ ደመና ስብሐት እምገጸ ሰማይ አርፈቀ፤ለወልደ ድንግል ርዕዮ እም ሐዋርያት ኢሐፀ፡፡

ነግሥ፦
ቀስተ ኪዳንከ ጽኑዕ ዘይባልሕ አመከራ፤እስመ መክብቦሙ እንተ ለትጉሃን ሰማይ ሐራ፤ቅዱስ ሚካኤል ድሙፀ ስብሐት ከመ እንዚራ፤ሰደኒ በአክናፊከ ውስተ ኤዶማዊት ደብተራ፤ኀበ ሀለዉ ኤልያስ ወእዝራ፡፡

ዚቅ፦
ሚካኤል መልአክ ደምረነ ዝክረ ኵሎሙ ቅዱሳኒከ፤እለ አስመሩከ በሥነ ምግባሮሙ በሕይወቶሙ፡፡

ነግሥ፦
ሰላም ለልደትኪ ወለተ ድኁሃን አድባር፤ለቤዝዎ ኵሉ ፍጡር፤ወሪደኪ ምድረ እምሉዓላዊት ሃገር፤
እንዘ ይዌድሱኪ በቃለ ሐዋዝ መዝሙር፤ኤልያስ በታቦር ወሙሴ በደብር፡፡

ዚቅ፦
ኦ ቡርክት እምኵሉ ፍጥረት፤አንቲ ውእቱ ህየንተ አርያም ዘበሰማት፤ዘኮንኪ አርያመ በዲበ ምድር
ብኪ አስተማሰሉ ቅዱሳን ነቢያት ካህናት ወነገሥት፤ገብሩ ሎሙ ቅድስተ ቅዱሳን ወውስቴታ ጽላተ ኪዳን ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

መልክአ ኤልያስ፦
ሰላም ለስንከ ኅብስተ ሕይወት ዘየኀይከ፤ምእረ ወካዕበ በእደ ቅዱስ መልአክ፤ለለጽባሑ ኤልያስ
እንተ ኢትትዌልጥ ዐርከ፤ሀቦሙ ለአግብርቲከ ሱላሜ ዘሠርክ፤ውስተ ማኅበሮሙ ኢይምጻእ ሐከከ፡፡

ዚቅ፦
ወሰሚዖ ራጉኤል ከመ ገብአ ኤልያስ እምሰብእ ወሰደ ሎቱ ኅብስተ ወወይነ ኤልያስኒ ተክለ ሀይመቶ ወተመጠወ እምውእቱ ኅብስት
ውእቱ ጸዋዕ በአምሳለ ሥጋሁ ወደሙ ለክርስቶስ፡፡

መልክአ ኤልያስ፦
ሰላም እብል ኩልያቲከ ምንትወ፤ርእስ ሕያዋን ኤልያስ እንተ ትገብር ሕያወ፤በዕለተ ጸዋዕከ አባ እምኑኀ ሰማያት ሐወ፤በልአ መሥዋዕቲከ ምስለ አእባን ዕፈፀወ፤ወምስለ ማዩ ለሐሰ እዳወ፡፡

ዚቅ፦
ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ፤ከመ መዓዛ ሠናይ፤ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኀ ሰማይ፡፡

መልክአ ራጉኤል፦
እጼውዕ ስመከ ወእኤምሀከ በተድላ፤ራጉኤል መልአክ ለዓለም መስተበቅላ፤እለ ያንኲረኵሩ ዘልፈ ለጠፈረ ሰማይ በማእከላ፤ድኅረ ኀለፈ መዓልት ለጽልመተ ሌሊት በክፍላ፤ለሥልጣነ ቃልከ ይትኤዘዙ ከዋክብት ወእብላ፡፡

ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ፥ሃሌ ሉያ፤ዓቢተነ በመድኀኒትከ፤ጸገወነ ንጸዉዕ ስመከ፤ኖላዊነ ኄር ትጉሕ ዘኢትነውም
ሰላመከ ሀበነ፡፡

መልክአ ኤልያስ፦
ሰላም ለእስትንፋስከ እስትንፈሰ እሳት በላዒ፤ኆኅተ አፉከ አኮ እምንፍኀተ ላህቡ ዘያውዒ፤መንፈስ እንተ ዘኢታስተርኢ፤ራጉኤል ካህን ራማ ጸሎተ ቅዱሳን ሠዋዒ፤ጽራሕየ ለቡ ወቃልየ አዒ፡፡

ዚቅ፦
ርድአኒ ወአድኅነኒ ወስመር ብየ፤በከመ ሠመርኮሙ ለቅዱሳን አበውየ፡፡

አንገርጋሪ፦
ጽሑፍ አስማቲሆሙ ለጻድቃን ወዓዲ ይቀድም መልአክ ገጾሙ በሰማያት ኀበ ዓምደ ወርቅ ኀበ ሀለዉ ኄኖክ ወኤልያስ በሕይወቶሙ፡፡

እስመ ለዓለም፦
ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ፤ወከመ ያብርሀ ብርሃነ ስብሐቲሁ በላዕሌነ፤እስመ በጾም ኤልያስ ሰማያተ ዐርገ፤ወዳንኤል እምአፈ አናብስተ ድኅነ፤ንጹም ጾመ ፍፁመ ወናፍቅር ቢጸነ፤ወናክብር ሰንበቶ ለአምላክነ፡፡

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
Forwarded from Quality move bot
ተዋህዶ ሀይማኖቴ ነው ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ መረዳት መጻህፍትን ማንበብ እፈልጋለው የየእለቱን ስንክሳር ማንበብ እፈልጋለው ያለ ሁሉ ሊቀላቀላቀላቸው ሚገባ ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል 3 ቻናሎች
👇 ከታች Join በሉ
✞ ኤልያስ በሰረገላ ✞
♡ የመዝሙር ግጥሞች ♡
✞  ኤልያስ በሰረገላ  ✞

ኤልያስ በሰረገላ ሰወረው ደመና(፪)
ደመና ደመና በሰረገላ(፪)

በመንፈስ ቅዱስ ሃይል---በሰረገላ
ታንፃ በስሙ-------------በሰረገላ
ይታደሉባታል------------በሰረገላ
ጽድቅና ስላመኑ---------በሰረገላ
ቤተክርስቲያን ሆይ------በሰረገላ
የእግዚአብሔር ስጦታ---በሰረገላ
አነጸሽ በደሙ------------በሰረገላ
አማኑኤል ጌታ-----------በሰረገላ
ደመና ደመና በሰረገላ(፪)
          አዝ= = = = =
በሰማይ ለሚኖር------------በሰረገላ
የእግዚአብሔር መንግስት--በሰረገላ
መገለጫ ይሁን-------በሰረገላ
የምድር በረከት-------በሰረገላ
የቅዱሳን አምላክ----በሰረገላ
እድሮ ሚኖርባት-----በሰረገላ
መላእክትና ሰው----በሰረገላ
ያመሰገኑባት------በሰረገላ
ደመና ደመና በሰረገላ(፪)
          አዝ= = = = =
የሕይወት መገኛ---------በሰረገላ
የፅድቅ ታዛ ነሽ---------በሰረገላ
አጌጥሽ በመንፈሱ-------በሰረገላ
በደሙ ተሰርተሽ---------በሰረገላ
አምላክ ተገለጠ--------በሰረገላ
ከሰማያት ወረዶ--------በሰረገላ
ስርየት አግኝተናል------በሰረገላ
ባንቺ ተዋህዶ---------በሰረገላ
ደመና ደመና በሰረገላ(፪)
          አዝ= = = = =
ሁሉን አሳልፋ----------በሰረገላ
ፀንታ የኖረች----------በሰረገላ
ከቶ ስትናወጥ--------በሰረገላ
በሲኦል ደጆች--------በሰረገላ
የዳቢሎስ ሴራ-------በሰረገላ
ቀስቱ ያልነካት-------በሰረገላ
ያልተቀላቀለች-------በሰረገላ
ተዋህዶ ንፅሂት-----በሰረገላ

ደመና ደመና በሰረገላ  ደመና ደመና በሰረገላ
በሰረገላ በሰረገላ በሰረገላ ተሰውረው ደመና(፫)

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ሥርዓተ ዋዜማ አመ ፫ ለታኅሳስ በአታ ለማርያም

ዋዜማ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝኔኪ፤ርስዒ ሕዝቤኪ ወቤተ አቡኪ፤እስመ ፈተወ ንጉሥ ስነኪ፤ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል፤ወይቤ፤ዝየ አኃድር እስመ ኃረይክዋ።

ምልጣን፦
እስመ ፈተወ ንጉሥ ስነኪ፤ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል፤ወይቤ ዝየ አኃድር እስመ ኃረይክዋ፤ወይቤ ዝየ አኃድር እስመ ኃረይክዋ።

አመላለስ፦
ወይቤ ዝየ አኃድር እስመ ኃረይክዋ/፪/
ወይቤ ዝየ አኃድር/፬/

በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ:-
ሰዓሊ ለነ ማርያም እንተ እግዚእ ኃረያ ሰዓሊ ለነ ማርያም።

እግዚአብሔር ነግሠ
በከመ ይቤ ኢሳይያስ ነቢይ ናሁ ይወርድ እግዚአብሔር ዉስተ ምድረ ግብፅ ተጽዕኖ ዲበ ደመና ቀሊል ደመናሰ ዘይብል ይእቲከ ድንግል ዘኃዘለቶ በዘባና ለአማኑኤል።

በ፭ እግዚኦ ጸራሕኩ ኃቤከ
ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን።

ይትባረክ
እግዚእትየ እብሌኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ ቃል ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ።

፫ት
ረከብናሃ በዖመ ገዳም በሣዕናሃ ትኩነነ መርሐ እንዘ ገዳመ ትነብር ወታስተኃዉዝ ዉስተ አድባር ሐገሩ ይእቲ ለንጉሰ ስብሐት።

ሰላም በ፫
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኲሉ ነገራ በሠላም ወኲሉ ነገራ በሠላም ሰላማዊት ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ወኲሉ ነገራ በሠላም ጥዕምት በቃላ ወሠናይት በምግባራ ወኲሉ ነገራ በሠላም ወኲሉ ነገራ በሠላም ንጽሕት ይእቲ በድንግልና አልባቲ ሙስና ዕራቊ ደመና ወኲሉ ነገራ በሠላም ማርያም ታዕካ በምድር ወታዕካ በሰማይ።

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፫ ለታኅሣሥ በዓታ ማርያም

የታህሳስ በዓታ ለማርያም


የየትኛውም ሥርዓተ ማህሌት መጀመርያ ነግስ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
ለማርያም ዘምሩ፤ለማርያም ዘምሩ፤መስቀሎ ለወልዳ እንዘ ትጸውሩ።

አመላለስ
ለማርያም ዘምሩ/፪/
ለማርያም ዘምሩ/፬/

መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል፤እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል
ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ወብሥራት ለገብርኤል፤ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።

አመላለስ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል/፫/
ወብሥራት ለገብርኤል/፫/

መልክዐ ኪዳነ ምሕረት(ነግሥ)
ሰላም ለእራኅኪ ተመጣዌ ኅብስት ወማይ፤ሶበ ያመጽኡ ለኪ መላእክት ሰማይ፤እንዘ ሀሎኪ ማርያም ወመቅደሰ ኦሪት ዐባይ፤ይትወከፍ ሊተ ኪዳንኪ ከመ መሥዋዕት ሠርክ ኅሩይ፤ለእመ ኅፍነማይ አስተይኩ ለጽሙዕ ነዳይ።

ዚቅ
አንቲ ውእቱ ንጽሕት እምንጹሐን፤ዘነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ከመ ታቦት፤ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ፤ስቴክኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ፤ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ።

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ።

ዚቅ
ወመሠረቱ ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ፤ዕጓለ አንበሳ ዕጓለ አንበሳ በከርስኪ ፆርኪ፤እምአንስት ቡርክት አንቲ።

አመላለስ
ወመሠረቱ/፪/
ወመሠረቱ ለዓለም አንቲ/፪/

ነግሥ
መቅደሰ ኦሪት ዘቦዕኪ ማርያም እምነ፤ወእሙ ለእግዚእነ፤በሕፅነ ሐና ተማኅፀነ፤ፈንዊዮ ለፋኑኤል ይዕቀብ ኪያነ፤በረምሃ መስቀል ረጊዞ ሰይጣነ።

ዚቅ
ፈንዊ ለነ እግዚእትነ፤ፋኑኤልሃ መልአከኪ ሄረ፤በኃይለ ጸሎቱ ይዕቀበነ ወትረ።

አመላለስ
ፈንዊ ለነ እግዚእትነ/፪/
ፋኑኤልሃ መልአከኪ ሄረ/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።

ዚቅ
ይዌድስዋ ኲሎሙ በበነገዶሙ፤ወበበማኅበሮሙ ለቅዱሳን፤ወይብልዋ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ።

ወረብ
"ይዌድስዋ ኲሎሙ"/፪/በበነገዶሙ/፪/
ወይብልዋ በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም ለልሳንኪ ሙኀዘ ኃሊብ ወመዓር፤ዘተነብዮ ወፍቅር፤ማርያም ድንግል ወለተ ድኁኃን አድባር፤ኅብእኒ እምዓይነ ፀር ወአንጽሕኒ እምነውር፤እስመ ተስፋየ አንቲ በሰማይ ወምድር።

ዚቅ
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍርኪ፤ኃሊብ ወመዓር እምታሕተ ልሳንኪ፤ወይቤላ ንዒ ንሑር ኀበ ደብረ ከርቤ፤ውስተ አውግረ ስኂን።

ወረብ
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍርኪ እምከናፍርኪ ኃሊብ ወመዓር እምታሕተ ልሳንኪ/፪/
ወይቤላ ሊቀ መላእክት ፋኑኤል ለማርያም ንዒ ንሑር ኀበ ደብረ ከርቤ ወደብረ ብርሃን/፪/

ወረብ ፪
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍርኪ ኃሊብ ወመዓር እምታሕተ ልሳንኪ/፪/
ወይቤላ ንዒ ንሑር ኀበ ደብረ ከርቤ ደብረ ገነት /፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም ለእመታትኪ እለ ፀንዓ ይፍትላ፤ሜላተ ወወርቀ በናዝሬት ወበገሊላ፤ማርያም ድንግል ለዮዲት ጥበበ ቃላ፤ብጽሂ በሠረገላ ንትመኃል መኃላ፤ከመ ታኅድርኒ በብሔር ዘተድላ።

ዚቅ
ገብርኤል መልአክ መጽአ፤ወዜነዋ ጥዩቀ፤በዕንቊ ባሕርይ እንዘ ትፈትል ወርቀ።

አመላለስ
ገብርኤል መልአክ መጽአ/፪/
ወዜነዋ ጥዩቀ/፬/

ወረብ
ገብርኤል መልአክ መጽአ"ወዜነዋ"/፫/ጥዩቀ/፪/
"በዕንቊ ባሕርይ"/፫/እንዘ ትፈትል ወርቀ/፪/

መልክአ ማርያም
ሰላም ለአብራክኪ በስብሐተ ልዑል ዘአስተብረካ፤እምአመ ወሀቡኪ ብፅአ ውስተ ኦሪታዊት ታዕካ፤ማርያም ድንግል መንበር ዘእብነ ፔካ፤ጊዜ ስደቶሙ ለኃጥአን እምዓጸደ ዓባይ ፍሲካ፤ጼውውኒ መንገሌኪ እኩንኪ ምህርካ።

ዚቅ
እንዘ ዘልፈ ትነብር ውስተ ቤተ እግዚአብሔር፤አስተርዓያ መልአክ፤ዘኢኮነ ከመ ቀዲሙ፤ግሩም ርእየቱ፤ኢያውአያ እሳተ መለኮት።

ወረብ
እንዘ ዘልፈ ትነብር ውስተ ቤተ እግዚአብሔር/፪/
አስተርአያ መልአክ ዘኢኮነ ዘኢኮነ ከመ ቀዲሙ ኢኮነ/፪/

መልክአ ማርያም
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ፤ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ፤ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ፤ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ፤ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ።

ዚቅ
ናሁ ተግህደ ልዕልናሃ ለወለተ ሀና፤ኅብስተ ሕይወት ተጸውረ በማኅጸና፤ጽዋዓ መድኃኒት፤ዘአልቦ ነውር ወኢሙስና፤እፎ አግመረቶ ንስቲት ደመና፤ኢያውአያ በነበልባሉ፤ወኢያደንገጻ በቃሉ፤አላ ባሕቱ ትብራህ፤ረሰያ ዘበጸዳሉ፤ይዜኑ ብሥራተ፤መልአኮ ፈነወ፤ዮም ተሠገወ በከመ ተዜነወ።
ወረብ
ናሁ ተግህደ ልዕልናሃ ለወለተ ሀና/፪/
ኅብስተ ሕይወት ተጸውረ በማኅጸና/፪/

ማኅሌተ ጽጌ
የኃዝነኒ ማርያም ዘረከበኪ ድክትምና፤አመ ቤተ መቅደስ ቦዕኪ እንዘ ትጠብዊ ኃሊበ ሀና፤ወያስተፌሥሐኒ ካዕበ ትእምርተ ልኅቀትኪ በቅድስና፤ምስለ አብያጺሁ ከመ አብ እንዘ ይሴስየኪ መና፤ፋኑኤል ጽጌ ነድ ዘይከይድ ደመና።

ዚቅ
ንጽሕተ ንጹሐን ከዊና፤ከመ ታቦተ ዶር ዘሲና፤ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በቅድስና፤ሲሳያ ኅብስተ መና፤ወስቴሃኒ ስቴ ጽሙና።

ወረብ
ንጽሕተ ንጹሐን ከዊና እመ አምላክ/፪/
ውስተ ቤተ መቅደስ ነበረት በቅድስና ነበረት በቅድስና/፪/

አንገርጋሪ
ጽርሕ ንጽሕት ማርያም፤ተፈሥሒ ሀገረ እግዚአብሔር፤ቃል ቅዱስ ይወጽእ እምኔኪ፤አእላፍ መላእክት ይትለአኩኪ።

ምልጣን
ቃል ቅዱስ ይወጽእ እምኔኪ፤አእላፍ መላእክት ይትለአኩኪ።

እስመ ለዓለም
በጽሐ ሠናይ ወአልፀቀ ዘመን፤ወበዓላ ለቅድስት ማርያም፤እንተ በላዕሌሃ ተመርዓወ ቃል፤አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ፤ወይቤላ መልአክ ተፈሥሒ ፍሥሕት፤ቡርክት አንቲ እምአንስት፤አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ፤ይመጽእ ላዕሌኪ መንፈስ ቅዱስ፤ወኃይለ ልዑል ይጼልለኪ፤አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ፤ዘኒ ይትወለድ እምኔኪ ቅዱስ ውእቱ፤ወይሰመይ ወልደ እግዚአብሔር፤አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ፤ኢሳይያስኒ ይቤላ ቅንቲ ሐቌኪ፤ወልበሲ ትርሢተ መንግሥትኪ፤አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ፤ዳዊትኒ ይቤላ በአልባሰ ወርቅ፤ዑጽፍት ወኁብርት፤አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ፤ይሰግዱ ለኪ ኵሎሙ ነገሥታተ ምድር፤ወይልህሱ ጸበለ እግርኪ፤አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ፤ወተወልደ እምኔሃ፤ወይቤላ ንዒ ርግብየ ሠናይት፤ንባብኪ አዳም።

ወረብ ዘእስመ ለዓለም
"በጽሐ ሠናይ ወአልፀቀ ዘመን"/፪/ወበዓላ ለቅድስት ማርያም/፪/
እንተ በላዕሌሃ ተመርዓወ ቃል አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ/፪/

ወረብ ዘእስመ ለዓለም
ይቤላ መልአክ ተፈሥሒ ፍሥሕት ተፈሥሒ ፍሥሕት ይቤላ መልአክ/፪/
ቡርክት አንቲ እምአንስት አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ ኀደረ/፪/

ወረብ ዘእስመ ለዓለም
ይመጽእ ላዕሌኪ መንፈስ ቅዱስ ኃይለ ልዑል ይጼልለኪ/፪/
አንጺሖ ሥጋሃ ኀደረ ላዕሌሃ መንፈስ ቅዱስ/፪/

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
Audio
እውነት ነጻ ታወጣችኋለች 
                                                  
Size:- 54.7MB
Length:-2:37:11
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from Quality move bot
ተዋህዶ ሀይማኖቴ ነው ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ መረዳት መጻህፍትን ማንበብ እፈልጋለው የየእለቱን ስንክሳር ማንበብ እፈልጋለው ያለ ሁሉ ሊቀላቀላቀላቸው ሚገባ ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል 3 ቻናሎች
👇 ከታች Join በሉ
#የፍቅር_ሥራ_ይህች_ናት

ባልንጀራውን የሚረዳውን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ይረዳዋል፡፡ ለወንድሙ የሚነቀፍበትን ስም የሚያወጣውን ፈታሒ በርትዕ እግዚአብሔር እንዲሰደብ ያደርገዋል፡፡ ክፉ ስለ ሠራ ወንድሙን በቤቱ ለብቻው ሆኖ የሚመክረው ሰው ግን በምክሩ ዐዋቂ ይሆናል፡፡ ወንድሙን በዐደባባይ የነቀፈ ግን ኀዘን ያጸናበታል፡፡ ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ብዛት ያስረዳል፤ በባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት አስረዳ፡፡

ወዳጁን ተሠውሮ የሚመክር ሰው ብልህ ባለመድኃኒት ነው:: ያ እንዳዳነው መክሮ አስተምሮ ያድነዋልና፡፡ ወንድሙን በብዙ ሰው ፊት የሚያመሰግነው ሰው እሱ እውነተኛ ጠላቱ ነው፣ በውዳሴ ከንቱ ይጎዳ ብሎ ነውና።

ኀዘን ያለበት የርሕራሄ ምልክቱ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ማለት ነው። የጠማማ ምልክቱ ጸብ ክርክር ነው፡፡ ወደ ክብር የሚያደርስ ረብህ ጥቅም ያግኝ ብሎ የሚመክር፣ የሚያስተምር በፍቅር ይመክረዋል፣ ያስተምረዋል፡፡ ቂም በቀል የሚሻ ሰው ፍቅር የለውም፡፡ አንድም እበቀለዋለሁ ብሎ የሚመክር ከፍቅር የተለየ ነው፡፡

ስሙ ይክበርና እግዚአብሔር በፍቅር ይመክራል፣ ያስተምራል፣ እበቀላለሁ ብሎ ያይደል፡፡ እሱስ በምሳሌው የተፈጠረው ሰውን ለማዳን ይገሥጻል፡፡ አንድ ጊዜስ እንኳን ቂም አይዝም፣ መዓትን አያዘጋጅም፡፡ የፍቅር ሥራ ይህች ናት፣ በቅንነት ትገኛለች፡፡ ቂም ለመያዝ እበቀላለሁ አትልም፣ በፍቅር ሰውን መናገር ነው።

ብልህ የሚሆን ቅን ሰው ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይመስለዋል፡፡ ሰውን ክፉ ስላደረገ እበቀለዋለሁ ብሎ አይገሥጸውም፣ ሊመክረው ወዶ ነው እንጂ ሌሎችንም ለማስፈራት ነው እንጂ። ተግሣጽስ በፍቅር ካልሆነ ተግሣጽ አይባልም፡፡ በጎ ነገር ያደርግልኛል ብሎ በጎ የሚሠራ ኋላ ፈጥኖ ይተዋል፡፡

(#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ - በዲ/ን ሞገስ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"የማርን ጥፍጥና ማርን ቀምሶ ለማያውቅ ሰው በመቅመስ እንጂ በቃላት ማስተማር እንደማይቻል ሁሉ የእግዚአብሔርን መልካምነት በቃላት በጠራ መልኩ ማስተማር አይቻልም። ራሣችን ወደ እግዚአብሔር መልካምነት ዘልቀን መግባት ይኖርብናል እንጂ።"

ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ - #መንፈሳዊው_መንገድ መጽሐፍ #አያሌው_ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#መጽሐፍ_ቅዱስ

በአንድ ተራራማ ስፍራ እርሻ በማረስ ከልጅ ልጁ ጋር የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበር፡፡ ይህ ሽማግሌ ዘወትር ፀሐይ ብርሃኗን ስትፈነጥቅ እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ያነባል፡፡ የልጅ ልጁ የአያቱን ተግባር ይከታተል ስለነበር እሱም ያያቱን ፈለግ በመከተል ጠዋት ጠዋት እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱን ማንበብ ጀመረ፡፡

አንደ ቀን ታድያ አያቱን “አባባ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እየሞከርኩ ነበር፡፡ ነገር ግን ልረዳው አልቻልኩም ደግሞም አንብቤ እንደጨረስኩ ወዲያውኑ እረሳዋለሁ እናም እንድረዳውና እንዳልረሳው ምን ማደረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቀ፡፡

ሽማግሌው ምንም ድምጽ ሳያሰሙ “ከሰሉን ወደ ምድጃው ጨመሩና እንካ ይሄን የከሰል ቅርጫት ይዘህ ወንዝ ውረድና ውሃ ይዘህልኝ ተመለስ” አሉት፡፡ ልጁ ትዛዙን ለመፈጸም ወደወንዝ ወርዶ ውሃውን ይዞ ሊመለስ ቢመክርም ቅርጫቱ ውሃውን እያንጠባጠበ ቤት ከመድረሱ በፊት ፈሶ አለቀበት፡፡ ሽማግሌው የልጁን ሁኔታ እያስተዋሉ “አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ይዘህ ስትመጣ ግን ፈጠን ፈጠን ብለህ ተመሰለስ ብለው”
ድጋሜ ላኩት፡፡ አሁንም ልጁ እንደተነገረው በፍጥነት ውሃውን ቀድቶ ሊመለስ ቢሞክርም ቤቱ ሳይደርስ ውሃው ፈሶ አለቀበት፡፡ አያቱንም “በቅርጫት ውሃ ማምጣት ስለማይቻል ሌላ መያዥ ይስጡኝና ላምጣ” ሲል ጠየቀ፡፡ ሽማግሌ አያቱም “እኔ የምፈልገው የቅርጫት ውሃ ነው፡፡ ጠንክረህ ባለመሞከርህ ነው ፈሶ ያለቀብህ” በማለት እንደገና ላኩት፡፡ በዚህ ጊዜ ልጁ በቅርጫት ውሃን ማምጣት እንደማይቻል ቢያውቅም ለአያቱ ታዛዥነቱን ለማሳየት ከበፊቱ ፈጥኖ ለማምጣት ሲሞክር ውሃው ፈሶ ስላለቀበት ባዶውን ቅርጫት እያሳየ “ተመልከት አባባ! እዲሁ ነው የምደክመው እንጅ እኮ ጥቅም የለውም” አለ፡፡

ከዚህ ጊዜ ምልልስ በኋላ ሽማግሌው “እስኪ ቅርጫቱን ተመልከተው” አሉት፡፡ ልጁ ቅርጫቱን ሲመለከት ከዚህ በፊት የማያውቀው ቅርጫት ይመስል ቅርጫቱ የተለየ ሆነበት የከሰል መያዣ እያለ በጅጉ የቆሸሸ ነበር፡፡ አሁን ግን ሙልጭ ብሎ ጸድቷል፡፡ ውስጡን ሲመለከተው ከመንጻቱ የተነሳ የበፊቱ ቅርጫት አልመስለው አለ፡፡

ስለዚህ ልጄ መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ የሚሆነው እደሱ ነው፡፡ ላትረዳው ትችል ይሆናል ወይም ደግሞ ያነበብከውን ሁሉንም ነገር ላታስታውሰው ትችል ይሆናል ዳሩ ግን ባነበብክ ቁጥር ለውጨኛው የሚተርፍ ውስጣዊ ንጽህና እያመጣህ መሆኑን አትዘንጋ የመንፈስ ሥራ እንደዚህ ነው በማለት አስተማሩት፡፡

(ከምስጋናው ግሸን ወልደ አገሬ)

(በድጋሚ የተፖሰተ)
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
አንድ ሰው መጥቶ እናንተ የምትለብሱትን አንዲት ቁራጭ ልብስ እንኳ ሳይሰጣችሁና ሰውነታችሁ በብርድና በዋዕየ ፀሐይ እየተቆራመደ ሳለ ቤታችሁን በወርቅና በተንቆጠቆጠ የመጋረጃ ዓይነት ቢያስጌጥላችሁ ምን ጥቅም አለው? እኛስ ነፍሳችን ዕራቁቷን ሳለች ሥጋችንን ወርቅ ብናለብሰው በወርቅ ብናስተኛው ምን ትርጉም አለው? ነፍሳችን በመሬት ላይ እየተንፏቀቀች ሳለ ሥጋችን በከበሩ ሠረገላዎችና የተለያዩ ማጓጓዣዎች ብትንፈላሰስ ምን ጥቅም አለው?

ልጆቼ ! እውነተኛውን ልብስ ልበሱ ብዬ እመክራችኋለሁ። እዚህ የሚቀረውን ሳይኾን ዘለዓማዊውን ልብስ ልበሱ። የሰርጉን ልብስ ልበሱ።

እስኪ በየገዳማቱ ሒዱና ይህን ከቅዱሳን አበው ወእማት ተማሩ። እነዚህ ቅዱሳን በእልፍ ወትእልፊት ዕንቁ የተሽቆጠቆጠ ልብስ ብትሰጥዋቸው አይቀበሏችሁም። ለምን? እነርሱ ጋር ያለው ልብስ እናንተ ይዛችሁት ከሔዳችሁት ይልቅ በእጅጉ እንደሚበልጥ ስለሚያውቁ! ይኸውም የነፍሳቸው ልብስ ማለቴ ነው።

ለእነርሱ ይዛችሁት የሔዳችሁት ልብስ ለአንድ ምድራዊ ንጉሥ ብትሰጡት እጅግ ያመሰግናችኋል። እነርሱ ግን ከዚህ ንጉሥ በላይ በከበረ ልብሱ ያጌጡ ናቸውና አይቀበሏችሁም። ወርቃቸውን ወደሚያስቀምጡበት መዝገብ (ልቡናቸው) ገብታችሁ ስታዩ'ማ ራሳችሁን ስታችሁ ትወድቃላችሁ ። የሀብታቸውን (ምግባር ትሩፋታቸውን) ብዛት የወርቃቸውን ንጻት እንዲህ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም ። እናንተም ከእነርሱ ተማሩና እውነተኛውን ልብስ ለመልበስ ተሽቀዳደሙ ።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ)
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ጴጥሮስን ለታላቅ ንስሓ የቀሰቀሰው የዶሮ ጩኸት ነበር ... ‹የዶሮ ጩኸት ጴጥሮስን ለንስሓ አበቃው› የሚለው ታሪክ ከዶሮ ጩኸት አልፎ እልፍ ሰባኪያን ‹ንስሓ ግቡ› እያሉ ሲጮኹ እየሰማን ምንም ለማይመስለን ለእኛ ለልበ ደንዳኖቹ መልእክቱ ምን ይሆን? የዶሮዎቹን ጩኸት ሰምቶ በመመለስ ፈንታ የዶሮዎቹን የአጯጯህ ስልት እያወዳደርን ሰባኪያን ለምናማርጥ ለእኛ መልእክቱ በእርግጥ ምን ይሆን?

በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡ አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሓ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው? ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሓ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡

(ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ - ሕማማት መጽሐፍ የተወሰደ)
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
2024/09/22 18:24:06
Back to Top
HTML Embed Code: