Telegram Web Link
አመ ፳ወ፭ ለህዳር ለቅዱስ መርቆሬዎ ስርዓተ ማኅሌት

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሉ አለም፤በአሐቲ ቃል።

ነግስ
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።

ዚቅ
ሠራዊተ መላእክቲሁ ለመድኃኔ ዓለም፤ይቀዉሙ ቅድሜሁ ለመድኃኔ ዓለም፤ወይኬልልዎ ለመድኃኔ ዓለም፤ሥጋሁ ወደሙ ለመድኃኔ ዓለም፤ወንብጻሕ ቅድመ ገጹ ለመድኃኔ ዓለም፤በአሚነ ዚአሁ ሰማዕታት ከዓዉ ደሞሙ በእንቲአሁ።

ዓዲ ዚቅ
፩ዱ አብ ቅዱስ ፩ዱ ወልድ ቅዱስ፤፩ዱ ዉእቱ መንፈስ ቅዱስ ዘአድኃኖሙ ለሰማዕት።

መልከአ ሚካኤል (ነግስ)፦
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤ለረዲኦትየ ከመ ዘይሰርር ዖፍ፤እንዘ ትሰርር ነዓ በክልዔ አክናፍ።

ዚቅ
ሚካኤል መልአክ ወረደ እምሰማይ፤ኀበ ቅዱስ መርቆሬዎስ፤ወአጥፍአ ኃይለ እሳት፤ወኢለከፎ ስጋሁ።

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት፤ወያሚሆሙ ለካህናት፤ነያ ጽዮን መድኃኒት።

መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለዝክረ ስምከ ገብረ ኢየሱስ ብኢል፤ወለስርዕትከ ጸሊም ዘቆናዚሁ ፍቱል፤መርቆሬዎስ ሰማእት ገባሬ ተአምር ወኃይል፤ለዮሐንስ ፍና ድኂን ከመ መራህኮ በኀቅል፤ምርሀኒ ለወልድከ ፍና ጽድቅ ወሣህል።

ዚቅ
ወሀሎ ፩ዱ ብእሲ ዘስሙ ፒሉፖዴር፤ዘበትርጓሜሁ መርቆሬዎስ ብሂል፤ነገረ ገድሉ መዓርዒር ለተናግሮ ዕፁብ ግብር፤ወዲበ ርእሱኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል።

ወረብ
ወሀሎ ፩ ብእሲ ዘስሙ ፒሉፖዴር ዘበትርጓሜሁ መርቆሬዎስ ብሂል፤
መዓርዒር ለተናግሮ ተናግሮ ዕፁብ ግብር።

መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለከናፍሪከ ወለአፉከ ዘተናገረ፤ዕበደ ዕልው ዳኬዎስ ወኀጒለ አርዳሚስ ድህረ፤መርቆሬዎስ ሰማእት አመ አፆሩከ ፆረ፤ተዐገስከ እስከ ለሞት እንዘ ትትዌከፍ ሐሣረ፤በዓለመ ተስፋ ሐዳስ ከመ ትንሣእ ክቡረ።

ዚቅ
ዘሕማማተ እግዚኡ መዋቅሕተ ፆረ፤ወርእሶ አምተረ ዓቢያተ ተናገረ፤አስተምህር ለነ ዮሐንስ ዘአጥመቀ ቃለ።

ወረብ
ዓቢያተ ተናገረ ወርእሶ አምተረ ዘሕማማተ እግዚኡ መዋቅሕተ ፆረ፤
አስተምህር ለነ መርቆሬዎስ ዘሰበከ ቃለ።

መልክአ መርቆሬዎስ
ሰላም ለልብከ ወለኅሊናከ ዘሐለየ፤በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትትዌከፍ ሥቃየ፤መርቆሬዎስ ሥዕልከ ከመ ጽንዐ ኃይሉ አርአየ፤ላዕለ ዑልያኖስ መዓምፅ አመ ባስልዮስ ጸለየ፤ኃይለ ረድኤትከ ይርአይ ዓላዊ ፀርየ

ዚቅ
ጸልዩ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ ኀበ ሥዕሉ ለቅዱስ መርቆሬዎስ፤ደነነ ሥዕል ከመ ኦሆ ዘይብል፤ ሰምዖሙ ጸሎቶሙ፤ወቀተለ ፀሮሙ።

ወረብ
ጸልዩ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ ኀበ ሥዕሉ ለቅዱስ መርቆሬዎስ፤
ደነነ ሥዕል ከመ ኦሆ ዘይብል ወተፈሥሑ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ

ወረብ ዓዲ፦
ጸልዩ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ ኀበ ሥዕሉ ለቅዱስ መርቆሬዎስ፤
ደነነ ሥዕል ከመ ኦሆ ሰምዖሙ ጸሎቶሙ

መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለጸአተ ነፍስከ ድኀረ ፈጸሙት ህማመ፤በአፈ ጕድብ ሰይፍ በሊህ አመ ክሣዳ ተገዝመ፤መርቆሬዎስ ቅድሜከ ሶበ እግረ ልብየ ቆመ፤ሐውፀኒ ለለጽባሑ ወጸግወኒ ሰላመ፤እስመ ረሰይኩከ አበ ወሰናይት እመ።

ዚቅ
መጠወ ነፍሶ ወመተርዎ ክሣደ፤ወተፈፀመ ስምዑ ለቅዱስ መርቆሬዎስ።

አመላለስ
መጠወ ነፍሶ ወመተርዎ ክሣዶ
ወተፈፀመ ስምዑ ለቅዱስ

ወረብ
መጠወ ነፍሶ ወመተርዎ ክሣ/2/
ወተፈፀመ ስምዑ ለቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ መርቆሬዎስ/2/

መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለበድነ ስጋከ ንጹሕ ወቅዱስ፤ወለግንዘትከ ፀዓዳ በማየ ደም ግፍዕ ርሑስ፤መርቆሬዎስ ሰማእት መኰንነ አስሊጥ ወፋርስ፤ላዕሌየ ይኅድር እግዚኦ በጸሎትከ ክርስቶስ፤እስመ ማኅደሩ ውእቱ ልቦና ወነፍስ።

ዚቅ
ከመ ኮከብ ብሩህ፤ ወከመ ዕጣን ንፁህ፤መርቆሬዎስ ኃያል መስተጋድል፤ዘዓቢየ ኃይለ ይገብር።

መልክአ መርቆሬዎስ፦
ሰላም ለመቃብሪከ ለህላዌከ መካኑ፤ወለስጋከ ቀይጠኑ፤መርቆሬዎስ ከማከ ኢተንስአ በበዘመኑ፤መኑ መኑ ዝይትማስለከ መኑ፤እንበለ ጊዮርጊስ ሰማእት ዘአዳም ስኑ።

ዚቅ
ጸለየ መርቆሬዎስ እንዘ ይብል ኀበ ይብል ኃበ ተቀብረ ሥጋየ ወተክዕወ ደምየ ህየ በረከት።

ምልጣን
ፈጸመ ሰምዓ ቅዱስ መርቆሬዎስ፤በመዋዕሊሁ ለዳኬዎስ ንጉስ፤ወኮነ መድኃኒተ ለኩሉ ዘነፍስ፤ወተፈሥሑ፤ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ።

አመላለስ
ወተፈሥሑ ባስልዮስ፤
ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ።

ወረብ
ፈጸመ ሰምዓ ቅዱስ መርቆሬዎስ በመዋዕሊሁ ለዳኬዎስ ንጉስ፤
ወኮነ መድኃኒተ ለኩሉ ዘነፍስ ወተፈሥሑ ባስልዮስ ወጎርጎርዮስ።

ዘሰንበት
በሰንበት ምሕሮሙ ወይቤሎሙ፤አክብሩ ሰንበተ፤ዓለመ ፈጠረ ወምድረ ሣረረ ዉእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤እምኵሉ ሰብእ ሰብእነ ዘፈጠረ ኀረየ፤መርቆሬዎስሃ ዓርከ፤ባስልዮስ ንጹሐ ወጎርጎርዮስ ላዕከ፤ዉእቱ ክርስቶስ ወይቤሎሙ፤ኢትግበሩ ዘንተ ቤት አቡየ ቤተ ምሥያጥ፤ዉእቱ ክርስቶስ እስመ ከመ መኰንን ይሜሕሮሙ፤አንከሩ ምሕሮተ ሞገሰ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፤ኵሎሙ እለ ርእይዎ አንከሩ።

ዓዲ
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ከመ ናዕብያ ወናክብራ ለዕለተ ሰንበት፤መላእክተ ሰማይኒ ወኵሉ ፍጥረት፤እለ ዉስተ ሲኦል እለ ዉስተ ደይን፤ያዕርፉ ባቲ ባቲ፤እስመ ቀደሳ አዕበያ ወአልዓላ ለዕለተ ሰንበት፤መኑ ከማከ ስቡሕ እግዚኦ በዉስተ ቅዱሳን፤መንክር ስብሐቲከ፤እግዚኦ ወትረ እሴብሐከ።

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
"መርቆሬዎስ" የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ/ethiopian orthodox mezmur/
መርቆሬዎስ /2/
የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ
እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ

ባስልዮስ ጎርጎሪወቀስ ሰምሯል ልመናቸው
ስዕሉ ዘለለ ታምራት አያችሁ
እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ
ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆሬዎስ

አዝ_

ዑልያኖስ ተገድሏል ሃይማኖት ይስፋፋል
ብሎ መሰከረ መርቆርዮስ ሃያል
ገፀ ከላባቱ ባህርይ ቀየሩ
እርሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ

አዝ_

ትካዜ ሀዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ
መርቆርዮስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ
በፀሊም ፈረሱ እየገሰገሰ
መርቆሬዎስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ

አዝ_

ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዎስ ወደደ
ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ
በጋለ ሹል ብረት መርቆሬዎስ ተወጋ
ስሙ ተሰየመ ከሰማዕት ጋ

አዝ_

አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር
መፍቅሬ አብ ካለ ያኘሎፓዴር
ቂሳርያ እስር ቤት መርቆሬዎስ ታሰረ
ወህኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ፀሐይ ወጣ ከሮሜ
ያሬዳውያን መንፈሳዊ የቅዱስ መርቆሬዎስ ማኅበር
ፀሀይ ወጣ ከሮሜ

ፀሀይ ወጣ ከሮሜ ብርሀን ነው ለአለም
መርቆሬዎስ /2/ የአምላክ ባለሟል


በእግዚአብሔር መላክ አሮስ ከሞት ድኗል
በሮም ሀገር መርቆሬዎስ ተወልዷል
እንደእናት አባቱ ኖህና ታቦት
በምግባር የፀና ሆነ በእምነት /2/

አዝ.........

ከእግዚአብሔር መላክ ሰይፍን ተቀናጅቷል
በጠላቶቹ ላይ ግርማውም ያስፈራል
ዲያብሎስ ይርዳል ስሙ ሲጠራበት
መርቆሬዎስ ብሎ ለተማፀነበት/2/

አዝ...........

እንደ ባስልዮስ እና ጎርጎርዮስ
ጋሹ አምባ ላይ ያለው ቅዱስ መርቆሬዎስ
ስለቴ ተሰማ ዘምር ዘምር አለኝ
መርቆሬዎስ ደርሶልኝ ችግሬ ቀለለኝ/2/

አዝ...........

ደምህን እንደጎርፍ ዳኬዎስ ቢያፈሰው
ስጋህን በእሳት ላይ ደፍሮ ሊያቃጥለዉ
የእሳቱን ቶን ደምህ አጥፎቶታል
ስለቅድስናው ሶስት አክሊል አግኝቷል/2/

አዝ............

አንገትህ ሲታረድ ቂሳርያ ታወከች
የተጋድሎ ፅናት ባይኖቿ ስላየች
ዝክርህን ዘክሮ ስምህን ለጠራ
በመንግስተ ሰማይ ይኖራል ካንተ ጋራ/2/
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
✞ቅዱስ መርቆሬዎስ✞
♡የመዝሙር ግጥሞች♡
#ቅዱስ_መርቆሬዎስ

ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕታዊው የኛ አባት
ተዋህዶን ምሰሶ ሆንካት
ከእናትህ ማህጸን ቸር አምላክ ሲያስብህ
ለኢትዮጲያ ብርሃን አረገህ(፪)
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
#ኅዳር_26_ #_ኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_ሀብተማርያም፡፡
#Share ያድርጉ
፠ አቡነ_ሀብተማርያም በሽዋ (የራውዕይ /ቡልጋ/) ከአባታቸው ፍሬ ቡሩክ ከእናታቸው ቅድስት ዮስቴና ነው የተወለዱት፡፡
፠ ወላጆቹ በተለይም እናቱ ከማግባቷ በፊት መናኝ ነበረች፡፡ ጻድቁን እንደምትወልድ በበቃ ባሕታዊ ተነግሯት ጻድቁን ወልዳ በጽድቅ ኑሮ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ በክብር አርፋለች፡፡
፠ ጻድቁ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› ሲባል ይሰማሉ፤ ይህንንም በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ ‹‹ማረን እባክህን›› እያሉ ይሰግዱ ነበር፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ፡፡ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል፤ የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል፡፡
፠ ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ መንነዋል፤ በታላቁ አባት በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኰሱ በኋላም ብዙ ትርፋትንና ተጋድሎን ሠሩ፡፡ ለአብነትም፤
*ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ፤
*በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ፤
*በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ፤
*ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ነው፤
*በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ፤
*ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ፥ ክቡር ደሙን ይጠጣሉ፤
*በልባቸው ውስጥ በፍጹም ቂምን፥ መከፋትን አላሳደሩም፡፡
* ረአዬ ኅቡዓት በመባል ይታወቃሉ፡፡
* በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ቦታውን ሲባርኩት ሦስት አጋንንት በጸሎቱ ሥልጣን የታሠሩለት ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡
* ‹‹#ጽድቅና_ትሩፋት_እንደ_ሀብተ_ማርያም፠››
፠ ጌታችን ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይሔዱ ነበር፡፡ ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ እንዲህ አላቸው፤
* ‹‹ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ፤ ስለ ምናኔህ፣ ስለ ተባረከ ምንኵስናህ፣ ስለ ንጹሕ ድንግልናህ፣ ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ፣ ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ፣ ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ፡፡››
* በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን፤ 500 የዕንቊ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ፡፡ በስምህ የሚለምኑ፤ በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ ‹አማንየ በርእስየ› ብዬሃለሁ›› አላቸው፡፡
* ቅዱሳን መላእክትም ‹‹ሀብተ ማርያም ወንድማችን›› ሲሉ አቀፏቸው፡፡ ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው፡፡ ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች፡፡ በዝማሬም ወሰዷት፡፡
✤ ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ሥልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነርሱም፤
1ኛ. #_መብረቅ
2ኛ. #_ቸነፈር
3ኛ. #_ረሃብ
4ኛ. #_ወረርሽኝ
5ኛ. #_የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡
፠ በተሰጣቸው ቃል ኪዳንም ከላይ ያሉትን 5ት መቅሰፍቶች የሚያርቁ በመሆናቸው፤ ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁን በደብረ ሊባኖስ ገዳም እነዚህ 5ቱ መቅሰፍቶች እንዳይቀርቡ የሀብተማርያም ካህናት ከኅዳር 1-7(10) ማዕጠንት ያጥናሉ፤ ደብረ ሊባኖስ ገዳምም ለደብረ ይሰበይ አቡነ ሀብተማርያም ገዳም 1ድ በሬ ስጦታን ያበረክታሉ፡፡
፠ በዛሬው ዕለት በኅዳር 26 ባረፈ ጊዜ፤ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው፤ በዝማሬ ፥ በማኅሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በጻድቁ መቃብር ቀበሩት፡፡
(ከወርቅ ንፁህ ፥ ከብርም የጠራ ፥ ከሁሉ የሚበልጥ ፥ የተመረጠ ፥ ሀብተማርያም መልአክ ዘበምድር ነው መልካሙ ዜናው እስከ አጽናፍ ተሰማ፡፡)
#_በዛሬዋ ዕለት #በናግራን ያሉ ክርስቲያኖች በ6ኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕታት የኾኑበት ዕለትም ነው፡፡

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
2024/09/22 16:40:32
Back to Top
HTML Embed Code: