Telegram Web Link
#አንኳን_አደረሳቹህ
ኅዳር ፲፪፤ #ቅዱስ_ሚካኤል በእልፍ አእላፍ መላእክት ላይ የተሾመበትና እስራኤልን የመራበት ክብረ በዓል ነው፡፡
#በዓለ_ሢመቱ_#ወበዓለ_መራኄ_ፍኖቱ_ለቅዱስ_ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት_
፨፨፨ #Share ያድርጉ
ኅዳር ፲፪ ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ፥ በእግዚአብሔር የጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ ለምስጋና የሚቆም፥ ለፍጥረት ሁሉ የሚማልድ፥ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመቱና እስራኤላውያንን በባሕረ ኤርትራ ያሸገረበት በዓል ነው፡፡ (እንኳን አደረሳችሁ)
፠ #፩ በዓለ ሢመቱ፤ ሚካኤል ማለት ማን እንደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ከሌሎች መላእክት ጋር በእለተ እሑድ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የተፈጠረ ሲሆን፤ እርሱም መጀመሪያ ከ100ው ነገደ መላእክት የ10ሩ ነገደ መላእክት (የኃይላት) አለቃቸው ነበር፤ በተጨማሪም ከሳጥናኤል ውድቀት በኋላ የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ የአጋእዝትን ነገድም (ሳጥናኤል/ሰማልያል/) ይመራቸው የነበሩትን 10 ነገዶችም በአለቅነት ደርቦ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በዛሬው ዕለት ለ100ውም(99ኙም) ነገደ መላእክት (ለእልፍ አእላፋት መላእክት) አለቃቸውም ቅዱስ ሚካኤል ኾኖ የተሾመበት ዕለት ነው፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡
ቅ/ሚካኤል ለሰው ልጆች ምሕረትን ከኅዳር 12 (ከበዓለ ሢመቱ) ጀምሮ እስከ ኅዳር 13 (የአእላፍ መላእክት) በዓል ድረስ ከአምላኩ ለፍጥረታት ሁሉ ምሕረትን የሚለምንበት ዕለታት ናቸው፡፡
፨፨፨
፠#፪ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት እየመራቸው ማውጣቱን የሚዘከርበት በዓል ነው፡፡
ይህም የሆነው ያዕቆብ በረሃብ 70 ኹኖ ወደ ግብፅ ከወረደ በኋላ ከ215 ዓመታት (አብርሃም ወደ ግብፅ በተሰደደ ከ430 ዓመታት) በኋላ፤ የዮሴፍን ዝና ያልሰማ፥ ዮሴፍን የማያውቅ ፈርዖን በግብፅ ነገሠ፡፡ እስራኤል ከእኛ ይልቅ በዝተዋል ጠላቶቻችን ቢነሱብን ከጣለቶቻችን ጋር ተደርበው ያጠፉናል በማለት አገዛዝ አጸናባቸው፥ ፍርድ አጓደለባቸው፡፡ የእስራኤል ሴቶች ልጅ ሲወልዱ ወንድ ከሆነ እንዲገደል በማድረግ መከራ አጸናባቸው፡፡ ለ215 ዓመታት በግብፅ በባርነት ከቆዩ በኋላ ከዕብራውያን ወገን የሆነችው ራሔል ጭቃ እያቦካች ምጥ በያዛት ጊዜ ከሥራዋ እንዲያሳርፏት ጠየቀች፤ ግብጻውያን ግን የሕፃናቱ ደም ጡቡን ያጠነክራል ርገጭ አሏት፡፡ ከማሕፀኗ የወጡ ሁለት መንትያ ልጆቿን እያየች ከጭቃ ጋር ረገጠች፤ ራሔልም መሪር ልቅሶን አለቀሰች፤ ስለ ልጆቿም መጽናናትን እንቢ አለች፡፡
የእስራኤል ንጉሥ ሆይ የሆነብንን እይ ስትል ራሷን ይዛ ታለቅስ ጀመር ፥ እንባዋንም ወደ ሰማይ ንጉሥ ወደ እግዚአብሔር ረጨች፡፡ የራሔል እንባዋ የሕዝበ እስራኤልን ሁሉ ጩኸት ፥ እሮሮ ይዛ ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰች፡፡ “. . . ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች የሉምና ስለ ልጆቿ መጽናናት እንቢ አለች” /ኤር 31፥5፤ ማቴ 2፥17/ እንዲል፡፡
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን አስነሳና፤ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል መሪነት፤ 10 ተዓምራትን በምድረ ግብፅ በ11ኛ ተዓምር ደግሞ በኅዳር 12 (ፈርዖንን ከነሠራዊቱ በኤርትራ ባሕር አስጥሞ) ወደ ተስፋይቱ ምድረ መራቸው፡፡
ባሕረ ኤርትራን እስራኤላውያን እንደተሻገሩም የእስራኤል ልጆች የሙሴ የአሮን እኅት ማርያም ከበሮ እየመታች ‹‹ንሴብሖ ለእግዚአብሔር ስቡሐ ዘተሰብሐ ፤ እግዚአብሔር ተዋጊ ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው እያሉ፡፡›› ጠላታቸውን የመታላቸውን ፥ እነሱንም በተአምራቱ ያሻገራቸውን ፥ ከጠላታቸው እጅ ያዳናቸውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ከዚህ በኋላ መጋቤ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው ፥ መና ከሰማይ እያወረደላቸው ፥ ውሃ ከጭንጫ እያፈለቀላቸው ፥ ቀኑን በደመና ፥ ሌቱን በብርሃን መርቷቸው አርባ ዘመን ተጕዘው የቃል ኪዳን አገራቸው ምድረ ርስት ከነዓንን (የዛሬዋ ኢየሩሳሌምን) ወርሰዋል፡፡ /ዘጸ. 15/
ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም እስራኤልን በሚመራበት ጊዜ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እስራኤልን ይረዳቸው ነበር፡፡ ከጠላቶቻቸው ጋር ሲዋጉም ሰልፉን ይመራ የነበረው ቅዱስ ሚካኤል ነበር፡፡ ለምሳሌ እስራኤላውያን ከኢያሪኮ አጠገብ በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ኢያሱን አነጋግሮታል፡፡
ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ በመሆኔ መጥቻለሁ” ብሎታል /ኢያሱ 5፥13-15/፡፡ ይህ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከኢያሱ ፊት ለፊት የቆመው መልአክ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል (እንዲሁም መልአኩ ቅዱስ ራጕኤል) ነው፡፡ ይህን ለአብነት አነሣን እጅ እስራኤል በሚበድሉበት ጊዜ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር የሚማልድላቸው ይህ ታላቅ መልአክ መጋቤ ብሉይ ቅ/ሚካኤል ነበር፤ እግዚአብሔር አምላክ በእደ መልአኩ ይጠብቀን፤ ከበዓሉ ረድኤት ፥ በረከት ይክፈለን፤ አሜን፨
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ሥርዓተ ማኀሌት ዘኅዳር ፲፪ ፤ በዓለ ቅዱስ ሚካኤል
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
+ የአያቶች ቀን +

እናትነት ጸጋ ነው:: አባትነትም ደስታ ነው:: ከሁለቱ በላይ ደግሞ አያት መሆን ይበልጣል:: ልጅን ከማየት የበለጠ የልጅ ልጅን የማየት ደስታ እጅግ ትልቅ ነው:: እናት ለልጅዋ ከምታሳየው ፍቅር የአያት ፍቅር የሚበልጠው በአያት እጅ ያደጉ ልጆች ስስትና እንክብካቤ የሚበዛባቸው ለዚህ ነው:: ወላጆች የሚቆጡት ልጅ አያት ሥር የሚደበቀው ለዚህ ነው::

የአባቶችና የእናቶች ቀን እንደሚታሰበው ሁሉ አብልጦ ሊታሰብ የሚገባው የአያቶች ቀን ነው:: ዕድሜ ቢጫናቸው እንኳን ለልጅ ልጆቻቸው ፈገግታቸው የማይደበዝዝ በዕድሜያቸው ፀሐይ መጥለቂያ ሳይደክማቸው ፍቅር የሚሠጡ የፍቅር ጥግ ማሳያዎች አያቶች ናቸው::

ዛሬ በቤተ ክርስቲያን የአያቶች ቀን በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው:: በምድር ካሉ አያቶች ሁሉ የሚበልጡት አያቶች ቅድስት ሃና እና ቅዱስ ኢያቄም የሚታሰቡበትክብረ በዓል ነው:: ድንግል ማርያም ከእናቶች ሁሉ እንደምትበልጥ ወላጆችዋም ከአያቶች ሁሉ ይበልጣሉ:: እርስዋን የአምላክ እናት ብለን እንደምናከብር እነርሱንም የአምላክ አያቶች ብለን እናከብራቸዋለን::
በመለኮቱ አባት እንጂ አያት ለሌለው ለመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ አያቶቹ የሆኑ ሃና እና ኢያቄም እጅ ክቡራን ናቸው::

ሃና ሰማይን ወለደች ልጅዋ ፀሐይን ወለደች:: ሃና ምንጭን ወለደች ልጅዋ የሕይወትን ውኃ ወለደች:: በጌታ የዘር ሐረግ ውስጥ የተቆጠሩ ሁሉ ክቡራን ናቸው የመጨረሻዎቹ አያቶቹ ደግሞ የመጨረሻው ክብር ይገባቸዋል::

ሃና እና ኢያቄም የልጅ ልጄ የሚሉት ፈጣሪያቸውን ነው:: እርግጥ ነው በሕይወት ቆይተው ቀድሞ በሕልም አይተው ያልተረዱትን የልጃቸውን ልጅ ክርስቶስን አቅፈው ለመሳም አልታደሉም:: ሆኖም ድል አድራጊው የልጅ ልጃቸው የሲኦልን መዝጊያ ሰብሮ ነፍሳትን ሲያወጣ አያቶቹንም አውጥቶአቸዋልና ልጃቸው የወለደችውን ፀሐይ በሲኦል ሲያበራ አይተው ሕልማቸው ተፈትቶአል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር 11 የቅድስት ሀና በዓል
ድሬዳዋ ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሥርዓተ ማኀሌት ዘኅዳር ፲፪ ፤ በዓለ ቅዱስ ሚካኤል
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሥርዓተ ማህሌት አመ ፲ወ፪ ለኅዳር ሚካኤል


የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።


መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለጒርዔክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ፤ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ፤ከመ ትትኃየዩኒሰ ወኢትኅድጉኒ ጽኑሰ፤ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ስጋየ ጌሠ፤ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።


ዚቅ
አመ ይፈጥራ እግዚአብሔር ለምድር፤ኢዜነዎ ለሰማይ፤ወኢተማከረ ምስለ መላእክቲሁ፤ወተከለ ፫ተ ዕፀ ህይወት በዲበ ምድር።


ነግሥ
ጐሥዐ ልብየ ጥበበ ወልቡና፤ለውዳሴከ ጥዑመ ዜና፤ቅዱስ ሚካኤል ልማድከ ግብረ ትሕትና፤አንተኑ ዘመራኅኮሙ ፍና፤ወአንተኑ ለ፳ኤል ዘአውረድከ መና።


ወረብ
አንተኑ ሚካኤል መና መና ዘአውረድከ/፪/
ወአንተኑ ለ፳ኤል መና ዘአውረድከ/፪/

ዚቅ
አዝነመ ሎሙ መና ይብልዑ፤ፀዓዳ ከመ በረድ፤ወርእየቱ ከመ ተቅዳ፤ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ፤አውኃዘ ሎሙ ማየ ህይወት፤ዘትረ ኴክኅ ፈልፈለ ነቅዕ ዘኢይነቅዝ፤ኅብስተ እምሰማይ ወሀቦሙ።


መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ፤ወልደ ያሬድ ሄኖክ በከመ ጸሐፈ፤ሶበ እጼውዕ ስመከ ከሢትየ አፈ፤ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ፤ለረዲኦትየ ነዓ ሰፊሐከ ክንፈ።

ወረብ
ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል ረዳኤ ምንዱባን/፪/
በከመ ከመ ታለምድ ዘልፈ/፪/

ዚቅ

ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል፤ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤ይስአል ለነ፤ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ።

@EotcLibilery

ወረብ፦
ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር/፪/
ይስአል ለነ አመ ምንዳቤነ ይስአል ሰፊሆ ክነፊሁ/፪/


መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለልሳንከ በነቢበ ጽርፈት ዘኢተኃበለ፤በእንተ ሥጋሁ ለሙሴ አመ ምስለ ሰይጣን ተበኃለ፤ሚካኤል ክብርከ እምክብረ መላእክት ተልዕለ፤ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ፤በብሂለ ኦሆ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ።

ወረብ
ቀዊምየ ቅድመ ስዕልከ ሶበ አወትር ስዒለ/፪/
"በብሂለ ኦሆ"/፪/ ፍጡነ አስምዓኒ ቃለ/፪/

ዚቅ
ረሰዮ እግዚኡ ለውእቱ ሚካኤል፤እምኲሎሙ መላእክት ይትለዓል መንበሩ፤ስዩም በኀበ እግዚኡ ምእመን።


ወረብ
እግዚኡ ረሰዮ ለውእቱ ሚካኤል/፪/
እምኲሎሙ መላእክት መላእክት ይትለዓል መንበሩ/፪/

መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለሕንብርትከ ሕንብርተ መንፈስ ረቂቅ፤ዘቱሣሔሁ መብረቅ፤ነግሀ ነግህ አንተ በአዝንሞ መና ምውቅ፤በገዳም ዘሴሰይኮሙ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ፤ሴስየኒ ሚካኤል ሕገከ በጽድቅ።


ወረብ
"በገዳም"/፫/ ዘሴሰይኮሙ/፪/
ለነገደ ለነገደ ኅሬ ደቂቅ/፪/


ዚቅ
ባሕረ ግርምተ ገብረ ዓረፍተ፤ወበውስቴታ አርዓየ ፍኖተ፤በእደ መልአኩ አቀቦሙ በገዳም ለሕዝቡ አርብዓ ዓመተ፤ወሴሰዮሙ መና ኅብስተ፤ኪነ ጥበቡ ዘአልቦ መስፈርተ።


ወረብ
በእደ መልአኩ አቀቦሙ መልአክ ለ፳ኤል/፪/
ወሴሰዮሙ መና በገዳም በገዳም አርብዓ ዓመተ/፪/

ወረብ
ባሕረ ግርምተ ዓረፍተ ገብረ አርአየ ፍኖተ እግዚአብሔር/፪/
በእደ መልአኩ አቀቦሙ ለ፳ኤል አርብዓ ዓመተ ለሕዝቡ በገዳም/፪/


መልክአ ሚካኤል
አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክእከ ኲሉ፤ለለ፩ዱ ፩ዱ ዘበበክፍሉ፤ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ፤ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኀ ሰማያት ዘላዕሉ፤ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ።

ዚቅ
ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ፤ወስዕለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ፤ተወከፍ ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ።


ወረብ
ተወከፍ "ጸሎተነ ውስተ ኑኃ ሰማይ"/፪//፪/
ወስእለተነ ከመ መዓዛ ሠናይ ሊቀ መላእክት/፪/


አንገርጋሪ
ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል፤ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር፤ይስአል ለነ፤ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ።


ምልጣን
ይስአል ለነ፤ረዳኤ ይኲነነ አመ ምንዳቤነ፤ሰፊሆ ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ።


አመላለስ፦
ሰፊሆ ክነፊሁ/፪/
ክነፊሁ ይጸልል ዲቤነ/፬/


ወረብ ዘአንገርጋሪ
ውእቱ ሚካኤል መልአከ ኃይል ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር/፪/
ይስአል ለነ ረዳኤ ይኲነነ ይስአል አመ ምንዳቤነ/፪/


እስመ ለዓለም
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤አስተምሕር ለነ ሰአልናከ፤በ፲ቱ ወ፵ቱ ትንብልናከ፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ዓይኑ ዘርግብ፤ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ይሰግድ በብረኪሁ፤እስከ ይመጽእ ሥርየት ለኃጥአን፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤መኑ ከማከ ክቡር።

ወረብ ዘእስመ ለዓለም ፩
ሚካኤል መልአክ እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል/፪/
አስተምሕር ለነ ሰአልናከ በ፲ቱ ወ፵ቱ ትንብልናከ/፪/

@EotcLibilery

ወረብ ዘእስመ ለዓለም ፪
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል/፪/
ሐመልማለ ወርቅ ልብሱ ዘመብረቅ ዓይኑ ዘርግብ ሊቀ መላእክት/፪/


ወረብ ዘእስመ ለዓለም ፫
ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል/፪/
ይሰግድ በብረኪሁ እስከ ይመጽእ ሥርየት ለኃጥአን/፪/

እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)🙏🙏🙏
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
 
በሕይወት ውስጥ መጀመሪያ ከፊት የሚመጡት ሰዎች "ሔዋንህ" ወይም "አዳምሽ" ላይሆኑ ይችላሉ። ልክ አዳም ከተፈጠረ በኋላ መጀመሪያ በእርሱ ፊት እንስሳትን እንዳገኘ እና ለእነርሱም የሚገባቸውን ስም እየሰጠ እንዳሰናበታቸው፣ አንተም አንዳንዴ በኑሮህ ቀድመህ የምታገኛቸው አካላት "ጎረቤት፣ የሥራ ባልደረባ፣ ጓደኛ" እያልክ ስም የምታወጣላቸው ብቻ ይሆናሉ። ለምን? "እንደ አንተ ያሉ (የሚመቹ) ረዳቶች" አይደሉማ። አዳም ለእንስሳት፣ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሁሉ ስም ካወጣላቸው በኋላ መጽሐፉ "ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር" ይላል።(ዘፍ 2፥20)

አዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት ከእንስሳቱ መካከል ፈልጎ በማጣቱ "በቃ የምን መኩራት ነው? ያሉት እነዚህ ስለሆኑ እኔን ባትመስል እንኳ ትንሽ ለእኔ የቀረበችውን ብመርጥ ይሻላል" አላለም። ከሌሎች ይልቅ በአካላዊ ቁመና ለእርሱ የምትቀርበውን ትልቅ ጦጣ (Chimpanzee) መርጦም ወደ ፈጣሪው በመውሰድ "እባክህ ጌታዬ፣ ለአንተ የሚሳንህ የለምና ትንሽ ጸጉሯን ብትቀንስ፣ ጅሯቷን ብታጠፋ እና ፊቷ አካባቢ ማስተካከያ ብታደርግላት እንደ እኔ ያለ ረዳት ትሆናለች" ብሎ ሲማጸን አናገኝም። ይህን ቢያደርግ ኖሮ አሁን የአዳምን ታሪክ የምናነብ ሰዎች ሁሉ በችኮላው እየተገረምን እንስቅበት ነበር። ምክንያቱም እግዚአብሔር ከጥቂት ቀን በኋላ አጥንቷ ከአጥንቱ፣ ሥጋዋ ከሥጋው የተፈጠረ ሔዋን የተባለች እጅግ ውብ ሚስት እንደሰጠው ስለምናውቅ።

ከአንተ ጋር በሃይማኖት፣ በአመለካከትና ይህን በመሳሰሉት ነገሮች ጨርሳ ልትገጥም የማትችል የማትመችህን ረዳት "ለአንተ ምን ይሳንሃል? አስተካክልልኝ" እያልክ ለምን ትታገላለህ። በፍጹም ስለማይሆንሽ ሰው ለምን የmodification ጥያቄ ታቀርቢያለሽ? ጥቂት ጊዜ ከታገስህ እግዚአብሔር ለአንተ የምትመችህን (compatible) ረዳት ያመጣልሃል። አሁን ግን ፊት ለፊት ያገኘሃት ጥሩ የሥራ ባልደረባ ወይም ጓደኛ እንጂ የምትመች ረዳትህ አይደለችም።

በሕይወት ውስጥ ቀድሞ የመጣ ሁሉ ባል ወይም ሚስት አይሆንም። መጽሐፍ ቅዱስም "ቢቻላችሁስ... ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ" ይላል እንጂ "ከሁሉ ጋር ተጋቡ" አላለንም።(ሮሜ 12፥18)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
“ፆም የፀሎት ምክንያት ናት፤ የፀጋ ዕንብ መገኛ ናት አርምሞን የምታስተምር ናት፤ ለበጎ ስራ ሁሉ ታነቃቃለች፤ የፀዋሚ ስጋው ምንጣፉን አንጥፎ ሌሊቱን ሁሉ ተኝቶ ማደር አይቻለውም በምን ጎኑ ይተኛዋል? ሰው አብዝቶ በፆመ ያህል በዚህ መጠን በትህትና ሁኖ እያለቀሰ ይፀልያል፤ ፀሎታት ከልቡናው ይታሰባሉ አንድም ፀሎተ ልብ ይሰጠዋል፤ በፊቱ የትእግስት ምልክት ይታያል በሃጢአቱ ያዝናል ክፉ ህሊና ይርቅለታል የበጎ ነገር መገኛ መከማቻ በምትሆን በፆም ይኖራልና፤ ፆምን የናቀ ያቃለለ ሰው በጎውን ነገር ሁሉ ከራሱ አራቀ፡፡”

ማር ይስሃቅ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡

በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡

እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
Audio
በእግዚአብሔር ዘንድ የተከበሩ 3 ነገሮች 
                                                  
Size:- 26.5MB
Length:-1:53:25
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/25 12:36:21
Back to Top
HTML Embed Code: