Telegram Web Link
“እግዚአብሔር ባይፈቅድ ነው”

| ጃንደረባው ሚድያ | ኅዳር 2016 ዓ.ም.|

✍🏽 ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ እንደጻፉት

ካለፉት ቀናት መካከል አንደኛው ቀን የትምህርት ቤት ወንድሜን ለመጠየቅ የሄድሁበት ቀን ነበር። ከተገናኘን ብዙ ቀን ሆኖን ስለነበር ለእግርህ ውኃ ላሙቅልህ፣ ምግብ ይቅረብልህ አላለኝም። እንዲሁ ያለፈውን ዘመናችንን በዛሬ ዐይናችን እያየን በዛሬ ሚዛን እየመዘንን በሚያስቀው ስንስቅ በሚያስጸጽተው ስንጸጸት ቆይተን ለእንግድነቴ የሚገባው ግብዣ ከተደረገልኝ በኋላ ዛሬአችንን ወደ መገምገም ተመለስን።

የቆሎ ተማሪ አፈር ላይ ተኝቶ ይማራል እንጅ “አፈር ፈጭተን ውኃ ተራጭተን” ይሉት ጨዋታ አያውቅምና ያ አፈር ላይ ተኝቶ አብሮኝ ይማር የነበረው ጓደኛዬ ዛሬ የአንድ ድርጅት ባለቤት ሆኗል። የሚኖሩበት ቤት ፀሐይ ሳትወጣ ብትዘገይ የሚያሞቅ፣ የተመኙትን ነፋስ የሚያነፍስ መሣሪያ የተገጠመለት ዘመናዊ ድንኳን ነው። በመጨረሻ የጠየቅሁት ጥያቄና የመለሰልኝ መልስ ነው ዛሬ ለምጽፍላችሁ ደብዳቤ መነሻ የሆነኝ። “ዜማ ቤት እያለን ማኅሌት በጣም ትወድ እንደነበር አውቃለሁ እንዲያውም ትዝ ካለህ ከማኅሌት ስትመለስ የመጀመሪያ ሥራህ የነበረው ተኝተው ያደሩ ተማሪዎች ላይ ውኃ መድፋት ነበር ዛሬስ እንዴት ነህ?” አልሁት ትንሽ እንደማፈር ሲል አየሁት።

ትንሽ እንደማሰብ አደረገና “እኔማ አገልግሎት ምን ያኽል እንደምወድ አንተም ታውቃለህ ነገር ግን የምወደውን አገልግሎት ሰዎች አስጠሉኝና ተውሁት። ለጥቂት ቀናት እንዳልሄድ አለመፈለጋቸውን እያወቅሁ ተጋፍቸ ሄድሁ፤ አንድ ቀን መኪናዬን ያልተገባ ነገር አደረጉብኝ ሌላም ልነግርህ የማልፈልገውን አደረጉብኝ፤ ሲሰለቸኝ መቼስ ሰው ይደለሁ? በቃ ማገልገሌን እግዚአብሔር ባይፈቅድልኝ ነው ብየ እርግፍ አድርጌ ተውሁት ይሄው አራት ዓመቴ ማኅሌቱን ከተውሁት አለኝ”።

እንዲህ አይነት መወሰኛ ቃል እየተጠቀምን ነገሮችን ሁሉ በጅምር የምናስቀር ብዙ ሰዎች መኖራችንን ባሰብሁ ጊዜ እንድጽፍ ተገደድሁ። ብዙ ሰዎች ብትጠይቋቸው ያላገቡት እግዚአብሔር ስላልፈቀደ ነው። ያልቆረቡት እግዚአብሔር ስላልፈቀደ ነው። ሥራቸው ስኬት ያላመጣላቸው እግዚአብሔር ስላልፈቀደ ነው። የጀመሩትን ነገር ሁሉ ያልጨረሱት እግዚአብሔር ስላልፈቀደ ነው። ሩቅ አስበው ከቅርብ የተመለሱት እግዚአብሔር ስላልፈቀደ ነው። እንዲህ እያሉ ይቀጥላሉ። ሁሉንም ነገር እግዚአብሔር ስላልፈቀደ ብለው ነው የሚተዉት።

ለአንዳንዶቹ የሚመስላቸው እግዚአብሔር ከፈቀደ ያለምንም ትግል ነገሮች ሁሉ የሚከናወኑ ይመስላቸዋል። እግዚአብሔር ከፈቀደ ነገሮች ሁሉ “ለይኩን” በሚል ትዕዛዝ እንዲፈጸሙላቸው ይፈልጋሉ። እግዚአብሔር የፈቀደልንን ሕይወት ለመኖር ሲባል እኮ ነው ይሄ ሁሉ ተጋድሎ፤ የሰማዕታት ተጋድሏቸው፣ የጻድቃን ምናኔአቸ፣ የደናግል የመነኮሳት ትዕግሥታቸው፣ የሰብአ ዓለም ሕግ መጠበቃቸው፣ የካህናት ትጋታቸው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማስቀየር የሚደረግ ይመስላችኋል? ይሄ ሁሉ ሩጫ እግዚአብሔር የፈቀደልንን ሕይወት እንዳናጣ ለመሆን ነው።

ሐዋርያትን “ሑሩ ወመሀሩ” ብሎ ያዘዘ ማነው? ቅዱስ ጳውሎስን “ንዋየ ኅሩየ ረሰይኩከ” ብሎ ያከበረ ማነው? ኃጥአንን ለንስሐ የጠራ ማነው? ነገር ግን በፈቀደላቸው መንገድ ሲጓዙ የሚገጥማቸውን ተጋድሎ ተመልከቱ። ዓለም ሳይፈጠር ጀምሮ መንግሥተ ሰማያት ለሰው የተዘጋጀች ስጦታ ናት ቢሆንም ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀልንን ስጦታ ዓለምን ካላሸነፍን አናገኘውም ማቴ 25፥34፣ 1ዮሐ 5፥5
የእስራኤል ከግብጽ መውጣት ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቆረጠ ነገር ነበር። “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ስቃያቸውንም አውቄአለሁ፤ ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወተትና ማር ወደምታፈሰው ወደ መልካሚቱና ወደ ሰፊይቱ አገር ወደ ከነአናውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዜወናውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ” ዘፀ 3፥7 ብሎ መውጣታቸው ፈቃዱ መሆኑን ገልጿል።

ዳሩ ግን እስራኤል የእግዚአብሔር ፈቃድ ስለሆነ ያለምንም ሰልፍ ግብጽን ለቀው መውጣት አልቻሉም። እግዚአብሔር ለእስራኤል መውጣትን እንደፈቀደ ሁሉ የፈርዖንን ልብ እንደሚያጸናም “እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ” ዘጸ 4፥21። ብሏል። ምን አይነት ነገር ነው? በአንድ በኩል ፈቅጃለሁ እስራኤል ይውጡ ይላል በሌላ በኩል የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ ይላል።

ተመልከተው! የእግዚአብሔር ፈቃድ ታግለህ እንድታሸንፍ ነው እንጅ ለይኩን ተብሎ በቃል በተፈጠረ ዓለም ውስጥ በቃል እንደማዘዝ ቀላል በሆነ መንገድ እንድትጓዝ አይደለም። እግዚአብሔር ከፈቀደልህም በኋላ አስማተኞች ይፈታተኑሃል፤ ፈርዖን ፍርድ ያጠብቅብሃል፤ አስገባሪዎች ግብር ይጭኑብሃል፤ አንዳንዴም ለጸሎት ለዝማሬ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ስታቀና ባዩ ጊዜ እንደ ሥራ ፈት ይቆጥሩህና ለማሰናከያ የሚሆን ሽልማት ያለው ሥራ ለምስጋና በተመደበው ጊዜ ያዘጋጁልሃል። እና አንዳንዴ እንዲያውም በቃ የጀመርሁት ጸሎት፣ ሱባኤ፣ ቅዳሴ፣ ቁርባን፣ ኪዳን የበለጠ ፈተናዬን ስላበዛብኝ ከሰይጣን ጋር እልህ ከምጋባ አርፌ ብቀመጥ ይሻለኛል እንድትል ያደርግሃል። እስራኤልም ያሉት እንዲሁ ነበር “በፈርዖንና በሠራዊቱ ፊት ሽታችንን አግምታችኋል፥ ይገድሉንም ዘንድ ሰይፍ በእጃቸው ሰጥታችኋልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ ይፍረድባችሁም” ዘጸ 5፤21 ብለው ሊያድኗቸው ከተላኩ አገልጋዮቻቸው ጋር መጣላት ጀመሩ። የተፈቀደልህ ቦታ እስከምትደርስ ድረስ ላንተ ነጻ መውጣት ከተላኩ ካህናት መነኮሳት ጋር ሳይቀር የሚያጋጭ ፈተና ያጋጥምሃል።

በአንድ በኩል እግዚአብሔር የላካቸው ሰዎች “እኔ እግዚአብሔር ነኝ ከባርነት ነጻ አወጣችኋለሁ፤ ከተገዥነትም አድናችኋለሁ በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም እታደጋችኋለሁ ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ” ዘጸ 6፥6 ብሏል ብለው ይነግሩናል። ግን እግዚአብሔር በሕይወታችን ውስጥ ወዴት አለ? በሥራችን የረዳን፣ መከራችን ያቀለልን፣ ባርነታችንን ያስቀረልን መቼ ነው? እንላለን አይደል? አወ ይቀላል ስንል መከራው እየበዛ ሲሄድ፤ በምንረግጠው ጭቃ ውስጥ የልጆቻችን ደም ተቀላቅሎ ስናይ፤ በከተማው የሚሰማ የገራፊዎች ጅራፍ ድምጽ ብቻ ሲሆን፤ እስራኤል በደሙ ጭቃ አቡክቶ በሚገነባው ፒራሚድ ግብጻዊ ሲያጌጥበት ስናይ ከዚህ ሌላ ስሜት ሊኖረን እንደማይችል ይታወቃል።

ነገር ግን እውነቱን ከመጽሐፍ ቅዱስ ተረዱት። እግዚአብሔር “ኃይሌን ባንተ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይነገር ዘንድ ለዚህ አሰነሣሁህ” ሮሜ 9፥17 ብሎ የኃይ መገለጫ አድርጎታል። እኛ በፈርዖን ላይ የሚገለጠውን ኃይሉን እንጠባበቃለን እንጅ እግዚአብሔር እኛን ለማዳን አልፈቀደም ብለን አናንጎራጉርም።

የጌታ ፈቃድ እስኪሆን እስኪደረግ ድረስ በብርቱ ትግል ውስጥ እናልፋለን። ከዚህ አስጨናቂ ሕይወት መውጣታችንን ቢወድም ኃይሉን በጠላቶቻችን ላይ እንዲያሳይ የኛ ትዕግሥት ያስፈልጋል። የእግዚአብሔርን ማዳን ገና በሰፊው ስትደረግልን በሕይወታችን ውስጥ እናያለን። ከተፈቀደልን ሕይወት የምንደርሰው በትዕግሥት ነው።

ከማንጎራጎር ወጥተን በእኛ ላይ የወደደውን ለማድረግ ሥልጣን ያለውን ጌታ የሚያደርገውን ሁሉ በማስተዋል መመልከት ነው። ሸክላ ሠሪ የወደደውን ሊሠራበት በእጁ ያለውን ጭቃ ሥልጣን የለውምን? እግዚአብሒርም በእኛ ላይ የወደደውን የሚያደርግበት ሥልጣን አለው።
በትግል የምትኖሩ ሁሉ እግዚአብሔር በትግል ውስጥ ለምን እንዳኖራችሁ ትግላችሁ ውስጥ እግዚአብሔር እየሠራ ያለውን መልካም ነገር መርምሩና ድረሱበት። ምናልባትም በእናንተ ትግል ውስጥ ፈታኞቻችሁን እየቀጣላችሁ ይሆናል። የእስራኤል መቆየት ለግብጽ ቅጣት ነበር እንጅ ጥቅም አልነበረም።

ግብጽ በውኃ ፋንታ ደም የቀዳችው፣ ምድሯ በቅማልና በጓጉንቸር የተሞላው፣ ለሦስት ቀናት ብርሃን ከማየት የተከለከለችው፣ ከንጉሡ ቤት ጀምሮ በሁሉም ግብጻውያን ቤት ውስጥ በማለዳ ሬሳ የተገኘው በእስራኤል መቆየት ነው። እስራኤልን መልቀቅ ጥቅሙ ለእስራኤል ብቻ ሳይሆን ለግብጻውያንም ነበር። ፈርዖን ግን ይህንን አላወቀም።

ሰላም የነሡን ሰዎች ሰላም ቢሰጡን ዕዳ ቆልለው የሚያስጨንቁን ሰዎች ባያስጨንቁን ዕረፍቱ ለሁላችንም ከእግዚአብሑእር ዘንድ ይሆንልን ነበር ግን አስገባሪዎቻችን ይህ አይገባቸውም። እኛማ እግዚአብሔር የፈቀደው ቀን ሲደርስ ከዚህ መውጣታችን አይቀርም። ምክንያቱም በትግል ውስጥ እንድናልፍ ፈቃዱ ቢሆንም በዚያው ውስጥ ሳለን እጃችንን ለሞት እንደንሰጥ ግን አያደርገንም።

ዳዊት ከተቀባ በኋላ በሳዖል መሳደዱ ዱር ለዱር መንከራተቱ አያስደንቅም? በእግዚአብሔር ፈቃድ ለንጉሥነት የተመረጠው ዳዊት ከዕለታት አንድ ቀን የሚበላው አጥቶ ያልተፈቀደለትን እንጀራ እስከ መብላት ደርሷል። ይህ ሁሉ መሆኑ የዳዊት መንግሥት የጌታ ፈቃድ ባይሆን ነውን? አይደለም! ጨለማውም የሚመጣው በጌታ ፈቃድ ነው። ብርሃንም የሚሆነው በጌታ ፈቃድ ነው። “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ዮሐ 15፥5 ማለቱን አስተውሉ!

ማስታወሻ:- ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የአራቱ ጉባኤያት መምህርና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ ሲሆን የመጻሕፍት ደራሲም ናቸው:: ሊቅ ሊቃውንት የጃንደረባው ሚዲያ ዐምደኛ ሲሆኑ ጽሑፎቻቸው ዘወትር ሰኞ የሚነበቡ ይሆናል::
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል ይሸልሙታል ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ ልቡናችንን በማንጻት ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ የክፋት እርሾን በማስወገድ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡

በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡

እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
Forwarded from 💎Super📣ፕሮሞሽን
ከመስከረም 17 ውጪ መስቀል የሚዘከርበት ወር እና ቀን መቼ ነው?
Forwarded from 💎Super📣ፕሮሞሽን
ጃንደረባው ሚዲያ በቴለግራም መጣ!

የሚለቀቁትን የአእላፋት ዝማሬ ለማጥናት JOIN በሉ::

@jan_yaredd
ኅዳር 21 ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን ወይም ታቦተ ሕጉ )

ጽዮንን ክበቧት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦቿንም ቅጠሩ፥ አዳራሿን ተመልከቱ፥ በብርታቷ የልባችሁን ተስፋ አኑሩ፡፡ /መዝ. 47፥12/
share እና like ያድርጉ
#ኅዳር_21_የታቦተ_ጽዮን_(#ጽላተ_ኪዳን_ወይም_ታቦተ_ሕጉ_) #ዓመታዊ_ክብረ_በዓል_የምናከብርበት_ምክንያት_

፩ኛ. በሊቀ ካህናት ኤሊ ዘመን በሕዝበ አስራኤል(በአፍኒን ፊንሐስ) ኀጢአት ምክንያት፤ ታቦተ ጽዮን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ (ኢሎፍላውያን) እጅ ተማርካ፤ ዳጐን የተባለ የአሕዛብ ጣዖትን ቀጥቅጣ አድቅቃ ወደ እስራኤል የተመለሰችበት በመኾኑ፡፡ (1ሳሙ. ከ1-6)

፪ኛ. ታቦተ ጽዮን መፍቀሬ ጥበብ ቅዱስ ሰሎሞን ወዳሠራው ቤተ መቅደስ (በዓለም ላይ እስካሁን ያልታየ ድግስ ደግሶ) የገባችበት እለት በመኾኑ፡፡ / (1ኛ ነገ. 8፥2፣ 2ኛ ዜና. 5፥1፣ ስንክሳር ዘሐምሌ 23)

፫ኛ. በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ (ዕብነ ሐኪም) አማካኝነት ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር በ318ቱ ሌዋውያን ካህናት ፥ በሊቀ ካህናቱ አዛርያስ እየተመራች ታቦተ ጽዮን ወደ ኢትዮጵያ የገባችበት በመኾኑ፡፡ /ክብረ ነገሥት፣ መጽሐፈ ምሥጢር፣ መጻሕፍተ ሰሎሞን ወሲራክ አንድምታ መቅድም፣ …/

፬ኛ. ነቢያት ስለ እመቤታችን በተለያየ ኅብረ መልክእና አምሳል (ዕዝራ በቅድስት ሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ፣ ……) ያዩበት በመኾኑ፡፡ /ሕዝ. 44፥1፣ መጽ. ዕዝራ/

፭ኛ. በንጉሥ አፄ ባዜን (በ4 ዓ.ም. አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ዋልድባን፣ ደብረ ዐባይን፣…… ሌሎችንም የኢትዮጵያ መካናት በስደት ከልጇ ጋር ባርካ አኵስም ጽዮን ላይ መጥታ የገባችበትና የባረከችበት፤ በወቅቱም አኵስምና አካባቢዋ በብርሃን ጎርፍ የተጥለቀለቁበት በመኾኑ፤ /ታሪከ ዋልድባ፣ ታሪከ አኵስም፣ ድርሳነ ዑራኤል፣ ....)

፮ኛ. በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቅዱሳን ጻድቃን ነገሥታት አብርሐ ወአጽብሐ አማካኝነት መሥዋዕተ ኦሪት ሲሰዋባት የቆየችው አኵሱም ጽዮን፤ ጽዮን ማርያም ተብላ ባለ 12 መቅደሶች ባሏት በወርቅና በዕንቊ ያሸበረቀች ቤ.ክ ሠርተው ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበትና ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ የታወጀበት፡፡

፯ኛ. በየጊዜው (በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አማካኝነት ስትፈርስ) ወደ ዝዋይ፣ ወደ ጣና ቂርቆስ፣ …… ተሰድዳ ቆይታ፤ ተመልሳ (ከዮዲት በኋላ በአንበሳ ውድምና፤ ከግራኝ በኋላ በአፄ ፋሲል የታነጹት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን) ቅዳሴ ቤቷ የተከበረበት በመኾኑ፡፡

፰ኛ. ወደ አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም በቦታው ርቀት ለመሳለም ላልቻሉ ክርስቲያኖች ዳግሚት ደብረ ጽዮን በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አዲስ አለም ላይ የተሠራችበት በመኾኑ፡፡

፱ኛ. ሴቶችም ወንዶችም የሚያስቀድሱበትና ያለ ዐምድ ዕፁብ ድንቅ በኾነና በሃግያ ሶፍያ ቤ.ክ. አምሳል የተሠራው የጽዮን ቤተ ክርስቲያን (ኅዳር 21 ጾም በመኾኑ ቅዳሴ ቤቷ የተከበረው ግን ጥር 30 ቀን 1957 ዓ.ም ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ዐፄ ኀይለ ሥላሴ፣ እቴጌ መነን፣ የታላቋ ብሪታንያ ንግሥት ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥና ልዑል ፊልፕ በተገኙበት ቢሆንም) ቅዳሴ ቤት የተከበረበት በመሆኑ፡፡
————
#ታቦተ_ጽዮንና #ጽዮን_ድንግል_ማርያም_

፠ ታቦተ ጽዮንን፤ ሌዋውያን ከበዋት ውዳሴ፥ ዝማሬ ያቀርቡላት እንደነበረው፤
✤ ዛሬም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ካህናትና ምእመናን ከሩቅ እና ከቅርብ ተሰብስበው በማኅሌት፥ በዝማሬ፥ በቅዳሴና በውዳሴ ያከብሯታል፡፡
፠ ታቦተ ጽዮን በደብተራ ኦሪት በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የኖረች ፥ የዮርዳኖስን ባሕር የከፈለች /ኢያሱ 3÷14-17/ ፥ ቅጽረ ኢያሪኮን ያፈረሰች /ኢያሱ 6÷1-21/ ፥ ዳጎን የተባለ የፍልስጤማውያንን ጣዖት የቈራረጠች /1ኛ ሳሙ. 5÷1-5/ ፥ በድፍረት ሊነካ የሞከረውን ኦዛን የቀሰፈች /1ኛ ሳሙ. 6÷6/ ፥ በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀምጣ ቤቱን በበረከት የመላች /2ሳሙ 6÷12/ ፥ ዳዊት የዘመረላት /2ሳሙ 6÷14/ ፥ ጠቢቡ ሰሎሞን በቤተ መቅደስ በክብር ያኖራት /1ኛ ነገ፣ 8÷1/ ፥ የእግዚአብሔር የክብር መገለጫ ናት፡፡
✤ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ንጽሐ ጠባይዕ ሳያድፍባትና የቅድስና ባሕርይ ሳይጎድፍባት፤ (በማየት፣ በመስማት፣ በመዳሰሰ፣ በማሽተት አንዳችም እድፍ ጉድፍ ሳያገኛት)
በንጽሕናና (በኀልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር) በቅድስና ጸንታ በኀጢአት ሳትለወጥ ኖራለች፡፡ /ውዳሴ ማርያም፣ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም፤ አንቀጸ ብርሃን፣ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ/ እንዲሁም ‹‹ምክንያታዊ ነውር ኃጢአት የሌለብሽ የኀጢአት ሸታ ያልደረሰብሽ ንጽሕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና ክብርት በልዕልና አንቺ ነሽ» ብሏታል ጠቢቡ ሰሎሞን /መሓ. 4÷7/
፠ ታቦተ ጽዮን በከበረ ወርቅ እንደተሸለመች
✤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ እና በንጽሐ ልቡና የተሸለመች ያጌጠች ናት፡፡
፠ ታቦተ ጽዮን የቃለ እግዚአብሔር ማደሪያ እንደሆነች፤
✤ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያምም ለአካላዊ ቃል ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያ ኾናለች፡፡ «ድንግል ማርያም ሆይ ሰማይና ምድርን ለፈጠረ አምላክ ለእርሱ ማደሪያ ሆንሽ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀንሸ ቻልሽው ተሸከምሽው ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ለመወሰን የታመንሽ አንቺ ነሽ» /ውዳሴ ማርያም፣ ቅዱስ ኤፍሬም/
——-
**** በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም እና በቃል ኪዳኑ ታቦት መካከል ጥልቅ የሆነ ምሥጢራዊ ትምህርት አለ፡፡ /ዘፀ. 25÷9-20/፡፡ ይህንንም በተመለከተ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል ምሥጢሩን ከምሥጢር አመሳጥሮ፤ እንደ ሸማ አንከባሎ፥ እንደ ወርቅ ከብልሎ እንዲህ አስቀምጥታል፤
«ታቦተ አምላከ እስራኤል ጽዮን ዘነገደት ምድረ ኢሎፍሊ፤
ወቀጥቀጠቶ ለዳጎን ነፍሳተ ብዙኃን ማህጎሊ፡፡
አመ ነገደት ቊስቋመ በኀይለ ወልዳ ከሃሊ፤
ወድቁ አማልክተ ግብፅ መናብርተ ሰይጣን ሐባሊ፤
ወተኀጉሉ ኲሎሙ ዘቦሙ አስጋሊ፡፡
ወደ ኢሎፍሊ ምድር ተማርካ የሔደች የእስራኤል አምላክ የቃል ኪዳኑ ታቦተ ጽዮን የብዙዎችን ነፍሳት ያጠፋ ዳጎንን ሰባበረችው፡፡ ድንግል ማርያምም ሁሉን ማድረግ ከሚችለው ከልጇ ጋር ግብፅ ወደሚባል ሀገር በሔደች ጊዜ የሐሰተኛ ሰይጣን ዙፋኖች የሆኑ የግብፅ ጣዖታት ፈረሱ ጠንቋይ አስጠንቋይ ያላቸው ሁሉ ዐፈሩ» /ኢሳ 19÷1፣ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል/

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
#በጽዮን_ስም_የተመሠረቱና_ዐቢይ_ዓመታዊ_ክብረ_በዓላቸው_ኅዳር_21_የኾኑ
✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አኵሱም ደብረ ጽዮን ማርያም (ከክርስቶስ ልደት 980 ዓመታት በፊት በቀዳማዊ አፄ ምኒልክ ዘመን ታቦቷ የመጣው)
✣ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ ዓለም ደብረ ጽዮን ማርያም (በዳግማዊ አፄ ምኒልክ ተመሠረተች)
✣ዝዋይ ደብረ ጽዮን ማርያም (ደቡብ ሸዋ)
✣ሳዶቅ አምባ ማርያም (በ1670 ዓ.ም. በአባ ሳዶቅ የተመሠረተች ፥ ሰሜን ተራሮች)
✣እንፍራንዝ ደብረ ጽዮን ማርያም (ጥንታዊዋ ደብር)
✣ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ደረስጌ ደብረ ጽዮን ማርያም (በወርቅና በዕንቊ ተደርጋ በራስ ውቤ የታነጸች፤ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የነገሠባት፤ ስሜን፣ ራስ ደጀን አጠገብ)
✣ ደብረ ጽዮን ማርያም (ነቀምት)
✣ ደብረ ጽዮን ሰላም አድርጊው ቅድስት ማርያም (ባሕርዳር)
✣ አርባ ምንጭ ደብረ ጽዮን ማርያም
✣ ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ማርያም (እንግሊዝ ፥ ለንደን)

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ሥርዓተ ዋዜማ ዘኅዳር ጽዮን


መኃትዉ አቡነ ቤት በ፫ት:-
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት፤ኲለንታሃ ወርቅ ሰብዓቱ መኃትዊሃ ወ፯ቱ መሣዉር ዘዲቤሃ"ሃሌ ሉያ፫"ኢትፍራህ ዘካርያስ ተሰምዓ ፀሎትከ።

ዋይዜማ በ፩:-
ሃሌ ሉያ ኢኃደጋ ለምድር እምቅድመ ዓለም ወእስከ ለዓለም፤እንበለ ካህናት ወዲያቆናት፤ዘካርያስ ካህን ነቢይ ወሰማዕት፤ዘርእየ፤ተቅዋመ ማኅቶት።

ምልጣን
ዘካርያስ ካህን ነቢይ ወሰማዕት ዘርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ዘርእየ ተቅዋመ ማኅቶት።

አመላለስ
ዘርእየ ተቅዋመ ማኅቶት/፪/
ዘርእየ ተቅዋመ ማኅቶት/፬/

በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ፦
ካህን ወነቢይ ወሰማዕት ሊቀ ካህናት ካህን ወነቢይ።

እግዚአብሔር ነግሠ
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ኲለንታሃ ወርቅ ዓረፋቲሃ ዘዕንቊ ወመሰረታ ዘጽድቅ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን።

ይትባረክ
አጽምእ ሰብአ ምዕመናነ(የአቋቋም)መሐይምናነ አርያሃ ወዘካርያስሃ ወልደ በራክዩ።

ሠለስት ነያ ሀገር
ዕዝራኒ ርእያ በርእየተ ብእሲት እምነ ይእቲ ቤተ ክርስቲያን ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት።

ሰላም ብርሃነ ሕይወት ቤት በ፪
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ኲለንታሃ ወርቅ ዓረፋቲሃ ዘዕንቊ ፯ቱ መሐትዊሃ ወ፯ቱ መሣውር ዘዲቤሃ እዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት ሰላማዊት።
 
   አመላለስ
  እዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት/፪/
  ለጽዮን ቅድስት ሰላማዊት/፬/።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሥርዓተ ማህሌት አመ ፳ወ፩ ለኅዳር ጽዮን ማርያም

የኅዳር ጽዮን
#ሥርዓተ_ማኅሌት

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር  ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ፤ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት፤እንዘ ትበኪ ከመ ብእሲት፡፡

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክር ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረት ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእም ቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡

ዘካርያስ ተቅዋም ዘወርቅ፤ዘሕዝቅኤል ነቢይ ዕፁት ምሥራቅ ለመሠረትኪ የኃቱ ዕንቈ ሰአሊ ለነ ማርያም በአሚን ንጽደቅ፡፡

ነግስ
ነቢያተ እሥራኤል ጸሐፉ በመጽሐፎሙ እሙነ፤ነገረ ሰቆቃው ወላህ በዘመኖሙ ዘኮነ፤ለባቢሎን ውስተ አፍላጋ አመ በጼዋዌ ነበርነ፤ውስተ ኵሃቲሃ እንዚራቲነ ሰቀልነ፤ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን እምነ፡፡

ዚቅ
ወይቤላ ኢትሬእዪኑ ላሃ ዚአነ፤እንተ ረከበተነ በእንተ ጽዮን፤ዕዝራኒ ርእያ ወተናገራ።

ወረብ
ወይቤላ ኢትሬእዪኑ ላሀ ዚአነ እንተ ረከበተነ/፪/
ዕዝራኒ ርእያ ወተናገራ/፪/

መልክዓ ማርያም 
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤እምነ ከልበኔ ወቍስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ማርያም ድንግል ለባሲተ ዐቢይ ትዕዛዝ፤ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ፡፡

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤እምነ ጽዮን በሀ፤ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ሥርጉት በስብሐት፤ዓረፋቲሃ ዘመረግድ፤ሥርጉት በስብሐት፤ወማኅፈዲሃኒ ዘቢረሌ፤ሥርጉት በስብሐት፤እምስነ ገድሎሙ ለሰማዕት፤ሥርጉት በስብሐት፤ታቦተ ሕጉ ለንጉሥ ዐቢይ፤ሥርጉት በስብሐት፤እንተ ክርስቶስ መሠረተኪ፤ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ፡፡

ወረብ

እንተ ክርስቶስ መሠረትኪ ፀሐየ ጽድቅ ያበርህ ለኪ ፀሐየ ጽድቅ/፪/
ለሰማዕት ሥርጉት በስብሐት ሥርጉት በስብሐት/፪/

መልክዓ ማርያም፦
ሰላም ለአስናንኪ ሐሊበ ዕጐልት ዘተዛወጋ፤ወመራዕየ ቅሩፃተ እለ እምሕፃብ ዐርጋ፤ማርያም ድንግል ለደብተራ ስምዕ ታቦተ  ሕጋ፤አፍቅርኒ እንበለ ንትጋ ለብእሴ ደም ወሥጋ፤ዘየዐቢ እምዝ ኢየኃሥሥ ጸጋ፡፡

ዚቅ
ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር በካህናት ሕፅርት፤ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት፤ንጉሥኪ ጽዮን ኢይትመዋዕ ለፀር ወኢየኃድጋ ለሀገር፡፡

ወረብ
ታቦተ ሕጉ ለእግዚአብሔር በካህናት ሕፅርት ወበመንፈስ ቅዱስ ክልልት/፪/
ንጉሥኪ ጽዮን ኢይትመዋዕ ለፀር ወኢየኃድጋ ለሀገር/፪/

መልክዓ ማርያም፦
ሰላም ለከርሥኪ ዘአፈድፈደ ተበጽዖ፤እምታቦተ ሙሴ ነቢይ ለጽሌ ትእዛዝ ዘየኀብኦ፤ማርያም ድንግል ጊዜ ጸዋዕኩኪ በአስተብቍዖ፤ለፀርየ ብእሴ አመጻ ኀይለ ዚአኪ ይጽብኦ፤እስከነ ያስቆቁ ጥቀ ድኅሪተ ገቢኦ፡፡

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም ወበጸሎት፤ተመጠወ ሙሴ ኦሪተ፤ጽላተ አሥሮነ ቃላተ፡፡

ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በጾም ወበጸሎት/፪/
ተመጠወ ሙሴ ኦሪተ ጽላተ አሥሮነ ቃላተ/፪/

መልክዓ ማርያም
ሰላም ለመከየድኪ እለ ረከቦን መከራ፤እምፍርሃተ ቀተልት ሐራ እንበለ አሣእን አመ ሖራ፤ማርያም ጽዮን ታቦተ ቃለ ጽድቅ መንፈቀ ዕሥራ፤ዕጐላት እም ዕጐሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ፤አፍቀርኩኪ አፍቅርኒ እም ይእዜ ለግሙራ።

ወረብ
ማርያም ጽዮን ታቦተ ታቦተ ታቦተ ቃለ ጽድቅ/፪/
ዕጐላት እም ዕጐሊሆን ከመ ኪያኪ አፍቀራ አፍቀራ እም ዕጐሊሆን/፪/

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ወሪድየ ብሔረ ሮሜ፤ለቤተ ክርስቲያን ርኢክዋ፤አእመርክዋ አፍቀርክዋ፤ከመ እኅትየ ሠናየ ኀለይኩ፤እምድኅረ ጉንዱይ መዋዕል፤ወእምዝ እምድኅረ ኅዳጥ ዓመታት፤ካዕበ ርኢክዋ ወትትሐፀብ በፈለገ ጤግሮስ፡፡

ወረብ
ሃሌ ሉያ ወሪድየ ብሔረ ሮሜ/፪/
ለቤተ ክርስቲያን ርኢክዋ አእመርክዋ አፍቀርክዋ ለቤተ ክርስቲያን/፪/

መልክዓ ማርያም፦
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ፤ለዘይስእለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ፤ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ፤ማርያም ዕንቍየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ፤ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ፡፡

ዚቅ
አብርሂ አብርሂ ጽዮን፤ዕንቍ ዘጳዝዮን፤ዘኃረየኪ ሰሎሞን፡፡

ወረብ
አብርሂ አብርሂ ጽዮን አብርሂ/፪/
ዕንቍ ዘጳዝዮን ዘኃረየኪ ሰሎሞን ንጉስ/፪/

ማኅሌተ ጽጌ
ዘካርያስ ርእየ ለወርኃ ሳባጥ በሠርቁ፤ተአምረኪ ለዘይት ማእከለ ክልኤ አዕጹቁ፤ማርያም ጽዮን ለብርሃን ተቅዋመ ወርቁ፤ዕዝራኒ በገዳም አመ ወዓለ ዉዱቁ፤ለኅበረ ገጽኪ ጽጌ  ሐተወ መብረቁ፡፡

ዚቅ
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፯ቱ መኃትዊሃ፤ወ፯ቱ መሣውር ዘዲቤሃ፤ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት፤ዘኲለንታሃ ወርቅ ወያክንት፤ዕዝራኒ ርእያ ለጽዮን ቅድስት እንዘ ትበኪ ከመ ብእሲት፤ዕዝራኒ ርእያ በርእየተ ብእሲት፤ወሶበ ርእያ ኢኮነት ብእሲተ አላ ሀገር ቅድስት፤ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ዘኲለንታሃ ወርቅ ወያክንት።።
 
ወረብ
ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን መኃትዊሃ ፯ቱ መኃትዊሃ/፪/
ዕዝራኒ ርእያ በርእየተ ብእሲት/፪/
አንገርጋሪ  
ዓይ ይእቲ ዛቲ እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ፤ከመ ማኅቶት ብርህት ከመ ፀሐይ፤ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት፤ዕዝራኒ ተናገራ ዳዊት ዘመራ፡፡

ምልጣን
ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት፤ዕዝራኒ ተናገራ ዳዊት ዘመራ፡፡

አመላለስ
ዕዝራኒ ተናገራ /፪/
ተናገራ ዳዊት  ዘመራ/፬/

ወረብ ዘአንገርጋሪ
ሙሴኒ ርእያ ሙሴኒ ርእያ ሀገር ቅድስት/፪/
ዕዝራኒ ተናገራ ተናገራ ዘመራ ዳዊት/፪/

እስመ ለዓለም
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት፤ኵለንታሃ ወርቅ በየማና ወበፀጋማ አዕፁቀ ዘይት፤ደብተራ ፍጽምት ሀገር ቅድስት፤ነቢያት ይትፌሥሑ በውስቴታ፤ሐዋርያት ይትኃሠዩ በውስቴታ፤ሐዋርያት ይትኀሠዩ በውስቴታ፤ወዳዊት ይዜምር በውስተ ማኅፈዲሃ፤ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ በቃለ ዳዊት ይሴብሑ፤ወይብሉ ኵሎሙ ሃሌ ሉያ፡፡

አመላለስ
ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ በቃለ ዳዊት ይሴብሑ/፪/
ወይብሉ ኵሎሙ ሃሌ ሉያ(፬)

ወረብ ዘእስመ ለዓለም
ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ኩለንታሃ ወርቅ በየማና ወበጸጋማ አዕጹቀ ዘይት/፪/
ነቢያት ይትፌስሑ ሐዋርያት ይትኃሠዩ በውስቴታ ወዳዊት ይዜምር በውስተ ማኅፈዲሃ/፪/

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
ስለ ጽዮን ዝም አልልም
ኢሳ 62:1
በሚገባ ይደመጥ

Size:-21.4MB
Length:-1:33:18

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን

ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን 
ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን
ውስተ አፍላገ ባቢሎን
ህየ ነበርነ ወበከይነ
እንዚራቲነ ሰቀልነ ውስተ ኲሓቲሃ

ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን
ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ
ተቀምጠን አለቀስን
መሰንቆአችንን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ
አዝ
ፅኑ መከራን ተቀበልን ተጨነቅን በፈተና
የደዌ ሞት በላያችን እንደዝናብ ወርዷልና
አሕዛብም ዘበቱብን እንዲህ ብለው በየተራ
ዘምሩለት ለአምላካችሁ ቢያድናችሁ ከመከራ

እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ
የማረኩን በጦራቸው በኃይላቸው የተመኩ
በጽዮን ደጅ ያለፍርሃት የጽዮንን ክብሯን ነኩ
ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ
ባቢሎንን አሻገረ የማረኩንን በትኖ

እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ
ስጋችንን ሊገንዘን የሞት ጥላ ቢያጠላም
እናልፋለን ሁሉን ባንቺ
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
ቅድስት ሆይ ከባረክሽን
እንድናለን ከደዌያችን
ለስጋና ለነብሳችን መድኃኒት ነሽ እናታችን

እግዚአብሔር ጽዮንን በመንግስቱ መርጧታልና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ሥርዓተ ማኅሌት ዘህዳር ፳፬ ካህናተ ሰማይ ወተክለ ሃይማኖት


ለማንኛውም ወርኃዊ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለመታክፍቲክሙ መሠረተ ዓለም እለ ፆሩ፤ኖትያተ ኖኅ ሥላሴ ወዕፀወ ዐባይ ሐመሩ፤ዲበ መንበርክሙ ሰብአ ሶበ አምላክ ነጸሩ፤ኪሩቤል ወሱራፌል ታህተ እገሪሁ ገረሩ፤እስመ ለሊሁ አዘዘ ወእሉ ተፈጥሩ፡፡

ዚቅ
እሉ ኪሩቤል ወሱራፌል የዓርጉ ሎቱ ስበሐት፤ እንዘ ይብሉ፤ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ እግዚአብሔር፤አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።

ዚቅ ዓዲ፦
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር፤ጽርሐ አርያም ማኅፈዱ መካነ ትጉሃን ዓፀዱ፤ካህናተ ሰማይ ቀዉማን በዓዉዱ፤አክሊላቲሆሙ ያወርዱ፤ቅድመ መንበሩ ይሰግዱ፤ይርዕዱ፤ኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ።

ነግስ
ሰላም ለክሙ ሚካኤል ወገብርኤል፤ሱራፌል ወኪሩቤል ኡራኤል ወሩፋኤል ሶርያል ወፋኑኤል፤ አፍኒን ወራጉኤል ወሳቁኤል፤ሊቃናተ ወነድ ዘሰማያዊት ማእፈድ፤በንተ በግዑ እቀብዋ ለዛቲ አጸድ።

ዚቅ
ሊቃናተ ነድ መላእክተ ምሕረት እለ ድልዋን ለሣህል፤ሰአሉ አስተምህሩ ለነ፤አስመ በጸሎት ትንብልናክሙ፤ትድኅን ወኢትማስን ሀገር።

ነግስ
ይትባረክ ስምኪ ማርያም ለዘአውፃእከነ እምፀድፍ፤በርኅራኄኬ ትሩፍ፤ይዌድሱኪ ኪሩቤል በከናፍር ወአፍ፤ሐራ ሰማይ ትጉሃን አኁዛን ሰይፍ፤አምሳለ ደመና ይኬልሉኪ በክንፍ

ዚቅ
ብፅእት አንቲ ማርያም ወዉድስት በአፈ ኩሉ፤ኪሩቤል ይሴብሑኪ ወሱራፌል ይቄድሱኪ፤መላእክት በበነገዶሙ ይትቀነዩ ለኪ፤ወለቶሙ ለነቢያት ይእቲ ማርያም፤እሞሙ ለሐዋርያት ይእቲ ማርያም፤ደብተራ ፍጽምት እንተ ኢገብራ እደ ሰብእ፤ዕፁበ ግብረ መንግስተ ሥጋ ኢያርኃወ፤ዕፁበ ግብረ።

ነግስ ዘዝክረ ቃል ፦
ካህናቲከ ይለብሱ ጽድቀ፤ወጻድቃኒከ ይትፌስሁ ጥቀ፤ተክለሃይማኖት በልብሱ ኮከበ ብርሐን ሠረቀ፤ካህናተ ሰማይ ዘይትአፀፋ መብረቀ፤አፍቀርዎ ወኮንዎ ማእረ ወአውቀ።

ዚቅ
ለእሙንቱ ሐራ ዕበዮሙ ተዓዉቀ፤ተክለ ሃይማኖት ዜነወ ጥዩቀ፤በእንቲአነ ይተንብሉ ጽድቀ፤ካህናተ ሰማይ ይሴብሑ ሊቀ፤ተ ልቢቦሙ ዘእሳት መብረቀ።

ዓዲ
ይቤ መምህርነ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ፤ለልየ ርኢኩ መንበሮ ለሊቅ፤ካህናት የዓጥኑ በማዕጠንት ዘወርቅ፤እምገበዋቲሁ ይወጽእ መብረቅ።

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክር ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረት ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእም ቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡

ዚቅ
አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት፤ወያሚሆሙ ለካህናት፤ነያ ጽዮን መድኃኒት።

ዚቅ ዓዲ ፦
ሱራፌል ወኪሩቤል ይኬልልዋ፤ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና መድሐኒት ይዕቲ፤ንብረታ ጽሙና፤ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት።

መልክዐ ተክለ ሃይማኖት፦
ሰላም ለእንግዳከ ዘጥበብ ምዕላድ፤ወዘመንፈስ ቅዱስ ማህፈድ፤ተክለሃይማኖት ያእቆብ እንተ እግርከ ግሙድ፤ያስተበጽዑከ ሰማያዊያን ነገድ፤ እለ ይገሥሡ እሳተ በዕድ።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ ብሩህ ከመ ፀሐይ ፀዓዳ ከመ በረድ፤ዘቦአ ቤተ መቅደስ ሃሌ ሉያ፤ዝኬ ውእቱ ገብርኤል መልአክ፤ ዘባጢሁ ለእሳት፤ዘልብሱ መብረቅ ሐመልማለ ወርቅ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ፤አስተብዕዎ ኩሎሙ መላእክት።

መልክዐ ተክለ ሃይማኖት፦
ሰላም ለአዕዳዊከ ዘገስሳ ነዶ፤ለእግዚአብሔር አምላክ ስብሐተ መላእክት ዘየዐውዶ፤ተክለሃይማኖት አብርሃም ዘጻመውከ በተአንግዶ፤አድኅነኒ እምቃሳሜ ወይን አመ ይሌዕል ማዕጸዶ፤እስመ አበ ስሩዕ ከመ ያድኅን ወልዶ

ዚቅ
ለካህናት ሰመዮሙ መረግደ፤እደዊሆሙ ይገሣ ነደ፤በቅድመ አቡሁ ይሠዉዑ ወልደ፤ወማዕጠንቶሙ ይትፈቀር ፈድፋደ።

መልክዐ ተክለ ሃይማኖት፦
ሰላም ለኩልያቲከ ዘፈተኖን በትዕግሥት፤ኢየሱስ ክርስቶስ አበ ብርሃናት፤ተክለሃይማኖት ሰጋዲ ከመ መላእክት፤ጸሎትከ ዘገበርክሃ እስከ ኊላቔ ምእተ አመት፤መድኃኒት ትኩነኒ እምግሩም ቅስት።

ዚቅ
ይሰግድ በብረኪሁ፤እስከ ይመጽእ ሥርየት ለኃጥአን፤ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤መኑ ከማከ ክቡር።

መልክአ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ፦
ሰላም እብል ለስእርተ ርእስክሙ ዘላህበሰ፤ዘቦቶን ዕፍረት ዘመአዛሁ እጹብ፤ዕሥራ ወርብዕ ሰማያዊያን አርባብ፤ምስለ አብያጺሁ እለ ይቄድሱ ኪሩብ፤ እምኔክሙ ይትአኰት ወይሴባህ አብ።

ዚቅ
መንበረ ልዑል የዓጥኑ ቃለ ፈጣሪ ይሰምዑ፤ብፁዓን ካህናት ጽርሐ አርያም የኃድሩ።

መልክአ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ፦
ሰላም ለእስትንፋስክሙ እስትንፋስ ርትዕ ወሣህል፤ኀዋኅወ ሰማይ አንትሙ እለ ሱራፌል፤ለእግዚአብሔር ዘይነብር ዲበ መንበሩ ልኡል፤ይቀውሙ ዓውዶ ወይኬልሁ በቃል፤ ዘነጸረክሙ ኢሳያስ ይብል።

ዚቅ
ኢሳይያስኒ ይቤ ርኢክዎ ለእግዚአብሔር፤ይነብር ዲበ መንበሩ ነዋህ ወብሩህ፤ወምሉዕ ቤተ ስብሐቲሁ፤መልዓ ምድር ስብሐቲሁ፤አዕላፈ አዕላፋት መላዕክት፤ወትዕልፊተ አዕላፋት ይቀዉሙ ዓዉደ።

መልክአ ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ፦
ሰላም ለእመታቲክሙ መንፈሳዊያን አንጋድ፤ ዘኅብራቲክሙ አምሳለ መረግድ፤ሊቃናት ዕሥራ ወ፬ቱ በፍቅድ፤ረስይዎ ከመ አዘቅት ወከመ ስቁር ጽኢድ፤ለኀጕለ ህይወትየ ዘይፈቅድ አብድ።

ዚቅ
ለካህናተ ሰማይ ኅብራቲሆሙ ከመ መረግድ፤ ወአልባሲሆሙ ፀዓዳ ከመ በረድ፤ ይቤ ተክለ ሃይማኖት ዘገብረ ሰማ፤ ለሥላሴ ይደሉ ስብሐት፤ እስመ ወሀቡነ ሲሳየ ዕለት፤ ኅብስተ ቅዳሴ ዘይሴሰይዎ መላእክት።

ማህሌተ ጽጌ፦
ዓቢይ ውእቱ ተአምር ጸግዮትኪ በድንጋሌ፤ወፈርዮትኪ በንጽሕ ቁርባነ አምልኮ መጥለሌ፤ማዕጠንተ ሱራፌ ዘወርቅ ወጽዋዓ ኪሩብ ዕንቈ ቢረሌ፤አልቦ ጸሎት ወአልቦ ትንባሌ፤እንበሌኪ ማርያም ዘየዓርግ ሉዓሌ።

ዚቅ
ናስተማስለኪ ኦ እግዝእትነ ማርያም፤በማዕጠንት ዘወርቅ፤ዘውስተ እደዊሆሙ ለሊቃነ ካህናት ሰማያዉያን፤እለ ይከዉኑ ጸሎተ ኩሎሙ ቅዱሳን መሐይምናን፤እምዲበ ምድር በዉስተ ማዕጠንቶሙ፤ከማሁ በስእለተ ስምኪ፤የዓርጉ ስእለቶሙ ለዕጓለ እመሕያዉ፤ዉስተ ማኅደረ ሥሉስ ቅዱስ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።

ምልጣን
ሰአሉ ለነ ጻድቃን ውሉደ ብርሀን፤ከመ ንድኅን በጸሎትክሙ፤ጸልዩ ለነ ካህናት አግብርት እግዚአብሔር፤እስመ ለክሙ ይቤለክሙ፤አማልክት አንትሙ፤ወደቂቀ ልዑል ኩልክሙ።

እስመ ለአለም፦
ጻድቅኒ ይቤ ለልየ ርኢኩ፤እሳት መንበሩ ለእግዚአብሔር፤ይወጽእ ኃይለ መለኮት ወክብር፤አመ ውስተ ውእቱ መንበር፤ህልዉ ካህናት ይቀውሙ ዓውዶ፤ ኅብራቲሆሙ ይመስል መረግደ፤ማ፦ ውእቱኒ ባረክሙ፤ወወሀቡ ስብሀት ለፈጣሪዎሙ።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
እርሱ ግን ተኝቶ ነበር
                         
Size 32.6MB
Length 1:33:34

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
ሰማይ ስማ ምድርም አድምጪ እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል 
                                                  
Size:- 53.7MB
Length:-2:34:05
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/25 10:23:14
Back to Top
HTML Embed Code: