Telegram Web Link
"እኛ ግን ይህን እንቃወም ከኃጢያት በቀር ምንም ክፉ ከበጎ ሥራ በቀርም ምንም በጎ እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኘው ነገር እንዴሌለ ለይተን ልናውቅ ይገባናል። ደስታን የሚያመጣው መንፈሳዊ ጸሎት እንጂ ጽኑ መጠጥ አይደለም ደስታን የሚያመጣው ቃለ እግዚአብሔር እንጂ ወይን አይደለም..ወይን የነፍስ መታወክ ያመጣል ፡ቃለ እግዚአብሔር ግን ጸጥታን ያመጣል።ወይን የነፍስ ሁከትን ያመጣል፡ ቃለ እግዚአብሔር ግን ሁካታን ያርቃል። ወይን ዓይነ ልቡናን ያጨልማል ፡ ቃለ እግዚአብሔር ግን የጨለመውን ዓይነ ልቡና ያበራል። ወይን (ስካር) ቀድሞ ያልነበሩትን ኀዘናት ያመጣል፣ ቃለ እግዚአብሔር ግን ቀድሞ የነበሩትንም ሳይቀር ያርቃል።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሥርዓተ ማኅሌት ዘዘመነ ጽጌ "በዓለ ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ፣ ወኢዮብ ጻድቅ፣ ወአቤል" "፮ኛ ሳምንት" "#ተፈጸመ"

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
ሃሌ ሉያ፤ ለክርስቶስ ይደሉ ስብሐት፤ ለዘአብጽሐነ እስከ ዛቲ ሰዓት፤ እግዚአ ለሰንበት፤ አኮቴተ ነዓርግ ለመንግሥትከ፤ ምድረ በጽጌ አሠርጎከ።

ማኅሌተ ጽጌ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ ዘኢየኃልቅ ስብሐተ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ።

ወረብ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስዕልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ/፪/
ዘኢየኃልቅ "ስብሐተ"/፪/ እንዘ እሴብሐኪ/፪/

ዚቅ
እለ ትነብሩ ተንሥኡ፤ ወእለ ታረምሙ አውሥኡ፤ ማርያምሃ በቃለ ስብሐት ጸውኡ፤ ቁሙ ወአጽምዑ ተአምረ ድንግል ከመ ትስምዑ፤ ጸልዩ ቅድመ ስዕላ ለቅድስት ድንግል፤ መርዓተ አብ ወእመ በግዑ።

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

ወረብ
እንዘ ተሐቅፊዮ "ለሕፃንኪ"/፪/ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ሚካኤል/፪/

ዚቅ
ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ንባብኪ አዳም፤ ከመ ፍሕሶ ቀይሕ ከናፍሪሃ፤ እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላዕክት፤ አልቦ ዘይመስል ዘከማኪ ክብረ፤ እግዚአ ለሰንበት በማኅፀንኪ ተጸውረ።

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል ምስለ ኲሎሙ መላእክት፤ ከመ ታዕርጊ ጸሎተነ ጊዜ መንፈቀ ሌሊት።

ማኅሌተ ጽጌ
ሰዊተ ሥርናዩ ለታዴዎስ ወለበርተሎሜዎስ ወይኑ፤ እንተ ጸገይኪ አስካለ በዕለተ ተከልኪ እደ የማኑ፤ ማርያም ለጴጥሮስ ጽላሎቱ ወለጳውሎስ ሰበኑ፤ ብኪ ምውታን ሕያዋነ ኮኑ፤ ወሐዋርያት መላእክተ በሰማይ ኮነኑ።

ወረብ
ማርያም ለጴጥሮስ "ጽላሎቱ"/፪/ ወለጳውሎስ ሰበኑ/፪/
ወሐዋርያት "መላእክተ"/፪/ በሰማይ ኮነኑ/፪/

ዚቅ
ኦ መድኃኒት ለነገሥት፤ ማኅበረ ቅዱሳን የዓውዱኪ፤ ነቢያት የዓኲቱኪ፤ ወሐዋርያት ይሴብሑኪ፤ እስመ ኪያኪ ኀቤ ለታዕካሁ ከመ ትኲኒዮሙ ማኅደረ፤ መላእክት ይኬልሉኪ፤ ጻድቃን ይባርኩኪ፤ አበው ይገንዩ ለኪ፤ እስመ ኪያኪ ኀቤ ለታዕካሁ ከመ ትኲኒዮሙ ማኅደረ።

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቌ ባሕርይ ዘየኀቱ፤ ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤ አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤ አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ዘየኀቱ እምዕንቊ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግስቱ ለጊዮርጊስ መንግስቱ ለሕዝበ ክርስቲያን/፪/

ዚቅ
ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት፤ ወስብሕት በሐዋርያት፤ አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ፤ ወትምክሕተ ቤቱ ለ፳ኤል።

ማኅሌተ ጽጌ
ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኮስኮስ ዘብሩር፤ ተአምርኪ ንፁሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር፤ ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር፤ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፤ ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር።

ወረብ

ናሁ "ተፈጸመ"/፪/ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/፪/
"አስምኪ ቦቱ"/፪/ ንግሥተ ሰማያት /፪/
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ፤ ጥቀ አዳም መላትኅኪ ከመ ማዕነቅ፤ ይግበሩ ለኪ ኮስኮሰ ወርቅ።


ሰቆቃወ ድንግል
ተመየጢ እግዝእትየ ሀገረኪ ናዝሬተ፤ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፤ በላዕሌኪ አልቦ እንተ ያመጽእ ሁከተ፤ ለወልድኪ ዘየኃሥሦ ይእዜሰ ሞተ፤ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ።


ወረብ
"ተመየጢ"/፪/ እግዝእትየ ማርያም ሀገረኪ/፪/
ወኢትጎንድዪ "በግብጽ"/፪/ ከመ ዘአልብኪ ቤተ/፪/

ዚቅ
ሃሌ ሉያ፤ ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት፤ ወንርዓይ ብኪ ሰላመ፤ ምንተኑ ትኔጽሩ በእንተ ሰላመ ሰጣዊት፤ እንተ ትሔውጽ እምርኁቅ፤ ከመ መድብለ ማኅበር ሑረታቲሀ ዘበስን ለወለተ አሚናዳብ።


መዝሙር
በ፮: ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ፤ ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበት፤ ወጸገወነ ዕረፍተ ከመ ንትፈሣሕ ኅቡረ፤ አዕጻዳተ ወይን ጸገዩ፤ ቀንሞስ ፈረየ፤ ሰሎሞን ጥቀ ኢለብሰ ከመ ፩ እምእሉ።

ዓራራይ
በሰንበት እውራነ መርሐ፤ በሰንበት አጋንንተ አውጽአ፤ እለ ለምጽ አንጽሐ፤ ቃለ ማዕነቅ ተሰምዓ በምድርነ፤ ሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት።

ዕዝል
መንክር ግብሩ ለ፩ እግዚአብሔር አብ ዘላዕለ ኲሉ፤ መንክር ግብሩ ለዘሠርዓ ሰንበተ ለዕረፍት፤ መንክር ግብሩ ለዘአሠርገዋ ለምድር በጽጌያት፤ መንክር ግብሩ ለዘገብረ ብርሃናተ ዓበይተ ባሕቲቱ።

ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤ እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤ እንተ በሥሉስ ትትገመድ፤ ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት ሐረገ ወይን፤ ሲሳዮሙ ለቅዱሳን ሐረገ ወይን፤ ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፤ ወጸገወ ሰላመ ለኵሉ።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናት 
                                                  
Size:- 64.3MB
Length:-3:04:43
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
፯ኛ ዙር ዓመት ፮ኛ ሳምንት
ማሕሌተ ጽጌ ተፈጸመ ጽጌ በዓለ ታዴዎስ ኅዳር ፪
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በጥቂቱ መታመን

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ "በጥቂቱ ታምነሃል በብዙ እሾምሃለሁ!.." ማቴ 25፥21፡፡ ይህም ማለት በምድራዊ ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ በሰማያዊ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ ማለት ነው፡፡ በዚኛው ዓለም ታማኝ ሆነ ከቆየህ በዘለዓለማዊነት ውስጥ እሾምሃለው ማለት ነው፡፡ ይህ መመሪያ በብዙ መስኮች ላይ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል... ዘመዶችህን በመውደድ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ጠላቶችህንም በመውደድ ላይ ይሾምሃል፡፡ ጠላትህን የምትወድበት ጸጋ ያድልሃል ማለት ነው፡፡

በትርፍ ጊዜዎችህ እግዚአብሔርን የምታገለግል ከሆንህ በሕይወትህ ጊዜ ሙሉ በእርሱ ላይ ትኩረት የምታደርግበትን ፍቅር ያድልሃል፡፡ የፈቃድ ኃጢአቶችን ከአንተ በማስወገድ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ያለ ፈቃድ ከሚመጡ ኃጢአቶች ነጻ ያወጣሃል፡፡

ንቁ ኅሊናህን ከክፉ አሳቦች የምትጠብቅ ከሆንህ እግዚአብሔር ንቁ ያልሆነው ኅሊናህን ንጽሕና ያድልሃል፤ ከዚህ በተጨማሪ የህልሞችህን ንጽሕናም ያድልሃል፡፡ ልጅ እያለህ ታማኝ ከሆንህ እግዚአብሔር ውጊያዎች በሚበዙበት በወጣትነትህ ዘመን ውስጥም ታማኝነትን ያድልሃል ሌሎች ሰዎች ላይ በቃላት ብቻ የማትፈርድባቸው ሆነህ በመገኘትህ ታማኝ ከሆንህ ይበልጥ አስቸጋሪ በሆነው በአሳብ እንዳትፈርድባቸው ያስችልሃል፡፡ ልክ እንደዚሁ ራስህን ከውጫዊ ንዴት በመጠበቅ ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አውስጣዊ ቁጣ፣ንዴትና ቅናት ነጻ ያወጣሃል፡፡

በተለመዱ መንፈሳዊነቶች (በመንፈስ ፍሬዎች) ላይ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የመንፈስ ስጦታዎችን ያድልሃል፤ በመጀመሪያው ላይ ታማኝ ሆነህ ካልተገኘህ ሁለተኛውን ፈጽመህ ልታገኘው አትችልምና፡፡

እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሚፈትሽህ በጥቂት ነገር ነው፡፡ በዚህች በጥቂቷ ነገር ላይ ታማኝ መሆንህ ካረጋገጥህ እርሱ በሚበልጠው ነገር ላይ ይሾምሃል፡፡ ውድቀትህንና አለመታመንህን በጥቂቷ ነገር ላይ ከገለጽህ ግን እግዚአብሔር በሚበልጠው ነገር ላይ አይሾምህም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና፦ "ከእረኞች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱህ ቢደክሙህ ከፈረሶች ጋር መታገል እንዴት ትችላለህ?" ኤር 12፥5 ብዙ ሰዎች ዝቅተኛውን ኃላፊነት መወጣት ሳይችሉ ከፍተኛውን ኃላፊነት ለመቀበል ማሰባቸው እጅግ አስደናቂ ነገር ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ ሳይጠቀሙ ተጨማሪ ጸጋ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ናቸው፡፡ ይህን ሲያደርጉም "በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ" የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በመዘንጋት ነው፡፡

"መንፈሳዊ ቃላትና ጥቅማቸው" ከሚለው #አያሌው_ዘኢየሱስ ከተረጎመው #የብጹዕ_አቡነ_ሽኖዳ መጽሐፍ የተወሰደ!!!
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
“ሕብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወጸአድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ ሥሙር አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር”

"የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጒርጒር ጠቃጠቆ የኾነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው፤ እነሆ የተወደደ (መልካም) ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በጒያሽ (በዕቅፍሽ) እንዲጠጋ (እንዲደገፍ፣ እንዲንተራስ) በርሱ ዐማጽኚ፡፡"

አባ ጽጌ ድንግል (ማህሌተ ጽጌ)
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
‹‹እስከማእዜኑ ትነብሪ ከመ ፈላሲ ወነግድ
ውስተ ርስትኪ ግብኢ እምብሔረ ባዕድ
ብሥራትኪ ድንግል ክብርተ ዘመድ
እስመ ጠፍአ ናሁ ቀታሌ ሕፃናት ብድብድ
በቤተልሔም አልቦ ዓመፃ ወሀይድ፡፡

እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ
ሀገረኪናሁ ገሊላ እትዊ
ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ
ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ዖዝያን ዜናዊ
እምግብፅ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ፡፡››

ትርጉም፡-
በዘመድ የከበርሽ ድንግል ሆይ! ሕፃናትን የሚገድል ድንገተኛ በሽታ ሄሮድስ ስለሞተ በቤተልሔም ቅሚያና በደል የለምና እንግዳ ሆኖ እንደሚኖር ምርኮኛ በባዕድ አገር እስከ መቼ ትኖሪያለሽ? ከስደት የመመለስሽ ብሥራት በነቢያት እንደተነገረልሽ (ሆሴ11÷1፣ ማቴ2፡19÷22) ወደ ርስትሽ ቤተልሔም ተመለሺ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ! ስሙ ናዝራዊ የሚባል ልጅሽን ለአዳምና ለሔዋን ክብር የባሕርይ አባቱ አብ ከግብጽ ይጠራዋል፣ማለት በግብጽ ስደት አይሞትም ኋላ በቀራንዮ ተሰቅሎ ዓለምን ያድናል ብሎ ነቢዩ ዖዝያን (ሆሴዕ) ትንቢት እንደተናገረ እስከ መቼ በባይድ አገር ትኖሪያለሽ? እነሆ ወደ አገርሽ ናዝሬት ተመለሽ፡፡

(ሰቆቃወ ድንግል)
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
Forwarded from Quality Button
የማንን ስልክ መጥለፍ ይፈልጋሉ?🤔
የፍቅረኛዎን ፣ የልጆን ወይስ የጓደኛዎን

እንግዳውስ መፍትሄው ትልቁን የHACKING ቻናላችንን መቀላቀል ነው።👨‍💻
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/+DZMqOdX2io5mNTA0
ኑ ወደ ወይነ ቃና ሕይወት

ተወዳጆች ሆይ! ሕይወታችን ጣዕም አጥቶ፣ እንኳን ከክርስትና ከሰውነትም ወርዶ፣ በሌላ ነገር ተተብትቦብን ሊኾን ይችላል፡፡ ኑ! ኑ ከነትብታባችን፤ ኑ ከነጣዕም አልባነታችን! ኑ ወደ ክርስቶስ እንቅረብና ሕይወታችን ወይነ ቃና ይኹን፡፡

ርኅርኅተ ኅሊና፣ አቁራሪተ መዓት እመቤታችን ዛሬም ታሳስባለች፡፡ ልጇ ወዳጇን “ወይን እኮ የላቸውም፤ ጣዕም እኮ የላቸውም፤ የሕይወት መዓዛ እኮ የላቸውም፤ልጄ ወዳጄ እባክህን ወይነ ቃና አድርጋቸው” እያለች፡፡

እንኪያስ ኑ ከነባዶ ማንነታችን፡፡ ኑ ከነውሃው ማንነታችን፡፡ ኑ ከነ ጣዕም አልባው ማንነታችን፡፡ ኑ ወደ ፍቅር ክርስቶስ እንቅረብ፡፡ ኑ በጸሎት ወደርሱ እንቅረብ፡፡ ኑ በንስሐ ወደ እርሱ እንቅረብ፡፡

ተወዳጆች ሆይ! ስለምን ከነ ሸክማችን እንቆያለን? ስለምን በኃጢአት እንደጐበጥን መሰንበትን እንመርጣለን? ስለምን በፆረ ገሃነም እንደተተበተብን እንኖራለን? ኑ ወደ ክርስቶስ እንቅረብ፡፡ ኑ ሸክማችንን እናራግፍ፡፡ ኑ ዕረፍተ ነፍስን እናግኝ፡፡ ኑ ወይነ ቃና እንኹን፤ ኑ ክርስቲያን (የክርስቶስ፣ ክርስቶሳውያን) እንኹን፡፡

ተወዳጆች ሆይ! የምንናገረው ስለ ቃላት ማማር አይደለም፡፡ ስለ ዘለዓለማዊ ሕይወት እንጂ፡፡ እስከመቼ በስደት? እስከ መቼ ከክርስቶስ ርቆ? እስከ መቼ በሞት ሕይወት? እስከ መቼ በዘፈን? እስከ መቼ በጫት? እስከ መቼ በዝሙት? እስከ መቼ በኃጢአት መንደር? እስከ መቼ? እኮ እስከ መቼ?

ኑ ወደ ወይነ ቃና ሕይወት!!! ቸርና ቅዱስ አባት ሆይ! በትብታብ የተያዘች ሰውነታችንን አበርታት፡፡ አንተን ወደ ማየት እንድትነቃቃ በመንፈስህ እርዳት፡፡ አማናዊው ወይን አንተን ጠጥታም ከክቡር ዳዊት ጋር “አጋንንት ሠሩልኝ፤ አንተ ግን ይንደዳቸው ይቆጫቸው ብለህ ሥጋኽን ሰጠኸኝ፡፡ ርእሰ ልቡናዬን በልጅነት ቀባኸኝ፡፡ ጽዋኽንም አትረፈረፍክልኝ” እያለች ታመሰግን ዘንድ በቸርነት እጅህ ደግፋት፡፡ አሜን!!!

ገብረ እግዚአብሔር ኪደ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ተመየጢ ተመየጢ

ጃንደረባው ሚድያ | ኅዳር 2016 ዓ.ም.

✍🏽 ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ እንደጻፉት

“አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ፤ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ ተመለሽ” መኃ 7፥1 በኖኅ መርከብ ውስጥ ሆኖ ዐይኖቹ አሻግሮ ማየት የማይፈልግ ማን አለ? ከዚያ ሁሉ ጥፋት በኋላ ምድርን መልሶ ማየት ያጓጓል። ለዐርባ ቀናት ከሰማይ የወረደውና ከምድር የገነፈለው ትኩስ ውኃ የተራሮችን ራስ ሳይቀር የሚገሽር ትኩሳት የነበረው ውኃ ነው።

ማንም ቢሆን ለአንድ መቶ ሃምሳ ቀናት ምድርን ይዟት የቆየውን ውኃ መጉደል አለመጉደሉን በልቡ ማውጣት ማውረዱ አይቀርም። በዚህ መካከል የምድሪቱን ዕጣ ፋንታ ሊያሳውቅ የሚችል ታማኝ መልዕክተኛ ማግኘት እንዴት መታደል ነው? መዓቱ ቆሟል፤ በመርከቧ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ የምድሩን ፊት ማየት ይፈልጋሉ። በዚህ ጊዜ ነው ኖኅ ርግብን ምድሩን አይታ እንድትመለስ የላካት። መጀመሪያ ሄደች ለእግሯ ማረፊያ ስላላገኘች ተመልሳ መጣች፤ ምድሩ በውኃ ተሞልቶ ነበርና። ዳግመኛ ላካት የውኃውን መድረቅ ለማመልከት የወይራ ዝንጣፊ ይዛ ተመለሰች ከሰባት ቀን በኋላ መልሶ ላካት አልተመለሰችም። ኖኅም ምድር ከጥፋት ውኃ ማረፏን በዚህ አወቀና ከመርከቡ ወጣ።

ርግቢቱን ወደ ዓለም ልኮ ኖኀ ከመርከብ ወጣ። ለጥፋት ውኃ መምጣት ምክንያት የሆነው ኃጢአት መጉደሉን የምትናገረዋ ርግብ እመቤታችን እስከትመጣ ድረስ የዚህችኛዋ ርግብ አገልግሎት እስከዚህ ድረስ ስለነበረ ነው − መመለሷን ሳይጠብቅ ከመርከብ የወጣው። የኖኅ ርግብ ሳትመለስ በዚያው መቅረቷ እንደ ቁራ የምድሩ ነገር ስቧት አይደለም፤ እውነተኛው ሰላም የሚሰበክበት፣ የጥፋት ውኃ በሚጎድልበት ሳይሆን የሰው ልጅ ከኃጢአት የሚያርፍበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ ርግቢቱ አትመለስም።

ከዚያ በኋላ የተነሡ ነቢያት ይህንን ስለሚያውቁ ነው እንደ ኖኅ ዘመን ከሚበሩት አእዋፍ መካከል የሆነችውን ርግብ ሳይሆን ከሰዎች መካከል አንዷ የሆነችውን ርግብ ተመየጢ ተመየጢ ሲሉ የኖሩት። ከጥፋት ውኃ ሳይሆን ከኃጢአት መውጫ ጊዜው መድረሱን የምታበሥራቸውን ርግብ በሕይወተ ሥጋ መቆየት እስከቻሉበት ዘመን ድረስ ተመየጢ ተመየጢ እያሉ ደጅ ይጠኗታል። ርግቧ ካልተመለሰች ሰላም በምድር ላይ መታወጁን ማን ይናገራል? ቁራም አልተመለሰም። ሌላ መልዕክተኛም አልተገኘም።

መጥቀው ከሚበሩ ንስሮች ይልቅ ለሰላም አብሣሪነት የተመረጠች ይህች ርግብ እንዴት ያለች የተመረጠች ናት? ይህች ርግብ የእመቤታችን ምሳሌ ናት ብለው ሊቃውንት ተርጉመዋል። በሰሎሞን መኃልይ ላይ “ርግቤ መደምደሚያዬ” መኃ 5፥2 ተብላ የተጠራች እመቤታችንን ቅዱስ ኤፍሬም “ተፈሥሒ ኦ ማርያም ርግብ ሠናይት፤ በጎ ርግብ እመቤታችን ደስ ይበልሽ” ብሎ አመስግኗታል። ከዚህ አያይዞ የመልክአ ውዳሴ ደራሲ ደግሞ “ርግበ ገነት ጽባሓዊ፤ በምሥራቅ በኩል የተተከለችው የገነት ርግብ” ብሏታል። ከእመቤታችን ቀድመው ለእናትነት ቀድመው የተመረጡ ብዙ ቢሆኑም የሰላም አለቃ ክርስቶስን ለመውለድ ግን አልተቻላቸውም። በቅድስና የተመረጡ የታወቁ ሴቶችም ነበሩ የእመቤታችንን ያኽል በሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ የታመነ የሰላም መልዕክተኛ ግን አልተገኘም።

በምድር ላይ የሚኖር ፍጥረት ሁሉ መምጣቷን እያሰበ ሲናፍቅ ነው የኖረው። በርግጥም በመጣች ጊዜ ክርስቶስን ይዛ በመገኘቷ መላእክት በምድር ላይ ለሚኖሩ ሁሉ “ለግዚአብሔር ምስጋና በሰማይ ይሁን በምድርም ሰላም” ሉቃ 2፥14 እያሉ አዋጅ ነገሩ። ስትጠበቅ የነበረችው የኖኅ ርግብ መጣችና ሰላምን ወለደችልን። ሰላም ከማንም ዘንድ የሆነችለን አይደለም፤ ሰላምን ተወልዳ ነው ያገኘናት ያውም ከሌላ አይደለም − ከእመቤታችን ነው።

ዛሬም የኖኅ ርግብ ሆይ! ተመየጢ ተመየጢ እንላለን።
ምድር እንደዚያን ጊዜው ሁሉ ሰላም የላትም። የሰላም ወሬ ሊያወራን የሚችል ማንም የለም። በያንዳንዱ ቀን ማለዳ መስኮታችንን ከፍተን የጥፋት ውኃ መጉደሉን የሚነግረን ሰው እንፈልጋለን ነገር ግን እስካሁን የነገረን የለምና ርግቢቱ እመቤታችን ሆይ እባክሽ ተመየጢ?

ይሆናል ብለን የላክነው ቁራ የምድርን በሬሳ መሞላት እንደ መልካም ነገር ሆኖለት ፊቱን ወደ እኛ አልመለሰም። ከኛ ጋር በነበረ ጊዜ በፊታችን ላይ ያየውን ጭንቀት ከኛ ተለይቶ ከወጣ በኋላ ረስቶት ሰላሙን ሊያበሥረን ወደኛ መመለስ አልፈለገም። ዛሬም የኛን ተሰብስቦ በአንድ ስፍራ መቀመጥ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ዓለምን እንደፈለገ ብቻውን ከወዲያ ወዲህ ይመላልስባታል። ነገሮችን ሁሉ ለብቻው ሊጠቀምባቸው ወደደ። የመርከቧ ነዋሪዎች ተጨንቀዋልና ርግቢቱ ድንግል ማርያም ሆይ እባክሽ ተመየጢ?

ወይናችን እንዲያፈራ፤ አበባም በምድራችን ላይ እንዲታይ በመርከቧ ውስጥ ያለን እኛ ልጆችሽ ምድርን እንድንወርሳት ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ።

ሔሮድስ ሞቷል፣ አርኬላዎስ ነግሷል አልልሽም፤ እንዳልሞተ ታውቂአለሽ። አርኬላዎስ ብለን የሾምናቸው ሁሉ ሔሮድስ እየሆኑብን ተቸገርን። በኛ ዘመን በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥልን፤ በልቡ እግዚአብሔርን መፈለግ ደስ የሚያሰኘው ንጉሥ እንኳን ባናገኝ በሔሮድስ ፋንታ ለይሁዳ የምንሾመው አርኬላዎስ ብንፈልግ አላገኘንም። የሕጻኑን ነፍስ የሚሿት ዛሬም አሉ አልሞቱም ግን ቢሆንም ተመየጢ!

ምድር የሞላት በግፍ የፈሰሰው የገሊላ አውራጃ ሕጻናት ደም ስለቆመ አይደለም ተመየጢ የምንልሽ ግፋችንን እንድታይልን ነው እንጅ። በኛ ዘንድ ስለልጆቿ የምታለቅስ ራሔል አሁንም እያለቀሰች ነው። ለቅሶም በራማ እየተሰማ ነው። ዋይታ በየደጁ አለ። ከሔሮድስ ቃል ተገብቶላቸው በገደሉት ሰው ልክ ሽልማት ሊቀበሉ የወጡት ገና አልተመለሱም። ግን ምን እናድርግ? ሰለ አባታሽ ስለ ኢያቄም፣ ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ እመቤቴ ሆይ ተመየጢ?

ካልተመለስሽማ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ደራሲ፤ “ወእቀውም ዮም በትሕትና ወበፍቅር” ብሎ የሚቀድስ፤ እንደ ዘካርያስ የሚያጥን፤ እንደ ሙሴ ቅብዐ ክህነት የሚቀባን ካህን ከወዴት እናገኛለን? ስለዚህ ነው ተመየጢ የምንልሽ። እመቤቴ ሆይ! አባቶቻችንን እንደ ጥንቱ የልብሳቸውን ዘርፍ ዳስሰን መፈወስ አምሮናል፤ ጥላውን ሲጥልብን የሚፈውስ ካህን ያስፈልገናል፤ ጋኔን ማውጣትም በገንዘብ ሆነ፥ እኛን ድሆችሽን ከአጋንንት እስራት ማን ነጻ ያውጣን? ተአምራት ማድረግም ትንቢት መናገርም ለግያዝ ሆነ።

ገንዘብ ሳይቀበሉ ከለምጻችን የሚያነጹን እነ ኤልሳዕ ቢፈለጉ አይገኙም። ስለሌሉ ሳይሆን ቅብዝብዝነታችንና ምልክት ፈላጊነታችን ካጠገባችን አርቋቸው ይኸው ባጠገባችን የሉም። ግሩም በሆነው በቊርባኑ ፊት በቆመ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ “ጎሥዐ” ብሎ የሚያመሰግን ካህን ዐይናችን ፈለገ፤ ልባችን ተመኘ፤ ነገር ግን በምስጋና እና በውዳሴ “ጎሥዐ” ማለትን ትተው በልሳነ ሥጋ “ጎሳ” የሚሉት በዝተውብን እየተጨነቅን ነውና ተመየጢ?

የጴጥሮስ ጥላ የጳውሎስ ሰበኑ እመቤቴ ሆይ ቀራጩ ማቴዎስ ወንጌላዊ ተብሎ የተጠራው፣ ዐሣ አጥማጆቹ ወንድማማቾች ሰውን ወደ ማጥመድ የተለወጡት፣ ገበሬው ታዴዎስ፣ አትክልተኛው በርተሎሜዎስ ለዚህ መዐርግ የበቁት ባንች ነው። ሿሚውን ወለድሽላቸው፤ ታሪካቸውን የሚለውጠውን ወደ ዓለም አመጣሽላቸው። በእኛ ዘንድ ግን ነገሮች ሁሉ ተገለባብጠውብናል። ዓሣ አስጋሪ የነበሩት እነዚያ ወንድማማቾችም እንደገና መረብና መርከባቸውን ይዘው ወደ ገሊላ ባሕር ገብተዋል። ማቴዎስም ወደ ቀራጭነቱ ተመልሷል፤ ታዴዎስም ወንጌልን በገበሬ ዘር መስሎ ያስተምረናል ብለን ስንጠብቅ ዘር ወደ መዝራት ተመልሶ ዘሩን እየዘራ ነው።
በርተሎሜዎሶቻችንም ሰውን ተክለው ያጸድቁታል ብለን ተስፋ ስናደርግ ሰፊ እርሻ ከመንግሥት ተቀብለው አትክልት እየተከሉ እንደሆነ ሰማን እንግዲህ በዚህ ሰዓት የቀረን ብቸኛ ተስፋ ያንች መመለስ ነውና ርግቢቱ ሆይ! እባክሽ ተመየጢ?

ከመጣሽማ እንኳን ሰዎች መላእክት ይወርዳሉ። “ወሰላም በምድር” የሚለው ቅዳሴአችንም እውነት ይሆንልናል። ከመጣሽማ አባ ሕርያቆስም ለከንቱ ውዳሴ ሳይሆን በማብዛት ያይደለ በማሳነስ፤ በማስረዘም ያይደለ በማሳጠር ምስጋናሽን ያቀርባል። አድማጭ ሲኖር ዜማ የሚያስረዝሙ አድማጭ እንደሌለ ካወቁ ምስጋናሽን አስታጉለው የሚወጡ እነዚህን አናገኛቸውም ነበር።

ከመጣሽልንማ እንዚራ ስብሐቱን፣ አርጋኖኑን፣ ሰዓታቱን፣ ኆኅተ ብርሃኑን፣ ማኅሌተ ጽጌውን፣ አንቀጸ ብርሃኑን በስምሽ የሚደርሱልሽ አዲሶቹ አባ ጊዮርጊሶች፣ ቅዱስ ያሬዶች ይነሡልን ነበር። ይሄው አዲስ ድርሰት አዲስ ምስጋና የሚያሰማን አጥተን ስንት ጊዜ ሆነን። የዳዊት የሰሎሞን ርግብ ድንግል ማርያም ሆይ ተመየጢ ተመየጢ? እናይሽ ዘንድ ተመለሺ::

ማስታወሻ:- ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የአራቱ ጉባኤያት መምህርና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ ሲሆን የመጻሕፍት ደራሲም ናቸው:: ሊቅ ሊቃውንት የጃንደረባው ሚዲያ ዐምደኛ ሲሆኑ ጽሑፎቻቸው ዘወትር ሰኞ የሚነበቡ ይሆናል::
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
Forwarded from Quality move bot
ተዋህዶ ሀይማኖቴ ነው ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ መረዳት መጻህፍትን ማንበብ እፈልጋለው የየእለቱን ስንክሳር ማንበብ እፈልጋለው ያለ ሁሉ ሊቀላቀላቀላቸው ሚገባ ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል 3 ቻናሎች
👇 ከታች Join በሉ
ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፭ ለህዳር አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ

የህዳር አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ  #ሥርዓተ_ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

👉Share ያድርጉ
መኃትው ዘአባ ዮሐኒ
በ፬
ዝንቱሰ ብእሲ ብእሴ እግዚአብሔር፤ዘኮነ ንብረቱ ገዳም ከመ ዮሐንስ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ፤በዘብድወ ጠፈ ወበሐሜለት።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለሕፅንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ።

ዚቅ
ይረፍቁ ምስሌሁ ኅሩያኒሁ፤በዳግም ምጽአቱ፤ይትፌሥሑ በመንግሥቱ እለ አምኑ ቦቱ።

መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለክሣድከ በሞገሰ አምላክ ሥርግው፤አኮ በቃማ ንዋየ ዓለም ሕስው፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ ደመና በገጸ ሃይማኖት ህልው፤ዝናመ ሣህልከ ኀበ ፍና መፍቅድ ፍንው፤ወረደ ያጥልላ ለነፍስየ በድው።

ዚቅ
አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኃልቀ ኄር፤አድኅነኒ እግዚኦ።

ዓዲ ዚቅ
ስማዕ ጸሎተነ ወስእለተነ፤ወሥረይ ኵሎ ኃጢአተነ፤ስማዕ ጸሎተነ ወስእለተነ።

መልክአ ሐዋርያት
ሰላም ለመዛርዒክሙ መዛርዓ ጸጋ ወብዕል፤ለክርስቶስ አምላክ አምሳለ መዝራዕቱ ልዑል፤፲ቱ ወ፪ቱ ሰባክያነ ቅዱስ ወንጌል፤ያኅልፈኒ ጸሎትክሙ እምድቀተ ሕማም ወኀጕል፤በስቊረተ መርፍእ ከመ አኅለፎ ለዕዑን ገመል።

ዚቅ
ወበጽጌሁ አርአየ ገሃደ አምሳለ ልብሰተ መለኮት፤ዕቊረ ማየ ልብን፤ጽጌ ወይን ተስፋሆሙ ለጻድቃን።

መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካልዕ
ሰላም ለመላትሒከ ወለተጸፍዖትከ አዕላፍ፤ወለአዕናፊከ ምውዝ ዘምስለ ከናፍር ወአፍ፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ፤ኢሐፀብኩ እግረ እንግዳ ከመ አብርሃም ትሩፍ፤ወከመ ጊዮርጊስ ኢይሙት ጐየይኩ እምሰይፍ።

ዚቅ
ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም፤በዝ መካን መዓዛሆሙ ለቅዱሳን፤ከመ ጽጌ ደንጐላት ዘቈላት ወከመ ሮማን ዘውስተ ገነት፤ለዘቀደሶ ለገብረ ሕይወት፤ኪያሁ ፍርህዎ ወሰብሕዎ፤ወተማኅፀኑ ኀቤሁ።

መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካልዕ
ሰላም ለእራኅከ ጒንዴ አጻብዕ ወአጽፋር፤ድኅረ ገቦከ ወከርሥ ለኅሊና ልብከ ኄር፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ አቡየ ዘወለድከኒ በፍቅር፤አድኅነኒ እምእዴሆሙ ለእለ ዴገኑኒ ጸር፤አባ በጸሎትከ ወልታ ጽድቅ ሥሙር።

ዚቅ
ፃማ ቅዱሳን ዲቤሁ አዕረፈ፤አፈዋተ ወንጌል ጸገየ ዘልፈ፤አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሃይማኖተ ተአጽፈ፤ኀበ ዓምደ ወርቅ ስሙ ተጽሕፈ።

ወረብ፦
ተጽሕፈ"ሃይማኖተ"/፪/ፃማ ቅዱሳን/፪/
ኀበ ዓምደ ወርቅ/፪/ስሙ ስሙ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ/፪/

መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለአማዑቲከ ወለንዋይከ ውስጥከ እንግልጋ፤ለኅንብርትከ ሰላም ወለሐቌከ ጸዋሬ ጋጋ፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጴጥሮስ ለቤተ ክርስቲያን ሠራዔ ሕጋ፤አስተምሕር ሊተ ያግዕዘኒ እምቅንየተ ሰይጣን ወፁጋ፤ጰራቅሊጦስ ኃያል ጰራቅሊጦስ ጸጋ።

ዚቅ
እለ ሎሙ ተርኅወ ገነት ዕለ ሎሙ ተነጽፈ ዕረፍት፤ይትፈሥሑ ጻድቃን በእግዚአብሔር መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ጽጌ ደንጐላት ወከመ ሮማን ዘውስተ ገነት፤ይትፈሥሑ ጻድቃን በእግዚአብሔር የዋሃን ውሉደ ብርሃን፤በትዕግሥት ኤሉ ውስተ አድባር።

ሰቆቃወ ድንግል
ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤ኢየሱስ ግፉዕ ምስካየ ግፉአን፤እግዚአብሔር ማኅደር ዘአልቦ ከመ ነዳያን፤ኢየሱስ ነግደ ወፈላሲ እንዘ ውእቱ ሕፃን፤ወልደ አብ ፍቁር በኀበ ሰብእ ምኑን፤መኃልየ ብካይ ኰነኒ ዘእሙ ኃዘን።

ዚቅ
አንተ ውእቱ ምርጉዞሙ ለጻድቃን፤ተስፋሆሙ ለስዱዳን፤መርሶሙ ለእለ ይትሀወኩ፤ብርሃነ ፍጹማን ወልደ አምላክ ሕያው።

ዓዲ ዚቅ
ሠርጎሙ ለሐዋርያት፤ንዋየ ነዳያን ወምስካየ ግፉዓን፤ሠርከ ነአኵተከ መሐሪ፤ንጉሥ ዘኢይትኄየይ ተግባሮ።

ማኅሌተ ጽጌ
ሶበ ዴገነኪ አርዌ በሊዓ ሕፃንኪ ዘኀለየ፤በዘትሠርሪ ገዳመ ወታፈጥኒ ጐይየ፤እንተ ጸገይኪ አክናፈ ከመ ዮሐኒ ጸገየ፤ብእሲተ ሰማይ ማርያም ዘትለብሲ ፀሐየ፤ተአምረኪ ጸሐፈ ዮሐንስ ዘርእየ።

ዚቅ
ሕፃናት ሶበ ኀለየ ሄሮድስ ዓርዌ ሰማይ፤ዘምስለ ዮሴፍ አረጋይ፤ነገደት ቊስቋመ ናዛዚተ ኀዘን ወብካይ።

ምልጣን
ይትፈሥሑ ጻድቃን በእግዚአብሔር እስመ ኢይመውቱ እምዝ ዳግመ ዔሉ ውስተ አድባር ወበዓታት ወግበበ ምድር መኒኖሙ ዘንተ ዓለመ አብደሮሙ ከብካበ ዘበሰማያት።

ዓዲ ምልጣን
ይትፈሥሑ ጻድቃን በእግዚአብሔር ወይከብሩ ኵሎሙ ርቱዓነ ልብ ወከማሁ ይትፈሣሕ አባ ዮሐኒ በሰማያት ምስለ መላእክት ዘፈጸመ ገድሎ በትዕግሥቱ።

እስመ ለዓለም
ትብሎ መርዓት ለመርዓዊሃ፤ወልድ እኁየ ሊተ ወአነ ሎቱ አፈቅሮ እስከ አመ ፈቀደ፤ነዓ ወልድ እኁየ ንፃዕ ሐቅለ ወናንሶሱ አዕፃዳተ ወይን፤ክብሮሙ ለቅዱሳን መርዓዊሃ ለቤተ ክርስቲያን፤አክሊለ ሰማዕት ተስፋ መነኮሳት፤ውእቱ አርአየ ስነ ጽጌያት።

ዓዲ እስመ ለዓለም
አባ ዮሐኒ ጸሎትከ ትባርከኒ፤ንብረቱ ገዳም ሑረቱ አዳም፤ውስተ ሐቌሁ ቅናቱ ዘዓደም፤በቊር ወበዕርቃን፤በሐፍ ወበድካም፤ፍጹም ምንኵስናሁ ለአባ ዮሐኒ።

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
" የተደፈረችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት " - ብፁዕነታቸው

ድርጊቱ የተፈፀመው ህዳር 1 ቀን ምሽት ላይ ነው።

መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ኤርምያስ ገ/ጻድቅ የቦሌ ቡልቡላ ምስካበ ቅዱሳን አቡነ ሳሙኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሲሆኑ በደብሩ ለሁለት ቀን በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ ኅዳር 1 ምሽት ጉባኤው ተጠናቆ ምዕመናን ሲባርኩ " ማንነቱ ባልታወቀ " ግለሰብ በጥይት ተመተዋል።

በኃላም ወደ ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል ገብተዋል። በአሁን ሰዓትም በህክምና ክትትል ላይ ናቸው።

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተፈፀመው ድርጊት " የተደፈረችው ቅድስት ቤተክርስቲያን ናት " ብለዋል።

ብፁዕነታቸውን ይህን ያሉት መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ኤርምያስ ገ/ጻድቅ በሆስፒታል ተገኝተው ከጎበኙ በኃላ ነው።

ሀገረ ስብከቱ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር እንደሚነጋገር የገለፁት ብፁዕነታቸእ " ለአገልጋዮች ነገ ዋስትና እንዲኖራቸው መሠራት አለበት " ሲሉ አስገንዝበዋል።

በተፈጸመው ድርጊት የተደፈረችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናትም ብለዋል ብፁዕነታቸው።

ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን በፖሊስ በኩል የተሰጠ ማብራሪያ የለም።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/25 08:26:31
Back to Top
HTML Embed Code: