Telegram Web Link
ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፮ ለህዳር ዘቊስቋም ማርያም

የህዳር ቊስቋም

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።


መልክአ ሥላሴ፦
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ  አመ ሐወጸ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም  ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።


ዚቅ
ስብሐት ለኪ ኦ ወላዲተ እግዚአ ኲሉ፤አኰቴት ወክብር ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን፤ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ፤ሰዓሊ ለነ ቅድስት።


ነግስ
ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል፤እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።


ዚቅ
ተውኅቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ወብስራት ለገብርኤል፤ወሀብተ ሠማያት ለማርያም ድንግል።


ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።


ዚቅ
ንዒ ርግብየ ኩለንታኪ ሠናይት፤ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት፤መሶበ ወርቅ እንተ መና፤በትረ አሮን እንተ ሠረፀት።


ወረብ
ፀምር ፀዓዳ መሶበ ወርቅ እንተ መና መሶበ ወርቅ[፪]
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት እንተ ሠረፀት መሶበ ወርቅ[፪]


መልክአ አርሴማ(በአርሴማ ደብር ላይ የሚቆም)
ሰላም ለሰኰናኪ ዘይድኅፅ በቤተ መያሲ፤ወለመከየድኪ ከዋዉ ዉስተ መካነ ስምዕ ገያሲ፤አርሴማ ስምኪ ሶበ ፀዉዓ ብእሲ፤በደምኪ አስተናሳኢ በድነ ልቡናሁ ግስሲ፤ወበማየ ሕይወት ካዕበ ጌጋዮ ደምስሲ።


ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ኢፈለወ ወአሌለየ፤ለልበ አይሁዳዊ ወአልቦ አረጋዊ፤ኵሉ ዘእምነ ወጸዉዓ ስማ ለማርያም(ለአርሴማ)፤ዉእቱ ይድኅን ወይረክብ ሕይወተ።


ሰቆቃወ ድንግል
በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ሕፀተ ግጻዌ ዘአልቦ፤ሰቆቃወ ድንግል እጽሕፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ፤ወይሌ ወላህ ለይበል ዘአንበቦ፤ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ሶበ በኵለሄ ረከቦ፤ርእዩ ለይብኪ ዓይነ ልብ ዘቦ።


ወረብ
"ከማሃ ሀዘን"[፪]ወተሰዶ ሀዘን[፪]
ሶበ በኵለሄ ረከቦ ከማሃ ሀዘን[፪]


ዚቅ
አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ፤ምንዳቤ ወኀዘነ፤ወኲሉ ዓፀባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ።


ወረብ
ረኃበ ወጽምዓ አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ[፪]
ምንዳቤ ወኃዘን አዘክሪ ድንግል[፪]


ሰቆቃወ ድንግል
ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፤ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕጻን ደከምኪ፤ሶበኒ የኃውር በእግሩ ከመ ትፁሪዮ ይበኪ፤አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፤ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ።


ወረብ
አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ[፪]
ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ[፪]


ዚቅ
ሐዊረ ፍኖት በእግሩ፤ሶበ ይስእን ሕጻንኪ፤ያንቀዓዱ ኃቤኪ ወይበኪ፤እኂዞ ጽንፈ ልብስኪ፤እስከ ትጼዉሪዮ በገቦኪ፤ወትስዕሚዮ በአፉኪ።


ሰቆቃወ ድንግል
አብርሂ አብርሂ ናዝሬት ሐገሩ፤ንጉስኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጸሩ፤ጣዖታተ ግብፅ ኲሎ ቀጥቂጦ በበትሩ፤ይጒየዩ ወይትኃፈሩ ሰራዊተ ሄሮድስ ፀሩ፤ ዘበላዕሌሁ እኩየ መከሩ።


ወረብ
ናዝሬት ሀገሩ"አብርሂ"[፫]ናዝሬት[፪]
ንጉስኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ ንጉስኪ በጽሐ[፪]

ዚቅ:-
አብርሂ አብርሂ ኢየሩሳሌም በጽሐ ብርሃንኪ፤ወስብሐተ እግዚአብሔር ወብርሃኑ ሠረቀ ላዕሌኪ፤አብርሂ ጽዮን፤በጽሐ ብርሃንኪ፤ተጽዕኖ ዲበ ዕዋል፤በሰላም ቦአ ኃቤኪ።


ወረብ:-
አብርሂ አብርሂ ኢየሩሳሌም[፪]
በጽሐ ብርሃንኪ ኢየሩሳሌም #ደብረ_[፪]


ምልጣን:-
ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም፤ወላዕለ ወልዳ ክርስቶስ በደብረ ቊስቋም፤እንዘ ይብሉ ስብሐት በአርያም፤አማን፤ወበምድር ሰላም።


ምልጣን ዘዜማ:-
እንዘ ይብሉ ስብሐት በአርያም፤አማን(መጨረሻ ላይ #በአማን)፤ወበምድር ሰላም።


ወረብ ዘአንገርጋሪ:-
ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም ወላዕለ ወልዳ
ክርስቶስ በደብረ ቊስቋም[፪]
እንዘ ይብሉ ስብሐት "ስብሐት በአርያም"[፪][፪]

እስመ ለዓለም:-
ይቤ ቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳሳት፤ሶበ ቦዕኩ ውስተ ዝንቱ ቤት፤አዕረፈት ነፍስየ እምፃማዓ ዘረከበኒ  በፍኖት፤ኀበ ኀደረት ቅድስት ድንግል፤ምስለ ፍቁር ወልዳ ኢየሱስ ክርስቶስ።


ዓዲ እስመ ለዓለም:-
መንግሥቱ ሰፋኒት ዘእምቅድመ ዓለም፤ወልደ ቅድስት ማርያም፤ኃሠሠ ምዕራፈ ከመ ድኩም ንጉሥ ዘለዓለም፤ግሩም እምግሩማን፤ብርሃነ ሕይወት ዘኢይጸልም ኃደረ ደብረ ቊስቋም፤ኃይል ወጽንዕ ዘእምአርያም።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ልዩ ልዩ መዝሙራት.pdf
555.5 KB
የተለያዩ መዝሙራት ግጥም

የመዝሙራትን ግጥም ለምትፈልጉ ሁሉ

#በየግሩፑ_ያጋሩት @EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ዮሐንስ አፈወርቅ
@kokuha_haymanot
በመጋቢ ብሉይ ወሀዲስ
#በአባገብረኪዳን ስለ

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

የተሰጠ ድንቅ ት/ት

የ3 ብር ፓኬጅ ቢገዙ ይበቃዎታል
ይህ ት/ት እንዳያመልጥዎ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ፖርኖግራፊ ምንድነው ?
@kokuha_haymanot
#ፖርኖግራፊ_ምንድነው_?

የብዙ ወጣት ችግር ነውና #ያድምጡት

👉 ፖርኖግራፊ ምንድነው ?
👉 ፖርኖግራፊ እንዴት ሱስ ይሆናል ?
👉 ፖርኖግራፊ የሚያስከትላቸው ቀውሶች ?
👉 ከፖርኖግራፊ ሱስ እንዴት እንላቀቅ ? ...

#አቅራቢ ፦ አቤል ተፈራ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ስለ ታቦት ክብር.pdf
88.4 KB
#ታቦት ምንድነው ? #ፅላትስ ምንድነው ? ታቦት በሀዲስ ኪዳን ተሽሯልን ? ክብረ ታቦትን በአጭሩ የሚያስረዳ ፅሁፍ ነው ያንቡት ።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ስለ ተዝካር እና ፍትሀት.pdf
309.4 KB
ብዙዎቻችን ሰው ሲሞትብን ወይም ሲሞት #ፍትሀት ከዛም #ተዝካር እናደርጋለን ። ለመሆኑ ተዝካር ምንድነው ? ፍትሀትስ ? ከየት የመጣ ባህል ነው ? መፅሐፍ ቅዱሳዊ ነውን ? ይህን አጭር ፅሁፍ ያንቡ ጥያቄውን ይመልስሎታል

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ስለ ቅዱሳን ምልጃ.pdf
82 KB
የቅዱሳንን ምልጃ በብሉይ ኪዳን እና በሀዲስ ኪዳን በጥቅስና በማስረጃ በግልፅና በአጭሩ የሚያስረዳ
ፅሁፍ ነውና ያንቡት #ምልጃ ቅዱሳንን ይወቁበት

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#እኔ_ክርስቲያን_ነኝ

“እኔ ክርስቲያን ነኝ፡፡ ለሚጠይቁት እንደዚህ ብሎ የሚመልስ ሰው በአንድ ጊዜ በኹሉም ነገሮቹ ላይ ማወጁ ነው፡፡ ሀገሩ የት እንደ ኾነ፣ ሥራው ምን እንደ ኾነ፣ ቤተሰቡ እነማን እንደ ኾኑ መመስከሩ ነው፡፡ ክርስቲያን የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ነዋሪ እንጂ በምድር ላይ ካሉት ከተሞች የአንዲቱም አይደለምና፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ተወዳጆች ሆይ ኑ አባቶቼና ወንድሞቼ እግዚአብሔር ለርስቱ ለመንግሥቱ የለያችሁ ምእመናን ሆይ ኑ፡፡ የልጅነትን ማኅተም ያለባችሁ የክርስቶስ ወታደሮች ሆይ ኑ፡፡ ልጆቼ ይኽን ለነፍሳችን ድኅነት እግዚአብሔር ያዘጋጀውን ትምህርት ትማሩ ዘንድ ኑ፤ ጊዜ ሳለልን እንመካከር ዘንድ ኑ፡፡ ኑ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ገንዘብ እናድርግ፡፡ ነፍሳችንን እንገዛት ዘንድ እንቻኮል፡፡

ዓይነ ልቡናችን ብሩህ ይኾን ዘንድ ኑ በዕንባ እንታጠብ (እናልቅስ)፡፡ ባለጸጋዉም ድኻዉም፣ ልዑላንም ሕዝቦችም፣ ወጣቶችም ጐረምሶችም፣ ሽማግሎችም ሕፃናትም፣ በአጣቃላይ ጣዕመ መንግሥተ ሰማያትን መውረስ ከምረረ ገሃነም መዳን የምትሹ ሁላችሁም ኑ፡፡

ከክቡር ዳዊት ጋር ሆነን ምሕረቱ የበዛ ባለጸጋውን እግዚአብሔርን “ነጽረኒ ወስምዓኒ እግዚኦ አምላኪየ" አቤቱ ፈጣሪዬ ልመናዬን ሰምተኽ በዓይነ ምሕረትህ እየኝ፤ ተመልከተኝ፡፡ "አብርሆን ለአዕይንትየ ከመ ኢኑማ ለመዊት" የሞት እንቅልፍ እንዳያንቀላፉ ዓይኖቼን አብራቸው” ብለን እንለምነው /መዝ.13፥3-4/፡፡ ከመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን እንደነበረው እንደ ዓይነ ስዉሩ ሰውም፡- “ተሣሃለኒ ኢየሱስ ወልደ ዳዊት" የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ ማረኝ” ብለን እንጩኽ/ማር.10፥48/፡፡ ዝም እንል ዘንድ የሚቈጡን ቢኖሩም እንደ በርጠሜዎስ ልጅ እንደ ጠሜዎስ ዓይነ ልቡናችንን እስኪያበራልን ድረስ አብዝተን ወደ ብርሃን ክርስቶስ እንጩኽ፡፡ ስለዚኽ ወደ ክርስቶስ እንቅረብ፤ ብሩህ ልቡናንም ገንዘብ እናድርግ፡፡ ገጻችንም ከቶ አያፍርም፡፡ ኑ! ሃይማኖትንና ምግባርን አንድም ልጅነትን መንግሥተ ሰማያትን ለመያዝ እንሩጥ። ይኽን ያደረግን እንደኾነም የዚህ ዓለም ነገር ከንቱ ሆኖ ይታየናል፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ንቁ እናድርግ፤ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ ብንመጣም አይዘጋብንምና ኑ እንፍጠን፡፡ ምሽቱ ቀርቧል፤ ለኹሉም እንደየሥራው የሚከፍለው ልዑለ ባሕርይ ኢየሱስ ክርስቶስም ሊመጣ ነው፡፡
/#ንስሐ - #በቅዱስ_ኤፍሬም #መቅረዝ_ዘተዋህዶ_ብሎግ/
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
Audio
ከሁሉ ታንሳለች ከሁሉ ትበልጣለች 
                                                  
Size:- 56.9MB
Length:-2:43:21
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ልጆቼ፦ እግዚአብሔርን በእምነት በፀሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ ድካም እንድንሻው እንዲሁ ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሔር ልናቀርብ ይገባናል፤ ልጃችን ቢጠፋብን ፈልገን በቅርብ ያላገኘነው እንደሆነ ሃይላችንን በድካም ድካማችንን በሃይል የምንለውጥ አይደለንምን? የጠፋውን ልጃችንን ስለመፈለግስ እናገኘው ዘንድ የብሱን በእግር ባህሩን በመርከብ የምንዞር አይደለንምን? ፈልገንም ያገኘነው እንደሆነ ዳግመኛ እንዳይጠፋብን ለመጠበቅ እንተጋ የለምን?

እንዲህ ከሆነ መሓሪ እግዚአብሔርን በእምነትና በፀሎት እንሻው ዘንድ ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሔርን ፈልጉት ነጋዴ ወርቅ ቢጠፋበት ወርቁን ያገኘው እንደሆነ ሁሉን ቦታ እንደሚፈልግ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እናት ልጇ ቢጠፋባት እስክታገኘው ድረስ አርፋ እንደማትቀመጥ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት እግዚአብሔርን እሹት ፈልጉት እስክታገኙት ድረስ በእምነት በፀሎት እሹት፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
2024/09/25 06:38:10
Back to Top
HTML Embed Code: