Telegram Web Link
#የቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ምክር_ተግሣጽ
(
#በጸሎተ_ሐሙስ በነግህ የሚነበብ)

ወደዚህ ወደሚያስፈራው ማእድ የምንቀርብባት ቀን ይህች ናት፤ እንግዲህ ነቅተን እንቅረብ፤ ራሳችንንም እናዘጋጅ፤ ከእኛ ውስጥ አንዱም እንደ ይሁዳ አይሁን፤ ወይም ሽንገላ ያለበት ክፉ አይሁን።

በአንደበቱም ምንም ምን ክፉ ነገርን አይናገር፤ በልቡም ሌላ ኀሳብ አያስብ፣ በዚያን ጊዜ ማእዱን የለወጠው ክርስቶስ እነሆ በዚህ አለና፤ እነሆ ከዚህ ሁኖ በዐይኑ ወደዚህ የሚመለከት እነሆ በዚህ አለ። እርሱ የተዘጋጀውን ቍርባን ለውጦ የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚያደርገው ነውና።

ይህም እንደ ዕሩቅ ብእሲ ባሕርይ አይደለም፣ ከሁለት ባሕርይ አንድ አካል የሆነ ስለ እኛ በዕንጨት መስቀል ላይ የተሰቀለ ክርስቶስ ነው እንጂ። ካህኑም በዚሁ አምሳል ይፈጽማል።

እኛም እርሱ እንደ ተናገረ ስጦታና ችሎታ ለእግዚአብሔር ነው እንላለን።

ይህ ሥጋየ ነው አለ፤ ይቺ ቃል የተዘጋጀውን ቍርባን ትለውጣለች። እንደዚህም ያ ቃል በኦሪቱ ብዙ ተባዙ ምድርን ምሉዋት ብሎ አንድ ጊዜ የተናገረው ትውልዶችን ነገዶችን በማስተኝ በተፈጥሮአችን ባሕርይ ሲሠራ ይኖራል።

እንደዚሁም ይህን ቃል አንድ ጊዜ ተናገረ፤ ያ ቃል በመላው ዓለም በአሉ አብያተ ክርስቲያናት የሚዘጋጀውን መሥዋዕት ሁሉ ሲፈጽም ይኖራል። ስለዚህ በልቡ ቂም በኀሳቡም ሽንገላ በሰውነቱ ተንኮል ያለበት እንግዲህ ወደርሷ ሊቀርብ አይገባውም። ከሱ የተነሣ በነፍሱ ላይ ፍዳ እንዳያመጣ።

በዚያን ጊዜ ይሁዳ ሥጋውን ደሙን ከተቀበለ በኋላ ሰይጣን አድሮበታልና።

እንግዲህ የበደለ የጌታ የእግዚአብሔር ፍርድ በነፍሱ ለመቀበል ብቻ አይደለም፤ በይሁዳ ላይ ሰይጣን እንዳደረ ስለጉስቍልናው ሐሣር ነው እንጂ። ሳይገባቸው ሥጋውን ደሙን በሚቀበሉ ላይ መጥቶ በውስጣቸው እንዲያድርባቸው እኛን ለማስረዳት ነው፤ በዚያ ጊዜ በይሁዳ እንደ ሆነበት ለሚገባቸው የምትጠቅም ስጦታ ናትና።

ይህንንም የምለው ንጹሕ የሆነ ሥጋውን ደሙን ከመቀበል ልንከለክላቸው አይደለም፤ ነገር ግን ይህን የምነግራችሁ ልትጠብቁትና ልትጠነቀቁበት ነው እንጂ።

ከእናንተ ማንም ማን እንደ ይሁዳ ሆኖ በልቡ ቂም ወይም መርዝ የሆነ ነገር ሽንገላ ይዞ ወደዚህ ማዕድ አይምጣ። ሥጋውና ደሙ መንፈሳዊ ምግብ ነውና።

ክፉ ደዌ በሆድ ሳለ ሥጋዊ ምግብን ቢመገቡት በበሽተኛው ላይ ደዌን እንደ ሚጨምርበት እንዲሁ ነው።

ይህም ከምግቡ ጠባይ አይደለም፤ አድሮበት ካለው ደዌ የተነሣ ነው እንጂ።

እንደዚሁም መንፈሳዊት ምሥጢር የሆነች ሥጋውና ደሙ ክፋትን ከተመላች ከሰው ሰውነት፡ ውስጥ ብትገባ ፈጽማ ትጐዳለች። ይህም ከሥጋው ከደመ አይደለም፤ በደዌ ኃጢአት ሀና ከተቀበለች ከደዌ ነፍስ ነው እንጂ።

ከሕይወት ማዕድ ለመቀበል በፈለግን ጊዜ ሰውነታችንን ልቡናችንን ፈጽመን እናንጻ፤ ከጸራና ከነጻ ማእድ የምንቀበል ከሆን።

ሰውነታችንን ፈጽመን የምናነጸውና የምናጠራው እንዴት ነው ብትል እኔ አሳይሃለሁ፤ በወንድምህ ላይ በልብህ ቂም ቢኖር ቍጣህንና ጥላቻህን ፈጽመህ ተዋት፤ አንተ ወደምታስፈራ መሥዋዕት ትቀርባለህና፤ እንግዲህ አክብራት፤ ፍራት፣ ክርስቶስ በእጆችህ መካከል ተሠውቷልና።

የተሠዋውም በምድራውያንና በሰማያውያን መካከል ፍቅር አንድነትን ያደርግ ዘንድ ነው፣ እርሱ በተከተሉት ሰዎች ፈንታ ነፍሱን ለውጧልና።

አንተ ግን በተገዢነት የሚተካከልህን ወንድምህን የምትጠላ እርሱም ጌታ ስለ አንተ ከመሞት ያልተከለከለ ሲሆን፤ አንተ ግን በወንድምህና በእንተ መካከል ያለውን ቂም በቀል ሳትተው ወደዚህ ግሩም ምሥጢር በምን ሥራ ትቀርባለህ? በየትስ ክርስቲያንነትህን ትገልጣለህ?

እኔ ዛሬ የተጋሁ ሁኛለሁና ወደ መተከዝም እደርሳለሁ ብትል ወደ ዓለም ተገዥነትና በፍቅሩም ወደ መያዝ እደርሳለሁ አልክ። ነገር ግን አይሁድ ጌታቸውን እንደ ሰቀሉ አልሰቀሉህም።

አንተ ግን ለጠላትህ ሞኝ አትሁን፤ ተስፋ ቆርጠህም በሰውነትህ አትተክዝ ልዑል እግዚአብሔር እንደ ቂመኛ ተበቃይ ምንም ምን አይጠላም።

በቃሉም አስረድቷል፤ እንዲህ ሲል፦ መባህን ወደ መሠዊያው በምታቀርብበት ጊዜ የተጣላህ (የተጣላኸው) ወንድም እንዳለ ብታስብ መባህን ከዚያ አኑረህ ሂደህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ።

አሁንም እኔ የጌታ ክርስቶስን ሥጋ ሲቀበሉ ብዙዎችን አያቸዋለሁ።

እንግዲህ ሕግ በሌለው በዚህ ልማድ እየተከተሉ ለመሔድ እንዴት ሠለጠኑ? ይህንንም የሚያደርጉ ፋሲካና ጾም ሲደርስ ነው፣ ጾምን ወይም በዓላትን መመልከት ብቻ አግባብ አይደለም፤ ሥጋንና ነፍስን ሁልጊዜ ማንጻት ነው እንጂ።

ከዚህ በኋላ ከሥጋው ከደሙ ይቀበል፤ ልቡን ካነጻ በበዓልም ቢሆን በጾምም ቢሆን ርኩስ አይሆንምና።

ከሚያስፈራ ሥጋው ይቀበሉ ዘንድ አግባብ አይደለም፤ እንግዲህ በኦሪቱ ሥርዓት እንኳን ወደ መስዋዕት በሚሔዱበት ጊዜ በሥራቸው ሁሉ ተጠንቅቀው ሰውነታቸውን በውስጥ በአፍአ እንዴት እንደሚያነጹ አስተውል።

አንተ ግን መላእክት ከእርሱ የሚደግጡለትና የሚንቀጠቀጡለት ሲሆን ወደዚህ መሥዋዕት ትቀርበዋለህ፤ በረከሰው ሰውነትህም ወደዚህ ማእድ በድፍረት ቀርበህ ደፍረህ ትቀበለዋለህ።

ወይስ ሥጋው ደሙ ለበቁ (ቅዱሳን) ነው ያለውን አልሰማህምን? በንስሐ ውስጥ ከአሉት ወገን ወደዚህ ቦታ ይግባ (ይገባ ዘንድ) የማይችል ቢሆን ነው።

ስለዚህም ነገር ማስረዘም ፈልጌ ነበር ነገር ግን ስለ እናንተ የልቤ ሐዘን ገታኝ።

እንግዲህ አስተውሉ፣ የጌታችንንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውንና ደሙን በሚገባ ትቀበሉ ዘንድ ልቡናችሁንና ሰውነታችሁን አንጹ።

ለእርሱ ክብር ምስጋና ዛሬም ዘውትርም ለዘላለሙ ይሁን አሜን።

(#ግብረ_ሕማማት_ዘሐሙስ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
__ፍትሐ ነገሥት ክፍል ፲፯__
አንቀጽ ፳፫ ለክርስቲያኖች ስለሚገቡ ምግቦች፣ ልብሶች፣ ስለ ቤት እና ስለ ተግባረ እድ ይናገራል።
፩) በወንጌል የተከለከሉ ምግቦች ደም፣ ጥሬ ሥጋ፣ ታንቆ የሞተውን፣ ለጣዖት የተሠዋውን፣ የአውሬውን ትራፊ፣ ሙቶ የተገኘውን፣ ሲያርዱ አንገቱን ቆርጠው የጣሉትን ናቸው። ለጣዖት የተሠዋውን አትብሉ የተባለበት ምክንያት ምእመናን ወደ ጣዖት አምልኮ እንዳይሳቡ ነው።
_
፪) ርኵስ ፍጥረት እንደሌለ እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ንጹሕ እንደሆነ ተጽፏል። መጽሐፍ ከከለከለው በቀር ከምግብ ሁሉ እንዳንከለከል መሆን ይገባናል።
_
፫) አእምሮ ወደማጥፋት የሚያደርስን ምግብ፣ አራቱን ባሕርያትን የሚያነዋውጽን ምግብ፣ አካል የሚያጎድልን ምግብ መብላት አይገባም። ይኽውም መርዝ እንዳላቸው እንስሳትና እፀዋት ያሉትን ነው።
_
፬) አትብሉት ከተባለው የምግብ ወገን ደህነኛውን የሚገድል ድውዩን የሚፈውስ ቢሆን ደህነኛው ከመብላት ይከልከል። ድውዩ ግን የሚያድነው ከመሆኑ የተነሣ መብላት ይገባዋል።
_
፭) ሁሉን ሊበሉት እንዲገባ የሚያምን ሰው ሁሉን ይብላ። የሚጠራጠር ሰው ግን እህል ይብላ። ሁሉን የሚበላ አረማዊም ሁሉን የማይበላ አይሁዳዊን ሃይማኖተ ግብዝ ብሎ አይንቀፈው። ሁሉን የማይበላ አይሁዳዊም ሁሉን የሚበላ አረማዊን ይህ ሁሉ በአፌ ብሎ አይንቀፈው።
_
፮) ለሰው ክፉ ነገር እየተጠራጠሩ መብላት ነው። በሃይማኖት የማይሠራው ሥራ ሁሉ ኃጢአት ነው። ለጣዖት የተሠዋውንኳ አምነው ቢበሉት ጉዳት አያመጣም።
_
፯) በመብል ምክንያት ወንድምህ የሚጎዳ ከሆነ የተፈቀደውን እንኳ ስለእርሱ ብለህ አትብላ።
_
፰) በገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ብሉ። ፍጥረቱ ሁሉ የእግዚአብሔር ገንዘብ ነውና። እያመሰገኑ ቢቀበሉት ሁሉም በስመ እግዚአብሔር ይከብራል።
_
፱) ካላመኑ ሰዎች ወገን የጠራችሁ ሰው ቢኖር እና ልትሄዱ ብትወዱ ሳትመራመሩ ያቀረቡላችሁን ሁሉ ብሉ። ለጣዖት የተሠዋ ነው ቢላችሁ ግን አትብሉ።
_
፲) በቀለም ያስጌጧቸውን ልብሶች ከመልበስ መጽሐፍ ከለከለ። ቤተመቅደስ ገብተው እግዚአብሔርን ሲያገለግሉ የሚለብሱት ልብስ ነጭ ሊሆን ይገባል።
_
፲፩) ሴቶች የወንድ ልብስ አይልበሱ አለ። እጀ ሰፊ ቀሚስ፣ ሱሪ አይታጠቁ። አርዓያ መለወጥ ሥርዓት ማፍረስ ነውና። ወንዶችም የሴቶችን ልብስ አይልበሱ። ይኽውም እጀ ሰብስብ ቀሚስ አይልበሱ።
_
፲፪) ወንዶች ከጣታቸው ቀለበት አያግቡ የምንዝር ጌጥ ነውና። ሴቶች በወርቅ የተጌጠ የሚያስመካ ልብስ አይልበሱ። ሹማምንት ግን ያጌጠ ልብስ ቢለብሱ ይገባቸዋል።
_
፲፫) መነኮሳት ከፀምር ወገን ደጓሳ ልብስ ይልበሱ።
_
፲፬) ማንኛውም ሕዝብ የወደደውን መልበስ ይገባዋል። ዘመን ያስገኘውን መልበስ ዘመን ባስገኘው ማጌጥ ይገባቸዋል። ከሕዝባውያን ወገን ብዙዎቹ ሰዎች ያገኙትን መልበስ ይገባቸዋል።
_
፲፭) ካህናት የወታደር ልብስ አይልበሱ። ካህናት የአናፂ ልብስን አይልበሱ።
_
፲፮) ወጠቢብኒ ቅዱስ ባስልዮስ ይቤ ይደሉ ለነ ከመ ንሥራዕ ልብሰነ በዘንከድን ዕርቃነነ። ዕርቃናችንን እንሠውር ዘንድ ልብስ መሻት ይገባናል። ወንድኃን እምቍር ወዋዕይ። ከቀን ሐሩር ከሌሊት ቁር ለመዳን ልብስ ያስፈልጋል [ቁጥር ፰፻፲፬]።
_
፲፯) ለሚኖሩበት ሰዎች ይጠቅም ዘንድ፣ ይሠውራቸው ዘንድ፣ ምግባቸውን ንብረታቸውን ያስቀምጡበት ዘንድ፣ ይሰበሰቡበት ዘንድ፣ ቤት መሥራት ይገባል።
_
፲፰) ጌታ ለወልደ እጓለ እመሕያውሰ አልቦቱ ኀበ ያሰምክ ርእሶ ተብሎ እንደተነገረው ቤት እንዳልነበረው ሁሉ ለባሕታውያንም በዚህ አብነት ቤት የላቸውም።
_
፲፱) የእንግዳ መቀበያ ይሆን ዘንድ ቤት ያስፈልጋል።
_
፳) ከሥራይ፣ ከጥንቆላ፣ ጣዖትን ከመሥራት፣ ከመዝፈን፣ ከተውኔት በስተቀር ክርስቲያን ሥራን ሁሉ መሥራት ይገባል።
_
፳፩) አንጥረኛ ሁሉ ጣዖት ከመሥራት ይከልከል። ከአመነ ከተጠመቀ በኋላ ይህን የሚያደርግ ቢኖር ንስሓ ይግባና ይተወው።
_
፳፪) ለጣዖት በገና የሚደረድር፣ የሚዘፍን ቢኖር በቀኖና ይለይ። ያም ባይሆን በውግዘት ይለዩ።
_
፳፫) ለክርስቲያኖች የሚገቡ ሥራዎች ግብርና፣ ማስገር፣ ልብስ መስፋት፣ ልብስ መሥራት፣ ቤት መሥራት፣ ሕክምና፣ አንጥረኝነት፣ ጠራቢነት፣ ጸሓፊነት፣ እንጀራ ጋጋሪነት ወጥ ሠሪነት፣ መምህርነት፣ ነጋዴነት፣ መርከብ መሥራት እና የመሳሰሉት ናቸው። ንግድ ከአንዱ ሀገር ያለውን ወደ አንዱ ሀገር ለመውሰድ በግድ ያለውድ ያሻል [ቁጥት ፰፻፳፬]።
_
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፲፰ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
_ፍትሐ ነገሥት ክፍል ፲፰__
አንቀጽ ፳፬ ስለ እጮኝነት፣ ስለ ጋብቻ ይናገራል።
፩) የጋብቻ ዓላማ ዘር ለመተካት ልጅ ለመውለድ፣ የፍትወት ጾርን ለማጥፋት እና ለመረዳዳት ነው።
_
፪) ወንድ ከሴት ሄዶ ማጨት ይገባዋል። አኮ መፍትው ትሑር ብእሲት ኀበ ብእሲሀ አላ መፍትው ይሑር ብእሲ ኀበ ብእሲቱ እንዲል።
_
፫) የፍትወት ጾር የጸናበት ሰው ካለ ማግባት ይገባዋል። በፈቲው ጾር ሲነዱ ከመኖር ማግባት ይሻላልና።
_
፬) የፍትወትን ፆር ድል መንሣት የተቻለው ሰው ማግባትን መተው ይገባዋል። ሚስት የሌለው ሰው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝበትን ሥራ ያስባል።
_
፭) ማግባት በኦሪትም በወንጌልም የታዘዘ ነው። አንተ ሰው ሚስት ብታገባ ልፍታት አትበል።
_
፮) በድንግልና እኖራለሁ ብሎ ከተሳለ በኋላ ማግባት እጅግ ያሳፍራል። ኃፍረት ነው። ቢያገባ ግን ሁለተኛ ሚስት እንዳገባ ሰው ፍርድ ይሆናል።
_
፯) በሁለተኛ ግቢ ፍትሐት ዘወልድን ደግመው ያጋቧቸዋል እንጂ ሥርዓተ ተክሊል አይደረግም።
_
፰) ካህናት ሁለተኛ ካገቡ ክህነታቸው ይሻራል። ከሦስተኛ ግቢ በኋላ መጽሐፍ አላዘዘም።
_
፱) በሰው በእንስሳዊ ባሕርዩ የፈቲው ጾር ቢጸናበት ማግባት ይገባዋል። [ቁጥር ፰፻፳፯]። የፈቲው ጾር በሰው ባሕርይ እንደ ጭቃ ተለውሳ እንደ ነሐስ ተንሳ ትኖራለች [ሐተታ ቁጥር ፰፻፴፮]
_
፲) ከቅዱሳን አባቶቻችን ማግባትን ለዝሙት የሚሻ አላገኘንም። ዘእንበለ ለከዊነ ዘርዕ ባሕቲቱ። ልጅ ለመውለድ ብቻ ነው እንጂ።
_
፲፩) ፅንስ ከገፋ ሆድ ከሰፋ በኋላ ወንድ ከሚስቱ የደረሰ ቢሆን ይህ ሥራ የማይገባ ነው።
_
፲፪) የሚያጭ ሰው ራሱ ፈቅዶ ሂዶ ማጨት ይገባዋል። እርሱ ካልሄደ ሽማግሌ ልኮ፣ ወይም ደብዳቤ ሰዶ ማጨት ይገባዋል። ማጫ መስጠት ግን ለአሳዳጊው ወይም ለመጋቢው ይገባል።
_
፲፫) የሥጋ ዘመድን ማግባት አይገባም። መጽሐፍ ካላዘዘው ጋብቻ የተወለዱ አይጋቡ። ማግባት የማይፈቀድባቸው የሥጋ ዝምድናዎች:-
√ የልጅ ልጅ ልጅ
√ የልጅ ልጅ
√ ልጅ
√ እናት፣ አባት
√ አያት
√ ቅድመ አያት
√ አጎት፣ አክስት
√ ወንድም፣ እህት
√ የወንድም ልጆች፣ የእህት ልጆች
፲፬) ሐዋርያትም፣ ሠለስቱ ምእትም ከአራተኛው ትውልድ እና ከዚያ በላይ መጋባትን አልከለከሉም። [እስከ ሰባት ያለው ትውፊት ነው]። ይህንን መክፈል መጨመር ለኤጲስ ቆጶሳት ተገባቸው። ስለሆነም ዓላውያን በዝተው ከሰባት ትውልድ በላይ ባያገኙ ግብፃውያን በአራተኛው ማግባትን ፈቅደዋል።
_
፲፭) በትውልድ አቆጣጠር የአጎት ልጅ አራተኛ ነው። አቆጣጠሩም ፩ኛ አባቴ እኔን ወለደኝ፣ ፪ኛ አያቴ አባቴን ወለደ፣ ፫ኛ አያቴ አጎቴን ወለደው፣ ፬ኛ አጎቴ ልጁን ወለደ ይላል። [ሐተታ] በሀገራችን ግን በአንድ ወገን ሰባት፣ በአንድ ወገን ሰባት ተከልክሎ በስምንተኛው መጋባት ነው።
_
፲፮) በክርስትና ከተዛመዱ በኋላ መጋባት አይገባም። ይህ ዝምድና መንፈሳዊ ዝምድና ይባላል። የሚከተሉትን የሚከለከሉ ጋብቻዎች ናቸው።
√ አንሺ፣ ከተነሺ (ሴት ወንድን ብታነሣ)
√ ባል የሚስቱን ክርስትና ልጅ፣
√ ሚስት የባሏን ክርስትና ልጅ፣
√ የአንሺ እናት አባት ከተነሽ እናት አባት፣
√ የአንሺ ወንድም ከተነሽ ወንድም፣
√ የአንሺ ልጅ ከተነሽ ልጅ፣
√ የአንሺ የሚስት ልጅ ከተነሽ የሚስት ልጅ፣
፲፯) ሴት ከሌላ የወለደቻት ልጇን ባሏ ክርስትና ላነሣው ልጁ ማጋባት አይገባትም። ወንዱም ቢሆን ከሌላ የወለዳት ልጁን ሚስቱ ክርስትና ላነሣቸው ልጅ ማጋባት አይገባውም።
_
፲፰) መንፈሳዊ ዝምድናን ያፈረሰ ቀኖናው ሚስቱን ፈትቶ ምንኵስና ነው።
_
፲፱) በማሳደግና በማደጎ ከተዛመዱ በኋላ መጋባት አይገባም። የሚከተሉት የሚከለከሉ ጋብቻዎች ናቸው።
√ አሳዳጊ ከአዳጊ ጋር፣
√ የአሳዳጊ ልጅ ከአዳጊ ጋር፣
√ የአሳዳጊው ልጅ ከአዳጊ ልጅ ጋር፣
√ የአሳዳጊ እናት አባት ከአዳጊ እናት አባት፣
√ የአዳጊ አያት ከአሳዳጊ አያት፣
√ የአዳጊ አክስት አጎት ከአሳዳጊ አክስት አጎት
፳) በጋብቻ ከተዛመዱ በኋላ መጋባት አይገባም። የሚከተሉት የሚከለከሉ ጋብቻዎች ናቸው።
© ልጅ የአባቱን ሚስት፣ ልጅ የእናቷን ባል፣
© የልጅ ልጅ የአያቱን ሚስት/ባል፣
© ልጅ የአባቱን ሚስት እኅት፣
© የልጅ ልጅ የአያቱን ሚስት እኅት፣
© ልጅ የአባቱን ሚስት እናት፣
© የልጅ ልጅ የአያቱን ሚስት እናት፣
© ልጅ የአባቱም ሚስት አያት፣
© የልጅ ልጅ የአያቱን ሚስት አያት፣
© አባት የልጁን ሚስት፣
© አያት የልጅ ልጁን ሚስት፣
© አጎት የወንድሙን ልጅ፣
© ወንድም የወንድሙን ልጅ፣
© አባት የልጁን ሚስት እኅት፣
© አያት የልጅ ልጁን ሚስት እኅት፣
© አባት የልጁን ሚስት እናት፣
© አያት የልጅ ልጁን ሚስት እናት፣
© አባት የልጁን ሚስት አያት፣
© አያት የልጅ ልጁን ሚስት አያት፣
© ወንድም የወንድሙን ሚስት፣
© አጎት የወንድሙን ልጅ ሚስት፣
© ወንድም የወንድሙን ሚስት እኅት፣
© አጎት የወንድሙን ልጅ ሚስት እኅት፣
© ወንድም የወንድሙን ሚስት እናት፣
© አጎት የወንድሙን ልጅ ሚስት እናት፣
© ወንድም የወንድሙን ሚስት አያት፣
© አጎት የወንድሙን ልጅ ሚስት አያት
© ባል የሚስቱን ዘመዶች
፳፩) የጌታ ሚስት ባሏ ነጻ ያወጣውን ባሪያ ማግባት አይገባትም። [ሐተታ] ልጇን ማግባት ነውና።
_
፳፪) በሃይማኖት የማይመስለንን/የማትመስለንን ማግባት አይገባም።
_
፳፫) አባለ ዘሩ ሩካቤ ማድረግ የማይችል ወንድ ማግባት የለበትም። ፈናፍንታምም ማግባት የለበትም። ፈናፍንት ማለትም የወንድና የሴት አካል ያለው ነው። የሚጠመቅበት ቀን የሚሸናበት ጾታ ታይቶ ይሆናል። በወንድ አካሉ የሚሸና ከሆነ በ፵ ቀኑ፣ በሴት ከሆነ በ፹ ቀኗ ትጠመቃለች።
_
፳፬) ሴት ልጅ በማኅፀኗ ሩካቤን የሚከለክል አፅም ካለባት ማግባት አይገባትም።
_
፳፭) እብድ ማግባት አይገባውም።
_
፳፮) አካላትን የሚቆራርጥ ደዌ ሥጋ ያለባቸው ሰዎች ማግባት አይገባቸውም።
_
፳፯) ስትሰስን ተገኝታ የተፈታችውን ሴት ንስሓ መግባቷ እስኪታወቅ ድረስ፣ ጎረቤቶቿ መመለሷን እስኪመሰክሩላት ድረስ። ከተመሰከረለት በኋላ ፍትሐት ዘወልድ ተደግሞላት ታግባ።
_
፳፰) ሚስት ባሏ ከሞተ ከ፲ ወር በፊት ሌላ ማግባት አይገባትም። በዚህ በ፲ ወር ውስጥ መተጫጨት ግን ይቻላል።
_
፳፱) ከሐፃኒ ከመጋቢ በታች ያለ ሕፃን ሐፃኒ መጋቢ ሳይፈቅድለት ማጨት አይገባውም። በባልና በሚስት ፈቃድ ነው እንጂ ያለሁለቱ ፈቃድ ጋብቻ አይጸናም አይፈጸምም።
_
፴) አካለ መጠን ያልደረሰችን ሴት ማግባት አይገባም። ከመተጫጨት ግን አይከለክልም።
_
፴፩) ያጨ ሙሽራ ማጫ ከሰጠ በኋላ ሊመነኩስ ቢወድ ለሙሽራይቱ የሰጠውን ማጫ መቀበል ይገባዋል።
_
፴፪) ለማግባት አስቀድሞ መተጫጨትና ቃል መጋባት በፍጹም ምክር በፍጹም ፈቃድ ይፈጸም ዘንድ ነው። መልኩን ግብሩን ጸባዩን አጥንቱን ለመመርመር ነው። ለሠርግ የሚያስፈልገውን ለማዘጋጀት ነው።
_
፴፫) ባልና ሚስት እርሱም ሌላይቱን እርሷም ሌላውን ሳያውቁ የተጋቡ እንደሆነ ፍቅር ይጸናል።
_
፴፬) መነኵሴን ማግባት አይገባም። ከስልሳ ዓመት በላይ የሆናትን ሴት ማግባትም አይገባም።
_
፴፭) ማጨት ቃል ኪዳን መጋባት ነው። ከጋብቻ አስቀድሞ የሚሆን አለኝታ ነው። በደብዳቤም ያለ ደብዳቤም ይሆናል። በእጮኝነት ጊዜ ካህናት እጅ ለእጅ አያይዘው፣ አንድ የሚያደርጋቸውን መስቀል አስጨብጠው፣ አንድ ቀለበት አድርገው በደብዳቤ ይወስኑላቸው።
_
፴፮) ያለ ትልወት፣ ያለ ማጫ ማግባትም ይገባል [ይቻላል]።
_
፴፯) ሰባት ዓመት ላልሞላው ሕፃን ማጨት አይገባም።
_
፴፰) አጭቶ ለማግባት ቀን ያልወሰነ ሰው በሀገር ያለ ቢሆን ሁለት ዓመት ይጠብቁት። ሩቅ ሀገር የሄደ ቢሆን ሦስት ዓመት መጠበቅ ይገባል። በታወቀ ምክንያት የቀረ ቢሆን አራት ዓመት መጠበቅ ይገባል። ከዚህ ያለፈ ቢሆን ግን ለሌላ ማጋባት ይገባል።
_
፴፱) በፈቃዷ የምትኖር ሴት የፈለገችውን መርጣ ማግባት ትችላለች። በእናት በአባቷ ቤት ያለች ከሆነች ግን በቤተሰቦቿ ፈቃድ ይሁን።
_
፵) የሚጋቡ ሰዎች አካለ መጠን ያላደረሱ እናት አባት አሳዳጊ የሌላቸው ድኆች ቢሆኑ ፲፭ ዓመት እስኪሆናቸው ይጠብቁ። ከዚያ የፈቀዱትን ያድርጉ።
_
፵፩) አንዲትን ሴት ከታጨች በኋላ ሌላ ወንበዴ አስገድዶ ቢደፍራት እና ያጫት አልቀጥልም ካለ አስገድዶ የደፈራት ሚስት የሌለው ከሆነ ከወደደችው ሊያገባት ይገባል።
_
፵፪) ወንዶች ፈጽመው አካለ መጠን የሚያደርሱበት 20 ዓመት ነው። ይህም ባይሆን 25 ዓመት ነው። ሴቶች ደግሞ 12 ዓመት ነው። ይህም ባይሆን 15 ዓመት ነው።
_
፵፫) ከተጫጩ በኋላ የአንደኛው ግብሩ ጠባዩ የከፋ መሆኑን ተረድቶ እምቢ ቢል ይችላል። እምቢ ያለች ሴቲቱ ከሆነች ዓረቦኑን እጥፍ አድርጋ ትመልሳለች። ከሰጠ በኋላ አላገባም ያለ ወንዱ ከሆነ ዓረቦኑ ይቀርበታል።
_
፵፬) ልጁ በንጽሕና እኖራለሁ ካለ አባት ግድ አግባ ማለት አይገባውም።
_
፵፭) 25 ዓመት በላይ የሆናት ሴት ብትኖር አባት እናቷ ከማጋባት ቸል ቢሏት እርሷ ወደ ዳኞች አቤት ማለት ይገባታል። ራሷን የቻለች ከሆነች ግን ራሷ ማግባት ይገባታል።
_
፵፮) ጋብቻ ያለቁርባን አይጸናም።
_
፵፯) ለተጋቢዎች አንድ ልብስ ያለብሷቸዋል፣ ከጣታቸው አንድ ቀለበት ያገቡላቸዋል ጠባብ ከሆነ ፊት እርሱ አግብቶ ለእርሷ ይሰጣታል፣ አንድ መስቀል ያስጨብጧቸዋል። አንድ ዘውድ ይደፉላቸዋል እርሱ ደፍቶ ለእርሷ ይሰጣታል። ከዚያ እርሱ ቆርቦ ልብሱን ለእርሷ ይልክላትና ትቆርባለች። እሷም ከእናት ከአባቷ ቤት እርሱም ከእናት ከአባቱ ቤት ይቆያል። እንዲህ እያሉ ፵ ቀን ከኖሩ በኋላ ሠርግ ያደርጉላቸዋል። ልብስ የልጅነት፣ ቀለበት የሃይማኖት፣ ዘውድ የክብራቸው፣ መስቀል የመከራቸው ምሳሌ ነው።
_
፵፰) ሁለተኛ የሚያገቡ ካህናት ቢሆኑ ከሹመታቸው ይሻሩ። ከዚያ በኋላ ሦስተኛ ካገቡ ግን ርኩሳን ይሆናሉ።
_
፵፱) ሴት ስልሳ ዘመን ከሆናት በኋላ ተመልሳ አገባለሁ ብትል ከምእመናን ትለይ።
_
፶) ንጽሕ ጠብቀን ከሴት ርቀን እንኖራለን ብለው ከተሳሉ በኋላ ዳግመኛ የሚያገቡ ሰዎች ሕግ አፍራሾች ናቸው።
_
፶፩) አግብቶ ለፈታ ሰው መጽሐፈ ተክሊል ማድረስ አይገባም። ፍትሐት ዘወልድ ተደግሞለት በቁርባን ያገባል እንጂ።
_
፶፪) [ቁጥር ፱፻፮] ከሚጋቡት ሰዎች አንዱ ድንግል ቢሆን ለብቻው ተክሊል ያድርሱለት።
_
፶፫) ከሦስተኛ ጊዜ በላይ ማግባት የታወቀ ዝሙት ነው። ከአራተኛ ግቢ የተወለዱ ልጆች ለክህነት ለርስት አይገቡም።
_
፶፬) ብዙ ሴት ማግባት ዝሙት መውደድ ነው። በአንድ ጊዜ ሁለት ሴት ማኖር ለማንም አይገባውም። ይህን ያደረገ ካለ ግን ሁለተኛይቱን እስኪፈታት ድረስ ሥጋውን ደሙን ከመቀበል ቤተክርስቲያን ከመግባት ይከልከል።
_
፶፭) በሚስቱ ላይ ዕቁባት ያኖረ ካህን ቢሆን ከሹመቱ ይሻር፣ ጨዋ ቢሆን ከምእመናን አንድነት ይለዩት።
_
፶፮) ያመነች ሴት ያላመነውን ወንድ ብታገባ ከምእመናን ትለይ። ከእርሱ ተለይታ ንስሓ ብትገባ ግን ይቀበሏት። ልጁን ለኢአማኒ የዳረ ቢኖር ከምእመናን ይለይ።
_
፶፯) ወንድ ሚስቱ ከሞተች ጀምሮ አንድ ዓመት ሳይሆነው ማግባት አይገባውም። ዓመት ሳይሆነው ቢያገባ ግን ሚስቱ ከተወችው ሊወርሰው ከሚገባ ገንዘብ ሁሉ ይከልከል።
_
፶፰) ሴትም ባሏ ከሞተ ጀምሮ አሥር ወር ሳይሆናት ባል ብታገባ ከገንዘቡ ምንም ምን አትውረስ።
_
፶፱) ሳትሰስንበት ሰነፈች ደረቀች ብሎ ሚስቱን የፈታ ሰው ኃጥዕ ተብሎ ይፈረድበታል። በነውር የተፈታችውንም ንስሓ ሳትገባ ያገባት ሰው ቢኖር ኃጥዕ ተብሎ ይፈረድበታል።
_
፷) ባል ለሚስቱ የሚገባውን ፍቅር ያድርግላት፣ ሴትም ለባሏ የሚገባውን ፍቅር ታድርግለት።
_
፷፩) ጥምቀት የተነሣ ልጅ ያላቸው አባትና እናት በፊት ሁለት ቀን በኋላ ሁለት ቀን ከመገናኘት (ሩካቤ) መከልከል ይገባቸዋል።
_
፷፪) ሩካቤ የሚከለከልባቸው ጊዜያት
√ ሴት በወር አበባዋና በአራስነቷ ጊዜ
√ በጾም ወቅት፣ በሰሙነ ሕማማት
፷፫) በጾም ሩካቤ መከልከሉ ስለጾም የሚሆን ፈቃደ ነፍስ ይፈጸም ዘንድ ነው። ከሰሙነ ሕማማት ውጭ ባሉ አጽዋማት በፍትወት ጾር ድል የተነሣ ሰው ቢኖር የፈቲውን ጾር ማራቅ ይገባዋል። [ሩካቤ ይፈቀዳል። ይህ ግን ላልተቻለው ነው እንጂ ለተቻለውስ ሁሉንም አጽዋማት መታቀብ መልካም ነው]።
_
፷፬) ከሴት ማኅፀን አውጥቶ ከውጭ ዘርዕን መዝራት አይገባም።
_
፷፭) ላለመፀነስ ወይንም የተፀነሰውን ለማስወረድ መድኃኒት መጠቀም አይገባም።
_
፷፮) ሚስቱ እንደሰሰነች የነገሩት ሰው ቢኖርና ድርስ ነገሩን ባያውቅ፣ ድርስ ነገሩን ሊያውቅ ቢወድ ወደ ቤተክርስቲያን ዳኛ ወደ ኤጲስ ቆጶሱ ይውሰዳት። ከታቦቱ ፊት ያቁማት። ካህኑ መንቀል አንስቶ ይያዝ። ከርቤ ይጨምርበት። ከሐመደ ምሥዋዑ ከውሃው ይጨምሩበት። ከዚያ ይህንን በእጁ ይዞ። ክንብንብሽን አውርጂ ይበላት። በእግዚአብሔር ያምላት። ሌላ ሰው አልደረሰብኝም ብትል ባልሽ ከጠረጠረው ነገር የነጻሽ ከሆነ ይህን ውሃ ጠጪ ይበላት። በሐሰት ብትምዪ ግን ይህ የምትጠጪው ውሃ ሥጋሽን ያሳብጠው ይበላት። ሴትዮዋም አሜን አሜን ወአሜን ትበል። በታቦቱ ፊት ሆና ውሃውን ትጠጣ። ንጹሕ ከሆነች ደስ የምትሰኝበትን ልጅ ትወልዳለች።
_
፷፯) ማግባት ርኵስ ነው ብሎ ከጋብቻ የተከለከለ ሰው ኃጥዕ ነውና ከቤተክርስቲያን ይለይ።
_
፷፰) ሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን አትግባ። የደሟ ወራት እስኪፈጸም ድረስም አትቁረብ።
_
፷፱) ወንድ የወለደች ሴትም ከወለደች ጀምሮ 40 ቀን ከቤተክርስቲያን ውጭ ትቆይ። ሴት ከወለደች 80 ቀን ትቆይ።
_
፸) [ቁጥር ፱፻፴፮] አዋላጆች ወንድ ካዋለዱ 20 ቀን፣ ሴት ካዋለዱ 40 ቀን እስኪሆናቸው ድረስ ሥጋውን ደሙን አይቀበሉ።
_
፸፩) ባል ያላት ሴት ብትሰስንና ባሏ ባያውቅ ለብቻዋ ንስሓ መቀበል ይገባታል። ባሏ እያወቀ ሊፈታት ባይወድ ግን ሁለቱም ከምእመናን ይለዩ።
_
፸፪) የቄስ ሚስት ባሏ ከሞተ በኋላ ሌላ ብታገባ ንስሓ ይገባታል። በታች መቆም በኋላ መቀበል ይገባታል።
_
፸፫) ጋብቻ በሚከተሉት ነገሮች ይፈርሳል።
√ ባልና ሚስት ተመካክረው ከመነኮሱ
√ አንዱ የአንዱን ፈቃድ አልፈጽምም ቢል
√ አንዱ የአንዱን ሰውነት ሊያጠፋ ቢወድ
√ ባል ከሚስቱ ጋር መገናኘት (ሩካቤ) ካልቻለ
√ ሚስት ከባል ጋር መገናኘት ካልቻለች
(አፈ ማኅፀኗ ጠባብ ሆኖ ለሩካቤ ቢከለክል)
፸፭) ባል ሚስቱን ጋኔን ሲጥላት ቢያገኛት፣ ይህ ሁኔታ ካገባት በኋላ ያገኛት ከሆነ እርሱ መርዳት መታገሥ ይገባዋል። እርሱንም እንዲህ ያለ ነገር ቢያገኘው እርሷ መርዳት መታገሥ ይገባታል። ከማግባቷ በፊትም እያመማት ሳለ ደብቀው ቢያጋቡትና ቆይቶ ቢያውቅ መፍታት ይችላል።
_
፸፮) ከተጋቡ በኋላ ከሁለቱ አንዱን ደዌ ሥጋ ቢይዘው አንዱ ከአንዱ ሊለይ ቢወድ መለያየት አይገባውም። ሊፈታት ቢወድ ግን ትልወቷን ማጫዋን ሁሉ መስጠት ይገባዋል።
_
፸፯) ሰው በእሥራት ሳለ ወይም ባልታወቀ ምክንያት ቢጠፋ ግቢው ይፍረስ አንልም። መፈታትና አለመፈታቱ እስኪታወቅ ድረስ ባልና ሚስት ሆነው ይኑሩ እንጂ።ከአምስት ዓመት በኋላ ግን እንደ ፈቃዳቸው ይሆናል።
_
፸፰) ባል ዘማች ቢሆን እስከ ሁለት ዓመት ሚስቱ ትጠብቀው። ሚስት ስለ ባሏ ህልውና ምንም ዓይነት ዜና ካልሰማች፣ መሞቱንም ከመኳንንት ካልሰማች አታግባ። ሌሎች ሰዎች ሞቷል ብለው ቢናገሩ ለምስክርነት በመካከላቸው ወንጌል ያኑሩና ያምሏቸው። ድርስ ነገሩ ከታወቀ ከዚህ በኋላ ዳዊት እያስደገመች ቁርባን እያስቆረበች አንድ ዓመት ትጠብቅ። ከዚያ በኋላ ማግባት ትችላለች። ምስክሮች በሐሰት ሞቷል ብለው ቢመሰክሩ አሥር ወቄት ወርቅ ይክፈሉ። ሞተ ብለው ያወሩበት ወታደርም ከወደደ ሚስቱን መልሶ ወደ ቤቱ ያግባት።
_
፸፱) ባሏ ሳይፈቅድላት ከሌላ ወንድ ጋር ብትጠጣ፣ ወደ መሸታ ቤት ገብታ ብትስቅ ብትጫወት፣ ከቤቷ ወጥታ ከውጭ ከባዕድ ቤት ብታድር ይፍታት።
_
፹) ሚስት ባሏን ለመግደል ብትሞክር ወይም ሌለች ሊገድሉት እንደሆነ እያወቀች ዝም ካለችው ጋብቻቸው ይፈርሳል።
_
፹፩) ሚስት ያገባ ሰው በእርሱና በሚስቱ መካከል ክፉ ነገር ቢገኝ፣ ከምክንያት ወገን ማናቸውም ምክንያት ቢኖርበት ይታገሣት። ከክፋት ወደ በጎነት እስክትመለስ ድረስ ይምከራት ያስመክራት። መክሯት አስማክሯት ባትመለስ ወደ ደግ ቄስ ይውሰዳት። ቄሱም በመካከላቸው ሆኖ ያስታርቃቸው። ቄሱን አይሆንም ብትለው ኤጲስ ቆጶሱ አብረሽ ኑሪ ብሎ ይፍረድባት። ለኤጲስ ቆጶሱም ባትታዘዝ ባሏን ጥላ ብትሄድ ሁለተኛ አባብሎ ይመልሳት። በእምቢተኝነቷ ከጸናች ባሏ የወደደውን ማድረግ ይገባዋል። ሌላ ሊያገባ ቢወድ ያግባ። በንጽሕና መኖር ከፈለገ ይመንኩስ። እርሱ ገፊዋ ጠላቷ እንደሆነ ከታወቀና የቤት ቀጋ የሜዳ አልጋ ቢሆንባት ቃሉን አይቀበሉት። ግድ አብረህ ኑር ብለው ይፍረዱበት።
_
፹፪) ባል ከሚስቱ ሌላ ሴት ጋር ሲዘሙት ቢገኝ (ሴትም ከባሏ ሌላ ወንድ ጋር ስትዘሙት ብትገኝ) ዝሙቱን ባይተው ጋብቻው ይፈርሳል። ባልና ሚስት የሆኑ ዘማውያንን አያፋቷቸው። ካህናት ቀኖና ሰጥተው ያስታርቋቸው እንጂ።

አንቀጽ ፳፭
ይህ አንቀጽ እቁባት ማኖር እንደማይገባ ይናገራል።
፩) በኦሪት ነበር እንጂ በወንጌልስ እቁባት ማኖር አይገባም [የተከለከለ ነው]። ዕቁባት ማኖር ዝሙት ነው።
_
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፲፱ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ("የአምር አቡክሙ ሰማያዊ ዘትፈቅዱ ዘእንበለ ትስአልዎ።" ማቴ. ፮፡፰)
"በአማን ተንሥአ እግዚእነ = ጌታችን በእውነት ተነሥቷል።" ሉቃ. 24፥34

◆እባክዎን አንብበው ይጨርሱት!

👉ሞትን በሞቱ ድል አድርጎ የተነሣው የትንሣኤው ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለበዓለ ትንሣኤ በሰላምና በጤና ከመላ ቤተሰብዎ ጋር አደረስዎ!

የጌታችንና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድሞ በነቢያት አንደበት፣ ብሎም በራሱ አንደበት፥ በኋላም በአራቱም ወንጌላውያን የተረጋገጠ ጉዳይ መሆኑ ግልጽ ነው። ወንጌላውያኑም እንደሚከተለው ቅድስት ትንሣኤውን ከትበዋል፦

አ. ማቴዎስ፦ "እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ።" ማቴ. 28:6

በ. ማርቆስ፦ "አትደንግጡ፥ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።" (ማር. 16:6)

ገ. ሉቃስ፦ "ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።" (ሉቃ. 24:5)

ደ. ዮሐንስ፦ "ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ሦስተኛው ጊዜ ነበረ።" (ዮሐ. 21:14)

በመሆኑም ትንሣኤውን በዐይን የተመለከቱ የወንጌላውያንን ምስክርነት ያለመጠራጠር በፍጹም እምነት በማቅረብ የክርስቶስን ትንሣኤ በፍጹም ደስታ ለዓለም እንመሰክራለን።

👉ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ መመስከር የሚያስገኘው መዳን አለን

ሰው ሁሉንም ተግብሮ ሊያሟላቸው ከሚገቡ፦  <ማመን፣ መጠመቅ፣ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት (ስለ እግዚአብሔር መመስከር)፣ መቍረብ፣ ትእዛዛትን መጠበቅ፣ መልካም ሥራ መሥራት፣ መጋደል> ተብለው ከተዘረዘሩት ሰባት ዋና ዋና የመዳን መሥፈርቶች አንዱ መመስከር ነው። መዳንን ከሚያስገኙ ዋና ዋና መሥፈርቶችም መካከል አንዱ እንደ መሆኑ መጠን "ሐዋርያትም የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኀይል ይመሰክሩ ነበር።" (ሐዋ. 4:33) ተብሏል።

ቅዱስ ጳውሎስም "ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን ለይቶ እንደ አስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ።" (ሮሜ. 10:9) ብሏል። ሆኖም ግን ሌሎቸን መሥፈርቶች ጥሎ በመመስከር ብቻ የሚወረስ መዳን የለም።

👉በትንሣኤ በዓል ጊዜ ለምድራዊ ደስታ መገዛት ነውን?

የትንሣኤን በዓል ሰበብ በማድረግ ያልተገባ ሥጋዊ ፈቃድ የሚታይበትን ደስታ ማድረግ ለክርስቲያኖች የሚገባ አይደለም። በቅዱስ መጽሐፍም "የሙታን ትንሣኤን ከሚያምኑ ሰዎች ጋር በማያልቅ ደስታ በመንግሥተ ሰማይ ደስ ይልህ ዘንድ በምድር ያለች ደስታን እንቢ በላት።" (3ኛ መቃ. 10፡29) ተብሏል። እርስዎ በልተው ጠጥተው ሊያከብሩት በየዓመቱ የሚጓጉለት በዓለ ትንሣኤን ምናልባት የስካርና የቁንጣን ጊዜ አድርገው እያሳለፉ ከሆነ የበዓሉን አከባበር በውል አላወቁምና ራስዎን ወደ ጽድቅ በዓል ይመልሱ!!!

በዓል በመጣ ቍጥርም ማዕተብ አስረው፥ መስቀል አንጠልጥለው በስካር ባሕር ሰምጠው፥ በቁንጣን ምድረ በዳ የሚባዝኑትን፥ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ከማሰደብ ባሻገር የቀናችውን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን የሚያስነቅፉ፥ ብሎም ለሀገር ውድቀት ምክንያት የሚሆኑትን፥ በዓሉ በስካርና በቁንጣን የሚከበር የሚመስላቸው ወገኖቻችንን ክርስቶስ የሚፈልገው የትንሣኤ በዓልን ሳይሆን በአል የሚፈልገውን በዓል እያከበሩ እንደሆነ በማስረዳት ከእንደዚህ ዓይነቱ የበኣል አከባበር እንዲመለሱ መንፈሳዊ ግንዛቤ መስጠት ግድ ይለናል፣

👉ሥጋዊ ሞትን መፍራት አግባብ ነውን

የክርስቶስን ትንሣኤ ትንሣኤያችን ብለን የተቀበልን ክርስቲያኖች "ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞትም ይነሣል፥ ሕያው የሆነ የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘለዓለም አይሞትም።" (ዮሐ. 11:25-26) ብሎ አስቀደሞ ክርስቶስ እንደ ተናገረ የግድ በሥጋ የሚሆነውን አዳማዊ ሞት ልንፈራ አግባብ አይደለም። በእርግጥ ሁሉም ሰው ሥጋዊ ሞትን ይቀምሳል። ነገር ግን ከሥጋዊ ሞት በኋላ ዘለዓለማዊ ሕይወት መኖሩን እናምናለን።

ቅዱስ ጳውሎስም ልጁ ጢሞቴዎስን "በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ከዳዊት ዘር የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስበው።" 2ኛ. ጢሞ. 2:8 እንዳለ ክርስቶስን በፍጹም ትንሣኤ እናስበዋለን።

👉ሰዎች ከሞቱ በኋላ ዳግም ለመነሣታቸው ምን ያህል እውነትነት አለው

በቀጥታ ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሆን  መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ 10:24 ላይ
"ከሞትን በኋላ አንነሣም አትበሉ፤ ይሄን የሚናገሩና የሚያስቡ ሰዎችን በትንሣኤ ጊዜ እንዳይድኑ ዲያብሎስ ተስፋ ያስቈርጣቸዋልና፥ ትንሣኤም በደረሰችባቸው ጊዜ ያውቃሉ፤ ኀጢአታቸውን ያስብባቸው ዘንድ ባለማወቅ ኀጢአት የሠሩ ሰዎች በትንሣኤ ጊዜ ፈጽመው ያዝናሉ፤ በዚያች ቀን እንደሚነሡ አላመኑበትምና።" በማለት ይናገራል። ይሄውም ከበቂ በላይ እሙን ማስረጃ ነው። በትንሣኤ ሙታን ለሚጠራጠርም "አንተ ሰነፍና ልበ ባካና ሙታን የማይነሡ ይመስልሃልን? በሙታን ትንሣኤ በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አፍ መለከት በሚነፋ ጊዜ በዚያ እንደ አንቀላፋህ አትቀርምና እንዲህ አታስብ... ለሥጋ ለባሽም ሁሉ ትንሣኤ ይሆናል። አሜን" 1ኛ መቃ. 9:7-10 በማለት ተግሣጽን ጨምሮ ይጽፋል።

ትንሣኤ ሙታን መኖሩንም ዐውቀው ሰማዕትነትን ስለ ተቀበሉ ቅዱሳን ሲናገር "በኋለኛዪቱ ቀን በነፍስና በሥጋ ትንሣኤ እንዲደረግ ዐውቀው ሰውነታቸውን ለሞት ሰጡ።" 2ኛ መቃ. 13:11 ብሏል።

👉በትንሣኤ ጊዜ አነሣሣችን እንዴት ነው?

ቅዱስ ጳውሎስ "በሞቱ ከመሰልነው በትንሣኤውም እንመስለዋለን።" (ሮሜ. 6፡5) እንዳለ በሞቱ መስለነው ከሆነ ክርስቶስን በትንሣኤው መስለነው በክብር እንነሣለን። የክርስቶስን ትንሣኤ በየዓመቱ በልቶ ጠጥቶ ከማክበር ባሻገር ግን በክርስቶስ ትንሣኤ መነሣት የሚያስችለን የጽድቅን ተግባር አከናውነናል?

👉የጻድቃን ተንሣኤ ልዩነት አለውን?

ቅዱስ መጽሐፍ "ኮከብ ከኮከብ በክብር ይበልጣልና የሙታን ትንሣኤያቸው እንዲሁ ነው።" (1ኛ ቆሮ. 15:41-42) በማለት እንደ ገለጠው ሁሉም እንደ ሥራው መጠን ክብር አግኝቶ ይነሣል።

ቅዱስ መጽሐፍ "ኮከብ ከኮከብ በክብር ይበልጣልና የሙታን ትንሣኤያቸው እንዲሁ ነው።" (1ኛ ቆሮ. 15:41-42) በማለት እንደ ገለጠው ሁሉም እንደ ሥራው መጠን ክብር አግኝቶ ይነሣል። በማቴዎስ ወንጌል "ቦ ዘወድቀ ውስተ ምድር ሠናይ ወወሀበ ፍሬ ቦ ዘምእት ወቦ ዘስሳ ወቦ ዘሠላሳ = በመልካም እርሻ ላይ የወደቀ ዘር አለ፥ መቶ ያፈራ አለ፥ ስሳ ያፈራ አለ፥ መቶ ያፈራም አለ።" (ማቴ. 13:8) ተብሎ የቀረበውም ምሳሌ ጻድቃን በትንሣኤ ጊዜ እንደየክብራቸው ደረጃ እንዳላቸው የሚያስገነዝብ ነው። እርስዎስ የትኛው ደረጃ ላይ መድረስ የሚያስችል የጽድቅ ፍሬ አፍርተዋል?
Forwarded from የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ("የአምር አቡክሙ ሰማያዊ ዘትፈቅዱ ዘእንበለ ትስአልዎ።" ማቴ. ፮፡፰)
👉በትንሣኤ ጊዜ ኃጥኣን ጻድቃን ሆነው የሚነሡበት ዕድል ይኖር ይሆን?

በዳግም ምጽአተ ክርስቶስ ሰው እንደየሥራው ይነሣል እንጂ በስሕተት ጻድቁ ኃጥእ፥ ኃጥኡ ጻድቅ የሚሆንበት ዕድል የለም። ቅዱስ መጽሐፍም ይሄን በተመለከተ፦ "ወይን ብትተክልም በለስ ይሆን ዘንድ አይለወጥም፥ በለስም ብትተክል ወይን ይሆን ዘንድ አይለወጥም፤ ስንዴም ብትዘራ ገብስ ይሆን ዘንድ አይለወጥም፤ ገብስም ብትዘራ ስንዴ ይሆን ዘንድ አይለወጥም። ነገር ግን ሁሉ በየዘሩና በየወገኑ፥ በየፍሬውና በየዕንጨቱ፥ በየ ቅጠሉና በየሥሩ፥ ከእግዚአብሔር በሚገኝ የምሕረት ጠል በረከትን ተቀብሎ ፍሬን ያወጣል። እንደዚሁም ምድር እግዚአብሔር እንደ ዘራባት ነፍስንና ሥጋን ታስገኛለች፤ እግዚአብሔር የዘራቸው ሥጋና ነፍስ ተዋሕደው ይነሣሉ እንጂ በጎ ሥራ የሠሩ ሰዎች ክፉ ሥራ በሠሩ ሰዎች አይለወጡም፤ ክፉ ሥራም የሠሩ ሰዎች በጎ ሥራን በሠሩ ሰዎች አይለወጡም።" (2ኛ መቃ. 16:6-8) በማለት ገልጦ አብራርቶ ይናገራል።

ሁሉም በሥርዐትና በአግባብ እንደሚነሣ ቅዱስ ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮ. 15:20-23 በጻፈው መልእክቱ ላይ "አሁንም ክርስቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስቀድሞ ተነሥቶአል። በመጀመሪያው ሰው ሞት መጥቶአልና፥ በሁለተኛው ሰው ትንሣኤ ሙታን ሆነ። ሁሉ በአዳም እንደሚሞት እንዲሁ በክር ስቶስ ሁሉ ሕያዋን ይሆናሉ። ነገር ግን ሰው ሁሉ በየሥርዐቱ ይነሣል፤ በመጀመሪያ ከሙታን የተነሣ ክርስቶስ ነው፤ ከዚያ በኋላ በክርስቶስ ያመኑ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ ይነሣሉ።" ብሏል።

👉በትንሣኤ ጊዜ የሚፈርደው ማን ነው

" በእግዚአብሔር ፊት በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ።" (2ኛ ጢሞ. 4:1) እንደ ተባለ፥ አንድም  "የሚፈርድስ ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን ተለይቶ የተነሣው፥ በእግዚአብሔርም ቀኝ የተቀመጠው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚፈርደው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።" (ሮሜ. 8:34) ተብሎ እንደ ተቀመጠ ፈራጁ ሞትን በሞቱ ድል አድርጎ የተነሣው መደኅነ ዓለም ክርስቶስ ነው።

👉ጻድቃን ሆነን ብንነሣ የምንኖረው ከማን ጋር ነው?

እግዚአብሔር በቸርነቱ አግዞን ከኀጢአት ነፃ ሆን ለትንሣኤ ዘለክብር ቢያበቃን የምንኖረው በፍጹም ክብር እርሱን መስለን ከርሱ ጋር እንደምንኖር በሮሜ. 6:8 "ከክርስቶስ ጋር ከሞትንም ከእርሱ ጋር በሕይወት እንደምንኖር እናምናለን።" ብሏልና ጳውሎስ ምስክራችን ነው። አንድም ይሄው ሐዋርያ "በጥምቀትም ከእርሱ ጋር ተቀብራችኋል፤ በእርስዋም ከሙታን ለይቶ ባስነሣው በእግዚአብሔር ረዳትነትና በሃይማኖት ከእርሱ ጋር ተነሥታችኋል።" (ቈላ. 2:12) በማለት መልሶ አስረግጦ መስክሮልናል።

👉ከትንሣኤ በኋላ በክብር መነጠቅ አለን?

በክብር መነጠቅ ማለት እጅግ በረቀቀ የክብር ብርሃን መላቅ፣ ማደግ፣ መብቃት ማለት ነው። እኛም በሕገ እግዚአብሔር ጸንተን፥ በምግባርና በሃይማኖት ተጠብቀን ቅዱሳን ሆነን ብንገኝ ለዚህ መንፈሳዊ ክብር እንደምንበቃ ቅዱስ ጳውሎስ፦ "ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤  ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።" (1ኛ ተሰ. 4:16-18) በማለት ገልጧል።

●ትንሣኤ ዘለክብርን እንነሣ ዘንድ የትንሣኤያችን በኵር አምላካችን ክርስቶስ በቸርነቱ ይርዳን!

👉መምህር ያሬድ ዘርአ-ቡሩክ
👉ርእሰ አድባራት ወገዳማት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል - ድሬዳዋ
👉ሚያዝያ፦ ፰/፳፻፲፭ ዓ.ም

የዩቲዩብ ድሕረ ገጽ👇
https://www.youtube.com/@yaredzera-buruktube8843

የፌስቡክ ገጽ👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063724038968&mibextid=ZbWKwL

የፌስቡክ ገጽ👇
https://www.facebook.com/Yared.ZeraBuruk?mibextid=ZbWKwL

👉የቴሌግራም ቻናል
https://www.tg-me.com/yaredzer

👉ለሌላውም እንዲደርስ Share ያድርጉት!!!
__ፍትሐ ነገሥት ክፍል ፳__
አንቀጽ ፳፰ ስለውሰት ይናገራል።
፩) ውሰት በታወቀ ዕለት በታወቀ ቦታ ዋጋ ሳይሰጡ ወይም ሳይቀበሉ ጥቅም የሚገኝበትን ገንዘብ መዋስ ነው። አንድም ማዋስ ነው።
_
፪) እስከዚህ ቦታ ብሎ ከብት የተዋሰ ሰው ቢኖርና ከቦታው አልፎ ሄዶ ከብቱ ቢሞት መክፈል ይገባዋል። ቦታውን አልፎ ሳይሄድ ነገር ግን በራሱ ቸልተኝነት ከሞተበትም መክፈል ይገባዋል። ከገደል አፋፍ ሆና ስትበላ አይቶ ዝም ቢልና ብትሞትም ይከፍላል። ጌታው አብሮ ካለ ግን አይከፍልም።
_
፫) በዋጋ የተዋሰ ከብት ቢኖርና ቢጠፋ የተዋሰው ዋጋውን ይከፍላል። ከተወሰነው ቦታ አልፎ የሄደ ቢሆን ላዋሰው ሰው አልፎ የሄደበትን ጨምሮ ይስጥ።
_
፬) ያዋሰ ሰው በወደደው ጊዜ መልስልኝ ማለት ይገባዋል። የተዋሰ ሰውም እንዲሁ በወደደው ጊዜ መመለስ ይገባዋል።

አንቀጽ ፳፱
ይህ አንቀጽ ስለ አደራ ይናገራል።
፩) አደራ ጠባቂ ለአስጠባቂ የሚሰጣት ገንዘብ ናት። ይህችውም አስጠባቂ ከጠባቂ ዘንድ አምኖ የሚያኖራት ገንዘብ ናት። የተቀበላትም ሰው እንደገንዘቡ አድርጎ በፍጹም ትጋት መጠበቅ ይገባዋል። ተግቶ እየጠበቃት ብትጠፋ ዕዳ የለበትም።
_
፪) አደራ አስጠባቂው ብዙ ዘመን ኖሮ ቢጠፋ አደራ ጠባቂው ለአደራ አስጠባቂው ወራሾች አደራውን ይስጥ። ወራሾች ባይኖሩት ለመሥዋዕት ይሁን።
_
፫) የሰው አደራ የተቀበለ ሰው ለእገሌ ስጥልኝ ቢለው ስጥልኝ ላለው መስጠት ይገባዋል።
_
፬) አደራ ጠብቆ መመለስ ለለመደ ነው እንጂ ላልለመደ መስጠት አይገባም። አደራ ያኖሩበት ሰው ቢሞት አደራ ይቀራል።
_
፭) አደራ የተቀበለ ሰው ጠባቂ አስጠባቂ በኃይል ሰርቆ ቀምቶ እንዳመጣው እያወቀ አደራ ቢያኖር እጥፍ ሊያስከፍሉት ይገባል። የሌባ ዋሻ የቀማኛ ጋሻ ሆኗልና።

አንቀጽ ፴
ይህ አንቀጽ ስለሹመት ይናገራል።
፩) ግብሩን ጠባዩን ያሳመረ ሰው፣ የሹመትን ሥርዓቷን ያወቀ የጠነቀቀ መሾም ይገባዋል። ለጌታው ገንዘብ ከፍሎ ይሾማል።
_
፪) የጌታው ገንዘብ ያለተንኮል ያለስንፍና በሹሙ እጅ ቢጠፋ መክፈል አይገባውም።
_
፫) ሿሚና ተሿሚው ምስክር የሌለው ጠብ ቢጣሉ ሿሚው ምሎ በተናገረው ይሁን። በገንዘቡ አምኖ ሹሞታልና።
_
፬) ሹም በተሾመበት ገንዘብ እንደራሴ መሾም አይገባውም። ጌታው ሹም ብሎ ቢፈቅድለት ነው እንጂ።
_
አንቀጽ ፴፪
ይህም የሹመትን ነገር ይናገራል። ከአንቀጽ ፴ የሚለየው ይህ አንቀጽ ፴፪ የሐፃኒ የመጋቢ ነው። አንቀጽ ፴ የቤተ መንግሥት ነው።
፩) ለሽማግሌ፣ ለሕፃን፣ ለእብድ፣ ለታማሚ ጽኑ ሹም ሊሾሙላቸው ይገባል።
_
፪) አገልጋይ በጌታው ትእዛዝ ማዘዝ መሠልጠን ይገባዋል። ተሿሚዎች ገንዘብ ቢያጠፉ መክፈል ይገባቸዋል። [ሐተታ:- ጥንቱን መሾማቸው ሊጠብቁ ነውና]።
_
አንቀጽ ፴፩
ይህ አንቀጽ አገልጋይ ስለመግዛትና አገልጋይን ነጻ ስለማውጣት ይናገራል።
፩) ሰው ሁሉ ከአንድ ከአዳም በመገኘት ባለመገዛት አንድ ነው። ነገር ግን ጦርነትና ሌሎችም ምክንያቶች አንዱ ለአንዱ ይገዛ ዘንድ መገዛትን ታመጣባቸዋለች። ድል የተነሡት ድል ለነሡት እንዲገዙ ታደርጋለች
_
፪) አማኒ አገልጋይን ላላመነ ሰው መሸጥ አይገባም። የአገልጋይ ልጆች ለጌታቸው ይገዙ። አንድም ለአባታቸው ጌታ ይገዙ።
_
፫) አገልጋይን ነፃ ማውጣት ከትሩፋት ሥራ ወገን ናት። አገልጋይን ሁሉ ነጻ ማውጣት ይገባል።
_
፬) አገልጋይ በሚከተሉት ምክንያቶች ነጻ ሊወጣ ይችላል።
√ ከጌታው ዘመድ አንዱ ቀድሞ ገዝቶት ከነበረ፣
√ ጌታው ክርስትና ቢያነሣው፣
√ በጌታው ፈቃድ ክህነት ከተሾመ፣ ከመነኮሰ
√ ጌታው ፈቅዶ ባርያው ዘማች ከሆነ/ከዘመተ
√ ጌታውን ከሞት ቢያድነው (ተዋግቶ/መክሮ)
√ ጌታው ቢሞት
√ አገልጋዩ በጠላቱ እጅ ከተያዘ በኋላ ከድቶ ወደ ጌታው ቢመለስ ነጻ መውጣት ይገባዋል።
_
፭) ነጻ የወጣች አገልጋይ ነጻ ያልወጣውን አገልጋይ ማግባት አይገባትም።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፳፩ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የሕይወት አጋሬን እንዴት ልምረጥ

“ፍቅር ይዞኛል” “አፍቅሬአለሁ” ማለት በብዙ ወጣቶች ዘንድ የተለመደ ነገር ነው፡፡ ወጣትነትወንዶች ሴቶችን ሴቶችም ወንዶችን ለፍቅር የሚመርጡበት እድሜ ነው፡፡ በወጣትነት ዘመንበተቃራኒ ጾታ መሳብ፤ የራስን ሰው ለማግኘት ጊዜ ወስዶ ማሰብና መጨነቅ የተለመደ ክስተትነው፡፡ መፈላለግ ተፈጥሮአዊ ቢሆንም ሁሉም ለቁም ነገር ነው ለማለት ግን አያስደፍርም፡፡ በዚህየተነሣ ወጣቶች ተቃራኒ ጾታን ለጓደኝነት የሚመርጡባቸውን ምክንያቶች በሚገባ ማወቅ አስፈላጊ ያቸው ነው፡፡ የተወሰኑትን ምክንያቶች በዚህ ትምህርት ለማየት እንሞክራለን፡፡

1. ወጣቶች የተቃራኒ ጾታ ጓደኛ የሚይዙባቸው ምክንያቶች
ሀ. ጓደኛ የለውም (የላትም) እንዳይባሉ፤
ለ. ሌሎች ሲይዙ በማየት፤
ሐ. ለሩካቤ ሥጋ ፍላጎት (ለዝሙት) (2 ሳሙ 13፡11)፤
መ. በፍቅር ስለወደቁ (ዘፍ. 34፡3)፤
ሠ. የትዳር ጓደኛ ፈልገው (ዘፍ. 29፡18)፤
ረ. ለቁሳዊ ጥቅም ብለው (መሳ. 16፡5)
ሰ. በፉክክር ስሜት፣ ሌሎችም ለማናደድ ሲፈልጉ ወ.ዘ.ተ፡፡

2. የሕይወት አጋርን የምንመርጥባቸው ደረጃዎች፡-ወጣቶች የፍቅር ጓደኛ መፈለጋችሁ ኃጢአት ሳይሆን ተፈጥሮአዊ እና ጤናማ ስሜት ነው፡፡ነገር ግን ይህን የተቀደሰ ፍላጎት ያለ ጊዜው፣ በተሳሳተ ምርጫ እና ጤናማ ባልሆነ ፍላጎት እንዳናበላሸው ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መመዘኛዎችና ደረጃዎችን ማጤን ትክክለኛ ውሳኔ እንድንወስን ያስችለናል፡፡ እንዲሁም ያለጊዜው ባደረግነው ያልተገባ ግንኙት ወይምበተሳሳተ ምርጫችን እንዳንጸጸት ያደርገናል፡፡

2.1. አካላዊ ብቃት፦
ወንዶች ለአቅመ አዳም ሴቶች ለአቅመ ሔዋን መድረሳችንን፤ ሰውነታችን ሌላ ሰውን ለመቀበል የተዘጋጀ መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡

2.2. መንፈሳዊ ብስለት፡-
በመንፈሳዊ ሕይወት ጠንካራ መሆናችንን እንዲሁም ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቅ መንፈሳዊብስለት እንዳለን ለማረጋገጥ ራሳችንን ማየት ተገቢ ነው፡፡ በሕይወታችን ወይም በኑሮአችን ሁሉእግዚአብሔርን እንደምናስቀድም፣ የጸሎት ሕይወታችን ምን እንደሚመስል፣ መጽሐፍ ቅዱስንየማንበብና ለቃሉ ያለንን ፍቅር፣ የመንፈሳዊ ሕይወታችንን ጥንካሬ … ወ.ዘ.ተ ያጠቃልላል፡፡

2.3. የኢኮኖሚ ብቃት፦
ፍቅር ሓላፊነት እና ተጠያቂነት ያለበት ግንኙነት ነው፡፡ ገንዘብ ለዚህ ዓለም ኑሮ አስፈላጊ ነገርነው፡፡ ስለዚህ ከራሳችን አልፈን ሌላ ሰው ማኖር እንዲሁም መንከባከብ የሚያስችል አቅም አለኝ ወይብለን ራሳችንን መፈተሽ አለብን፡፡ ለመተዳደሪያ የሚሆን በቂ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ አለን ወይ? የሚለውን ጥያቄ በአስተማማኝ ሁኔታ መመለስ ይገባናል፡፡

2.4. የሥነ ልቡና ዝግጅት ፦
አንድን ሰው ለማፍቀር ከመነሣታችን በፊት ሥነ ልቡናዊ ዝግጅት ማድረግ አለብን፡፡ ፍላጎታችንን መመርመር፣ ሌላ ሰውን ለመቀበል የመንፈስ ዝግጅት ማድረግ፣ በስሜት ሳይሆንበእርጋታና በሰከነ መንፈስ ምርጫችንን ማጤንን አስፈላጊ ነው፡፡

ወጣቶች የሕይወት አጋራችሁን ስትመርጡ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላታችሁን አረጋግጡ፡፡ ፍቅር የከበረ የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ተገንዝባችሁ በስሜታዊነትየፍቅር ጓደኛ ከመምረጥና በኋላ ከመጸጸት ራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ከክፉ የጎልማሳነት (የወጣትነት) ምኞት በመራቅና በመሸሽ እያንዳንዱን ጉዞአችሁን በእግዚአብሔር ቃል እየመረመራችሁ እናፈቃዱን እየጠየቃችሁ በመንፈስ የምትመሩ ሁኑ፡፡

#አቤል_ተፈራ_በላይ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ተግሣጽ & ስድብ
ንድ ወቅት በአንድ ቤት ብዙ ሰዎች ተኝተው ሳለ አንዱ ፈርቶ ሌሎች የተኙ ሰዎች ሳይሰሙ ከዚያው ከቤት ይጸዳዳል። በኋላ ሲያስበው ሰው ሊስቅበት ነው። ከዚያ ሰገራውን በእጁ ይዞ የሁሉንም ልብስ እንደተኙ ይቀባዋል። እርሱም እጁን አባብሶ መልሶ ይተኛል። እነዚያ የተኙት ሰዎች በኋላ ነቅተው ወደ ውጭ ወጣ ብለው ሳሉ ልብሳቸውን ቢያዩት ሰገራ በሰገራ ሆኗል። ሰው እንዳይስቅብን ብለው እነርሱ እንዳላደረጉት እያወቁ ጠፍተው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ ይባላል። ያ አራም ግን በሰላም ከቤት ተኝቶ አደረ ይባላል።

አሁን እየሆነ ያለው ነገር ይህን ይመስላል። አራሞች በሰላም እየኖሩ ንጹሓን የሚሸማቀቁበት ክፉ ዘመን ነው። ነውረኞች ተወደው በሰላም እየኖሩ ነውረኞች ነውራቸውን የቀቧቸው ንጹሓን ሰዎች እየተሰደቡ ይኖራሉ። ምሁራን ዝም ብለው ተሳዳቢዎች ተናጋሪ የሆኑበት ዘመን ነው። ስድብና ተግሣጽ ይለያያል። ገሠጸ ተቆጣ፣ መታ፣ ደበደበ፣ አስተማረ ከሚለው የግእዝ ቃል ተግሣጽ የሚል ባዕድ ዘር ይወጣል። ትርጉሙ ቁጣ፣ ትምህርት ማለት ነው። መምህር ወመገሥጽ ዘኢያደሉ ለገጽ በሚልበት ጊዜ መገሥጽ የሚያስተምር ተብሎ ይተረጎማል እንጂ የሚሳደብ ተብሎ አይተረጎምም። ስድብ ጸዐለ ሰደበ ከሚለው የግእዝ ቃል የሚወጣ ሲሆን "ጽዕለት" መስደብ፣ መሰደብ ስድብ ይላል። ለምሳሌ ሕፃናትን መገሠጽ ይገባል ሲባል ትምህርት ሲገድፉ እና አልማር ሲሉ መቆጣት ይገባል ማለት ነው። እየቀጡ እየመቱ ማረም ይገባል ማለት ነው። ስንማታ ግን ሕይወታቸው እንዳያልፍብን ባለፈው በፍትሐ ነገሥት እንደተማርነው የምንማታበትን ኃይል በራሳችን ጉልበት ፈትነን አማትበን ሊሆን ይገባል። የሞት ብዙ ምክንያት አለውና ተብሎ ተገልጿል።

የተግሣጽ ትርጓሜ ይህ ነው። ከዚያ ውጭ ጥርግርግ እያደረጉ እየተሳደቡ ያሉ ሰዎችን መምህር ወመገሥጽ ማለት ትልቅ ነውር ነው። ንስሓ እንዳይገቡም መሰናክል መሆን ነው። እየተሳደበ የሚያስተምር ሰው መምህር ወመገሥጽ ሳይሆን መምህር ወመጽዕል ነው የሚባለው። ለቤተክርስቲያን ትልቅ ሸክም እየሆኑ ያሉት እነዚህ ናቸው። እናርማለን ይላሉ። ነገር ግን እነርሱ ተሳስተው ስታርማቸው ተሳዳቢ መንጋቸውን ይለቁብሃል። ደግሞ መንጋን መፍራት ተገቢ አይደለም። ማንኛውም መምህር በቀዳሚነት ሊፈራው የሚገባው እግዚአብሔርን ነው። ሁሉም ሰው በእግዚአብሔር ዳኝነት በመላእክትና በሰው ሁሉ ፊት ይቀርባል። ይህንን ነው ማሰብ። በክፉዎች መሰደብ ለመምህራን ክብር ነው። ከታገሡት ሐዋርያዊ ክብርን ያሰጣቸዋልና።

ስለዚህ ተሳዳቢነትን እንተው። ተምረን እናስተምር። ሳይማሩ ማስተማር ጥፋት ይኖረዋልና። ከተሳሳትን ይቅርታ እንጠይቅ። ሰው አምላኪ አንሁን። የሰውን መልካምነቱን ብቻ እንውሰድ። ክፉ ነገሩን አብነት ማድረግ አይገባም።

© በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
ዓይኖቹ እንደወይን ቀይ ጥርሶቹ እንደወተት ነጭ ናቸው


Size:- 13.2MB
Length:-57:48

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#የትዳር_ዋና_ዓላማ

አንዳንድ ትዳሮች ለባል፣ ለሚስት፣ ለልጆችና ለሌሎች ሰዎች በረከትን ይዘው ይመጣሉ፡፡ አንዳንድ ትዳሮች ደግሞ ይህን ይዘው አይመጡም፡፡ ይዘው ካለመምጣታቸውም በላይ ለባልም፣ ለሚስትም፣ ለልጆችም፣ ለሌሎች ሰዎችም ችግር ይኾናሉ፡፡

ለመኾኑ የእነዚህ ትዳሮች ልዩነቱ ምን ላይ ነው? የእነዚህ ትዳሮች ዋና ልዩነቱ ትዳሩን ግብ ባደረጉበት ዓላማ ላይ ነው፡፡ አንድ ወንድና አንዲት ሴት የሚጋቡት የሩካቤ ፍላጎታቸውን ለማርካት ወይም በቁሳዊ ነገር ለመረዳዳት ከኾነ ጋብቻቸው በረከት ይዞ አይመጣም፡፡ #ጽድቅን #ዓላማ አድርገው ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው ዓለም ለመጓዝ ለሚጋቡት ግን ትዳራቸው ለተጋቢዎቹ ብቻ ሳይኾን ለልጆቻቸውም ለሌሎች ሰዎችም ታላቅ የኾነ ደስታን ያመጣል፡፡

እግዚአብሔርም ጋብቻን የመሠረተው ለዚህ ነው - የምንኩስና ሕይወትን መምራት ለማይችሉ ሰዎች #ጽድቅን #ዓላማ #አድርገው እንዲኖሩበት ! ! !

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
አምስቱ የንስሐ መንገዶች ገጽ 97
ትርጉም - ገብረ እግዚአብሔር ኪደ )
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
“ላገቡት” የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ባልና ሚስት አንድ መኾናቸውን ብዙ ጊዜ ስለ ተማራችሁት እርሱን አልደግምላችሁም፡፡ ከዚህ ተነሥቼ ግን ጥያቄ ልጠይቃችሁ፦ ከሰውነታችሁ ውስጥ አንዱ ሕዋስ ቢታመም ቆርጣችሁ ትጥሉታላችሁን? ከሕመሙ ይፈወስ ዘንድ የምትጥሩ አይደላችሁምን? ለትዳር አጋራችሁም እንደዚህ መኾን አለባችሁ፡፡ እንደዉም'ኮ፥ ከሰውነታችሁ ሕዋስ ውስጥ ያለው በሽታ አንዳንዴ ላይድን ይችላል፡፡ የትዳር አጋራችሁ ግን፥ ምንም ክፉ ቢኾንም ሊለወጥ ይችላል፡፡

በሰውነታችን ላይ የሚኖረው አንዳንዱ ችግር ለምሳሌ ልምሾ እጅ ወይም እግር ሥራ መሥራትን ሊከለክለን፣ በሌላዉ የሰውነታችን ክፍል ላይ ጫና ሊያሳድርብን ይችላል፤ ነገር ግን ይበልጥ እንክብካቤ እናደርግለታለን እንጂ ቆርጠን አንጥለዉም፡፡

ታዲያ መዳን ለማይችለው ሰውነታችን ይህን ያህል እንብካቤ እያደረግንለት ሳለ፥ የመዳን (የመለወጥ) ዕድል ያለው አካላችንን (ባለ ትዳራችንን) መቁረጥ (መፍታት) እንደ አማራጭ ማስቀመጣችን እንዴት ብናብድ ነው?
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፩_
ሲኖዶስ የግሪክ ቋንቋ ሲሆን ትርጉሙ ጉባኤ፣ ሸንጎ፣ የጳጳሳትና የሊቃውንት ማኅበር ማለት ነው።
፩) የሐዋርያት ሲኖዶስ የሚባሉት አራት መጻሕፍት ናቸው። እነዚህም:-
√ ግጽው (ረስጠጅ)
√ ትእዛዝ (ረስጠብ)
√ ሥርዓተ ጽዮን (ዓይን)
√ አብጥሊስ (ረስጣ/ረስጠአ)
ናቸው። የሲኖዶስ ውሳኔ የቤተክርስቲያኗ ሕግ እና ሥርዓት ሆኖ ይሠራል።
π
፪) በቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚታወቀው ኤጲስ ቆጶስ ድንግል መሆን እንዳለበት የተወሰነው በአልቪራ ጉባኤ ስፔን በ305/6 ዓ. ም ነው። በኋላ በኒቅያው ጉባኤ ቀርቦም ጸድቋል።
π
፫) የኒቅያ ጉባኤ አርዮስን ካወገዘ በኋላ ሌሎች የሥርዓት ጉዳዮችንም ወስኗል።
π
፬) አንዳንድ ሲኖዶሶች ወቅትንና አካባቢን መሠረት አድርገው የተደነገጉ ናቸው።
π
#ግጽው #ሲኖዶስ
ቁጥር ፲፭:- በቅዱስ ጴጥሮስ ጸሎትና ልመና እግዚአብሔር ጠንቋዩን ሲሞንን አጠፋው።
√√√
ትእዛዝ ፩:- ጸሎታችን ወደ ምሥራቅ ይሁን። ምጽአቱ ከምሥራቅ እንደሚሆን በዚህ አወቅን።
√√√
ሰንበት በእግዚአብሔርና በሕዝቡ መካከል የቃል ኪዳን ምልክት ነው።
√√√
ትእዛዝ ፪:- ለጸሎት፣ መጻሕፍትን ለማንበብና ቁርባን ለማቅረብ በየእሑዱ በሦስት ሰዓት ይሰብሰቡ። በዚህች ቀን መልአኩ ክርስቶስን እንደምትፀንስ ለማርያም አብሥሯታልና። ጌታ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶበታልና።
√√√
ትእዛዝ ፫:- በዕለተ ረቡዕ ተሰብስበው ጸሎት ያድርጉባት። በዚህች ቀን አይሁድ ይዘው እንደሚሰቅሉትና እና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ ነግሯቸዋልና። በዚህም ቀን አዝነዋል ተክዘዋልና።
√√√
ትእዛዝ ፬:- በዕለተ ዓርብ በዘጠኝ ሰዓት ተሰብስበው ጸሎት ያድርጉ። ክርስቶስ መከራ ተቀብሎበታልና።
√√√
ትእዛዝ ፭-፮:- ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳት ለምእመናን ሊቃውንትን ይሹሙላቸው። ቀሳውስትን፣ ዲያቆናትን፣ ንፍቅ ዲያቆናትን፣ አናጉንስጢሶችን ይሹሙላቸው።
√√√
ትእዛዝ ፰:- የጌታችንን የልደት በዓል በተወለደባት ቀን ታኅሣሥ ፳፱ን አክብሩ። እስመ ውእቱ ርእሰ ኵሉ በዓላት።
√√√
ትእዛዝ ፱:- የጌታችንን የጥምቀት በዓል ጥር 11 ቀን ያድርጉ። የምስጋና ቀን ናትና።
√√√
ትእዛዝ ፲:- በየዓመቱ ፵ ቀን ይጹሙ። የክርስቶስን ሕማሙን፣ ስቅለቱን፣ ሞቱንና ወደ መቃብር መውረዱን ያስቡ። በትንሣኤው ቀንም ፋሲካን ያድርጉ። ከሰንበታት በስተቀር ቅዳሜና ዓርብን ጨምሮ ፵ ቀን ጾመው ሲጨርሱ በዓል ያድርጉ። እሑድ ትንሣኤው ነው። ከእነዚህ ቀናት በኋላ እስከ ኃምሳኛው ቀን መጨረሻ ድረስ ጾም የለም።
√√√
ትእዛዝ ፲፩:- ከትንሣኤው በኋላ በ፵ኛው ቀን ጌታችን ወደ ሰማይ ያረገበትን በዓል አክብሩ።
√√√
ትእዛዝ ፲፪:- ከኦሪት ከነቢያት መጻሕፍት ሁሉ እና የሐዋርያትን ዜና በቤተክርስቲያን በታላቅ አትሮንስ ላይ ያንብቡ። ከዚያ በኋላም የመጻሕፍት ሁሉ ፍጻሜ ነውና ከወንጌል ያንብቡ። ሕዝቡም ሁሉ በእግሩ ቆሞ ይስማ። የሕይወትና የመድኃኒት የምሥራች ነውና።
√√√
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፪ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፪_
#ግጽው
ትእዛዝ ፲፫ ሕግና ሥርዓትን የማያውቅ ሰው በምእመናን ላይ አይሾም። በምእመናን ላይ ሊሾም የሚገባው በጠባዩ ቸር፣ ታጋሽ፣ በጉዞው ሁሉ ጥሩና ትሑት ይሁን። ይህን ካላደረገ ይሻር። ቃሉንና ትእዛዙንም አይቀበሉት። በአሠራሩ ታማኝ አይደለምና።

ትእዛዝ ፲፬:- ሐሰተኛን እና ሐሜተኛን ሰው ከሹመት ይከልክሉት።

ትእዛዝ ፲፭:- በኮከብ ቆጠራ የሚታመንና በጥንቆላ የሚያምን ሁሉ ከሹመት ይወገድ። ክርስቲያኖችን እግዚአብሔርን ከማያውቁት ጋር የሚያስተካክል ከክህነት ሥልጣን ይሻር።

ትእዛዝ ፲፯:- በዝሙትና በስስት የሚታወቅ እንዲሁም የዚህን ዓለም ጥቅም የሚፈልግ ቄስም ሆነ ዲያቆን ከሹመቱ ይሻር።

ትእዛዝ ፳:- የዚህን ዓለም ሥራ የሚሠራን ሰው በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ላይ እንዲያዝዝ ሹም አያድርጉት። ጸሎት የያዘ ቄስም ሆነ ዲያቆን ጸሎቱን አቋርጦ ወደሌላ ነገር አይሂድ። እንደዚህ የሚያደርግ ከሆነ ወደቀድሞ ቦታው መመለስ አይሆንለትም (አይገባውም)።

ትእዛዝ ፳፩:- ለቅዱሳን ሰማዕታት በሞቱበት ቀን መታሰቢያ ያድርጉላቸው።

ትእዛዝ ፳፩:- መዝሙረ ዳዊትን ቀንም ሌሊትም ይጸልዩት። መዝሙረ ዳዊት ተአምኖ ኃጣውእ፣ ጸሎት፣ ምስጋና አለበትና። ችግር፣ ሐዘንና፣ መከራ በአጋጠማቸው ጊዜ ከጥፋት ያመልጡ ዘንድ ይጸልዩ።

ትእዛዝ ፳፫:- በቤተመቅደስ ለማገልገል ከሕዝብ የተመረጡ ካህናት ሰባት ይሁኑ።

ትእዛዝ ፳፬:- ዐመፀኛውን ጻድቅ የሚያደርግ፣ ንጹሑን የሚያበሳጭ የተወገዘና ርጉም ይሁን። እንደዚህ የሚያደርገውን ከሹመቱ ይከልክሉት። ስለዐመፀኛነቱም ይመስክሩበት። ዐመፀኛ ከሆነ ጵጵስናው አያስፈራህ። (በእንተ ዐመፃሁ ወኢያፍርህከ ጵጵስናሁ)።

ትእዛዝ ፳፭:- በሰዎች ላይ የሚኩራራና በራሱ የሚታበይ ወደ ሹመት አይቅረብ። ከሌሎች ሰዎች እንደሚበልጥ እንደሚከብርና እንደሚሻል ራሱን የሚያይ፣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በንቀት ዓይን የሚመለከት በሹመት ላይ አይቀመጥ።

ትእዛዝ ፳፮:- በየአውራጃው ባሉ ቀሳውስት ላይ በመካከላቸው ሆኖ የሚያዛቸውና የሚገሥጻቸው ሊቀ ካህናት ይሹሙ።

ትእዛዝ ፳፯:- በጸሎት ጊዜ ንጉሥ በሰው ሁሉ ፊት ከምእመናን ጋር ይሁን። ለቁርባን ወደ መሠውያው ቦታ ይግባ። መቆሚያውም ከሊቃውንትና ከተሾሙ ካህናት ጋር በዚያ ይሁን።

ትእዛዝ ፴:- ቁርባንን በዕለቱ ያቀብሉት እንጂ ለነገ አያሳድሩ።

ሊቃነ ካህናቱ ኒቆዲሞስና ገማልኤል፣ ሐና፣ ቀያፋ፣ ሊቃነ ካህናት ሌሊት ወደክርስቶስ ይመጡ ነበር። በክርስቶስም ያምኑ ነበር። ነገር ግን አይሁድን ፈርተው ይህንን አልገለጹም። ከክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ሁላቸውም አምነዋል።

የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እርስ በእርሳቸው ይተባበራሉ።

ሐዋርያት ከጠንቋዮች ጋር ይጋደሉ ነበር። ስለ ሃይማኖታቸው ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ እኛም የፈጠረንን አስቆጥተነዋልና ይህች የደረሰችብን ችግር ታስታርቀናለች ይሉ ነበር። ከእነርሱ መካከል ብዙ ጊዜ ንብረቱ የተዘረፈበት አለ፣ ከገንዘቡ ከልጆቹና ከቤቱ የራቀም አለ፣ የሰቀሉትም አለ። እስኪሞቱ ድረስ በፈቃዳቸው ይታገሡ ነበር።

ምእመናን ለአማልክት የተሠዋንና በክት የሆነውን ከመብላት፣ ደምን ከመጠጣት፣ ለባዕድ አምላክም ከመሳል እንዲታቀቡ ያዝዟቸው ነበር።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፫
መ/ር በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፫____
#ትእዛዝ #ሲኖዶስ
ትእዛዝ ፩:- ኤጲስ ቆጶስ ሁለት ወይም ሦስት ኤጲስ ቆጶሳት በተገኙበት ይሾም። ቄስ ዲያቆንና የቀሩት ሹማምንት በአንድ ኤጲስ ቆጶስ ሥልጣን ብቻ ይሾሙ።

ትእዛዝ ፪:- ጌታችን ካዘዘው (ስንዴ፣ የወይን ፍሬ፣ መብራት፣ ዘይት፣ ንጹሕ ዕጣን) ውጭ ቁርባን ያሳረገ ይሻር።

ትእዛዝ ፫:- ካህን በአገልግሎት ምክንያት ሚስቱን አይፍታ። ከፈቱ ይለዩ። ካልመለሷት ግን ይሻሩ።

ትእዛዝ ፬:- ካህናት ቀንና ሌሊቱ እኩል ከመሆኑ በፊት ከአይሁድ ጋር ቅድስት ፋሲካ እንድትውል ካደረጉ ይሻሩ።

ትእዛዝ ፭:- ኤጲስ ቆጶስ፣ ቄስና ዲያቆን ከዚህ ዓለም ተግባር ውስጥ አይግቡ። ገብተው ከተገኙ ግን ይለዩ።

ትእዛዝ ፮:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ከካህናት አንዱ ምክንያቱን ሳይናገር በቅዳሴ ግን ቁርባን ባይቀበል የማይገባው ሆኖ ከተገኘ ይቅር ይበሉት። ምክንያቱን ካልተናገረ ግን ይባረር። በአሳረገው መሥዋዕት ላይም በንጽሕና እንዳላሳረገው ሆኖ ለሕዝብ እንቅፋት ሆኗልና።

ትእዛዝ ፯:- ወደ ቤተክርስቲያን የሚገባ አማኝ ሁሉ መጻሕፍትንም የሚሰማ ነገር ግን ጸሎት እስከሚያደርጉ ድረስ የማይቆም ቁርባንም የማይቀበል ከሆነ በላዩ ላይ አይጸልዩለት። ሊባረርም ይገባዋል። በቤተክርስቲያን ክርክርንና ብጥብጥን ፈጥሯልና።

ትእዛዝ ፰:- ከቤተክርስቲያን ከተባረረ ሰው ጋር አይጸልዩ።

ትእዛዝ ፲:- ካህን ከተባረረ ካህን ጋር ቢጸልይ እርሱም ይባረር።

ትእዛዝ ፲፩:- ኤጲስ ቆጶስ የሹመት ቦታውን ትቶ በሌላ ሀገረ ስብከት ሊሾም አይገባም።

ትእዛዝ ፲፪:- ያለ ኤጲስ ቆጶሱ ሥልጣን የሥራ ቦታውን ቢተውና ወደሌላ የሥራ ቦታ ቢሄድ እንዳያገለግል እኛ እናዛለን። በይበልጥም ኤጲስ ቆጶስ ወደቦታው እንዲመለስ ቢልክበትና ባይሰማው ከሹመቱ ይባረር። ባለበት ቦታ እንደ ሕዝባዊ ሆኖ ይቁረብ።

ትእዛዝ ፲፫:- ወደ ተውኔት ቤት የምትሔደውን ያገባ ክህነት ሊሾም አይገባውም።

ትእዛዝ ፲፬:- ዋስ የሚሆን ካህን ይሻር።

ትእዛዝ ፲፭:- በራሱ ፈቃድ ራሱን የሰለበ ክህነት አይሾም።

ትእዛዝ ፲፮:- በዝሙት፣ በሐሰት መማል፣ በመስረቅ የሚገኝ ካህን ይሻር።

ትእዛዝ ፲፯:- ክህነት ወደሚገቡበት ጊዜ አናጉንስጢስና መዘምራን ማግባት ቢፈልጉ ያግቡ። ከተሾሙ በኋላ ግብ ማግባት አይገባቸውም።

ትእዛዝ ፲፰:- ሰዎች ይፈሩት ዘንድ የሚደባደብ ካህን እንዲሻር እናዛለን።

ትእዛዝ ፲፱:- በታወቀ ኃጢአት ምክንያት በትክክል የተሻረ ኤጲስ ቆጶስም ቢሆን ቄስም ቢሆን ዲያቆንም ቢሆን ከተደፋፈረና ሥልጣን ባለው ጊዜ ይሠራውን የነበረውን መሥራት ከጀመረ ፈጽሞ ከቤተክርስቲያን ይራቅ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፬ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
__የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፬__
#ትእዛዝ #ሲኖዶስ
ትእዛዝ ፳:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን መማለጃ በመስጠት የሹመት መዓርግ ቢይዝ ይሻር። የሾመውም ይሻር። ከክህነት ሥርዓትም እስከ መጨረሻው ይባረር።

ትእዛዝ ፳፩:- ኤጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያንን በዚህ ዓለም የአገዛዝ ሥርዓት ለመግዛት የሚፈልግን ሰው ከረዳ ይሻር።

ትእዛዝ ፳፪:- ቄስ ኤጲስ ቆጶስን ቢንቅ ይለይ።

ትእዛዝ ፳፫:- ኤጲስ ቆጶስ ያባረረውን ቄስ ወይም ዲያቆን ራሱ ካልፈቀደ በስተቀር ሌላ ኤጲስ ቆጶስ እንዲመለስ አያድርገው።

ትእዛዝ ፳፬:- ሊቀ ጳጳሳት የሁሉንም ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶሳት ያውቅ ዘንድ ይገባል።

ትእዛዝ ፳፭:- ኤጲስ ቆጶስ የሀገረ ስብከቱ ኤጲስ ቆጶስ ካልፈቀደለት የእርሱ ባልሆነ ሀገረ ስብከት ላይ ለመሾም አይደፋፈር። ተደፋፍሮ የተገኘ ካለ እርሱም የሾማቸውም ይሻሩ።

ትእዛዝ ፳፯:- የኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ ይደረግ። በቤተክርስቲያን ላይ ስለአለ ስሕተትና እንቅፋት ስለሚሆኑ ነገሮችም ይተርጕሙ። የመጀመሪያው ጉባኤ በበዓለ ኃምሳ መካከል ይሁን። ሁለተኛው ጉባኤ ጥቅምት 12 ይሁን።

ትእዛዝ ፳፰:- ኤጲስ ቆጶስ የእግዚአብሔርን ገንዘብ ለዘመዱ ልጆች መስጠት የለበትም።

ትእዛዝ ፳፱:- ከቀሳውስት ወይም ከዲያቆናት ማንም ኤጲስ ቆጶሱን ሳያማክር ምንም አያድርግ።

ትእዛዝ ፴፩ [የጦር ሠራዊት]:- የንጉሥ ሠራዊትም ከጠላት ጋር ጦርነት የሚያደርጉት በራሳቸው ምግብ አይደለም።

ትእዛዝ ፴፪:- ወደ ጭፈራ ቤት የሚሔድና የሚዞር ስካርም የሚያበዛ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ይተው። አልተውም ካለ ግን ይባረር። ሕዝባውያንም ቢሆኑ እንደዚሁ ይሁኑ።

ትእዛዝ ፴፫:- ወደ ከኃድያን ጥምቀት ወይም ወደ ቁርባናቸው የሚሔድ ካህን ይሻር።

ትእዛዝ ፴፬:- ሥጋ መብላት፣ ጋብቻ፣ ወይን መጠጣት እንደ ርኩስ የሚቆጥር ቢኖር ይህን ሐሳቡን ይተው ዘንድ ይንገሩት። ካልተወ ግን ይሻር። ሕዝባዊ ቢሆንም እንዲሁ ይደረግ።

ትእዛዝ ፴፭:- ከኃጢአት ንስሓ የሚገቡትን አልቀበልም የሚል ካህን ቢኖር ይሻር።

ትእዛዝ ፴፯:- ከካህናት መካከል በገበያ የሚበላ ወይም የሚጠጣ ቢገኝ ከካህናት አንድነት ይለይ። ከካህናት መካከል አንዱ ኤጲስ ቆጶስን ቢሳደብ ይሻር። በሕዝብ ላይ በተሾመ ሰው ላይ መጥፎ ቃል አትናገር ይላልና። ቄስን ዲያቆንን የሚሳደብም ይባረር።

ትእዛዝ ፴፰:- ካህናትን ወይም ሕዝብን የሚንቅና የእግዚአብሔርን መልእክት የማያስተምር ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ይባረር። በንቀቱ ቢቀጥልበት ይሻር።

ትእዛዝ ፴፱:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ከካህናት የተቸገረን አይቶ ቸል ቸል ካለ የሚፈልገውን ነገርም ባይሰጠው ይለይ። በዚሁ በቸልታው ከቀጠለም ወንድሙን እንደገደለ ይቆጠራልና ይሻር።

ትእዛዝ ፵:- ከኃድያን በውሸት የጻፉትን መጽሐፍ ያሳየ ሕዝብንና ካህናትንም ለማጥመድ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት ቆጥሮ ወደ ቤተክርስቲያን ያስገባ ሰው ቢኖር ይሻር።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፭ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
__የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፭__
#ትእዛዝ #ሲኖዶስ
ትእዛዝ ፵፪:- ከካህናት መካከል ከኃድያንን ከመፍራት የተነሣ ቢክድ የካደው የክርስቶስን ስም ከሆነ ይባረር። የካደው ክህነትን ከሆነ ይሻር። ንስሓ ከገባ ይቀበሉት እንደ ሕዝብ ሆኖም ይግባ።

ትእዛዝ ፵፫:- ከካህናት አንዱ ደም ያለው ወይም ያልታረደ ወይም አውሬ የነከሰው ወይም በክት ከበላ ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይለይ።

ትእዛዝ ፵፬:- ከቀዳም ስዑር በስተቀር በሰንበትና በዕለተ እሑድ ከካህናት መካከል አንዱ ሲጾም ቢገኝ ይሻር።

ትእዛዝ ፵፭:- ከካህናት መካከል በከኃድያን ቦታ ይጸልይ ዘንድ ቢገባ ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይባረር።

ትእዛዝ ፵፮:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ሁለት ጊዜ ተሹሞ ቢገኝ እርሱም የሾመውም ይሻር።

ትእዛዝ ፵፯:- ደዌ ሕመም ካልከለከለው በስተቀር ጾመ አርብዓን፣ ረቡዕና ዓርብን የማይጾም ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ወይም አናጉንስጢስ ወይም መዘምር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነ ደግሞ ይባረር።

ትእዛዝ ፵፰:- ከካህናት አንዱ ከአይሁድ ጋር ቢጾም ወይም ፋሲካን ከእነርሱ ጋር ቢያደርግ ወይም ለበዓላቸው ስጦታ ቂጣ ቢቀበል ወይም ይህን የመሰለ ቢያደርግ ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነ ይባረር። ሕዝባዊ ሆኖ ዘይትና መብራት ወደ አይሁድ ምኵራብና ወደ አሕዛብ ምኵራብ ቢወስድ ከምእመንነቱ ይሻር።

ትእዛዝ ፵፱:- የተሾመ ካህን ከቤተክርስቲያን ሠም ወይም ቅባት ቢሰርቅ ይባረር። የሰረቀውንም አምስት እጥፍ አድርጎ ይክፈል።

ትእዛዝ ፶፩:- በኤጲስ ቆጶስ ላይ የከኃድያንን ምስክርነትና የአንድን ኤጲስ ቆጶስ ምስክርነት አይስሙበት። ኤጲስ ቆጶስነትን ይዋረሱ ዘንድ ትክክል አይደለም። ኤጲስ ቆጶስ የቤተክርስቲያንን ሀብት ለፈለገው ሰው አይስጥ። አንድ ዓይኑ የታወረ ወይም አንድ እግሩ አንካሳ የሆነ ሰው ኤጲስ ቆጶስነት የሚገባው ቢሆን ይሾም። ነውረ ነፍስ እንጂ ነውረ ሥጋ አያረክስምና። መስማት የተሳነውና ዐይነ ስውር ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ አይሾም።

ትእዛዝ ፶፪:- ጋኔን ያደረበት ካህን ሆኖ አይሾም። ከምእመናን ጋርም አብሮ አይጸልይ።ጌቶቹ እንዳያዝኑ ነጻ ያልወጣ ሰው ካህን ሆኖ ይሾም ዘንድ አናዝም።

ትእዛዝ ፶፫:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ዓለማዊ ሹመትንና ክህነትን ሁለቱን ለመሥራት ወታደር ሆኖ ማገልገል ቢፈልግ ይሻር። [መንግሥትነት] ንጉሥን ወይም መኮንንን የሚያቃልል ይበቀሉት። ካህን ከሆነ ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነ ደግሞ ይባረር።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፮ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/23 22:21:08
Back to Top
HTML Embed Code: