Telegram Web Link
Audio
በሰማይ ደመና ይመጣል
                         
Size 27MB
Length 1:17:39

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
_ወሊድን በተመለከተ__
ልጅን መውለድ ብዙ ተባዙ ያለውን አምላካዊ ቃል መፈጸም ስለሆነ ትልቅ ክብር ነው። ወላድ እናቶቻችንም ክቡራት ናቸው። ባለማወቅ (ላለዝበው ብየ ነው እንጂ በድንቁርና ልል ነበር) የወለደች ሴት እስላም ናት፣ ርኵስ ናት የሚሉ ሰዎች ከእውቀት ጋር የተጣሉ ሰዎች ናቸው። ወንድ ከወለደች በኋላ ለ40 ቀን ቤተክርስቲያን አትገባም። የማትገባበት ምክንያት ግን እስከዚያ ድረስ ደም ስለሚፈሳት ነው። ደም የሚፈሰው ሰው ደግሞ ቤተክርስቲያን አይገባም። ይህ ለወላድ ሴት ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ወንዱም ቢሆን እንቅፋት መትቶት አካሉ ቢደማ ቤተክርስቲያን አይገባም። አፍንጫው ቢነስር ብቻ ከመድማት ወገን በአንዱ ቢደማ ቤተክርስቲያን አይገባም። ርስሐት (ዝንየት) ካገኘውም 24 ሰዓት ጠብቆ ይገባል እንጂ ከዚያ በፊት እንዲገባ ሥርዐት አልተሠራም። ሴት ልጅ የወለደች እናትም እስከ 80 ቀን ቤተክርስቲያን አትገባም። ይኽውም ደም ስለሚፈሳት ነው። በወር አበባ ያለች ሴትም ቤተክርስቲያን አትገባም ይኽም ደም ስለሚፈሳት ነው። ቤተክርስቲያን መፍሰስ ያለበት የክርስቶስ ደም ብቻ ነው። የፍጡር ደም መፍሰስ የለበትም። ይህ ሥርዐት የተሠራውም ለቤተክርስቲያን ክብር ተብሎ እንጂ የወር አበባ፣ በወሊድ ጊዜ የሚፈሰው ደም ርኵሰት ሆኖ አይደለም። ክቡራት ወላድ እናቶቻችንን እንደ ርኵስ ማሰብ የርኵስ ሰዎች እሳቤ ነው። እናቶችን ልጅ ስለወለዱ እናከብራቸዋለን እንጂ ርኵስ ናቸው አንልም። የወለዱ እናቶችን በወለዱ ቀን በሌላ ቀንም ሄዶ "እንኳን ማርያም ማረችሽ" ማለት የክርስቲያን ሥራ ነው። ከቤተክርስቲያን መግባት፣ ሥጋውን ደሙን ከመቀበል አይከለክልም።


ፍትሐ ነገሥት አንቀጸ ቀሳውስት ላይ ቁጥር ፪፻፴፯ (237) ላይ፣ በደስ ፰ (8)፣ አቡሊዲስ በጻፈው መጽሐፍ በስምንተኛው አንቀጽ ቄስ ሚስቱ ብትወልድ ከአገልግሎት አይከልከል ይላል። ቀሲስ ሶበ ወለደት ብእሲቱ ኢይትከላእ እንዲል። አንዳንድ ቦታ ላይ ገጠር የወለደችን ሴት በአሥረኛው ቀን ጸበል የሚረጩ ቄሶች አሉ። ጸበል በረከት ያለው ስለሆነ መረጨቷ ጉዳት የለውም። ነገር ግን ርኵሰቷን ስለሚያስለቅቅ ተብሎ ከሆነ የሚረጨው ነውር ነው። መጀመሪያም ልጅ በመውለዷ ርኵስት አልሆነችምና። ይሄ ከትምህርቷ ገፋ ያለማድረግ ችግር ነው። ጸበል ተረጨችም አልተረጨችም ምንም ዓይነት ነውር የለባትም። ያ ብቻ ሳይሆን በማየ ገቦ (ሕጻኑ በተጠመቀበት ማይ) እናቲቱንና ክርስትና የሚያነሱ ሰዎችን መርጨት ትልቅ ውንብድና ነው። ማየ ገቦ ልጅነት የሚያሰጥ ስለሆነ ሕጻኑ ብቻ ይጠመቅበታል እንጂ ለሌላ ሰው አይረጭም።

ስለ አዋላጆች (መወልዳት) በፍትሐ ነገሥት ተነግሯል። ይኽውም ሴት ያዋለዱ አዋላጆች እስከ ፵ ቀን ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ፣ ወንድ ያዋለዱ አዋላጆች ደግሞ እስከ ፳ ቀን እንዳይገቡ ሥርዓት ተሠርቷል። በዘመናችን ደግሞ አዋላጅ ነርሶች (Midwives) አሉ። ሥራቸው ማዋለድ ነው። ለእነርሱ ዘለዓለም ቤተክርስቲያን አይግቡ የሚል ትምህርት የለንም። ሥርዓቱ ሲሠራ በነበረው ዘመን የነበሩ አዋላጆች እና አሁን ያሉ አዋላጆች ሚናቸው የተለያየ ስለሆነ ለአሁን ዘመን አዋላጆች የሚመጥን ሥርዓት እንዲሠራልን በዚሁ አጋጣሚ ለቅዱስ ሲኖዶስ የምናሳስበው ይሆናል ማለት ነው። ምክንያቱም የአሁን አዋላጆች ያለምንም ደም ንክኪ ሊያዋልዱ የሚችሉበት መንገድ ስለሚኖርና ጥንቃቄያቸው ከቀድሞው ከፍ ያለ ስለሆነ ነው። ሕክምናን በተመለከተ የቀዶ ሕክምና ሐኪሞችን ሁሉ ያካተተ ሥርዓት ቢሠራ መልካም ነው።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለረጅም ዘመናት በአገራችን ኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት ጸንቶና ልዩነቶች ተወግደው እንዲኖሩ አርአያና ምሳሌ የሆነ ተቋማዊ አደረጃጀት ፈጥራና በአንድ መዋቅራዊ አስተዳደር ጸንታ መኖሯ የሚታወቅ ነው፡፡
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በአገራችን እየተከሰቱ ባሉ አለመግባባቶች መነሻነት ከአገራችንም አልፎ ጸንቶ በቆየው የቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ መዋቅር ላይ እየተከሰቱ ካሉ ተግዳሮቶች መካከል አንዱ በፌዴራል መንግስትና በትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መካከል በተፈጠረው የእርስ በእርስ ጦርነት ነው፡፡
በዚሁ ምክንያት በቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ መዋቅርና በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት መካከል አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ግንኙነት መቋረጡን ተከትሎና በጦርነቱ ምክንያት ሁሉም የባንክ ተቋማት ሥራቸውን በማቆማቸው በየጊዜው እንደሌሎች አህጉረ ስብከት ለትግራይ አህጉረ ስብከት ይላክ የነበረው በጀት መላክ አልተቻለም፡፡ ይህም በጦርነቱ ከደረሰው ጉዳት በላይ በመዋቅሮቻችን ሥር ተመድበው ይሰሩ የነበሩ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶችና አገልጋይ ሠራተኞች ላይ የበጀት እጥረት አጋጥሞ ቆይቷል፡፡
ምንም እንኳን በባንክ መዘጋት ለአገልጋይ ሠራተኞች በጀት መላክ ባይቻልም የደመወዝ መክፈያ የባንክ ሂሣባቸው በአዲስ አበባ ከፍተው ሲገለገሉ የቆዩት አባቶች ማለትም፡
- ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ የመቐለ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣
- ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የማዕከላዊ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስና
- ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የሽሬ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በጦርነቱ ወቅትም ሆነ ከጦርነቱ በኋላ እስከአሁን ድረስ ያለምንም መቆራረጥ ወርኃዊ ደመወዛቸው ወደ ባንክ ሂሣባቸው ሲገባ የቆየና እየገባ ይገኛል፡፡
- የብፁዕ አቡነ መርሐክርስቶስ የአዲግራት ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የባንክ ሂሣብ ግን በዚያው በሚኖሩበት አካባቢ የተከፈተ በመሆኑና በአካባቢው የባንክ አገልግሎት በመቆሙ በጀቱን ማድረስ ያልተቻለ ነው፡፡ በዚህም የዋናው መ/ቤት በእጅጉ ያዘነና በአገሪቱ የተከሰተው ጦርነት ሰላማዊ እልባት አግኝቶ መንግስታዊ መዋቅራዊ ግንኙነቱ እንደተጀመረ የተከሰቱ ችግሮችንና የደረሰውን የጉዳት መጠንና ማዕከል ያደረገ ውይይት በማድረግ ተገቢና ችግር ፈቺ በጀት ለመመደብ ይቻል ዘንድ ለሁሉም የትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቃነጳጳሳት በቁጥር 197/897/2015 በ1/6/2015 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ ቤተ ክርስቲያናችን ጥሪ አስተላልፋለች፡፡
ቢሆንም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር ፈቺ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ሲገባ በክልሉ የተከሰተውን ችግር ቤተ ክርስቲያናችን እንዳላዘነችና የጉዳቱ ቀጥተኛ ተጠቂ መሆኗን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ምላሽ አዘል መግለጫ እንደደረሰን ጉዳዩን በጽሞናና በትዕግስት በማየት በጥናት ላይ የተመሰረተ ችግሩን ሊፈታ የሚችል የአቀራራቢ ሽማግሌ ልዑካንን ለመመደብ በዝግጅት ላይ እያለን መጋቢት 13 ቀን 2015ዓ.ም. የቤተ ክርስቲያናችንን ጸንቶ የቆየ ተቋማዊ አንድነትና ነባር መዋቅራዊ አደረጃጀትን በሚንድ መልኩ “መንበረ ሰላማ የትግራይ ጠቅላይ ቤተ ክህነት” ጽ/ቤት የሚል አዲስ ሕገወጥ ክልላዊ መዋቅር በመፍጠርና ያለምንም በቂ ማስረጃ ዋናው መ/ቤት በጀት እንደከለከለ፣ የሠራተኞችን ደመወዝ እንዳገደ በአጠቃላይ በክልሉ በሚገኙ አህጉረ ስብከት ላይ አቅዶ ችግር እንደፈጠረ የሚያስመስልና ሕገ-ቤተ ክርስቲያኑን የጣሰ መግለጫ ከመሰጠቱም በላይ በሕገ-ቤተ ክርስቲያኑ ላይ በግልጽ እንደተደነገገው በሁሉም አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ሊመደቡ የሚችሉት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔና በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ መሆኑ እየታወቀ ሆን ተብሎ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በሥራ ላይ እያሉና ሲኖዶሳዊ አንድነቱ ጸንቶ ባለበት ሀኔታ ላይ ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ውጭና ያለቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ የቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ አሠራርን በጣሰ ሁኔታ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ሊቃነ ጳጳሳት ተመድበው በሚሠሩባቸው የውጭ ዓለማት አህጉረ ስብከት ላይ ሊቃነ ጳጳሳት ከቀኖና ውጭ ራሳቸውን በራሳቸው በመመደብ መግለጫ መስጠታቸውን በመገናኛ ብዙኃን በመስማታችን በእጅጉ አዝነናል፡፡
በመሆኑም የእምነትና የታሪክ መሠረት በሆነው በታላቁ የትግራይ አህጉረ ስብከት እንዲህ ዓይነት መዋቅርን የሚንድና ቤተ ክርስቲያናችንን ለአደጋ የሚያጋልጥ በዓለም መላውን የእምነቱን ተከታዮች የሚያሳዝን አድራጐት ለታሪካዊ ለትግራይ ሕዝብና ሊቃውንት የማይመጥን አድራጎት ከመሆኑም በላይ ለቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራዊ አንድነትና መስፋፋት ተጋድሎ የፈጸሙ የቀደሙ ቅዱሳን አባቶቻችንን ያሳዘነ መሆኑን ለተከበረው የትግራይ ሊቃውንትና ሕዝብ የተሰወረ እንዳልሆነ በጽኑ እናምናለን፡፡
በመሆኑም ከላይ በዝርዝር ለመግለጽ እንደሞከርነው ፡-
1. በትግራይ ክልል የሚገኙ አህጉረ ስብከት በጀት እንዳይላክ በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነ አንድም ውሳኔ የሌለና በተፈጠረው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት የባንክ አገልግሎት በመቆሙ የተከሰተ የግንኙነት መቋረጥ መሆኑ ታውቆ በጀቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቆመበት ጊዜ ጀምሮ ከአህጉረ ስብከት ጋር በመነጋገር ለመላክ ዝግጁ መሆናችንን እናሳውቃለን፡፡

2. በክልሉ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የደረሰውን ጉዳትና ችግር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተሰማትን ሐዘንና በችግሩም ወቅት ለአህጉረ ስብከቱ በበጀት ተደራሽ ባለመሆናችን ያስከተለው ችግር ያሳዘነን መሆኑን በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ ገልጸን እያለንና የተከሰተው ጦርነት እንዲቆም በጸሎትና በምሕላ ስንማጸን መቆየታችን ወደጐን ተትቶና ተዘንግቶ ቤተ ክርስቲያናችን የጦርነቱ ደጋፊ በሚያስመስል መልኩ የተሰጠው መግለጫ ተቀባይነት የሌለውና ቤተ ክርስቲያናችንንም የማይገልጽ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

3. እናት ቤተ ክርስቲያን በኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በዳጩ ሆሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሕገወጥ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት ፈተና ለመፍታትና የቤተ ክርስቲያናችንን ሲኖዶሳዊ አንድነትን ለማጽናት በከፍተኛ ኃላፊነት እየሠራች ባለበት ሁኔታ ለዚህ የቤተ ክርስቲያናችን ተልዕኮና ተቅማዊ አንድነት መጽናት በጸሎትም በሐሳብም ልንታገዝ ሲገባ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ አበው የእምነትና የታሪክ መሠረት በሆነው የትግራይ ሊቃውንት እንዲህ ዓይነት ድርጊት መከሰቱ ለአገሩም ሆነ ለሕዝቡ የሚመጥን አድራጐት ባለመሆኑ በአስቸኳይ እንዲቆም እናሳስባለን፡፡
4. በክልሉ ያለው አጠቃላይ መዋቅራዊ ችግሮችን በሚመለከትና አጠቃላይ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተከሰቱትን ችግሮች ተወያይቶ ለመወሰን መጋቢት 21 ቀን 2015ዓ.ም. በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 3 የሕግ ድንጋጌ መሠረት የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ የተጠራ ስለሆነ በክልሉ በቅዱስ ሲኖዶስ ተመድባችሁ በመሥራት ላይ የምትገኙ ሊቃነጳጳሳት በጥሪው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው ላይ እንድትገኙና ክልላዊ ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ውይይት ላይ በመሳተፍ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከአደራ ጭምር ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡
5. የተከበራችሁ በትግራይ ክልል የምትገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እናት ቤተ ክርስቲያን በአባቶቻችሁ ሐዋርያዊ ተልዕኮ ጸንታ እስከአሁን መቆየቷን ለእናንተ መንገር ለቀባሪው ማርዳት ነው፡፡ በመሆኑም በአገራችን በተከሰተው ፖለቲካዊ ችግር ዘመናትን በጽናት የተሻገረችውን እናት ቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አንድነቷ መፍረስ ሲኖዶሳዊ ልዕልናዋ መጣስ የሌለበት መሆኑን በጽናት እንደምታምኑ እምነታችን የጸና ነው፡፡
ስለሆነም በሚያልፍ ችግር የማያልፍ ታሪክ ጥለን ማለፍ ስለሌለብን እንደቀደሙ አባቶቻችሁ አበው ሊቃውንት ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ አንድነት አስፈላጊውን ዋጋ ሁሉ በመክፈል በጽናት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ በቀደሙ አባቶቻችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

6. የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስቱም በክልሉ ተፈጥሮ የቆየው ችግር በሰላማዊ መንገድ በውይይት በመፈታቱ እናት ቤተ ክርስቲያን የተሰማትን ደስታ እየገለጸች አስቀድሞ ችግሩ ከመከሰቱ በፊት አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችን የተመራው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለቀረበው የሰላም ጥሪ እናት ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛውን ሚና እንደተጫወተች እናስታውሳለን፡፡
በመሆኑም በተከሰተው ችግር የተፈጠሩ ጉድለቶች ካለ ጉድለቶችን ለማረምና ችግሮቹን ለመፍታት ቤተ ክርስቲያናችን ያላትን የጸና አቋም እየገለጽን በክልሉ የተከሰተውን ተቋማዊ አንድነትን የሚጥስና ቀኖና የጣሰ አደረጃጀት እንዲቆም የበኩሉን ሚና በመጫወት ለቤተ ክርስቲያናችን ተቋማዊ አንድነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በመጨረሻም መላው በትግራይ ክልል የምትገኙ ምእመናንና ምእመናት በአሁኑ ወቅት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተከሰተው ፈተና እንዲወገድና አንድነቷ ጸንቶ እንዲኖር በጸሎትና በምሕላ ጸንታችሁ ስታግዙ እንደቆያችሁት ሁሉ አሁንም በክልሉ የተከሰተውን ቀኖናዊ ጥሰትና ሕገወጥ አደረጃጀት ቆሞ እናት ቤተ ክርስቲያን በአንድነቷ ጸንታ እንድትኖር እንደአሁን ቀደሙ በጸሎትና በምሕላ ጸንታችሁ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ እየጠየቅን የኢፌዴሪ መንግስትም እንደአሁን ቀደሙ በሲኖዶሳዊ አንድነት ላይና በቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራዊ አደረጃጀት ላይ የተጋረጠው ችግር ልዩ ትኩረት በመስተጠና የበኩሉን ሚና በመጫወት የቤተ ክርስቲያናችንን ሲኖዶሳዊ አንድንትና ነባር መዋቅራዊ አደረጃጀት ጸንቶ እንዲኖር አገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
መጋቤት 15 ቀን 2015 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የሕገ ወጥ ቡድኑን የሹመት ይጽደቅልን ጥያቄን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መቼውንም የማትቀበለው ጥያቄ ነው
••••
የመንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
••••
በዛሬ ዕለት የተካሔደውን በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በሕገ ወጥ መንገድ በተሾሙ የቀድሞ አባቶች መካከል የነበረውን ውይይት አስመልክተው መግለጫው የሰጡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊ ሊቀ ሥዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ ሲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ከመጋቢት ፮/፳፻፲፭ ዓ/ም ጀምሮ በሕገ ወጥ የተሾሙ ግለሰቦችን አስመልክቶ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ለመቀበል ያከናወነውን ተግባራት አብራርተዋል።
••••
በዚህም ቅዱስ ሲኖደስ በቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ከሕገ ወጥ የተሾሙ ግለሰቦች በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ጽ/ቤት የይቅርታ መመልከቻ እንዲያስገቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ ያስተላላፈ ቢሆንም በይቅርታ ደብዳቤ አስገብተው ከተመለሱት ከአንዱ " አባ " ኃይለ ኢየሱስ ከተባሉት ውጭ ሌሎች ግን በይቅርታ ከመመለሰ ይልቅ ለውይይትና ሕገ ወጥ ድርጊቱም እንዲጸድቅላቸው መጠየቃቸውን ተገልጿል።
••••
የመምሪያው ኃላፊ ሊቀ ሥዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ ቀጥለው ቤተ ክርስቲያን የይቅርታ ቤት የሰላም ዓደባባይ የንስሓ ሰገነት በመሆኗ ለፍቅር ረጅም ርቀት በመጓዝ ግለሰቦቹ ጋር በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ እንዲሁም በሌሎች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አማካኝነት መወያያቷን አስታውሰዋል። ከዚህም አልፎ ቤተ ክርስቲያን የሀገር ሰላም የኢትዮጵያውያን የደኅንነት ኑሮ በእጅጉ ስለሚያሳስባት በብዙ ርቀት ለይቅርታ በሯን ከፍታ ስትጠባበቅ እንደነበረችም አክለው ገልጸዋል።
••••
ይሁን እንጂ በዛሬው ዕለት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የመጡት ሁሉንም እንወክላለን ያሉት 6 ግለሰቦች ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና ከብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ ጋር የተወያዩ ሲሆን በውይይቱ ግን የተዘረጋው የቤተ ክርስቲያን የፍቅርና ይቅርታ እጅ በግለሰቦቹ ግን እንደመልካም አልታየም። ከዚህ ይልቅ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ከተደረሱ 10 የስምምነት ነጥቦች መካከል በተራ ቁጥር 6 የሚገኘው ውሳኔ "በሕገ ወጥ መንገድ የተሾሙት "አባቶች" ወደ ቀደመ አገልግሎታቸው ይመለሳሉ" የሚል ቢሆንም ግለሰቦቹ ግን በመርሕ ደረጃ ስምምነቱን እንቀበለዋለን በአፈጻጸም ደረጃ ግን ቅዱስ ሲኖዶስ ሹመታችንን ያጽድቅልን" የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን የመምሪያው የሓላፊ ገልጸዋል።
••••
ስለሆነም ይላሉ የመምሪያው ሓላፊ ቤተ ክርስቲያን እስካሁን የሄደችበት የይቅርታ መንገድ እጅግ የሚያስመሰግን ሲሆን ከዚህ በኋላ ሕገ ወጦቹን በተመለከተ ቤተ ክርስቲያን የሚከተለውን ውሳኔ መወሰኗን አስታውቀዋል።
፩.በየትኛውም መንገድ የጋራ ውይይት አይኖርም
፪.ለይቅርታ የሚመጡ ከሆነ በቡድን ተሰባስቦ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ እንዲሆን
፫.የይቅርታ ማመልከቻውን እያንዳንዳቸው ለመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
••••
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዚህና በሌሎች መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ መጋቢት ፳፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም (21/07/2015 ) ምልዓተ ጉባኤ መጠራቱ የሚታወስ ነው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡

ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡

ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፡፡ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
ነጻ የምንሆነው መቼ ነው?
                         
Size 20MB
Length 57:29

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ሰበር_ዜና

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል።

በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን በይቅርታ የተመለሱት በቁጥር 20ዎቹ መነኮሳትም ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው የክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ ሆኖ በምንኩስና ስማቸው እንዲጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

#EOTCTV

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በመግለጫው አሳወቀ።

ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል።

በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን በይቅርታ የተመለሱት በቁጥር 20ዎቹ መነኮሳትም ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው የክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ ሆኖ በምንኩስና ስማቸው እንዲጠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"ጾምህና ምጽዋትህ ሁለት ዋጋ አላቸው፡፡ ከሰው ክብርን ሽተህ የምትጾም ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ እንድትበረታ ደንቁርናህም እጅግ ጽኑ እንዲሆን እወቅ፡፡ ነገር ግን እጆችህን ለተቸገረ ሰው የምትዘረጋ ሕሊናህን ግን ወደ አምላክ የምታነሣ ከሆነ፣ እንዲሁም ስትጾም ጾምህን በእግዚአብሔር ፊት ያደረግህ እንደሆነ ከፈጣሪህ ዘንድ መልካምን ዋጋ ትቀበላለህ፡፡ ይህ ኃይለ ቃል “ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡” (ማቴ.6፥21) ብሎ ጌታችን ካስተማረው ትምህርት ጋር አንድ ዓይነት ትርጉም ያለው ነው፡፡

ጾምና ምጽዋታችን በከንቱ ፈቃዳችን ምክንያት ለኃጢአት አሳልፎ እንዳይሰጠንና በደላችንንም እጥፍ ድርብ እንዳያደርግብን አምላካችን ይህን ማስተዋል ዘወትር ይሰጠን ዘንድ በዚህ የጦም ወቅት እንለምነው፡፡

ለወደደንና በእኛ ጥቂት ድካም ዘለዓለማዊ ዋጋን ለሚሰጠን ለእርሱ ምስጋና ይሁን ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

#ቅዱስ_ኤፍሬም
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ቤተሰብና_ምጽዋት

ኦርቶዶክሳውያን ባልና ሚስት ለጸሎት የሚኾን ቤት ከማዘጋጀት በተጨማሪ፥ ምጽዋት ከመስጠት አንጻርም ሊበረቱ ይገባቸዋል፡፡ ቢቻል ቢቻል ድኾችን በየጊዜው የሚመግቡባት አንዲት ቤት ብትኖራቸው መልካም ነው፡፡ ይህቺን ቤትም “የክርስቶስ በዓት” ብለው ሊሰይሟት ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም በድኾቹ አድሮ በዚያች ቤት ውስጥ መጥቶ የሚመገበው ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና፡፡ ከዚሁ በተጨማሪ በቤተ ክርስቲያን ሙዳየ ምጽዋት ሳጥን እንዳለች ኹሉ ክርስቲያኖችም በየቀኑ ምጽዋት የሚያስቀምጡባትና አጠራቅመውም ድኾችን የሚረዱባት ትንሽ “ሙዳየ ምጽዋት” ማዘጋጀት ይገባቸዋል፡፡ ምጽዋት ባለበት ዲያብሎስ የለምና፡፡ በየቀኑ ጸሎት ከመጀመራቸው በፊትም በሙዳየ ምጽዋቷ ውስጥ የዓቅማቸውን ምጽዋት በማስቀመጥ መጀመር አለባቸው፡፡   

ከድኾች በተጨማሪ የኦርቶዶክሳውያን ባልና ሚስት ቤት ዘወትር ለመነኰሳት ክፍት መኾን አለበት፡፡ ቅዱሳኑ ምድራውያን መላእክት ወደዚያ ቤት ሲገቡ፥ እኩያት አጋንንትም በአንጻሩ እንደ ጢስ ተነው እንደ ትቢያ በነው ይጠፋሉና፡፡

(ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው፣ ገጽ 63-64 ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"እውነተኛ ሐሴት ትፈልጋላችሁን? እንግዲያውስ ለድሆች መጽውቱ፤ ክርስቶስን ወደ ቤታችሁ ጥሩት፡፡ ይህን ስታደርጉ ማዕዱ ቢነሣም ሐሴቱ አይነሣም፤ ይቀጥላል እንጂ፡፡ በተለይ ደግሞ በዚህ በወርሐ ጦም ይህን አብዝታችሁ አድርጉት።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#አትርሳ!

አንድ ሰው ወደ ቤተ መንግሥት አንዲት ሴተኛ አዳሪን ይዞ መጥቶ በንጉሡ ፊትም ሩካቤ ቢፈጽም፣ ወይም ቢሰክር፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ተግባር ቢፈጽም የቅጣት ቅጣት ይደርስበታል፡፡

አሁን ራሳችንን ጥያቄ እንጠይቅ፡፡ እግዚአብሔር የሰማይም የምድርን ንጉሥ ነው ወይስ አይደለም? ነው! የምናደርገውን ማንኛውም ድርጊት ይመለከታል ወይስ አይመለከትም? ኧረ ይመለከታል!
ታዲያ በምድራዊ ንጉሥ ፊት ከላይ የጠቀስናቸውን ነውሮች ደፍሮ የፈጸመ ሰው ጽኑ ቅጣት የሚቀጣ ከኾነ እንደዚህ ያሉ ተግባራትን በእግዚአብሔር ፊት ለማከናወን የምንደፍረው ለምንድን ነው? ምድራዊው ንጉሥ ቢቀጣ ምድራዊ ቅጣትን ነው፡፡ ሰማያዊው ንጉሥ ሲቀጣ ግን ሰማያዊ ቅጣት እንደ ኾነ አናውቅምን? ...

ሰው ሆይ! እያንዳንዷን ድርጊትህ የሚመለከት የሰማይም የምድርም ንጉሥ እንዳለ በፍጹም አትርሳ፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ- አምስቱ የንስሐ መንገዶች እና ሌሎች - ገጽ 119)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"እጅግ የምወዳችሁ ምእመናን ሆይ የጾም ጥቅሟ ምን ያህል የበዛ እንደሆነ ነፍሳችን ከዚህ ብዙ ጥቅምን እንደምታገኝ ከጌታችንና እና ከአገልጋዮቹ ተምረናል፡፡ ስለሆነም የጾም ወራት ሲቃረብ ግድ የለሽነትንና ሞራለ ቢስነትን ከእኛ አስወግደን ንዑድ ክቡር የሚሆን ጻውሎስ፡- የውጭው ሰውነታችን ይበልጥ ሲጠፋ የውስጡ ሰውነታችን ይበልጥ ይታደሳል’’ ብሎ እንዳስተማረን እጅግ ደስ ተሰኝተን ልንቀበለው ይገባናል ብዬ እማልዳችኃለሁ፡፡ /2ኛ ቆሮ 4፡16/

ጾም የነፍስ ምግብ ሥጋ ሰውነታችን እንዲወፍር እንደሚያደርግ ሁሉ ጾምም ነፍስን ያበረታል ፈጣንና መንፈሳዊ ክንፍን ይሰጣል፤ ወደ ሰማያዊ ምስጢር ገብታ በፅሞና እንድትያዝ ያደርጋታል የዚህን ዓለም  ተድላና ደስታ እንድትንቅ ያስችላታል፡፡

ቀላል ጭነትን የተሸከሙ መርከቦች ፈጥነው ባህሩን እንደሚሻገሩ እጅግ ብዙ ጭነትን የተሸከሙት ግን ባህሩንና ወጀቡን ቶሎ ማለፍ እንደሚያቅታቸው ሁሉ ልክ እንደዚሁ ጾምም ውስጣዊ ምስጢር እንድንገባ በዚያም ስላሉ አይነገሬ በረከቶችን እንድናስብ በዚህ ዓለም ላይ ያሉት ሁሉም ነገሮች እንደ ጠዋት ጤዛ ፈጥነው የሚያልፉ እንደሆኑ እንድንገነዘብ ታደርጋለች፡፡

ከዚሁ በተቃራኒ አብዝቶ መብላትና ራስን አለመግዛት ደግሞ አእምሯችን የጠፋ ሥጋችን የወፈረ ውስጣችን በእግረ ብረት የተጠፈረ በዚህ ሁሉ ተከበን እጅግ በከፉ ምግባራት የተያዝን የዘለዓለማዊ ሕይወታችን ጠላቶች ሆነን እንድንጓዝ ያደርጉናል፡፡

ስለዚህ ተወዳጆች ሆይ! መብልንና ራስን አለመግዛት ተከትለው የሚመጡትን ኃጣውእ በማወቅ ከድኅነታችን ጋር  በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ቸልተኞች አንሁን፡፡"

( ኦሪት ዘፍጥረት - በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/24 04:29:58
Back to Top
HTML Embed Code: