Telegram Web Link
ክርስቶስና ዮናስ በትንቢተ ዮናስ

ክፍል አንድ

ጥቂት ስለመጽሐፉ

የትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ በዐራት ምዕራፎችና በጠቅላላው በ48 ቁጥሮች ተከፋፍሎ የሚገኝ የብሉይ ኪዳን የትንቢት መጽሐፍ ነው፡፡ የተጻፈው ከነነዌ ከተመለሰ በኋላ በ770 ቅ.ል.ክ አካባቢ እንደሆነ ይታመናል፡፡ መጽሐፉ ለአሕዛብ ከተጻፉ የብሉይ ኪዳን ሁለት መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ነው (ለአሕዛብ የተጻፉ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት ትንቢተ ዮናስና ትንቢተ አብድዩ መሆናቸውን ልብ ይሏል)፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እግዚአብሔር ለሰዎች ማለት ለሕዝብም ለአሕዛብም (እንደ ሕዝብ ለዮናስ፣ እንደ አሕዛብ ደግሞ ለመርከበኞችና ለነነዌ ሰዎች) ፍቅሩን በተለያየ መንገድ ገልጧል፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ የምናገኛቸው ዋና ዋና ገጸ ባሕርያት ዮናስ፣ መርከበኞችና የነነዌ ሰዎች ሲሆኑ እግዚአብሔር በዮናስ በኩል መርከበኞችንና የነነዌን ሰዎች አስተምሯል፤ በመርከበኞች፣ በባሕሩ ማዕበል፣ በቅሏ፣ ቅሉን በበላችው ትልና በምሥራቁ ነፋስ በኩል ደግሞ ዮናስን አስተምሯል፡፡

ስለፀሐፊው

በመጽሐፉ ውስጥ ስሙ ባለመጠቀሱ፣ ከምርኮ በኋላ ጥቅም ላይ የዋሉ ቃላት መኖራቸውና በወቅቱ የነበረው የነነዌ ንጉሥ ስም ባለመጠቀሱ ምክንያት ፀሐፊው ዮናስ አይደለም በማለት የሚከራከሩ ጥቂት አይደሉም፡፡ ፀሐፊው ግን ዮናስ ለመሆኑ ብዙ ማሳያዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ስሙ ለምን አልተጠቀሰም ስለሚባለው ይህ የብዙ ቅዱሳት መጽሐፍት ፀሐፍት ልማድ ነው፡፡ ለምሳሌ መግቢያው ከትንቢተ ኢዩኤል፣ ከትንቢተ ሚክያስ፣ ከትንቢተ ሶፎንያስ፣ ከትንቢተ ሐጌ፣ ከትንቢተ ዘካርያስና ከሌሎችም ጋር በጣም የሚመሳሰል ነው፡፡ “የሰማይ አምላክ” /ዮና 1÷9/ የሚለውን ቃል ከምርኮ መልስ በኋላ እነዕዝራ፣ እነዳንኤልና እነነህምያ በብዛት ተጠቅመውበት ስለሚገኝ ብቻ መጽሐፉ ከምርኮ መልስ ከዮናስ በኋላ ነው የተጻፈ ማለት ብዙ የሚያራምድ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ቃላት ከዚያ በፊት በተጻፉ ቅዱሳት መጻሕፍት የሉም ማለት ቃለቱ አይታወቁም ማለት አይደለም፡፡ ደግሞም ዮናስ ከመርከበኞችና ከንጉሡ ጋር ነው እነዚህን ቃላት የተጠቀመ፤ ምክንያቱም ለእነርሱ የሰማይ አምላክ ከሚለው የተሻለ እግዚአብሔርን የሚገልጥበት መንገድ ሊያገኝ አይችልምና፡፡ ቃሉም ፈጣሪን ለማለት መሆኑ በሁሉም ዘንድ የተረዳ ነውና፡፡ በወቅቱ የነበረውን የነነዌ ንጉሥ ስም ባለመጥቀሱም ፀሐፊው ከዮናስ በኋላ በተነሣ ሌላ ነቢይ ነው የተጻፈ የሚሉም የመጽሐፉን አላማ ባለመረዳታቸው ሆኖ ነው የምናገኘው፡፡ የመጽሐፉ ዓላማ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ያለውን ፍቅር ማሳየት ስለሆነ የሰዎችን ንስሐቸውንና ያገኙትን ምሕረት እንጂ የንጉሡን ስም መጥቀስ አላስፈለገም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በጣም አስፈላጊ ሆኖ ካላገኘው በስተቀር የሰውን ስም አይጠቅስም፡፡

በመጽሐፉ ማንነት ላይ የተነሡ ጥያቄዎች

አንዳንድ አካላት በመጽሐፉ ውስጥ የምናገኛቸውን ገጸባሕርያትና ታሪኮች ትንቢታትም ጭምር በምሳሌ መልክ የቀረቡ እንጂ በትክክል የተፈጸሙ አይደሉም በማለት በመጽሐፉ ላይ የሚከተሉትን አራት የማንነት ጥያቄዎች አቅርበዋል፡-

1ኛ. መጽሐፉ ከትንቢት መጽሐፍ እንጂ ከታሪክ መጽሐፍት ውስጥ አለመሆኑ በታሪኩ ተአማኒነት ላይ ጥያቄ ያነሳሉ፡፡
መጀመሪያ ላይ የትንቢት መጽሐፍ መሆኑ የመጽሐፉን ታሪካዊነት እንደማያስቀረው ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መጽሐፉ ከትንቢት መጽሐፍት ጋር የተመደበበት ምክንያት ፀሐፊው ነቢይ ስለነበረና መጽሐፉም የትንቢት ይዘት ስለነበረው ነው፡፡

2ኛ. የነነዌ ሰዎች ንስሐ ፈጣንና የወል መሆኑ፣ የንጉሡም ውሳኔ እንዲሁ ፈጣን በመሆኑ ያልተጠበቀና ከእውነት የራቀ ነው በሚል መጽሐፉን ላለመቀበል የሚዳዳቸውም አልጠፉም፡፡
ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት በዓሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ቆይቶ የብስ ላይ የተወረወረው ዮናስ ከተማዋን በስብከቱ አናወጣት፡፡ እስኪ እናስበው ከዓሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ገብቶ ከመበላት ተርፎ በተአምር የወጣ ሰው በምን አይነት መንፈስና ወኔ የተደረገለትን ነገር ይመሰክር ይሆን? ከተማዋን ከዳር ዳር እየጮኸ አዳረሳት፡፡ እነርሱም ይመጣባቸው ዘንድ ስላለው የእግዚአብሔር ቁጣ ደነገጡ፤ ንስሐም ገቡ፡፡ ጌታችንም የነነዌ ሰዎች በዮናስ ስብከት ንስሐ እንደገቡና ይልቁንም በፍርድ ቀን መጥተው በዚህ ትውልድ ላይ እንደሚፈርዱበት በማይታበል ቃሉ ተናግሮላቸዋል /ማቴ 12÷41፣ ሉቃ 11÷32/፡፡ ስለዚህ ይኼ ደካማ ተቃውሞ ነው፡፡

3ኛ. በዓሣ ሆድ ውስጥ ሰው ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት መቆየት አይችልም፤ ይልቁንም በዚያ ውስጥ መጸለይ ሊታመን የማይችል ታሪክ ነው በማለት የተቃወሙም ነበሩ፤
ይህ ተቃውሞ በቅዱስ ጄሮም ዘመን ተነስቶ ስለእነዚህ አካለት አባ ሄሮኒመስ (አባ ጄሮም) እንዲህ ብሎ ነበር፡- “እነዚህ ሰዎች ግን አማኞች ናቸው ወይስ ከሀድያን? ሃይማኖት ካላቸው እውነት እንደሆነ መቀበል አለባቸው፡፡ ደግሞስ ይህን መቀበል ካልተቻለ ሦስቱ ሕፃናት የልብሳቸውን ዘርፍ እሳቱ ሳይነካው፣ ጭስ ጭስ እንኳን ሳይሸቱ ከእሳቱ እንዴት ሊተርፉ ቻሉ? ውኃው እንደ ግድግዳ በግራና በቀኝ ቁሞ በደረቅ የተሻገሩትስ? ዳንኤልንስ አንበሳው ሊበላው አይደለም እንዴት ሊነካው እንኳ ሳይችል ቀረ? …”
በነገራችን ላይ ዓሣ አንበሪ በጣም ትልቅ ፍጡር ከመሆኑ የተነሣ በተለያዩ ጊዜያት በዚህ ዓሣ የተዋጡ እንስሳት አጥንታቸው ሳይሰባበር ወይም ብዙ ሳይጎዱ እንደወጡ በሳይንቲስቶች ሳይቀር የተረጋገጠ እውነታ ነው፡፡ ለምሳሌ ዓሣ በማጥመድ ላይ የነበረ አንድ ብሪታንያዊ በዚህ ግዙፍ ፍጡር ከተዋጠ ከ48 ሰዓታት በኋላ ጎትተው ሲያወጡት ራሱን ስቶ (unconscious) ብቻ ሆኖ ነበር ያገኙት፡፡ ሕይወቱንም ካስተረፉለት በኋላ የሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮናስ (Jonah of the 20th century) ብለው ሰይመውት ነበር፡፡ ስለዚህ ይህ የዮናስን በዓሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ምንም ሳይጎዳ መቆየቱንና በዚያ ውስጥም ሆኖ መጸለዩን የማያምን ካለ በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ለማመን የሚቸገር ነው የሚሆነው፡፡

4ኛ. በመጽሐፉ ውስጥ ያሉ አገላለጦች በሌሎች መጻሕፍት እንዳሉት ምሳሌያት እንጂ ትክከለኛ ክስተት አይደሉም የሚል ተቃውሞ የሚያነሱም ነበሩ፡፡ ለዚህም ማስረጃ ይሆናቸው ዘንድ የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ይጠቅሳሉ፡- “የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደ ነፆር በላኝ፤ ከፋፈለኝ፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደረገኝ፤ እንደ ዘንዶም ዋጠኝ፤ ከሚጣፍጠውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ፡፡ … በባቢሎንም ላይ እበቀላለሁ፤ የዋጠችውንም ከአፍዋ አስተፋዋለሁ” /ኤር 51÷34፡ 44/፡፡
“ከሁለት ቀን በኋላ ያድነናል፤ በሦስተኛውም ቀን ያስነሣናል፤ በፊቱም በሕይወት እንኖራለን” /ሆሴ 6÷2/፡፡ ስለዚህ ዮናስን የእስራኤል፣ ዓሣ አንበሪውን የባቢሎን፣ የዓሣውን ሆድ የምርኮ እና ወደ ዮናስ የመጣውን የእግዚአብሔር ቸርነት ከእስራኤል የማይለየው የእግዚአብሔር ምሕረት ምሳሌ እንጂ የተፈጸመ ታሪክ አይደለም በማለት በጠባቡ ይመለከቱታል፡፡
በኤርሚያስና በሆሴዕ የትንቢት መጻሕፍት ውስጥ የምናገኛቸው ምሳሌያት ትንቢተ ዮናስን ተራ ምሳሌ የሚያሰኙ አይደሉም ይልቁንም ሁለቱም ነቢያት ከትንቢተ ዮናስ እውነተኛ ክስተት ጋር የሚገናኝ ምሳሌ አገኙ ያሰኛል እንጂ፡፡
በሌላ በኩል ጌታችን በማቴ 12÷39-40 እና በሉቃ 11÷29-30 ላይ የነነዌን ሰዎች እያነሳሳ ሲያመሰግናቸው ይሄ እኮ ምሳሌ እንጂ በትክክል የተፈጸመ ታሪክ አይደለም በማለት የተከራከረ ከረበናተ አይሁድ መካከል አንድ ስንኳ አልነበረም፡፡ ከዚህም በላይ መጽሐፉ ዮናስንና አባቱን በመጥቀስ የሚጀምር፣ የሁለቱም የትውልድ ቦታ የታወቀ (2ነገ 14÷25)፣ በመጽሐፉ የተጠቀሱ ቦታዎችም (እነእዮጴ፣ ጠርሴስና ነነዌ) በትክክል የነበሩና ያሉ ቦታዎች እንጂ ለምሳሌ ብቻ የቀረቡ ስሞች አለመሆናቸውን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ይልቁንም መጽሐፉ በዮናስ ውስጥ ክርስቶስን፣ በነነዌ ሰዎች ውስጥ ደግሞ ተነሳሕያንን የምንመለከትበት መነጽራችን ነው፡፡ ለዛሬ በመጽሐፉ ውስጥ አለፍ አለፍ ብለን በወፍ በረር ክርስቶስን በትንቢተ ዮናስ ውስጥ ከዮናስ ጋር እያነጻጸርን እናያለን፡፡

ክፍል ሁለት ይቀጥላል።
ጥር 29/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ
ምንጭ :-ዲ/ን ዶ/ር የሸወስ መኳንንት
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#Update

ቤተክርስቲያኗ መንግስት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቃት እንዲሁም ህገወጥ ናቸው ስትል የፈረጀቻቸው አካላት እየፈፀሙት ነው ላለችው ህገወጥ ድርጊት እገዛ ከመስጠት እንዲታቀብ አሳሰበች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በትላንትናው ዕለት መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በተመለከተ የሰጠውን መግለጫ እንደማትቀበለው አሳውቃለች።

ቤተክርስቲያኗ ትላንት መንግስት መግለጫውን ሲያወጣ ፤ " በሻሸመኔ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ሕገ ወጥ፤ አስነዋሪ እና ጭካኔ የተሞላበት የአደባባይ ግድያ እና የሕዝብ ፍጅት ያልጠቀሰና ሐዘኑን እንኳን መግለጽ ያልቻለበትና ያላወገዘ መሆኑን አንስታ ይህም " የመንግሥትን ግልጽ ሚና በቀላሉ ለመረዳት እንድንችል ያደርገናል " ብላለች።

" መንግሥት ሕገ ወጥ አካላትን ድጋፍ ከመስጠት እና የእነርሱ ልሳን ሆኖ በመቅረብ የቤተ ክርስቲያንን ክብር እና ልእልና ከሚያንኳስስ ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲታቀብ እናሳስባለን " ያለችው ቤተክርስቲያኗ ፤ " ሕገ ወጡ ስብስቦች እየፈጸሙ ላሉት ድርጊትም የሰጠውን ድጋፍ እና እገዛ በይፋ ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ በመጠየቅ ያቁም " ስትል አሳስባለች።

tikvahethiopia

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from 1,000-20,000 Promotion via @Wenderad_love_bot
🚦 wifi password 🔑 መለመን ቀረ!! ለማንኛውም ስልክ ይሰራል👈 ከናተ የሚጠበቀው #JOIN የሚለውን መንካት ብቻ ነው
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ዛሬም እስር እና ማንገላታት ቀጥሎ መዋሉን ገለፁ።

ተሚማ የተሰኘው ሚዲያ ፤ በዛሬው ዕለት የአርሲ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ታምራት ወልዴ መታሰራቸውን ገልጿል።

ሚዲያው ፤ " ሕገ ወጡን ቡድን የሚደግፉት የመንግሥት አካላት ሥራ አስኪያጁን ቁልፍ አስረክበው እንዲወጡ ቢነግሯቸውም አልቀበልም በማለታቸው ዛሬ ጠዋት ታሥረዋል " ሲል ነው ያስረዳው።

በሌላ በኩል በሀገረ ስብከቱ ያሉ 13 ወጣቶችም በዛሬው ዕለት መታሠራቸው ተነግሯል።

በሌላ በኩል በቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ ዛሬ የኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ጥቁር ለብሰው የዋሉ ሲሆን ጥቁር ልብስ የለበሱ ምእመናን በኮልፌ ፊሊዶሮ ልደታ፣ በቀራንዮ መድኃኔዓለምና በወይብላ ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ማርያም አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ ፖሊስ ድብደባ መፈፀሙን የቤተክርስቲያና መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በሌላ በኩል በአንዳንድ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሰራተኞች ጥቁር እንዳይለብሱ ፤ የቤተክርስቲያኗን ትዕዛዝ እንዳይፈፅሙ የማድረግ እንቅስቃሴ መኖሩን የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን አሳውቀዋል።

ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ ምዕመናን #ጥቁር_ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ጸሎትና ምሕላ እንዲያቀርቡ በቤተክርስቲያኗ የቀረበው ጥሪ በቀጣይ ቀናትም ተግባራዊ ሆኖ ይቀጥላል።

ፎቶ፦ የጾመ ነነዌ የፀሎት ስነስርዓት

tikvahethiopia

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የቶማስ አካል ሻሸመኔ
[ሊቀሊቃውንት ስምዓኮነ መልአክ]

በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ከታወቁ ሰማዕታት መካከል አንዱ የመራስ አገር ኤጲስ ቆጶስ ቶማስ ነው። በተጋድሎ የጸና ለወንጌል የሚተጋ የክርስቶስ ወታደር ነው። ቤተ ክርስቲያን ከመከራው ሳታርፍ አላርፍም ብሎ ስለወሰነ የቆስጠንጢኖስ መንግሥት መከራውን እስኪያስቆመው ድረስ በየቀኑ ስለክርስቶስ ጽኑ ጽኑ መከራን ከመቀበል አላቋረጠም። ከሀድያኑ እየመጡ በየጊዜው አሰቃይተውታል። አንድ ጊዜ አልጨረሱትም። አካሉን ቀስ እያደረጉ በየጊዜው እየቀነጣጠሱ አጅ፣ እግር፣ አፍንጫ፣ ከንፈር የሌለው አደረጉት። አካሉ ተቆራርጦ በማለቁ ምክንያት ደቀ መዛሙርቱ በቅርጫት አድርገው በአህያ ይጭኑት ነበር።

ሻሸመኔ ቶማስን መሰለች፤ መከራ ተመላለሰባት፤ ግፍዕ በዛባት።
ቤታቸው እየተጎተቱ ወጥተው በዐደባባይ የታረዱ ምዕመናን ያየንባት ከተማ ናት - ሻሸመኔ።
የፀነሰች ሴት ቢወለድም ክርስቲያን ነው ሚሆን በሚል ስሌት በማኅፀኗ ያለውን ፅንስ አውጥተው የገደሉባት ከተማም ናት። በማኅፀን ያሉ ሕጻናት ሰማዕት ሲሆኑ ያየንባት!
የክርስቲያኖች ቤት በአንድ ቀን እንደ ደመራ የነደደባት የመስቀል ዐደባባይ ናት።
ዛሬም ከኢትዮጵያ ከተሞች ቀድማ መስቀሉን ተሸከመች።
የለመደችውን የሰማዕትነት ጉዞ ከሁሉ ቀድማ ጀመረች።
ሻሸመኔ ነፍሷን ሰጠች።
ልጆቿን ስለ መንግሥተ ሰማያት መራራ ሞትን ታገሡ ብላ አሰለፈች።
ሻሸመኔ ደጋግማ የክርስቶስ ከተማ መሆኗን አሳየች።

ገዳዮቿ ዛሬም አልሰለቹም። እንደ ቅዱስ ቶማስ የቀረውን አካሏን ሊቆራርጡ ዛሬም ሰይፍ ጨብጠው መጡ።
ወዮ ለነዚህ ነፍሰ ገዳዮች!
ወዮ ለነዚህ ጳጳሳት ነን ባዮች! በሚካኤል ደጅ ያላመነ ያልተጠመቀ ሰው አቆሙበት። ይች ቤተክርስቲያን በእውነት ምን በደለቻቸው ትናንት ካህን ሆነው ያቆረቧቸው የባረኳቸው ምዕመናን ላይ አስለቃሽ ጭስ የሚተኩስ ወታደር ይዘው ሲገቡ እንዴት አስቻላቸው?
ለምዕመናን ሊሞቱላቸው ሲገባ ገድለው አስወጧቸው። ወዮ ለኒህ ሰዎች! ምን ከፍለው ይሆን ይችን ቤተ ክርስቲያን የሚታረቋት?
ባልተወለዱ በተሻላቸው
ቀን መውጣቱ የደከመ መበርታቱ
የተጠቃ ማጥቃቱ መች ይቀራል ያኔ ኃዘናቸው ከባድ ይሆናል።

የሻሸመኔ አባቶቼና እናቶቼ እኅት ወንድሞቼ በመካከላችሁ ሆኜ መከራችሁን ባልካፈልም ባለሁበት ስለናንተ አለቅሳለሁ። እኔ ልሰደድላችሁ። ሰው ቢጨንቀው ሮጦ ቤተ ክርስቲያን ይጠለላል ዛሬ ግን ከቤተ ክርስቲያን አስወጧችሁ፤ መጠጊያ አሳጧችሁ። ወንጌል የሰበክንበትን ታቦት ያከበርንበትን ቦታ ከሃይማኖታችን ውጭ የሆኑ ሰዎችን አቁመውበት አየሁት። እጅግ አዝኛለሁ የኔ ዘመን ሰማዕታት መንግሥተ ሰማያት ለናንተ ቅርብ ናት አይዟችሁ።
ስለናንተ የሰሙ አበው ሁሉ ስለናንተ ይጸልያሉ።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ክርስቶስና ዮናስ በትንቢተ ዮናስ

ክፍል ሁለት

ክርስቶስና ዮናስ

ዮናስ ለአሕዛብ የተላከ ብቸኛ ነቢይ ነበር (ለዚያም ነው በሌሎች ነቢያት ላይ ያላየነውን ጠባይ በዮናስ ውስጥ የምናገኝ፡፡ ሌሎች ነቢያት ቢላኩ ለእስራኤላዊያን ነበር እርሱ ግን ከዚያ በፊት ማንም ታዝዞ የማያውቀውን ትዕዛዝ ስለታዘዘ (ለአሕዛብ መላክ) ለጊዜውም ቢሆን እምቢ አልላክም ብሎ ከእግዚአብሔር ፊት ሲኮበልል እናያለን)፤ ክርስቶስም ለሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለአሕዛብም ጭምር ስለመጣ ስለእርሱ “እርሱ ለአሕዛብ ፍርድን ይናገራል” /ማቴ 12÷18/ ተብሎለታል፡፡ ዮናስ ማለት የዋህ ማለት እንደሆነ ክርስቶስም “እኔ የዋህ ነኝና” /ማቴ 11÷29/ ሲል እናገኘዋለን፡፡
ርግብ ዮናስ ወደ ባሕሩ ከተወረወረ በኋላ በዚያ ያለውን መከራ አልፎ የነነዌን ሰዎች በስብከቱ እንዳዳናቸው ክርስቶስም በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ከታዬና ብዙ ጸዋትወ መከራን ከተቀበለ በኋላ ነበር ያዳነን፡፡
ማዕበሉ ተሳፋሪዎችን ሲያስጨንቃቸው ዮናስ ግን በመርከቧ የታችኛው ክፍል ውስጥ ገብቶ ተኝቶ ነበርና ወደ አምላኩ እንዲጸልይና እንዲያድናቸው ቀስቅሰውት እንደነበር ከመርከቡ አለቃ አነጋገር መረዳት ይቻላል፡- “የመርከቡም አለቃ ወደ እርሱ ቀርቦ ምነው ተኝተሃል? እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ ተነሥተህ አምላክህን ጥራ አለው” /ዮና 1÷6/ እንዲል፡፡ ክርስቶስም እንዲሁ በታንኳ ውስጥ ተኝቶ እንደነበርና ማዕበሉም ታላቅ እንደነበር፣ ሐዋርያትም ቀስቅሰውት እንደነበረ እንዲህ ተብሎ ተጽፎ እናገኛለን፡- “እነሆም የባሕሩ ማዕበል ታንኳውን እስኪደፍነው ድረስ በባሕሩ ውስጥ ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው ቀሰቀሱትና “አቤቱ እንዳንሞት አድነን” አሉት” /ማቴ 8÷24-25/፡፡ እዚህ ላይ ዮናስ የተኛባት መርከብ የመስቀሉ ምሳሌ ስትሆን፣ የዮናስ እንቅልፍ የክርስቶስን ሞት የሚወክል መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ እንቅልፍ ሰው ወድዶና ፈቅዶ የሚያመጣው እንደሆነ ሁሉ የክርስቶስም ሞት በእንቅልፍ የመመሰሉ አንዱ ምክንያት በፈቃዱ የተቀበለው በመሆኑ ነው፡፡
በመርከቧ ውስጥ የነበሩ ሁሉ ማዕበሉ በማን ምክንያት እንደመጣባቸው ለማወቅ በተጣጣሉት ዕጣ መሠረት ዕጣው በዮናስ ላይ በወደቀ ጊዜ ዮናስ “ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንዳገኛችሁ ዐውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ” ብሎ ነበር፡፡ ከዚህ እንደ ምንረዳው ዮናስ ይዘው ወደ ባሕሩ ይወረውሩት ዘንድ ፈቃደኛ መሆኑንና እነርሱም ወደ ባሕሩ የጣሉት የእርሱን ፈቃድ ተከትለው እንጂ አስገድደውት አለመሆኑን ነው፡፡ ክርስቶስም በይሁዳ እጅ ለአይሁዳውያን ተላልፎ ከመሰጠት ጀምሮ እስከ ሞት የደረሰው በፈቃዱ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ምንም እንኳን ዮናስ ምክንያቱ እኔ ነኝ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ ቢላቸውም እነርሱ ግን ወደ ምድሩ ሊመለሱ አጥብቀው ቢቀስፉም አልቻሉም ነበር፤ “ሁሉም አንድ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ” /ዮና 1÷14/፡፡ ይህም ከአዳም ጀምሮ እስከ ዮሐንስ ድረስ የተነሡ አበውና ቅዱሳን ቢጮኹም የዓለሙን መድኃኒት ክርስቶስን እስኪያገኙ ድረስ እንዳልተሳካላቸው የሚያስታውስ ነው፡፡
በመጨረሻም መርከበኞቹ ወደ ምድሩ ሊመለሱ ስላልቻሉ ዮናስን ወደ ባሕሩ መጣል የመጨረሻ አማራጭ አድርገው በወሰዱ ጊዜ እግዚአብሔርን አንድ በጣም የሚደንቅ ልመና ለምነውት ነበር፤ ይኸውም፡- “አቤቱ! አንተ እንደወደድህ አድርገሃልና ስለዚህ ሰው ነፍስ አታጥፋን፤ ንጹሕ ደምንም አታድርግብን” /ዮና 1÷14/ የሚል ነበር፡፡ ይህ አነጋገራቸው ጲላጦስን ነው የሚያስታውሰን፡፡ ጲላጦስ ክርስቶስን ሊያድነው የቻለውን ሁሉ ካደረገ በኋላ መጨረሻ ላይ አሳልፎ ሲሰጣቸው “እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ለራሳችሁ ዕወቁʼ ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ” /ማቴ 27÷24/፡፡ የሚገርመው ልክ በመርከቡ ውስጥ እንደነበሩት ሰዎች ሁሉ ጲላጦስም ከአሕዛብ ወገን መሆኑ ነው፡፡
ዮናስ ለማዕበሉ ተላልፎ ሲሰጥ በመርከቧ ውስጥ የነበሩ ሁሉም እንደዳኑ፣ “እጅህን ከአርያም ላክ” እያሉ ሲጮኹ የነበሩ ነፍሳት ሁሉ መዳናቸው እውን የሆነው ከክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት ተላልፎ መሰጠት በኋላ ነው፡፡ በዮናስ ከመርከቧ መወገድ መርከቧ ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ሁሉ ሊውጣቸው ሰፍ ብሎ የነበረው ሞት እንደሞተ፣ በባሕር በምትመሰል በዚህች ምድር የፈተና ማዕበል የሚንኖር እኛም ድኅነታችን የተፈጸመው በክርስቶስ መገፋትና ለሞት ተላልፎ መሰጠት በኋላ ነው፡፡
ዮናስን ወደ ባሕሩ ከጣሉት በኋላ “ባሕሩም ከመናወጡ ጸጥ አለ፡፡ ሰዎቹም እግዚአብሔርን እጅግ ፈሩ፤ ለእግዚአብሔርም መሥዋዕትን አቀረቡ፤ ስእለትንም ተሳሉ” ይላል ትንቢተ ዮናስ /ዮና 1÷15-16/፡፡ ቤተ ክርስቲያን ዘአሕዛብም እግዚአብሔርን መፍራቷ፣ ለእግዚአብሔር መስገዷ፣ መጸለይዋ እና መስዋዕት ማቅረቧ ከክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት በኋላ ነው፡፡
ዮናስ እግዚአብሔርን “አምላኬ” ይለዋል፤ ክርስቶስም የተዋሃደውን ሥጋ የፈጠረ ነውና አባቱን “አምላኬ” /ዮሐ 20÷17/ ብሎታል፡፡ ዮናስ በጸሎቱ “ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ፤ ፈሳሾችም ከበቡኝ” /ዮና 2÷4/ ማለቱ በክርስቶስ ላይ የደረሰውን መከራ የሚያወሳ ሲሆን፣ ዮናስ በፈሳሾች ተከበብሁ ማለቱም ክርስቶስ ለጥምቀታችን የሚሆን ፈሳሽ በመከራው እንዲከበን አድርጎ መከራውን በእኛ ሕይወት እንደቀየረው የሚያስታውስ ነው፤ “ፈሳሽ ወንዝ የእግዚአብሔርን ከተማ ደስ ያሰኛል” /መዝ 43÷4/ እንዲል፡፡ በዮና 2÷4 “ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ ዐለፉ” የሚለው በክርስቶስ ላይ የደረሰው ለ5500 ዓመታት የተጠራቀመውን ግፍና መከራ የሚያመለክት ሲሆን አስቀድሞ ስለሚቀበለው መከራ በመዝ 41÷7 ላይ “ማዕበልህና ሞገድህ በላዬ ዐለፉ” በማለት በነቢዩ አንደበት ከተናገረው ጋር አንድ ነው፡፡
ዮናስ “እኔም ከዐይንህ ፊት ተጣልሁ” /የና 2÷5/ እንዳለ ክርስቶስም “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ?” /ማቴ 27÷46/ ብሏል፡፡ በመቀጠልም “ውኃ እስከ ነፍሴ ድረስ ፈሰሰ፤ ጥልቁ ባሕር በዙሪያዬ ከበበኝ” /ዮና 2÷6/ በማለት የጸለየው ክርስቶስ አስቀድሞ በነቢዩ ዳዊት አንደበት “አቤቱ ውኃ እስከ ነፍሴ ደርሶብኛልና አድነኝ” /መዝ 68÷1/ በማለት ካስነገረው ትንቢት ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡
ዮናስን ጥልቁ ባሕር ሊያስቀረው አልቻለም ነበር፤ ክርስቶስንም መቃብር ሥጋውን፣ ሲዖል ደግሞ ነፍሱን ይዘው ማስቀረት አልቻሉም፡፡ ነቢዩ በሦስተኛው ቀን ከዓሣው ሆድ ውስጥ እንደወጣ፣ ክርስቶስም ሙስና መቃብርን አጥፍቶ በሦስተኛው ቀን ከሙታን መካከል ተለይቶ ተነሥቷል /ማቴ 12÷40/፡፡
ነቢዩ “አቤቱ ፈጣሪዬ! ሕይወቴ ጥፋት ሳያገኛት ወደ አንተ ትውጣ” /ዮና 2÷7/ አለ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በማቴ 26÷38-39 “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዘነች፤ አባቴ ሆይ የሚቻልስ ከሆነ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ” በማለት በተዋሃደው ሥጋ የደረሰበትን ፍጹም መከራ ተናግሯል፡፡ በዚሁ በዮና 2÷8 ላይ “ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ ቅዱስ መቅደስህ ትግባ” እያለ የጸሎቱን ሥሙርነት ተናግሯል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ቅድስተ ቅዱሳን ወደ ተባለው ወደ መስቀሉ የገባው ክርስቶስ መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልእክቱ ምዕራፍ ዘጠኝ ከጠቀሰው ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡
ዮናስ ያ ሁሉ መከራ ደርሶበት በዓሣ አንበሪው ሆድ ውስጥ ሆኖ “እኔ ግን ከምስጋናና ከኑዛዜ ጋር እሠዋልሃለሁ” /ዮና 2÷10/ ሲል እናገኘዋለን፤ ክርስቶስም በመስቀል ላይ ሆኖ እንዲያ እየተዘባበቱበትና ተጠማሁ ሲላቸው ሆምጣጤ እየሰጡት “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ሲል እናገኘዋለን፡፡
“እግዚአብሔርም ዓሣ አንበሪውን አዘዘው፤ እርሱም ዮናስን በየብስ ላይ ተፋው” /ዮና 2÷11/ የሚለውም “ነፍሴን በሲዖል አትተዋትምና ጻድቅህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም” /መዝ 15÷10/ ተብሎ ለክርስቶስ ከተነገረው ትንቢት ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡
ዮናስ ከዓሣ አንበሪው ሆድ ውስጥ ከወጣ በኋላ በቀጥታ ወደ ታላቋ ከተማ ወደ ነነዌ ገብቶ ከዳር ዳር እየዞረ በስብከቱ አናወጣት፡፡ በስብከቱም ንጉሡንና መኳንንቱን ንስሐ እንዲገቡ አድርጎ ከንጉሡ በወጣች አዋጅ መሠረት እንስሳት እንኳን ሳይቀሩ እንዲጾሙ ተደረገ፡፡ ክርስቶስም በመካከላችን ተገኝቶ የመንግሥትን ወንጌል በሰበከልን ጊዜ ንጉሥ የተባለ ሥጋን እና እንስሳት የተባሉ ፈቃዳተ ሥጋን ለፈቃደ ነፍሳችን እንድናስገዛ ሲያደርግ፣ መኳንንት (የቤተ መንግሥት ሰዎች) የተባሉም እውቀታችን፣ ኀይላችንና ጥበባችን ሲሆኑ እነዚህንም ለመልካም አምልኮ እና ለአገልግሎት እንድናውላቸው አድርጓል፡፡
ነቢዩ ዮናስ “በአሕዛብ ድኅነት የገዛ ሕዝቡን (የእስራኤልን) ጥፋት ያወጀ ብቸኛ ነቢይ ነኝ” በማለት ስለወገኖቹ ግድ ብሎት ከሕይወት ሞትን መረጠ “አቤቱ! ከሕይወት ሞት ይሻለኛልና እባክህ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ” /ዮና 4÷3/ ያለው ክርስቶስ ስለእኛ በፈቃዱ የተቀበለውን ሞት የሚወክል ነው፡፡
ከዚያም ዮናስ ዳስ ሠርቶ ከጥላው በታች ሲቀመጥ እግዘዚአብሔር አምላክ ከጭንቀቱ ታድነው ዘንድ፣ በራሱ ላይም ጥላ ትሆነው ዘንድ በዮናስ ራስ ላይ ከፍ ከፍ እንድትል አድርጎ ቅልን አበቀለለት፡፡ ግን ቅሏ በሌሊት እንደበቀለች በሌሊት ደረቀች፡፡ ቅሏ የአይሁድ ምሳሌ ስትሆን በሌሊት በቅላ በሌሊት መድረቋ በጨለማው ዘመን አምነው በዛው በጨለመው ዘመን የቀሩና ብርሃን ክርስቶስን ሳይቀበሉ በብርሃን ሳይመላለሱ ለመቅረታቸው ምሳሌ ነው /ዮሐ 1÷9-12/፡፡ በሌላም በኩል ቅሏ የመስቀሉ ምሳሌ ትሆናለች፤ ይኸውም እግዚአብሔር ለዮናስ ቅልን በማዘዙ ከጭንቀቱ እንደዳነና በጥላዋ እንደተከለለ፣ ቤተ ክርስቲያንም ከመስቀሉ ሥር ሰላምንና ደስታን አግኝታለችና፡፡
ቅሏን ያደረቃት፣ ዮናስንም ሞቱን እስኪናፍቅ ድረስ የለበለበው ያ የምሥራቁ ትኩስ ነፋስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ሞቷን እስክትመኝ ድረስ መከራና ስቃይን ለማምጣት ከክርስቶስ ዳግም ምጽአት ቀደም ብሎ የሚመጣው የሐሳዊ መሲሕ ምሳሌ ነው፡፡
ታላቂቱ ከተማ ነነዌ የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ስትሆን፣ ሰዎቿም “ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ” /ዮና 4÷11/ የተባለላቸው ልክ እንደ ሕፃናት ምንም የማያውቁ ናቸው፡፡ የቤተ ክርስቲያን ምእመናንም “እንደዚህ ሕፃን”፣ “እንደ ሕፃን” /ማቴ 18÷2፡4፡5፣ ማር 10÷15/ የተባሉ ለመንግሥቱ የተገቡ ለጥፋት ያልታጩ ናቸው፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ምንጭ፦ Jonah by Father Tadros Y. Malaty

ዲ/ን የሺዋስ መኳንንት
ጥር 30/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/24 20:30:29
Back to Top
HTML Embed Code: