Telegram Web Link
ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ቦንጋ ለመግባት ቢሞክርም በሕዝበ ክርስቲያኑ እና በጸጥታ ኃይሎች ቅንጅት ዕቅዱ መክሸፉ ተገለጸ።

በከፋ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙት 12 ወረዳ ቤተ ክህነቶች የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ሳሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥያቄያችን ካልተመለሰ የካቲት 5 ቀን ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል ብሎ መናገሩን ተከትሎ ለዛሬ የታሰበው ሰልፍ እንዲቀር ነገር ግን ሁሉም በተጠንቀቅ እንዲጠብቅ ተነጋግረው ቆይተዋል።

ነገር ግን ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት አካባቢ ሕገ ወጡ ቡድን እየመጣ ነው መባሉን ተከትሎ በቦንጋ ከተማ በአሥሩ አድባራት የሚገኙ ካህናትና ምእመናን በነቂስ ወጥተው የኦሮሚያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አዋሳኝ ወደ ሆነችው ጎጀብ ወደ ተባለችው ኬላ ደርሰው ከክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ኬላውን ዘግተው በመጠበቅ ላይ ሳሉ ሕገ ወጡ ቡድን ይደርሳል።

ሕገ ወጡ ቡድን በኦሮሚያ ፖሊስ ታጅቦ የመጣ ቢሆንም ግር ግር በመፍጠር ለመግባት ቢሞክሩም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ፣ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት ከምእመኑ ጋር ሆነው በመከላከላቸው ወደ ጅማ መመለሳቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ወደ ቦንጋ የሚያስገቡ መንገዶች ሁሉ ተዘግተው የመኪና እንቅስቃሴ ቆሟል። ሕዝበ ክርስቲያኑም በከፋ በሚገኙት በአሥሩም አድባራት ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ ላይ ይገኛል። ተሚማ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በኦሮሚያ ያለችውን ቤተ ክርስቲያን በኃይል እየተቆጣጠረ የሚገኘው ሽብርተኛውና ወራሪው ስብስብ በሻሸመኔ ከተማ 35 ምዕመናንን በከባድ መሳሪያ በማስጨፍጨፍ በዛሬው ዕለት ወደ ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመግባት ፎቶ የመነሳት መርሐግብር ማካሄዱን ለመገንዘብ ተችሏል !

በምዕራብ አርሲና በሌሎች አካባቢዎች በየአብያተ ክርስቲያናቱ ፎቶ ትነሱ ይሆናል እንጂ ያስጨፈጨፋችሁት እና የልጆቹን ደም ረግጣችሁ በመግባት የቀለዳችሁበት ኦርቶዶክሳዊ ምዕመን የደረሰበትን ሰቆቃ መቼውንም አይረሳውም !

ለሕግ የበላይነት በእጅጉ እቆረቆራለሁ የሚለው የኢትዮጵያ መንግስት ሽብርተኞችን እና ወራሪዎችን መደገፍ ሊያቆም ይገባል !

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"መሬት እንስጣችሁና አብነት ት/ቤት ሥሩልን"
የዳሰነች ወረዳ አስተዳዳሪ

በትናንትናውና በዛሬው ዕለት በዳሰነች ወረዳ ከ1000 በላይ ኢ አማኒያን የሥላሴን ልጅነት ያገኙ ሲሆን የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያንም ተመርቋል።

በዕለቱ የተገኙት የቀድሞው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ቀብራራው "የኦሞ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያንን ቦታ የሠጠሁት እኔ ነኝ ዛሬ በመጠናቀቁ ደስተኛ ነኝ፤ አባቶቼ አሁን እኛ ተስፋችን በእናንተ ነው እባካችሁ ቤተክርስቲያን ችግር ውስጥ ናት፤ እኛ እስከ ሕይወት መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን"ብለዋል።

የአሁኑ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ፍቅረ ማርያም በበኩላቸው "እኔ ስሜን ያወጡልኝ አባ ኪዳነ ማርያም ሲሆኑ ስም ብቻ ሳይሆን ዲያቆን ትሆናለህ ሕዝብ ታስተዳድራለህ ነበር ያሉኝ፤ ባሉኝ መሠረት ይኸው ዛሬ ለዚህ በቃሁ። አባቶቼ ግን ዛሬ እኔ የሕዝብ ጥያቄ ለእናንተ አቀርባለሁ እሱንም እንደምትፈቅዱልኝ እትማመናለሁ በማለት የቀድሞ አስተዳዳሪ የቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ስጥቷል እኔ ደግሞ የወረዳ ቤተ ክህነት መሥሪያ ቦታ እሰጣለሁ:: እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤት እና ማሰልጠኛ ያስፈልጋል ለእሱም የሚሆን እሰጣለሁ:: በዋናነት ደግሞ የተጠመቅነው እንድንጸና ገዳም ስለሚያስፈልገን ገዳም የሚሠራበት እሰጣለሁ; ይህንን እንዲፈቅድልን በማለት እጠይቃለሁ ሲሉ ተማጽነዋል።
በዕለቱ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት  ብጹዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድንና ስካንዲናቪያን ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም በእንባ ሰምተዋቸዋል።

የስዊድንና ስካንዲናቪያ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስም "የእኛን ጥያቄ ነው ይጠየቃችሁት" ያሉ ሲሆን ጥያቄያቸው እንደሚመልስ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ቃል ገብተዋል ።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
🖤 ቅዱስ ሲኖዶስ በነነዌ ጾም የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ
መግለጫ ሰጠ
•••••••••
በጾመ ነነዌ የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን መግለጫ ሰጥቷል፤ በዚህም የምእመናን ድርሻ ምን እንደሆነ ተገልጿል፡፡
•••
ሁሉም ምእመናን እና ምእመናት በጾመ ነነዌ በሦስቱም ቀናት ጥቁር ልብስ መልበስ፣ በጸሎት መርሐ ግብሩ ተገኝቶ ጸሎት መጸለይ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና የአባቶችን መልእክት ሰምቶ መተግበር እንደሚገባው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡
•••
የጸሎት መርሐ ግብሩም ጠዋት ኪዳን እና ምሕላ፣ ቅዳሴ፣ የሰርክ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር እንዲሁም ማታ የቤተሰብ ጸሎት ናቸው፡፡
•••
በመጨረሻም ምእመናን ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱበት ጊዜ ለጸሎት ከሚያስፈልጉ መጽሐፍት ውጪ ሌላም ምንም ዓይነት መፈክር ይዞ መምጣት የማይቻል መሆኑን አስረድተዋል።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/24 22:27:44
Back to Top
HTML Embed Code: