Telegram Web Link
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጾመ ነነዌን በማስመልከት ጾምና ጸሎት አወጀ።

ቅዱስ ሲኖዶስ አዋጁን ያስተላለፈው ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት በሰጠው መግለጫ ነው።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በቤተክርስቲያኗ በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮች በጣሰ ሁኔታ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ ጥር 18 ቃለ ውግዘት ታላልፎ እንደነበር ገልጿል።

" ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ አልቻሉም " ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ ከዚህም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ነው ብሏል።

እንዲሁም የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ፣ ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ መንግሥት ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር አልቻለም ያለ ሲሆን " ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ተረድተናል " ሲል አሳውቋል።

በዚህም " ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን #ጥቁር_ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ " ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አስተላልፏል።

" ጥቁር ልብስ  የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው " ሲልም አክሏል።
(ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክስ በመመስረት ሂደት ላይ መሆኗን አሳወቀች።

ቤተክርስቲያኗ ይህን ያሳወቀችው ዛሬ ከህግ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በሰጠችው መግለጫ ነው።

ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ለመመስረት ጥያቄ የቀርበ ሲሆን ክስ የመመስረት ሂደት ጊዜ ስለሚፈልግ ጊዜያዊ እግድ እንዲሰጥ ጥያቄ መቅርቡ ታውቋል።

ክሱ / እግዱ የቀረበው በልደታ ምድብ ሁለተኛ መሰረታዊ መብቶች እና ነፃነቶች ምድብ ችሎት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ክስ የቀረበባቸው ተጠሪዎች በቀድሞ ስማቸው 1ኛ. አባ ሳዊሮስ ፣ 2ኛ. አባ ኤዎስጣቴዎስ ፣ 3ኛ. አባ ዜና ማርቆስ ፤ እንዲሁም ኤጲስቆጶሳት ተብለው ተሹመዋል ተብሎ መግለጫ የተሰጠባቸው 25 ግለሰቦች ያሉበት መሆኑን ቤተክርስቲያኗ ገልጻለች።

አንድ ግለሰብ ተፀፅተው ስለተመለሱ ክሱ እንደማያካትታቸው ቤተክርስቲያን ጠቁማለች።

በተጨማሪ ፤ ጠበቃ ኃይለሚካኤል ከፈሌ ተጠሪ ሆነው የተካተቱ መሆኑ ተገልጿል።

ሌሎች ፦
- የፌዴራል ፖሊስ
- የኦሮሚያ ክልል መንግስት
- የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ የክሱ / የአቤቱታው አካል መሆናቸውን ቤተክርስቲያን አሳውቃለች።

ክስ የቀረበው ለምንድነው ? ቤተክርስቲያኗ ክስ ያቀረበችው ህጋዊ ሰውነቷን የጣሰ ህገወጥ ድርጊት ስለተፈፀመ፣ በአገልጋዮች አባቶች ፣ ካህናት እና ምዕመናን ላይ በደል ስለተፈፀመ መሆኑ ገልጻለች።

ቤተክርስቲያኗ ህገወጥ ብላ በይፋ የፈረጀችው ቡድን ወደ ቤተክርስቲያን ቅጥር እንዳይደርስ፣ ንብረት እንዳያንቀሳቅስ፣ የቤተክርስቲያኗ ጥቅምና መብት እንዲከበር ይህ ክስ በዝርዝር እስኪታይ የዕግድ ትዕዛዝ እንዲተላለፍ ለፍርድ ቤት ጠይቃለች።

ተጨማሪ መረጃዎች ይኖራሉ።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ልዩ መረጃ!

ብፁዕ አቡነ ያሬድ ታሠሩ!

ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

ብፁዕ አቡነ ያሬድ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዛሬ ምሽት 3:45 አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሚገኘው መንበረ ጵጵስናቸው ተወስደው መታሠራቸው ተገለጸ።

ብፁዕነታቸው በዛሬው ዕለት ማምሻውን ከአዲስ አበባ ወደ ሀገረ ስብከታቸው መድረሳቸውን ተ.ሚ.ማ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ታምራት ወልዴ ቤትም መከበቡንና እስካሁን ያለውን ሁኔታ ማወቅ እንዳልቻሉም ነው ምንጮቻችን የገለጹት።

ሕገ ወጡ ቡድን ሾሜዋለሁ ያለው ግለሰብ በነገው ዕለት እንደሚመጣ የተነገረ ቢሆንም ምእመናኑ ሕጋዊውን ቅዱስ ሲኖዶስን ብቻ እንደሚቀበሉም ገልጸዋል።

#Ethiopia
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa


@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ብፁዕ አቡነ ያሬድ በአሰላ መቆየት አይችሉም ተብለው በዚህ ሰዓት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#Update

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ዛሬ ምሽት 3:45 አሰላ ከተማ ደብረ ምጽላል ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከሚገኘው መንበረ ጵጵስናቸው ተወስደው ታስረው እንደነበር ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

ብፁዕነታቸው በዛሬው ዕለት ማምሻውን ነበር ከአዲስ አበባ ወደ ሀገረ ስብከታቸው መድረሳቸው የተጠቆመው።

ዘግየት ብለው የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን ባወጡት መረጃ ብፁዕ አቡነ ያሬድ በአሰላ #መቆየት_አይችሉም ተብለው በዚህ ሰዓት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ መደረጉን አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ " በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሻሸመኔ ከተማ በሕገ ወጥ የተሾመው ቡድን መንበረ ጵጵስና እና ቤተ ክርስቲያን ሰብረን እንገባለን በማለት በምእመናን ላይ ስጋት ተፈጥሯል " ሲሉ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዲዮ፣ አማሮ፣ ቡርጂና ምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተናግረዋል።

ከሰሞኑን የሀገረ ስብከቱ አገልጋዮች ያለምክንያት እየታሰሩ ነው ያሉት ብፁዕነታቸው ይህንንም ለሚመለከተው የዞን ፀጥታ አካል ለማሳወቅና ጥበቃ እንዲያደርጉ ብንደውልም፣ መልእክት ብንጽፍም ሊመልሱልን አልቻሉም ብለዋል።

በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ለኦሮምያ ክልል የሚመለከታቸው አካላት በተለይም ጥበቃና ከለላን በተመለከተ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አስቀድሞ ደብዳቤ ቢጻፍም ምንም አይነት የቃልም ሆነ የተግባር መልስ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው " መንግሥት በሕገ ወጡ ቡድን የሚደረገውን ድርጊት ማስቆም ካልቻለ ምእመናን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ለሚፈጠረው ችግር ኃላፊነቱን ይወስዳል " ብለዋል። ምእመናን ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲጠብቁም መልእክት አስተላልፈዋል።

tikvahethiopia
@EotcLibilery
Forwarded from የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ("የአምር አቡክሙ ሰማያዊ ዘትፈቅዱ ዘእንበለ ትስአልዎ።" ማቴ. ፮፡፰)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#Update

የ ' ፌደራሉ መንግሥት ' በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች።

ቤተክርስቲያኗ በሻሸመኔ ከተማ አንድ ሰው በፀጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደሉን ገለፃለች።

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጉዳዩን በተመለከተ ፤ " እየሞተ ያለው ሕዝብ ነው ቅጠል አይደለም እየተበጠሰ የሚወድቀው ፤ #ይሄ_ፖለቲካ ነው። የፌደራል መንግሥት በሻሸመኔ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ለሚደረገው ግድያ ኃላፊነቱን ሊወጣና ሊያስቆም ይገባል። " ብለዋል።

በሻሸመኔ ምንድነው የሆነ ?

ተ/ሚ/ማ የተባለው የቤተክርስቲያኗ ሚዲያ " በዛሬው ዕለት ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ሻሸመኔ ይመጣል መባሉን ተከትሎ ጠዋት ሁለት (2:00) ሰዓት ላይ ሥርዓተ ቅዳሴ እንደተፈጸመ ሕዝቡን ለመጥራት በከተማዋ ያሉ አድባራት ደወል ደውለዋል " ሲል ገልጿል።

" ጥሪው ሰምቶ ሁሉም ምእመን ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ ይጀምል ፤ በዚህ ጊዜ ወደ ሻሸመኔ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሔዱ ምእመናን የቤተክርስቲያኑ በር በመዘጋቱ ከውጪ ቆመው ነበር።

በእንዲህ ሁኔታ ውስጥ እያለ የከተማው ፖሊስ ሕዝቡን ለመበተን ተኩስ ከፍያል ፤ እስካሁን ድረስ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ሰማዕትነትን ተቀብሏል፤ በውል ያልታወቀ ሰውም በጥይት ተመቷል " ሲል የነበረውን ሁኔታ አስረድቷል።

በሌላ በኩል ቤተክርስቲያኗ ፤ " ትናንትና ሌሊት ሊቀ ጳጳሷን አስሮ ከከተማ ያባረረው ኃይል   በአርሲ ሀገረ ስብከት መናገሻ አሰላ ኦርቶዶክሳውያንን እያሠረ  ይገኛል " ብላለች።

በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ያሉትም እንዲወጡ እየተነገራቸውና ያ የማይሆን ከሆነ የኃይል እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ተዝቶባቸዋል ብላለች።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ያሉት ሁኔታዎች እየከረሩ መጥተው ለሰው ህይወት #መጥፋት ምክንያት እስከመሆን የደረሱ ቢሆንም መንግስት እስካሁን ስለጉዳዩ ምንም ያለው ነገር የለም።

ቤተክርስቲያን በበኩሏ ለዚህ ሁሉ መሆን ህገወጥ ሲመት አከናውነዋል ፤ ተቀብለዋል ባለቻቸው ግለሰቦች እና የመንግስት ተቋማት ላይ ክስ ለመመስረት በሂደት ላይ ነች።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በሻሸመኔ ከተማ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት ደረሰ!

በሻሸመኔ ከተማ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ኦርቶዶክሳውያን ቁጥር ሁለት የደረሰ ሲሆን በአራቱ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለጸ።

አብያተ  ክርስቲያናት ውስጥ ያሉት ምእመናን እስካሁን ድረስ በቅጽር ግቢ ውስጥ እንዳሉ ናቸው። ነገር ግን አሁን ላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣውን የጸጥታ ኃይል አባላት በዱላ እያባረሩ ይገኛሉ።

የከተማዋ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አካላት ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ውጪ ላሉት የከተማዋ ነዋሪዎች ነጠላ በማደል ሻሸመኔ ስታዲዮም ተገኝተው ሕገ ወጡን ቡድን እንዲቀበሉ እያስተባበሩ ያሉ ሲሆን በመኪና ከተማውን እየዞሩ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በዚህ ሰዓት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከሻሸመኔ እስከ አርሲ ነገሌ ድረስ ያለውን ቦታ ተቆጣጥሯል።

ምንጭ: ተሚማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ፕሮፌሰር ቄስ ዶ/ር ጄሪ ፒላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የሚነኩ እና አንድነቷን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሁኔታዎች በእጅጉ እንደሚያሳስቧቸው ገለጹ።

“የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት እና ጥንታዊ ከሆኑ አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ ነች፤ ይህች ቤተ ክርስቲያን ስለሰላምና አንድነት የደም ዋጋ ከፍላለች” ብለዋል። የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት በአሁኑ ሰዓት ከጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተነጠለውን ቡድንም እንደሚቃወመው ገልጸዋል።

ዋና ጸሐፊው አክለውም "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕጋዊ እውቅና ያገኘች የሃይማኖት ተቋም እንደመሆኗ በውስጥ ሕጓና በቀኖናዋ እንድትመራ በመፍቀድ በምእመናን መካከል አንድነትና ሰላም እንዲሰፍን የምታደርገውን ጥረት እንዲደግፉ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች በሙሉ እንጠይቃለን።" ሲሉ አሳስበዋል።

የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን ለፍትህ፣ ለእርቅ፣ ለአንድነትና ለሀገሪቱ ሰላም ይጸልያል ብለዋል።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሰበር ዜና

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ከኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ አዋጅ

በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረው አስቸኳይ ምልዐተ ጉባኤ በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና የብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ በሚል በሕገ ወጥነት በቀድሞ ስማቸው አባ ሳዊሮስ የተባሉ ግለሰብ መሪነት ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ በተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግሥት በሚመራቸው ቦታዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ አህጉረ ስብከት የሆኑትን ሥርዓተ አምልኮዋን የምትፈጽምባቸው በየመዋቅሩ የሚገኙ አስተዳደር ቢሮዎችን  ከሕግ አግባብ ውጭ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ግለሰቦችን በማካተት በመንግሥት ልዩ ኃይል ድጋፍ በመውረር እና በመስበር የሕግ አግባብነት በሌላቸው  እንዲሁም መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው በማሸግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ እየተፈጸመባት የሚገኝ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ለመረዳት ችሏል፡፡
መንግሥትም ሰላም እና ደህንነትን ከማስጠበቅ ባለፈ የሕይወት እና የአካል ደህንነት መብትን እንዲሁም የመንቀሳቀስ መብትን በመገደብ ያለአግባብ ታግተው መቆየታቸውን ከሊቃነ ጳጳሳት ውስጥ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን ከዚህ ቀደም መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ ድርጊታቸውም ሳይታቀቡ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑትን ብጹዕ አቡነ ያሬድን በሕገ ወጥ መልኩ የዜግነት መብታቸው ተጥሶ በደረቅ ሌሊት በማሰር እና በማዋከብ ከሀገረ ስብከታቸው ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን እንዲሁም የተለያዩ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትን ወደየ አህጉረ ስብከታቸው እንዳይሄዱ ማስፈራሪያ በመላክ የቤተ ክርስቲያችንን ክብር እና ልዕልና እጅጉን የሚጎዳ እና አሳዛኝ ድርጊት እየተፈጸመባት ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የየሀገረ ስብከት ሥራ አኪያጆችንና ሠራተኞችን፤ አገልጋይ ካህናትንና ምእመናን በሕገ ወጥ መልኩ በማሰር እንደ መንግሥት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ባለመወጣቱ ቤተ ክርስቲያናችን እጅጉን አዝናለች፡፡

ከዚህም አልፎ መንግሥትም በቤተ ክርስቲያችን በኩል በተደጋጋሚ የተሰጠውን ማሳሰቢያ ችላ በማለቱ ምክንያት በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ ሕገ ወጦቹ መንግሥትን ተገን በማድረግ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሕገ ወጥ መልኩ ወረራ ለመፈጸም ባደረጉት እንቅስቃሴ ቤተ ክርስቲያንችንን ለመጠበቅ በወጡ ምእመናን ላይ ፖሊስ በወሰደው እርምጃ ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የአደባባይ የግድያ ወንጀል ተፈጽሟል፡፡ ሌሎች በቁጥር ያልታወቁ ምእመናንም ላይ ከፍተኛ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ 

ይህንንም ሕገ ወጥ ተግባር በተመለከተ ተገቢውን ሕጋዊ የሰላም እና የደህንነት ከለላ እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት በተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቤተ ክርስቲያናችን ብትሰጥም ይህንን ማሳሰቢያ ወደጎን በመተው መንግሥት ሕገ ወጡን ቡድን በመደገፍ እና በማስፈጸም ከላይ የተገለጹትን አሳዛኝ ድርጊቶች በይፋ በአደባባይ ፈጽሟል፡፡

ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በጠራው አስቸኳይ ጉባዔ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡

1. በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ የክፍል ኃላፊዎች፤ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ላይ የተፈጸመውንና እና እየተፈጸመ ያለውን ሕገ ወጥ እስር እና ወከባ ቅዱስ ሲኖዶስ በፅኑ አውግዟል፤
2. በጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፤ ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የወጡት ምዕመናን ላይ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ የተፈጸመው ሕገ ወጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የተፈጸመው አሰቃቂ የሞት ድርጊትን ፍጹም ታወግዛለች፤ ተገቢውን ሲኖዶሳዊ እና ሃይማኖታዊ ጸሎት በማድረግ በሁሉም አጥቢያ ሥርዓተ ፍትሐት እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3. ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባስተላለፈው ውሳኔ እና በሰጠው መግለጫ መላው የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታዮች ጾመ ነነዌን ሙሉ የሱባዔ ጊዜ በማድረግ ጥቁር ልብስ ያለውን ትርጓሜ በመግለጥ እንድንሰነብት መግለጫ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
3.1. ለዚህም ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 3 ቀናት በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ የምትገኙ ማናቸውም ካህናት እና ምዕመናን ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ በየአብያተ ክርስቲያናት እና በገዳማት ያለውን ሥርዓተ ጸሎት እንድትመሩ እና እንድትከታተሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.2. በየትኛውም እንቅስቃሴ ይህንን ጥቁር ልብስ በመልበስ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ንቁ በመሆን እንድትፈጽሙ፤ ሆኖም ግን ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዓለም አቀፍ የጸሎትና የምህላ መርሐ ግብር ካወጀበት ቀን በኃላ በተለያዩ ከተሞች የጥቁር ልብስን ሆነ ተብሎ ከገበያ እንዲወጣ እየተደረገ መሆኑን በመረዳታችን ምዕመናን ያላችሁን ተመሳሳይ አልባሳት በመጠቀም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን በእንቅስቃሴያችሁ ሁሉ እንድትፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.3. በነዚህ ቀናት ውስጥ አገልግሎቱ በድምጽ ማጉያ እንዲከናወን እና የሙሉ ጊዜ ሆኖ በሰባቱ የጸሎት ሰዓታት እየተጠበቀ በተመሳሳይ ሰዓታት ለአምስት ደቂቃ ያህል በማያቋርጥ ደወል በመደወል የማስተጋባት ሥራ እንዲሠራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
3.4. ይህንንም የየአህጉረ ስብከት፤ የወረዳ ቤተ ክህነት እና የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሰበካ ጉባኤያት በመከታተል እንድታስፈጽሙ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
3.5. የአኃት አብያተ ክርስቲያናት፤ የኦርቶዶክስ ዓለም፤ እውነቱን የምታውቁና የምትደግፉ ማናቸውም ኃይማኖታዊም ሆነ ማህበራዊ ተቋማት እና ግለሰቦች የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ በመደገፍ በአንድነት ትቆሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላፋለን፡፡
4. በነዚህ የጸሎትና የምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ እንደሆነ
4.1. በየካቲት 5 ቀን 2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ በየአጥብያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠዋቱ 1፡30 ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተፈጸመ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ሁሉም ገዳማት፣ አድባራት እና አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት ደወል በመደወል ምእመናን በሙሉ እስከ ጠዋቱ 2፡30 ድረስ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከየአጥቢያው በመነሳት የጥምቀተ ባህር ወይም የመስቀል አደባባይ ላይ ታቦተ ሕጉን በማክበር፤ በማጀብ በዝማሬ እና በእልልታ በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4.2. የዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናሳውቃችሁ መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡ 
5. ማንኛውም የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ቤተ ክርስቲያን ያዘዘችውን ሰላማዊ ጥያቄ በሚከወንበት ማንኛውም የአገልግሎት ጊዜ ተግባራቱ ሰላማዊ መሆናቸውን በመገንዘብ ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት አውቆ እንዲያስፈጽም ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፤

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ዳሰነች ወረዳ በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት በዳሰነችኛ ቋንቋ ቅዱስ ወንጌልን ሲማሩ ከነበሩ ወገኖች መካከል 1182 አዳዲስ አማንያን ብጹዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና ብጹዕ አቡነ ኤልያስ የስዊድንና እስካንዲናቪያን ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ በተገኙበት በኦሞ መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ጥምቀት ተፈጽሞላቸው የቅድስት ሥላሴን ልጅነት በማግኘት የቤተ ክርስቲያን አባላት ሆነዋል፡፡

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ኦሮሚያን የኦርቶዶክሳውያን እስርቤት ማድረጉ ቀጥሏል።

በአዲስ አበባ አጎራባች ዞኖች በይበልጠጥም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሰበታ መሥመር የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን በአፈሳ መልክ መጋዙ ቀጥሏል። በጅማ እና ሻሸመኔ በምዕራብ አርሲ ወረዳዎች በምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ የወረዳ ሊቃነ ካህናት አባቶች ቀሳውስት ዲያቆናት በጅምላ እየታሠሩ መሆኑ መረጃዎች እየደረሱን ነው።

ትላንት የታሰሩ ምእመናን ምግብና ውሃ እንዳያገኙ ተደርገዋል። የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እስካሁን ዝምታን መርጠዋል።

ምንጭ: EOTC TV
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"ደረታችንን ለጥይት ሰጥተን በረሃብ አንበገርም" - የአርሲ ነገሌ ምእመናን

ለሕገ ወጡ ቡድን ሽፋን እየሰጠ የሚገኘው የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የጸጥታ ኃይል ከዐርብ ምሽት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያናቸውን ሲጠብቁ ላደሩ ምእመናን ምግብ እንዳይገባ ከልክሏል።

ከዚህም ባለፈ ከቤተ ክርስቲያኑን ለቅቀው ወጥተው ሕገ ወጡን ቡድን እንዲቀበሉ ለማግባባት ቢሞክርም ደረታችንን ለጥይት ሰጥተን በረሃብ አንበገርም የሚል መልስ በመስጠት በአቋማቸው ጸንተዋል።

ምንጭ: ተሚማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/25 00:30:31
Back to Top
HTML Embed Code: