Telegram Web Link
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ ተሰጠ ።
(ኢኦተቤ ቴቪ ጥር ፩፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ)
መግለጫውን የሠጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት; ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ : በመንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።

ቅዱስነታቸው ዛሬ ማለዳ በተሰማው ሕገ ወጥ "ሢመተ ጳጳሳት" ጉዳይ በሰጡት መግለጫ ጉዳዩ ከቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ውጪ በሕገወጥነት የተከናወነ መሆኑን በመግለጽ :-
1. በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአስቸኳይ ወደ መንበረ ፓትርያርክ እንዲመጡ ጥሪ ቀርቧል።
2. መንግሥት ክስተቱ በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት ተመልክቶ በጉዳዩ ላይ ሕጋዊ ሓላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
3. ምዕመናን ቤተክርስቲያንን ከመቸውም ጊዜ በላይ በንቃት እንዲጠብቁ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።
የመግለጫውን ሙሉ ቃል በኢትዮ ሣት EOTC TV እንዲሁም ከታች በተዘረዘሩት የዲጂታል አማራጮች መከታተል ይቻላል።
EOTC TV
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from 𝗨𝘁𝗼𝗽. (ባሕራን)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM


EOITC TV | ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ የተላለፈ መልእክት።

†                      †                      †
Audio


EOITC TV | ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ የተላለፈ መልእክት።

†                      †                      †
ስብስብ ስም ዝርዝር

የውሸት የተሾሙት ዝርዝር
1. አባ ተክለ ሃይማኖት ።።።።።።። የቀድሞ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ
2. አባ ገብረ እግዚአብሔር ።።።።።። የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት አስተዳዳሪ
3. አባ ሽኖዳ ።።።።።።።።። አለም ገና ኢየሱስ አስተዳዳሪ
4. አባ ወልደ ጊዮርጊስ ።።።።።።። ወለቴ ዮሐንስ አስተዳዳሪ
5. አባ ገብረ ኢየሱስ ።።።።።። አለም ገና ሚካኤል አስተዳዳሪ
6. አባ ገብረማርያም ነጋሳ ።።።።። የኦሮምያ ቤተ ክህነት መስራች
7. አባ ጳውሎስ ከበደ ።።።።። የሐረር ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የነበረና በተሐድሶነት የተባረረ
8. አባ ጸጋ ዘአብ አዱኛ ።።።።።።። የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መጽሐፍ መምህር

ይቀጥላል. .....
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምን አሉ ?

ብፁዕ አቡነ አብርሃም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፦

" በፈተና የሚያጸናው ሁል ጊዜ ፈተናዎችን እያሳለፈ ለዘመናት ሲጠብቃት የነበረ እግዚአብሔር ዛሬም ጥበቃውና መግቦቱ እንደማይለያት ሙሉ እምነት አለን ፣ በደረሰው ክስተትም እጅግ አዝነናል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ታዝናለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከ3ሺ ዘመን በላይ የራሷን አንድነት ከማስጠበቅ አልፋ የሀገርን አንድነት ስታስጠብቅ ለሰው ልጆች አንድነት ትልቁን ድርሻ በመውሰድ ስትሠራ የኖረች አሁንም ያለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ነች።

ይህንን አንድነቷን የሚንድ ሕጋዊ ሰውነቷን የሚጥስ አላስፈላጊ ክስተት ተፈፅሟል።

በዚህም ቅዱስ ፓትርያርኩ በአስተላለፉት ጥሪ መሠረት ከሀገር ውስጥ ከሀገር ውጭ የምትገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከነገው ዕለት ጀምሮ የቅዱስነታቸውን ጥሪ በመቀበል እንድትገኙ።

የተፈጠረው ችግር በዝርዝርና በጥናት ቅዱስ ሲኖዶስ አይቶ የመጨረሻውን ውሳኔ እስከሚሰጥበት ጊዜ ድረስ ምእመናንና አገልጋዮች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሁላችሁም በየአላችሁበት ቤተ ክርስቲያንን ጠብቁ።

ተመሳስለውና የሌለ ሐሳብ እያቀረቡ ሕዝብን ከሚለያዩ ሠዎች እንድትጠበቁና እንድትጠብቁ በጽናት፣ በትእግስትና በፍቅር ሕጋዊ በሆነ ነገር ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን እንድትጠብቋት በአንድነቷ የተረከብናትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአንድነቷ ለነገው ትውልድ ለማስረከብ የእያንዳንዳችንን ድርሻ እንድንወጣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። "

(ከአ/አ ሀገረስብከት)

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
" ክሰቱት በሀገር ላይ ጭምር የሚያስከትለውን ጉዳት በመመልከት መንግስት ሕጋዊ ኃላፊነቱን ይወጣ " - የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ ከፍተኛ የዶግማና ቀኖና ጥሰት በመፈፀም ተፈፅሟል ካለችው ህገወጥ የ " ጳጳሳት " ሹመት ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግስት የቤተክርስቲያኗን ህጋዊ ሰውነት በማስጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አስቸኳይ ጥሪ አቅርባለች።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም ፤ " ሕጋዊ ሰውነቷ የተረጋገጠ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በሕጋዊ ሰውነቷ የመጠበቅ የማስጠበቅ ኃላፊነቱ የመንግሥት ነው " ብለዋል።

የተፈጸመው ድርጊት " ግፍ ነው " ሲሉ የገለፁት ብፁዕነታቸው " መንግሥት ይሄንን ተመልክቶ የቤተ ክርስቲያኗን ሉዓላዊነት #በመጠበቅ እና #በማስጠበቅ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክስተቱ #በሀገር ላይ ጭምር ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን በመጠቆም መንግስት በጉዳዩ ላይ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርባለች።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/25 18:13:36
Back to Top
HTML Embed Code: