Telegram Web Link
+++ ከጵጵስና ሽሽት +++

ረዣዥሞቹ ወንድማማቾች ተብለው የሚጠሩት አውሳብዮስ ፣ አሞንዮስ ፣ ዲዮስቆሮስና አውሳሚዮስ በቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ላይ በብዙ መልኩ ይጠቀሳሉ። "አውሳብዮስ አሞንዮስ ተናግረውታል" የሚል ማስረጃ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትርጓሜ መጻሕፍት ላይ ማግኘት የተለመደ ነው። እነዚህ ቁመታምና መልከ መልካም የነበሩት ወንድማማቾች ሕይወታቸውን ለቤተ ክርስቲያን የሠጡ የዘመኑን ፍልስፍና ተምረው በሃይማኖት እውቀት የመጠቁ ነበሩ። የእስክንድርያ ትምህርት ቤት ቀደምት ሊቃውንትን መጻሕፍትም እጅግ ያነበቡ ፣ ከሊቃውንት ተርታ የሚመደቡ የታሪክና የትርጓሜ መምህራን ነበሩ።

ከእነዚህ ወንድማማቾች መካከል አንዱ አባ አሞንዮስ ነው። ይህ አባት ከእውቀት ጋር ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ሕይወት የነበረው ነበር። ለዚህም ማሳያ የሚሆነን በዚያን ዘመን የዓለም ማእከል ወደነበረችውን ሮም በሔደበት ወቅት ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ አብያተ ክርስቲያናት ውጪ አንድም ነገር ሳይጎበኝ መመለሱ ነው።

አባ አሞንዮስ በበአቱ ተወስኖ በሚኖርባት ሄርሞፖሊስ የምትባል ከተማ የነበሩ ምእመናን መንፈሳዊ ሕይወቱንና ጥልቅ እውቀቱን ተመልክተው ጳጳስ ሆኖ እንዲሾምላቸው ተመኙ። ስለዚህም ወደ እስክንድርያው ፓትርያርክ ጢሞቴዎስ ሔደው አመለከቱ። ፓትርያርኩ የአባ አሞንን መንፈሳዊነትና እውቀት በመረዳት ጳጳስ አድርጎ ሊሾምላቸው ፈቀደ። ምእመናኑ ተደስተው ወደ አባ አሞንዮስ እየገሰገሱ ደረሱ። ወደ በአቱ ሲገቡ ግን ያጋጠማቸው ነገር እጅግ አስደንጋጭ ነበር።

አባ አሞንዮስ ሕዝቡ ወደ ፓትርያርኩ ሔደው ጳጳስ አድርገው ሊያሾሙት እንደሆነ ሰምቶ ጳጳስ ሆኖ ላለመሾም የቀኝ ጆሮውን ቆርጦት ነበር። ይህንን ያደረገው በሥርዓቱ መሠረት ጳጳስ የሚሆነው ለአገልግሎት የሚከለክል የአካል ጉድለት የሌለበት ሰው እንደሆነ ስለሚያውቅና ምእመናኑም "ጳጳሳቸው ጆሮው ቆራጣ ነውእንዳይባሉ ፈርተው ይተዉኛል" ብሎ አስቦ ነበር።

ይህን ያዩት ምእመናን በሁኔታው ቢደነግጡም ይህን የመሰለ አባት ማጣት ስላልፈለጉ ወደ ፓትርያርኩ ተመለሱ። ነገሩን የሰሙት ፓትርያርክ ጢሞቴዎስ ግን "ይህን ሥርዓት አይሁድ ይጠብቁት እኔ ግን አፍንጫውም ቢቆረጥ እሾመዋለሁ" አሉ።

ምእመናኑ ደስ ብሏቸው ወደ አባ አሞንዮስ ተመለሱ። አባ አሞንዮስ በአቱን ጥሎ ሮጠ። ምእመናኑ ተከታትለው ያዙት። እየተንፈራገጠ እያለቀሰ ወደ ፓትርያርኩ ሊወስዱት ሞከሩ። አባ አሞንዮስ ግን "እባካችሁ ተዉኝ ግድ ብላችሁ ብትወስዱኝና ብታሾሙኝ ምላሴን እቆርጣለሁ" አላቸው። ይህንን ከማድረግ እንደማይመለስ ስለተረዱ ምእመናኑ እያዘኑ ተዉት።

መጽሐፈ መነኮሳት ሹመትና ክብር እንደ ጥላ ነው ይላል። የሚከተሉትን ይሸሻል የሚሸሹትን ይከተላል። በቤተ ክርስቲያን ሓላፊነት እንጂ ሥልጣን ባይኖርም ቤተ ክርስቲያን ግን ከትናንት እስከ ዛሬ መሾምን እንደ ጦር የሚፈሩና በግድ እያለቀሱ የሚሾሙ አባቶች ነበሯት ፣ ዛሬም አሏት። እያለቀሱ የተሾሙትም የቤተ ክርስቲያንን ዕንባ ይጠርጋሉ።

ይህን ታሪክ የጻፍሁት "ዛሬ ምን አባት አለና ..." የሚለውን የተለመደ የስድብ ዶፍ ለመቆስቆስ አይደለም። ይህን ማድረግ ለአሕዛብ መሳለቂያ ከመሆን በቀር ምንም አይጠቅምም። "ለቤተ ክርስቲያን ቅን መሪን የሚሠጥ" እያልን በማለዳ ደጅ የምንጠናው አምላካችን ወደ መንፈሳዊ ማዕረግ ሊመጡ የታሰቡትን የቀደሙትን አበው መንፈስ እንዲያድልልን የምንጸልይበት ብርቱ ጊዜ ግን አሁን ነው።

አንድ ገጣሚ እንዳለው "ቤተ ክርስቲያን እንደ ኦሪቱ ዘመን ምነው በድንኳን በሆነችና ምነው ጠቅልለን ይዘናት በሸሸን" የሚያሰኝ ጊዜ ላይ ነን። ለምናየው ክፉ ነገር የኛን ኃጢአት ምክንያት ብናደርግና ብናነባ የሚሻልበት ጊዜ ነው። ለአንዱ ደግ መሪ ለሙሴ ሕዝቡን አጥፍቼ ሌላ ሕዝብ ልቀይርልህ ያለ ፈጣሪ ሕዝቡ ቅን ሆኖ ቢገኝ ደግሞ መሪ መቀየር የሚሣነው አይምሰለን። መሰዳደቡን ትተን ሃይማኖታቸው የቀና ደገኛ አባቶችን እንዲሾምልን እንጸልይ።
(ይ ዲ "ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን)

"በውስጥሸ ሰላም ይሁን አልሁ ፣ ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ። "
(መዝ 122:9)

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ሰኔ 24 2008 ዓ ም
ከለን ጀርመን

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በዚህ ደረጃ ወርዳችሁ ከምናያችሁ ብትሞቱ ይሻላችሁ ነበር።
#የ26ቱ_ተሿሚወች_የቀድሞ_ስም እና የጵጵስና ስም እንዲሁም የተመደቡበት ሀገረ ስብከት
1. ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ነጋሳ አቡነ ገብርኤል ምእራብ ወለጋ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
2. ቆሞስ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ አቡነ ባስልዮስ የድሬዳዋ ሐገረ ስብከት ጳጳስ
3. ቆሞስ አባ ገብርኤል ወልደ ዮሐንስ አቡነ ጢሞቴዎስ የጉራጌ ሶዶ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
4. ቆሞስ አባ አባ ገብረ እግዚአብሔር ታደለ አቡነ ጳውሎስ የምእራብ አሩሲ ሀገረ ስብከት ጳጳስ
5. ቆሞስ አባ ሚካኤል ገብረ ማርያም አቡነ ኤልሳዕ የከንባታ ሀገረ ስብከት ጳጳስ
6. ቆሞስ አባ ኃይሉ እንዳለ አቡነ ገሪማ የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ
7. ቆሞስ አባ ተክለ ማርያም ስሜ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጉጂ ሊበን ሀገረ ስብከት ጳጳስ
8. ቆሞስ አባ ኃይለ ኢየሱስ መንግሥቱ አቡነ እዝራ የከፋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ

9. ቆሞስ አባወልደ ኢየሱስ ኢፋ አቡነ ኢያሱ የቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
10. ቆሞስ አባ ጳውሎስ ከበደ አቡነ ዳንኤል የሀድያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
11.ቆሞስ አባ ኃልለ ኢየሱስ ተስፋዬ አቡነ በርሱማ የምስራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
12. ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ ገለታ አቡነ ሚናስ የሆሩ ጉድሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
13.ቆሞስ አባ ፀጋ ዘአብ አዱኛ አቡነ ኤጲፋንዮስ የምሁር ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ
14. ቆሞስ አባ ኃይለ ማርያም ጌታቸው አቡነ አቤል የምእራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
15. ቆሞስ አባ ወልደ ጊዮርጊስ ኃይለ ሚካኤል አቡነ በርተሎሜዎስም የከሚሴ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
16. ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ገብሬ አቡነ ራጉኤል የባሌ ሀገረ ስብከት ረዳት ሊቀ ጳጳስ
17. ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ገብረ ማርያም አቡነ ዑራኤል የጎፋ ባስኬቶ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
18. ቆሞስ አባ ኃይለ ሚካኤል ንጉሴ አቡነ አኖሪዮስ የጊኒር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
19. ቆሞስ አባ አብርሃም መስቀሌ አቡነ ኒቆዲሞስ የዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
20. ቆሞስ አባ ንዋየ ሥላሴ አክሊሉ አቡነ ሀብተ ማርያም የምእራብ ጉጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
21. ቆሞስ አባ ኪዳነ ማርያም ቶሎሳ አቡነ ተክለ ሐዋርያት የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
22. ቆሞስ አባ ወልደ ማርያም ፀጋ አቡነ አብሳዲ የቦረና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
23. ቆሞስ አባ አምደ ሚካኤል ኃይሌ አቡነ መርቆሬዎስ የአሩሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
24. ቆሞስ አባ መርሐ ጽድቅ ኃይለ ማርያም አቡነ ደቅስዮስ የጌዲኦ ቡርጂ አማሮ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
25. ቆሞስ አባ ሞገስ ኃይለ ማርያም አቡነ ኤፍሬም የመናገሻ ቅድስት ማርያም ጋራ መድኃኒዓለም እና ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የበላይ ኃላፊ ጳጳስ ።
26 . ቆሞስ አባ ገብረ ኢየሱስ ንጉሴ አቡነ አለልአዛር የቡኖ በደሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
እንግዲህ ለአቀባበል መዘጋጀት ነው
🙄😜

👉#ወላዲተ_አምላክን_ብትሞቱ_ይሻላል
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
"ጌታችን በመርከብ ውስጥ ሕዝቡ በሐይቅ ውስጥ"

Size:-22.7MB
Length:-1:39:03

💠ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን 💠

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ቅዱስ ሲኖዶስ ህገወጥ ነው ያለውና ቤተክርስቲያንን ያሳዘነው ፤ ምዕመኑንም ያስደናገጠው የ " ጳጳሳት " ሹሙት ምንድነበር ?

ትላንት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የሆነ የዶግማና ቀኖና ጥሰት ተፈፅሞ ጳጳሳትን የመሾም ተግባር መከናወኑን መግለጿ ይታወሳል።

ይኸው ሲመተ ጳጳሳት ፤ #ከቅዱስ_ሲኖዶስ እውቅና ውጭ #በሕገወጥ መልኩ የተከናወነ መሆኑን ነው ቤተክርስቲያን ያሳወቀችው።

ድርጊቱ በርካታ ምእመናንንም ያስደነገጠ ነበር።

ቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ የሆነ የዶግማና ቀኖና ጥሰት በተፈፀመበት መልኩ ተከናውኗል ያለችውን ሹመት ማነው ያካሄደው ?

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-23-2
ኢ-ቀኖናዊ በሆነ መልኩ የተፈጸመውን ''ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት'' አስመልክቶ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የአቋም መግለጫ አወጣ
በምስካዬ ኅዙናን የሚገኘው "የአባ" ሳዊሮስ ቢሮ እና መገልገያ ቤቶች ታሽገዋል።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሚዛን ቴፒ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ቢሮ መታሸጉ ተገለጸ።

ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

በነ 'አባ' ሳዊሮስ ሕገ ወጥ ሹመት ኤጲስ ቆጶስ ሆነው የተሾሙት የሚዛን ቴፒ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ አባ ሚካኤል ገብረ ማርያም ቢሮ መታሸጉ ተገልጿል።

በትናንትናው ዕለት የሿሚዎቹን ጳጳሳት ማረፊያ ቤትን ጨምሮ የተሿሚዎች ቢሮዎች እየታሸጉ መሆኑን መግለጻችን ይታወሳል።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ኢ-ቀኖናዊ በሆነ መልኩ የተፈጸመውን ''ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳት'' አስመልክቶ ከሀገር አቀፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት የተሰጠ መግለጫ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/25 16:20:28
Back to Top
HTML Embed Code: