Telegram Web Link
የግሥ ጥናት ክፍል አስራ ሁለት
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ሀለወ=ኖረ
፪) ኀለወ=ቀራ፣ጠበቀ
፫) ሐሰወ=ዋሸ
፬) ኀረወ=በሳ፣ነደለ፣ቆፈረ
፭) ኄረወ=ቸር ሆነ
፮) ኀተወ=በራ፣ቦግ አለ
፯) ሐይወ=ዳነ
፰) ኀጸወ=ሰለበ
፱) ሀፈወ=ወዛ፣ደከመ
፲) ለሐወ=አለቀሰ
፲፩) ሎለወ=ጠበሰ፣አቃጠለ፣ለበለበ
፲፪) ለቀወ=ከፈተ፣አላቀቀ
፲፫) ለበወ=ልብ አደረገ፣አስተዋለ
፲፬) ለከወ=ፈዘዘ፣ቦዘ፣ደነገዘ
፲፭) ለወወ=ተኮረ፣ደፈረ (የማየት)
፲፮) ሌወወ=ጠመጠመ
፲፯) ለውለወ=ተውለበለበ፣ አውለበለበ (የምላስ)
፲፰) መሐወ=አሸ (የእሸት)
፲፱) ምህወ=ቀለጠ፣ሟሟ፣ውሃ ሆነ
፳) ማህከወ=አስፈራ፣አስደነገጠ
፳፩) ማለወ=ሸፈነ፣ጨለመ
፳፪) መስወ=አቀለጠ፣አሟሟ፣ ውሃ አደረገ
፳፫) መረወ=ማገረ
፳፬) መንተወ=መንታ አደረገ፣ መንታ ወለደ
፳፭) መጠወ=ሰጠ
፳፮) መጽለወ=ጠወለገ
፳፯) መጽወ=ዘመነ በልግ ሆነ
፳፰) ስሕወ=ተሳበ፣ተጎተተ
፳፱) ሰለወ=ሰላ
፴) ሠረወ=ነቀለ
፴፩) ሰንቀወ=መታ (የመሰንቆ፣ የበገና)
፴፪) ሰንተወ=ገበረ
፴፫) ሰካዕለወ=ቆጠቆጠ፣መነጠረ
፴፬) ረሰወ=መልሕቅ ጣለ፣ገታ፣ አቆመ
፴፭) ረበወ=አስተማረ
፴፮) ቈለወ=ቆላ
፴፯) ቀልጰወ=ዋጠ
፴፰) ቀስተወ=ሳበ፣ገተረ፣ ለጠጠ
፴፱) ቀበወ=ታመመ፣ሆድን ነፋ
፵) ቀተወ=ተወራረደ (የውርርድ)
፵፩) ቀነወ=ቸነከረ
፵፪) ቀንተወ=ገበረ
፵፫) ቀንጸወ=ቀነጣ
፵፬) ቀድወ=አማረ፣ አሸበረቀ፣ ጠራ
፵፭) ባረወ=ቆፈረ
፵፮) ባሕተወ=ብቸኛ ሆነ
፵፯) ቤዘወ=አዳነ
፵፰) በድወ=ምድረ በዳ ሆነ
፵፱) በፅወ=አንቀላፋ
፶) ተሐመወ=አማች ሆነ
፶፩) ተኄረወ=ቸር ሆነ
፶፪) ተለወ=ተከተለ
፶፫) ተመርዐወ=ተሞሸረ፣ተዳረ
፶፬) ተሰርገወ=ተሸለመ
፶፭) ተሰነአወ=ተስማማ
፶፮) ተሠገወ=ሰው ሆነ
፶፯) ተስጥወ=ተቀበለ፣መለሰ
፶፰) ተሰፈወ=ታመነ፣አመነ፣ተስፋ አደረገ
፶፱) ተቀሐወ=ተከራከረ፣ተሟገተ፣ ተፈካከረ
፷) ተባሕተወ=ብቸኛ ሆነ
፷፩) ተአኀወ=ወንድም አማች ሆነ
፷፪) ተአበወ=አባት ሆነ
፷፫) ተአደወ=ተደፋፈረ
፷፬) ተዐፅወ=ዕጣ ተጣጣለ
፷፭) ተኬነወ=ብልሃተኘ ሆነ
፷፮) ተደለወ=ተዘጋጀ፣ተሰናዳ
፷፯) ኖለወ=ጠበቀ (የእንስሳ)
፷፰) ነቀወ=ጮኽ (የአራዊት የአዕዋፍ)
፷፱) ነበወ=ተናገረ
፸) ኖተወ=ዋኘ
፸፩) ነዐወ=አደነ
፸፪) ዐለወ=ወነጀለ፣ከዳ፣ዐመፀ፣ ሸፈተ
፸፫) አመርዐወ=ሙሽራ አደረገ፣ ሞሸረ
፸፬) አመንሰወ=አጠፋ
፸፭) አመንተወ=መንታ አደረገ
፸፮) አመድለወ=ግብዝ አደረገ
፸፯) አስሐወ=አወለቀ
፸፰) አስቆቀወ=አለቀሰ፣አስለቀሰ
፸፱) አስተሰነአወ=አስማማ
፹) አሰውሰው=ሠራ (የመሠላል)
፹፩) አስተዳለወ=አዘጋጀ
፹፪) አስፈድለወ=መነጠረ
፹፫) አርኀወ=ከፈተ
፹፬) አቀምጠወ=ተለመ (የእርሻ)
፹፭) አብቀወ=ከፈተ (የአፍ)
፹፮) አተወ=ገባ
፹፯) አንሶሰወ=ተመላለሰ፣አመላለሰ
፹፰) አንቃዕደወ=አንጋጠጠ፣ ተንጋጠጠ
፹፱) አንባሕቀወ=አፋሸከ፣አዛጋ፣ አላቀቀ
፺) አንጎገወ=ተቅበዘበዘ፣አቅበዘበዘ፣ ባከነ፣ አባከነ፣ ተንከረተተ፣ አንከረተተ
፺፩) አንፀወ=ደረቀ
፺፪) አንጾጸወ=አረጋገፈ
፺፫) ዐውየወ=ተፍጃጀ፣ጮኽ
፺፬) ዐደወ=ተሻገረ፣አለፈ
፺፭) አድለወ=አደላ
፺፮) አጥዐወ=አመለከ (የጣዖት)
፺፯) ዐፀወ=ዘጋ
፺፰) አጸንጰወ=ጠመዘዘ (የሚጠመዘዝ ነገር)
፺፱) ከዐወ=አፈሰሰ
፻) ከወወ=ቅልጥፍጥፍ አለ
፻፩) ወልተወ=መከተ (የጋሻ)
፻፪) ወረወ=ወረወረ
፻፫) ወርዘወ=ጎለመሰ
፻፬) ወይለወ=አለቀሰ
፻፭) ዘመወ=በደለ፣ሴሰኛ ሆነ
፻፮) ዘረወ=በተነ
፻፯) ዜነወ=ነገረ፣አወራ
፻፰) ደለወ=ተገባ
፻፱) ደመወ=ደም ሆነ
፻፲) ደንቀወ=ደነቆረ
፻፲፩) ደንጸወ=ነፈገ
፻፲፪) ጓሕለወ=ሸነገለ
፻፲፫) ጓሕነወ=ጮኽ፣አመሰገነ (የዜማ የምስጋና)
፻፲፬) ገለወ=ሸፈነ
፻፲፭) ገነወ=አመለከ
፻፲፮) ገጸወ=ለየ፣አየ፣ገለጠ
፻፲፯) ጠወወ=አጣመመ
፻፲፰) ጠበወ=ጠባ (የጡት)
፻፲፱) ጽሕወ=ተግ አለ፣በራ (የዝናም)
፻፳) ጸለወ=ቀቀረ (የማድመጥ)
፻፳፩) ጸልሐወ=ሽነገለ፣ አሞኘ
፻፳፪) ጸመወ=ጨመተ፣ደነቆረ
፻፳፫) ጻመወ=ደከመ
፻፳፬) ጸቀወ=ወጋ (የካስማ)
፻፳፭) ፆተወ=ወገን ሆነ
፻፳፮) ጼነወ=ሸተተ
፻፳፯) ጻዕደወ=ነጭ ሆነ
፻፳፰) ፄወወ=ማረከ፣ቀማ
፻፳፱) ጸገወ=ሰጠ
፻፴) ፈተወ=ወደደ
፻፴፩) ፈነወ=ላከ
                        
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የግሥ ጥናት ክፍል አስራ ሦስት
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐልዘዘ=አፈራ (የዛጎል ልብሱ)
፪) ሐመዘ=መርዝ አደረገ
፫) ኀበዘ=ጋገረ
፬) ሐንዘዘ=አናዘዘ
፭) ሖዘ=አማረ
፮) ሎዘ=ጠመዘዘ
፯) ለዝለዘ=ታመመ
፰) መሐዘ=ጎለመሰ
፱) ምዕዘ=ሸተተ (የጥሩ)
፲) መዝመዘ=አሸ፣ወለወለ
፲፩) ሰመዘ=ነቀለ (የሚነቀል ተክል ዓይነት)
፲፪) ሰረዘ=ለየ፣ከፈለ
፲፫) ሰከዘ=ወጋ
፲፬) ሮዘ=ወለወለ
፲፭) ረዘዘ=አፈራ
፲፮) ረገዘ=ወጋ
፲፯) ቈለዘ=ቆጠቆጠ
፲፰) ቀንፈዘ=ደነበ፣ጨመረ
፲፱) ቀዘ=ቅዝዝ ቅዝዝ አለ
፳) ቀፈዘ=አሰረ
፳፩) በለዘ=ደገፈ
፳፪) ብዕዘ=ነፋ (የዋሽንት)
፳፫) በዝበዘ=አማ፣ነቀፈ
፳፬) ቤዘ=በራ፣አበራ
፳፭) ተሐገዘ=ተጋገዘ፣ተረዳዳ
፳፮) ተመርጎዘ=ተመረኮዘ፣ተደገፈ
፳፯) ተዐርዘ=ተራቆተ፣ታረዘ
፳፰) ተዐረዘ=ለበሰ
፳፱) ተከዘ=አዘነ፣ተወዘወዘ
፴) ተገአዘ=ተከራከረ
፴፩) ተፋወዘ=ተጫወተ
፴፪) ነቅዘ=ነቀዘ
፴፫) ነዝነዘ=ነዘነዘ
፴፬) ናዘዘ=አረጋጋ
፴፭) አኀዘ=ያዘ
፴፮) አሕዘዘ=ስርግርግ አደረገ፣ዋጠ
፴፯) አመንዘዘ=አጽንቶ ያዘ፣ አመነቸከ፣ አስጨነቀ፣ አስቸገረ
፴፰) አስዖዘዘ=ስቅጥጥ ስቅጥጥ አለ፣ስቅጥጥ ስቅጥት አደረገ
፴፱) ዐረዘ=ለበሰ
፵) አንበዘ=ልብ አሳጣ
፵፩) አውገዘ=ለየ
፵፪) አዘዘ=አዘዘ
፵፫) አግዐዘ=ነጻ አወጣ
፵፬) አግዘዘ=ጀጎለ፣አጠረ
፵፭) አፈርዘዘ=በተነ፣አጠፋ፣አበነነ
፵፮) ከረዘ=ሰቀለ
፵፯) ኰበዘ=ጋገረ
፵፰) ውሕዘ=ፈሰሰ፣አጎረፈ
፵፱) ደረዘ=ወጋ
፶) ደንበዘ=ደገፈ
፶፩) ደንዘዘ=ደነዘዘ፣ፈዘዘ
፶፪) ደንገዘ=ደነገዘ (የመደነቅ)
፶፫) ደንጎዘ=ሠራ (የጭራ የጸጕር)
፶፬) ገበዘ=ሸመ
፶፭) ገነዘ=አሰረ፣ገነዘ
፶፮) ግዕዘ=ነቀፈ
፶፯) ጠረዘ=ጠረዘ
፶፰) ፎዘ=ወለወለ
                        
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የግሥ ጥናት ክፍል አስራ አራት
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ኀለየ=አሰበ፣አወጣ፣አወረደ
፪) ሐለየ=ዘፈነ፣ዘመረ፣አመሰገነ
፫) ሐመየ=አማ
፬) ኀመየ=አሰረ፣ቀፈደ
፭) ሐሰየ=አሸ፣አበራየ
፮) ኀረየ=መረጠ
፯) ሐቀየ=አፋጨ
፰) ሐብለየ=በዘበዘ
፱) ሀከየ=ሰነፈ
፲) ሀውለየ=አላገጠ፣አፌዘ፣አቃለለ፣ ናቀ፣ሰደበ
፲፩) ሐወየ=ድንግዝግዝ አለ፣መሸ፣ ጨለመ
፲፪) ሐይደነየ=አበደ
፲፫) ሀደየ=አበሰለ፣አሞከከ
፲፬) ሐገየ=ባጀ
፲፭) ሐፀየ=አጨ
፲፮) ልሕየ=ወዛ፣ተቅለጠለጠ
፲፯) ሌለየ=ለየ
፲፰) ለቀየ=ከፈተ
፲፱) ለበየ=ተሳሳተ፣ ልበ ቢስ ሆነ፣ ተደናገረ
፳) ላኰየ=ተጣላ፣ተከራከረ፣ ተሟገተ
፳፩) ሎየ=ጠመጠመ፣ጠቀለለ፣ ፈትሉን በእንዝርት አከረረ
፳፪) ላጸየ=ላጨ
፳፫) ለፈየ=ከፈለ፣ሁለት አደረገ
፳፬) መለየ=አቀለጠ
፳፭) ሜመየ=ለየ
፳፮) መስየ=መሸ
፳፯) መረየ=ጠነቆለ
፳፰) ማረየ=ጠነቆለ
፳፱) መኰየ=ተወራረደ፣ተከራከረ
፴) ሰሐየ=አጠፋ
፴፩) ሰመየ=ስም አወጣ
፴፪) ሴሰየ=መገበ
፴፫) ሰረየ=አቃለለ (የኃጢአት)
፴፬) ሠረየ=መድኃኒት አደረገ (የክፉ የበጎ)
፴፭) ሤረየ=በደም አለለ
፴፮) ሰቀየ=አጠጣ (የተክል ብቻ)
፴፯) ሣቀየ=ሥቃይ አሳየ፣አሠቃየ፣ አስጨነቀ
፴፰) ሰትየ=ጠጣ
፴፱) ሠነየ=አማረ
፵) ሰነየ=ሁለት አደረገ
፵፩) ሥዕየ=መነሻ፣ በተነ፣ አዘራ
፵፪) ሰከየ=ከሰሰ
፵፫) ሳኰየ=ተቅበዘበዘ፣ዞረ፣ባከነ፣ ተንከረተተ
፵፬) ሦየ=ሸተ፣በሰለ
፵፭) ሠዘየ=ለየ፣ነጠለ
፵፮) ሰድየ=አማረ
፵፯) ሰፈየ=ሰፋ፣ጠቀመ፣ሸለለ
፵፰) ርሕየ=ሸተተ
፵፱) ረመየ=ወጋ
፶) ረሰየ=አደረገ
፶፩) ረቀየ=ረጨ፣ አሞቀ
፶፪) ርእየ=አየ፣ተመለከተ
፶፫) ረዐየ=ጠበቀ
፶፬) ረወየ=ረካ
፶፭) ረድየ=ከፈለ፣አበደረ (የአራጣ)
፶፮) ቀረየ=አሟረተ
፶፯) ቀልየ=ጥልቅ ሆነ
፶፰) ቄቀየ=ነፈገ
፶፱) ቀበየ=አዘጋጀ
፷) ቀነየ=ገዛ (የሰው)
፷፩) ቃነየ=ቃኘ፣ደረደረ
፷፪) በልየ=አረጀ
፷፫) ቤበየ=ለየ
፷፬) በከየ=አለቀሰ
፷፭) በድየ=ምድረ በዳ ሆነ
፷፮) ተሐሥየ=ተደሰተ
፷፯) ተሐበየ=ዋስ ሆነ
፷፰) ተሀየየ=ቸል ቸል አለ
፷፱) ተለሀየ=ተጫወተ
፸) ተመነየ=ተመኘ
፸፩) ተመኵሰየ=ሞክሼ ሆነ፣በስም ተባበረ
፸፪) ተሰካተየ=ተማማለ
፸፫) ተሰጥየ=ተሰጣ፣ተዘረጋ
፸፬) ተረሰየ=ተሸለመ፣አጌጠ
፸፭) ተርዕየ=ተሰማራ
፸፮) ተቈናደየ=ተጓደደ፣ተኳደደ
፸፯) ተነሀየ=አቃለለ (የኃጢአት)
፸፰) ተነበየ=ተናገረ (የትንቢት)
፸፱) ተዐበየ=ኮራ (የልብ ትዕቢት)
፹) ተአርወየ=አውሬ ሆነ
፹፩) ተዋንየ=ተጫወተ
፹፪) ተዘጋደየ=ተዘጋጀ
፹፫) ተጋነየ=እጅ ተነሳሳ
፹፬) ተፈየ=ገረፈ
፹፭) ተፋጸየ=አዳነቀ
፹፮) ንህየ=አረፈ
፹፯) ነሰየ=ረሳ፣ዘነጋ
፹፰) ነከየ=ነካ
፹፱) ነድየ=ተቸገረ
፺) ነጸየ=ነጨ፣ነቀለ፣መለጠ
፺፩) ነፈየ=ነፋ (የወንፊት)
፺፪) ዐለየ=መለሰ፣ቀለሰ፣ለገመ
፺፫) አሌለየ=ማለደ (የመገሥገሥ)
፺፬) አመስከየ=ተጠጋ፣አስጠጋ
፺፭) አመክነየ=አመካኘ
፺፮) አማዕለየ=ወነጀለ
፺፯) አማዕረየ=አበጀ፣አዘጋጀ፣ አስተካከለ
፺፰) አሜረየ=አሠገረ
፺፱) ዐሰየ=ሰጠ
፻) አስተርአየ=ታየ፣አሳየ
፻፩) አስተባረየ=አፈራረቀ፣አስተጋገዘ
፻፪) አስተዋደየ=አጣላ
፻፫) ዐረየ=ተካከለ
፻፬) አርሰየ=አስጠጋ
፻፭) አቃረየ=ሠዋ
፻፮) አቅሌለየ=አቅላላ
፻፯) አቅዜዘየ=ቅዝዝ ቅዝዝ አለ
፻፰) አበየ=እንቢ አለ
፻፱) ዐብየ=ከፍ ከፍ አለ
፻፲) አናሕሰየ=አቃለለ፣ይቅር አለ
፻፲፩) አንቤበየ=ለየ
፻፲፪) አንከየ=ሰጠ
፻፲፫) አንጌገየ=ተቅበዘበዘ፣ ዞረ፣ አቅበዘበዘ፣ ባከነ
፻፲፬) አንጠየ=ዘበዘበ፣ጨቀጨቀ፣ ነዘነዘ
፻፲፭) አአየ=ዞረ፣ተመለሰ
፻፲፮) አከየ=ከፋ
፻፲፯) አውቀየ=ቆረጠ
፻፲፰) አወፈየ=ሰጠ
፻፲፱) ዐየየ=ዞረ፣ባከነ
፻፳) ዐደየ=ከፈለ፣ብድር መለሰ (የበጎ የክፉ)
፻፳፩) አጥረየ=ገዛ
፻፳፪) ዐፀየ=ተላ
፻፳፫) አፈየ=ጋገረ፣አበሰለ
፻፳፬) ኰሰየ=ለየ፣ነጠለ፣ከፈለ
፻፳፭) ከረየ=ቆፈረ፣ማሰ
፻፳፮) ወሐየ=ጎበኘ
፻፳፯) ወቀየ=ጠበቀ፣ተጠባበቀ
፻፳፰) ውዕየ=ተቃጠለ
፻፳፱) ዋከየ=በራ
፻፴) ወደየ=ጨመረ፣ዶለ
፻፴፩) ዘረየ=በተነ፣ለየ
፻፴፪) ዘርከየ=ሰደበ፣አዋረደ
፻፴፫) ዘበየ=ገዛ
፻፴፬) ዘነየ=ሳተ (የፍትወት)
፻፴፭) ደኀየ=ቆፈረ
፻፴፮) ደርበየ=መታ፣ወጋ
፻፴፯) ደበየ=ጎተተ
፻፴፰) ዳነየ=ዳኘ፣ፈረደ
፻፴፱) ደወየ=ታመመ
፻፵) ጎሐየ=አረመ
፻፵፩) ገለየ=ለየ፣ቆጠቆጠ፣ቆረጠ
፻፵፪) ጎርዐየ= አነቀ፣ ፈጠረቀ
፻፵፫) ገነየ=ተገዛ
፻፵፬) ጎንደየ=ዘገየ
፻፵፭) ጎዕተየ=ጣረ፣ጋረ፣ለፋ
፻፵፮) ጎየ=ሸሸ
፻፵፯) ጌገየ=በደለ
፻፵፰) ጎጠየ=ቸነከረ
፻፵፱) ጠለየ=ለመለመ
፻፶) ጠሰየ=አጠፋ፣ ደመሰሰ
፻፶፩) ጠነየ=ፈለገ
፻፶፪) ጥዕየ=ዳነ
፻፶፫) ጠወየ=ጠመመ
፻፶፬) ጻሕየየ=አረመ
፻፶፭) ጸለየ=ለመነ፣ጸለየ
፻፶፮) ጸምሐየ=ጠወለገ
፻፶፯) ጸማሕየየ=ጠወለገ፣ደረቀ
፻፶፰) ጸረየ=ጠራ
፻፶፱) ጸበየ=ወረደ፣ፈሰሰ
፻፷) ጸብለየ=ትቢያ ሆነ
፻፷፩) ጸደየ=ዘመነ በልግ ሆነ
፻፷፪) ጸገየ=አበበ
፻፷፫) ፈለየ=ለየ፣መረጠ
፻፷፬) ፈረየ=አፈራ
፻፷፭) ፈደየ=ከፈለ (የክፉ የበጎ)
፻፷፮) ፋጸየ=አፏጨ
                           
@EotcLibilery
@Eotclibilery
@EotcLibilery
#የግሥ #ጥናት #ክፍል #አስራ #አምስት
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ኀለደ=ጨረሰ፣ፈጀ፣ከተተ
፪) ሐመደ=አከሰለ፣አመድ አደረገ
፫) ሐረደ=አረደ
፬) ሐርበደ=ተስበደበደ፣ተንበደበደ (የፍርሀት)
፭) ሀየደ=አንጸባረቀ፣በዘበዘ
፮) ሄደ=ቀማ፣ነጠቀ
፯) ሐደደ=ፈጨ
፰) ልሕደ=ተደላደለ፣ተቀማጠለ
፱) ለመደ=ለመደ
፲) መለደ=ሰበሰበ
፲፩) መሰደ=ሸመተ
፲፪) መረደ=ጠበጠበ፣ተራመደ
፲፫) መርደደ=ጨከነ፣ደፈረ፣ተጋ፣ ፈጠነ
፲፬) ምዕደ=መከረ (ጎበኘ)
፲፭) መደደ=ቆረጠ
፲፮) ሞገደ=ማዕበል አደረገ፣አነሳሳ፣ አወከ (የማዕበል)
፲፯) ሞፈደ=ጫረ
፲፰) ሶደ=ጫረ
፲፱) ሰደደ=አባረረ፣አሳደደ
፳) ሰገደ=ሰገደ
፳፩) ርዕደ=ተንቀጠቀጠ፣ራደ፣ ተንበደበደ
፳፪) ሮደ=ከበበ (የክፉ)
፳፫) ረፈደ=ረፈደ
፳፬) ቀለደ=ቀዳ
፳፭) ቀልደደ=ቀነደበ
፳፮) በረደ=በረደ፣ቀዘቀዘ
፳፯) በርደደ=ደበደበ፣ቀጠቀጠ፣ ሞረደ
፳፰) በዐደ=ለየ፣ነጠለ
፳፱) በየደ=ረጋ
፴) በድበደ=ታመመ
፴፩) ተማኅፈደ=ሠራ
፴፪) ተአንገደ=እንግዳ ሆነ
፴፫) ተካየደ=ተማማለ፣ ቃል ኪዳን ገባ
፴፬) ተዋሐደ=አንድ ሆነ
፴፭) ተዋረደ=ተዋረደ
፴፮) ተዘምደ=ዘመድ ሆነ
፴፯) ተይህደ=አመነ
፴፰) ተጋየደ=ተቀዳደመ፣ተሯሯጠ
፴፱) ተፀምደ=አገለገለ
፵) ንእደ=አማረ
፵፩) ነደ=ነደደ፣ተቃጠለ
፵፪) ነገደ=ሄደ
፵፫) አሐደ=አንድ አደረገ
፵፬) አለደ=ሰበሰበ፣ለቀመ፣ከመረ፣ አከማቸ
፵፭) ዐመደ=ቆረጠ
፵፮) አስተዋደደ=አስማማ፣አጓደደ
፵፯) አስተጋየደ=አቀዳደመ
፵፰) አብደ=ሰነፈ
፵፱) አብረደ=አበረደ፣አቀዘቀዘ
፶) አንጎድጎደ=ተነዋወጠ፣ አነዋወጠ፣ተንጎደጎደ፣አንጎደጎደ
፶፩) አኬደ=አበራየ
፶፪) አውደደ=አስማማ፣አዋደደ፣ አንድ አደረገ
፶፫) ዖደ=ዞረ
፶፬) ዐደደ=አባረረ
፶፭) ዐጸደ=ቦታ አደረገ
፶፮) ዐጸደ=አጨደ
፶፯) አጽዐድዐደ=ነጭ አደረገ፣አነጣ
፶፰) ክሕደ=ካደ
፶፱) ከብደ=ከበደ
፷) ኬደ=ረገጠ
፷፩) ውኅደ=ጎደለ
፷፪) ወለደ=ወለደ
፷፫) ወሰደ=ወሰደ
፷፬) ወረደ=ወረደ
፷፭) ግህደ=ገለጠ
፷፮) ገለደ=ጋረደ፣ሸፈነ፣አስጌጠ፣ ጎዘጎዘ፣ አነጠፈ
፷፯) ገመደ=ቆረጠ፣አጨደ
፷፰) ጎነደ=ደነደነ
፷፱) ገደ=አስገደደ
፸) ገድገደ=ገደገደ
፸፩) ጎድጎደ=መታ፣ቀፈቀፈ፣እጁን ጸፋ
፸፪) ጰሰደ=ጠነሰሰ፣ጠጀ
፸፫) ጽሕደ=ለዘበ፣ለሰለሰ
፸፬) ፀመደ=ጠመደ
፸፭) ፈረደ=ፈረደ
፸፮) ፈቀደ=ወደደ
፸፯) ፈድፈደ=በዛ
                          ።
#የ"ገ" #ግሥ
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐመገ=አደፈረሰ
፪) ኀደገ=ተወ
፫) ሐገገ=ሕግ ሠራ፣ወሰነ፣ደነገገ
፬) ሎገ=ጠመዘዘ፣ሠራ
፭) ለግለገ=ታመመ
፮) መለገ=ቻለ፣ታገሠ
፯) መረገ=መረገ፣ለሰነ
፰) መዘገ=ነጠቀ፣አወጣ
፱) ሰረገ=ሰርግ አደረገ
፲) ሰነገ=አሰረ፣ሰነገ፣አነቀ
፲፩) ሰብጎጎ=አጠራ፣ሠራ (የብረት)
፲፪) ሰፍነገ=አጠጣ
፲፫) በግበገ=ታመመ
፲፬) ተንተገ=ተነተገ፣ተረኮሰ
፲፭) ተዛወገ=ጎረቤት ሆነ
፲፮) ተዳረገ=አንድ ሆነ
፲፯) ተፀወገ=ተከፋ፣አስከፋ
፲፰) ነሠገ=ቆለፈ፣ዘጋ
፲፱) ነትገ=ጎደለ
፳) ዐለገ=ሰለበ
፳፩) አረገ=ሸመገለ፣አረጀ
፳፪) ዐርገ=ወጣ
፳፫) ዐነገ=አሰረ (የጉትቻ)
፳፬) አንገለገ=አከማቸ፣ሰበሰበ፣ ተከማቸ፣ ተሰበሰበ፣ ተጠራቀመ
፳፭) ዖገ=አላገጠ
፳፮) ዔገ=መነጨ
፳፯) ወተገ=ሳበ፣ቀማ
፳፰) ዘንጎጎ=አሽሟጠጠ፣አማ
፳፱) ደለገ=ከረፋ
፴) ዳረገ/ደረገ=ሰጠ
፴፩) ደንገገ=ወሰነ፣ደነገገ (የድንበር የባሕር)
፴፪) ደግደገ=ከሳ፣ቀጠነ
፴፫) ጸጎ=ዳር ድንበር አወጣ
፴፬) ፈለገ=መነጨ
፴፭) ፈርገገ=ሻረ፣ደረቀ፣አተረ
፴፮) ፈገ=ፍግግ ፍግግ አለ
፴፯) ፈገገ=ከረፋ፣ሸተተ
                    
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የግሥ ጥናት ክፍል አስራ ስድስት
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐብጠ=አበጠ
፪) ሐንፈጠ=አጓለበ፣ጠረጠረ (የማንፈስ)
፫) ኄጠ=ሸነገለ፣አታለለ፣ደለለ
፬) ኀፈጠ=መታ፣ደሰቀ፣ደበደበ
፭) ለበጠ=ለበጠ፣ሸለመ
፮) ሎጠ=ለወጠ
፯) ለጥለጠ=መዘነ
፰) መለጠ=መለጠ፣ላጠ
፱) መሠጠ=ነጠቀ፣ቀማ
፲) ሜጠ=መለሰ፣ቀለሰ
፲፩) ሰሐጠ=ነካ፣ቆነጠጠ
፲፪) ሰለጠ=ጨረሰ፣ፈጸመ
፲፫) ሠበጠ=አደረጎተ
፲፬) ሶጠ=ጨመረ፣ደባለቀ፣ቀላቀለ
፲፭) ሦጠ=ገረፈ
፲፮) ሤጠ=ሸጠ
፲፯) ሠጠጠ=ቀደደ
፲፰) ቀሠጠ=ቀሠጠ
፲፱) ቀበያውበጠ=ቀላወጠ
፳) ቀንጦሰጠ=ተሰለፈ፣አሰለፈ
፳፩) ቀጥቀጠ=መታ፣ቀጠቀጠ
፳፪) ተሠልጠ=ሰለጠነ
፳፫) ተሣየጠ=ተወዳጀ
፳፬) ነሐጠ=ሠራ (የቤት)
፳፭) ነቈጠ=ጫረ (የነቍጥ)
፳፮) አምሠጠ=አመለጠ
፳፯) አስዖጠጠ=ስቅጥጥ ስቅጥጥ አደረገ
፳፰) አስፈጠ=አሳተ፣አታለለ
፳፱) አቍጠጠ=አቀጠነ፣አመነመነ
፴) ዐበጠ=መለሰ
፴፩) አንሦጠጠ=ስቅጥጥ ስቅጥጥ አለ፣ስቅጥጥ ስቅጥጥ አደረገ
፴፪) አከጠ=መገበ
፴፫) አጸዐጥዐጠ=አጣፈጠ፣ጣፈጠ
፴፬) ውኅጠ=ዋጠ
፴፭) ወለጠ=ለወጠ
፴፮) ወፈጠ=ተኮሰ (የሸክላ የብረት የልብስ)
፴፯) ዘበጠ=መታ
፴፰) ገበጠ=ታመመ
፴፱) ፀበጠ=ያዘ፣ጨበጠ
፵) ጽዕጠ=ጣፈጠ
፵፩) ፈለጠ=ለየ
                             ።
#የ"ጰ" #ግሥ
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐርጰጰ=ፈጨ
፪) ሀንጰጰ=ታመመ
፫) ሄጰ=ነደፈ
፬) ሰሐጰ=ነካ
፭) ሰለጰ=ዋጠ
፮) ሠረጰ=ቀደሰ
፯) ቀለጰ=ዋጠ
፰) ቀልጰጰ=ከመረ፣አሰረ
፱) ቈርጰጰ=ቆረጠመ
፲) ዐንጰጰ=ታመ
፲፩) አክረጰ=አነጣ
፲፪) ኰረጰ=ሠራ (የብረት)
፲፫) ዘረጰ=ሰደበ
፲፬) ጎሐጰ=ጎሸመጠ
፲፭) ገነጰ=ሰገበ
፲፮) ጌጰ=በረረ
                           ።
የ"ጸ" ግሥ
የግሥ ጥናት ክፍል
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐረጸ=ፈጨ
፪) ሐነጸ=ሠራ (የቤት)
፫) ኀንጸጸ=ጠረጠረ
፬) ሐንፈጸ=አንጓለበ፣አንጓለለ
፭) ሐወጸ=ጎበኘ
፮) ሐጸ=ጎደለ
፯) ለሐጸ=ላጠ
፰) ለምጸ=ታመመ
፱) ለጽለጸ=መዘነ
፲) ለፈጸ=ለወሰ፣አሸ፣አበቀ
፲፩) መሐጸ=ቆረጠ
፲፪) ምኅፀ=አማጠ
፲፫) ሞርየጸ=አሟጨ
፲፬) መፀ=ቦካ፣ኾመጠጠ
፲፭) ሥሕጸ=ጥልቅ ጥልቅ አለ (የነገር)
፲፮) ሠረጸ=በቀለ
፲፯) ሰርወጸ=ጋረጠ
፲፰) ሰነጸ=አለዘበ፣ሠራ፣አስጌጠ
፲፱) ርሕፀ=ወዛ
፳) ረምፀ=ጋለ
፳፩) ሮጸ=ሮጠ
፳፪) ረየፀ=ገራ
፳፫) ረገፀ=ረገጠ
፳፬) ቀረፀ=ሸለተ፣ቆረጠ፣ላጨ
፳፭) ቀብጸ=ተስፋ አጣ
፳፮) ቀነጸ=ዘለለ
፳፯) ቀፈጸ=ገለጠ፣ገፈፈ
፳፰) በረጸ=ብልጭ አለ
፳፱) በቈጸ=ጫረ፣ተረኮሰ
፴) ቤጸ=ለየ
፴፩) ተማወጸ=ተከካሰ
፴፪) ተባየጸ=ባለ እንጀራ ሆነ
፴፫) ተጋህረጸ=ተጣላ
፴፬) ተጋየጸ=ተጌጊያጠ
፴፭) ንሕጸ=አረፈ
፴፮) ነቅጸ=ደረቀ
፴፯) ነፍጸ=ሸሸ
፴፰) ዐመፀ=በደለ
፴፱) አመጎፀ=አጣላ
፵) አስተሐየጸ=ተመለከተ፣ አመላከተ
፵፩) አንፈርዐጸ=ዘለለ
፵፪) አንፈጸ=አዘራ፣አነፈሰ
፵፫) አዕቀጸ=አሰነካከለ
፵፬) ዐፀ=ዱር ሆነ
፵፭) ድኅፀ=ዳጥ ሆነ
፵፮) ደምፀ=ተሰማ
፵፯) ደረጸ=ወጋ
፵፰) ደነጸ=ነፈገ
፵፱) ደንገፀ=ደነገጠ
፶) ደጎጸ=መታ
፶፩) ገመጸ=በደለ
፶፪) ገለጸ=ገለጠ
፶፫) ገሠጸ=ተቆጣ
፶፬) ገገጸ=አፈገፈገ፣ወደኋላ አለ
፶፭) ጎየጸ=ተናጻ
፶፮) ፈለጸ=ፈለጠ፣ሰነጠቀ
                         
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#የግሥ #ጥናት #ክፍል #አስራ #ሰባት
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ኀለፈ=ሄደ
፪) ኀሠፈ=አከከ
፫) ሐቀፈ=አቀፈ
፬) ኀደፈ=አስተማረ
፭) ሐፈ=ወዛ
፮) ለአፈ=ጎረሰ
፯) ለፈፈ=ጻፈ
፰) መንተፈ=አባዘተ
፱) ሰረፈ=አጠነ፣አጤሰ
፲) ሰየፈ=ቆረጠ
፲፩) ሰደፈ=መታ
፲፪) ሰፈፈ=ተንኳፈፈ፣ ሰፈፈ
፲፫) ረጕነፈ=ጎዘጎዘ
፲፬) ቈለፈ=ቆላፍ ሆነ፣ቆለፈ
፲፭) ቀሠፈ=ገረፈ
፲፮) ቀረፈ=ላጠ
፲፯) ቀደፈ=ቀዘፈ (የታንኳ)
፲፰) ቀጠፈ=ቀጠፈ፣ሰረቀ
፲፱) ተኀለፈ=ተናገረ
፳) ተለሐፈ=ተጫወተ
፳፩) ተሳተፈ=አንድ ሆነ፣ተሳተፈ
፳፪) ተርፈ=ቀረ
፳፫) ተዐጽፈ=ለበሰ
፳፬) ተወክፈ=ተቀበለ
፳፭) ተወዝፈ=አጌጠ
፳፮) ተዛወፈ=ተጫወተ
፳፯) ነተፈ=ቆረጠ፣በጨቀ፣በጠሰ
፳፰) ነዘፈ=ለበሰ
፳፱) ነደፈ=ወጋ
፴) ነገፈ=አራገፈ
፴፩) ነጠፈ=ኮላ፣አጠራ፣አቀለጠ፣ አነጠረ
፴፪) ነጸፈ=አነጠፈ
፴፫) ነፅፈ=ደረቀ፣ነጠፈ
፴፬) ነፍነፈ=አካፋ (የዝናም)
፴፭) አለፈ=ቆጠረ
፴፮) አስተኀለፈ=አዋጅ ነገረ
፴፯) አስተናደፈ=በገረ፣አስበገረ፣ ሠራ (የቤት)
፴፰) አንዘፍዘፈ=አንዘፈዘፈ፣ ተንዘፈዘፈ
፴፱) አንገፈ=አዳነ
፵) አንጸፍጸፈ=አንጠፈጠፈ
፵፩) አዕረፈ=አረፈ፣አሳረፈ
፵፪) አዕቀፈ=አሰነካከለ፣አናቀፈ
፵፫) አኰፈ=አቋተ፣አቆመ
፵፬) አውቀፈ=ሠራ (የአንባር)
፵፭) አዝለፈ=አዘወተረ
፵፮) አጥነፈ=አያያዘ፣አዋደደ
፵፯) ዐጠፈ=ሠራ፣ጠቀለለ፣አከረረ
፵፰) ዐጸፈ=ለበሰ
፵፱) ከልተፈ=አሰረ (የሰው)
፶) ኰተፈ=አሰረ (የሰው)
፶፩) ከነፈ=በረረ
፶፪) ወፀፈ=ወነጨፈ
፶፫) ዘለፈ=ሰደበ
፶፬) ደሐፈ=ደፋ፣ገፋ
፶፭) ገሐፈ=ጠረገ፣ጋፈ
፶፮) ገለፈ=ጣዖት ሠራ
፶፯) ገረፈ=አጠመደ
፶፰) ጎረፈ=ኀጢአት ሠራ
፶፱) ገዝፈ=ደነደነ
፷) ገደፈ=ጣለ
፷፩) ጸሐፈ=ጻፈ
፷፪) ፀረፈ=ሰደበ
፷፫) ጸነፈ=ዳርቻ ሆነ
፷፬) ጸንገፈ=ከበደ (የሸክም)
፷፭) ጸየፈ=ጸያፍ ሆነ
፷፮) ጸድፈ=ወደቀ
፷፯) ጸፍጸፈ=ሠራ
፷፰) ፈልሰፈ=ብልሃተኛ ሆነ
                           ።
የ"ፐ" ግሥ
   ግእዝ=አማርኛ
፩) ሐስቀፐ=አረሰ፣አለሰለሰ
፪) ሰለፐ=ሠራ፣ቀባ
፫) ሴለፐ=ወገን ሆነ
፬) ሰረፐ=ቀደሰ
፭) ሮፐ=ጸና
፮) ተረፐ=አጠመደ
፯) ቴረፐ=በዛ፣በረከተ
፰) ቴፐ=ደበበ፣ሠራ
፱) አስኮተፐ=አረሰ
፲) ኤፐፐ=ወደደ
፲፩) ከተፐ=ጻፈ
፲፪) ዴፐ=ሸመቀ
                            
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ለማስታዎስ ያህል
_ ስም____ትርጉም
1 ፊላታዎስ፦የአምላክ ወዳጅ
2 ሮብዓም፦ሕዝብ ይብዛ
3 ቴዎድሮስ፦የእግዚአብሔር ስጦታ
4 ሮቤል፦እነሆ ወንድ ልጅ
5 ማራናታ፦ጌታ ሆይ ና
6 ቤቴል፦የእግዚአብሔር ቤት
7 ቄርሎስ፦የተመረጠ ምርጥ
8 እስጢፋኖስ፦አክሊል
9 ሳውል/ሳኦል፦ከእግዚአብሔር የተለመነ
10 ሴዴቅያስ፦የእግዚአብሔር ጽድቅ
11 ፊቅጦር፦ኀዘኔን አራቀልኝ
12 ንፍታሌም፦ታጋይ የሚታገል
13 ዮርዳኖስ፦ወራጅ
14 ዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
15 ገነት፦የአትክልት ስፍራ
16 ፊልድልፍያ፦የወንድማማች ፍቅር
17 ዲና፦ፈረደ
18 ማኑሄ፦እረፍት
19 መልሕቅ፦ከብረት የተሠራ የመርከብ ማቆሚያ
20 ራማ፦ከፍታ
21 ኤርምያስ፦እግዚአብሔር ከፍ ያደርጋል
22 ሐና፦ ስጦታ
23 ሕርያቆስ፦ኅሩይ
24 ፊልጶስ፦ወንድም ወዳጅ
25 ቶማስ፦ፀሐይ
26 ጎርጎርዮስ:-ንቁሕ የተጠበቀ
27 ማትያስ፦ፀሐይ
28 ቀሌምንጦስ፦ግንብ
29 አቤል፦በግ ወይም ደመና
30 ኖኅ፦ደስታ
31 ሴም፦ተሾመ
32 ይሥሐቅ፦ደስታ አንድም
33 ሙሴ፦የውሃ ልጅ
34 አሮን፦የእግዚአብሔር ተራራ
35 ጌዴዎን፦እግዚአብሔር ኃያል ነው
36 እሴይ፦ዋጋየ
37 አሚናዳብ፦መንፈስቅዱስ
38 ዳዊት፦የተወደደ ልበ አምላክ
39 ዕንባቆም፦ጠቢብ አዋቂ አስተዋይ
40 ሄኤሜን፦ምኞቴን አገኘሁ
41 አሞጽ፦እግዚአብሔር ጽኑ ነው
42 ዮናስ፦ርግብ
43 ሐጌ፦የእግዚአብሔር መልእክተኛ
44 ራኄል፦በግዕት
45 ዕዝራ፦ረዳቴ
46 ሔርሜላ፦ከክብር ዘመድ የተገኘች
47 መርቆሬዎስ፦የአባት ወዳጅ
48 ኤጲፋንዮስ፦ምስጢር ገላጭ
49 ሜሮን፦የተባረከ ሽቱ
50 ሱላማጢስ፦ሰላማዊት
51 ሶምሶን፦ፀሐይ
52 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ
53 ማርታ፦እመቤት
54 ሊዲያ፦ፈራሂተ እግዚአብሔር
55 ኤፍሬም፦ፍሬያማ ፍሬው
56 ኤፍራታ፦ክብርት የተከበረች
57 ታዴዎስ፦ተወዳጅ
58 ኢየሩሳሌም፦የሰላም ሀገር
59 ሄኖስ፦ሰው
60 ሰሎሜ፦ሰላም
61 ሩሐማ፦ምሕረት
62 ዮዳሔ፦እግዚአብሔር ያውቃል
63 ቴዎፍሎስ፦የእግዚአብሔር ወዳጅ
64 ኑኃሚን፦ደስታየ
65 ናትናኤል፦የእግዚአብሔር ስጦታ
66 አዛሄል፦እግዚአብሔር ያያል
67 ኢዮስያስ፦እግዚአብሔር ይደግፋል
68 ኢዩኤል፦እግዚአብሔር አምላክ ነው
69 በርናባስ፦የመጽናናት ልጅ
70 ሶፎንያስ፦እግዚአብሔር ሰውሯል/ጠብቋል
71 ሕዝቅኤል፦እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጣል
72 ኬልቅያስ፦እድል ፈንታየ እግዚአብሔር
73 ሳሙኤል፦እግዚአብሔር ሰማኝ
74 ሚኪያስ፦ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!
75 ሆሴዕ፦እግዚአብሔር ያድናል
76 ሔዋን፦የሕያዋን ሁሉ እናት
77 ሕዝቅያስ፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው
78 መልከጼዴቅ፦የሰላም ንጉሥ
79 ሚልኪያስ፦መልእክተኛየ
80 ሣራ፦ልዕልት
81 ስምዖን፦ሰማ
82 ብንያም፦የቀኝ እጄ ልጅ
83 ናሆም፦መጽናናት ማለት ነው።
84 ናታን፦ እግዚአብሔር ሰጥቷል
85 አልዓዛር፦ትርጉሙ እግዚአብሔር ረድቷል
86 አስቴር፦ኮከብ
87 አቤሜሌክ፦የንጉሥ አገልጋይ
88 አቤሴሎም፦አባቴ ሰላም ነው
89 አብድዩ፦የእግዚአብሔር አገልጋይ
90 አብራም፦ታላቅ አባት
91 አብርሃም፦የብዙዎች አባት
92 አኪያ፦እግዚአብሔር ወንድሜ ነው
93 አክዐብ፦የአባት ወንድም
94 ባሮክ፦ቡሩክ
95 አዳም፦መልካሙ
96 ኢሳይያስ፦ እግዚአብሔር ደኅንነት ነው
97 ባርቅ፦መብረቅ
98 ኢያሱ፦እግዚአብሔር አዳኝ ነው
99 ኢዮሳፍጥ፦እግዚአብሔር ፈርዷል
100 ኢዮራም፦እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ
101 ኢዮርብዓም፦ሕዝቡ እየበዛ ይሄዳል
102 ቤተልሔም፦የእንጀራ ቤት
103 ኢዮአስ፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
104 ኢዮአቄም፦እግዚአብሔር አቆመ
105 ኢዮአብ፦እግዚአብሔር አባት ነው
106 ኢዮአታም፦እግዚአብሔር ፍጹም ነው
107 ኢዮአካዝ፦እግዚአብሔር ይዟል
108 ኤልሳዕ፦እግዚአብሔር ደኅንነት ነው
109 ኤልያስ፦እግዚአብሔር አምላክ ነው
110 ኤልያቄም፦እግዚአብሔር ያስነሳል
111 ኤዶም፦ቀይ/የገነት ሌላ ስም ነው
112 እስራኤል፦ከእግዚአብሔር ጋር ይታገላል ያሸንፍማል
113 ኤልሳቤጥ፦እግዚአብሔር መሐላየ ነው
114 ኤልሻዳይ፦ሁሉን ቻይ አምላክ
115 ሀሌሉያ፦እግዚአብሔርን አመስግኑ
116 ሰሎሞን፦ሰላማዊ
117 ኬብሮን፦ኅብረት
118 አዛርያስ፦እግዚአብሔር ረድቷል
119 ኤደን፦ደስታ
120 ዖዝያን፦እግዚአብሔር ኃይሌ ነው
121 ዘካርያስ፦እግዚአብሔር ያስታውሳል
122 ይሳኮር፦ ዋጋዬ
123 ይዲድያ፦በእግዚአብሔር የተወደደ
124 ዮሐናን፦እግዚአብሔር ጸጋ ሰጪ ነው
125 ዮሐንስ፦እግዚአብሔር ጸጋ ነው
126 ዮሴፍ፦ይጨምር
127 ዮናስ፦ርግብ
128 ዮናታን፦እግዚአብሔር ሰጥቷል
129 ዮአኪን፦እግዚአብሔር ያቆማል
130 ዮካብድ፦እግዚአብሔር ክብር ነው
131 ምናሴ፦ማስረሻ
132 ዮፍታሔ፦እግዚአብሔር ይከፍታል
133 ዲቦራ፦ንብ
134 ዳንኤል፦እግዚአብሔር ፈራጅ ነው
135 ጎዶልያስ፦እግዚአብሔር ታላቅ ነው
136 ጽዮን፦አምባ
137 ጳውሎስ፦ብርሃን ማለት ነው።
138 ሴት፦ምትክ ማለት ነው።
139 ጴጥሮስ፦አለት ማለት ነው።
140 ሄኖክ፦ታደሰ ማለት ነው።


ምንጭ:-ቅዱሳት መጻሕፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት እንዲሁም የአንድምታ ትርጓሜ መጻሕፍት አወጣጥቼ ነው የጻፍኩት።

መ/ር በትረ ማርያም አበባው
(የትርጓሜ መጻሕፍት መምህር)

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
በጸሎት ውስጥ በመትጋት ብዛት ወደ እግዚአብሔር መድረስ ትችላላችሁ !!

እግዚአብሔርን ከወደዳችሁት ትጸልያላችሁ። አብዝታችሁ የምትጸልዩ ከሆናችሁ ከቀን ወደ ቀን ለእርሱ ያላችሁ ፍቅር እየጨመረና እየጠለቀ ይሄዳል። ይህ ደግሞ የተለመደ ነገር ነው ምክንያቱም አንድ ሰው ከወደዳችሁ ከእርሱ ጋረ መነጋገርን ትወዱታላችሁና። ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ጸሎት ነው።

በመጸለይ እንዴት መጸለይ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ። ለማለት የፈለግሁት ወደ እርሱ ፍቅር በሚመራችሁ መንገድ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ ትማራላችሁ ለማለት ነው።

በጸሎት ውስጥ በመትጋት በጸሎታችሁ ውስጥ ወደ ምትናገሩት ወደ እያንዳንዱ ቃል ጥልቀት ልትደርሱ ትችላላችሁ። ከዚህ በተጨማሪ ከቀን ወደ ቀን ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር እየተጠጋችሁ ትመጣላችሁ ከእርሱ ጋር ለመነጋገርም ትናፍቃላችሁ። ስለሆነም ጸሎት እንዴት እግዚአብሔርን መውደድ እንዳለባችሁ ያስተምራችኋል።

እንዲህ ባለ ጠባይ በጸሎታችሁ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገሩ አንደበታችሁ ከእርሱ ጋር እንዴት መነጋገር እንዳለባችሁ እየለመደ ይመጣል። ይህ ደግሞ አዲስ ቋንቋ መማር የሚፈልግ ሰው ይመስላል። ይህ ሰው ይህን ቋንቋ በሚገባ ባያውቅና መጀመርያ ላይ ቢሳሳትም እንኳ ይህን ቋንቋ መናገር አለበት። ብዙ ጊዜ በመደጋገም ግን አንደበቱ ቋንቋውን ይለማመደዋል በሚገባ እስከሚጠቀምበት ድረስም ቀላል እየሆነለት ይመጣል።

በእናንተም ቢሆን እንዲሁ ነው ይበልጥ ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገራችሁ ስትመጡ አንደበታችሁ ይበልጥ ከእርሱ ጋር መነጋገርን እየለመደ ይመጣል። ከዚህ በኋላ በፍቅር ስሜት ውስጥ ሆናችሁ ከእርሱ ጋር መነጋገርን ታውቃላችሁ።

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እናት እና አባት ማን ማን ይባላሉ
#ግዝረት
ግዝረት ከጌታችን ከመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው፡፡ እነዚህ ንዑሳን በዓላት የሚባሉትም ስብከት፣ ብርሃን፣ ኖላዊ፣ ግዝረት፣ ቃና ዘገሊላ፣ ልደተ ስምዖን፣ ደብረ ዘይት፣ የመጋቢት መስቀልና መስቀል ናቸው፡፡ ነቢያት ይወርዳል፤ ይወለዳል ብለው በትንቢት ይጠባበቁት የነበረው መሲሕ የዓለም ብርሃን፣ የነፍሳት ጠባቂ መሆኑን አምነን የምናከብራቸው ስብከት፣ ብርሃንና ኖላዊ ይባላሉ፡፡
ከእናቱና ከደቀመዛሙርቱ ጋር በሰርግ ቤት የተገኙበት ቃና ዘገሊላ፣ በአርባ ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበትና አረጋዊ ስምዖንን የሰላሳ ዓመት ጎልማሳ የሆነበት “ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ ዐይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና” በማለት የተናገረበት ልደተ ስምዖን ከንዑሳን በዓላት ይመደባሉ፡፡ የዚህ ጽሑፍ ትኩረት ግዝረት በመሆኑ ሀተታዬን ወደ እሱ እመልሳለሁ፡፡
ፍቅር ወልድን ከዙፋኑ ስቦት ወርዶ ሥጋ ማርያምን ተዋሕዶ፣ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ማሕፀኗን ዓለም አድርጎ ከቆየ በኋላ ታኅሣሥ ሃያ ዘጠኝ በዘመነ ማቴዎስ ተወለደ፡፡ በተወለደ በስምንተኛ ቀኑ ሥርዓተ ኦሪትን ሊፈጽም ተገረዘ፡፡ ግዝረትን በስምንተኛው ቀን መፈጸሙ፣ በተወለደ በአርባ ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ መሔዱ ሕገ ኦሪትን ሊያጸና፣ ሊፈጽም፣ ምሳሌውን በአማናዊው ሊተካ እንጂ ኦሪትን ሊሽር ላለመምጣቱ እማኝ ምስክር ነው፡፡ የተሻረ ነገር መታሰቢያ የለውም የተፈጸመ፣ በምሳሌና በትዕምርታዊነት የተወከለ ግን ጥንተ ታሪኩን፣ ትንቢቱን ጠይቀን ምሳሌውን ከትርጓሜ መጻሕፍት እንረዳለን፡፡
ግዝረት አይሁድ የአብርሃም ልጅ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማኅተም ነው፡፡ በሕግና በሥርዐት የሚመሩ መሆናቸውን አንድ አምላክ ማመናቸውን የገለጡበት ነው፡፡ አይሁድ በግዝረት የአብርሃም ልጅነታቸውን እንዳረጋገጡ፣ ክርስቲያኖችም በጥምቀት የሥላሴ ልጅነታቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ ይህም የሚሆነው ግዝረት የጥምቀት ምሳሌ መሆኑን ያስረዳል፡፡ በሐዲስ ኪዳን ጥምቀት እንጂ መገረዝ፣ አለመገረዝ አይጠቅምም፡፡ በሐዲስ ኪዳን ግዝረት በፍቃድ እንጂ እንደ አይሁድ እኛም የአብርሃም ልጆች እንድንባል የምንገረዝ አይደለም፡፡
ለእኛ ለክርስቲያኖች ከሥላሴ በመንፈስ ቅዱስ መወለድ እንጂ መገረዝ የአብርሃም ልጆች አያሰኘንም፡፡ አለመገረዝ እንደማይጠቅም ቢያውቅም ጌታችን መገረዝ ያስፈለገው ሕገ ኦሪትን ለመፈጸም ሲሆን በእኔ ግን ምስጢረ ጥምቀትን ፈጽሜ አድናችኋለሁ ሲለን ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የማይጠቅምና ለነገረ ድኅነት የማያበቃ ነገር ቢያጋጥመን እንኳ በጥበብና በማስተዋል እንድናደርገው ሲያስተምረን ነው፡፡ ሥርዐተ ኦሪታችንን ስላፈረሰብን ለሞት አበቃነው ብለው ምክንያት እንዳያገኙና ይህንን ስበብ አድርገው ከነገረ ድኅነት ተለይተው እንዳይቀሩ የሚያደርጉትን በማድረግ፣ የሚወዱትን በመውደድና አብሯቸው የሥርዐታቸው ተካፋይ በመሆን በፍቅር ስቦ ወደ አማናዊው ድኅነት፣ ወደ ጥምቀትና የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ወደማመን መልሷቸዋል፡፡
የመምህሩን አሰረፍኖት የሚከተለው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በደርቤን በሚያስተምርበት ወቅት ጢሞቴዎስ ሲከተለው መገረዝ አለመገረዝ ጥቅምም ጉዳትም እንደሌለው እያወቀ የገዘረው በዙሪያው ብዙ አይሁድ ስለነበሩ እነርሱን ላለማስከፋትና ላለማስደንበር መሆኑን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ “.. የኦሪት ሕግ ለማዳን ብቁ አለመሆኗን እየደጋገመ በድፍረት ይሰብክ የነበረው መምህረ አሕዛብ ቅዱስ ጳውሎስ እንኳ አይሁድን ላለማስደንበር ሲል ሥርዐተ ኦሪትን ይፈጽም ነበር፡፡” /1978፣ 29/ በማለት ገልጸዋል፡፡
ግዝረት ለእስራኤል ከአብርሃም ለመወለዳቸው ምልክት ብቻ ሳይሆን የአብርሃምን ሃይማኖት ለመያዛቸውም መታወቂያ ነበረች፡፡ ጌታችንም ምንም እንኳ የባሕርይ አምላክ ቢሆን በሥጋ የአብርሃም ልጅ ነውና የአብርሃም ልጅነቱን የአብርሃምን ሃይማኖት ማጽናቱን ለማስረገጥ ግዝረትን ፈጸመ፡፡ አንድም በግዝረት ደም ይፈስሳለና አብርሃም በዘጠና ዘጠኝ ዓመቱ በመገረዝና ደሙን በማፍሰስ አበ ሰማዕታት ተብሏልና ግዝረት የሰማዕትነ ምሳሌም ነው፡፡


ጥር ስድስት በሚነበበው ስንክሳር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አረጋዊ ዮሴፍን ሕፃኑን የሚገርዝ ባለሙያ ፈልጎ እንዲያመጣ እንደነገረችው፣ አረጋዊውም ባለሙያውን ፈልጎ እንዳመጣ ይናገራል፡፡.

ባለሙያውም ሕፃንን በደምብ ያዙልኝ ብሎ ለመግረዝ ሲሰናዳ ባለሙያ ሆይ ደሜ ሳይፈስ መግረዝ ትችላለህን ብሎ እንደጠየቀው፣ ከስቅለቱ በፊት ደሙ እንደማይፈስ እንዳስተማረው፣ በዚህም ምክንያት ለመግረዝ የመጣው ባለሙያ፣ አምላክ ወልደ አምላክ መሆኑን አምኖ እንደሰገደለት ለመግረዣ ያዘጋጀው ምላጭም እሳት ላይ እንደተጣደ ቅቤ መቅለጡን ይተርካል፡፡

በመቀጠልም ክርስቶስ ዘር ምክንያት ሳይሆነው እንደተፀነሰ፣ ማኅተመ ድንግልናዋን ሳይለውጥ እንደተወለደ እንደ ነቢዩ ሕዝቅኤል “ሳይከፈት ገብቶ ሳይከፍት እንደወጣ” ስለት ምክንያት ሳይሆነው፣ በግዝረት ምክንያት ደም ሳይፈስ በተአምራት ተገረዘ፡፡ በአጠቃላይ ግዝረት በኦሪት የአብርሃም ልጅነትን፣ የአብርሃምን ሃይማኖት መያዝን ማረጋጋጫ ማኅተም ሲሆን በሐዲስ ኪዳን በጥምቀት ተተክቷል፡፡

ለአማናዊው ግዝረት /ለጥምቀት/ ምሳሌ በመሆኑም በሥራ የአብርሃም ልጅነትን፣ በእምነት የሥላሴ ልጅነትን አግኝተንበታል፡፡ ወርደህ ተወልደህ፣ በነፍስ በሥጋ፣ ከተቆራኘን ባለጋራ አድነን ብለን የተጣራነው ተሰመቶ፣ ሥርዓተ ኦሪትን ፈጽሞ ወደ ሥርዓተ ሐዲስ የሚያሸጋግረን መሆኑን ያመንበት፣ በጥምቀቱ ቦታ በዮርዳኖስ የተቀበረው የባርነታችን ደብደቤ የሚቀደድ መሆኑን በምሳሌ ያወቅንበት ግዝረት ነው፡፡
@ጥር 6 ቀን ከሚነበበው ስንክሳር የተወሰደ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ገሃድ ምንድን ነው?

ገሃድ መገለጥ መታየት ነው፡፡ በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት እድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲህ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኃላ በ 30 ዓመት እድሜው በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ይሰቀላል ይሞታል ይነሳል ብለው የተናገሩለት መሲሕ እርሱ መሆኑ ተገልጦአልና፡ አንድም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠለት በመሆኑ ገሃድ ይባላል፡፡ (ማቴ 3፡13-17)
ይህን በማሰብ የምንጾመው ጾም “የገሃድ ጾም” ይባላል፡፡ ቀኑም በዓለ ጥምቀት ከመዋሉ አንድ ቀን ቀድሞ ማለትም ጥር 10 ቀን ለ 11 አጥቢያ ነው፡፡ስለዚህ ጥር 10 ቀን ከ ሰባቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው የገሃድ ጾም ነው ማለት ነው!

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
+ ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ +

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታቦታት ላይ የተጻፈው ምንድር ነው? ተብለው ቢጠየቁ መልስዎ ምን ይሆን? ‹ዐሥርቱ ትእዛዛት ተጽፈዋል› ካሉ መልስዎ ትክክል አይደለም፡፡ ትክክለኛውን መልስ ከመመልከታችን በፊት ጥቂት ነገሮች ስለ ታቦት እንመልከት፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ታቦት አስፈላጊነት በሚሠጡ ማብራሪያዎች ላይ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት የሚናገሩ ጥቅሶችን በመጥቀስ በመሆኑ ምክንያት ስለ ታቦት የሚነሡ ጥያቄዎች እንዳያቋርጡ ያደረገ ይመስላል፡፡ ስለዚህ በዚህች አጭር ጽሑፍ ‹ነገርን ከሥሩ› የሚለውን አካሔድ ሳንከተል በቀጥታ ስለ ሐዲስ ኪዳን ታቦት ብቻ እንመለከታለን፡፡

ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጌታችን በመጨረሻዋ ምሽት ሐሙስ ምሥጢረ ቁርባንን ባስተማረ ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱ በተሰበሰቡበት ‹‹እንጀራውን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ሠጣቸው እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ እንካችሁ ጠጡ ይህ ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው አለ›› (ማቴ. 26፡26) ጌታችን አስቀድሞ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ብሎ በትምህርት የመሠረተውን ምሥጢረ ቁርባን በተግባር ለሐዋርያቱ በዚህ መልኩ አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ. 6፡56) ሐዋርያቱም ከጌታችን ዕርገት በኋላ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹እንጀራውን በመቁረስ ይተጉ ነበር›› (ሐዋ.2፡42) ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ ሠጥቻችኋለሁ›› በማለት ሥጋ ወደሙን እንዴት መቀበል እንደሚገባና ‹ሳይገባው የሚቀበል የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ›› እንዳለበት በማስተማር የቁርባንን ሥርዓት ደነገገ፡፡ (1ቆሮ. 11፡23-30)

ልብ እንበል የክርስቶስ ሥጋና ደም መሠጠቱን የሚያምን አንድ ክርስቲያን ይህ የከበረ ሥጋና ደም እንደ ተራ ማዕድ በየቦታው ፣ በየጠረጴዛው ሊቀርብ ይችላል ብሎ ለማሰብ እጅግ ይከብደዋል፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ስደትዋ እስካበቃበት ዘመን ድረስ በሒደት እየተሻሻለ በመጣ የቤተ መቅደስ ሥርዓት የሐዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት በክብር ለመሠዋትና ለምእመናን ለማቀበል በቅታለች፡፡ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣ መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉት አሮንና ልጆቹም የተለየ ልብስ ለብሰው የበጉን ደም በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ቀርነ ምሥዋዕ (የመሠዊያ ቀንድ) ላይ እየቀቡ ሥርዓቱን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ለበግና ለፍየል መሥዋዕት ይህ ሁሉ ክብር ከተሠጠ እንደ በግ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው የእግዚአብሔር በግ ፣ እንደ ሊቀ ካህናትነቱ እጁን በመስቀል ላይ ዘርግቶ የተሠዋውና ሥጋና ደሙን እንካችሁ ብሉ ብሎ የሠጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት መሠዊያ ምንኛ የከበረ ይሆን?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣ በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ ከሠጠው ታቦት ጋር አንድ አይደለም፡፡ የቀደመው ታቦት በአራት ካህናት የሚያዝ በውስጡ ጽላት የሚቀመጥበት ሲሆን የአሁኑ ታቦት ግን የጽላት ቅርጽ ያለው ጽሌ (ሰሌዳ) ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት በሦስት ስያሜ ትጠራዋለች - የቃልኪዳኑ ታቦት ፣ ጽላት እና መሠዊያ ብላ፡፡ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስላደረገው ስለ ቀድሞ ቃልኪዳን ሳይሆን ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ተብሎ ስለተሠጠው እና ‹‹ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› ብሎ ጌታችን ስለ ሠጠን አዲሱ ኪዳን ነው፡፡ (ማቴ. 26፡26-30) የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው በሥጋ ወደሙ ስለተሠጠን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ታቦት መባሉ ደግሞ እግዚአብሔር በረድኤት የሚያድርበት ፣ በሥጋ ወደሙ ደግሞ በአካል የሚገለጥበት ዙፋን ስለሆነ ነው፡፡

ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/)

አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡ የኦሪቱን ያልመሰለው አሁን ያለነው ሐዲስ ኪዳን ላይ ስለሆነና የታቦቱ አገልግሎት የተለየ ስለሆነ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦ ት ከቀድሞው አንድ ታቦት ተለይቶ በቁጥር የበዛውም ለብዙዎች መድረስ ያለበት የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት መሠዊያ ስለሆነ ነው፡፡ መድኃኒት ቤት የሚበዛው መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሲበዙም አይደል? ታቦት የበዛው በታቦቱ የሚሠዋው መሥዋዕት ለብዙዎች ስለ ኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰውና ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻው ያለሱ ሕይወት የላችሁም የተባልነው ሥጋና ደሙ ለኃጢአት በሽተኞች ስለሚያስፈልገን ነው::

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ ‹‹የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ግን (የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት) የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት (ጌታችን) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊያ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው፡፡›› (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 109) ሌላው አስገራሚ ነገር አቡነ ጎርጎርዮስ በታቦት ሥርዓት ከግሪኮች አንዲሚስዮን ጋር እንደምንመሳሰል ጠቅሰው ሲጽፉ ግሪኮቹ ደግሞ ስለ አንዲሚስዮን ሲያብራሩ ከኢትዮጵያ ታቦት ጋር የሚመሳሰል ብለው መጻፋቸው ነው።

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ. 2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያከብር አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡
2024/09/25 14:27:16
Back to Top
HTML Embed Code: