ሰይጣንን አጠመቁት ማለት ምን ማለት ነው ? *****
/በመምህር ቢትወደድ ወርቁ/
ጌታችን ሰዱቃውያንን " መጻህፍትና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ " ማቴ 22:29 እንዳላቸው ዛሬም የመጻህፍትን ፊደል (ገጸ ንባብ) ብቻ እያዩ ገደል ገብተው ገደል ሊከቱን የተነሱ ሰዎች እንደ አሸን ፈልተዋል:: ከሰሞኑ ብቻ ሳይሆን ከጥንቱም በገድለ ተክለ ሃይማኖት ጻድቁ ሰይጣንን እንደያዙት እንደገረዙት እንዳጠመቁትና በመጨረሻም ለምናኔ ዓለም እንዳበቁት የሚገልጸውን የገድል ክፍል ጠቅሰው ኦርቶዶክሳውያንን ሊያሸማቅቁን ይፈልጋሉ:: ዳሩ ግን የቅዱሳት መጻህፍትን አጻጻፍ ምሥጢር ለተረዳ ሊሸማቀቁ የሚገባቸው እነርሱ መሆናቸውን ይረዳል ባለማወቃቸው ምክንያት ከገቡበት የስንፍና ዐዘቅት እንዲወጡም ይመኝላቸዋል::
በመጽሐፍ እንደተነገረን ሰው ክቡር ፍጥረት ነው::ክቡር የሚሰኝበትን ግብር(ሥራ) ይዞ ጸንቶ ከኖረ "እንደ መልአክ ሆነ" : "እንደ መልአክ ይሆናል" የሚባልበት ደረጃ ይደርሳል:: ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ "ፊቱ እንደ መልአክ ፊት ሆኖ አዩት" የሐዋ 6:15 ተብሎ የተነገረለትን ምሥክርነት ስንመለከት ነው:: ጌታችንም ሰው ፈቃደ እግዚአብሔርን ሲፈጽም በህጉ በትዕዛዙ ጸንቶ ሲኖር ከክብር ወደ ክብር ከኃይል ወደ ኃይል በመሸጋገር እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደሚሆን ተናግሯል:: ማቴ 22:29-30 መዝ 83(84): 6-7 ይህም ብቻ ሳይሆን ሰው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሲኖር የሥጋ ፈቃዱን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሲሰቅል " ክርስቶስን መሰለ" እስከ መባል ይደርሳል:: ሐዋርያው "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ " 1ቆሮ11 :1 " እርሱንም የሚመስሉትን አክብሯቸው" ፊልጵ 2:29 ማለቱ ለዚህ ነው :: ሰው በእምነት በበጎ ምግባር በትሩፋት ሲኖር ከክብር ወደ ክብር እንደሚሸጋገር የክብሩም ጣሪያ ፈጣሪውን መምሰል እንደሆነ እንደ ሥጋ ፍላጎቱ ከዚያም ሲያልፍ እንደ ሰይጣን ፈቃድ ሲኖር ኖሮም በሰይጣን አሠራር በጥንቆላ በሟርት ሞራ በመግለጥ በመተት ደም
በማፍሰስ በአመድ በመንከባለል ምናምን አዙሮ በመጣል በመሳሰሉት ሰይጣናዊ ግብሮች ጸንቶ ሲኖር ከውርደት ወደ ውርደት ከሰውነት ወደ እንስሳነት ከእንስሳነትም ወደ ቁስነት ይሸጋገራል:: ከውርደት ወደ ውርደት አሸጋግሮ " እንስሳ" "ድንጋይ" "ሰይጣን" የሚያሰኘውም ሰውነቱ ሳይሆን ክፉ ግብሩ ጸያፍ ተግባሩ ነው:: የውርደቱ መጨረሻም "እንደ ሰይጣን ሆነ" " ሰይጣን ሆነ" መባል ይሆናል:: ይህ የቅዱሳት መጻህፍት እውነት እንደ ሆነ የሚከተሉትን ኃይለ ቃላት በማንበብ እንረዳ :
ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት "ሰው ክቡር ፍጥረት ሆነ ሳለ አላወቀም ነገር ግን እንደሚጠፉ እንስሳት መሰለ" መዝ 48:12
በዮሐንስ ራእይ መጽሐፍም አስማተኞች ሴሰኞች ነፍሰ ገዳዮች ጣዖት አምላኪዎችና ሐሰተኞች አምስቱ ውሾች ተብለዋል ራእይ 22:15
ጌታችን ሔሮድስን ከቀበሮ ጋር የሚያመሳስል ጠባይዕን ጠባዩ ስላደረገ ቀበሮ ብሎታል:: ሉቃ 13:32
ሐዋርያቱ ቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስም የሐሰት ትምህርት የሚያስተምሩትን ንስሐ ከገቡ በኇላ ወደ ቀደሞ ክፉ ሥራቸው የሚመለሱትን በውሻና በእሪያ መስለዋቸዋል::
መጥምቁ ዮሐንስም ልባቸው እንደ አልማዝ የጠነከረ አይሁድን በድንጋይ መስሏቸዋል ማቴ 3:1-10
ቃል በቃልም ናቡከደነጾር እግዚአብሔርን ንቆ ጣዖትን አምልኮ ጥንቆላና ሟርትን ሞራ መግለጥና መተትን በግዛቱ እንዲሠለጥን በማድረጉ በትዕቢትም በመታጀሩ ምን እንደገጠመው መጽሐፍ ሲነግረን " መኖሪያው ከምድረ በዳ አህዮች ጋር ነበረ እንደ በሬ ሳር በላ አካሉም ሰማይ ጠል ረሰረሰ " ዳን 5:20-21 ይላል:: ይህ እግዚአብሔር ላይ ማመጽ መጨረሻ ውርደቱ ሰይጣንን መስሎ ሰይጣን የሰይጣን ልጅ መባል ነው::
ከእናንተ መካከል አንዱ ዲያብሎስ ነው ዮሐ 6:70-71
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ይሁዳ ለደቀመዛሙርቱ የተናገረው ቃል ነው:: ጌታችን ይሁዳን ዲያብሎስ ብሎ የጠራው ይሁዳ በጥንተ ተፈጥሮው ዲያብሎስ ሆኖ ሳይሆን ግብሩ ሰይጣናዊ በመሆኑ ነው:: ይሁዳ ሰይጣንን የሚመስል ሳይሆን ሰይጣን እንደተባለ እናስተውል:: ይሁዳ በክፉ ግብሩ ጸንቶ በመኖሩ ዲያብሎስ እንደተባለ ቀረ:: ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችንን "አተሙት" ባለው ጊዜ ይህ ሀሳብ ከሰይጣን እንጂ ከእርሱ ባለመሆኑ "አንተ ሰይጣን" ብሎት ነበር:: ንስሐ በመግባቱ ግን ቅዱስ ለመባል በቅቷል:: ማቴ 16:23 :: ከክፉ ከአመጸኞች ከነፍሰ ገዳዮችና ከመሳሰሉት ሰዎች መሐከል መኖርም ከሰይጣን ጋር መኖር እንደሆነ ተነግሯል::ራእይ 2:9-13 ሰው በግብሩ ሰይጣን የሰይጣን ልጅ እንደሚባል መጻህፍት ደጋግመው ይነግሩናል:: ዮሐ 8:44 በአባቶቻችን የገድል መጻህፍትም በጥንቆላ ደም በማፍሰስ በመተት ጸንተው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች "ሰይጣን" መባላቸው ለዚህ ነው:: ከእነዚህ መጻህፍትም መካከል አንዱ ገድለ ተክለሃይማኖት ነው:: በዚህ የገድል መጽሐፍ ጻድቁ ሰይጣንን እንደ ያዙት እነደገረዙት እንዳጠመቁትና ለምንኩስናም ክብር እንዳበቁት ተጽፏል:: ሰይጣን የተባለው በቁሙ ከሰማይ የወደቀው ሰይጣን የመሰላቸው ሰነፎች በተለይ ተሐድሶዎቹና አባቶቻቸው ሉተራውያን ከገድሉ ያነ አውጥተው ሲሳለቁ እያየናቸው ነው:: በዚህ ገድል ላይ ሰይጣን የተባለው በኃጢአት ጸንቶ በጥንቆላና ሟርት እየኖረ ምትሀታዊ ነገሮችን እየሠራ በባህርም እየኖረ ከእሳትም ገብቶ እየወጣ የሰው ደምን እንደ ነብር እየመጠጠ ሰዎችንም እያሳተ ይኖር የነበረ ሰው ነው:: በቤተክርስቲያንም ልቡሰ ሥጋ ጋኔን ( ሥጋ የለበሰ ጋኔን) ይባላል:: ይህንም ከቤተክርስቲያናችን መምህራን በተጨማሪ E A W Budge በእነዲህ አይነት ሰይጣናዊ ግብር ጸንተው የነበሩ ሰዎች በገድለ ተክለሃይማኖት ሰይጣን እንደተባሉ መስክሯል:: (The life and miracles of Teklehaymanot : london 1906 : P 80 ) መቼም ሰው የሚበሉ ደም የሚመጥጡ ሰዎች እነደነበሩ በእጃችን ባለ ተንቀሳቃሽ ስልክ google ን ብነጠይቀው ያስነብበናል:: መናፍቃኑ አልተረዱትም እንጂ በዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ "አውሬው" እየተባለ የተጠራው በቁሙ አውሬ ሳይሆን የዕለተ ዓርብ ፍጥረት ሰው ነው:: ሐዋርያው ይህን አውሬ " የአመጽ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ" ብሎ ጠርቶታል :: 2ተሰ 2:3 ራእይ 13:1-15::
ቢትወደድ ወርቁ
በሐምሌ 2009 ዓ ም እንደለጠፈው ሳይቀነስ ሳይጨመር
ከፃድቁ በረከት ይክፈለን።
@EotcLibilery

Forwarded from Markdown List 📋
የጸሎተ ሃይማኖት ትንታኔ.pdf
2.2 MB
#ጸሎተ_ሃይማኖት
የቤተክርስቲያናችን ዋና ጸሎት የሆነውና በቤተክርስቲያናችን የ11 ሰዓቱ የማታ ጉባኤ ከመጀመሩ በፊት የሚፀለየው ጸሎተ ሃይማኖት ትንታኔ ወይም ማብራሪያ እነሆ

Audio
✝የሰውነትህ ብርሃን ዓይንህ ነው✝
Size 23.4MB
Length 1:07:07
በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Size 23.4MB
Length 1:07:07
በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
✝ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም✝
Size 13.8MB
Length 39:38
በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Size 13.8MB
Length 39:38
በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
+ ጌታ የተወለደው የት ነው? +
የገና ዋዜማ የት ልትሔድ አሰብህ? ምሽቱንስ የት ልታሳልፍ ነው? የትኛው ሆቴል? የትኛው የሙዚቃ ድግስ? "የገናን በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ ልዩ የሙዚቃ ድግስ" ላይ ጌታ የለም:: ባለ ልደቱ ጌታ የት ነው ያለው? አድራሻው ከጠፋብህ የተወለደ ዕለት የሆነውን ልንገርህ!
የተወለደውን ክርስቶስ ለማየት ብዙ ሀገራትን አልፈው ተጉዘው የመጡት ሰብአ ሰገል በኮከብ ተመርተው ነበር::
ለእስራኤላውያን እረኞች በታሪካቸው ውስጥ በሚያውቁአቸውና በለመዱአቸው መላእክት ልደቱን የገለጠው አምላክ ኮከብ ሲቆጥሩና ሲጠነቁሉ ለኖሩት ሰብአ ሰገል ደግሞ በሚያውቁት ኮከብ መራቸው::
ሕጻኑ ክርስቶስ ገና ከመወለዱ ብዙ እንደ ጣዖት የሚመለኩ ነገሮችን ድል አድራጊ መሆኑን አሳየ::
በሲና በረሃ እስራኤል ጥጃን አምላክ ብለው በወርቅ ጣዖት ሠርተው ነበር:: በቤተልሔም ጥጃ ትንፋሹን ለክርስቶስ በመገበር አምላኬ እርሱ ነው ሲል መሰከረለት:: በሬም ገዢውን አወቀ ሕዝቤ ግን አላወቀኝም የሚለው ተፈጸመ:: ከዋክብትንና ፀሐይን ያመልኩ የነበሩን የዞረዳሸት (ዞራስትራኒዝም) ፍልስፍናን የሚያምኑ ሰብአ ሰገልም በሚያመልኩት ኮከብ ፈጣሪያቸውን አገኙ:: ቅዱስ ኤፍሬም እንዳለው "የሚያመልኳት ፀሐይም በሰብአ ሰገል ጉልበት ለፈጣሪዋ ሰገደች"
ኮከብ የሚወጣበት ጊዜ በዚያን ቀን የሰውን ዕጣ ፈንታ ይወስናል ብለው የሚያምኑም ብዙዎች ናቸው:: ይህ የሆነው በኮከቤ ምክንያት ነው! ኮከባችን አይገጥምም የሚባባሉ ብዙዎች ናቸው:: ይህ ሁሉ ባዕድ አምልኮ ነው:: ኤሳውና ያዕቆብ መንትዮች ናቸው:: የተወለዱት በአንድ ቀን ነው:: እነርሱ በተወለዱ ቀን የወጣው ኮከብም አንድ ነው:: "ኮከባቸው" አንድ ሆኖ ሳለ ምነው ነገራቸው ሁሉ አልገጥም አለ? ኮከባቸው ይገጥማል ምነው እነርሱ አልገጠሙም? ስለዚህ ሐሰት ነው::
የተወለደው ንጉሥ ግን ኮከቡ ዕጣ ፈንታውን የሚወስነው ሳይሆን ከዋክብትን በየስማቸው የሚጠራቸው በቁጥር የሚያውቃቸው ጌታ ነው:: እንደ ዮሴፍ 11 ከዋክብት ሐዋርያቱ ከይሁዳ በቀር የሰገዱለት እናቱ ማርያምም እንደ ያዕቆብ በልብዋ እያሰበች የተደነቀችበት የከዋክብት ጌታ የጨረቃ ንጉሥ የፀሐዮች ሁሉ ፀሐይ ነው እርሱ::
ሰብአ ሰገል መሪያቸው የነበረውን ኮከብ ሲያጡት ወደ ሔሮድስ መጡና "የተወለደው ንጉሥ ወዴት ነው?" አሉ::
እውነትም ጠቢባን ናቸው:: መንገድ ከጠፋብን : መሪ ኮከብ ካጣን ልደቱን የፈለግንበት እናክብር አላሉም:: የተወለደው ወዴት ነው? ብለው ቤተ መንግሥት ሔደው ጠየቁ:: ጥሩ በዓል ለማክበር ከቤተ መንግሥት የተሻለ ሥፍራ የለም:: በቤተ መንግሥት ራት እየበሉ ጮማ እየቆረጡ በዘፈን ታጅበው በዓሉን ማክበር ይችላሉ:: እነርሱ ግን የትም ቢሆን ንጉሡን ሳናገኝ አንቆይም:: እሱ የሌለበት ቦታ ቤተ መንግሥትም ቢሆን ልደቱን አናከብርም:: አይ ሰብአ ሰገል! ይህንን ዘመን መጥተው ቢያዩ ምን ይላሉ?
ወዳጄ አንተ የጌታን ልደት የት ታከብራለህ? መቼም
ልደት የሚከበረው ባለ ልደቱ ባለበት ሥፍራ ነው:: በእውነት የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በጭፈራ ቤት ነውን? በመጠጥ ቤት ነውን? የት ነው ያለው ብለህ ጠይቀሃል?
"የሚመራኝ ኮከብ የለም" ትል ይሆናል:: ምንም ቢሆን ግን ሕፃኑ በሌለበት ልደቱን ለማክበር መወሰን የለብህም:: ምንም ያሸበረቁ ሥፍራዎች ቢኖሩም እንዳትታለል:: የሔሮድስ ቤተመንግሥት ውበት የግብዣው ስፋት አታልሎህ የተወለደውን ንጉሥ እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ:: እሱ ከሌለበት ያማረ ሥፍራ ይልቅ እሱ ያለበት በረት ይሻልሃል:: እሱ ያልመረጠውን ሥፍራ መርጠህ ከመንገድ አትቅር:: "የተወለደው የአይሁድ ወዴት ነው" ብለህ ጠይቅ::
እሱ ደሃ ሆኖ ባለጠጋ የሚያደርግህን ንጉሥ በሚያልፍ ደስታ አትጣው:: በስካር በዝሙት በጭፈራ በሔሮድስ ቤተ መንግሥት ቀልጠህ ቀርተህ የተወለደውን ሕፃን ሳታየው አትቅር:: እሱ በተወለደባት ሌሊት አንተ ስትሞት አትደር:: እመነኝ የተወለደው ይሻልሃል ከሞቱት ጋር ጊዜህን አታጥፋ::
ሰብአ ሰገል "የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?" ብለው ለአይሁድ ንጉሥ ሔሮድስ ጠየቁት:: የአህያ ውኃ ጠጪው ሔሮድስ ክው ብሎ ቢደነግጥም ፈገግ ብሎ ላጣራላችሁ ቆይ ብሎ አቆያቸው:: መጽሐፍ አዋቂዎቹን ጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠሩ:: እነ ሊቄ መለሱ:: "እንደተነገረው ትንቢት ከሆነማ" አሉ ኩፍፍፍስ ብለው
"በይሁዳ ቤተልሔም ነው" ብለው የተወለደውን ንጉሥ አድራሻ ተናገሩ:: ሔሮድስ ከነተንኮሉ ለሰብአ ሰገል መልእክቱን አደረሰ:: ሰብአ ሰገልም ሔደው ለንጉሡ ሰግደው እጅ መንሻ አቀረቡ::
ሔሮድስን ትተን እስቲ የጸሐፍቱን ነገር ትንሽ እናስተውለው:: የተወለደውን ጌታ አድራሻ ጠቁመው ለሰብአ ሰገል መንገድ የመሩ እነርሱ ግን መንገድና እውነት ሕይወትም የሆነው ጌታ የተሰወረባቸውን የታወሩ መሪዎች በሽተኛ ሐኪሞች የተራቡ መጋቢዎችን እስቲ ልብ እንበላቸው:: "ጥሩምባ ነፊ ቀብር አይገኝም" ማለትስ አይሁድ ናቸው::
ሌላውን ወደ ጌታ እየመራ እርሱ ከጌታው የራቀ : የእርሱን ቃል ሰምተው ሰዎች ሲድኑ እርሱ በኃጢአት ቁስል የተወረሰ ስንት አይሁድ እለ? ቅዱስ አምብሮስ እንዳለው የኖህ መርከብ ሲሠራ ሚስማርና መዶሻ እያቀበለ የሠራ ነገር ግን ከጥፋት ውኃ ያልዳነ ስንት በየቤቱ አለ::
እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል ማለት ቀላል ነው:: እንደተጻፈው መኖር ግን ከባድ ነው:: ከመጽሐፍ ጥቅስ ማውጣት ቀላል ነው የሚጠቀስ ሕይወት መኖር ግን ከባድ ነው:: ወዳጄ ለብዙ ሰብአ ሰገሎች ስለተወለደው ንጉሥ ነግረሃል:: በአንተ ሕይወት ውስጥስ "የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?" ወይስ በአንተ ሕይወት ገና አልተወለደም? ወይስ እንደ እንግዶች ማደሪያ ቦታ የለም ብለህ መልሰኸዋል? ኸረ እኔ እንኩዋን የቆሸሸ ሕይወት ነው ያለኝ እሱ በእኔ አያድርም አትበል? እንደ በረት ብትሸት እንደ እንስሳ እየኖርህ ቢሆንም አትፍራ እርሱ አይጠየፍህም? ወደ ልብህ መለስ ብለህ እንዲህ ብለህ ራስህን ጠይቅ "በእኔ ሕይወት ውስጥ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?"
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 27 2012 ዓ ም
ሻሸመኔ ኢትዮጵያ
ተሻሽሎ የተጻፈ

የመንፈስ ቅዱስ በገና የሆነ ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ጌታ ልደት ከደረሰው ዝማሬ መካከል እንዲህ አለ
★ ★ ★
ዮሴፍ እግዚአብሔር ወልድን እንደ ሕፃንነቱ አቀፈው ፣ እንደ አምላክነቱም አገለገለው። በመሐሪነቱ እጅግ ደስ አለው በፈራጅነቱ ግን እጅግ ፈራው።
እንዲህ ሲል:
የልዑልን ልጅ ለእኔ እንደ ልጅ ይሆን ዘንድ ማን ሠጠኝ? እናትህ በጸነሰች ጊዜ ተቆጥቼ ነበር ፣ በስውር ልተዋትም አስቤ ነበር። በማኅፀንዋ ውስጥ ከድህነቴ ሊያወጣኝና ባለጠጋ ሊያደርገኝ የሚችል የተሰወረ ሀብት እንዳለ አላወቅሁም ነበር። ከእኔ ዘር የሚሆን ዳዊትስ አክሊል የደፋ ንጉሥ ነበር ፣ እኔ ግን የተናቀ ደሃ ሆንሁ። እንደርሱ ንጉሥ በመሆን ፈንታ አናጢ ሆንኩ። አሁን ግን እነሆ አክሊል ወደ ቤቴ መጣ ፣ የአክሊላት ሁሉ ጌታ በእቅፌ ነውና!
★ ★ ★
ድንግል ማርያም ሕፃኑን እያባበለች በመደነቅ ቃል ነደደች
እንዲህ ስትል
"ድንግሊቱን እጸንስ ዘንድ የሰጠኝ ማን ነው?
ይህንን አንድ ሲሆን የበዛ ፣ ታናሽ ሲሆን ታላቅ የሆነ ፣ ከእኔ ጋር ሲሆን በሁሉ የሞላ ሕፃን የሠጠኝ ማን ነው?
....
በእኔ [ማኅጸን] ውስጥ እያለህ ከእኔም ውጪ በሁሉ ቦታ ነበርህ ፣ በወለድሁህ ጊዜም ረቂቅ አምላክነትነህም ከእኔ ውስጥ አልወጣም። በእኔ ውስጥ ነህ ፣ ከእኔም ውጪ ነህ! ይህ ነገር ለእኔ ለእናትህን ያስደነቀኛል።
የሚታየው ሰውነህን በፊቴ ባየሁ ጊዜ የማይታየው አምላክነትህን በሕሊናዬ አየዋለሁ። ቅዱስ ሆይ በሚታየው ሰውነትህ ውስጥ አዳምን አየዋለሁ ፣ በማይታየው መለኮትህ ውስጥ ደግሞ በአንተ ሕልው ሆኖ የሚኖረውን እግዚአብሔር አብን አየዋለሁ።
አንተ ምንጭ ሆይ ለአንተ ለማጠጣት የጡቶችን ምንጭ እንዴት ልከፍታቸው ይቻለኛል? ሁሉን ከገበታህ የምትመግብ ሆይ እኔ አንተን ልመግብህ እንዴት ይቻለኛል? የክብርን ነጸብራቅ የተጎናፀፍከው ሆይ እንደምን በጨርቅ ልጠቀልልህ እችላለሁ?
ምን ብሎ እንደሚጠራህ አንደበቴ አያውቅም። አእላፋት ስሞች ለአንተ አይበቁህም ፣ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ስትሆን የሰው ልጅ ነህና ፣ የዳዊት ልጅ ስትሆን የማርያም ልጅ ነህና!
ልጄ ሆይ ከእኔ ጋር ሆነህ ሳለ ከሰው ልጆች ሁሉ ጋር በመሆንህ አልቀናም። ለሚያምንብህ አምላክ ነህ ፣ ለሚያገለግልህ ጌታ ነህ ፣ ለሚወድህም ሁሉን ያንተ ታደርገው ዘንድ ወንድም ነህ!"
የአንደበቶች ሁሉ ጌታን አንደበት እንደሌለው ያደረገው ምን ይሆን? ልጄ ሆይ አንተን በድንግልና መፅነሴን ክፉ ሰዎች እየዘለፉ ነው።
ቅዱስ ሆይ ለእናትህ አንደበት ሁነኝ ፣ አንተን ከማን እንደፀነስሁህ ይረዱ ዘንድ ተአምርህን አሳይ።
ሁሉን የምትወድደው ሆይ ስለ አንተ ብዬ የተጠላሁ ሆንሁ ፣ ለሰው ልጆች መሸሸጊያ የሆንህ አንተን በመፅነሴ መከራን ተቀበልሁ።
አቤቱ በዮናስ ላይ እንደተቆጣ ባሕር በእናትህ ላይ ተቆጥቷል።
ሔሮድስ የተባለ ማዕበል የባሕርን ጌታ ሊይዝህ ፈልጓል። የእናትህ ፈጣሪዋ ሆይ ወዴት እንደምሸሽ ንገረኝ"
💥💥💥💥💥💥
ጌታችን ስለተወለደባት ምሽት ደግሞ ቅዱስ ኤፍሬም አንዲህ አለ....
‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡
ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን ፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!
ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት ፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም!
ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡
ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን!
ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው
እንዳይታበይባት!
ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን
አንበቀልባት!
የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት!
የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!
ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው!
ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡
ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!
የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት!
ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!››
ታኅሣሥ 26 2013 ዓ ም

እንኳን አደረሳችኁ !
#ልደቱ_ለእግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ
#ጌና_እና_ልደት
ጌና እና ልደት ዋዜማና ክብረ በዓል /የተለያዩ ቀናት/ ቢኾኑም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ጌና ልደትን እየተካ እንጠቀምበታለን፤ ነገር ግን ይህ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡ ልዩነት ስላለውም የኢትዮጵያ ብርሃን የተባለው አፈ ጳዝዮን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለጌናና ለልደት ለ2ቱም በዓላት ለየብቻቸው በመጽሐፈ ምሥጢር ድርሰት ደርሶላቸዋል፡፡
#ጌና፤ የልደት በዓል ዋዜማ ቀን ሲኾን በዚህ ቀን ‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የተባለለትን ‹‹የገና ጨዋታ›› እንጫወታለን፤ የምንጫወትበት የኳሱ ስያሜ ‹‹ሩር›› ሲባል ስያሜውን ያገኘው፤ ሰብዓ ሰገል እልፍ እልፍ ሠራዊት አስከትለው የተወለደውን አይሁድ ንጉሥ ፍለጋ ወደ ንጉሡ ሔሮድስ ደርሰው ነበርና፤ ሔሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ፈልጎና በውስጡ ሸሽጎ ለሰብዓ ሰገል ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ስታገኙትም ንገሩኝ ብሎ ሰድዷቸዋል፤ ነገር ግን በዚያው ሳይነግሩኝ እንዳይሄዱ በማለት እነርሱ ሳያውቁ ‹‹ሩር›› የተባለ ሰላይ በመሃላቸው አስገብቶ ነበርና ሰብዓ ሰገልን ይመራቸው የነበረው ኰከብ ተሠውሮባቸዋል፤ ሰብዓ ሰገል ሠራዊታቸውን ቢያጣሩ ከመሃከላቸው የተቀላቀለ ሩር የተባለ የሔሮድስን ሰላይ አገኙ ይህንንም ሰላይ የሰብዓ ሰገል ሠራዊት አንገቱን በሰይፍ ቀልተውታልና ያን ለማስታወስ ዛሬ በገና ጨዋታ ላይ ሩር የተባለው ኳስ የሔሮድስ ሰላይን ‹‹ሩር›› እንዲያስታውስ አባቶች ሥርዐትን ሠሩ፡፡
#ልደቱ_ለእግዚእነ_ኢየሱስ_ክርስቶስ
#‹‹ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ::›› /#ቅዱስ_ያሬድ/
ጌታችን ለሰው ልጆች ብሎ፤ የሰው ልጆች ፍቅር አገብሮት ንጽሕትና ቅድስት ከኾነች ከእመቤታችን ያለ ወንድ ዘር በመጋቢት 29 ተጸንሶ ታኅሣሥ 29 በ1ዓ.ም. (ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ በ5,500 ዓመት) በበረት ተወልደ፡፡ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን በረት ቻለው፤ ወሰነውም በሌሊት መንጋቸውን የሚጠብቁ እረኞች ነበሩ፡፡ መልአኩ መጥቶ እንዲህ አላቸው፡- ‹‹እነሆ! ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡ ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ›› አላቸው፡፡ ሉቃ2፡10-12፡፡ ከመለአኩም ጋራ ሠራዊተ መላእክት መጥተው ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዕጓለ እመሕያው /ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ/›› አሉ፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ እረኞቹ እርስ በርሳቸው ‹‹እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ፣ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ›› ተባባሉና ፈጥነው መጡ፡፡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ፡፡ አይተውም ስለዚህ ሕፃን የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ፤ የሰሙትን ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር አደነቁ፤ የብርሃን እናቱ እመ አምላክ ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር፡፡ ሉቃ 2፡13-19፡፡
መላእክትም ሰማይ መንበሩ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆኑለት አምላክ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ በጎል ተኝቶ በጨርቅ ተጠቅልሎ አይተውት ደስ ብሏቸው ወደ ሰማይ ቢያርጉ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በዕሪና ከመንበሩ አይተውት ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት›› ብለው አመስግነውት በጣዕም ላይ ጣዕም፤ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ደስ ብሏቸዋል፡፡ ልደቱን ይሹታልና፤ መላእክትም ብቻ አይደሉም እንስሳትም አራዊትም ደስ ብሏቸዋል፡፡ #ይህም_ሊታወቅ_አንድ_ባሕታዊ_በቋራ_/_ኋላ_ማኅበረ_ሥላሴ_ገዳም/_ቋርፍ_ሲምስ_ቶራ_ሚዳቋ_ዮም_ተወልደ_ መድኀኔ_ዓለም_ዮም_ተወልደ_ቤዛ_ኵሉ_ዓለም_ዮም_ተወልደ_ከሣቴ_ብርሃን፡፡ እያለች ስትዘል አይቷል። በጌታችን በልደቱ የባሕር ውኃ ወተትና ማር ተራሮች እንጀራ እንጨቶችም የበረከት ፍሬ ሆነዋል፡፡ ልደቱንም በኮከብ ተረድተው ሰብአ ሰገል (የጥበብ ሰዎች) ስማቸውም ማንቱሲማር፣ ሜልኩ በዲዳስፋ የተባሉ የፋርስ ነገሥታት ከገነት የተገኘ ወርቅ፣ ዕጣን ከርቤ አምጥተው ገብረውለታል፡፡ /ዘኅ 20፡17፡፡
‹‹ሰው ሆይ! ፈጽመህ ደስ ይበልህ፣ እግዚአብሔር ዓለሙን ወዶታልና አንድ ልጁንም የሚያምንበት ሁሉ እስከ ዘለዓለም ፈጽሞ ይድን ዘንድ አሳልፎ ሰጥቷልና ልዑል ክንዱን ሰደደልን፡፡››
‹‹በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው፤ በቅዱሳን ላይ የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰው ሆኗልና ኑ ይህን ድንቅ እዩ፤ ስለተገለጠልን ምሥጢር ምስጋና አቅርቡ፤ ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና ቃል ተዋሕዷልና ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ፣ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት፡፡ የማይታወቅ ተገለጠ፣ የማይታይ ታየ፣ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥ ሰው ሆነ፡፡››
‹‹ከቅድስት ሥለሴ አንዱ ወልድ መዋረዳችንን አይቶ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ባሕርዩን ዝቅ አደረገና መጥቶ በድንግል ማኅፀን አደረ፤ ከብቻዋ ከኃጢአት በቀርም እንደ እኛ ሰው ሆነ፡፡ ነቢያት ትንቢት እንደተናገሩለት በቤተልሔም ተወለደ፤ ፈጽሞ አዳነን፣ ወገኖቹም አደረገን፡፡››
ይህችም ዕለት፤ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ትንቢት የተናገረላት ናት፡- ‹‹እነሆ ድንግል ፀንሳ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፣ ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች፣ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ /ት.ኢሳ. 7፥14/
**ነቢይ ሕዝቅኤል ‹‹እግዚአብሔርም አለኝ ‹ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች፣ አትከፈትም፣ የሚገባበትም የለም የእስራኤል ፈጣሪ እግዚአብሔር እንደተዘጋች ይገባባታልና ተዘግታ ትኑር››› አለ፡፡
**ነቢዩ ዳንኤልም ‹‹ሌሊት በራእይ አየሁ ‹እነሆ ታላቁ እንደ ሰው ልጅ በሰማይ ደመና መጣ፤ ዘመኑን ወደሚያስረጅ ደረሰ፣ ከፊቱም አቀረቡት፣ የዘላለም አገዛዝ፣ ጌትነት፣ መንግሥት ተሰጠው፡፡ ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል፤ አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው፤ መንግሥቱም የማያልፍ የማይጠፋ ነው››› አለ፡፡
**ዳግመኛም ኢሳይያስ ‹‹እግዚአብሔር እንደ እኔ የሥጋ መጋረጃ በመጋረድ ተገለጠልኝ›› አለ፡፡ አሁንም ደግሞ ‹‹አዲስ ሰማይ አዲስ ምድር እሠራ ዘንድ አለኝ›› አለ፡፡ ሁለተኛም ‹‹በእሴይ ሥር በትር ትወጣለች፣ ከእርሷም ጽጌ አበባ ይወጣል›› አለ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና ይኸውም ሥልጣን በጫንቃው የሆነ ክርስቶስ ነው፣ ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ይባላል›› አለ፡፡
**ነቢዩ ኤርምያስም ስለ እግዚአብሔር ‹‹በዚያን ወራት ለዳዊት ብርሃንን አወጣለሁ፣ በምድርም የቀና ፍርድን ያደርጋል፣ እግዚአብሔርም ያመኑትን ያድናቸዋል›› አለ፡፡
**ኤልሳም ‹‹እግዚአብሔር ከሰማይ ይወርዳል፣ በእስራኤል ልጆች አደባባይም በመመላለስ ለሕዝቡ ዕውነትን ያስተምራቸዋል፡፡ ከአብርሃም ልጅነት ልዩ ከሆኑ ወገኖች በቀር አሕዛብ ሁሉ ይታዘዙለታል›› አለ፡፡
**ናሆምም ‹‹እግዚአብሔር በእኔ አርአያ ይመጣል፣ ልብሱም እንደልብሴ ነው›› አለ፡፡

ኢዩኤልም ‹‹የእግዚአብሔር ዙፋን የሆነች ብላቴና ድንግልን አየሁ፣ እርሷም እንደ እሳት ያልባት ነበር፡፡ ስለእርሷ ‹ይህች ማናት/› ብዬ ኪሩብን ጠየቅሁት፡፡ እርሱም ‹ከአዳም ልጆች የተመረጠች የእግዚአብሔር ዙፋን ይህች ድንግል ናት፣ በእርሷም የተጎሳቆሉ አሕዛብ ይድናሉ፤ ለአመነባትም ረድኤትና መጠጊያ ናት› ብሎ ነገረው፡፡››
ዳዊትም በመዝሙሩ ‹‹እግዚአብሔር አንተ ልጄ ነህ፣ ዛሬም በተዋሕዶ ወለድኩህ አለኝ፡፡ ለምነኝ አሕዛብን ርስት አድርጌ እሰጥሃለሁ፣ ግዛትህም በመላው ዓለም ነው፡፡›› ዳግመኛም አብ አለ ‹‹ቀዳማዊ ወልድ በኃይል ቀን ካንተ ጋራ ሳለሁ ከአጥቢያ ኮከብ በፊት ከሆድ ወለድኩህ፣ እንደ መልከ ጸዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለሙ አገልጋይ ካህን ነህ ብሎ እግዚአብሔር ማለ፣ ከማለም አይፀፀትም፡፡››
ዕንባቆምም ‹‹አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም አይቼ አደነቅሁ፤ በሁለት እንስሳ መካከል አየሁህ›› (ዕን ፫፥፪)
**ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም ‹‹በበረት ውስጥ የዓለም ገዢ መተኛት እጅግ ድንቅ ነው፤ በበረት ከጽርሐ አርያም ይልቅ ረዘመ፤ ከምድር ዳርቻም ሰፋ፤ ሕዝቅኤል ካየው ሠረገላ ዳንኤልም ካየው ኪሩባዊ ዙፋን በረት በለጠ (ሕዝ 1፡18-23፣ ዳን 7፡9) ብለው ተናገሩላት፡፡
#ኢትዮጵያና ግብፅ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርሰቶስ ልደት በዓልን ታኅሣሥ 29 (በ4ት ዓመት 1ዴ ታኅሣሥ 28) ቀን ያከብራሉ፤ ለምን የሚለውን ከባሕረ ሓሰብ ሊቃውንትና ከመጻሕፍት እንድታነቡ እየጋበዝን ይህን ሁኔታ በጥልቀት ካጠኑት ዐበይት ሊቃውንት መካከል ዋናዎቹ #ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ፤ #ሰዒድ ወልደ በጥሪቅ፤ #መበንጋዊ/ማኅቡብ/፤ #ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ/አልአሚድ/፤ #ወልደ መነኰስ፤ #ሐዋርያት በዲድስቅልያ አንቀጽ 29 ገጽ 37፤ ሊቃውንት ወመምህራን ዘኢትዮጵያ ወግብፅ /ለአብነትም ከኢትዮጵያውን ደብረ ቢዘንና የጕንዳጒንዶ ሊቃውንት፣ አለቃ አሥራስ የኔሰው፣ አለቃ ሰዐት ከብቴ … እንዲሁም ቅዱስ ድሜጥሮስና ዮሐንስ አቤልሄሬም(ዮሐንስ አቡሻኽር) ከግብፅ ሊቃውንት/ ይጠቀሳሉ፡፡