Telegram Web Link
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሰዋል፤ ያበሰብሰዋልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ የተተረጎመ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#ትንሿ_ቤተክርስቲያን_በኦርቶዶክሳዊ_ቤተሰብ

[ባለትዳሮች] በቤታቸው ውስጥ ማድረግ ያለባቸው ቤተ ክርስቲያን መጥተው ያዩትን ነው፡፡ ለምሳሌ፦

👉 ቤተክርስቲያን ውስጥ የጠዋትና የሰርክ ጸሎት እንዳለ ኹሉ እነዚህ ባለ ትዳሮችም የጠዋትና የሰርክ ጸሎት በቤታቸው ውስጥ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ያለው የኅብረትና የአንድነት ጸሎት እንደ ኾነ ኹሉ፥ ባልና ሚስት ልጆችም ሳይለያዩ አብረው መጸለይ አለባቸው፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ውስጥ ከቅዳሴ በኋላ ትምህርተ ወንጌል እንዳለ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም እራት ከበሉ በኋላ ቃለ እግዚአብሔር ሊማማሩ ይገባቸዋል፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ውስጥ ራሳቸውን ገዝተው የሚኖሩ ትጉሃን መነኰሳት እንዳሉ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም ይህን ትግሃትና ምስጋና ወደ ቤታቸው ይዘዉት ሊኼዱ ይገባቸዋል፡፡

👉 ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማታ ላይ ኅብስቱን አበርክቶ ሕዝቡን ከመገባቸው በኋላ ወዲያው ወደ መኝታ እንዲኼዱ እንዳላደረገ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም ወደ መኝታቸው ከመኼዳቸው በፊት የቀን ውሎአቸውን መገምገም አለባቸው፡፡

👉 ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሊት ሌሊት ሲጸልይ ያድር እንደ ነበረ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም ሌሊት ላይ ነቅተው መጸለይ ይገባቸዋል፡፡ ሕፃናት ካሉም አብረዋቸው እንዲነሡ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ጾም እንደሚታወጅ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም በቤተ ክርስቲያን ከሚታወጀው ጾም በተጨማሪ ከንስሐ አባቶቻቸው ጋር ተመካክረው በፈቃዳቸው ሊጾሙ ይገባቸዋል፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳለው፥ ባልና ሚስትም የቤታቸውን ግድግዳ፣ መስኮትና በር በመስቀል ሊያስጌጡት ይገባቸዋል፡፡ ማማተብ በማይችሉ ልጆቻቸው ግንባርም አድገው ራሳቸው ማማተብ እስኪችሉ ድረስ እነርሱ ያማትቡላቸው፡፡ ቅዱሳት ሥዕላትም በቤታቸው ውስጥ ሊኖሩ ይገባል፡፡

ቤታቸው ትንሿ ቤተ ክርስቲያን የምትኾነው በዚህ መንገድ ነው፡፡

#ኦርቶዶክሳዊ_ቤተሰብ
#በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ መጽሐፍ፥ ገጽ 60 - 61
ትርጉም፦ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
እጅግ የተወደደና የተከበረው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ

“ወዳጄ ሆይ ወንድምህ ከአንተ ይልቅ አስተዋይና አዋቂ ብርቱም ቢሆን በዚህ ቅር አይበልህ ከዚህ ይልቅ እግዚአብሔርን አመስግን

ከወንድምህ አስተዋይነትና ብርታት ትጠቀማለህና በዚህ ሳታቆም ራስህን ስጦታየ ምንድነው?ወንድሜን እህቴን በምን ልጥቀም ?ብለህ ጠይቅ

ይህን ጥያቄ በትክክል ስትመልስ እንደመለስከው ምላሽም ስትተገብር በአንድ መልኩ በሚበልጥህ ሰው ቅር መሰኘትህን በሌላ መልኩ ደግሞ የምትበልጠውን ወንድምህን መናቅህን ታቆማለህ”
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#ማግባት_ለሚሹ
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው፤ እንዲህ ያለውን፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" (1ኛ ቆሮ.7፥2)። "ከድህነት ይወጣ (ትወጣ) ዘንድ" ነው የሚለውን? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡

ስለዚህ #ልጆቼ! እማልዳችኋለሁ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡ የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡

#አባቶች_ሆይ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት፦ ሀብትን አላየም፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡

#እናቶች_ሆይ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡

እናንተ ማግባትን የምትሹ #ወጣቶች_ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡

#እናንተ_ልጃገረዶች_ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡

የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
ልጄ! ሐሰተኛ አትኹን፤ ሕሰት ከስርቆት ያደርሳልና፤ ወርቅ ውዳሴ ከንቱ የምትወድ አትኹን ይህ ሁሉ ከስርቆት ያደርሳልና አለ ናትናኤል።

ልጄ! አጒረምራሚ አትኹን፤ ማጒረምረም ሰውን ወደ ስድብ ያደርሰዋልና፤ ክፉ ነገር የምታስብ ተጋፊ አትኹን፤ ክሕደት በዚህ ይመጣልና፤ ኃዳጌ በቀል (ይቅር ባይ) ኹን፤ ቂም በቀል የሌላቸው ሰዎች መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉና፤ ይቅር ባይ ርኅሩኅ ኃጢአት በሌለበት በንጹሕ ልብ ሁሉን የምትወድ ኹን፤ ትሑት ቸር ኹን፤ ከሰማኸው ቃል የተነሣ በመፍራት ከክፉ ሥራ ተጠብቀህ ኑር፤ አትታበይ ሰውነትህን ከትዕቢተኞች ጋር አንድ አታድርግ፤ ከትሑታን ከደጋግ ሰዎች ጋር ነው እንጂ፣ ያገኘህን መከራ ሁሉ አመስግነህ ተቀበል፤ ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ምንም ምን የሚደረግ እንደሌለ ዕወቅ አለ፤ ይሁዳ ታዴዎስ።

ልጄ! ቃለ እግዚአብሔር የሚነግርህን የሕይወት ምክንያት የኾነህን ለልጅነት ያበቃህን ሰው እንደ ዐይን ብሌን ውደደው በመዐልትም በሌሊትም አስበው እግዚአብሔር እንደ አከበረው አክብረው፤ እግዚአብሔር ስሙን ከሚጠሩበት ቦታ ከዚያ ይኖራልና፤ በትምህርታቸው ትጽናና ዘንድ እየሔድክ ሌሎች ቅዱሳንን ጠይቅ፤ ከቅዱሳን ጋር የሚውል ቅዱስ ይኾናልና።

በሚቻል መጠን አክብረው፤ ከደከምክበት ከሥራህ ፍሬ ስጠው፤ እግዚአብሔር በእርሱ ምክንያት መንፈሳዊ ምግብን የዘለዓለም ሕይወትንም እንድታገኝ አድርጎኸልና፤ የሚያልፈውን የዚህን ዓለም ምግብ ልትሰጠው ይገባሃል፤ ለሠራተኛ ዋጋው ይገባዋልና፤ በዐውድማ የበሬውን አፉን አትሰረው፤ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማነው? አለ ቶማስ።

የተጣሉትን በፍቅር አንድ አድርግ እንጂ ሰውን የሚለያይ ሥራ አትሥራ፤ በእውነት ፍረድ፤ ለባለጸጋ አድልተህ በድኻው አትፍረድ፤ ብዕል ለእግዚአብሔር ቁም ነገሩ አይደለምና፤ ትዕቢተኛውን መናፍቁን አታክብረው፤ መጽሐፍም አትጥቀስለት፤ እንደ አነጋገሩ መልስለት እንጂ፤ ስትጸልይ አትጠራጠር፤ የምትለምነውን አስተውል እግዚአብሔር ይፈጽምልኻል።

በምትመጸውትበት ጊዜ ክፉ ነገርን አታስብ፤ ከሰጠህ ዋጋህን ታገኛለህና፤ የሰጠህ ምንም ምን ገንዘብ በእጅህ ቢኖርህ ከኃጢአትህ መዳንን ሻ ፈልግ፤ ያገኘኸውን በምትሰጥበት ጊዜ ወላዋይ ኣትኹን፤ ዋጋህን የሚሰጥህም ማን እንደሆነ ዕወቅ፤ የለመነኸንም አታሳፍረው፤ ማናቸውንም ሁሉ ከነዳያን ጋር ተካፈል እንጂ ገንዘቤ የግሌ ነው አትበል፤ በኀላፊው ገንዘብ እርስ በርሳችሁ አንድ ከኾናችሁ በማያልፈው እንደምን አንድ አትኾኑም።

ወንድሞቼ! እማልዳችኋለሁ፤ ዕድሜ ሳላችሁ ከዚህም ጋር በጎ ሥራ መሥራት ሲቻላችሁ የአላችሁን መስጠት ቸል አትበሉ፤ እግዚአብሔር የሚመጣበት ቀን ቅርብ ነውና፤ የሚታየው የማይታየው ሁሉ ያልፋል እግዚአብሔር ይመጣል፤ የሚሰጠው ዋጋም ከእሱ ጋር ነው፤ ለራሳችሁ ፈጻምያነ ሕግ ኹኑ፤ እግዚአብሔር እንደ አስተማራችሁ ሌሎችን አስተምሩ፤ የተማራችሁትን ጠብቁ፤ በተማራችሁት ላይ አትጨምሩ፤ ክተማራችሁትም አታጉድሉ አለ በርተሎሜዎስ፤ ወንድሞቼ! የቀሩትን ትእዛዛት መጻሕፍት ያስተምሩዋችኋል አለ ጴጥሮስ።

(#ሃይማኖተ_አበው_ዘስምዓት 125፥10-16)
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
ከእኔ ጋር ያልሰበሰበ ይበትናል 
                                                  
Size:- 43.6MB
Length:-2:05:19
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵
ሥርዓተ ማኅሌት ዘየካቲት ኪዳነ ምሕረት
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፣ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፣ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።


ዚቅ
ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤ እምአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለውልደ ስብእ፤ ለሕይወት ዘለዓለም፤ ለኪ ይደሉ ከመ ትኩኒ መድኃኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤ ኦ መድኃኒተ ኵሉ ዓለም፤ ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት።

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኃኒት ለነፍስ ወሥጋ፤ እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ወኃጥአን ይስዕንዎን፤ ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዶ ፍኖተ፤ ይፈኑ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ፤ መድኃኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ።

ወረብ
ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኃኒት ለነፍስ ወሥጋ ማርያም ድንግል/፪/
እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ወኃጥአን ይስዕንዎን/፪/

መልክአ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማሰልዎ በኮከብ፤ ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤ ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኃኒት ዘዐርብ፤ ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ኅሊና ቀዳማይ አብ፤ አመ እምገነቱ ተሰደ በኀዘን ዕፁብ።

ዚቅ
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም፤ አመ ይሰደድ እምገነት።

ወረብ
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አንቲ ውእቱ/፪/
አመ ይሰደድ እምገነት/፬/


መልክአ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለአዕዛንኪ እለ ተበስራ ኪዳነ፤ እምአፈ ፈጣሪ ወልድኪ ዘባሕርየኪ ተከድነ፤ አምሕለኪ ማርያም ከመ ኢታርእይኒ ደይነ፤ እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ፤ ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ።

ዚቅ
ኪዳንኪ ኮነ ለኃጥአን ቤዛነ፤ ኪዳንኪ ኮነ ኪዳንኪ ኮነ፤ ለኃጥአን ቤዛነ ኪዳንኪ ኮነ።

ወረብ
ኪዳንኪ ኮነ/፮/
ለኃጥአን ቤዛነ ኪዳንኪ ኮነ/፬/


መልክአ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለመዛርዕኪ ወለኲርናዕኪ ምፅንጋዕ፤ እለ ሐቀፋሁ ለክርስቶስ ባሕርየ መለኮት ኅቡዕ፤ ማርያም ኅሪት እምነ መላእክት ወሰብእ፤ ተዝካረኪ ለእመ ገብረ በተአምኖ ጽኑዕ፤ በመንግሥት ሰማይ ምስሌኪ ይነግሥ ኃጥእ።

ዚቅ
አመ ይነግሥ ወልድ በደብረ ጽዮን፤ ክፍልኒ ድንግል ዕቁም በየማን፤ ምስለ አባግዕ ቡሩካን።


ወረብ
ይነግሥ ወልድ በደብረ ጽዮን አመ ይነግሥ ወልድ/፪/
ክፍልኒ ድንግል ዕቁም በየማን/፪/

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
መፍትው እንከ ንወድሳ ወንግበር ተዝካራ፤ ለቅድስት ድንግል ዓፀደ ወይን፤ መሶበ ወርቅ እንተ መና።


መልክአ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለመልክዕኪ እመልክዐ ሐና ወኤልሳቤጥ፤ ዘብዑድ ስኑ ወልምላሜሁ ፍሉጥ፤ ማርያም ድንግል ድንግልተ፧ አፍአ ወውስጥ፤ ቤዛ ይኩነኒ ኪዳንኪ በገጸ ፈጣሪ ሥሉጥ፤ አመ ወርኀ ነጊድ የኃልቅ ወይጸራዕ ሤጥ።

ዚቅ
ቃለ እግዚአብሔር እምድንግል አስተርአየ፤ ኤልሳቤጥ ኮነት ዓባየ፤ እስመ ወለደት ነቢየ።


ወረብ
እምድንግል አስተርአየ ቃለ ቃለ እግዚአብሔር/፪/
ኤልሳቤጥ ኮነት ዓባየ"እስመ ወለደት ነቢየ"/፪/ /፪/

አንገርጋሪ
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር፤ ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤ አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤ አማን፤ ኪዳንኪ ኢየኃልቅ።

አመላለስ
'አማን በአማን'/፪/ ኪዳንኪ 'አማን በአማን'/፪//፩/
ኪዳንኪ ኢየኃልቅ/፬/


ወረብ
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ/፪/
አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ ምሥራቅ ደብረ ሕይወት/፪/


ቅንዋት-
ዕፎኑ ንዜኑ ዕፎ ዕንጋ ንዜኑ እንበለ ይትመሰው ማኅፀነ ድንግል ኢማሰነ፤ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ ዘኵለሄ ሀሎ ወአልቦ አመ ኢሀሎ ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ፤ ሰማይ  ወምድር ዘኢያገምሮ፤ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ ነቢያት ቀደሙ አእምሮ፤ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ ሐዋርያት ተለዉ አሠሮ፤ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ ዕንባቆም ነቢይ ዘአንከረ ግብሮ፣ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ ዕሌኒ ንግስት ኀሠሠት መስቀሎ፤ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ ወለዕውርኒ ዘከሠተ ዓይኖ ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ ወለሠይጣንኒ ዘቀጥቀጠ ኃይሎ፤(ማ-)ዕፎ ዕንጋ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ፤ ፆረቶ እግዝእቱ ለአዳም ወአግመረቶ ማርያም

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት።

ጥንታዊት፣ ታሪካዊት፣ ብሔራዊትና ዓለም አቀፋዊት በሆነችው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥር ከሚገኙት ጥንታዊያን ገዳማት መካከል ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አንዱና ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል።

ይህ ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳም በርካታ ቅርሶችና መናንያን የሚገኙበት ገዳም ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት በተከሰተበት ዘረፋና ቃጠሎ ከባድ ጉዳቶችን ያስተናገደ መሆኑም ይታወሳል።

በዛሬው ዕለት ከሀገረ ስብከቱ በደረሰን መረጃ መሰረትም፦

1. የገዳሙ መጋቢ አባተክለማርያም ዐሥራት
2. የገዳሙ ጸሐፊ አባ ኪዳነ ማርያም ጥላሁን
3. የገዳሙ የመጽሐፍ መምህርና ቀዳሽ አባ ገ/ማርያም አበበ
4. በአመክሮ የሚኖሩ መናኝ ኃይለማርያም ወልደሰንበት

የካቲት 12 ቀን "ኦነግ ሸኔ" በተባለው ታጣቂ ቡድን ከተወሰዱ በኋላ አራቱም በትላንትናው አለት የተገደሉ ሲሆን አባ ኪዳነማርያም ገ/ሰንበት የተባሉት አባት ቆስለው በገዳሙ እንደሚገኙ ታውቋል።

በአሁኑ ሰዓትም ታጣቂዎቹ ወደ ገዳሙ ለመግባት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት መንገድ እንዳይኖርና መናንያኑና የገዳሙ ቅርስ አደጋ ላይ እንዳይወድቁ የፌዴራልና የክልሉ የጸጥታ አካላት ገዳማዊያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከአደራ ጭምር መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
የካቲት ፲፬ቀኝ ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም
አዲስ አበባ -ኢትዮጵያ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
2024/09/21 03:18:04
Back to Top
HTML Embed Code: