Telegram Web Link
ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ስለሚገኘው "መነኩሴ "ነኝ ባይ ግለስብ በሀገረ ስብከቱ የማይታወቅ መሆኑን የአርሲ ሀገረ ስብከት ገለጸ !

የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

የአርሲ ሀገረ ስብከት ሰሞኑን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ራሱን "መነኩሴ"በማስመሰልና በአርሲ ሀገረ ስብከት አገልጋይ እንደሆነ በመግለጽ የሚንቀሳቀሰውን ግለሰብ የማያውቀውና ሐሰተኛ "መነኩሴ" መሆኑን ለጠቅላይ ቤተክህነት በጻፈው ደብዳቤ አስታወቀ።

ከየካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በማኀበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የሚገኘው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ተችቶ የማስተቸት ድራማዊ ትዕይንት ላይ የቀረበው አስመሳይ " መነኩሴ "ግለሰብ በሀገረ ስብከታችን በተለይ በአሰላ ከተማ በቅዳሴ መምህርነት በስብከተ ወንጌል እንዳገለገለ በማስመሰል በሰጠው የሀሰት ምስክርነትን በተመለከተ እውነተኛ ምላሽ መስጠት ማስፈለጉን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ"መነኩሴ "መሳዩ ግለሱብ በሀገረ ስብከቱ በየተኛውም የከተማና የገጠር ገዳማትና አድባራት የማይታወቅና ምንም ዓይነት አገልግሎት ሲሰጥ ያልነበረ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ በሀገረ ስብከቱ የሚገኙት ሁሉንም አገልጋዮች የሚታወቁና የተመዘገቡ መሆኑን የጠቀሰው ሀገረ ስብከቱ ግለሰቡ በሀገረ ስብከቱ ካሉት አገልጋዮች መካከል የማይታወቅና ያልተመዘገበ ከመሆኑም በላይ ሀገረ ስብከቱ በፍጹም የማያውቀው ቀሳጢ ነው በማለት ሐሰተኛ ማንነትን በመላበስ የቤተክርስቲያንን ስም ለማጠልሸተ የተሰማራ መሆኑን ገልጿል።

ስለሆነም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ግለሰቡ የቤተ ክርስቲያናችንን ዓርማ ወይም አልባሳት በመልበስና የሀገረ ስብከታችንን መልካም ገጽታ በማጉደፉ ግለሰቡንና እዩ ጩፋ የተባለውን አጽራረ ቤተ ክርስቲያን በሕግ እንዲጠይቅን ስንል በታላቅ አክብሮት. እናሳስባለን፤በማለት ለጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ ጨምሮ ገልጿል።


ምንጭ: የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
እሴተ ሃይማኖት 
       ክፍል 1                               
Size:- 14.2MB
Length:-40:45
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
ማኅበረ ቅዱሳን ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ መግለጫ አወጣ !

የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ዛሬ የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ማኅበሩ በመግለጫው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን መንፈሳዊ አንድነት የጠየቀ ሲሆን "ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርገው ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም" የሚንቀሳቀሱ ያላቸውን "አንዳንድ አባቶች" ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በማሳሰብ ጉዳዩንም በመከታተል መረጃውን ለምእመናን አደርሳለሁ ብሏል።፡፡

ይመለከታቸዋል ላላቸው ሌሎች የቤተ ክርስቲያን አካለትም ጥሪውን አስተላልፏል።

1. የተከበራችሁ አበው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ሆይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፡፡ እንዳለ በዚህ ታላቅ የፈተና ወቅት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማስጠበቅ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጣችሁን ኃላፊነት ለመወጣት ምእመናንን አቅጣጫ በመስጠት የቀደሙ አባቶቻችሁን ፈለግ በመከተል ዛሬም በጽናት እንድትተጉ፤ ያከበረቻችሁን ቤተ ክርስቲያን በአንድነት ሆናችሁ እንድትጠብቁ በልጅነት መንፈስ በትሕትና እንጠይቃለን፡፡ በተጨማሪም የአባትነት የዋህ ልቦናችሁን በመጠቀም ያዘኑ፣ የጠቀሙ፣የተቆረቆሩ መስለው ቀርበው የግል ፍላጎታቸውን ለመፈጸም የሚጥሩ ስለሚኖሩ ሁሉንም በጥንቃቄ እንድትመረምሩ፤ቀኖች ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን በመዋጀት አንድነታችሁን እንድታጠነክሩና በቤተክርስቲያን ዙሪያ ስለሚፈጠሩ ችግሮች በጥልቀት እንድትወያዩና እንድትመካከሩ እናሳሰስባለን።

2. ከዚህ ውጭ ቤተ ክርስቲያንን በማይጠቅማት ጉዳይ የግል ፍላጎትንና ምድራዊ ዓላማን መሠረት አድርጋችሁ ከቤተ ክርስቲያን ሕግና ቀኖና ውጭ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊን ለመተካት፣ ፓትርያርክ ለመሾምና የመሳሰሉትን ለመፈጸም የምትንቀሳቀሱ አንዳንድ አባቶች ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ማኅበራችን ይህንን ጉዳይ እየተከታተለ መረጃውን ለምእመናን የሚያደርስ መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን፡፡

3. ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ መምህራነ ወንጌል፣ ካህናት ሆይ በጸሎትና በትምህርት ምእመናንን በማጽናናት፤ ከእውነት ጋር በመቆም እውነታውን በማሳየት ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን ዘብ እንዲቆሙ በማድረግ ድርሻችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን።

4. ውድ ምእመናንና የማኅበራችን አባላት የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ከአሳዳጆቿ የመጠበቁ ዋነኛ ኃላፊነት በዘመኑ ባለን ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርሰቲያን፣ ካህናትና ምእመናን ሁላችን እጅ ላይ ወድቆአል፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ ለአባቶችና ለካህናት ትተን “እኔ አያገባኝም፤ አይመለከተኝም” ልንል አይገባም፡፡ ሁሉም በየድርሻው ቤተክርስቲያኑን ለመጠበቅ መትጋት አለበት፡፡ በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰውን ጥፋትና ሊመጣ ያለውን ፈተና አስቀድሞ በመረዳት ቅዱስ ሲኖዶስ ቀደም ሲል በወሰነው መሠረት በየአጥቢያችን፤ በተለያየ መልኩ በመደራጀት፤ በቤተክርስቲያን ላይ ጥፋት ለማድረስ የሚመጡትን በመከላከል የቤተ ክርስቲያንን ስደት ለማስቆም መንፈሳዊ ግዴታችንን እንድንወጣ እንጠይቃለን፡፡

5. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በልዩ ልዩ አገልግሎት እየተሳተፋችሁ ያላችሁ ሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ ማኅበራትና ሌሎችም ሁላችንም አንድነታችንን በመጠበቅ በጋራ አገልግሎቶችን በመፈጸም ድርሻችንን እንድንወጣ ለተግባራዊነቱ ጥሪ እናቀርባላን፡፡

6. ገዳም ድረስ ገብቶ መሣሪያ ያልያዙና: ራሳቸውን እንደሞቱ ቆጥረው እየኖሩ ያሉ መነኮሳት ላይ ግድያ የፈጸመ ማንኛውም የታጠቀ ኃይል (መደበኛም ይሁን ኢመደበኛ: በግልም ይሁን በቡድን: አማኝም ይሁን ኢአማኝ) ድርጊቱ ከሰውነት ተፈጥሮ የወጣ ነው፡፡ ምናኔንና የክህነት ክብርን በተቃረነ መልኩ ሰብእና የጎደለው ጥቃት ማድረስ ኢትዮጵያዊ ባህልም አይደለም፡፡ ጥቅም የሌለው ከንቱ ተግባር ነው፡፡ በዚህ የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ ይኖራል ብለን አናምንም፡፡ ጤነኛ በሆነ አእምሮ ታስቦ የተፈጸመ ነው ማለትም አይቻልም፡፡ ማስተዋል ተወስዶባቸው እውቀት ተሰውሮባቸው እንጂ ይህንን ማድረግ ቀርቶ ማሰቡም የሙት ሐሳብ ነው፡፡ ቀድሞ የሞተው ሟቹ ሳይሆን ገዳዩ ነው፡፡ በዚህ መንገድ የቤተ ክርስቲያን አማኞች ሲበዙ እንጂ ሲያንሱ በታሪክ አልታየም:: ይህ ድርጊት ክርስቲያኖችን ሲያጠነክር እንጂ ሲያዳክም ታይቶ አይታወቅም፡፡ መጽሐፍ “ጎርፍም መጣ ነፋስም ነፈሰ ያንን ቤት ገፋው በዓለት ላይ ስለተመሠረተ አልወደቀም ” ባለው መሠረት ቤተክርስቲያን በጽኑ ዐለት ላይ የተመሠረተች ስለሆነ አታሽነፏትም። ዲዮቅልጥያኖስም አላጠፋትም:: ዲያብሎስም ዝናሩን እንዲሁ ጨረሰ:: ስለዚህ አትድከሙ: አትሳቱም እናንተ ሳትወለዱ የነበረች ቤተ ክርስቲያን እናንተ አልፋችሁም እንደ እናንተ ላሉት በስሑት መንገድ ለሚጓዙት ሁሉ እየጸለች ትቀጥላለች:: ሐሳቧም፣ ሥራዋም፣ ዓላማዋም፣ ግቧም ሰማያዊ ነውና።

በመጨረሻም ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያን ህልውና በላይ የሚያስቀድመው አንዳች ነገር የሌለ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና ለማለፍ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት ጋር በመናበብ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን በዚሁ አጋጣማ እያሳወቅን፥ የሁላችንም የመሰባሰብና የአገልግሎት ማእከል ቤተ ክርስቲያን በመሆኗ ከሁሉም ነገር በፊት ቅድሚያ ሰጥተን ሊመጣ ካለው አደጋ ቤተ ክርስቲያናችንን የመጠበቅ ኀላፊነት በትጋት እንወጣ ሲል ማኅበረ ቅዱሳን በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል፡፡
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#አሰቦት

" የገዳማውያኑን የእርዳታ ጥሪ በተጠንቀቅ ጠብቁ " - አባ ገ/ሚካኤል

በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም አካባቢ በከፍተኛ ደረጃ የሰደድ እሳት የተነሳ ሲሆን ከትላንት ምሽት ጀምሮ ግን ወደ ገዳሙ በከፍተኛ ሁኔታ #እየተጠጋ እንደሆነና እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል።

አባ ገ/ሚካኤል የተባሉ የገዳሙ አገልጋይ ለተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል በሰጡት ቃል ፤ የእሳት ቃጠሎ መነሻው በሥርዓት ያልታወቀና የሰደድ እሳት እንደሆነ ገልጸዋል።

ከ3 ዓመታት በፊት ከፍተኛ እሳት ተከስቶ ለዘመናት የኖሩ የገዳሙን ብርቅዬ አራዊትና ደን ማውደሙን አስታውሰዋል።

በአሁኑ ሰዓት እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ፤ የእሳቱ አደጋ የሚከፋ ከሆነና መቆጣጠር ካልተቻለ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን የገዳማውያኑን የእርዳታ ጥሪ በተጠንቀቅ ሊጠብቁ ይገባል ብለዋል።

#ተሚማ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
እኔን ጣሉኝና ማዕበሉ ይተዋችኋል 
                                                  
Size:- 40.6MB
Length:-1:56:26
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#Amahra

በሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት በላይ ጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን 11 የቅኔ ተማሪዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው በላይ ጋፊት  ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 11 የቅኔ ተማሪዎች  እንዲሁም 1 በግብርና የሚተዳደር የአካባቢው ነዋሪ ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት ተገድለው እንደሞቱ ተነግሯል።

የሟች ቤተሰቦች በሰጡቅ ቃል የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 6:00 ገደማ እንደሆነ ተማሪዎቹ በጎጇቸው ሳሉ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ፦

- " ፋኖን ታስጠልላላችሁ " ፣

- " ለፋኖ አባላት ጥይት የማያስመታ መድኃኒት ትሰጣላችሁ "

- " እናንተም የፋኖ አባላት ናችሁ " በማለት 11 ተማሪዎች እንዲሁም የጩኸት ድምፅ ሰምቶ ወደ ጉባኤ ቤቱ ሲሄድ የነበረን የአካባቢው ነዋሪ መግደላቸውን ገልጸዋል።

አሁን የተገለጸው የሟቾች ቁጥር በዛሬው ዕለት በትክክል የተገኘ እንደሆነ እና በሰዓቱም በጉባኤ ቤቱ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች ወደተለያየ አቅጣጫ ስለተበታተኑ የሟቾች ቁጥር አሁን ከተጠቀሰው ቁጥር ሊልቅ እንደሚችል ተጠቁሟል።

ከጥቂት ጊዜያት በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ ከ12 ያላነሱ የአቋቋም ተማሪዎች በአዴት ፍልሰታ ደብር ተገድለው እንደነበር ተገልጿል።

የዞኑ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ስለ ጉዳዩ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም። #ተሚማ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ሳሙኤል አንድነት ገዳም ተነሥቶ የነበረው የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱ ተገለጸ !

የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአባ ሳሙኤል አንድነት ገዳም አካባቢ በከፍተኛ ደረጃ የሰደድ እሳት መነሳቱ የሚታወስ ሲሆን በአበው መነኮሳት ጸሎት ፣ በአርድእቱ እና በአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያንና በሚሊሻው ጠንካራ ተሳትፎ እሳቱ ሙሉ ለሙሉ መጥፋቱን ሀገረ ስብከቱ አስታውቋል።

ስለሆነም ገዳሙን ከእሳት አደጋ ለመታደግ ከቦታው ድረስ በመገኘት የእሳቱ ወላፈን እየገረፋችሁ ፣ ጭሱ እያፈናችሁ ፣ ጠንካራ ተሳትፎ ላደረጋችሁ ፣ እንዲሁም በቦታው ተገኝታችሁ ተሳትፎ ለማድረግ ፍላጎት ቢኖራችሁም በቦታ ርቀትና በነገሮች አስገዳጅነት ላልተገኛችሁ ፣ በሐሳብ ፣ በጸሎት ፣ በገንዘብ የደገፋችሁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በዚህኛው ዓለም በዕድሜ፣ በጤና ፣ በሐብት ፣ በወዲያኛው ዓለም በሰማያዊው በረከት ይጎብኟችሁ በማለት የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ክቡር ሊቀ ኅሩያን ቆሞስ አባ ፍቅረ ዮሐንስ ብርሃኑ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ሲል ሀገረ ስብከቱ በፌስ ቡክ ገጹ አስነብቧል።


ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
2024/09/21 05:38:52
Back to Top
HTML Embed Code: