ማኅሌተ ጽጌ
እግዚአብሔር ጽጌ ትንቢት ለቢሶ ሥጋኪ ሥጋ ዚአነ፤አመ አስተርአየ በምድር ወተአምረ ለነ፤ንዌድሰኪ እንዘ ንብል ምክሃ ዘመድነ፤ዮም በፍሥሃ ለማርያም እምነ፤አስተርእዮ በሰማይ ኮነ።
ዚቅ
አስተርአየ ዘኢያስተርኢ፤ኮነ እሙነ አስተርእዮቱ ለመድኃኒነ ክርስቶስ፤እሙነ ኮነ አስተርእዮቱ፤እምድንግል ተወልደ፤እሙነ ኮነ አስተርእዮቱ፤በሥጋ ረቂቅ፤እሙነ ኮነ አስተርእዮቱ፤በ፴ ክረምት በዮርዳኖስ ተጠምቀ፤በበህቅ ልህቀ።
አንገርጋሪ
ኢኮነ ነግደ ወፈላሴ ሀገሪቶሙ ለቅዱሳን፤ንሕነ ሰብአ ቤቱ ለእግዚአብሔር ኲልነ፤አምላክ ኀደረ ውስተ ሥጋ ተአቊረ፤እንዘ ኢይትጋባዕ በሙላድ፤ዘድንግል መናሥግተ ኢያርኂዎ፤ዘኪሩቤል ኢርእዮ።
አመላለስ
ዘድንግል መናሥግተ ኢያርኂሆ/፪/
ኢያርኂሆ ዘኪሩቤል ኢርእዮ ኢያርኂዎ ኢርእዮ ዘኪሩቤል/፪/
ወረብ ዘአንገርጋሪ
'አምላክ ኀደረ'/፪/ ውስተ ሥጋ ተዓቊረ እንዘ ኢይትጋባዕ አምላክ ኀደረ/፪/
ዘድንግል መናሥግተ 'ኢያርኂዎ'/፪/ ኢርእዮ ዘኪሩቤል/፪/
እስመ ለዓለም
እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤ቃል ቅዱስ፤መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፤ዘመንበሩ ዓቢይ ውእቱ፤ያቀድም አእምሮ ኅሊና ሰብእ፤መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፤ግሩም እምግሩማን፤ዘመጽአ ውስተ ዓለም፤መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፤ስብሐት ዘኢየኃልቅ፤ወስን ዘኢያንጸበርቅ፤መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፤ዘይሥዕሎሙ ለሕፃናት፤ወይነግሥ ለመላእክት፤መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፤እስመ ንጉሥ ውእቱ ሰከበ በጎል፤ሰገዱ ሎቱ ሰብአ ሰገል፤መንበሩ ዘኪሩቤል ኀደረ ላዕሌኪ፤እምግርማሁ ትርዕድ ምድር ዜናዊ ስቡሕ ዘለዓለም፤ወእስከ ለዓለም ንጉሥ ውእቱ።
ወረብ ዘእስመ ለዓለም
ዘመንበሩ ዓቢይ መንበሩ ውእቱ መንበሩ ዘኪሩቤል/፪/
ያቀድም 'አእምሮ'/፪/ ኅሊና ሰብእ/፪/
@mezigebehayimanot

#እመቤታችን_ለምን_ሞተች?
እንኳን ለ አስተርእዮ ማርያም በዓል አደረሳችሁ!!!
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኩሉ"
"ሞት ለሟች ይገባል
የማርያም ሞት ግን ለሁሉ ይደንቃል!!!" ፤ ደራሲ፡፡
✔✔✔ጥር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት ይታሰባል፡፡
ሞት በአዳም በደል ምክንያት የመጣ ዕዳ ነው፤ባህርያዊ ሳይሆን ባህርያዊ መስሎ ከባህርያችን ጋር ተስማምቶ የሚኖር ፍዳ ነበር፡፡ ሞት ጌታችን ሳይገድለው/ሳይሽረው በፊት ወደ ሲኦል መውረጃ መንገድ ነበር፤
ለአጋንንት እግር እርግጫ፤ ለመንጸፈ ደይን ተመቻቻተን የምንሰጥበት ሂደት፤ሥጋ በመቃብር የሚፈርስበት፤ነፍስ በሲኦል የምትሰቃይበት ክስተት ነበር፡፡
👉ክርስቶስ ሲመጣ ግን ይህ ሞት የሚለው ንባብ ሳይቀየር ትርጉሙና ምሥጢሩ ተቀየረ፤መጠጫው ጽዋው ሳይቀየር መጠጡን እንደመቀየር ነው፤መሞት በሐዲስ ኪዳን መሻገር ነው፤ወደ ዘለዓለም ሕይወት መጠራት፤መቃብርም ለትንሣኤ ዘጉባኤ መቆያ ስፍራ ነው፡፡
✔እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለምን ሞተች? ሞት የጥንተ አብሶ ውጤት ከሆነ እመቤታችንም የሞተችው ጥንተ አብሶ ስላለባት ነው ብለው የሚከራከሩ ወገኖች አሉ፤
አነዚህ ሰዎች በሐዲስ ኪዳን ሞት ምን እንደሆነ ያለመረዳታቸውና እንዲሁም የእመቤታችን ሞት ምክንያቱ ምንድነው የሚለውን ባለማወቃቸው ምክንያት የሚናገሩት ነው፡፡
ሞት ጥንተ አብሶ ያለበት ብቻ ነው የሚሞተው ከተባለ ጌታችን ራሱ መሞቱ ጥንተ አብሶ ስላለበት ነው ያሰኛል፤ ይህ ደግሞ እርሱ ንጹሕ ሆኖ ሳለ ስለእኛ ሞተ የምንለውን የድኅነት ፅንሰ ሀሳብ ከንቱ ያደርግብናል፤ስለዚህ ሞት ከክርስቶስ በኋላ የመብቀል ሂደታችን መሆኑን እንመርምር፡፡
ይህን ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይነግረናል:—
"አንተ ሞኝ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም"፤ይላል 1ኛ ቆሮ 15፡36፡፡ ሰለዚህ ሞት በሐዲስ ኪዳን ሕያው ለመሆን የምናልፍበት ሂደት (process) ነው፡፡
ራሱ ጌታችንም ሲያስተምረን:—
"እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም"፤ዮሐ 5፡24፡፡
ዳግመኛም ፦ "እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘለዓለም ሞትን አያይም" ብሏል፤ዮሐ 8፡51፡፡
ይህም ማለት ነፍስ ከሥጋ አትለይም ማለት አይደለም፤እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ነፍስ በገነት እንደምትኖር፤ ከዚያም በትንሣኤ ዘጉባኤ ጊዜ ነፍሳችን ከሥጋችን ጋር ተዋሕዳ ተነሥተን ከመላእክት ጋር እያመሰገንን የምንኖረውን ዘላለማዊ ሕይወት ለመግለጽ እንጂ፡፡
👉እመቤታችን ቃሉን በመስማትና በማመን በመጠበቅ የመጀመሪያዋና ተወዳዳሪም የሌላት ናት፤ ማንም ሊሰማው የማይችለውን "ቃል ሥጋ ኮነ" ን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማች መስማት ብቻ ሳይሆን ያመነች ናት፤ቅድስት ኤልሳቤጥ "ወብፅዕት አንቲ እንተ ተአምኒ ከመ ይከውን ቃል ዘነገሩኪ እምኀበ እግዚአብሔር ፤
(ከእግዚአብሔር የተነገረሽ ቃል እንደሚፈጸም ያመንሽ አንቺ ብፅዕት ነሽ) ብላ እንዳመሰገነቻት (ሉቃ 1፡45) "ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም" ብላ ስታምን ነበር ሞትን ያለፈችው፤ትንሣኤ ልቡናን ቀድማ የተነሣችው፤ ይህ ምሥጢር የተከናወነባት ናት፤እያንዳንዱን የጌታን ቃል በልብዋ ትጠብቀውና ታስበው እንደነበር ተጽፏል፤ሉቃ 2፡51፡፡
እንዲህ ከሆነ ሕይወት የሆነውን ጌታ ፀንሳ፤ወልዳ የድንግልና ጡት ያጠባች ሆና እንዴት ትሞታለች?
ሕይወትን የዳሰሱ እጆች፤ሕይወትን የተመለከቱ ዓይኖች፤ሕይወትን ያቀፉ ጉልበቶች እንዴት ለሞት ይሰጣሉ? ብለን ስንጠይቅ የሚከተሉት ምላሾች ይኖሩናል፡፡
➊ ከተገፋችበት ፤ከተንከራተተችበትና የኀዘንና የመከራ ሰይፍን ካስታናገደችበት ዓለም ወደማያልፈው ዓለም ወደመንግሥተ ሰማያት መጠራቷን፤የማያልፈውን ዋጋ እንደተቀበለች ለማሳየት እንጂ የሞት ሞት የሚባለውን መፍረስና መበስበስን፤ወደ ሲኦል መውረድን የሚያሳይ እንዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል።
ይህንንም ቅዱስ ያሬድ "ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ ፈለሰት እምዘ ይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤ዳዊት አቡሃ በመሰንቆሁ እንዘ የኀሊ፤የሰው እጅ ያልሰራት ድንኳን ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረላት እመቤታችን አባቷ ዳዊት በመሰንቆው እያመሰገናት ከሚያረጀው ዓለም ወደማያረጀው/ወደማያልፈው ሄደች"
በማለት እነደነገረን ነው፡፡
➋ ከሰማይ የወረደች (ኃይል አርያማዊት) ናት የሚሉ አሉና ሰው እንደሆነች እና ከምድር እንደተገኘች፤ሙሉ የሰውነት ማንነት ያላት መሆኑን ለማጠየቅ ነው፤ እመቤታችንን ሞት ባያገኛት ካልዕ ፍጥረት (ልዩ ፍጥረት) ስለሆነች ነው ብለው ብዙዎች በተከራከሩ ነበር፤ይህም ደግሞ ክርስቶስ የነሣውን ሥጋና ነፍስ (ምሥጢረ ተዋሕዶን) ጥያቄ ምልክት ውስጥ ይከተው ነበርና በዚህ ምክንያት በሕገ ሰብእ በሩካቤ ብእሲ ወብእሲት ስለተገኘች በሕገ ሰብእ ሞት ተጠርታለች፤ ይህ ሞቷ እሷን ሌላ ፍጥረት የጌታን ተዋሕዶ ምትሐት ከማለት የሚታደግ መድኃኒትም ጭምር ነው፡፡
➌ ፍትሑ ርቱዕ (ፍርዱ ቅን የሆነ) እግዚአብሔር ለማንም እንደማያዳላ ያጠይቃል፤ እመቤታችን እንደማንኛውም ሰው ሞትን ባታይና ባትቀምስ ፍርዱ ትክክል አይደለም፤ አንዱን በሞት ይወስዳል ሌላውን ይተዋል፤ወዲህም ልጅዋ አምላክ ነውና ሞትን ያልቀመሰችው በልጅዋ ምክንያት እንጂ እርሷ የተለየ ቅድስና ስላላት አይደለም በተባለ ነበርና ሞትን እንድትቀምስ ፈቅዷል፤ሞትን መቅመሷ በክብር ላይ ክብር ቢጨምርላት እንጂ ቅንጣት ታህል ክብር አይቀንስባትምና፡፡
ይህንንም ደራሲው፦
"ኢያድለወ ሞተ ክርስቶስ ለሥጋ አባሉ፤ክርስቶስ ሥጋውን ለነሳበት አካል በሞት አላዳላም" በማለት ተናግሯል፡፡
ቅዱስ ያሬድም ፦
"እንበይነዝ አእምሩ በውስተ ፍትሕ ከመ ኢያደሉ ትጥዓም ሞተ እሙ ወእመ ኩሉ
አዘዘ ወልድ በርቱዕ ቃሉ"
(በፍርድ እንደማያዳላ ስለዚህ ነገር ዕወቁ፤የእርሱ እናት፤የሁሉ እናት እመቤታችን ሞትን ትቀምስ ዘንድ ወልድ በማይሻር ቃሉ አዘዘ) በማለት አስረግጦ ተናግሯል። (የዕለቱ ዚቅ)፡፡
➍ በነገረ ማርያም ላይ እንደተጻፈው እመቤታችን የዕረፍት ጊዜዋ መድረሱን ጌታችን ሲነግራት እንዴት እኔ የአንተ እናት ሆኜ ሞት ያገኘኛል? በማለት ጠይቃለች፤ቅዱስ ያሬድ እንደገለጸው "እፎኑመ እመ አምላክ በከየት ደንጊፃ ከመ ኩሉ ሰብእ ሞት ሶበ ሐወጻ፤እንደማንኛውም ሰው ሞት በጎበኛት ጊዜ የአምላክ እናት እንደምን አለቀሰች?" (የዕለቱ ዚቅ)፡፡
ጌታችንም አንቺ ስትሞቺ ባንቺ ሞት ምክንያት ከሲኦል የሚወጡ ነፍሳት አሉ በማለት ነገራት፤ እመቤታችንም ርኅርኅት ናትና ♥በኔ ሞት ምክንያት ነጻ የሚወጡ ነፍሳት ካሉ አንድ ጊዜ አይደለም ሰባት ጊዜ ልሙት♥ ብላ መልሳለታለች፤ይህም ማለት ሁሉም ነፍሳት በእመቤታችን ሞት ምክንያት ከገነት ይወጣሉ ማለት ሳይሆን እግዚአብሔር ባወቀ የእናቱ ሞት ቤዛ እንዲሆናቸው የመረጣቸው ነፍሳት መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡
• በብሉይ ኪዳን ጥንተ አብሶ ያለባቸው ሰዎች ሲሞቱ መልአከ ሞት ይታያቸው ነበር ለእመቤታችን ግን ልጅዋ ራሱ ክርስቶስ ነው የተገለጠላት፤
• በብሉይ ኪዳን የሞቱ ሰዎች ወደ ሲኦል ነበር የሚወርዱት እመቤታችን ግን ሥጋዋ በገነት ነፍሷ በልጅዋ እጅ ነበር፤
• ከአዳም ልጆች ወገን የመጨረሻውን ትንሣኤ የተነሣ የለም፤እመቤታችን ግን እንደ ልጅዋ ተነሥታለች ዐርጋለች፤መዝ 131፤8፡፡

ሰለዚህ የእመቤታችን ሞት ይደንቃል፤ሁላችን ከሞታችን በፊት የሰራነው ብዙ ኃጢአት አለ፤ እመቤታችን ግን ንጽሕት ናት
ሞቷም በሲኦል ስላሉ ውስን ነፍሳት በልጅዋ ፈቃድ ቤዛ ሆኖ የተሰጠ፤የተከፈለ ነው፡፡
ሞት ለሟች ይገባል
የድንግል ሞቷ ግን ለሁሉ ይደንቃል!!!
የእመቤታችን አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን
ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን!
ልጅዋ ወዳጅዋ ፍቅሩን በሕይወታችን፣ ፍቅሯን በልባችን ይሣልብን ያሳድርብን!!!
አሜን!!!!
Revised Post
መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ከ ኖርዌይ ኦስሎ (Norway, Oslo)

ስርዓተ ማህሌት አመ ፳ወ፩ ለጥር ዘአስተርእዮ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፣ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ሃሌ ሉያ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሥላሴ ዋህድ፤ዕፎኑመ እመ አምላክ በከየት ደንጊፃ፤ከመ ኲሉ ሰብእ ሞት ሶበ ሐወጻ፤ዮሐንስ በልብሱ ከደነ ገፃ።
ወረብ
እፎኑመ እመ አምላክ በከየት ደንጊፃ በከየት እመ አምላክ/፪/
ከመ ኲሉ ሰብእ ሞት ሶበ ሐወጻ በከየት/፪/
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤መጽአ ውስተ ዓለም፤ወዓለሙኒ ኢክህለ ፀዊሮቶ፤ፆረቶ ወአግመረቶ ማርያም።
ነግሥ
ለምንት ይዜኃር ኃያል በኃይሉ፤ወባዕል በብዝኃ ብዕሉ፤ኢያድለወ ሞተ ክርስቶስ ለሥጋ አባሉ፤ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ፤ሞታ ለማርያም የአፅብ ለኲሉ።
ዚቅ
እንበይነዝ አእምሩ በውስተ ፍትሕ ከመ ኢያደሉ፤ትጥዓም ሞተ እሙ ወእመ ኲሉ፤አዘዘ ወልድ በርቱዕ ቃሉ።
መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።
ዚቅ
ለዛቲ ድንግል ሠረቀ ላዕሌሃ ብዕለ ጸጋሁ ለአብ፤ወአግአዛ እምእኩይ ውስተ ሠናይ፤እሞት ውስተ ሕይወት፤ወረሰየ ይዝክሩ ስማ ውስተ ኲሉ ምድር።
ወረብ
ለዛቲ ድንግል ሠረቀ ላዕሌሃ ብዕለ ጸጋሁ ለአብ/፪/
ወአግአዛ እምእኩይ ውስት ሠናይ እሞት ውስተ ሕይወት/፪/
መልክአ ማርያም
ሰላም ለእስትንፋስኪ ዘመዓዛሁ ሕይወት፤ከመ መዓዛ ዕፅ ኅሩይ ዘውስተ ገነት፤ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት፤ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት፤በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት።
ዚቅ
አንጺሆ ሥጋሃ ቀዲሶ ኪያሃ፤ኃደረ ቃል ላዕሌሃ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይቤላ ለድንግል፤ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ሰሎሞን ይቤላ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት፤ፍናወ ዚአኪ ገነት፤እስመ ኪያኪ ኀርየ ለታዕካሁ፤ከመ ትኩኒዮ ማኅደረ ለልዑል።
ወረብ
'አንጺሆ ሥጋሃ'/፪/ ላዕሌሃ ኃደረ/፪/
ቀዲሶ ኪያሃ 'ሃሌ ሉያ'/፪/ ይቤላ ለድንግል/፪/
መልክአ ማርያም
ሰላም ለገቦኪ ዘሐመልማለ ወርቅ ክዳኑ፤በከመ ዳዊት ይዜኑ፤ማርያም ድንግል ለያዕቆብ ሞገሰ ስኑ፤በልኒ እግዝእትየ አፈቅረከ አኮኑ፤እንዘ ረዳኢትከ አነ ዘይክለከ መኑ።
ዚቅ
እምሰማያት ወረደ ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር፤ኖላዊ ኄር ኖላዊሆሙ ለ፳ኤል፤ወረደ ስኖ ለያዕቆብ ዘአፍቀረ፤ወስኑሰ ለያዕቆብ ዘይቤ ይእቲ ሥጋ እንተ ነሥአ፤መድኅን እማርያም።
ወረብ፦
ወስኑሰ ለያዕቆብ 'ዘይቤ'/፪/ ያዕቆብ/፪/
'ይእቲ ሥጋ'/፪/ እማርያም እንተ ነሥአ መድኅን/፪/
መልክአ ማርያም
ሰላም ለፀአተ ነፍስኪ እንበለ
ፃዕር ወፃማ፤ለነቢር ዘልፈ በየማነ ወልድኪ ፌማ፤ማርያም ድንግል ለባሲተ ሞገስ ወግርማ፤አጽንዒ በረድኤትኪ ለሕይወትየ ድካማ፤እምሕይወተ ኄራን አበው ኢታሕጽጺ ዐቅማ።
ዚቅ
ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና፤ጠሊላነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና።
ወረብ
ጊዜ ዕረፍታ ለማርያም 'ጊዜ'/፫/ ዕረፍታ ለማርያም/፪/
ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ/፪/
መልክአ ማርያም
ሰላም እብል በድነ ሥጋኪ ጽሩየ፤ዘተመሰለ ባሕርየ፤ማርያም ድንግል ዐጸደ ወይንየ፤ንስቲተ ለዕበየኪ እንተ አቅረብኩ ግናየ፤ኢይትኃደግ ዲበ ምድር ምሥጢ ሰማየ።
ዚቅ
ኦ ትቤ ማርያም እወጽእ እምዝንቱ ሥጋየ፤ወአሐውር ውስተ ሕይወት ዘለዓለም፤ኦ ተዘከርኬ ዮሐንስ ዘይቤለከ ሊቅ አመ ትረፍቅ ዲበ ዕንግድዓሁ።
መልክአ ማርያም
ሰላም ለግንዘተ ሥጋኪ በእደ ሐዋርያት አርጋብ፤በአፈወ ዕፍረት ቅድው ዘሐሳበ ሤጡ ዕፁብ፤ማርያም ድንግል ወለተ ኅሩያን ሕዝብ፤ረሰይኩኪ እግዝእትየ ህየንተ እም ወአብ፤ይሕፅነኒ ከመ ጥብ ፍቅርኪ ሐሊብ።
ዚቅ
ተጋብኡ በቅጽበት ለግንዘተ እሙ ቅድስት፤ብፁዓን ሐዋርያት ቦኡ ኀቤሃ፤በሰላም አምኁ ኪያሃ፤በስብሐት ገነዙ ሥጋሃ።
መልክአ ማርያም
ሰላም ለመቃብርኪ ለጌቴሴማኒ በመርኅባ፤እንተ ይእቲ ለኢየሩሳሌም ቅሩባ፤ማርያም ድንግል ለሀገረ መንግሥት ርግባ፤ትትሜጦ ወርቀ እምአፌር ወጸበለ አፈው እምሳባ፤ጌቴሴማኒ ለሥጋኪ ምስካባ።
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ዓውዳኒ ዘጽድቅ ወመርኅባኒ ዘዕንቊ፤አንቀጸ አድኅኖ ሐዳስ ንድቅ።
መልክአ ማርያም
ሰላም ለመቃብርኪ ለኢየሩሳሌም በአድያማ፤እንተ ይእቲ ጌቴሴማኒ ስማ፤ማርያም ሰንበት ዕረፍተ ጽዑራን እምፃማ፤አመ ኀደረ ላዕሌኪ ፀሐየ ቅዱሳን ዘራማ፤ኃይለ ልዑል ጸለለኪ በመንክር ግርማ።
ዚቅ
ኢይሜንንዋ ኪያሃኒ ወአድያሚሃኒ ነያ ጽዮን ቅድስት ሀገረ እግዚአብሔር።

• በብሉይ ኪዳን ጥንተ አብሶ ያለባቸው ሰዎች ሲሞቱ መልአከ ሞት ይታያቸው ነበር ፤ ዲያብሎስ ኅሱም ገጹን ጽሉም ራእዩን ገልጦ ሲታያቸው ሰውነታቸው ይቀዘቅዛል ነፍስ ደንግጣ ከሥጋዋ ትለይ ነበር
ለእመቤታችን ግን ሕይወት የሆነው ልጅዋ ራሱ ክርስቶስ ነው የተገለጠላት፤
• በብሉይ ኪዳን የሞቱ ሰዎች ወደ ሲኦል ነበር የሚወርዱት እመቤታችን ግን ሥጋዋ በገነት ነፍሷ በልጅዋ እጅ ነበር፤
• ከአዳም ልጆች ወገን የመጨረሻውን ትንሣኤ የተነሣ የለም፤እመቤታችን ግን እንደ ልጅዋ ተነሥታለች ዐርጋለች፤መዝ 131፤8፡፡
ሰለዚህ የእመቤታችን ሞት ይደንቃል፤ሁላችን ከሞታችን በፊት የሰራነው ብዙ ኃጢአት አለ፤ እመቤታችን ግን ንጽሕት ናት
ሞቷም በሲኦል ስላሉ ውስን ነፍሳት በልጅዋ ፈቃድ ቤዛ ሆኖ የተሰጠ፤የተከፈለ ነው፡፡
ሞት ለሟች ይገባል
የድንግል ሞቷ ግን ለሁሉ ይደንቃል!!!
የእመቤታችን አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን
ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን!
ልጅዋ ወዳጅዋ ፍቅሩን በሕይወታችን፣ ፍቅሯን በልባችን ይሣልብን ያሳድርብን!!!
አሜን!!!!
መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
@mezigebehayimanot
@mezigebehatimanot

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአሜሪካ የነበራቸውን ሐዋርያዊ አገልግሎት ጨርሰው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ እንዳይገቡ መከልከላቸው ተሰምቷል።
ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
ብፁዕነታቸው ከሳምንታት በፊት በቋሚ ሲኖዶስ እውቅና ወደ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ የአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ ዓመታዊ በዓል፣ የከተራና የጥምቀት በዓላትን ከመንፈስ ልጆቻቸው ጋር ያከበሩ ሲሆን ለአዳጊ ሕጻናትም ማዕረገ ዲቁና መስጠታቸው ይታወቃል።
ብፁዕነታቸው በአሁኑ ሰዓት ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያው ይገኛሉ ሲሉ መረጃ ሰጭዎቻችን አድርሰውናል ሲል ማኅበረ ቅዱሳን ቴቪ አስታውቋል።
@Nigatu5

ብፁዕነታቸው ወደ አሜሪካ እንደተመለሱ ተሰምቷል።
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደ ሀገር እንዳይገቡ በመከልከላቸው ወደ አሜሪካ ለመመለስ መገደዳቸውን አሳውቀዋል።
ብፁዕነታቸው ከደቂቃዎች በፊት ለማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ፤ " አሁን አሳፍረውኝ ተመለስኩ፤ ወደ አሜሪካ ወደመጣሁበት መለሱኝ ፤ ወደ ስራዬ እንዳልመለስ ከለከሉኝ። " ብለዋል።
ለቴሌቪዥን ጣቢያው ቃላቸውን በሰጡበት ወቅት አውሮፕላኑ ሊነሳ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ወደ አሜሪካ እንዲመለሱ የሚደረግበት ምክንያት ምንድነው ? ተብለው ተጠይቀው ፤ ብፅዕነታቸው ፤ " በቃ ግሪን ካርዱን ብቻ ነው የምንፈልገው እኛ ያንተን ፓስፖርት አንፈልግም ግሪንካርድ ብቻ ነው የምንፈልገው ብለው ወሰዱ በሩን ዘጉ !! " ሲሉ ተናግረዋል።
ይህን ያደረጉት የደህንነት ሰዎች ናቸው ብለዋል።
ብፅዕነታቸው ወደ አውሮፕላን እንዲገቡ ከመደረጋቸው በፊት ውጭ ላይ ሲጉላሉ እንደነበር ተናግረው አንድ የኢሚግሬሽን ሰው " የማውቀው ነገር የለም ግሪንካርዱ ትክክል አይደለም " እንዳላቸውና እሳቸውን ግሪንካርዱ ገና 3 ዓመት እንደሚቀረው እንደነገሩት አስረድተዋል።
ይህን ሲያስረዱ ከግለሰቡ መልስ እንዳልተሰጣቸውና " ሌሎች ሰዎችንም #ዲፖርት እያደረግን ነው " በማለት እንደነገራቸው ገልጸዋል።
ብፅዕነታቸው የአሜሪካ ፓስፖርት እንዳላቸው ገልጸው ፤ " እሱን ምንም ለማድረግ ስላልቻሉ ግሪንካርድ እንወስዳለን በማለት ወስደዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ከሳምንታት በፊት ለአገልግሎት ከሀገር ሲወጡ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ሌሎችም " ሊያስቀሩህ ይችላሉ " የሚል ነገር ሰምተው እንደነገሯቸው ነገር ግን በአሜሪካ የያዙትን አገልግሎት መተው ስላልፈለጉ ወደ አሜሪካ መሄዳቸውን ገልጸዋል።
ብፅዕነታቸው ወደ አሜሪካ በሄዱበት ወቅት " ኮበለሉ " የሚሉ መረጃዎች ተሰራጭተው እንደነበር ይታወሳል። በኃላም ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ ፤ በህጋዊ መንገድ በቤተክርስቲያን እውቅና ከሀገር እንደወጡ ፤ የሚደበቁም ሆነ የሚኮበልሉ የወንጅል ሰው እንዳልሆኑ አሳውቃ ነበር።

⛪️መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ እንወቅ⛪️:
ሴምና ያፌት
| ጃንደረባው ሚድያ | ጥር 2016 ዓ.ም.|
✍🏽 ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ
ምድር ከጥፋት ውኃ መድረቅ በኋላ በኖኅ መርከብ ውስጥ ከነበሩ እንስሳትና አራዊት በቀር ሌላ አንዳች ፍጥረት አልነበረባትም። በምድር ላይ የሚርመሰመሰውን ሥጋ ለባሽ ፍጥረት ሁሉ ለጥፋት የዘነበው ውኃ ሙልጭ አድርጎ ደምስሶታል። ኖኅ ከመርከብ ሲወጣ ምድርን በዝሙታቸው ያበላሿት የቃኤል ልጆች በከተሞቻቸው አልነበሩም። ቅዱስ መጽሐፍ “በምድር ላይ ስማቸው የታወቀ ኃያላን ሆኑ” ዘፍ 6፥4 ብሎ የሚጠራቸው ኔፊሊሞች አሁን የሉም። የደብር ቅዱስ ባህታውያንን በውበታቸው ያሳቱ የቃኤል ቆነጃጅትም እንደ ቀድሞው በከተሞች መካከል ሲመላለሱ አይታዩም።
እግዚአብሔር ከተቆጣ ጉልበት አያድንም፤ ውበትም ልብ አያራራም፤ ደም ግባትም አያኖርም፤ ሀብትና ዝናም መሸሸጊያ ሊሆን አይችልም። የእግዚአብሔር ትዕግሥት ምድርን ከዝሙቷ ካልመለሳት በቀር ከቁጣው የሚያስጥላት ምንም ነገር የለም።
ምድርን ሁሉ ባዳረሰው በዚያ ጥፋት መካከል ራሱንና ቤተሰቡን ማትረፍ የተፈቀደለት ኖኅ ብቻ ነበረ፤ በእግዚአብሔር ፊት ብቻውን ጻድቅ ሆኖ ተገኝቷልና። ከገነት ያስወጣችን ኃጢአት በዚህ ምድርም ከመኖር ከለከለችን። በገነት ሳለን እርግማንን አመጣችብን፤ በዚህ ምድርም ላይ የጥፋት ዝናምን አዘነመችብን። ወዮ! ከኃጢአት የተነሣ በሰው ላይ የደረሰው መከራ ብዛቱን ማን ቆጥሮ መጨረስ ይችላል?
እሳት ከሰማይ ቢዘንብብን፣ ንፍር ውኃ ቢያቃጥለን፣ ምድር ተከፍቶ ቢውጠን፣ ረሀብና ቸነፈር ቢያጠቃን፣ ድርቅ ምድራችንን እንዳታበቅል ቢያደርግብን፣ እርስ በእርሳችን መስማማት ቢያቅተን ይህ ሁሉ የሆነው በሌላ አይደለም፥ በኃጢአት ምክንያት ነው። ወደን በሠራነው ኃጢአት የማንወደው መቅሰፍት እየመታን እንኖራለን። ጣፍጦን የፈጸምነው ኃጢአት መራራ ሞትን እያስፈረደብን ወደ ሲዖል ያወርደናል። እኛ ኃጢአትን መሥራታችንን፣ ኃጢአትም እኛን ማስጠፋቷን ቀጥላለች።
ከአባታቸው ጻድቅነት የተነሣ ከሞት የተረፉት የኖኅ ልጆች ከመርከብ ከወጡ በኋላ በሌላ መንገድ ኃጢአት በራቸውን ስታንኳኳ ተመልክተናል። ለካ ያ ሁሉ ምድርን ለመቶ ሃምሳ ቀናት የሸፈናት ውኃ ኃጥአንን እንጅ ኃጢአትን ከምድር ላይ አላጠባትም ኖሯልና ኃጢአት አሁንም በሰዎች ልብ ውስጥ ሥር መስደድ ጀመረች። ሰይጣን አዲስ አዲስ የኃጢአት አሠራሮችን ማምጣት ልማዱ ነው። ከመርከብ የወጣው ትውልድ እንዳያመልጠው የቀደመውን ኃጢአት ይዞ አልቀረበም፤ አዲስ የኃጢአት አሠራር ይዞ ብቅ አለ እንጅ። እስካሁን የአባቱን ዕርቃን አይቶ በገዛ አባቱ የሚሳለቅ ትውልድ አልነበረም ዛሬ ግን ከሦስቱ የኖኅ ልጆች መካከል አንዱ የሆነው ካም የአባቱን ዕርቃን አይቶ ተሳለቀ፤ ብቻውንም አይቶ ሊቀር ስላልፈለገ ለወንድሞቹ ሁሉ የአባታቸውን ሀፍረት እንዲያዩ ቅስቀሳ አደረገ። “የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው” ዘፍ 9፥22 እንዲል።
ሰይጣን ዘመናዊ ነው፤ አሠራሩም ለትውልድ እንዲስማማ አድርጎ ማቅረብም ልዩ ችሎታው ነው። የአንድ ዘመን ትውልድ የተቀጣበትን ኃጢአት ለሌላ ትውልድ በማቅረብ ተከታይ ማጣት አይፈልግም። ስለዚህ ምን ያደርጋል መሰላችሁ፥ የፅንሰ ሀሳብ ልዩነት ባይኖረውም የንድፈ ሀሳብ ልዩነት አድርጎበት በሌላ መንገድ ያቀርበዋል። ያን ጊዜ ተከታዮችን ማግኘት ይችላል ማለት ነው። በዓለም ላይ ታላላቅ ጥፋቶችን ያስከተሉ ታላላቅ ኃጢአቶች ከአዳም ኃጢአት {አምላክነትን መሻት} ጀምሮ እስከ ሞተ ወልደ እግዚአብሔር ድረስ ሰባት ናቸው። እነዚህን ለአዲሱ ትውልድ በሌላ መንገድ ያቀርባቸዋል እንጅ ሌላ አዲስ ኃጢአት አያቀርብም።
ዮሐንስ በራእዩ የተመለከታቸው ሰባቱ የአውሬው ራሶች የተባሉትም እነዚሁ እንደሆኑ የሐዲስ ኪዳን መምህራን ያስተምራሉ ራዕ 13፥1 ከመርከብ በወጣው ትውልድ መካከል የገባችው ይህች የዛሬዋ በደል ኖኅ ወደ መርከቡ ከመግባቱ በፊት የነበረው ትውልድ የማያውቃት ሌላ በደል ናት − እሷም የአባትን ዕራቁትነት ማየት ናት። አዳም ዕራቁቱን በነበረ ጊዜ በገነት ዕፀዋት መካከል መሸሸጉ ዕራቁትነት አሳፋሪ ነገር በመሆኑ ነው። እግዚአብሔርም ዕርቃኑን ያሳይበት ዘንድ የገነትን ዕፀዋት በቅጠላቸው እንዳይሠውሩት አላደረጋቸውም። ዕርቃንን መግለጥ የማይገባ ስለሆነ ነው።
ሴምና ያፌት እንደ እግዚአብሔር ሆነዋል፤ የኖኅን ዕርቃን አላዩምና። ይህንን ነገር በሰሙ ጊዜ በማስተዋል ያደረጉትን ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገርላቸዋል። “ሴምና ያፌትም ሸማ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ የኋሊትም ሂደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም” ዘፍ 9፥23 ተባለላቸው።
አስተዋይ ትውልድ እርቃንን በማየት አይደሰትም። እርግማን ከምድራችን ላይ እንዲወገድ የሚያደርግ እንዲህ ያለ ትውልድ ያስፈልገናል! ወደ ኋላ ሂዶ የታሪክ ዕርቃንን የሚሸፍን። እንዲህ ያለ ዘመን እንዲመጣልን እንጸልያለን፤ የአባቱን ሀፍረት ላለማየት በትክሻው ላይ ልብስ የሚያኖር ትውልድ እንዲሰጠን። ሴምና ያፌት በዚህ ዘመን ሊኖሩን ያስፈልገናል።
የሆነ ዘመን ላይ ከጭንቅ ያወጡን፣ ክፉውን ዘመን ያሻገሩን ሰዎች ጥቂት ኅፀፅ ስናገኝባቸው በሰዎች ፊት መሳቂያና መሳለቂያ የምናደርጋቸው ከሆነ ሰውነታቸውን ረስተናል ማለት ነው። ያኔ የታላቁ ቀላይ ምንጮች ተነድለው የሰማይም መስኮቶች ተከፍተው ከላይና ከታች የጥፋት ዝናም በዘነመ ጊዜ በጥበባቸው የምንሳፈርበትን መርከብ የሠሩልንን ሰዎች መሆናቸውን መዘንጋት አይገባንም።
ወደ ኋላ ተመልሶ በአባቶቹ የሚሳለቅ ትውልድ መፍጠር ምን ያደርጋል። ምንም ይሁን ምን ከጥፋት ውኃ ያተረፈን አባቶቻችን የሠሩት ሥራ ነው። ያንን ሞት ያለፍነው አባቶቻችን በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ስለነበራቸው ነው። ወደ ኋላ ከተመለስንም የምንሻገርበት መርከብ፤ የምንጠጋበት ወደብ የሠሩልን መሆናቸውን ማሰብ ይገባናል እንጅ ዕርቃናቸውን እያነሣን ብናሳይ ከመረገም በቀር ምንም ጥቅም የለውም።
ከእኛ በፊት የነበሩ አባቶቻችን የሠሩትን ታሪክ ቀድሞ ያጠና ካለ ለሚሰሙት ሁሉ መናገር ያለበት ኖኅ ደክሞ መተኛቱን እንጅ ዕርቃኑን መሆኑን አይደለም። ይህ ዛሬ ዕርቃኑን ያየነው ኖኅ ነው ዛሬ በሕይወት እንድንኖር ያደረገን። በቤተ መንግሥት፣ በቤተ ክህነት፣ በማኅበራት፣ በግለ ሰቦች፣ በመኳንንት፣ በካህናት የደረሱ ጥፋቶች የተነገሩ የማይገቡ ቃላት ሊኖሩ ይችላሉ። ዛሬ ላለው ትውልድ በየቀኑ ብናዘክረው እግዚአብሔር በመርከብ ጭኖ ከሞት ቢያሻግረው ሌላ ሞት እንዲገጥመው ማድረግ ካልሆነ ሌላ ጥቅም የለውም። ይህንን ቀን እንድናይ መጽሐፍ ጽፈው፣ ጉባኤ ዘርግተው፣ አገር ለአገር ዞረው አስተምረው ክፉውን አመል በመልካም አመል እንድንለውጥ አድርገው የደከሙልን ብዙ አባቶች አሉ።
የፖለቲካ፣ የጎሣ፣ የሃይማኖት መሪ የነበሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ምናልባት የማይጠቅም ታሪክ ሠርተው እንኳን ብናገኛቸው ለሚመጣው ትውልድ የማይነበብ የሚል ከላዩ ላይ ጽፈንበት እንጅ እንዲሁ ማስተላለፍ አይገባም። ሴምን ያፌትን መሆን ይገባናል። “የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፤ እግዚአብሔር ያፌትን ያስፋ በሴምም ድንኳን ይደር ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን” ዘፍ 9፥26 ብሎ የሚመርቀን አባት የምናገኘው ሴምና ያፌትን በመሰለ ሥራ ብንገኝ ነው። የሌሎችን ኃጢአት በትዕግሥት የራሳችንን ኃጢአት በንስሐ ማለፍ ከቻልን ከጻድቁ ኖኅ አፍ የወጣው የሴምና የያፌት በረከት ዛሬም በኛ