Telegram Web Link
ላይ ነው። ከእኛ መካከል የሌላውን ነውር

የሚሠውር ሴምና ያፌትን የሚመስል ማነው?

ማስታወሻ :- ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የአራቱ ጉባኤያት መምህርና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ ሲሆን የመጻሕፍት ደራሲም ናቸው::
https://www.tg-me.com/EotcLibilery
የትዳር ዓላማ ከገባን

"የትዳር ዓላማ፥ ሊቁ እንደሚነግረን ጽድቅን ለመፈጸም ነው፡፡ ይህን ዓላማ አድርጎ ወደ ትዳር የሚገባ ክርስቲያን ልጅ ባይወልድ እንኳን አይፋታም፤ .... አንዳቸው ቢሰንፉ እንኳን ከዝሙት ተጠብቀውና ራሳቸውን ገዝተው እግዚአብሔርን በማመስገን ይኖራሉ እንጂ አይፋቱም፡፡ ጋብቻ የተሰጠው ለዚህ ነው፡፡ የጋብቻ ግቡ ይኼ ነው፡፡ የጋብቻ ጥቅሙ ይኼ ነው፡፡"

"በአሁኑ ሰዓት በባልና በሚስት መካከል የሚፈጠሩት ችግሮች አብዛኞቹ ይህን ካለመገንዘብ የሚመጡ ናቸው፡፡ ወጣቶች የትዳር ዓላማ ጽድቅ እንደ ኾነ ከገባቸው ግን በመካከላቸው የሚፈጠሩትን “አለመግባባቶች” በቀላሉ መፍታት ይችላሉ፡፡ መጽደቂያ ኾነው በተሰጡት ነገሮች እንዲሁ አይጨቃጨቁም፡፡ አንዱ ሲቈጣ፥ ሌላኛው የትዳር አጋር የትዳር ዓላማ ጽድቅን መፈጸም እንደ ኾነ ከገባው ይታገሣል፡፡ የአንዱ ጠባይ ክፉ ቢኾን ሌላኛው የትዳር አጋር የትዳር ዓላማ ምን እንደ ኾነ ከተረዳ ይህን የትዳር አጋሩን ክፉ ጠባይ ወደ መልካም ለመቀየር ይጥራል፡፡ ከሰውነታችን አንዱ ክፍል ለምሳሌ እጅ ቢታመም ከሌላው ሰውነታችን ይልቅ ልዩ እንክብካቤ እንደምናደርግለት ኹሉ ይህን የትዳር አጋርም የትዳር ዓላማ ጽድቅን መፈጸም እንደ ኾነ ከተረዳ የተረዳውንም በተግባር ለመኖር የሚጥር ከኾነ ለባለቤቱ ልዩ እንክብካቤ ያደርጋል እንጂ አይማረርም፡፡ ይህ ግን እንደ ተናገርን የትዳር ዓላማ ከገባው ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ዓላማ ትተን መመዘኛችን በዚህ ምድር በሚቀሩ ነገሮች ላይ መኾን የለበትም፡፡ የትዳር አጋርን የምንፈልግበት ምክንያት ጽድቅን ለመፈጸም መኾን አለበት፡፡"

(ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው ገጽ 40-41 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
እስኪ ንገረኝ! ምንስ ታስባለህ? በነፍሱ መከራ የሚቀበለው የትኛው ነው፡- የተሳደበ ሰው ወይስ የተሰደበ ሰው? የተሳደበ ሰው እንደ ኾነ ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም አስቀድሜ እንደ ነገርኩህ አንድን ሰው ኃጠአተኛ የሚያሰኙት ከውስጥ ከሰውዬው የሚመነጩ ክፋቶች እንጂ ከአፍአ የሚመጡ አይደሉምና ከድርጊቱ ራሱ የታወቀ ነው - “ስሜት” መባሉም ለዚህ ነውና፡፡ ዳግመኛም በተሳዳቢው ላይ በሚፈጥሩት ነገር የታወቀ ነው፡፡ ተሳዳቢው ሲቈጣ ዓይነ ልቡናው ይታወራልና፤ አእምሮው ይታወካልና፤ [የጤና መታወክ ሳይቀር] ሌሎች ስፍር ቊጥር ጉዳትም ይደርስበታልና፡፡ ስለዚህ መከራ እየተቀበለ ያለው ተሰዳቢው ሳይኾን ተሳዳቢው መኾኑን መረዳት ይቻለናል፡፡
ምናልባት “እርሱ ልጄን ሞኝ ብሎ ተሳድቦአል” ልትለኝ ትችላለህ፡፡ እኔም እልሃለሁ፡- መሳደብ ራስን መጉዳት እንደ ኾነ ነግሬሃለሁ፤ ስለዚህ ሰውዬው ደካማ ኾኖ ስለ ተሳደበ አንተም እርሱን መስለህ ደካማ ኾነህ የስድብ አጸፌታ አትስጥ፡፡ እስኪ ልጠይቅህ! አንተም መልስልኝ! ይህ ሰው ልጅህን በመሳደቡ መልካም ነገር አደረገን? መቼስ “አዎ መልካም አድርጓል” አትለኝም፡፡ እንግዲያውስ አንተም እርሱ የፈጸመው መልካም ያልኾነን ግብር አታድርግ፡፡ ልጅህ በተሰደበ ጊዜ ወይም በእንደዚህ ዓይነት ሌሎች ኹኔታዎች ውስጥ በልብህ ሊፈጠር የሚችለውን ስሜት እረዳለሁ፡፡ ኾኖም እርሱን [ተሳዳቢውን] ባለመምሰል በራስህ ላይ መከራን ከማምጣት ተከልከል እልሃለሁ፡፡
ምናልባት “እንደዚህ በማድረጌ እንዳሸነፈኝ ቈጥሮ ቢንቀኝስ? ይህ ሳይበቃውና ከልጄም አልፎ እኔንም ጭምር ቢሰድበኝስ?” ብለህ ትጠይቀኝ ይኾናል፡፡ እኔም፡- “እንዲህ ያደረገውን ሰው በተሳሳተ መንገድ እየኼደ እንደ ኾነ በትሕትና ገሥጸው፣ ራሱን ከመጉዳት በቀር እርሱ አንተን በፍጹም ሊጎዳህ እንደማይችል ምከረው” ብዬ እመክርሃለሁ፡፡ በየውሃት፥ በልብ ውስጥ ያለውን የቊጣ ስሜት መፈረካከስ ይቻላልና፡፡ ስለዚህ በየውሃት ወደ ተሳዳቢው ኺድና ገሥጸው፡፡
ሰዎች እኛን ሲጎዱን ወደ እነርሱ የምንኼደው ግን እኛ እንደ ተጎዳን ለመናገር እንዳልኾነ በደንብ አስተውል፡፡ የምንኼደው ተጎጂዎቹ እነርሱ ራሳቸው ስለ ኾኑና ስለ እነርሱ መዳን ስንል ነው፡፡ ስለዚህ አንተም ወደ ተሳደበው ሰው ስትኼድ ልጅህ በመሰደቡ ምክንያት ወይም አንተ ራስህ እንደ ተሰደብክ በመቁጠር አይኹን፡፡ ተሳዳቢው ሰው አንተን ንቆህ አጥቅቶህ ሊኾን ይችላል፡፡ ነገር ግን ልጄ ተሰደበ ወይም እኔ ተናቅሁ ተጠቃሁ ብለህ አትኺድ፡፡ መኼድ ያለብህ ተሳዳቢው ሰው ራሱን እየጎዳ እንደ ኾነ አስበህና ስለ እርሱ መዳን ብለህ ነው፡፡ ስለዚህ እንደ ሰይፍ የሰላውን የቊጣ ሰይፍህን መልሰው፤ ወደ ሰገባውም ክተተው፡፡

(ነገረ መከራ - ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው #ገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ እንደተረጎመው)
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
"ከንቱ ውዳሴ በመንገድ ሁሉ የሚከተልህ የተሸሸገና ጭንብል ያጠለቀ ሌባ ነው። አሳዳጅ በመሆኑ በጣም ደኅንነት በሚሰማህ አሳቻ ሰዓት ሳታውቀው ይዘርፈሀል፤ ይገድልህማል። "

ቅዱስ ጎርጎርዮስ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#ምስባክ
ዘየካቲት ፪ ወ ፫

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ 
                                                  
Size:- 36.8MB
Length:-1:45:37
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#የክርስቲያን_መከራ

ለአንድ ክርስቲያን መከራ ለጥቅሙ የሚሰጠው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን መከራን መቀበል ማለት ከሰማያዊ ክብር መሳተፍ ነው፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ ፡- ስንፍናንና ክፉ ፈቃድን የሚያርቅ፣ ዓለማዊ ግብር መውደድን፣ ውዳሴ ከንቱ መውደድን የሚያርቅ ነውና የክርስቲያን መከራ ክብርን ያስገኛል፡፡ ነፍስን የሚረዳ፣ በክብር ላይ ክብርን የሚያስገኝ ነውና የክርስቲያን መከራ የሚያሳዝን መከራ አይደለም ብዬ እነግርሃለሁ፡፡

የቅዱሳኑ ክብራቸው እንዲህ ደምቆ ልናየው የቻልነው ከምን የተነሣ እንደ ኾነ እንመልከተው፡፡ ስላገኛቸው መከራ አይደለምን? ፈቃድህ ከኾነ ገና ከመነሻው አንሥተን እንቍጠራቸው፡፡ አዎ! ከአቤልና ከኖኅ ጀምረን እስኪ እንቍጠራቸው፡፡ እነዚህ ቅዱሳን በዚያ ለመቍጠር እንኳን በሚታክቱ ክፉዎች ሰዎች መካከል እየኖሩ ያለ መከራ ክብርን ማግኘት አልተቻላቸውም፤ እንዲህ እንደ ተባለ፡- “ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበረ፤ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኘው” (ዘፍ.6፥9)፡፡ ተመልከት! ለእኛ አብነት የሚኾኑን እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች አሉን፡፡ ብዙ አበውን፣ ብዙ ሕፃናትን፣ ብዙ መምህራንን አብነት አድርገን መከራ እንቀበላለን፡፡ በሰብአ ትካት መካከል ኾኖ መከራ ስለ ተቀበለው ስለ ኖኅ ምን እንላለን? በዙሪያው ስለ ነበረው እንግዳና አስደናቂ ዝናብስ ምን እንናገራለን? ወይስ አብርሃም ከአገር አገር ሲሰደድ መኖሩን፣ ሚስቱን እንደ ቀሙት፣ ጦርነትና ረሃብ እንዳገኘው እናገር ዘንድ ይገባኛልን? ወይስ እጅግ አስጨናቂ ነገሮች ስላገኙት፣ ከቦታ ቦታ ስላሳደዱት፣ ድካሙ ከንቱ ይኾንበት ስለ ነበረው፣ በድካሙ ላይ ሌሎች ሰዎች ይጠቀሙበት ስለ ነበረው ስለ ይስሐቅ ልናገርን? ወይስ ስለ ያዕቆብ ልናገርን? ያዕቆብ ያገኘውን መከራ እዘረዝር ዘንድ አይገባኝም፤ እርሱ ራሱ ለፈርዖን የተናገረውን ምስክር አድርጌ ላቅርብ እንጂ፤ እንዲህ ያለውን፡- “የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ኾኑብኝ፡፡ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም” (ዘፍ.47፥9)፡፡ ወይስ ስለ ዮሴፍ ልናገር ይገባኛልን? ወይስ ስለ ሙሴ፣ ወይስ ስለ ኢያሱ፣ ወይስ ስለ ዳዊት፣ ወይስ ስለ ኤልያስ፣ ወይስ ስለ ሳሙኤል፣ ወይስ ስለ ነቢያት ኹሉ ልናገር ይገባኛልን? እነዚህ ኹሉ በመከራ እንደ ከበሩ አታውቅምን? ሰው ሆይ! ከዕረፍትና ከቅምጥል ሕይወት ክብርን ልታገኘ ትሻለህን? እኔ እነግርሃለሁ፤ በፍጹም አታገኘውም፡፡

ወይስ ስለ ሐዋሪያት ልናገርን? እነዚህስ ከኹሉም በላይ መከራ ተቀበሉ፡፡ ጌታችን ክርስቶስም እንዲህ ብሏልና፡- “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” (ዮሐ.16፥33)፤ “እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝኑማላችሁ፡፡ ዓለም ግን ደስ ይሏል” (ዮሐ.16፥20)፤ “ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ መንገዷም ቀጭን ናትና የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው” (ማቴ.7፥14)፡፡ ታዲያ እስኪ ንገረኝ! ጌታችን መንገዷ ጠባብ ናት እያለ አንተ ሰፊውን መንገድ ትፈልጋለህን? ይህስ እንደ ምን ሊኾን ይችላል? በሌላ መንገድ የምትኼድ ከኾነም ወደ ሕይወት አትደርስም፤ እንደ ምርጫህ ምረረ ገሃነም ያገኝሃል እንጂ፡፡

የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው በገብረ እግዚአብሔር ኪደ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሰዋል፤ ያበሰብሰዋልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ የተተረጎመ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#ትንሿ_ቤተክርስቲያን_በኦርቶዶክሳዊ_ቤተሰብ

[ባለትዳሮች] በቤታቸው ውስጥ ማድረግ ያለባቸው ቤተ ክርስቲያን መጥተው ያዩትን ነው፡፡ ለምሳሌ፦

👉 ቤተክርስቲያን ውስጥ የጠዋትና የሰርክ ጸሎት እንዳለ ኹሉ እነዚህ ባለ ትዳሮችም የጠዋትና የሰርክ ጸሎት በቤታቸው ውስጥ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ያለው የኅብረትና የአንድነት ጸሎት እንደ ኾነ ኹሉ፥ ባልና ሚስት ልጆችም ሳይለያዩ አብረው መጸለይ አለባቸው፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ውስጥ ከቅዳሴ በኋላ ትምህርተ ወንጌል እንዳለ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም እራት ከበሉ በኋላ ቃለ እግዚአብሔር ሊማማሩ ይገባቸዋል፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ውስጥ ራሳቸውን ገዝተው የሚኖሩ ትጉሃን መነኰሳት እንዳሉ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም ይህን ትግሃትና ምስጋና ወደ ቤታቸው ይዘዉት ሊኼዱ ይገባቸዋል፡፡

👉 ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማታ ላይ ኅብስቱን አበርክቶ ሕዝቡን ከመገባቸው በኋላ ወዲያው ወደ መኝታ እንዲኼዱ እንዳላደረገ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም ወደ መኝታቸው ከመኼዳቸው በፊት የቀን ውሎአቸውን መገምገም አለባቸው፡፡

👉 ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሊት ሌሊት ሲጸልይ ያድር እንደ ነበረ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም ሌሊት ላይ ነቅተው መጸለይ ይገባቸዋል፡፡ ሕፃናት ካሉም አብረዋቸው እንዲነሡ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ጾም እንደሚታወጅ ኹሉ፥ ባልና ሚስትም በቤተ ክርስቲያን ከሚታወጀው ጾም በተጨማሪ ከንስሐ አባቶቻቸው ጋር ተመካክረው በፈቃዳቸው ሊጾሙ ይገባቸዋል፡፡

👉 በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳለው፥ ባልና ሚስትም የቤታቸውን ግድግዳ፣ መስኮትና በር በመስቀል ሊያስጌጡት ይገባቸዋል፡፡ ማማተብ በማይችሉ ልጆቻቸው ግንባርም አድገው ራሳቸው ማማተብ እስኪችሉ ድረስ እነርሱ ያማትቡላቸው፡፡ ቅዱሳት ሥዕላትም በቤታቸው ውስጥ ሊኖሩ ይገባል፡፡

ቤታቸው ትንሿ ቤተ ክርስቲያን የምትኾነው በዚህ መንገድ ነው፡፡

#ኦርቶዶክሳዊ_ቤተሰብ
#በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ መጽሐፍ፥ ገጽ 60 - 61
ትርጉም፦ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
እጅግ የተወደደና የተከበረው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ

“ወዳጄ ሆይ ወንድምህ ከአንተ ይልቅ አስተዋይና አዋቂ ብርቱም ቢሆን በዚህ ቅር አይበልህ ከዚህ ይልቅ እግዚአብሔርን አመስግን

ከወንድምህ አስተዋይነትና ብርታት ትጠቀማለህና በዚህ ሳታቆም ራስህን ስጦታየ ምንድነው?ወንድሜን እህቴን በምን ልጥቀም ?ብለህ ጠይቅ

ይህን ጥያቄ በትክክል ስትመልስ እንደመለስከው ምላሽም ስትተገብር በአንድ መልኩ በሚበልጥህ ሰው ቅር መሰኘትህን በሌላ መልኩ ደግሞ የምትበልጠውን ወንድምህን መናቅህን ታቆማለህ”
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#ማግባት_ለሚሹ
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው፤ እንዲህ ያለውን፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" (1ኛ ቆሮ.7፥2)። "ከድህነት ይወጣ (ትወጣ) ዘንድ" ነው የሚለውን? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡

ስለዚህ #ልጆቼ! እማልዳችኋለሁ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡ የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡

#አባቶች_ሆይ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት፦ ሀብትን አላየም፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡

#እናቶች_ሆይ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡

እናንተ ማግባትን የምትሹ #ወጣቶች_ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡

#እናንተ_ልጃገረዶች_ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡

የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
ልጄ! ሐሰተኛ አትኹን፤ ሕሰት ከስርቆት ያደርሳልና፤ ወርቅ ውዳሴ ከንቱ የምትወድ አትኹን ይህ ሁሉ ከስርቆት ያደርሳልና አለ ናትናኤል።

ልጄ! አጒረምራሚ አትኹን፤ ማጒረምረም ሰውን ወደ ስድብ ያደርሰዋልና፤ ክፉ ነገር የምታስብ ተጋፊ አትኹን፤ ክሕደት በዚህ ይመጣልና፤ ኃዳጌ በቀል (ይቅር ባይ) ኹን፤ ቂም በቀል የሌላቸው ሰዎች መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉና፤ ይቅር ባይ ርኅሩኅ ኃጢአት በሌለበት በንጹሕ ልብ ሁሉን የምትወድ ኹን፤ ትሑት ቸር ኹን፤ ከሰማኸው ቃል የተነሣ በመፍራት ከክፉ ሥራ ተጠብቀህ ኑር፤ አትታበይ ሰውነትህን ከትዕቢተኞች ጋር አንድ አታድርግ፤ ከትሑታን ከደጋግ ሰዎች ጋር ነው እንጂ፣ ያገኘህን መከራ ሁሉ አመስግነህ ተቀበል፤ ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ምንም ምን የሚደረግ እንደሌለ ዕወቅ አለ፤ ይሁዳ ታዴዎስ።

ልጄ! ቃለ እግዚአብሔር የሚነግርህን የሕይወት ምክንያት የኾነህን ለልጅነት ያበቃህን ሰው እንደ ዐይን ብሌን ውደደው በመዐልትም በሌሊትም አስበው እግዚአብሔር እንደ አከበረው አክብረው፤ እግዚአብሔር ስሙን ከሚጠሩበት ቦታ ከዚያ ይኖራልና፤ በትምህርታቸው ትጽናና ዘንድ እየሔድክ ሌሎች ቅዱሳንን ጠይቅ፤ ከቅዱሳን ጋር የሚውል ቅዱስ ይኾናልና።

በሚቻል መጠን አክብረው፤ ከደከምክበት ከሥራህ ፍሬ ስጠው፤ እግዚአብሔር በእርሱ ምክንያት መንፈሳዊ ምግብን የዘለዓለም ሕይወትንም እንድታገኝ አድርጎኸልና፤ የሚያልፈውን የዚህን ዓለም ምግብ ልትሰጠው ይገባሃል፤ ለሠራተኛ ዋጋው ይገባዋልና፤ በዐውድማ የበሬውን አፉን አትሰረው፤ ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማነው? አለ ቶማስ።

የተጣሉትን በፍቅር አንድ አድርግ እንጂ ሰውን የሚለያይ ሥራ አትሥራ፤ በእውነት ፍረድ፤ ለባለጸጋ አድልተህ በድኻው አትፍረድ፤ ብዕል ለእግዚአብሔር ቁም ነገሩ አይደለምና፤ ትዕቢተኛውን መናፍቁን አታክብረው፤ መጽሐፍም አትጥቀስለት፤ እንደ አነጋገሩ መልስለት እንጂ፤ ስትጸልይ አትጠራጠር፤ የምትለምነውን አስተውል እግዚአብሔር ይፈጽምልኻል።

በምትመጸውትበት ጊዜ ክፉ ነገርን አታስብ፤ ከሰጠህ ዋጋህን ታገኛለህና፤ የሰጠህ ምንም ምን ገንዘብ በእጅህ ቢኖርህ ከኃጢአትህ መዳንን ሻ ፈልግ፤ ያገኘኸውን በምትሰጥበት ጊዜ ወላዋይ ኣትኹን፤ ዋጋህን የሚሰጥህም ማን እንደሆነ ዕወቅ፤ የለመነኸንም አታሳፍረው፤ ማናቸውንም ሁሉ ከነዳያን ጋር ተካፈል እንጂ ገንዘቤ የግሌ ነው አትበል፤ በኀላፊው ገንዘብ እርስ በርሳችሁ አንድ ከኾናችሁ በማያልፈው እንደምን አንድ አትኾኑም።

ወንድሞቼ! እማልዳችኋለሁ፤ ዕድሜ ሳላችሁ ከዚህም ጋር በጎ ሥራ መሥራት ሲቻላችሁ የአላችሁን መስጠት ቸል አትበሉ፤ እግዚአብሔር የሚመጣበት ቀን ቅርብ ነውና፤ የሚታየው የማይታየው ሁሉ ያልፋል እግዚአብሔር ይመጣል፤ የሚሰጠው ዋጋም ከእሱ ጋር ነው፤ ለራሳችሁ ፈጻምያነ ሕግ ኹኑ፤ እግዚአብሔር እንደ አስተማራችሁ ሌሎችን አስተምሩ፤ የተማራችሁትን ጠብቁ፤ በተማራችሁት ላይ አትጨምሩ፤ ክተማራችሁትም አታጉድሉ አለ በርተሎሜዎስ፤ ወንድሞቼ! የቀሩትን ትእዛዛት መጻሕፍት ያስተምሩዋችኋል አለ ጴጥሮስ።

(#ሃይማኖተ_አበው_ዘስምዓት 125፥10-16)
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
2024/11/15 12:53:54
Back to Top
HTML Embed Code: